Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ወረራውን በመመከት ለመልሶ ማጥቃት መዘጋጀት ያስፈልጋል ( ኮ/ል አለበል አማረ )

$
0
0

ኮ/ል አለበል አማረ

ህወሃት ” ጸረ- ሰላም ሃይሎችን ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለ2010 ለልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር” በሚል መፈክር ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ነሃሴ የሚዘልቅ በጎንደር ምድርና ህዝብ ላይ ሰፊ የወረራ አቕድ ማውጣቱንና ፈጻሚ ሃይሉንም እያዘጋጀ መሆኑን እየሰማን ነው። ህወሃት በዚህ የጥፋት የወረራ እቅድ አላማ አድርጎ የተነሳው፥ የጎንደርን አማራ በማንበርከክ የጀመረውን የተስፋፊነት አባዜ በማጠናከር ያሰባቸውን የአማራ መሬቶች ወደ ትግራይ ለማካለልና ለሱዳንም ሊሰጥ የተስማማውን መሬት ለመቸር፣እንዲሁም ጎንደር ላይ ተረባርቦ በሚያገኘው ድል ሌሎችንም ህዝቦች ለማንበርከክ ይረዳኛል በሚል ተስፋ የተዘጋጀ እቅድ መሆኑ ታውቋል።

ይህንን የጥፋት የወረራ እቅድ ለማስፈጸም ሁለት ክ/ጦሮች በዋነኛነት እና ከ5 ሌሎች ክ/ጦሮች የተውጣጣ ሃይል በተጨማሪነት እየተዘጋጀ ሲሆን ከፌደራ ፖሊስም የተወሰነ ሃይል መመደቡ ታውቋል፥ የአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎችን በጥርጣሬና በስጋት እንደተመለከቷቸውና ይህም ለህወሃትና ብአዴን አለመተማመን እንደሚያሰፋ ወሬወች እየተሰሙ ነው/ተጨማሪ ጥናት ያስፈልገዋል።እንደተሰማው፥ እቅዱ ሁሉንም የጎንደር አካባቢወች ሙሉ በሙሉ ከመቆጣጠርም በላይ ሰፊ የጦር መሳሪያ ዘርፋ እቅድም አብሮ ተካቷል።

የጸጥታ ሃይል አሰላለፍ ከመሃል ጎንደር፣ ከትግራይ፥ ከሱዳን እና ከሰቆጣ አቅጣጫ እንደሚንቀሳቀስ ታውቋል።

መላው አማራ ይህንን የትግሬ ህወሃት ወረራ ለማክሸፍና አጋጣሚውንም ለመጨረሻ ድል ለመጠቀም በሁሉም አቅሞቹ መረባረብ አለበት። እንደሚታወቀው ህውሃት እንዲህ አይነት ወረራ ሲያካሂድ መጀመሪያ የመገናኛ ዘዴወች ይቆራርጣል፥ እኛም ቀድምን ለዚህ መፍትሄወች ከማበጀታችንም በላይ ጠላት የሚጠቀምባቸውን የመገናኛ ዘዴወች ለማፈራረስ መዘጋጀት አለብን። ትግሬው ህወሃት ክረምቱን እየጠበቀ የሚያካሂደው ዘመቻ ሆን ብሎ ገበሬውን ከአዝመራው ለማለያየትና ለማደህየት መሆኑ ታውቆ የገበሬው አዝመራ እንዳይጎዳ የተቻለውን ጥረት እየተደረገ በአማራ ምድር የሚገኙ የትግሬ ወያኔ ንብረቶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀት። ይህ የትግሬ ወያኔ ወረራ ዛሬ በጎንደር አማራ ላይ ቢካሄድም ነገ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወገን ላይ የማይቀር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለጸረ ወረራው ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማስተላለፍ፣ በተለይም አማራው ጉዳዩ የራሱ መሆኑን ተረድቶ በያለበት ተደራጅቶ በወንድም እህቶቹ ላይ የሚደርሰውን ግፍ በያለበት እየተመካከረ እንዲበቀል ማድረግና በአጠቃላይ የአካባቢውን ነባራዊና ህሌናዊ ሁኔታውችን በመዳሰስ ወረራውን በማክሸፍ የመልሶ ማጥቃት እቅድ እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል። ይህ የትግሬ ወያኔ ወረራ፥ አማራው ሃምሌ 5 የወልቃይት መላ አማራ ቀን ብሎ ሰይሞ ለማክበር በውጭም በውስጥም እየተንቀሳቀሰ ባለበትና የአማራ የፖለቲካ ድርጅቶች ውህደት ለመፈጸምና ቀጣዩን ትግል በብቃት ለመምራት እየተዘጋጁ ባሉበት ሁኔታ መከሰቱ ትግሉን ይበልጥ ለማጠናከር አመች ሁኔታ ይፈጥርልናል።

The post ወረራውን በመመከት ለመልሶ ማጥቃት መዘጋጀት ያስፈልጋል ( ኮ/ል አለበል አማረ ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles