(ሳተናው) በአራት የመንግስት ኢንተርፕራይዞች ሽያጭና ግዢ ሁለት ክሶች የቀረበበት ሜድሮክ ከእህት ካምፓኒዎቹ አንዱ ሆሪዞን ፕላንቴሽን የግል ካምፓኒ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲዘጋና የተወዘፈበትን የግማሽ ቢልዩን ብር ዕዳ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ኢንተርፕራይዝ እንዲከፍል ተወስኖበታል፡፡
ጎጀብ የእርሻ ልማት፣ሆሪዞን አዲስ ጎማ፣ሊሙ የቡና እርሻና በበቃ ቡና የተባሉት ድርጅቶች ለሜድሮክ በመሸጣቸው የቅድመ ክፍያ ተፈጽሞና ሙሉ ክፍያቸው የሚፈጸምበት ጊዜ በውል ስምምነቱ ተጠቅሶ ንብረቶቹ እንዲዘዋወሩ ተደርገው ነበር፡፡
ሆሪዞን ፕላንቴሽን በውሉ ሰፍሮ የነበረውን የክፍያ ጊዜ መከተል ያልቻለው ባስተናገደው የፋይናንስ ቀውስ ምክንያት መሆኑን አስታውቋል፡፡ሆሪዞን በበኩሉ የስድስት ወራት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠውና በሁሉም ጉዳዩች የተፈጠረውን ስህተት ለማስረዳት እንዲችል ጠይቆ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛው ችሎት ለወራት ጉዳዩን ሲመለከት መቆየቱን በማስታወስ ሁለቱ ካምፓኒዎች ያቀረቡትን አቤቱታ ሳይቀበል ቀርቷል፡፡በአጠቃላይ የቢልየነሩ ሼህ አላሙዲን ንብረት የሆነው ሜድሮክ እንዲከፍል የሚጠበቀው እዳ 433.571.241 ብር ስለመሆኑ ከቀረበበት ክስና ከተሰጠው ውሳኔ መረዳት ተችሏል፡፡ፍርድ ቤቱ የተላለፈው ውሳኔ በተቀመጠለት የግዜ ገደብ ሳይፈጸም ከቀረም ጥቅሙ እየተሰላ የብሩ መጠን እንደሚጨምር አስጠንቅቋል፡፡
ምንጭ ፎርቹን
The post የሼህ አላሙዲን ሜድሮክ ግማሽ ቢልዩን ብር እንዲከፍል ተወሰነበት appeared first on ሳተናው .