የህወሐት በጥልቀት መታደስ በመቀሌ ዩንቨርሲቲ አስተማሪዎችና የእስታፍ ሰራቶኞች ፍጹም ተቀባይነት ከማጣቱም በላይ ተሰብሳቢዎቹና ሰብሳቢዎቹ ይቅርና በሀሳብ ሊግባቡ በቋንቋም ሳይ ግባቡ ከአንድ ሳምንት በላይ የጭቅጭቅ ስብሰባ ሳይግባቡ ተበትነዋል ። ስብሰባው የተካየደው በዋናው የዩንቨርሲቲው ግቢ እንዳ እየሱስ እና በአዲ ሀቂ የቢዝነስና የኢኮኖሚክስ ግቢ በሁለት ቡዱን ተከፋፍለው ነው የተካየደው ።
1 .በእንዳየሱስ ግቢ ስብሰባው የመሩት .፡
1, 1 አቶ ንጉሰ ገበረ የህወሐት ማ / ኮሚቴ ነበር
1,2 ጥለሁን ወደዝዬ የህወሐት ማ/ኮሚቴ ነበር
1.3 ደጉተር ተወልደ ገብረእግዚአቢሄር የጠ /ምኒስቴር አመካሪ
1.4 ደጉተር ዓብደር ቃድር የዩንቨርሲቲው ም /ፕረዝዳንትና አከዳሚክ ሀላፊ ናቸው ።
2 በአዲሀቂ ግቢ ስብሰባው የመሩት ፡
2 .1ደጉተር አዲስ አለም ባሌማ የሀወሐት ስራ አስፈጻሚና የትግራይ ክልል ም / ፕረዝዳንት ፡
2. 2 ደጉተር ክንደያ ገብሪሂወት የመቀሌ ዩንቨርሲቲ አምስቱ ግቢዎች ፕረዝዳንት ፡ ናቸው ።
በሁለቱም ቡዱኖች የተደረጉ ስብሰባዎች ለሰብሳቢዎች የቀረቡ ጠያቄዎች ዋናዎቹ ፡
1 ለዚህ ሁሉ ህብረተሰብ ለመሰብሰብ ሰትመጡ ለምን አጀንዳ ልተዋያዩ እንደመጣችሁ ታውቃለችሁን ?።
2 ለምን የስብሰባ በቂ ዝግጅት አልተደረገም ? ይህ ሁሉ ህብረተሰብ ጊዜው በከንቱ መባከኑ ለምን ?
3 የኢትዮጱያ ህዝብ ጠባብነትና ትምክህተኝነት ድሮም ዛሬም አልነበረውም ፡የለውምን ። ዋና ጠባብነትና ትምክህተኝነት በህወሀትና በኢህአደግ አማራሮች ነው ያለው ለምን የናንተ ብልሽት ወደ ህዝብ ትለጥፋላችሁ ?
4 ለመሆኑ በጥልቀት መታደስ ማለት ቡልሹውነታችሁ ለመጠራረግ ማለት ነው ፡ እናንተ በሁሉም ነገር የተበላሻችሁ እናንተው ናችሁ ፡በመሆኑ እንዴት ብላችሁ ነጻ ሆናችሁ ለዚህ ሁሉ ሊሂቅ እናሳምናለን ብለችሁ ታምናላችሁ በማለት ጥያቄ አንስተዋል ።
ሌሎችም የስብሰባ መሪዎች ሊመሉሳቸው አቅማቸው የማይፈቅድሉዋቸው ተነስተዋል ።
ሰብሳቢዎች እንደነ ደጉተር አዲስ አለም ባሌማ ጥየቄ አንመልስም ዝም ብላችሁ እኛን ብቻ አድሙጡን በማላታቸው አብዛኛው ተሰብሳቢው ስብሰባው እየረገጠ ወጥቷል። በተለይ ደጉተር አዲስ አለም ባሌማ በተሰብሳቢዎች ከባድ ጥያቄ የተነሳ በመናደዳቸውና ተስፋ በመቁረጣቸው በመድረኩ ታመው በመውደቃቸው ስብሰባው በሌሎች ለመምራት ተሞክሯል ። ሆኖም ግን ተሰብሳቢዎች ተቃውሞ በማሰማት ስብሰባው ረግጠው ወጥተዋል ።
በትግራይ በጥልቀት ለመታደስ በአዲ ግራት ፡በአክሱም ዩንቨርሲቲዎች ፡ እንዲሁም በሽሬ ካንፓስ የተደረገ የሙሁራን ህብረተሰብ ስብሰባ የህወሐት ኢህአደግ አመራር በሚፈልገው መንገድ ግቡን ፡ አልመታም ። ምክንያቱም ፓርቲው ይዞት የመጣ የመወያያ ወይ በጥልቀት ሙሁሩ እናድስበታለን ብለው ይዘውት የቀረቡት አጀንዳ ፡ እንዲሁም የሰብሳቢዎች የአቅም ማነስ ፡ ከዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ። በመሰረቱ በጥልቀት መታደስ የሚሉት ማጭበርበርና የገዥ ፓርቲ እድሜ ማራዘምያ በመሆኑ ስብሰባው ግቡን አልመታም ።
ሌላ የዩንቨርሲቲው አስተማሪዎች የሚጠብቁት የነበረ እንደሙያቶኞችና ተመራማሪዎች ይጠቡቁት የነበረ ፡ስለ የትምህርት ጥራት ፡ የትምርት አመራር በሚመለከት ፡ ስለ መተካካት ተግባራውነት ፡ ስለዘረኝነት ስለ የህወሐት ኢህአደግ ብለሹውነት በሚመለከት የጠራ መልስ ለማግኜትና ሀገሪቱ በቡቁ ሊሂቃንና ተመራማሪዎች ሊትመራ እንዴትና እነማን ይሙራት የሚለው መልስ እንዲነገር ይፈልጉ እንደነበር ሲናገሩ ይሰማሉ ።
በህወሀት መንደር ግን ይቅርና ተባላሽተናል ፡ አቅማችን ተሟጥጦ አልቀዋል ፡በሀሳብም በአካልም አርጅተናል ሊሉስ ካሁን በኃላ 40 አመት ራሳቸው ልጆቻቸው እንደሚመሩን ነው እያንጸባረቁ ያሉ ።
የዚሁ ተጨባጭ ማስረጃ ሊሆን የሚችለው ህወመት ፡በአዴን ፡ ኦሆደድ ፡ ደሄደን ወዘተ በጥልቀት እንታደስ ብለው ክረምቱ ሙሉ ስብሰባ ተቀምጠው ከርመው ፡ከጭንቅላታቸው እስከ ጥፍር እግራቸው ሸትተውና በስብሰው ፡አገር ሙሉ አባላሽተው እያሉ በለፉት 15 አመት የተሀድሶ ጉዟችን ድልን አስመዝገበናል ብለው በአነድ ቃል አውጀው ነው ወጥተው ያሉ ።በመሆኑም የህወሐት ኢህአደግ በጥልቀት መታደስ ከወዲሁ ባዶና መታለያ ተሀድሶ መሆኑ ተረጋግጧል ።
በዚሁ ስብሰባ የተሳተፉ ሙሁራን ፡ ቢሄር ፡ቋንቋ ፡ ሀይማኖት ፡ ቀለም ፡ ዘር ፡ሳይለያያቸው በአንድ ድምጽ የተቃውሞ ድምጽ አሰምተው ነው የወጡ ።
በመጨረሻ የህወሀት ኢህአደግ መሪዎች በአሁኑ ጊዜ እንደ ለ42 አመት አያታለላችሁን የመጣችሁ ጊዜና የሰው አቅም አይደለም ይዛችሁ ያላችሁት አሁን ያለው በአስር ሚሊዮን የሚቆጠር ሙሁርና አልፎም በሁሉም አይነት ሙያ ተመራማሪ የሆነ ሀይል ቁጥር ስፍር የለውም ። በመሆኑም ዝም ብሎ ቢመለከታችሁ የፈራ እንዳይመስላችሁ ፡ ይልቁንስ ሀገሪቱ በሰላማዊ መንገድ ለዚሁ ቡቁ ሊሂቅ ማስረከቡ ጊዜ የማይሰጠው አጀንዳ ነው ። ይህ ካደረጋችሁ ለእናንተም ለልጆቻችሁም ይበጃል ።
በዚሁ በጥልቀት መታደስ በሚመለከት በተክክል በነጻነት ይሁን ተገደው በየመድረኩ የሚናገሩት ያሉና መላው የህወሐት ኢህአደግ መሪዎች የሚናገሩት ያሉት በፍጹም አይገናኝም ። ጠ / ምኒስቴር የሚናገሩት ያሉ ከምሬታቸው በእምነታቸው ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ልክ እንደ የእንግሊዝ ጠቅላይ ምኒስቴር ከስልጣናቸው መውረድ አለባቸው ከነዚህ ሰው በላዎች እንዴት ይኖራሉ ? ወይም ለ90 ሚሊዮን ህዝብ እያታለሉን ናቸው ።
ከአስገደ ገብረስላሴ ፡
15 /1 2009 ዓ ም
↧
በመቀሌ ዩንቨርሲቲ በጥልቀት መታደስ – ሀወሐት በሚፈልገው ግቡን አልመታም!! [ ከአስገደ ገብረስላሴ]
↧