ለመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተደረገ የእራት ግብዣ ላይ የተገኙት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትሩ አቶ ጌታቸው እረዳ ከልክ ባለፈ ሁኔታ በጠጡት አልኮል ሳቢያ እጅግ ተዋርደው ማምሸት ብቻ ሳይሆን ዝግጅቱ ሳያልቅ በአጃቢዎቻቸው ተይዘው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ተደርጎአል።
ሰውየው ከሰከሩ በዃላ የኦሮሞ ተወላጅ የመንግስት ባለስልጣኖችን ተራ በሆነ ስድብ ሲያሸማቅቁአቸው ነበር ያመሹት። ከት ብለው እየሳቁ፡
” ይቅርታ አልጠይቅም። አሁንም ጋኔሎች ናችሁ። ምን አባህ ታመጣለህ። ወዲ (??????) (ቃሉን እዚህ ላይ መግለፅ ይከብደኛል) ። ከጋላ ወደ ማታውቁት ኦሮሞነት ቀይረን ሰው ያደረግናችው እኛ ነን” እና
ሌላም ሌላም አሰቃቂ ስድቦችን ሲሳደቡ አምሽተዋል። ይህን እየሰሙ መቛቛም ያቃታቸው ኦሮሞ ባለስልጣኖች ዝግጅቱን አቛርጠው እየወጡ ሲሄዱ የድምፅ ቀረፃ አድርገው ይሆናል በሚል ጥርጣሪ በህወሓት ካድሪዎች እንደሌባ እየተፈተሹ እና ሞባይል ስልካቸው ተቀምቶ እየተመረመረ እንዲሄዱ ተደርገዋል።
አቶ ጌታቸው በተጨማሪም ወደ አማራ ባለስልጣኖች ጠጋ በማለት፡
“የአማራን መሪት ለሱዳን የምንሰጠው ለእናተ ቛሚና መቛቛም የማትችሉት ጠላት እንዲኖራችሁ ለማድረግ ነው። እኛን የሚያገባን የለም እዛው ከሱዳን ጋር ጨርሱ። መሪቱ በአማራ ወረራ የተያዘ የሱዳን መሪት ነው። ( እየሳቁ ) ብርሀኑ ነጋ መጥቶ ያስመልስላችዋል”
በማለት ሲያዋርዱአቸው አምሽተዋል።
አቶ ጌታቸው በዚህ ሳያቆሙ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያምን ጨምሮ በርካታ የደቡብ ተወላጅ ባለስልጣናትንም ወርፈዋል። አቶ ሀይለማርያምን
“ለዘብተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር አየር ላንድ ውስጥ አንደኛ ተባለ”
በማለት ሲያሸማቅቃቸው አምሽቶአል። አቶ ሀይለማርያም ከመበሳጨት ይልቅ ሲስቁ ተስተውለዋል።
ጌታቸው ረዳ ከዚህ ሁሉ የተዋረደ ተግባሩ በዃላ በኮሙኒኬሽን ሚኒስትርነት ከቀጠለ በጣም እንገረማለን ብለውኛል የተከበሩት ምንጮቸ። ረጅም እድሜ እና ጤና ለእናተ።
እኔ ግን እላለው! እንኳን ሰድባዋቸው አዳራሽ ዘግተው እንደልጅ ሲገርፉአቸውም በፀጋ ከመቀበል ውጭ ያሳዪት ተቃውሞ የለም። ማንም አይነቀንቀውም ጌታቸው ነገም ያው ከአንጎበሩ ሲነቃ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ነው።
ከንግግሩ ሁሉ በጣም የገረመችኝ ግን ” የአማራን መሪት ከኢትዮጵያ ቆርሰን ለሱዳን የምንሰጠው ለአማራ ቛሚ ጠላት ለመፍጠር ነው” የምትለዋ ናት።