በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችን ትብብርና ድጋፍን ከወገኖቻቸው ይሻሉ!!!
*********************
በቀን 12/2009 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ከጣና ሀይቅ ዳርቻ የተነሳው ወጀብ አዘል ዝናብ የ29 ግለሠብ መኖሪያ ቤቶችንና በማህበር የተሰራ 15 ቤቶችን እንዲሁም የቁንዝላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጣራና ግድግዳቸው ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን ሁለት የቁም እንስሳወችን ገድላል፡፡የበቀሉ የተለያዪ አዝዕርቶችና የደረሱ የጓሮ አትክልቾች ከጥቅም ውጭ ሲሆኑ የ9ኛ የ10ኛ ክፍል ተማሪወች የሚማሩበት የትምህርት ቁሳቁስና የትምህርት መረጃወችና የፈተና ወረቀቾች ለብልሽት ተደርገዋል፡፡ የ9ኛ ክፈፍል ተማሪወች የማጠቃለያ ፈተናቸውን በፈራረሰውና በተጎዳው ክፍል እየወሰዱ ናቸው፡፡ የከተማውና የአካባቢው ማህበረሰብም የተጎዱትን ግለሰቦች በገንዘብና በጉልበት በማገዝ ቤተታቸውን የመገንባትና የመስተባበር ስራ አየሰሩ ናቸው፡፡ ይህ ከስተት ታይቶ የማታወቅና አስከፊ በመሆኑ የጠፉትን ንብረቶች የመፈለግና የወደሙትን የማሰባሠብ ስራ እያከናወኑ ነው፡፡
ወጀቡ ከፍተኛ ርቀት የተጓዘ ሲሆን ዕድሜ ጠገብ ዛፎችና ትልልቅ ዕፅዋቶችን አጥፍቷል፡፡ከወረዳና ከአካባቢው የተወጣጡ ኮሚቴ ተቋቁሞ በስነ ልቦና የመደገፍና ጉዳት የደረሠባቸውን ግለሠቦች ህብረተሰቡ እንዲረዳቸው የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጦል!!
#ምንጭ ሰሜን አቸፈር ሚዲያ
——————————–
የአንበጣው መንጋ የወረራቸው አካባቢዎች የመንግሥት እገዛ ተነፍጓቸዋል፤
በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞኖች የገበሬውን ሀብት ንብረት የሚያወድም አደገኛ አንበጣ ተከስቷል፡፡ አንዱ የአንበጣ መንጋ በቀን 16 ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ የሚችል ሲሆን ባሕር ዛፍን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ሰብልና እጽዋት መድምዶ በመብላት ያወድማል፡፡ በምዕራብ ጎጃምና በአዊ ዞኖች ከአራት ወረዳዎችና ከ50 በላይ ቀበሌዎች በአንበጣው መንጋ ተወረዋል፡፡
አንበጣው የሚመርጠው የለም፤ ገበሬዎች ‹‹ሁሉን በይ አንበጣ›› ይሉታል፡፡ የግብርናና የልማት ባለሙያዎች ለክልሉ መንግሥት ግብርና ቢሮ አንበጣው መጥፋት የሚችልበትን መድኃኒት ወይም ማንኛውም ዓይነት እገዛ ቢጠይቁም በአገር ውስጥ ለዚህ ዓይነት አንበጣ መከላከያ የሚሆን መድኃኒት የለም የሚል መልስ እንደተሰጠ ሰምተናል፡፡ አስቸኳይ ርብርብ ተደርጎ መከላከል ካልተቻለ በስተቀር አጠቃላይ የምዕራብ ጎጃምንና የአዊ አካባቢዎች ያለውን ሰብልና እጽዋት አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሊያወድም ይችላል ተብሏል፡፡
እስካሁን ድረስ ባለው ከሃምሳ በላይ ቀበሌዎች በበልግ ዝናብ የበቀለ ሰብልና በአካባቢው ያለውን እጽዋት ሁሉ እንዳወደመ ለማወቅ ተችሏል፡፡

The post በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ በቁንዝላ ከተማ ወጀብ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ 35 ሚሊዮን የሚጠጋ ሀብትና ንብረት አወደመ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.