Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

አንድ ቀልድ፤ ካንዲት ስንኝ!

$
0
0

አንድ ቀልድ፤ ካንዲት ስንኝ!

አንድ ሰውዬ አሉ ወደ ቤቱ ሲገባ አመሻሽ ላይ ዘራፊዎች የገዛ በሩ ላይ ጠብቀው ሙልጭ አድርገው ይዘርፉታል። ከዛ ወደ ቤቱ ሲገባ ለሚስቱ ስለ ሁኔታው ይነግራታል። ሚስቱም ከሌቦቹ ይልቅ በባሏ ተናዳ፤
‘’ሽጉጥ ይዘህ ነው የምትዞረው ለስሙ ቢያንስ ቢያንስ ወደ ሰማይ ተኩሰህ አታስደነግጣቸውም እንዴ…?’’ ብላ ትጠይቀዋለች፤

ባልየውም፤ የኔ ቆንጆ አትቆጪ እንጂ… ሽጉጡንማ እንዳይዘርፉኝ ብዬ መጀመሪያ በአጥር ላይ ወደ ግቢ ወርውሬዋለሁኮ! ብሏት እርፍ…

እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው!

ሽጉጥ በየቦታው ጠባቂውም ሞልቶ፤
የሚጠፋው በዛ የሚገኘው ጠፍቶ!

በሰላም እደሩልኝ…


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles