ዜና በጨዋታ፤ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ቤራዊ ፈተና ተራዘመ!
ዛሬ ራዲዮ ፋና በማለዳ ዜናው ሰበር ዜና ብሎ እንደነገረን የአስራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና ተራዝሟል። እንደ ራዲዮ ፋና ከሆነ ፈተናው የተራዘመበት ምክንያት የእንግሊዘኛ ፈተና ኮድ አስራ ሁለት መሰረቁ በመረጋገጡ ነው!
አሁን ጨዋታዋ ትምጣ…
እርግጥ ነው ራዲዮ ፋና እና ትምህርት ሚኒስቴር እፍረት ይዟቸው እንጂ የተሰረቀው ፈተና እንግሊዘኛ ብቻ ሳይሆን ሁሉም በሚባል መልኩ ነው።
ትላንት ፈተናው መሰረቁን ገና ከመስማታችን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የተሰረቀ ፈተና የለም ብለውን ነበር። ሰውዬው ይሄንን መግለጫ የተቀረጹት ከፈተናው መሰረቅ ዜና ቀድመው በመሆኑ ድሮውንም መዝረክረካቸውን እንዳወቁት ማሳያ ነው።
ከሁሉ በላይ ግን የዚህ ፈተና መሰረዝ ከአምስት ወራት በላይ ለፍትህ ሲጮሁ ለነበሩ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ትልቅ ድል እና እፎይታ ነው። ቀድሞውንም ፈተናው እንዲራዘም አጥብቀው ሲወተውቱ ሰሚ ያጡት እነዚህ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲህ እጁን ተጠምዝዞ ፈተናውንም ለመሰረዝ በመቻሉ ደስታቸውን እየገለጹ ነው!
እኔ ራሴ ቀላል ደስ ብሎኛል!?
ዜናው በዚህ አበቃ፤
የሚቀጥለው ዜና የቤተ መንግስቱ ቁልፍ ተሰርቆ አቶ ሃይለማሪያም ውጪ አደሩ… የሚል እንዳይሆን ፈራሁኝ በቃ!