ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ዐይን-ዐውጣ ስርቆት አይተናል- ፎቆች ሲጠፉ አይተናል፣ ቢልዮኖች ደብዛቸው ሲጠፋ አይተናል፣ በ1 ቢልዮን ብር ያልቃሉ የተባሉ ፕሮጀክቶች በ6ና 10 ቢልዮን ብር ሲያልቁ አይተናል፣ ብዙ ብዙ አይተናልና ጆሯችን ከእንዲህ ዐይነቶቹ ዜናዎች ጋር በብዙ ተላምዷል፤ ቢሆንም ግን ክፋትን፣ ውሸትን፣ ስርቆትን ቅቡል ማድረግ የለብንምና አሁንም እንናገራለን፣ እንፅፋለን፤
ከታች የምታዩት ከአፈር የተሰራ ትንሽ ኩሬ በአፅቢ ወንበርታ በሕዝብ ጉልበት በትንሽ ቀናቶች ውስጥ የተሰራ የውሃ ማቆርያ ኩሬ ነው፡፡
ትላንት ትግራይ ቲቪ ከምስሉ የምታዩትን ኩሬና አንዲት ትንሽ ማጣርያ ማእከል ለመገንባት “88 ሚልዮን ብር አወጣሁ” ብሎ እጅግ ከፍ ባለ ድምፅ ዜና ሰራ፤
ኩንትራክተሩ- ብዙ አልተወራለትም እንጂ በሐገራችን ውስጥ ከስኳር ኮርፖሬሽንም፣ ከቴሌም፣ ከኤልፓም በላይ የጨካኝ ቀማኞች ዋሻ የሆነው የትግራይ የውሐ ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡
በዓቲ ዕሉላት ጎሓላሉ ዝኾነ ኢንተርፕራይዝ ማይ ትግራይ “88 ሚልዮን ብር ወፃኢ ገይሩ” ብወፈራ ጉልበት ህዝቢ ኣፅቢ ወንበርታ ዝሰርሖ ፕሮጀክት ማይ ንዚ ይመስል- ፍልፍል ሓበሬታ ቶግ ቲቪ እዩ:
ጥሉላት ሓበሬታታት ድማ እቲ ፕሮጀክት ካብ 5 ወይ 6 ሚልዮን ንላዕሊ ዝውድእ ኣይኮነን ይብሉ፤
እንታይሞ ክንብል፤ ሓደ መዓልቲ ግን ክንፀባፀብ ኢና፤ ግዘ ንኹሉ መልሲ ኣለዋ!