ብአዴን ከተከታይነት ለመውጣት በሚሊተሪው፤ በሕዝብ ደህንነቱ እና በሃብት በሕገመንግስቱ መሰረት እንኳን የሚጋእትን አላገነችም ስለዚህ ገና በቅንፍ ውስጥ ናት የራሷን ሃሳብ ለማደረግ የሚያስችል አቅም የላትም። ገና ከተከታይነት አልወጣችም።
ብአዴንና አለቃው ሕወሓት ።
“የትግራይ ሕዝብም ሆነ የሕወሐት አባላት ማወቅ ያለባቸው የወልቃይት ጥያቄ የብአዴን ጥያቄ አይደለም”
አዲሱ ለገሠ ከትግሬዎች የወይን መጽሔት ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ ። እዛው ጽሑፍ ላይ ብአዴን ውስጥ ችግር እንዳለና በአሁኑ ስዐት ሕብረተሰቡ ከብአዴን እንዳፈነገጠ ያትታል ።
ይህ እንግዲህ የምናየው ነገር በመሆኑ ክርክር አይኖረንም ። ከሰሞኑ አንድ ያላማረኝ ነገር እያስተዋልኩ ነው ። ብአዴንን አትንኩ ፤ ለብአዴን ጠበቃ እንቁም ዓይነት ነገር ። እንደኔ እንደኔ ብአዴን እንደ ድርጅት የዐማራ ሕዝብ ጠላት ነው ። በመካከለኛ አመራር ላይ ያሉ ዐማራዎች ቁጭቱ ቢኖርባቸውም ምንም ሲያደርጉ አላየንም ። ይህም በድርጅቱ ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ መፍጠር ስለማይችሉ ነው ። እንደ ድርጅት ስናወራ ደግሞ ድርጅቱ እንደ ድርጅት ከሚያደርገው አንጻር ነው ።
ለምሳሌ አያሌው ጎበዜ መሬት ለሱዳን ይሰጥ ብለህ ፈርም በተባለ ጊዜ መሬት ይሸጥ ብየ እንኳ አልፈርምም ነበር ያላቸው ። ይህንኑ ተከትሎ ብአዴን እንደ ድርጅት አቅም ስለሌለው አያሌው ጎበዜ ሲባረርና ደመቀ መኮንን ሲተካ መከራከር አልቻለም ።
እዚህ ላይ ሁለት ነገር እንይ ፦
በመጀመሪያ አያሌው ጎበዜ መሬት ይሰጥ ብየ አልፈርምም ቢልም በሌላ አቋሙ ላይ ብታዩት ከድሮው ዘመን እያነፃፀረ ዐማራን የምድር ገነት እንደፈጠሩለት አድርጎ ይቀባጥር ነበር ።
ሁለተኛው ነገር አያሌው ጎበዜ ይህን በማለቱ ለዐማራው አንድም ለውጥ አላመጣለትም (ድርጅቱ የማይረባ ስለሆነ ሊያግዘው አልቻለም) ።
ከሰሞኑ ንጉሥ ጥላሁን የተባለ ምንም ዓይነት ርሕራሔ እንዳታሳዩዎቸው በማለት ከቀባጠረ ዓመት ሳይሞላው ለገዱ ጥብቅና ቆመ ተብሎ ንጉሥ ጥላሁንን ትልቅ ነገር አድርጎ ማናፈስ ። አንድ ሰው ቀድሞ በነበረው ስራው እንወስነው እያልኩ አይደለም ። ነገር ግን ንጉሥ ጥላሁን ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት ሳንሰጥ ማለፍ እንችላል ።
ገዱ ። የገዱም ነገር የተያያዘ ነው ። ገዱ ምንም እንኳን እንደሌሎቹ ባይቀባጥርም አሁንም ገዱ ብቻውን ወይንም አንዳንድ ሰዎች በድርጅቱ ውሳኔ ላይ ተፅዕኖ መፍጠር እስካልቻሉ ድረስ ብአዴንን ጠነከረ ሊያስብሉት አይችሉም ። አንዳንድ ሰዎች እንደግለሰብ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በግለሰብ ደረጃ ያላቸውን ሕዝባዊነት እንጅ ያሚያሳየው ድርጅቱን ሊወክል አይችልም ። ድርጅቱን ሊወክል የሚችለው የእነርሱ ሐሳብ በድርጅቱ ላይ ሲንፀባረቅ ብቻ ነው ። ገዱ ትግሬ ባሕርዳር ላይ ዐማራን ሲገድል ከስልጣን አንሱኝ ብሎ ነበር ያለቀሰው ። ምክኒያቱም ምንም ማድረግ ስላልቻለ ። ገዱ ነገ ሊገሉት ይችላሉ ፤ ሊያስሩት ይችላሉ ድርጅቱ ምንም ሊያስጥለው አይችልም ።
አንዳንዶቻችን በውስጥ መስመር በምንገናኛቸው የብአዴን ልጆች ይመስለኛል ድርጅቱን የምናይበት መነፀር ። ይህ ስሕተት ነው ። ብአዴን ውስጥ ያለው አብዛኛው ዐማራ ለዐማራነቱ እንደሚያደላ ግልፅ ቢሆንም አመራሩን እንደገና ማዋቀር እስካልቻለ ድረስ የድርጅቱን ቅርፅ ሊቀይረው አይችልም ። አሁን ባሉበት ሁኔታ ይህን ነገር ማድረግ ይችላሉ ? አይችሉም !! ከቻሉም ደግየ ።
The post ብአዴንና አለቃው ሕወሓት – ወንደሰን በየነ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.