Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የአርቲስቶቻችን የባዶ መሶብ ግብዣ – በ: ሀ. ህሩይ, ቶሮንቶ

$
0
0
በ:   ሀ. ህሩይ, ቶሮንቶ
  ሰኔ,2017
 ሰሞኑን በተወሰኑ አርቲስቶች የተዘጋጀውን ወደ ሀገር የመመለስ ጥሪ ወይም ውትወታ በቴሌቪዥን ስመለከት ስልችት ያለኝን የሰራዊት እና የሙሉዓለምን የቅብብሎሽ ማስታወቂያ በተደራጀ መልኩ እንደገና አየሁት።
መቼም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን የሚመለከት እና ሬዲዮኑን የሚሰማ አድማጭ የነዚህን አርቲስቶች   የሳሙና፣ የ ኦሞ፣ የቢራ፣ ፓስታ ፣የሎተሪ ፣የውሃ ፣የኤግዚቢሽን አረ ምኑ ቅጡ ተመሳሳይ አሰልቺ ማስታወቂያ ሲያዳመጥ እና ሲመልከት በብስጭት ቴሌቪዥኑን ያጠፋ ሬዲዮኑን የዘጋ ብዙ ሰው እንደሚኖር እገምታለሁ።
 ወይ ጉድ!  የሰራዊት እና የሙሉዓለም አልበቃ ብሎ እነ ሸዋእፈራው፣ አበበ ባልቻም ተጨምረው ጭራሽ አሁን ደግሞ በቡድን ተደራጅተው በወሬ ቅብብሎሽ  ያደንቁሩን?   እንዳውም ቁጥራቸው በዝቶ ስመለከት እንደተለመደው የብሔር ብሔረሰብ ልብስ ይለብሳሉ ብዬ ነበር።
የሚያሳዝነው ነገር ልክ ቀይ ምንጣፍ አንጥፈው ወይም በሀገራችን ባህል መሠረት ቄጤማ ወይም ሳር ጎዝጉዘው ይቀበሉ ከዛም ደግሞ በተገቢው መልኩ ያሚያቋቁሟቸው ይመስል ለመመለስ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ስይሟሉ  ናፍቃችሁናል ኑልን ማለታቸው ነው።
በፌስ ቡክ ለጥሪአቸው መልስ የሰጠችውን አንዲት  እህትን በጣም አድንቄአታለሁ። እውነትሽን ነው።  ከእነዚህ አስመሳዮች እና  ዝና ፈላጊዎች  የሚገኝ መፍትሄ የለም። ሀገር አላችሁ ብቻ ብሉ ተመለሱልን ማለት ለችግሩ መፍትሄ አይደለም። ከሱ በፊት የሚሰሩ እና መሟላት ያለባቸው በርካት ቅድመ ሁኔታዎችና  ጉዳዮች አሉ። አይደለም ከሳኡዲ አረቢያ ለመምጥት አዲስ አበባ ውስጥ ለመጓጓዝ እንኳን የአውቶቡስ ወይም የታክሲ ገንዘብ ያስፈልጋል። ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚጣ ሰው ደግሞ ማረፊያ እና ምግብ ሌላም ብዙ ነገር ያስፈልጋል።  ታዲያ አርቲስቶቻችን ይህንን ማሰብ እንዴት ተሳናቸው?
 ሀገራችን ለከፍተኛ ረሀብ በተጋለጠችበት ግዜ (በ1977ዓ.ም) ማይክል ጃክሰን እና ሌሎች ድንቅ ይዓለማችን ዘፋኞች የሌለን ምግብ እና ውሃ ብሉ ወይም ጠጡ ብለው ባዶ መሶብ እያሳዮ ወይም አቅርበው የተራበውን ህዝብ ብላ አላሉም ግብዣም አልጠሩትም። ምክንያቱም የሌለን ነገር መጋበዝ ፋይዳ እንደሌለው ያውቃሉና።
ያደረጉት ግን ምግብ የሌለው መሶብ ከፈትው ብሉልን ሳይሆን መሶቡን በምግብ ነው የሞሉት። ይህንን ለማድረግ እንዲርዳ ኮንሰርት አዘጋጅተው “We are the World” የሚለውን ዜማ በማዜም ወገኖቻችንን ከረሀብ ለመታደግ ገንዘብ ነው ያሰባሰቡት። ታዲያ እነ ሰራዊት ምነው ይሄንን ማሰብ ተሳናቸው? ወይስ የተለመደውን ማስታወቂያ የሚሰሩ መሰሏቸው ይሆን?
 ችግሩ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ወይም ድራማ የሚሰራበት ሳይሆን ትክክልኛ እና አፋጣኝ መንግሥታዊ መፍትሄ የሚያስፈልገው ነው። በአረብ ሀገራት በተለይም በሳኡዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ችግር ከተፈጠረ ዓመታት አስቆጥሯል። በመንግሥት በኩል ግን ለችግሩ መሠረታዊ መፍትሄ  አልተሰጠም። ችግሩ ጉልቶ ሲመጣ ብቻ “ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ” ዓይነት መተራመስ ነው ያለው። ትርምሱም ቢሆን ከዜና ሽፋን ያለፈ ነው አያሰኝም።
 በየሀገሩ የሚገኙ የሀገራችን ኤምባሲዎች ዋና ሥራ የኢህአዴግን ፖለቲካዊ ማራመድ ነው። በውጭ  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚፈለጉት ሀገራቸው ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ፣ የግንቦት 20 እና የህዋሀትን ልደት እንዲዘክሩ ብቻ ነው?
 ስለዚህ አርቲስቶቻችን መንግሥትን እንደመንግሥት ኃላፊነትቱን እንዲወጣ እና ዜጎቸን እንዲታደጋችው ንገሩት።ለጉዳዩ ምን እርምጃ እየወሰደ እንደሆን ጠይቁት።

The post የአርቲስቶቻችን የባዶ መሶብ ግብዣ – በ: ሀ. ህሩይ, ቶሮንቶ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles