የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር በተገኙበት በጀርመን በርሊን ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ሕዝብ አዳራሹን ሞልቶ እየተመለሰና ከውጭ ሆኖ እየተከታተለ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከበርሊን ዘገቡ:: ባልተለመደ መልኩ የሕወሓት ኢምባሲ ሰራተኞችና ለትምህርት ወደዚያው የተላኩ የባለስልጣናት ዘመዶች “አርበኞች ግንቦት 7 የ እናት ጡት ነካሽ ነው” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን ይዘው ከአዳራሹ ፊት ለፊት ተቃውሞ እያሰሙ ነው::
አርበኞች ግንቦት 7 የጠራው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ እየተካሄዱ ነው ያሉት እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከውጭ የሕወሓት ሰዎች የትግራይ ክልልን ባንዲራ ይዘው በመቃወም ላይ ናቸው ብለዋል:: ‘የኢትዮጵያ ሕዳሴ በሕዝቦቿ እውን ይሆናል’; “አዲሲቷ ኢትዮጱያልማትን እንጂ ጦርነትን እና ሽብርን አትሻም” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን የያዙት እንዚሁ 15 የማይሞሉት ሰልፈኞች አርበኞች ግንቢት 7ን ለመደገፍ በሄደው ሕዝብ ድምፃቸው እንደተዋጠ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል::
የበሊኑን ስብሰባ እንዳለቀ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን::
(ዘ-ሐበሻ)