Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

የመምህራን አድማ በአማራው ክልል ስር እየሰደደ ነው – የሚሊዮኖች ድምጽ

$
0
0

ነገ ሰኞ በበርካታ የሰሜን ጎንደር ከተሞች መምህራን የሥር ማቆም አድማ ሊያደረጉ እንደሚችሉ አንዳንድ መረጃዎች እየወጡ ነው።
ከየካቲት 27 ጀመሮ በምእራብ ጎጃም ዞን የተጀመረው የመምህራን ተቃዉሞ በምስራቅ ጎጃም፣ በወሎ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን እየተሳፋ ሲሆን፣ ከሰኞ ጀመሮች በሰሜን ጎንደርም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ሊኖር እንደሚችል እየተነገረ ነው።
በምእራብ ጎጃም ዞን፣ በቋሪት፣ በአዴት፣ በሰቀላና በዳየም፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ወርቅ፣ በሸበል ፣ በመርጦ ለማሪያም፣ በበርታ ፣ በቻግኒ በቡብኝና በሞጣ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን በደራ ወረዳና በጋይንት ፣ እንዲሁም በወሎ ብዙ ት/ቤቶች መምህራን በአድማ ላይ ናቸው።
በአዊ ዞን ሁሉም ት/ቤቶች ስራ ለማቆም መወሰናቸውን መረጃዎች እየወጡ ሲሆን፣ በመራብ ጎጃም ዞን በቋሪት የመሰናዶ ት/በት ብዙ መምህራን ከሥራ አምቆም አድማ ጋር በተያያዘ ታስረውል።
በወልዲያ መሰናዶ ት/ቤት የጥልቅ ተሃዶ በሚል ለፕሮፖጋንዳ መምህራን መምህራን ስብሰባ እንዲገኙ ቢጠየቁም፣ መምህራኑ ስብሰባው ሳይካፈሉ ቀርተዋላ። መምህራኡኑ በቀጣይነት የሚያደርጉትን እንደተወያዩ ለማወቅ ተችሏል።
በአማራው ክልል እየተደረገ ያለው የመምህራን የስራ ማቆም አድማን ተማሪዎች ሊቀላቀሉት ይችላሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ህዝቡ ሰላማዊ በሆነ መንገድና በመናበብ መብቱን ለማስከበር ከሚያደረገው ትግል ወደ ኋላ የማያፈገፍግ መሆኑን የሚያመላክት ነው።
መምህራኑ እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴዎች የአገሪቱን ሕገ መንግስት ሆነ የአለም አቀፍ ሕግን ያከበረ እንቅስቃሴ ነው።

የዓለም ሴቶች ማኅበርን በተመለከተ የእቴጌ መነን ቃል

$
0
0

ግርማዊት እቴጌ መነን ይህንን ቃል የተናገሩት ከዛሬ 80 ዓመት በፊት ሲሆን መግለጫውን ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ አውጥቶታል። (Copied from an Amharic Chrestomathy by Edward Ullendorff page 37)

መረጃውን ያደረሱን Getachew Selassie; gashaselassie@gmail.com

የሂወት ውል /Hewett Treaty/

$
0
0

የሂወት ውል በ1876 ዓ.ም (1884) አጼ ዮሐንስ ከእንግሊዝና ግብጽ ጋር ውል የገቡበት ሲሆን ንጉሱ በሰሩት የፓለቲካ ቀመር ስህተት የኢትዮጵያን ጥቅምና ሙብት አሳልፈው ለወራሪዎች የሰጡበት፣ ከጎረቤት ደርቡሾች ጋር ጠላትነት በመፍጠር ለጎንደር መተማ መውደም (በደርቡሾች መቃጠልና መዘረፍ) እንዲሁም ለራሳቸው ለዮሐንስም ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነ፣ ኢትዮጵያን እርስ በርሱ ተያያዥነት ወዳለው ችግር ውስጥ የከተተ አስጠቂ ውል ነው። ይህንን ውል ተከትሎ እንግሊዝ ምጽዋን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ባለቤት ለሆነችው ለኢትዮጵያ ማስረከብ ሲገባት ለጣሊያን አሳልፋ ሰጠቻት። ጣሊያን ሳትለፋና ሳትደክም እንደ ገና ስጦታ ከእንግሊዝ ከተበረከተላት ከምጽዋ ወደብ በመነሳት ወደ ውስጥ ሃገር ቀስ በቀስ መስፋፋት ጀመረች።

ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ምጽዋ ላይ ስትደራጅ ብሎም ያለማቋረጥ ወደ ውስጥ ስትስፋፋ አንድ ነገር መደረግ አለበት እያሉ ራስ አሉላ በተደጋጋሚ በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉስ ለነበሩት ለአጼ ዮሐንስ ቢያሳስቧቸውም ለቴዎድሮስ ሞትና ለዮሐንስ መንገስ ባለውለታ የሆኑትን እንግሊዞችን ላለማስቀየም እንዲሁም በፈረመት የሂወት ውል ምክንያት ሁለት እጃቸው የታሰረው አጼ ዮሐንስ ምንም ማድረግ አልቻሉም ነበር። በተለይም ራስ አሉላ አንተን አውርዶ መንገስ ይፈልጋል በማለት እንግሊዞች የሚያስወሩትን ወሬ በማመን አሉላን በማግለላቸው የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጣሊያን እየተጠናከረ መጣ፣ ኢትዮጵያም የበለጠ የችግር አረንቋ ውስጥ እየገባች ሄደች።

የጣሊያኖችን የማይቆም መስፋፋት እና የንጉሱን ቸልተኝነት መታገስ ያልቻሉት ራስ አሉላ አባ ነጋ ሰሃቲ እና ዶጋሊ በሚባሉ ቦታዎች ከጣሊያኖች ጋር ጦርነት በማድረግና ወራሪውን በማሸነፍ ለጊዜው የጣሊያንን መስፋፋት የገቱት ቢሆንም ንጉሱ የሃገር ጉዳይነቱን በመተውና አሉላ ለስልጣኔ ያሰጋኛል በሚል መሠረተ ቢስ ጥርጣሬ ያለኔ ፍቃድ ለምን ከጣሊያን ጋር ጦርነት ገጠምክ ወደሚል የግል ተራ ጥል ውስጥ ገቡ። በዚህም የተነሳ ንጉሱ መቀመጫቸውን አስመራ በማድረግ እስከ ምጽዋ ድረስ በመወርወር ጣሊያንን ሲያስጨንቁ የነበሩትን ጀግናውን ራስ አሉላን ከስልጣናቸው በማንሳታቸው የተነሳ በተፈጠረ ክፍተት በመጠቀም ጣሊያኖች ያለከልካይ አስመራ ከተማ ሰተት ብለው መግባት ቻሉ።

አጼ ዮሐንስ የሰሩት ስህተት ለአጼ ምኒልክ እዳ ሆነባቸው። ስለዚህ አጼ ዮሐንስ በሰሩት ስህተት ምኒልክ ምን ያድርጉ? የትግራይ ባላባቶች ከጣሊያን በሚያገኙት አልባሌ የካኪ ሱሪና ኮት የሃገራችንን ጥቅም ለጣሊያን አሳልፈው ሲሰጡና በጥቅማ ጥቅም ሲሞዳሞዱ ጀግናው ምኒሊክ ናቸው ከሸዋ ድረስ ሺ ኪሎ ሜትር ተጉዘው ሄደው አድዋ ላይ ጣሊያንን አሸንፈው ከነጭ ባርነት ትግራይን ነጻ ያወጡት። ለምን በጣሊያን አልተገዛንም ካልሆነ በስተቀርር የሚያመዛዝኑበት ህሊና ካለቸው አጼ ምኒሊክ ለትግራይ ባለውለታ ናቸው። (Dereje Tefera የጻፈውን Bahirdar Press ፌስቡክ ላይ ታትሞ የተገኝ)

ወመኑ ዘይደምሮ ብርሃን ውስተ ጽልመት : ዳሸን ቢራን በፋሲል ከነማ ላይ መደረት – መስቀሉ አየለ

$
0
0

ዳጎን የተባለውን ጣኦት በታቦተ ጽዮን ላይ የመጫን ያህል ነው።ይኽን እብሪት የተፈለገውን ያህል መንገድ ተጉዞ ወደኋላ መመለስ የማይቻል ግድ ይለዋል፤ ካልሆነ ግን ዘመነ ሚጠት እስኪመጣ ደጋፊው ስደት ላይ መሆኑን ማመን አለበት፤ስለሆነም የጋንግሪኖቹ ሴራቸው ስጋና ደም እንዳይገዛ የቻለ ንቁ ሆኖ ወደ እርስቱ የሚመልሰውን ዛሩባቤልን ከመሃሉ ይፈልግ፤ ያልቻለ ደግሞ እንደ ባሮክና አቤሚሊክ ስልሳ ስድት አመት ይተኛና ዘመነ ሚጠት በደረሰ ግዜ የሶስተኛው ነጋሪት ድምጽ እንዲቀሰቅሰው ይሁን። ከዛ በመለስ የቀረበው ምርጫ ግን የጣኦቱን መስዋት በልቶ እንደ ሶሎሞን ከክብር መውረድ ነው። እርሱ የማርያም መንገድ አይሆንም።

በሮማን ኤምፓየር ዘመን ፈርኦኖቹ የሚዝናኑበት እስታዲዩም ነበር፤ዛሬም ድረስ በሮምና በወቅቱ የነርሱ ሁለተኛ መናገሻ በነበረችው በዛሬዋ ፓልሜራ (ሲሪያ) ውስጥ ይገኛሉ። የጨዋታውም አይነት በነገስታቶቹ ፊት የተመረጡና ጉልበት ያላቸው ባሮች “ፋያቲንግ ቱ ዴዝ” መጫወት ነበር። እድል ያልቀናው በወኔና በጭብጫ ገብቶ በጥቂት ደቂቃወች ውስጥ አስከሬን ሆኖ ይወጣል። ንጉሱ ከፈለገና ይበልጥ መደሰት ከፈለገ ደግሞ የጨዋታው አይነት ባሪያ ለባሪያ መሆኑ ቀርቶ ፍልሚያው ከአንበሳ ጋር ሊሆንለት ይችላል። ባሪያው በራሱ ላይ መብት የለውምና ባለቤቱን ለማስደሰት እስከ ተፈለገ ድረስ ሁን የተባለውን መሆን የምርጫው ነገር አይደለም። መንፈሱ ያልተሰበረ; ከሰውነት ተራ ወርዶ ወደ እቃነት ያልተለወጠና በነፍሱ ጭምር ለማሰብ አቅም ያለው ሰው ሲሆን ግን እንዲህ አይነቱን ውርደት ፈጽሞ አይሸከምም ነበር። “ለመሞት-ለመሞት ከነ ክብሬ ልሙት እንጅ በኔ ሲቃይ ሌላው ቁጭ ብሎ የእረፍት ቀኑን የሚዝናናብኝ ማነው?” ብሎ የሞቱን ጽዋ በራሱ እጅ እንዲወስዳት የሚያስችለው ከፍ ያለ የሞራል አቅም የገነባ ነበር ማለት ነው።

ዛሬ የአባይ ወልዱ ጭፍሮች ፋሲል ከነማን “ወርሰነዋል” ሲሉ ማሳየት የፈለጉት ይህንኑ ነው፣ “ጎንደሬ ምን ታመጣለህ፤ ስትፈልግ ይኽንን ሁሉ ተጨዋች ከሰውነት ተራ አውርደን የራሳችን ግላዲያተር ማድረግም እንችላለን” ነው ዋናው መልእክት። “ከእንግዲህ አርማኽ ቢሆን የዳሸን ቢራ መሆኑን እንድታውቀው ይሁን” ነው መልእቱ፤ አጼ ቲዎድሮስ የኮሶ ሻጭ ልጅ ብሎ የሰደበውን ሰው ባሊ ሙሉ ኮሶ ግቶ እንደገደለው ዛሬም ጋንግሪኖቹ ድፍን ጎንደሬን ባሊ ሙሉ ኮሶ ለመጋት መፈለጋቸውን ነው የሚያሳየው። ይህ ሁሉ እንግዲህ በዙሪያቸው እንደ አርተሌ እሳተ ጋሞራ የሚንቀለቀለው የጸረ ወያኔ ብሄርተኝነት ገንፍሎ ሳያጠፋቸው በፊት ውሃ ሊያፈሱበት እና የህዝቡንም መንፈስ አኮላሽቶ ህዝቡን ለለየለት ባርነት ማዘጋጀት ነው አለማው።

አንድ የአገዛዙን እውነተኛ ገጽታ የሚያሳይ የቀልድ ክሊፕ አይቸ ነበረ። ሰውየው ኑሮ ቢከብደው ሚስቱን ተሰናብቶ እራሱን ሊያጠፋ በአካባቢው ወደ ሚገኝ እረጅም ድልድይ ይሄዳል፤ ጫፉ ላይ ቆሞ ሃሳቡን ለመሰብሰብ ሲታገል አጋዚው ያገኘውና “እዚህ ምን ታደርጋለህ” ሲል ይጠይቀዋል። ሰውየው ደግሞ “ኑሮ ቢከብድብኝ መከራ ቢወድቅብኝ ሚስቴን ተሰናብቸ እራሴን ላጠፋ መጣሁ” ሲል ይመልስለታል፤ አጋዚው ቢሆን ግን ምክንያቱን ከሰማ ቦሃላ “እዚህ እራስህን ማጥፋት አትችልም፤ ከፈለክ ሌላ ቦታ ፈልግ” ይለዋል፤ ሰውየው ግራ በመጋባት ለምን ብሎ ቢጠይቀው የአጋዚው መልስ እንዲህ የሚል ነበር።”ቦታውን በሊዝ ገዝተነዋል” የሚል ነበር።

ዛሬ ከፋሲል ተጨዋቾች ውስጥ ማነው የነገሩ ስሌት የገባው ይሆን። ጥቂቶቹ ቀርተው አንዱ እንኩዋን “አርማየን አልሰጥም፤ማተቤን አልበጥስም” ብሎ ወደታች አርማጮሆ ወርዶ የጎቤን ሱሪ መውረሱን ቢያውጅ በእግር ኳስ ተጨዋቾች ታሪክ የመጀሪያው ሃውልት ሆኖ ይጻፋል። ክልቡን ከደመወዝ በላይ አሻግሮ ማየት የቻለ፤ ፋሲል ከነማ በዚህ የአብዮት መባቻ ወቅት ፈክቶ በመውጣቱ የጸረ ውያኔ ትግሉ ማኒፌስቴሽን መሆን መቻሉ ጋንግሪኖቹን እንቅልፍ እንደ ነሳቸው ያወቀ፤ ኳስ ማንቀርቀቡንና በጥይት ማንጠርጠሩን እኩል የሚያውቅ፤ የክፉ ግዜ ሰልፈኛ የደግ ግዜ ሰላምተኛ; “ደመዛችሁን ውሰዱ እንጅ ማተቤ ላይ መብት የላችሁም” የሚል ማን ይሆን ?፤ በላይ ዘለቀ ሚስቱንና ልጁን ላፈነበት እና “ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፣ እጅህንም ለኛ ስጥ” ብሎ ለላከበት የፋሽስት ሰላቶ የመለሰውን መልስ ልብ ብሎ የሰማ የዘመናችን በላይ ማን ይሆን ?፤ “ኳስ ለምኔ፤ ጠመንጃ ምርኩዜ!” ብሎ ግዳይ የሚወጣ የወንድ ቁና የቱ ይሆን..

የብአዴን የሰሞኑ መገለጫዎች ህወሓት ብአዴንን “አይደገምም” የሚል ከነቴራ ያለበሱበትን ሂደት ያመላክታል – ኤርሚያስ ለገሰ

$
0
0

የብአዴን የሰሞኑ መገለጫዎች ህወሓት ብአዴንን “አይደገምም” የሚል ከነቴራ ያለበሱበትን ሂደት ያመላክታል – ኤርሚያስ ለገሰ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እና ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የዓድዋን በዓል በድምቀት አከበሩ

$
0
0

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እና ሰማያዊ ፓርቲ  የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን በጋራ በድምቀት አከበሩ ።  መሪ ቃላቸውም “የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የጥቁር ህዝብ ድል ነው” የሚል የነበረሲሆን ከተጋባዥ እንግዶች መካከል አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ድንቁ ወልደማርያም እና አቶ ሚካኤል መልዐከ ” የአድዋ በዓል ሲከበር ታላቁን የጥቁር ህዝብ ድል የመሩት እምዮ ምኒልክ እንደ ንጉስ ቤተ መንግስት ተሰይመው ሳይሆን እንደ ጦር ጀነራል በጦር ሜዳ ውለው ለጀግኖች አርበኞች ቆራጥ አመራር በመስጠት ነውና ታሪክ ለዘለዓለም ሲያከብራቸው ይኖራል” ብለዋል ። የሰማያዊ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ እና የመኢአድ ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር በዛብህም የበዓሉን ታዳሚዎች  በአድናቆት ከመቀመጫቸው ያስነሳ ጆሮ ገብ ንግግር አድርገዋል ። በዓሉ የሁለቱ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን በአዲስ መልክ “ተራማጅ የዜጎች ንቅናቄ ”  በሚል እየተደራጀ ካለው ስብስብ ጋር አንድ ትልቅ አማራጭ ሀይል ሆኖ የመውጣት ፍላጎትና ጅምር መኖሩንም የሚያመላክት የነበረ መሆኑ ብዙዎችን አስደስቷል ።

አዳማ ከኦሮሚያ የመውጣት መብቷ ሊከበር ይገባል – ይመር አብዶ

$
0
0

የአዳማ ልጅ ነኝ። እዚያው ተወልጄ ያደኩ። አባቴ ኦሮሞ ሲሆን እናቴ ጉራጌ ናት። አባቴ ኦሮምኛ ይናገራል። ግን ቤታችን የሚነገረው አማርኛ ነው። በአብዛኛው የናዝሬት ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ነው። በከተማዋ በየመንገዱ በብዛት የሚነገረው አማርኛ ነው። አዳማ ናዝሬት እንደ አዲስ አበባ ናት ማለት ይቻላል።

የናዝሬት ህዝብ አጣብቂኝ ዉስጥ ያለ ሕዝብ ነው የሚመስለው። ናዝሬት የኦሮሚያ ክልል መንግስት መቀመጫ ናት። በዚያ የክልሉ ምክር ቤት ጨፌው ይሰበሰባል። የጨፌዉን ስብሰባ ለተመለከተ ግን በምንም መስፈርትና  ሚዛን ፣ የናዝሬትን ሕዝብ የሚወክል ስብስበ ስለመሆኑ የሚያመላከት ነገር አይታይበትም። ለምሳሌ አብዛኛው የናዝሬት ህዝብ በጨፌው የሚነገረዉ ንግግርና ዉይይት መከታተል እንኳን አይችልም።የሕዝብ ተወካይ ነን ባዮቹ ተሳስተው እንኳን በጨፌ ዉስጥ አማርኛ አይናገሩም።

በክልሉ ሆነ በከተማዋ መስሪያ ቤቶች ከሄድን፣  አቶ ግርማ ካሳ እንደገለጹት፣ ማመልከቻ ለማስገባት ችግር ነው። በአማርኛ ጽፈን፣ ገንዘብ በመክፈል ወደ ቁቤ እስተርጉመን ነው ማመልከቻውን የምናስገባው። ከክልሉ መንግስት ደብዳቤ ከተላከልንም፣ የተጻፈውን የሚተረጉምልን  መፈለግ ግዴታ ነው። ይህ አይነት ችግር ያለባቸው ከአዳማ ናዘሬት ነዋሪዎች 2% ወይም  5% ቢሆኑ እሺ፣ ግን 75% የሚሆነው ህዝብ ለዚህ አይነት ችግር የተጋለጠ ነው።

አብዛኞቹ የናዝሬት ነዋሪዎች እየፈራን ነው የምንኖረው። የመብት ጥያቄ ብናነሳ ኦህዴዶች የፈለጉትን ሊያድርጉብን ይችላሉ። ዘመኑ የነርሱ ነውና። ተወልደን ባደግንበት ከተማ፣ አማርኛ ተናጋሪ በመሆናችን መጤ ነው የሚሉን። በመሆኑም አብዛኛው ህዝብ ዝምታን መርጦ ነው ያለው።

የአቶ ግርማ ካሳ ጽሁፍን ዘሃበሻ ላይ ሳነብ፣ በአብዛኛው የናዝሬት ነዋሪ ልብ ውስጥ ያለውን ትልቅ ጉዳይ አጉልቶ በማውጣቱ እንደ ናዝሬት ነዋሪ ደስ ነው ያለኝ። በዚህ አጋጣሚ ለአቶ ግርማ ምስጋናዬን ማቅረብ እወደለሁ። ስለ ወልቃይት ጠገዴ ብዙ ይወራል። “በወልቃይት መሬቱ የትግራይ ነው፣ እናንተ ትግሬ ናችሁ፤ ትግሬነትን የማትቀበሉ ከሆነ ወደ አማራው ክልል መሄድ ትችላላችሁ” እየተባሉ ነው። የወልቃይት ጥያቄም ትኩረት አግኘቶ ሕዝብን ማንቀሳቀሱ ተገቢ ነው።

በተመሳሳይ ሁኔታ እንደ ናዝሬት  ባሉ ከተሞች የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪዎችም በግድ ኦሮሞነት እየተጫነባቸው ነው። ኦሮምኛ የማይናገሩ ከሆነ ፣ ራሳቸውን ከኦሮሞነት ጋር የማያስተሳስሩ ከሆነ መኖር እንዳይችሉ ተደረጎ ነው ኦህዴድ እየተንቀሳቀሰ ያለው። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንዲከበርለት ፣ ከትግራይ ክልል ወጥቶ ወደ ጎንደር እንዲቀላቀል እያደረገ ያለው ትግል ትኩረት እንደተሰጠው፣ አቶ ግርማ እንደጠየቁት፣ የናዝሬት ሕዝብ ጨመሮ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞች ከኦሮሚያ ወጥተው የራሳቸው አስተዳደር የመመስራት መብታቸው ሊጠበቅላቸው ይገባል። የናዝሬት ህዝብ በማይወክሉት መተዳደር የለበትም።

የአዳማ ህዝብ ሆነ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለው ህዝብ ቢጠየቅ ሊመለስ የሚችለው የታወቀ ነው። አቶ ግርማ እንዳሉት ከኦሮሚያ ዉጭ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ነው የሚፈለገው። የሕዝብ ፍላጎት ደግሞ በማስፈራርት፣ በኃይል ወደ ጎን ማድረግ አይቻልም። እርግጥ ነው በአንዳንድ የኦሮሚያ ዞኖች አሁን ያለችው ኦሮሚያ እንድትቀጠል ጠንካራ አቋምና ፍላጎት አላቸው። ሆኖም ግን የነርሱን ፍላጎት በሌላው ላይ መጫን አይችሉም። እነርሱ የፈለጉት ወይም እኛ የፈለግነው ሳይሆን ሕዝብ የፈለገው ነው መሆን ያለበት። ህዝብ ደግሞ በወረዳ ደረጃ፣ በዞን ደረጃ ከአንድ ክልል ወጥቶ ራስን ማስተዳደር ወይንም ከሌላ ክልል ጋር መቀላቀል ከፈለገ መብቱ እንደሆነ መታወቅ አለበት።

በድንገት ተቀስቅሶ የዝቋላ ተራራን ደን ያቃጠለው እሣት በቁጥጥር ስር ዋለ

$
0
0

የ3ሺህ ሜትር ከፍታ ያለው በዚሁ የዝቋላ ተራራ ከዚህ በፊት ሙሉ ለሙሉ በደን የተሸፈነ እንደነበር ይነገራል፡፡ የአቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚገኝበት ይኸው ገዳም ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን የአካባቢው ህብረተሰብ  ደኑን ለተለያዩ ግልጋሎቶች  እየተጠቀመበት በመምጣቱ  ተራራው እየተራቆተ መምጣቱም ተመልክቷል፡፡ አሁን ደግሞ የዝቋላ ተራራን ሸፍኖ የሚገኘው ደን ሳይታብ በተነሳው ድንገተኛ እሳት ሰፊው ቦታ የሚሸፍነው ደን መቃጠሉ ተገልጿል፡፡ ይሁንእንጂ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የኢትዮጵያ አየር ኃይል  ሰራዊት አባላት ፣የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የገዳሙ ነዋሪዎች ባደረጉት ርብርብ  በቁጥጥር  ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

ስለደኑ የቃጠሎ መንስኤ ግን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ደኑ ከቅርብ አመታት ወዲህ በተደጋጋሚ የመቃጠል አደጋ እያጋጠመው በመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና ደኑን መልሶ ለመተካት ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ጥሪ ቀርቧል፡፡

 


ባለ ጠጎች ሆይ! የግፍ ክምርን ናዳ ፍሩ – በላይነህ አባተ

$
0
0

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

በሃያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን ልጆችና እናቶች ምግብ ሲለቅሙና ቆሻሻ ውስጥ ሲኖሩ በቆሻሻ ናዳ ማለቅ እስከማውቀው ድረስ በኢትዮጵያ ብቻ የተከሰተ እልቂት ነው፡፡ ይህ እልቂትም የሁላችንም የቁም ሞት ነው፡፡ ልጆችና እናቶች ቆሻሻ ሲበሉ በቆሻሻ ናዳ ያለቁት ለማኙ አገዛዝ በእነዚሁ ቆሻሻ በሚበሉት ዜጎች ሥም ሳይታክት እየለመነ በሚረጠበው ገንዘብ ከሆዳም በላጠጎች ጋር እየተሻረከ ውሀና መብራት የሌለው ፎቅ በሚቆልልበት ከተማ ነው፡፡

ባለጠጎች ሆይ! የራሱን ፍላጎት ለማራመድ የዓለም ባንክ ለማኝ ገዥዎችን እየገዛና የናንተን የባለ ጠጎችን ፎቅ እያሳዬ “አድገዋል” እያለ ሲያታልል የገጠጠው አጥንታችንና በቆሻሻ ናዳ ያለቁት ዜጎቻችን ፍትህ ለጠፋባት ምድር ሳይሆን ለሰማዩ እያመለከቱ ነው፡፡ ለናንተ ከፎቅ ለተሰቅላችሁት ባለጠጎችና በቆሻሻ ተመጋቢዎች፣ሶማልያና ሱዳን በሚያልቁት ወታደሮች ሥም በተረጠቡት ልጆቻቸውን በውጪ አገር ዩኑቨርሲቲዎችና ከተማዎች ለሚያንቀባርሩት ለማኝ ገዥዎች ባይታያችሁም ቆሻሻ መመገባችን፣ ቆሻሻ ውስጥ መኖራችን፣ እንጀራ ስንፈልግ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ መታረዳችን፣ ቀይባህርና ሜዲትራንያን መስመጣችን፣ በአረብ አገር እየተዠለጥን መደብደባችን፣ የአፍሪካን ወህኒዎች መሙላታችንና፣ የሚቆጠረው ጎድናችን እንደሚያረጋግጠው ችጋር ፈጅቶናል፡፡ ከነፍሰ-ገዳይ ገዥዎች በመሞዳሞድ የናጠጣችሁ ባለ ጠጎች የሕዝብን ደም እንደ ትኋን እየመጠጣችሁ የቁንጣንን ፌስታ ስታሽካኩ ስንቱ እንደ ቀለም ተመጦ የጠኔ እሽሩሩን ይቆዝማል? ስንቱ ከቆሻሻ ውስጥ ምግብ ሲለቅምና ቆሻሻ ውስጥ ሲያድር አለቀ? የናንተ ልጆች በአውሮጳ፣ አሜሪካና ቻይና በጥጋብ እንደ ፌንጣ ሲፈናጠዙ ስንቱ ህጻናት በጠኔና ጠኔ- ወለድ በሽታዎች ከጎዳና ዳር ሲያቃስት ዋለ?

ሰው በትጋቱና በሥራው ስለሚለያይ ባለ ጠግነትና ድህነት ይኖራሉ፡፡ ነገር ግን ባለ ጠግነት በኢትዮጵያ የሚበቅለው የትጋት፣ የጥበብና የሥራ እርግብ ዘርቶት ሳይሆን የጭካኔ፣ የማጭበርበር፣ የመዋሸት፣ የመክዳትና የመስሎ አዳሪነት ቁራ በትኖት ነው፡፡ ሰነፎች፣ ድልዱሞችና ቀጣፊዎች ባለ ጠጋ ሲሆኑ ትጉኃን፣ ጥበበኞችና እውነተኞች ምንዱብ ድሆች ይሆናሉ፡፡ ይህንን የተገላቢጦሽ የንብረት ሥርጭትም እንኳን ጥበበኛና እውነተኛ ድሆች ዱልዱምና ቀጣፊ ቱጃሮችም ያምናሉ፡፡

በኢትዮጵያ ንብረት ለማካበት ህሊናን እንደ ቅርፊት ገሽልጦና እግዚአብሔርን ክዶ ስስትን እንደ ሞራ መልበስንና ነፍሰ-ገዳይ ማምለክን ይጠይቃል፡፡ ንብረት ማፍራት ለነፍሰ-ገዳይ ጉቦ መነስነስን፣ ቤተሰብንና ጓደኛን አሳልፎ መስጠትን፣ ሁለት እግር አንስቶ ውሸትን ማቡነንን፣ አይንን በጨው ታጥቦ  ማጭበርበርን፣ ጥቁር ካባ ደርቦ በአድሎ መፍረድን፣ አይኔን ግንባር ያርገው ብሎ በቅጥፈት መመስከርን፣ እንደ እንጨት ሸብቶ ጭራ መነስነስን፣ ኮፍያን አጥልቆ መነኩሴ መምሰልን፣ መስቀልን ጨብጦ ይሁዳን መሆንን፣ ምሁር ነኝ እያሉ ለድልዱም መታዘዝን፣ ወዳጅ መስሎ ቀርቦ አቃጥሮ ማስገደልን ይጠይቃል፡፡ “ካለእነዚህ ሰይጣናዊ ግብሮች በትጋቴና በሥራዬ ባለጠጋ ሆኛለሁ!” የሚል ቱጃር እስቲ እጁን ያውጣ!

ነፈሰ-ገዳይዎች ሕዝብን ለመግደልና ለመግዛት ባሩድን ይጠቀማሉ፡፡ ባሩዱን የሚተኩስ ካድሬና ሰላይ ለመቅጠርም ገንዘብ ያግበሰብሳሉ፡፡ ገንዘብ  የሰይጣን መሳሪያ እንደሆነም ቅዱሱ መጽሐፍ ያስተምራል፡፡ ይህ የሰይጣን መሳሪያ ገንዘብም እሚመጣው ሰራዊታችንን፣ ክብራችንን፣ እርስታችንንና የተፈጥሮ ሐብታችን እንደፈለጉ ከሚጠቀሙትና እጣፈንታችንንም በመወሰን ላይ ካሉት ምዕራባዊና ምስራቃዊ ቅኝ ገዥዎች ነው፡፡ ይህ የቅኝ ገዥዎች ገንዘብ እሚገባውም ከባንዳ ነፈሰ-ገዳይዎች እጅ ነው፡፡ ባንዳ ነፍሰ-ገዳዮችም በዚህ ገንዘብ ሎሌ ባለ ጠጎችን ይፈጥራሉ፡፡ ሎሌ ባለ ጠጎችም የበለጠ ለመክበር ቦንድ፣ በልማት፣ በጫራታና በስጦታ ስም ጉቦ ለነፍሰ -ገዳዮች መልሰው ይሰጣሉ፡፡ በዚህ የቀለበት አዙሪት ገንዘብ ከቅኝ ገዥ ወደ ባንዳ ነፍሰ-ገዳይ  ከዚያም ወደ ነፍሰ-ገዳይ አምላኪ ባለ ጠጋ፤ ተመልሶም ወደ ነፈሰ-ገዳይ ገዥ፤ በመጨረሻም ወደ ቅኝ ገዥ  ባንኮች ሲሽከረከር የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቆሻሻ ውስጥ ምግብ ሲፈልግ በቆሻሻ ናዳ ያልቃል፤ በርሃብ ተግጦ አጥንቱ ይፈጣል፡፡ የፈጠጠው አጥንቱም ፎቶ እየተነሳ በዓለም ጋዜጦችና መጽሔቶች ይታያል፡፡ ይህንን በጋዜጣና በመጽሔት የሚታይ የገጠጠ አጥንትም ልመና እማይታክታቸው ነፍሰ-ገዳይዎች የገንዘብ መለመኛ አኮፋዳ ያደርጉታል፡፡ ያኮፋዳው ገንዘብ ሲመጣም በተዋቀረው የገንዘብ አዙሪት ቀለበት ይሽከረከራል፡፡ ከገንዘቡ አዙሪት ቀለበት የራቀውና ገንዘብ የተለመነበት የድሃ አጥንት ግን ለቀበርም ሳይበቃ ጆፌ ይግጠዋል፤ የተረፈውንም አውሬ ይቆረጥመዋል፡፡

ሐዋርያው ያዕቆብ ፩፡፱-፲”የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሳር አበባ ያልፋልና፡፡” እንዳለው ሕዝብ አእምሮውንና ሕዋሳቱን ታስሮ በርሃብ ሲረግፍና ሲዋረድ እናንተ በግል አውሮፕላን እየበረራችሁ፣ በአውሮጳና በአሜሪካ እየታከማችሁ፣ በድሃ ቁስል ፎቅ እየሰራችሁ፣ ባማረ አውቶሞቢል እየተመማችሁና በጎዳና አዳሪ እየተፋችሁ በውርደታችሁ ትመካላችሁ፡፡ ሕጻናት ምግብ ከቆሻሻ ሲፈልጉ በቆሻሻ ናዳ እንደ ቅጠል ሲረግፉ እናንተ “ለቦንድ፣ ለጫራታ፣ ለልደት፣ ለሰርግ፣ ለልማት፣ ለልጆቻችሁ መማርያ ወዘተርፈ” እያላችሁ ጉቦ ለነፍሰ-ገዳዮች በመነስነስ በውርደታችሁ ትንደላቀቃላችሁ፡፡ ይህንን የውርደት መንደላቀቅ እግዚአብሔር ስለሚያይ እንደ ሳር አበባም ትረግፋላችሁ፡፡

መስማት ባትፈልጉም አሁንም ሐዋርያው ያዕቆብ በ፭፡፩-፮ ያለውን ላስታውሳችሁ፡፡

ባለ ጠጎች ሆይ ስለሚደርስባችሁ ጭንቅ ዋይ ዋይ እያላችሁ አልቅሱ፡፡ ሐብታችሁ ተበላሽቷል፤ ልብሳችሁም በብል   ተበልቷል፡፡ ወርቃችሁም ብራችሁም ዝጓል፡፡ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል፡፡ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላል፡፡ ለኋለኛው ቀን መዝገብን አከማችታችኋል፡፡ እንሆ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፡፡ ያጫጆችም ድምጽ ወደ ጌታ ፀባዖት ጆሮ ገብቷል፡፡ በምድር ላይ ተቀማጥላችኋል፣ በሴሰኝነትም ኖራችኋል፤ ለእርድ ቀን እንደሚያወፈር ልባችሁን አወፍራችኋል፡፡ ጻድቁን ኮንናችሁታል፣ ገድላችሁታልም፡፡

አዎ! “የተናገርኩት ከሚጠፋ የወልድኩት ይጥፋ!” እሚል ሕዝብ ህይወቱን፣ ክብሩን፣ መሬቱንና ሌላውንም የተፈጥሮ ሐብቱን  በቱጃር ቅኝ ገዥዎች፣ በምታመልኳቸው ባንዳ ነፍሰ-ገዳይዎችና በናንተ ተቅምቶ ይጮኻል፡፡ በተቀማ ሐብት የደነደነው ልባችሁም በገጠሩ፣ በከተማው፣ በትምህርት ቤቱና በመንገዱ የሚያቃስተውን የሕጻናት ጠኔ አልሰማ ብሏል፡፡ የሕጻናት ጠኔ እንቅልፍ ነስቷቸው ለፍትህ እሚታገሉትን አሳስራችሁ ሥራቸውንና ንብረታቸውን ወስዳችኋል፡፡ ከነፈሰ-ገዳዮች እየተሞዳሞዳችሁ አንዳንዶችንም አስገድላችኋል፡፡

ባለ ጠጎች ሆይ! የእናንተ ልጆች በአሜሪካ፣ በአውሮጳና በቻይና ከተሞች ቁንጣንን ሲተፉን ሲያድሩ ምስኪን ህጻናትና እናቶቻቸው ከቆሻሻ ምግብ ሲለቅሙ ረግፈዋል፡፡ የእነዚህ ህጻናትና እናቶች ነፍስ ይጮኻል! ጩኸቱም ወደ ጌታ ፀባዖት ደርሷል፡፡ በምድር ተቀማጣላችኋል፡፡ ከነፍሰ-ገዳዮች ጋር ግብር በልታችኋል፡፡ እንደ ፍሪዳ ልባችሁንም አዎፍራችኋል፡፡ የትጉሁን፣ የጥበበኛውንና የእውነተኛውን ንብረት ቀምታችኋል፡፡ ከነፈሰ-ገዳዮች ጋር በማበር ጻድቁን ኮንናችኋል፣ አስገድላችሁታልም፡፡ ያስገደላችሁንት ደም ጠጥታችኋል፣ ያስራባችሁትን ሥጋም ለብሳችኋል፡፡ ሥጋችሁ ከድሀ የተገሸለጠ ሥጋ፤ ደማችሁ ከሙት የተማገ ደም ነው፡፡ አሜሪካ፣ አውሮጳና ኤሽያ እሚሽቀረቀቱት ልጆቻችሁ ሥጋና ደምም የድሀ ልጆች ሥጋና ደም ነው፡፡ ስለሚደርስባችሁ ጭንቅ ዋይ ዋይ እያላችሁ አልቅሱ፡፡ ሐብታችሁ ተበላሽቷል፤ ልብሳችሁም ብል በልቶታል፡፡ ወርቃችሁም ብራችሁም ዝጓል፡፡ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል፡፡ ሥጋችሁም እንደ እሳት ይቃጠላል፡፡

ባለ ጠጎች ሆይ! የግፍ ክምርን ናዳ ፍሩ! ከናዳው እንድትተርፉ እጇን ወደ እግዚአብሔር የዘረጋችውን የኢትዮጵያን ጩኸት ስሙ፡፡ ጆሯችሁን እንደ አኩክ የደፈነውን ስስት መንቅራችሁ የህሊናን ደወልና የርሃብ ጉንፋን የሚስሉትን ወገኖቻችንን አዳምጡ፡፡ የድሀን ሥጋ ለገፈፋችሁት ድሃ፣ የሙትን ደምም ለመጠጣችሁት ሙት መልሱ፡፡ ለለማኝ ነፈሰ-ገዳይ  ገዥዎች መስገዱን ተውና ፊታችሁን ወደ ሕዝብና እግዚአብሔር አዙሩ፡፡ ልቡናውን ይስጣችሁ፤ ኢትዮጵያንም እንደገና ቆሻሻ ስትበላ በቆሻሻ ናዳ ከማለቅ ይጠብቃት፡፡ አሜን፡፡

 

መጋቢት ሁለት ሺህ ዘጠኝ ዓ.ም.

 

አድዋን ወደ ፖለቲካ ድል መቀየር ለምን ተሳነን? እርግማን ሁለት: “ምኒልክ ኤርትራን ሸጠ፤ ትግራይን በደለ”

$
0
0

ከዝግጅት ክፍሉ:- “አድዋን የሚያህል ወታደራዊ ድል ስለምን ወደ ፖለቲካዊ ድል መቀየር ተሳነን? በሚል ርዕስ የመጀመሪያውን ክፍል ማቅረባችን ይታወሳል፤ ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህኛው ክፍል ሁለት ዕትም እርግማን ሁለት “ሚኒልክ ኤርትራን ሸጠ፤ ትግራይን በደለ” የሚለው ርዕስ ዳሰናል፡፡


የኢትዮጵያ አገራዊነት ታሪክ ተፃሪሪ ትርጓሜና የዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ምስረታ ሂደት የተመዘዙ መንታ ሰበዝ ናቸው፡፡ “ቅኝ ግዛት” vs “አገር ምስረታ፣ ማቅናት/ግንባታ” የሚሉ ተፃራኒ ትርጓሜዎች እንዳሉ ሁሉ፤ “አገር ሻጭ” እና “ባንዳ” የሚሉ የፖለቲካ እርግማኖች የዘመናዊት የኢትዮጵያ የታሪክ ገጽታ  አካል ሆነው ቀርበዋል፡፡ ማንነትን የታከከ የታሪክ ትርጓሜ ባለበት ሁኔታ እነዚህ ብያኔዎች ሊጠፉ የማይችሉ የታሪክ ፍም እሳቶች ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ በገዥዉ ኃይል ፊት ታሪክ ትምህርት መሆኑ ቀርቶ ፍርድ ቤት ሆኗል፡፡

አፄ ዮሐንስ አራተኛ ከእርሱ በፊት እንደነበረው ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስም ሆነ ከኋላው እንደተከተሉት ነገሥታት በሚያሟግት የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ያለፈ መሪ ነው፡፡ አፄ ዮሐንስ ወደ ስልጣን የመጣበት መንገድ ምኒልክ ወደስልጣን ለመውጣት ከተጓዘበት የዲፕሎማሲ መንገድ የሚለይ አደለም፡፡ ስልጣን የኃይል ሁሉ ማዕከል በሆነበት ቦታ ገባሪነትን መካድ ለኢትዮጵያ መሳፍንቶች የተለመደ ባህሪ ነበር፡፡ በውጭ ኃይሎች ድጋፍ የጦር መሳርያ አቅምን ማጠናከር፤ ጊዜና ወቅት ጠብቆ ወደ ንግሥና መንበር መውጣት፤ የዮሃንስ እና የምኒልክ መንታ ገፀ-ባህሪያት ናቸው፡፡

አፄ ሚኒሊክ “የጣልያን ተላላኪ ባንዳ ነበር” ማለት የሚቀናቸው የትግራይ ብሔረተኛ ልሂቃን የዮሐንስን የቀደመ የታሪክ እድፍ ተስቷቸው አይጠቅሱትም፡፡ የስዊዝ ሰው የሆነው ሙሲንጀር ፓሻ የጊዜው ያገር ጥናት ተጓዥ መንገደኛ ነበር፡፡ ይህ ሰው በምጽዋና በከረን አመታትን አሳልፈዋል፡፡ የወቅቱ ደጃች ካሳ (ዮሐንስ) እና የእንግሊዞችን ግንኙነት በማቃናት ቀዳሚ ሰው ነበር፡፡ በዚህ ሰው አገናኝነት ከእንግሊዞች ጋር የተወዳጀዉ  ደጃች ካሳ ለናፒየር ጦር የመቅደላ መንገድ ሁነኛ ጠቋሚ ነበር፡፡ ያለ አንዳች ግነት ስለ ሥልጣን ለውጭ ኃይሎች በመታመን (ባንዳ፡- ለባዕድ ሥርዓት ታማኝነትን ማሳየት) አስገባሪውን (አፄ ቴዎድሮስን) በመክዳት ባገኘው የጦር መሳርያ ድጋፍ ታግዞ ወደ ስልጣን የወጣው ቀዳሚው ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ አራተኛ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩ መሳፍንቶች  ለአብነት በቴዎድሮስ ዘመን እንደ አገው ንጉሴ ያሉ መሳፍንቶች ከውጪ መንግስታት ጋር ቢፃፃፉም በውጭ ሀይሎች የጦር መሳሪያ ድጋፍ ወደ ሥልጣን ለመውጣት የተሳካለት መሳፍንት አልነበረም፡፡ ከዳጃች ካሳ (ዮሐንስ በስተቀር)!!

የአፄ ምኒልክ መንገድ ከዚህ ብዙ የራቀ መሆኑን መካድ ያስተዛዝባል፡፡ የአፄ ምኒልክ እና የጣልያኖች ግንኙነት ከአፄ ዮሐንስ የንግስና ዘመን ይጨምራል፡፡ ሚኒሊክ የዘር ሀረጉን የሚስበው ከአፄ ልብነ ድንግል ነው፡፡ ከዚያም ባለፈ የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የልጅ ልጅ የኃይለ መለኮት ልጅ በመሆኑ የመሀል ኢትዮጵያን ግዛት በመቆጣጠርና የደቡብ እና ምዕራብ ኋላም የምስራቅ ኢትጵያ ግዛቶችን በመጠቅለል ወደ ንጉሠ ነገሥትነቱ የመውጣት ምኞት ነበረው፡፡ ለዚህም ይመስላል አፄ ዮሐንስ ከነገሰበት 1964-1870 ዓ.ም ለተከታታይ ሰባት ዓመታት ለአፄ ዮሐንስ ሳይገብር የሥልጣን ተፎካካሪና የዙፋን ወደረኛ ሆኖ የተቀመጠ፡፡ በነገራችን ላይ በነዚህ ጊዜያት የአፄ ምኒልክ ማኅተም “ንጉሠ ነገሥት” ይል ነበር፡፡ በተመሳሳይ መልኩም የአፄ ዮሐንስ ማኅተም “ንጉሠ ነገሥት” ይል ነበር፡፡ (ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ፣ ተክለ ፃዲቅን፣ ሀሎርድ ማክስን ያጤኗል)

በሁለቱ ወደረኞች ማሀከል የነበረውን የሥልጣን ሽኩቻ ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ በውብ ብዕሩ “አንዲቷ ኢትዮጵያ በዮሐንስና በምኒልክ ተከፍላ የሁለት ነገሥታት ሀገር ሆነች፡፡ ሁለቱም በቤገ-ምድርና በጎጃም፣ በወሎ፣ በላስታ አውራጃ ላይ የውስጥ ፍልምያ ሲያሳዩ፤ እንደዚሁም የውጪ መንግስታትን ወዳጅነት አጥብቀው በደብዳቤና በየመልክቶቻቸው አማካኝነት ይሻሙ ነበር፡፡ ሁለቱም የውጭ ሀገር መንግሥታት ወዳጅነት የሚሻሙት አጠገባቸው ባሉት ሀገር ጎብኝና ነጋዴዎች ወይም ምጥዋ በሚቀመጡት ቆሲሎቻቸው ጎን ባላንጣን አስጠልቶ ራስን ለማስወደድ ነው (አፄዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት ፤ ገፅ 57)” ሲል ይገልፀዋል፡፡

በሁለቱ ወደረኞች መሀል የነበረው የስልጣን ሽኩቻ መጋቢት 14 ቀን 1870 ዓ.ም ልቼ ላይ በምኒልክ ይቅርታ ጠያቂነት ዕርቅ ቢወርድም ተከታዮቹን አስራ አንድ ዓመታት (1871-1881) ምኒልክ የግዛት ወሰኑን ወደ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች በማስፋት የመሬት ይዞታውን (Land power) የግብር መሰብሰብ አቅሙን እና የጦር መሳሪያ ክምችት ሀይሉን በማጠናከር ስራ ተጠምዶ ነበር፡፡ ዓመታዊ ግብሩን በማስገባት ዮሐንስን የሚያዘናጋው ምኒልክ የጦር መሳሪያ ክምችቱና የሰራዊት ብዛት ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አልታየም፡፡

ጣሊያኖች በእንግሊዝ ችሮታ ምፅዋን በቁጥጥር ስር አድርገው ወደ አገር ውስጥ በሚገባ ማንኛውም አይነት እቃ ላይ ተፅኖ ሲያደርጉ አፄ ዮሐንስ የምኒልክ ከጣሊያን ጋር መቀራረብ አልወደደውም ነበር፡፡ የምኒልክ እና የጣልያኖች ወዳጅነት በውጫሌ ውል የወዲያው ግፊት (immediate cause) ሆኖ እስከተፈጠረው የአድዋ ጦርነት ጊዜ ድረስ ቆይቶል፡፡

ጣሊያኖች የወቅቱ ጠላታቸውን አፄ ዮሐንስ እንዲዳከምላቸው አፄ ምኒልክን ለማቅረብ መሞከራቸው የቀኝ ግዛት መሀንዲሶች ዘዴ ይመስላል፡፡ ይህም ሆኖ በርከት ያለ የጦር መሳሪያ ያስታጠኩትን ምኒልክ መጠርጠራቸው አልቀረም፡፡ ይህን ጉዳይ የታሪክ ጸሃፊዉ ፕሮቲ ክሪስ “Empress Taytu and Menilek II” በሚል መጽሀፉ የወቅቱ የጣሊያን መንግስት ወኪል የነበረው አንቶሎኒ በምኒልክ የበዛ መሳሪያ ክምችት ያደረበትን ስጋት ለምኒልክ አንስቶ እንደ ተማፀነው ጽፏል፡፡ ለምኒልክ፣ ለጣይቱ፣ ለራስ ዳርጌና ለአዛዥ ወልደ ፃዲቅ እንዲሁም ለሁለት አስተርጓሚዎች እንደየ ማዕረጋቸው ሥጦታዎችን ካጎረፈ በኋላ ምኒልክ ያገኘውን መሳሪያ ጣሊያኖችን ለመውጋት እንዳይጠቀምበት በክርስቲያናዊ ደንብ መሃላ ይፈፅምለት ዘንድ ተማፅኖ ነበረ (ገፅ 57-8 ይመልከቱ) የውጫሌው ውል ተደራዳሪ እና ፈራሚ የነበረው ጣሊያናዊው አንቶኖሊ እንደሚለው 1880 ዓ.ም ላይ (ከውጫሌ ውል አንድ ዓመት ቀደም ብሎ መሆኑ ልብ ይሏል) ምኒልክ  የደቡብ፣ የምዕራብ እና የምስራቅ የኢትዮያ ግዛቶችን ጨምሮ 196,000 (አንድ መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ) ሰራዊት እንደነበረው ሮቢስን “The Attempt to Establish a protectorate over Ethiopia” በሚለው መጽሃፍ (ገፅ 66) ይነግረናል፡፡

በነዚህ ጊዜያት ሁሉ አፄ ዮሐንስ በስም ደረጃ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ በሰሜን ኢትዮጵያና አካባቢው (ብቻ) የተገደብ እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር፡፡ የአፄ ዮሐንስ የንግሥና ዘመን ፍፃሜ ሦስት አመታት ሲቀረው ሚኒሊክ (የሐር ላይ ባንዴራውን ሲያውለበልብ) በግዛት ወሰን፣ በግብር ማሰሰባሰብ፣ በጦር መሳሪያ ክምችትና በዲፕሎማሲ የበላይበት አፄ ዮሐንስን ይበልጠው ነበር፡፡ የአፄው የንግሥና ዘመን እየተሸረሸረ የመጣ ለመሆኑ ምኒልክ በተለየ ሁኔታ የአስራ አንድ አመታት (1871-1881 ዓ.ም) የሥልጣን ግስጋሴ ይነግረናል፡፡ በነዚህ ጊዜያት አፄ ዮሐንስ የውጭ ኃይሎች ፍልሚያ ቢኖርበትም ምኒልክን ለማስቆም ከቶውንም አልሞከረም፡፡ ይህ ሁኔታ ከማዘንና ከርህራሄ የመጣ ሳይሆን የአካባቢው የተፈጥሮ ሀብት መመናመንና የማህበራዊ መሰረት መጥበብ ተከትሎ ከተፈጠረ የአቅም መዛል የመጣ ነበር፡፡

የዛሬዋ ኤርትራ ይህንን ስያሜ ከመያዝዋ በፊት “ባህረ ነጋሽ፣ ምድረ ሌማሴን፣ ከበሳ” በመባል ትጠራ ነበር፡፡ ኤርትራ የሚለው መጠሪያም ሆነ ፖለቲካዊ ቁመና ያገኘችው ጣልያን የቀይ ባህር ጠረፍን ታክካ ወደ አካባቢው መዝለቋ ኋላም መስፋፋቷ ከተመዘገበበት 1879 ዓ.ም ወዲህ ነው፡፡ (በተለይም የዘውዴ ረታን፤ የተከስተ ነጋሽን ሥራዎች ያጤኗል) በዚህም ጊዜ ደግሞ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ ነበር፡፡

ከ1864-1881 ዓ.ም በኢትዮጵያ ውስጥ የተደረጉ ታላላቅ ጦርነቶች (ተድአሊ፣ ኩፊት፣ ጉራዕ፣ ጉንደት {ጉንዳጉዲ}) ኢትዮጵያ በድል የተወጣችው በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግስት ነበር፡፡ ወራሪው የግብፅ ኃይል በጉንደት እና በጉራዕ ተከታታይ ሽንፈት፤ ሌላ ጊዜ አውሳ ላይ በአፋሮች እጅ ወድቆ የግብፅ ጦር አፋር በረሃ ላይ የቀረው፤ በአፄ ዮሐንስ የንግስና ጊዜ ነበር፡፡ ጣልያን የአሉላን እጅ የቀመሠበት ውርድት በሮማ ፒያሳ ቺንኮ ቼንቶ (“የአምስት መቶዎች አደባባይ”) በሚል ያስታውሰዋል፡፡ ዮሐንስ በዚህና መሠል ድሎች የታደለ ቢሆንም አገር ውስጥ “የአቻዎች አውራ” በሚል ከያዘው የንጉሠ ነገሥትነት ማዕረግ የተሻገረ በራሱ አቅም የሚቆጣጠረው መሬት ከምኒልክ አንፃር የተዳከመ ነበር፡፡ የውጭ ኃይል ላይ ያስመዘገበው ድልም የግብፅን ጦር ከመጠራረግ ውጪ የጣልያንን ጦር ከምጽዋና ከአሰብ አካባቢ ማራቅ አልቻለም ነበር፡፡ በራስ አሉላ እንግዳ (አባ ነጋ) የተመራው ጦር ዶጋሊ ላይ የጣልያንን ጦር ከመታ በኋላ ሀያ ሦስት ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ማትርቀው ምፅዋ በመሻገር የጣልያንን ጦር ያልወጋበት ሁኔታ በቀጣይ ጊዜያት ጣልያን የዶጋሊን ቁጭቷን በሰሓጢ ላይ (መጋቢት 1880) ያለምንም ወሳኝ ውጊያ ምሽግ ላይ አድፍጦ በመተኮስ የአፄ ዮሐንስ ጦር አታክቶ በመመለሱ ረገድ ተሳከቶለታል፡፡ (ባህሩ ዘውዴን፣ ተክለፃዲቅን፣ ሮሊንስንን…ያጤኗል) ለዲፕሎማሲ ሽፋን ጥለውት የወጡትን ሰሓጢን በኃይል መልሰው ያዙት ዮሐንስ እጁ ላይ የነበሩትን ድሎች መልሰው እንደጉም ይተኑበት እንደነበር የዶጋሊው ጦርነት ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ ምናልባት የዶጋሊው ድል በመቀጠል ጦሩ ወደ ምፅዋ የማዝመት ሁኔታ ቢኖር ድል ከኢትዮጵያ ጋር መሆን በቻለ ነበር፡፡

ሠላም ያልተገኘባቸው የአፄ ዮሐንስ ድሎች ኤርትራ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ለተስፋፊው የጣልያን ጦር ምቹ ጊዜ እየፈጠሩ እንደነበር ከዶጋሊ ድል በኋላ በአፄው መሪነት ሰማንያ ሺህ ጦር በማዝመት የተሞከረው የሰሓጢ ጦርነት የጣልያንን ይዞታ በማጠናከር የዮሐንስን የድል ተስፋ በማጨለም የተደመደመ መሆኑ ነው፡፡ ሰሓጢ ዮሐንስ ከጣልያኖች ጋር ለመጨረሻ ጊዜ የተያየባት የስንብት ቦታ ሆነች፡፡

ዮሐንስ እጅግ በሚያስቆጭ መልኩ መተማ ላይ ሲሰዋ፤ በምፅዋ፣ አሰብ፣ አስመራ፣ ሰሓጢና ቆላማው ክፍል ተወስኖ የነበረው የጣልያን ጦር ያለምንም ጊዜ ማባከን የደጋውን ክፍል ወረረው፡፡ (ዘውዴ ረታን፣ ተክለፃዲቅን፣ ባህሩን … ያጤኗል) ቀደም ሲል በወቅቱ የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስተር ፍራንቺስኮ ክርስቲ “ኤርትራ” በሚል የተሰየሙና አካባቢዎችና የደጋውን ክፍል ጠቅልለው ከሰሜን ኢትዮጵያ ግዛት ነጠሉት፡፡ የዮሐንስ ያልታሰበ ሞት ለምኒልክ የስልጣን በር ሲከፍት ለጣሊያን ጦር “ኤርትራ” የሚል ግዛት እንዲረከብ ዕድል ፈጠረለት፡፡ በተደጋጋሚ ጦርነት የደቀቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦር ከዮሐንስ ሞት በኋላ መበታተን ዕጣ ክፍሉ ሆነ፡፡

እስከዚህ የታሪክ ሂደት ድረስ ምኒልክ በኤርትራ ጉዳይ አንዳች የሚያገባው ነገር አልነበረም፡፡ ጣልያን በቀይ ባህር ዳርቻ የምትቆናጠጥበት ዕድልን ያገኘችው በ1862 ዓ.ም በጣልያናዊው ጂሴፔ ሳፔቶና “ሩባቲኖ” የተባለ የመርከብ ኩባንያ ጋር ተቀናጅተው ከአፋሩ ሱልጣን መሀመድ ሃሰን አሰብን ገዝተው ነው፡፡ በዚህ ጊዜ እንኳን ምኒልክ አፄ ዮሐንስም ንጉሠ ነገሥት አልሆነም፡፡ የያኔዋ ኢትዮጵያ በአፄ ተክለጊዮርጊስ ነበር የምትመራው፡፡ የኋላ ኋላ ይህ የግል ይዞታ የነበረው ወደብ ወደ ጣልያን መንግስት ሲጠቃለልም ሆነ እንግሊዝ ከአፄ ዮሐንስ ጋር አድዋ ላይ “የሂወት ውል” እየተባለ የሚጠራውን ስምምነት ስትፈራረም እና እንግሊዝ በሶስት ወራት ልዩነት ስምምነቱን አፍርሳ ነሃሴ 1876 ዓ.ም ምፅዋን ለጣሊያን ስታስረክብ ምኒልክ በደቡብ ዘመቻ እንደተጠመደ ነበር፡፡ አፄ ዮሐንስ 150 ኪ.ሜ በማይሞላ ርቀት መቀሌ  ላይ ተቀምጦ ሁኔታውን በቁጭት ያስተውል ነበር፡፡

አፍቃሪ ኢትዮጵያ የሆነው የታሪክ ጸሐፊ ሩቤንስን ከላይ በጠቀስነው መጽሃፉ እንዳለው ዮሐንስ ከእንግሊዝ ጋር ያደረገው “የሂወት ውል” አንድ ደካማ ጠላት (ግብጽ) በሁለት ጠንካራ ባላጋራዎች (የጣልያና የሱዳኑን የማሃዲ ንቅናቄ) መተካት ሆነ፡፡ በሂደት የታየውም እንግሊዝ ውሉን ወደ ጎን ገፍታ ምጽዋን ለጣልያን በመስጠት፤ ለጣልያን ወረራ በር ስትከፍት እስላማዊ ተሃድሶንና የሱዳን ብሄርተኝነትን አዳብለው ለተነሱት መሃዲስቶች ደግሞ በኢትዮጵውያንና በኢትዮጵያ ግዛት ላይ በበቀል ስሜት እንዲዘመቱ አደረጋቸው፡፡

የአፄ ዮሐንስ መካር አልቦ የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ (የኃይማኖት ፖሊሲዉን ጨምሮ) እና ህብረት ያልታየበት የመተማ ጦርነት ዘመቻ የራሱን የኢትዮጵያን አንገት አስቆረጠ፡፡ የዮሐንስ የታሪክ ሽንፈቶች ለመከላከል ታጥቀው የተነሱ የትግራይ ዘዉጌ ብሄርተኛ ልሂቃን (ህወሓታዊያንና ዮሃንሳዊያን) የኤርትራን ጉዳይ ከምኒልክ ጋር ያዛምዱቱል፡፡ ህወሓት የበረሃ ማኒፌስቶውን ሳጋና ማገር በምኒልክና በአማራ ጥላቻ ላይ በማቆም፤ ሸዋን የስተቶች ሁሉ ቋት በማድረግ ትግራይን የምሉኼ በኩልሄዎች “አገር” (ልብ አድርጉ “አገር” ነው ያልነው!!) ያደርጋታል፡፡

ድህረ – ደርግን ተከትሎ የታሪክ ቅራኔዎችን በዞረ ድምር ሂሳብ ካላወራረድኩ የሚለዉ ህወሓት፤ በምኒልክ የደቡብ እና ምስራቅ ዘመቻዎች የደረሰውን ጥቃት እያስታወሱ ዛሬም ድረስ ቁጭታቸው ያልበረደላቸውን ዘውጌ ብሄርተኞች እያስተባበሩ በምኒልክ ላይ ፖለቲካዊ እርግማን ማውረድ ሥራቸው አድርገውታል፡፡ መንግስታዊ የመዋቅር ድጋፍ ያለው ይሄው ፖለቲካዊ እርግማን ምኒልክን “ኤርትራን የሸጠ” በሚል ከአድዋ ድል ለመነጠል እስከመሞከር የደረሰ የታሪክ ኑፋቄ ስብከት አደባባዩን ተቆጣጥሮታል፡፡

በወደብ አጠቃቀም፣ በንግድና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ የሚያስተኩረውን የውጫሌን ውል ለኤርትራ መሸጥ እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡ የትግራይ ብሄርተኛ ልሂቃን የዮሐንስ “የሂወት ውል” ስምምነት በኢትዮጵያ ላይ ያስከተለውን ጉዳት ማስታወስ አይፈልጉም፡፡ ዛሬ ላይ ብርቅ የሆነው የህብረት ስሜት ትላንት በአባቶቻችን አብሮነት (ህብረት) የታየበትን የአድዋን ድል አሳንሶ በማቅረብ የመበሻሸቂያ መድረክ አድርገውታል፡፡

100ኛው የአድዋ ድል በዓል ሲከበር “ድሉ የትግራውያን እንጂ የሌሎች አይደለም” በሚል አይናቸውን በጨው አጥበው በአደባባይ ሲከራከሩ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ላይ ተገልብጠው “አድዋ ተቀጥላ ድል እንጂ ዋና ዋና ድሎች በአጼ ዮሃንስ ጊዜ የተገኙት ናቸዉ” በማለት (በዘንድሮዉ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ አድዋ ከተማ ተገኝቶ ንግግር ያደረገዉን የትግራይ ክልል ኃላፊ አባይ ወልዱን የንግግር ይዘት ያስታዉሷል) ከታሪክ ጋር መላተማቸዉን ቀጥለዋል፡፡ በአጼ ዮሃንስ የንግስና ጊዜ የተገኙ ድሎችን ከፍ አድርጎ ለማድረግ በምኒልክ መሪነት የተገኘዉን የአድዋን ድል ማሳነስ ምን የሚሉት የታሪክ ድህነት ነዉ? በመሀል ቤት በተለያዩ አመታት በሁሉም አዉደ ዉጊያዎች ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ህይወታቸዉ ያለፈ አባቶች ተረስተዋል፡፡ ሥም አልባ ጀግኖች አስታዋሽ የላቸዉም፡፡ ታሪክን በዜግነት ማዕቀፍ ሳይሆን በዘዉግ መነጽር ማየት የሚቀላቸዉ የህወሓት ሰዎች፤ ጊዜና ሁኔታዎች ፈቅደዉ የአድዋ ድል በአጼ ዮሃንስ መሪነት የተገኘ ቢሆን (ኑሮ) ይሄኔ ድሉ በአፍሪካ ደረጃ እንዲከበር የኢትዮጵያን ህዝብ ካዝና ከማራገፍ አልፎ ለክፉ ቀን ያስቀመጡትን የግዙፉን ኤፈርት ትልቅ በጀት ይዞ ለድል መታሰቢያዉ በድምቀት መከበር እንዲቀሳቀስ ባደረጉ ነበር፡፡

ምኒልክ ላይ ፖለቲካዊ እርግማን ማዉረድ የዮሃንስን የታሪክ ሽንፈቶች የሚያጠፋ ይመስል፤ ትዉልድና የታሪክ ትርጓሜ በተሳሳተ አቅጣጫ እንዲፈስ ማድረጉን ተያይዘዉታል፡፡ ይህ የኑፋቄ መንገድ የነገዋን ኢትዮጵያ በተለይም ትግራዋያንን በመነጠል የሚጎዳ እንጂ ምኒልክን የሚያረክስ አይደለም፡፡ ምኒልክ በስጋ ቢሞትም ኢትዮጵያ እስካልተበተነች ድረስ በመንፈስ ይኖራል፡፡ የምኒልክን የአንድነት ስሜት ጊዜና ወቅቱ በሚጠይቀዉ ማህበራዊ ዕድገት መሰረት በመግራት ኢትዮጵያን ወደከፍታዋ ለማዉጣት አቅሙም ፍላጎቱም የሌላቸዉ የህወሓት ሰዎች፤ ከሙት ሥርዓት ጋር ራሳቸዉን እያላተሙ በምኒልክና በዘመኑ ጀግኖች ተጋድሎ የቆመችዉን ኢትዮጵያ መበዝበዛቸዉን ተያይዘዉታል፡፡ የነገሩ ምጸትም ይሄዉ ነዉ፡፡ ምኒልክን እየረገሙ በረከቱን ለብቻ መብላት፡፡

ዶ/ር ዘዉዴ ገብረ ሥላሴ ኦክስፎርድ ዮኒቨርስቲ ባሳተመለት “Yohannes IV of Ethiopia; A political Biography” በሚል ሥራዉ፤ በ1879 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ አጼ ዮሃንስ ለምኒልክ በጻፈለት ደብዳቤ “… በእግዚአብሔር ቸርነት ጣሊያኖች ተዋርደዉና ተንቀዉ ይመለሳሉ” (ገጽ፤199 ላይ ይመልከቱ) ብሎት ነበር፡፡ አጼ ዮሃንስ በርግጥ ስለ ጣልያኖች በዓለም ፊት መዋረድና መሸነፍ በትንበያ መልክ የጻፈዉ ደብዳቤ ልክ ነበር፡፡ አጼዉ ባያሳካዉ እንኳ አባ ዳኘዉ መሪነት በዘመኑ የወንድ የሴት አርበኞች ብርታትና  የተዋጣለት ቅንጅት ጣሊያንን ድል መንሳት ተችሏል፡፡ በትግረኛ ቋንቋ “ኢይጥዕሞ መዓር…” እንዲሉ የትግራይ ብሄርተኛ ልሂቃን በተለይም የህወሓት ሰዎች፤ የምኒልክና የዘመኑ ጀግኖች ድል አይጥማቸዉም፡፡ ነገሩ ጣማቸዉም አልጣማቸዉም ምኒልክ ከነሰብዓዊ ድክመቱ ዓምዳ ዉዳድ ለኢትዮጵያ (ለኢትዮጵያ መሰረትና ምሰሶ) ነዉ!!

ለመሆኑ አጼ ዮሃንስ ከምኒልክ የተሻለ መሪ ነበር? ታሪኩ ይህን አያረጋግጥም፡፡ የአጼ ዮሃንስ ለባዕድ ሥርዓት (ለእንግሊዝ) የማደግድግ ነገር ብዙ የተባለለት ጉዳይ ነውና ይህን አንዘረዝርም፡፡ ከ1870-1875 ዓ.ም ድረስ በነበሩ ዓመታት አጼ ዮሃንስ በትግራይ፣ በወሎ፣ በዋጅራቱ፣ በራያና አዘቦ የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች በሙሉ በግድ ኦርቶዶክስ ክርስትናን እንዲከቀበሉ “ሰማይ ዓምድ የለዉ፤ እስላም ሀገር የለዉ” የሚል አዋጅ አወጀ፡፡አዋጁ ግልጽ ነዉ፡፡ ክርስትናን ያልተቀበለ የመሬት ባለቤት ሊሆን አይገባም፤ በያኔዋ የኢትዮጵያ ግዛት ዉስጥም መኖር አይችልም ለማለት ነዉ፡፡ ቀሳዉስትን ከጦር ሠራዊቱ ጋር ይዞ የዘመተዉ አጼ ዮሃንስ፤ በጊዜዉ ያደረሰዉን አጠቃላይ ክስተት በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተ መጽሐፍት ኤጀንሲ የሚገኘዉ “ታሪከ ነገሥት” እንዲህ ይተርክልናል “መከራዉን የፈሩ እስላሞች በልባቸዉ ሳያምኑ ባፋቸዉ ብቻ ‹አምነናል› እያሉ ተጠመቁ፡፡  ሥጋ ወደሙ ከተቀበሉ በኋላ በስዉር ካፋቸዉ እያወጡ እስከ መጣል ደረሱ፡፡ መከራዉን ያልፈሩት እስላሞች ግን ‹ክርስቲያን ከመሆን ሞት ይሻለናል› እያሉ እኩሉ በሞተ፣ እኩሉም በእስራት፣ እኩሉም በመወረስ፣ እኩሉም ካገር እየወጡ በመሰደድ ተቀጡ (ታሪከ ነገሥት፤ገጽ 75 ላይ ይመልከቱ)”፡፡

ከዚህ የማይፋቅ የታሪክ ማስረጃ እንደምንረዳዉ አጼ ዮሃንስ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ የከፋ ቅጣት ማድረሱን ነዉ፡፡ የአጼዉ የኃይማኖት ፖሊሲ ጸረ-እስልምና እንደነበር ለንግስት ቪክቶሪያ በላከላት ደብዳቤ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል “ባገሬ አዘቦ የሚባል የኦሮሞ እስላም አገር አለ፡፡ ከርሱ ሽፍታ ተነሳብኝ፡፡ እርሱን ለማጥፋት ዘመትሁ፡፡እርሱንም በእግዚአብሔር ኃይል አጠፋሁት” ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ በተፈራረቁ ነገስታት እንደተበደሉ የማይካድ እዉነታ ነዉ፡፡ የአጼ ዮሃንስን ያህል ያስጨነቃቸዉ ንጉሥ ግን ከቶዉንም ያለ አይመስልም፡፡ በሀበሻ ምድር ሙስሊሞችን ብቻ እየለየ እንዲያሳድድ ተፈቶ የተለቀቀ እብድ ዉሻ ይመስል የወሎ ሙስሊሞችን እንዲህ አራቆቷቸዋል “(አጼ ዮሃንስ) አልጠመቅም ያለዉን እስላም ወሎ ከረሙ፡፡ ከእስላም ወገን በኃይማኖቱ የጸናዉና ጉልበት ያለዉ ወደ መተማ እየተሰደደ ከድርቡሽ ጋር ተደባለቀ፡፡ እኩሉም ወደ ሐረርና ቀቤና፣ ወደ ጅማ ተሰደደ፡፡ በዚሁም ምክንያት በያዉራጃዉ ሁሉ ሽፍታ ብቻ ሆነ፡፡ በየጅረቱም ሁሉ መጋደልና የሰዉ ደም መፍሰስ ሆነ (ታሪከ ነገሥት፤ ገጽ 60)”፡፡

የአጼ ዮሃንስ የከረረ የኃይማኖት ፖሊሲ መነሻዉ ግልጽ ይመስላል፡፡ የአጼዉ መሰረት ትግራይ ነዉ፡፡ በትግራይ ዉስን የሠራዊት ኃይል የጊዜዋን ኢትዮጵያ ማስከበር የሚታሰብ አይደለም፡፡ ወዲህም ለአጼ ቴዎድሮስ የዉድቀት መፋጠን የካህናቱ እጅ እንዳለበት ተረድቷል፤ ኃይማኖታዊ ፖሊሲዉን ተከትሎ ከአዉሮፓ መንግሥታት የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደሚያገኝ አስቦ ነበር፡፡ (ለንግስት ቪክቶሪያና ለንጉሥ ዊልያም አራተኛ እንዲሁም ለፈረንሳይ መንግስት የላከቸውን የደብዳቤ ይዘቶች ያጤኗል) በዉጤቱ ግን ዛሬም ድረስ በዞረ ድምር የታሪክ ቅራኔ ቁስል ያልሻረ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ቂምና መሃዲስቶችን በተቀላቀሉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች ትብብር መተማ ላይ በተካሄደዉ ጦርነት የንጉሠ ነገሥትነት ዘመኑን አሳጠረ፡፡ አልፎ ተርፎም የጎንደርና አካባቢዉ ህዝብና ታሪካዊ ቅርሶች ወደሙ፡፡

አጼ ዮሃንስ የጎጃሙን ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ከምኒልክ ጋር አደመብኝ በሚል ለራሱ እንኳን ኋላ ላይ ሲያስበዉ የዘገነነዉን እልቂት በጎጃም ገበሬዎች ላይ ፈጽሟል፡፡ አጼ ዮሃንስ የቅጣት ሰይፉን መዞ ፊቱን ወደ ጎጃም ሲያዞር የጎጃም ገበሬዎች፡-

“በላይኛዉ ጌታ በባልንጀራዎ

በቅዱስ ሚካኤል በባልንጀራዎ

በጽላተ ሙሴ በነጭ አበዛዎ

ጎጃምን ይማሩት ፈሪም አንልዎ”

የሚል ተማጽኖ ቢያሰሙም ከመዐቱ አልተረፉም፡፡ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ “አጤ ምኒልክ” በሚለዉ መጽሃፉ “የትግሬ ወታደር ቄሱን ተበተስኪያን፣ ገበሬዉን ከዱሩ፣ ነጋዴዉን ተመደብሩ እያወጣ ጨረሰዉ (ገጽ፣ 54)”፤ “ጎጃምን የመሰለ ደግ አገርም ሦስት ወር ሙሉ በትግሬ አንበጣ ተደመደመ” (ገጽ፣52) በሚል በወቅቱ የደረሰዉን እልቂትና ዉድመት ይገልጸዋል፡፡ አጼ ዮሃንስ ለራስ ዳርጌ በጻፈዉ ደብዳቤ “በእኔም በድሃዉም ኃጢአት እንደሆን አይታወቅም አገሩን (ጎጃምን) ሳጠፋ ከረምሁ” (ኀሩይ ወልደ ሥላሴ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከሳባ እስከ ታላቁ የአድዋ ድል፤ ገጽ 179 ይመልከቱ) በማለት ጸጸቱን ይገልጻል፡፡

በኢትዮጵያ የነገሥታት ታሪክ በተለይም በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ሂደት ወስጥ ብዙ ሰብዓዊ ጥፋት እንደደረሰ መካድ አይቻልም፡፡ ነገሥታቱ ከሰብዓዊነት አኳያ “አለማወቅ” የሚባል ሰብዓዊ ጉድለት እንደነበረባቸዉ “ፍትሐ ነገስት”ን በማስታወስ መረዳት አይከብድም፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ የነገሥታቱ ሠራዊት ይህ ነዉ የሚባል ቋሚ ደመወዝ የሌለዉ በመሆኑ ዘመቻ በወጡ ቁጥር ቅጥ ካጣ ጭካኔቸዉ ጋር የገበሬዉን ንብረት መዝረፍና ማዉደም የሰርክ ተግባራቸዉ ነበር፡፡ በዚህ መሰል አሰቃቂ ሂደት የተጨፈለቁ የማህበረሰብ ክፍሎች፤ ጉዳት የደረሰባቸዉ ወገኖች መኖራቸዉ እሙን ነዉ፡፡ እንደዚህ ባሉ ዘመቻዎች የቀደሙትን ነገሥታት ገትተን የዘመናዊት ኢትዮጵያ መስራትች አባቶች የሆኑት የቴዎድሮስ፣ የዮሃንስ እና የምኒልክ ሠራዊት በተፈራራቂነት በገባራቸዉ ላይ ጥፋት አድርሰዋል፡፡ በጊዜ ሂደት መጠኑ እየቀነሰ ቢሄድም ገባሮቹ በባርነት ተፈንግለዋል፡፡ መሬታቸዉንም ተነጥቀዋል፡፡ ባህላዊና ሰብዓዊ ክብራቸዉ የተረገጡም አሉ፡፡ ትልቁ ቁም ነገር የዚህን ሁሉ ግፍ መደባዊ ይዘት መረዳቱ ላይ ነዉ፡፡

ታሪክን ገልብጦ ማንበብ የሚቀላቸዉ የህወሓት ሰዎች በዘመናዊት ኢትዮጵያ ዉስጥ የአገር ምስረታ ሂደት ዉስጥ የደረሱ ጥፋቶችን ከአንድ ቋንቋ ተናጋሪ በዳይነት (አማራ) ጋር ብቻ ለማያያዝና ቂምን ወደ ትዉልድ ለማሻገር ሥርዓተ-ትምህርት ከመቀየር ሐዉልት እስከ መስራት ድረስ የዘለቀ እኩይ ድርጊት ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዉጤቱም አገራዊ የጋራ ማንነቶችን (የጋራ ጸጋና መከራዎቻችን፤ ድልና ሽንፈቶቻችን) እየጠፉ አካባቢያዊ ማንነት አለቅጥ ተወጥሯል፡፡ እንዲህ ያለዉ አዝማሚያ መጨረሻዉ አገር በመበተን የሚቆም ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንስ ሁኔታችን ለርስ በርስ ጦርነት የቀረበ ሆኗል፡፡

በአገራችን የፖለቲካ ባህል በአሳዛኝ መልኩ እየበረታ የመጣ ክፉ በሽታ አለ፡፡ እርሱም ኃላፊነት መዉሰድ አለመቻል፡፡ ይህ ክፉ ልማድ ከ1960ዎቹ ትዉልድ የጀመረ ቢሆንም በድህረ-ደርግ በአደባባይ ዘዉጋዊ ልባስ አግኝቶ ማንነትን የታከከ ታሪክ ትርጓሜ ተንተርሶ አገሪቷን ወደ ብተናና እልቂት እየገፋት ይገኛል፡፡ ይህ ጉዳይ ዛሬ ላይ ከቁጥጥራቸዉ ቢወጣም የህወሓት ሰዎች በተጠና መልኩ ሲተገብሩት የኖሩት ጉዳይ ነዉ፡፡

ለህወሓት ሰዎች ታሪክ ትምህርት ሳይሆን ፍርድ ቤት ነዉ፤ አንዱን ንጉሥ ኮንነዉ ሌላዉን የሚያጸድቁበት፡፡ ከሦስት አመት በፊት የአጼ ምኒልክ 100ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ ቀን የትኛዉም ዩኒቨርስቲም ሆነ እንደ ባህልና ቱሪዝም ያሉ መንግስታዊ ተቋማት በአገር አቀፍ ደረጃ ሳያከብሩት አልፏል፡፡ አሳፋሪዉ ነገር “የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር”ም የገዥዎችን ቁጣ ፈርቶ ዝምታን መርጦ ማለፉ ነበር፡፡ በጊዜዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን (እንደ ሥርዓቷ) ሰማያዊ ፓርቲ በየግላቸዉ አቅማቸዉ በፈቀደ መጠን አክብረዉት ነበር፡፡ በአንጻሩ መጋቢት 2/2009ዓ.ም የትግራይ ክልል ደራሲያን ማህበርና መቀሌ ዩኒቨርስቲ በመተባበር የአጼ ዮሃንስን 128ኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ በደመቀ መልኩ አክብረዉታል፡፡ ዮሃንስ ከነሰብዓዊ ጉድለቶቹ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበር፡፡ በተለያዩ አዉደ ዉጊያዎች ከዉጭ ወራሪ ኃይሎች ጋር በጀግንነት ተፋልሟል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ደንበር ላይ የተዋደቀ ብቸኛዉ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነዉ!! በዚህና መሰል ጉዳዮች ታሪክ ከነድል-ሽንፈቶቹ ሲያሥታዉሰዉ ይኖራል፡፡ጥያቄው ለዮሃንስ የተሰጠዉ ክብር ለምኒልክ ሲሆን ለምን ይነፈጋል? የህወሓትና አክራሪ የትግራይ ብሄርተኞች ዮሐንስ የፈጸመዉን ሰብዓዊ ጥፋት ወደ ጎን ትተዉ በታሪክ ፍርዳቸዉ ነጻ ሊያወጡ ሲሞክሩ፤ ስለ ምኒልክ ለምን የብዜትና ፈጠራ ታሪኮችን በፖለቲካ ርግማን መልኩ ሲያዘንቡ ይታያል? ዮሃንስ በፈጸመዉ ጭፍጨፋ ታሪክ ነጻ ካወጣዉ ምኒልክንስ ታሪክ ስለምን ይኮንነዋል?

ለዚህ ነዉ ለህወሓት ሰዎች ታሪክ ትምህርት ሳይሆን ፍርድ ቤት ነዉ የምንለዉ፡፡ ዮሃንስን ከፍ አድርጎ ምኒልክ ላይ የፖለቲካ ርግማን የሚያወርድ የመቀሌ ችሎት!! በመስመር መሀል የትግራይ የአካዳሚያ ልሂቃን፣ ህዝባዊ የታሪክ ጸሃፍት፤ የ“አረና ፓርቲ አመራሮች” እና ብዙሃኑ የትግራይ ወጣቶች የመቀሌዉ የታሪክ ፍርድ ችሎት አጨብጫቢዎች መሆናቸዉን ስንታዘብ አድዋን የሚያህል ወታደራዊ ድል ስለምን ወደ ፖለቲካዊ ድል መቀየር እንደተሳነን ይገለጽልናል፡፡

የከረረ ዘዉጌ ብሄርተኝነት የክፉ ዉሾች ጉሮኖ ነዉ፡፡ ከታሪክ ዝንባሌ የመነጨ ሲሆን ደግሞ የአሳሞች ጋጥ ይሆናል (የጆርጅ ኦርዌል፤ Animal farm ላይ ያሉትን አሳማዎች ያስታዉሷል) አገራዊ ጅግኖቻችን እያወረድን ዘዉጋዊ ጀግና ማድረጋችንን ከቀጠልን የአድዋ ድል መንፈስ ፍጹም እየራቀን እንጅ እየቀረበን ሊመጣ አይችልም!!

(በቀጣይ ዕትማችን ከአድዋ ድል በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ ከአዲሱ የአማራ ዘዉጌ ብሄርተኛ ቡድን ላይ የታዘብናቸዉን እና የጽሁፉን ማጠቃለያ እናቀርባለን)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ረጲ (ቆሼ) ላይ የደረሰው አደጋ በአ.አ ከተማ መስተዳደር የተፈፀመ ጭፍጨፋ መሆኑን የሚያረጋግጡ 10 ምክንያቶች

$
0
0

ከስዩም ተሾመ

1ኛ) ቆሼ የአገልግሎት ዘመኑ ሊጠናቀቀ ስለሆነ ከከተማው መስተዳደሩ የመሬት ይዞታ ውጪ ኦሮሚያ ውስጥ 37ኪ.ሜ ገብተህ #ሰንዳፋ ላይ ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ ለመገንባት ታቅዳለህ፣

2ኛ) የሰንዳፋውን ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ ለመገንባት ከሚያስፈልገው 1ቢሊዮን ውስጥ አብዛኛውን  ከፈረንሳይ በብድርና እርዳታ ታገኛለህ፣

3ኛ) ለግንባታው በወጣው ጨረታ መጀመሪያ ላይ የፈረንሳይ ድረጅት ይቀርባል፡፡ በ2ኛ ዙር ለይምሰል 6 ድረጅቶች ተጫረቱ ካልክ በኋላ ያው  የፈረንሳይ_ድርጅት እንዲያሸንፍ ታደርጋለህ፣

4ኛ) ሌላ የፈረንሳይ ድርጅትን የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ ታደርጋለህ፡፡

5ኛ) በሰንዳፋ አከባቢ ከሚኖሩ አርሶ-አደሮች  41ሚሊዮን ብር በጀት ይዘህ በኋላ ላይ 16ሚሊዮኑን የት እንደገባ ሳይታወቅ ለካሣ የተመደበው  25ሚ.ብር ብቻ ነው ትላለህ፡፡

6ኛ) ከመሬታቸው ለሚፈናቀሉ አርሶ አደሮች የአውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው በሚል ማባበያ 137ሄክታር መሬት 18ብር በካ.ሜ እየከፈልክ ታስነሳለህ፡፡

7ኛ) ገና ሥራው ሳይጀመር ብሩን ቀርጠፈህ ከበላህ በኋላ በተረፈችው የሽቦ_አጥር ታጥርና “ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ ገነባሁ” ብለህ ትጠርቃለህ፣

8ኛ) ከላይ 1-7 በተጠቀሰው መሠረት፦ በሕገወጥ መንገድ፥ በተጭበረበረ ጨረታ፥ ያለ በቂ ካሣ፣…ለይስሙላ ያጠርከው የሽቦ_አጥር ቆሻሻው በአከባቢውና በህዝቡ ጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት መከላከል አልቻለም፡፡

9ኛ) የሰንዳፋ አከባቢ ነዋሪ ከአ.አ የሚወጣው ቆሻሻ በጤናማ አከባቢ የመኖር መብታችን ይከበር ብሎ ቆሻሻ እንዳይደፋ መንገድ ዘጋ፡፡

10ኛ) ከላይ 1-9 በተጠቀሰው መሠረት፦ የአገልግሎት ዘመኑን በጨረሰና “ዳግም ላይከፈት ተዘግቷል” ወደተባለው የረጲ (ቆሼ) የቆሻሻ ማስወገጃን ትመለሳለህ፡፡፡…በዚህ መልኩ በንዝህላልነትና በሌብነት የሰው_ልጅን በቆሻሻ አፍነህ ትፈጃለህ!!

ሰበር ዜና! ህዝብ ይወቀው! ይሰራጭ!- ብአዴን ወልቃይቴወችን ሰብስቦ ትግሬ ነን በሉ እያለ ነው! – አስናቀው አበበ

$
0
0

ዛሬ ባህርዳር ላይ የወያኔ ተላላኪው የብአዴን አሻንጉሊት የክልሉ ምክርቤት በወልቃይት ጉዳይ ላይ ይወያያል። ከመደበኛ ስብሰባው በፊት ቋሚ ኮሜቴወችን እና ቄሶችን የማሳመን ስራ እየተሠራ ነው። የአማራን ህዝብ ባዶ እግር የሚሄድ እያለ የሚዘባበትበት ድንች እራስ አለምነው የማሳመን ብቃት ያላቸውን ሰወች ለይቶ በዝግ ስብሰባ ለማሳመን እየሞከረ ሲሆን ሳሞራ እና ቅጥቅጡ የወያኔ የአየር ሀይል ሀላፊ ሞላ ከቦታው እንደታዩ ታውቋል።
ተያይዞልዘው የመጡ ፎቶወች ቢኖሩም ለጊዜው እኒህን ብቻ አውጥተናል። የወልቃይት ጥያቄ የሚመለሰው ወደታሪካዊ ቦታውና ማንነቱ ሲመለስ ነው። ያም የሚሆነው በወያኔ መቃብር ላይ ነው። በስብሰባው ላይ የተገኙ ወልቃይቴወች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ይድረሳቸው። የህዝቡን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ተግባር ላይ እንዳይሰማሩ። ለጥንቃቄ ዝርዝር ማንነታቸው እጃችን ገብቷል!
ህዝብ ያሸንፋል©!

ሰበር ዜና!…..ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ከእስርቤት ዛሬ ተፈታ

$
0
0

ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ እንኳን ተፈታህ ።በጣም ደስ ብሎናል።ያለምክንያት አሰሩህ ያለምክንያት ፈቱህ።
ይሄ የወያኔ ድራማ ድሮም የተለመደ ነው
ነገር ግን በወገኖቻችን የደረሰውን እልቂት ትኩረት ለማስቀየስ የሚደረገው ከንቱ ሙከራ የትም አያደርስም።
በሁለት ስሜቶች ተሞልተን አሁንም የሚብሰውን አጀንዳ ለአለም እናሳውቃለን።ተቃውሟችንን እና ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

Yoseph Yitna

ከቆሼ መደርመስ አደጋ ስር ለ3 ቀን ተቀብራ የቆየችው ሴት በሕይወት የተረፈችበት አስደናቂ ክስተት በመሴ ሪዞርት

$
0
0

ከቆሼ መደርመስ አደጋ ስር ለ3 ቀን ተቀብራ የቆየችው ሴት በሕይወት የተረፈችበት አስደናቂ ክስተት በመሴ ሪዞርት

ወያኔ ዘመነ ምህረትን ለመያዝ ከፍተኛ ገንዘብ መመደቡ ታወቀ (በለገሠ ወ/ሃና _ የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ም/ኃላፊ)

$
0
0
ሸንቁጥ አየለ

ዘመነ ምህረት

በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራዉ እና የህጋዊዉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) ም/ል ፕሬዝደንት አቶ ዘመነ ምህረት ለአንድ ዓመት ከ4 ወር ታስሮ በ10.000 ዋስ ከእስር እንደተፈታ ይታወቃል:: በውጭ ሆኖ የፍርድ ቤቱን ጉዳይ እየተከታተለ በነበረበት ጊዜ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ለመግደል ተልዕኮ የተሰጣት ሴት በዝግጅት ላይ እንዳለች በቤተሰብ ብርታት መክሸፉም ይታወቃል:: የመግደል ሙከራ የተደረገበት አቶ ዘመነ ምህረትን ለመያዝ በአሁኑ ወቅት ወያኔ በመቶ ሽህ የሚቆጠር ገንዘብ መመደቡ ታውቋል ፡፡

በዋናነት ይህ ተልኮ የተሰጣቸው የደህንነት አባል የሆነው መኮንን አለባቸው እና ጓደኛው አለማየሁ አማረ ትክክለኛው የአባቱ ስም ናሁሰናይ የተባለ የትግራይ ሰዉ ገንዘቡን ተቀብለዋል::
እነዚህ ሰዎች ከዘመነ ጋር የስጋ ዝምድና ያላቸውን
1ኛ. አሰፋ ሙላትን የዘመ የአጎት ልጅ በበረከት ስምዖን የሰለጠነ አርማጭሆ የነበረ አሁን ጎንደር የሚኖር
2ኛ. በለጠ ጋሼ የዘመነን የአጎት ልጅ ያገባ እና የHIV ታማሚ የሆነ ሰዉ
3ኛ. አስምሮ አንባው የተባለዉን እና የዘመነን የአክስት ልጅ ያገባዉን ሰዉ ነው::

እነዚህ በመኮነን አለባቸው እና በአለማየሁ አማረ የተመለመሉ ሰዎች ናቸው:: ዘመነ ያለበትን ካገኙም ህይወታቸውን እንደሚቀይሩላቸው ቃል ገብተውላቸዋል ::ለጊዜውም በርካታ ገንዘብ ተሰጥቷቸዋል:: እነዚህ ይሁዳዎች ዘመነን በማፈላለግ ላይ እንደሚገኙ አውቀናል:: መኮንን እና አለማየሁ የተባሉት ሁለት ሰዎች በርካታ ሰዎችን ያሳፈኑ ነፍሰ በላዎች መሆናቸውን የጎንደር ሰው ሁሉ ያውቀዋል:: በቅርቡ እንኳን የአረጋን / ቴዎድሮስ /የአክስት ልጅ የሆነውን ፍቅሬ ግርማይን አብረው እየበሉ አብረው እየጠጡ አሳፍነውታል:: እስካሁንም ያለበት አይታወቅም:: ፍቅሬ ግርማይ ማክሰኝት ከተማ ላይ የታወቀ ስጋ ቤት የነበረዉ ነጋዴ ነበረ ፡፡

በውይይት እና በድርድር ለውጥ እናመጣለን ለምትሉም ከሃዲዎቹ እነ ልደቱ: አበባዉ መሃሪ: ዶ/ር በዛብህ ወያኔ በድርድር እንደማያምን እየነገራችሁ ነው ፡፡
ወያኔ በአንድ እጁ ይቃወሙኛል ያላቸውን ሰዎች ለማያያዝ እና ለመግደል ብዙ ብርይመድባል:: በሌላኛው እጁ ደግሞ እንደራደር እንወያይ እያለ የማስመሰል የጥሪ ወረቀት ይበትናል ፡፡ የሚያሳዝነዉ ደግሞ እንደራደር እና እንወያይ እያለ የሚያቀርባቸዉ እና የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ያደረጋቸዉ እራሱ በአንድ እጁ ጠፍጥፎ የሰራቸዉን እነ አበባዉ መሃሪ: ዶ/ር በዛብህ” ልደቱ አያሌዉ እና ትዕግስቱ አወልን የመሳሰሉ ከሃዲያን ግለሰቦች መሆኑ ነዉ:: የኢትዮጵያ ህዝብ እያንዳንዱን ነገር እንደሚከታተል ግን ከሃዲያን እና እነዚህን ከሃዲያን ደግፋችሁ የቆማችሁ ወገኖች ሁሉ ልብ በሉ::

አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ባሰብሽ – ታዛቢው

$
0
0

እንደሚታወቀው በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በጎንደርና በጎጃም አሁን በሀገራችን ላይ ያንሰራፋውን የትግራይ ነፃ አውጪ ወይንም ወያኔን ፣ አማራው ነፍጥ አንስቶ እየተፋለመው እንደሆነ ይታወቃል ። ይህ የህብረተሰቡ ክፍል መሳሪያ አንስቶ ከወያኔ ጋር በትንቅንቅ ላይ ያለውና አሁን የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ያስቻለው ወይንም ያስገደደው የህልውናው ጉዳይ እንደሆነ ግልፅ ነው ። የአማራው ሕዝብ በዘር ወይንም በጎሳ መደራጀትን አጥብቆ የሚቃወም ብቻ ሳይሆን የሚጠላውም ፣ የሚፀየፈውም ጭምር በመሆኑ ይህ በጠባብነት መደራጀትን መጥላቱ ላለፉት 25 ዓመታት ክፉኛ እንዲጠቃ አድርጎታል ። በሐገራችን ያሉ ብሄር ብሄረሰቦች ሁሉም ወያኔ ባመቻቸላቸው መድረክ በመጠቀም እንደ አንድ ሕዝብ ከማሰብ ይልቅ አገርን ባሳነሰና እጅግ ዝቅ ባለና ባኮሰሰ ፣ ጠባብነትን ዋና መርሆ ባደረገና ባነገበ አስተሳሰብ አገር እንደ አገርነት መቀጠል እንዳትችል በሚያመቻች ስንኩል አላማ ተሰባስበው እንደ ፈጣሪያቸው ወያኔ ሁሉም አማራውን የጋራ ጠላት በማድረግ በአማራው ላይ የተነሱና ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያ የሚል ስም መስማት የማይፈልጉ ፣ የመጨረሻ ግባቸውም መገንጠል ወይንም መገነጣጠል የሆኑ ሲሆን ፣ አማራው ግን የለም አሻፈረኝ በብሄር ፣ በዘር ፣ በጎጥ አልደራጅም በማለቱ የሁሉም በትር ተሸካሚ ሆኖ እንዲቆይ ተገዷል ።

ይህ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ማለቱና የመንደርና የጎጥ አደረጃጀትን መቃወሙ በራሱ እንደወንጀል ስለተቆጠረበት ለዘመናት ከኖረበት ስፍራ ባለፉት  25 ዓመታት ከኖረበት ፣ ከወለደበት ፣ ከከበደበት ቀዬው በግድ ሲያፈናቅሉት ፣ ቤት ንብረቱን ሲዘርፉትና ሲያጋዩት ፣ አልፈው ተርፈው ያለ ርህራሄ አዛውንት አባቶችን ፣ ሴት እናቶችን ፣ ህጻናትን በግፍ ሲገድሉበትና ሲያሳድዱት ይህን ሁሉ በደልና ስቃይ በመታገስ ሁሉም ያልፋል ፣ ዛሬም ነገም ለዘለዓለም አንድ ኢትዮጵያ ፣ አንድ ህዝብ በማለት በአማራነቱ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቱ መደራጀትን በመምረጡ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ በደልና ሰቆቃን በሚያስገርም ጥንካሬ ሲያስተናግድ ኖሯል ።

ስልጣን ላይ ባለው ወያኔ አይዞህ ባይነትና አጋዥነት አሌ የማይባል ግፍና በደልን ግተውታል ። በተጨማሪም በወያኔዎች (Systematic) በሆነ መልኩ የአማራውን የመጠጥ ውሃ  በመበከል ብዙዎች የብክለቱ ታማሚና ከፍ ሲልም በዚያ ሳቢያ ህይወታቸውን እንዲያጡ ሲያደርግ ፣ ሴቶችንም መውለድ እንዳይችሉ  የሚያመክን መርፌ በመውጋት ባሰቃቂ ሁኔታ ያልተማረውን ወገን በማታለል የስውር የዘር ማጥፋት ዘመቻ ያካሄዱበት ሲሆን በተጨማሪም በሰበብ አስባቡ ያካባቢውን ህዝብ በውሃ ቀጠነ ሲገድሉና ሲረሽኑ በመኖራቸው የተነሳ እራሱ የወያኔ ፓርላማ ተብዬ ባመነው አሃዝ እንኳን 2.5 ሚሊዮን አማራ እንዳጠፉ ወይንም እንደበሉት አምነዋል ። እንዲያውም ባንዳንድ ግምቶች ይህ ቁጥር ወደ 5 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይነገራል ።

እንግዲህ አማራው ይህን ሁሉ ግፍና በደል በትእግስት ለ25 ዓመታት ካስተናገደ በኋላ ዛሬ በአማራነቱ ቢደራጅ ያ የአማራውን ሕዝብ አመለካከት ከኢትዮጵያዊነት አመለካከት ዝቅ ያረገዋል ማለት አይደለም ። የህልውና ጉዳይ እንጂ ። አንድ ሰው ጅብ የሱንም የጓደኞቹንም እግር መቆርጠም ቢጀምር የለም መጀመሪያ የጓዶቼን እግር ላድን አይልም ፣ መቼም ይህ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው ፣ እየሞተ ያለ ሰው እየሞቱ ያሉትን ላድን የሚል አልታይቶም ፣ አልተሰምቶም ። ያማ ቢሆን ኖሮ አማራው በሚሞትበት ሰዓት ፣ የአማራው ገፈት ተቋዳሽ ባይሆኑም እንኳን እንዲሁ በሰበብአዊነት ብቻ ሊጮሁለት በተገባ ነበር ። ያ ግን አልሆነም ይልቁንም እነሱ ጮማ እየቆረጡ ውስኪ ሲጎነጩ ነው የተስተዋለው ። ዛሬ ግን አማራው ቆርጦ መነሳቱን ሲያዩና ሲመለከቱ ሁሉም አፋቸውን ሳያሙዋሹ ለማሞጥሞጥ ሲቻኮሉ ይታያል ። ለመሆኑ ስለ አማራው ሰቆቃ ማን ጮኸለት? እራስን ዞር ብሎ መመርመርም ይገባል እኮ አንዳንዴም ።

ለዘመናት ኢትዮጵያ እያለ መጮሁ ሰሚ ጆሮ አጥቶ ዛሬ የራሱን ህልውና ስለተፈታተነው ጨርሼማ አልጠፋም ማለቱ ወንጀል ሆኖ ሊቆጠርበት አይገባም ። “ብልጦች የማይሄዱበትን መንገድ ፣ ሞኞች ይሩጡበት ማለት” አግባብ አይሆንም ። ዛሬ አማራው በአማራነቱ መደራጀቱና ለህልውናው የሚያደርገው ተጋድሎ ያሳሰባቸው ወያኔን ጨምሮ ሁሉም በጎጥና በመንደር ተሰባስበው ለ25 ዓመታት አማራውን ሲያሳድዱና ሲያፈናቅሉ ፣ ሲገድሉ የነበሩ  ናቸው ። እራሳቸው በመንደር መደራጀታቸው ሳያንስ እራሳቸውን ፣ የከሌ ነፃ አውጪ ፣ የማንትስየው ነፃ አውጪ ብለው የተሰባሰቡ መሆናቸው እየታወቀ ፣ ፀረ ኢትዮጵያ ፣ ፀረ አንድነት መሆናቸው እየታወቀ ፣ እነሱ ሲያደርጉት እሰየው ፣ አማራው ሲያደርገው አፍ ማሞጥሞጥ ምን ይባላል? አማራው እንደነሱ ነፃ አውጪ ነኝ አላለ ። መገደል ፣ መሰደድ ፣ መዘረፍ ፣ መፈናቀል ስለቸኝ እራሴን ህልውናዬን አስከብራለሁ አለ እንጂ ። የአማራው መሰባሰብ ወያኔን እንዳሰጋው ሁሉ መሰሎቹንም ያሰጋቸውና ያሳሰባቸው እንደሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው ። ኡኡታውና ጩኸቱ መሰረቱ ስለሚታወቅ እምብዛም ለጩኸታቸው ጆሮ መስጠት አያስፈልግም ። አማራው አሸናፊ ሆኖ ከወጣ ኢትዮጵያ እንደ ሐገር ልትቆምና ፣ ኢትዮጵያ አንድ ሐገር ፣ አንድ ሕዝብ ፣ የሚለው መሰረት ይጣላል ከሚል ስጋት እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይሆንምና ኡኡታው ይገባናል ።

ማንም ስብስብ ዛሬ አማራውን በሙሉ አፉ መተቸት የሚችልበት የሞራልም ሆነ የዜግነት ብቃት የለውም ። አማራው ዛሬ እራሱን ከጥፋት ለመታደግ የሚያደርገው ተጋድሎ እንጂ እንደሌሎቹ ኢትዮጵያዊነትን የዘነጋ ወይንም ዝቅ ያረገ እንዳልሆነ ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው፣ አማራን በጭራሽ ከኢትዮጵያዊነት መለየት እንደማይቻል የኢትዮጵያን ታሪክ መመርመር እራሱ ከበቂ በላይ የሆነ አጥጋቢ መልስን ይሰጣል ።

ላለፉት 25 ዓመታት አማራው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እያለ ሲጮህ ለጩኸቱ ጆሮ የሰጠ አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ማለቱ በራሱ የጥቃት ሰለባ እንዲሆንና ሁሉም በየአቅጣጫው ጦሩን እንደሰበቀበት የሚዘነጋ አይደለም ። ዛሬ በሃገሪቱ እንደ አሸን ፈልተው የምናያቸው ፣ ለቁጥር አዳጋች በሆነ ሁኔታ በጎጥና በመንደር ዝቅ ሲልም በቤተሰብ የተደራጁት በስልጣን ላይ ያለውን ወያኔ ጨምሮ ያሳደዱት እንደሆኑና እንደነበሩ የማይክዱት ሃቅ ነው ።

ዛሬ የአማራው ሕዝብ በደል ስላንገሸገሸው ከወያኔ ጋር በመተናነቁ ፣ ወያኔ የሚይዘው የሚጨብጠው በማጣቱ የተነሳ ሳይወድ በግዱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ አገሪቷን በተለይም አማራው ያለበትን ስፍራ ሁሉ የጦር ቀጠና እንዳደረገ ፣ ታንክና ከባድ መሳሪያውን በማውጣት አማራው ባለበት ቦታ ሁሉ በማስፈርና በማከማቸት አጥፊና ጠፊ ጊዜያቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ ማንም እያስተዋለው ያለ ጉዳይ ነው ።

አማራውም ባልሞት ባይ ተጋዳይነት በየአካባቢው በጎበዝ አለቃ በመደራጀትና በመሰባሰብ የወያኔን መንግስት ተብዬ እንደ አስም በሽተኛ ትንፋሽ እያሳጠረው እንደሆነ የዘወትር ዜና ከሆነ ሰነባብቷል ፣ ለዚህ እውነታ ወያኔ እራሱ ጥሩ ምስክር ነው ። ስለሆነም በተለይ በቅርቡ በሞት የተለየን አርበኛ ጎቤን እንኳን ለማስገደል አይገቡ ገብቶ ለሆዳቸው ባደሩ ወገን በምንላቸው ነገር ግን በኩርማን እንጀራ  በተገዙ ርካሽ ባንዳዎች ጎቤን እንዳስገደሉ የሁላችንም የቅርብ ጊዜ ክፉ ትውስታችን ነው ።

እንግዲህ ወያኔ የተከፈለውን ክፍያ በመክፈል የቻለውን እርቀት ሁሉ በሆድ አደሮች ሊጓዝ እንደሚችል እያወቅን በምን ሂሳብ ይሆን ዛሬ በተለይ አማራ ካልሆኑ ይልቁንም ልክ እንደ ወያኔ አማራውን በጠላትነት የሚፈርጁ ፣ መፈረጅም ብቻ ሳይሆን ከወያኔ ጋር አብረው አማራውን ያረዱና ያሳረዱ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ተብዬ እንደነ ሌንጮ ያሉ ፣ እንደነ ደሚት ያሉ ፣ የነ ስዬ አድናቂና አጨብጫቢ ካሉ እንደነ ግንቦቴ ከመሳሰሉት ጋር አብሮ ተሰልፎ ወያኔን መዋጋት የሚቻለው ? ሌንጮ ወያኔ ካሮት ሲያሳየው የሚላላስ ፣ ወያኔ በትር ሲያነሳ የሚያኮርፍና የሚፈረጥጥ ፣ የቀደመ ታሪኩ የበከተ የበሸቀጠ ሲሆን ፣ የትግሬው ደግሞ እራሱን ደሚት ብሎ የሚጠራው ወያኔ “ለ” መሪያቸው የነበረው ሞላ አስገዶም የተባለው የዘሬን ብለቅ ያንዘርዝረኝ ብሎ 700 ወታደር ከነትጥቁ ይዞ ወደ ፈጣሪው ወያኔ ጉያ እንደገባም ሰምተናል ። ዛሬ ደሞ የግሞች ስብስብ በግሞ ሰብሳቢነት ግንባር ተፈጥሮ ከኦሮሞው ነፃ አውጪ ሌንጮ ፣ ደሚትን ጨምሮ የአማራው የትግል አጋር ነን ሊሉን ሲዳዳቸው ይስተዋላል ። እዚህ ላይ እጅግ ማስተዋል የሚያስፈልግ ይመስለኛል ወያኔ በራሱ በአማራው መሃል ሰርጎ በመግባት ሆድ አደሮችን በኩርማን እንጀራ በመግዛት “እርስ በርሱ ስጋን በኩበት ጠበሱ” ብሎ እንደተሳለቀብን መዘንጋት አይገባም ። ስለሆነም ትላንትና በበደኖ ፣ በዴዴሳ ፣ በአሩሲና በመሳሰሉት ስፍራዎች አማራውን ሲገሉትና ሲያስገድሉት የነበሩትን እነሌንጮን አዝሎ ሌላ ደሚት የሚባል ወያኔ “ለ”ን ይዞ ያውም “ወያኔ ወይም ሞት” ብሎ ያስመሰከረን ፣ አንዲሁም የስዬ አብረሃ ፍቅረኛን በጓሮ ማስገባት ማለት ፣ እነዚህን ኩርማን እንጀራ አይገዛቸውም ብለን ይሆን? አይደለም ሆዳቸው ተጨምሮበት ሲፈጥራቸውም አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ የገባው የአማራው ጥላቻ በራሱ የሳት እራት ሊያደርግ እንደሚችል ከወዲሁ ማየትና መገንዘብ ብዙም የሚያመራምር አይማስለኝም ፣ ስለሆነም “አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ባሰብሽ” ይላልና ያገራችን ሰው ይሄ ሁኔታ እጅግ ሊታሰብበት ይገባልና የአማራው ሕዝብ ንቃ እንዳትበላ ማለት እወዳለሁ ።

 

ድል ለአማራው ተጋድሎ

 

ታዛቢው

አውሮፖ የሚኖሩ ከሆኑ ይህ ለመጄመሪያ ጊዜ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ( ጎህ)

$
0
0

አውሮፖ የሚኖሩ ከሆኑ ይህ ለመጄመሪያ ጊዜ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ( ጎህ) አመራር አካላት የሚገኙበት የውይይት መድረክ እንዳያመልጥዎ።
ማርች 25 ፍራንክፈርት

የማህበረሰብ ጠንቅነት ዝንባሌን እንዴት ማወቅና መጠንቀቅ እንችላለን?  የነገሰው(ትርጉም  በአማኑዔል)

$
0
0

ላለፉት በርካታ አመታት  እኛ በውጭና በሀገር ዉስጥ  የምንገኝ  ኢትዮጵያውያንና ትዉልደ  ኢትዮጵያውያን  በኢትዮጵያውያ ዉስጥ የተሻለ መንግሥታዊ  አስተዳደር እንዲመጣና  ባጠቃላይ ፍትህ  እንዲሰፍን ያላሰለሰ ጥረት ስናደርግ ቆይተዋል::  ይሁን አንጂ በተለያዩ ተቆጥረዉ በማያልቁ  ምክንያቶች፣ አብዛኞቹ ደግሞ እራሳችን በፈጠርናቸዉ ድክመቶች እስካሁን የከፈልናቸዉ መሥዋቶች፣ ድካማችንና ልፋታችን የታለሙለትን  ያህል ግብ ሊመቱና ፍሬያማ ሊሆኑ አልቻሉም:: በዚህም የተነሳ ብዙዎቻችን በመሰላቸትና በምሬት ይመስላል፣ ከዋናዉ ጠላታችን ከወያኔ ጋር ከመታገል ይልቅ ምሬትና ብስጭታችንን ስርዓቱን በሚደግፉ የዉጭ ሃያላን መንግሥታትና ባመዛኙ ደግሞ ኃይላችንን እርስ በርሳችን በመነታረክ ላይ እያባከንን እንገኛለም(ተጠምደናል):: ከዚህ በፊት ስንጓዝበት ከነበረዉ የተሳሳተ ጉዞ ሳንማር አሁንም  የቀድሞ ስተታችንን በመደጋገም፣እያንዳንዳችን በግል ኃላፊነት እንደሚሰማዉ ግለሰብና ዜጋ ለህዝባችን ሰላምና ለትዉልድ የምናወርሰዉ ሀገር ለመፍጠር መፍትሄ ከመሻት ይልቅ  አንዱ ልላዉ ላይ ጣት በመቀሰር፣ እርስበርስ ስም ለማጥፋት መሞከር ፣ አንዱ ብሔር ሌላዉን ለቀድሞዉና ለአሁኑ ችግሮቻቺን ተጠያቂ  ለማረግ በመጣርና የተለያዩ  ምክንያቶችን በመደርደር ከትግላችን ይልቅ እንደዉም የምንታገለዉን መንግሰስት በሚጠቅም መልኩ የእርስ በርስ ትርምሱ ላይ በማተኮር ህዝባችንንና ራሳችንን  ከዚህ አስከፊና የታሪክ ጠባሳችን ከሆነዉ ስርዓት ለማላቀቅና  ለመታደግ የምናደርገዉን ጉዞ እያወሳሰብነዉ መተናል ::

እዚህ ላይ ባንክሮ ሊሰመርበት የሚገባዉ ነገር ይህ አባባል(ከላይ የተጠቀሱት ትችቶች)ግን በአሁኑ ሰዓት በተለያየ መልኩ በተናጥልም ሆነ በጋራ እየተደረጉ ያሉትን ትግሎችና መስዋቶችን ለማኮሰስ የታለመ ሳይሆነ በአንፃሩ ግን ለትግሉ ሕይወታቸዉን አሳልፈዉ የሰጡና መስዋትነት እየከፈሉ ያሉ ወገኖቻችን ላይ ደንቃራ ወይም መሰናክል በመሆን ከላይ በተጠቀሱት ትግሉን ለማሽመድመድ አስተዋፆ እያደረጉ ባሉ ዘለፋ፣ትችትና ከጥቅማቸዉ ጉዳታቸዉ በሚያመዥን ንትርኮች ላይ አላስፈላጊ ግዜና ኃይላቸዉን እያጠፉ ያሉ የሕብረተሰባችን ክፍሎችን ለማለት ነዉ:: በዚህ አጋጣሚ ሳልጠቅስ ማለፍ የማልሻዉ ነገር ደግሞ አዳጋች፣ ፈታኝና እልህ አስጨራሽ ሁኔታዎችን በቆራጥነት በማለፍ እስከ ከፍተኛዉ የህይዎትና ሌሎች መስዋትነቶችን ለሀገራቸዉና ህዝባቸዉ ነፃነት ለከፈሉና እየከፈሉ ላሉ ወጎኖቻችን አድናቆትና ምስጋና ማቅረብ ብቻ ሳይሆን በምንችለዉ  አቅማችን ሁሉ ላጋርነት መዘጋጀት የዜግነት፣ የትዉልድና የወገን አጋርነት ግዴታችን መሆኑን ነዉ ::

ባሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ መስዋትነት እየከፈለ መሆኑ አጠያያቂ ባይሆንም ዳሩ ግን ከዚህ ህዝባችን ከተዘፈቀበት የኑሮ እሽክርክሪት፣ ሽኩቻና የማህበረሰብ ሽባነት በተፈለገዉ ፍጥነት ፈልቅቆ ለማዉጣትና ባንድነት ወደተሻለ የጋር እቅድ፣ የትግል ስልትና ለድል  ለማብቃት ከፊታችን የተጋረጡብን መሰናክሎች ምንድናቸዉ? እስካሁን የተጓዝንባቸዉን የትግል ስተት መስመሮች ወደኋላ ትተንና ተምረን ሁላችንንም ነፃ ሊያወጣ የሚችለዉን መንገድ እንዴት እንቀይስ?  ህብረተሰባችን አቅሙን አስተባብሮ በጋር ለነፃነቱ፣ እንደ ጥንት አባቶቹ ባንድ ላይ፣ ነፃ መዉጣት እንደሚሻ ህብረተሰብ በጋራ መቆም ያልቻለዉና አቅሙን ያሽመደመዱት   ሁኔታዎች ምንድናቸዉ ?

እንደኔ  ግንዛቤ ከላይ ከተዘረዘሩትና እንዲሁም  ተቆጥረዉ ለማያልቁ ችግሮቻችን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ካሉ መሀበራዊ ችግሮቻችን መካከል ቀላል የሚመስል ነገር ግን ማህበረሰባችንን በጋር አብሮ በሚያረጋቸዉ ጥረቶች ሁሉ ጣልቃ በመግባት እያሽመደመዱት ወይም  የህብረተሰብ ሽባ እያደረጉት ካሉት መካከል እንደ ሰደድ እሳት በፍጥነት እየተስፋፋና እየተሰራጨ  ያለዉ  ፀረ-ኢትዮጵያዊነት፣ ፀረ-ሕዝብ፣ ፀረ-ሕብረተሰብ፣ በተለይ በወጣቱ ትውልድ መካከል ቀላል የሚመስል ነገር ግን አደገኛ የማህበረሰብ ጠንቅነት አዝማሚያ ወይም ዝንባሌ እየተበራከት መምጣቱ ነዉ:: ወደድንም ጠላንም ሕዝባችን በማህበረሰብ ጠንቆች (ፀረ-ኢትዮጵያ ግለሰቦችና ቡድኖች) እየተዋጠ ይገኛል:: ሁኔታዉን ዉስብስብ የሚያደርገዉ ደግሞ እነዚህ ማህበራዊ ጠንቆች ይህን አደገኛ ስነምግባር (dangerous role model)የወረሱት ከዋናዉ የሕብረተሰባችን ጠንቅ ከሆነዉና በመንግሥትነት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከተዘፈዘፈዉ ከወያኔ የዱርዬና ተላላኪ ስርዓት መሆኑ ነዉ:: ስለሆነም ዋናዉና ትልቁን የማህበረሰባችንን ችግር ተነጋግሮና ተወያይቶ በጋራ ለመፍታት ይህን አይነቱን እንደሰደድ እሳት እየተስፋፋና በተለይ ወጣቱን የህብረተሰባችን ክፍል በፍጥነት እየበከለ ያለ የህብረተሰብ በሺታ ከምንጩ ለማድረቅና የተመረዙ  የሕብረተሰባችን ክፍሎችን፣ ቤተሰባችንንና ወዳጆችችንን ከዚህ አስከፊና አደገኛ ዝንባሌ ለማዳን በግልና በጋር መዉሰድ ስላለብን እርምጃዎች መምከር  አለብን:: ህዝባችን ከገባበት አጣብቂኝ  ሁኔታዎች  እንዲወጣና በጋራ ጠላቱ ላይ ባንድነት እንዲነሳ፣ በጋር ጥቅም ላይ የተመሰረት ተራማጅ አጀንዳና የጋራ ግብ ላይ ለማሰለፍ  ከተፈለገ እነዚህ አደገኛ ተልኮና አዝማሚያ ያላቸዉ ነገር ግን  ራሳቸዉን በተለያየ ጭምብል የሸፈኑ የህብረተሰብ ጠንቅ  ግለሰቦች፣ ቡድኖችና የትዉልድ ጠንቅ የሆነ አፍራሽ ተልኳቸዉ በማህብረሰባችን ዘንድ በግልፅና በይፋ መታወቅ  አለበት :: በዋናነት  አሳሳቢ  እየሆነ የመጣዉ ደግሞ  እነዚህ የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች ከግዜ ወደግዜ ቁጥራቸዉ እየጨመረ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን የተማሩ እያልን ከምንጠራቸዉ የሕብረተሰባችን ክፍል ዉስጥ መሆኑና ከዚህም ጋር በተዛመደ  በህብረተሰቡ ዉስጥ ያላቸዉን ቦታ(their status in society) ለተለያዩ መሰሪ፣ ጎጂና ለአፍራሽ  ተልኮዎች  በመጠቀም አብሮ በኖረ ሕዝብ ዉስጥ፣ በተለይ  ወጣቱንና ያልጠረጠሩ የዋሆችን በመደለልና በመጠምዘዝ ወደ አደገኛና አሳሳቢ ዝንባሌ ለመምራት፣ የመርዝ መልእክት በቀላሉ ማሰራጨት መቻላቸዉ ነዉ:: ከላይ እንደተጠቀሰዉ ያለጥርጥር  የነዚህ  የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች  አመለካከት የተቀረፀዉ(role model የሆናቸዉ)  በመንግስትነት ደረጃ ተቀምጠዉ  ህዝባችንን ከሚያጭበረብሩና ከሚያወናብዱ ወያኔ ተላላኪዎች ቢሆንም በመሃላችን ግን እራሳቸዉን በተለያየ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪነት/ተከራካሪነት ስም ከናንበዉና  በተለይ ወጣቱን የምያማልሉበት የዘር ፖለቲካና ጥላቻ ሌት ተቀን ሲሰብኩ ይዉላሉ::

እነዚህ ከኛዉ  ሕዝብ ዉስጥ የወጡና የሕብረተሰባችን አካል ሆነዉ ሳለ በማያሻማ ሁኔት አዉቀዉም ይሆን ሳያዉቁ(ለማለት ባያስደፍርም) ለሕዝባችን የማያልቅ ስቃይና መከራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛሉ :: ስለሆነም ከእያንዳንዳችን፣ ስለ ሀገር፣ ስለዜጎችና ወገኖቻችን የመቆርቆር ኃላፊነት ከሚሰማን ሁሉ ምን ማድረግ ይጠበቃል ወደሚለዉ አንኳር ጥያቄ ስናመራና እነዚህን በማህበረሰብ ጠንቅነት በሺታ የተመረዙ የህዝባችን ጠንቅ ከመሆን ይልቅ ጠቃሚ አባል/አካል እንዲሆኑ ምን ማድረግ እንችላለን ብለን ስንጠይቅ፤ከሁሉም በላይ ደግሞ ከንደዚህ አይነት ቡድኖችና ግለሰቦች እያሰራጩብን ካለው ማኅበራዊ በሽታ ራሳችንን፣ቤተሰባችንና ክፉ የማንመኝላቸዉን ወገኖቻችንን እንዴት እንከላከል የሚሉትና የመሳሰሉትን አንገብጋቢ ጥያቄዎች አንስተን መፍትሄ ለመሻት ትኩረት መስጠት ያለብንና ጠቃሚ ይመስሉኛል::

እንደመነሻም እዲሆነን ግን ስለ ማህበረሰብ ጠንቅነት ባህሪ(ዝንባሌ) መጀመሪያ በሚገባ መረዳት ለመፍትሄዉ ተቀዳሚ ጉዳይ ይመሥለኛልና እስቲ ስለህብረተሰብ ጠንቅነት ባህርያት ግንዛቤ ለማስጨበት የሚረዱና በዚያዉም የዚህ የማኅበረሰብ በሺታ በእኛ ኅብረተሰብ በተለይም ወጣቱን ለመጠበቅና ታማምዎቹንም ለመርዳት(ሊረዱ የሚችሉትንና ፈቃደኛ የሆኑትን ማለቴ ነዉ ) አስተዋፆ ያረግ ዘንድ  ስለባህርያቸዉ ትንሽ እንበል::
የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች አዲስ የተከሰቱ አደሉም፣ በህብረተሰብ ዉስጥ ለዘመናት  በመግደል፣ በማስገደል፣ በጅምላ ፍጅት ዉስጥ በመሳተፍ አልያም የሃይማኖት ወይም ሌላ የቡድን ከታዮቻቸዉን(cults)ባላቸዉ የተፅኖ የመፍጠር፣ የማታለልና የመዋሸት ከፍተኛ  ችሎታ በመጠቅም ራሳቸዉን በግልና በጅምላ እንዲያጠፉ ሲያሳምኑ፣ ሲያስፈጁና ሲፈጁ፣ ሲገሉና ሲያስገድሉ  ነረዋል:: ዛሬም በዚህ  ባለንበት ክፍለ ዘመን(modern era) መረጃ በተፈለገዉ ፍጥነት በሚሰራጭበት፣ ዉሸትና እዉነት በቀላሉ ማመሳከር በሚቻልበት ዘመንም እንኳ ብዙ ቁጥር ያላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች በንደዚህ አይነት ግለሰቦችና ቡድኖች ሲያታልሉ፣ሲጎዱና በተለያየ አስከፊ የህይዎት ዉጣዉረድ ዉስጥ ሲማገዱ ይስተዋላል:: ስለሆነም በነዚህ የማህበረሰብ ጠንቆች ተፅኖ ስር፣ በግልም ሆነ እንደማህበረሰብ፣ ሳንወድቅና ችግር ዉስጥ ሳንዘፈቅ ልናዉቃቸዉና ለራሳችን፣ ለቤተሰባችንና አጠቃላይ ለሕብረተሰባችን ጥንቃቄ እንድናደረግ  የሚያስችሉን አንዳንድ አይነተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች አይነተኛ ባህሪያትን በጥቂቱ እንመልከት፤

1ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች ከፍተኛ የማሰብና የማስተዋል አቅም ሲኖራቸዉ ነገር ግን  ይህ ተሰጥዖቸዉን(የአዕምሮ ከፍተኛ የማሰበ ችሎታቸዎን) ሌሎችን ከማገዝና ከመርዳት ይልቅ ለማታለልና ለማጭበርበር  ይጠቀማሉ:: ይህም ከፍተኛ የአዕሮ የማሰብ ችሎታቸዉና አፍራሽ ዝንባሌቸዉ በሕብረየሰብ ዉስጥ አደገኛ ያረጋቸዋል::  ለዚህም ነዉ ብዙዎቹ ብዙውን ጊዜ በህግ አስከባሪዎችና ሕዝብ ሳይጠረጠሩ ወይም ሳይያዙ  በተሳካ ሁኔታ ወንጀል ሰርተዉ ለማምለጥ ወይም ለመሰወር የሚችሉት::
2ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች የጥፋተኝነት፣የኃፍረት ወይም የጸጸት ስሜት የሚባል ነገር አልፈጠረባቸዉም:: አንጎላቸዉ አነዚህን ስብዕናዎችና ስሜቶችን የሚያከናዉኑ ክፍሎች ይጎሉታል::በዚህም የተነሳ፣ የቅርብ ጓደኞቻቸዉ ላይ ሳይቀር፣ ማንኛዉም ሰዉ ላይ ያለምንም ማመንታ ማንኛዉንም አይነት ጉዳት ከማድረስ፣ ክደት ከመፈፀምና ብሎም  ጥቅም ካስገኘላቸዉ ግድያን ከመፈፀም የሚከለክላቸዉ ስብዕና አልተፈጠረባቸዉም:: የፈለገዉን ያህል ሌላዉን ግለሰብ ወይም ህብረተሰብ ሊጎዳ ቢችልም ጥቅማቸዉን ልያስከብር የሚችል ማንኛዉንም ነገር ከማረግ ወደኋላ አይሉም:: ለዚህም ነዉ ብዛት ያላቸዉ ከፍተኛ በተለይ ያምባገነን መንግስት ስልጣን ላይ የደረሱ እንዲህ አይነት ግለሰቦችንና ቡድኖችን ማግኘት የተለመደ የሆነዉ ::
3ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች ብዙዎቹ ትኩረትን የሚስቡ እና የሚመስጡንግግሮችን የማረግ ችሎታም አላቸዉ::  ያድማጭን ቀልብ  ሊስቡ የሚችሉ ቃላት የመምረጥና ያለምንም ማቋረት ኃሳባቸዉን በትረካ አገላለፅ  በማቅረብ የተጠበቡ ባለቅኔዎችም ሊሆኑ ይችላሉ::
4ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች የፈጠራ ዉሸትና ስለራሳቸዉ የሕይወት ተሞክሮ ከመጠን በላይ አጋነዉ ማዉራት ይወዳሉ፣ አዉርተዉም አይጨርሱም፣ነገር ግን ኪነጥበባዊ በተላበሰ መልኩ ሲናገሩት ላድማጭ ተዓማኒና ተቀባይነት እንዲኖረዉ  የማረግ ኃይል አላቸዉ::

 

5ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች በሌሎች ላይ የበላይነትንና ማንኛዉንም መስዋዕትነት ከፍለዉ ክርክርን ማሸነፍ ይፈልጋሉ:: በክርክር መረታትን በጣም ከመጥላታቸዉ የተነሳ  የዉሸት ናዳና  ትርጉመ ቢስ ማስረጃዎችን ወይም ምክንያቶችን በመደርደር ተፎካካሪቸዉንና ባላንጣ መስሎ የምታያቸዉን ሰዉ ሁሉ ለመርታት ማለቂያ ወደሌለዉ ጭቅጭቅ ዉስጥ ይገባሉ:: እነዚህን ሰዎች በምንም ዓይነት ምክንያታዊ ጋጋታ ማሳመን ማሸነፍ/መርታት አይቻልም:: እንደዉም ከራሳቸዉ ሃሳብ በተቃራኒ ማሳመኛ ምክንያቶች ወይም አሳማኝ መረጃዎች  ከቀረቡላቸዉና መረጃዎቹ በበዙባቸዉ ቁጥር ንዴትና እልህ ዉስጥ ይገባሉ::

6ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች ብዙን ግዜ ጥሩ ተክለ-ሰዉነትና የደስደስ አላቸዉ:: ሰዎችንና ተከታዮችን የመሳብ ተሰጥዖ አላቸዉ በተለይ በተለያየ ምክንያት እርዳታ ፈላጊ፣ በህይወታቸዉ ዉጣዉረድና አስቸጋሪ ሁኔታዎች የገጠማቸዉና ምክር ወይም የህይዎት አቅጣጫ(guidance) የሚፈልጉና የሚሹ ሰዎች ሲያጋጥሟቸዉ ከመርዳት ይልቅ፣  ደካማ ጎናቸዉን በመጠቀም ለራሳቸዉ ጥቅም ብቻ ኢላማቸዉ ያረጓቸዋል:: አብዛኞቹ የማህበረሰብ ጠንቆች ጠንካራ የወሲብ መስህብና አንዳንዴም ግራ የሚያጋባ የፍትወት ባህርያት(absurd sexual appetite) ያሳያሉ::  እዚህ ላይ ግን  ሁሉም ጠንካራ የወሲብ መስህብና ፍላጎት ያላቸዉ  ሰዎች ሁሉ  የማህበረሰብ ጠንቆች ናቸዉ ብሎ ለመደምደም አደለም::

7ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች ከተራዉ ሕብረተሰብ በተለይ ሁኔታ ግብታዊና ጥልቅ (intense)ናቸዉ:: አንዳንድ ግዜም መደበኛ ሰዎች ሊሰሯቹ የማይፈልጉ ወይም የማይወዱትን ግራ የሚገባ ድርጊት ሲያረጉ

ይታያሉ :: ህገወጥ ወይም በሕግ የተደነገጉ ባይሆኑም ማህበረሰብ በጋር ባህልን፣ደንብን ወይም ሃይማኖትን መሰረት ያረጉ ከማኅበራዊ ውሎች(social contracts/norms)ና ስነምግባሮች ተፃራሪና ጥራዝ ነጠቅ የሆኑ ተግባሮች ሲያረጉ ይስተዋላሉ::

8ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች ስለፍቅር ያላቸዉ አመለካከት ሙሉ በሙሉ የራስን ጥቅም በማስጠበቅ (completely self-serving or selfishness) ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሲሆን አላማዉም እራሳቸዉ የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት  እንጂ እንደ ጤነኛ ሰዉ አይነት የፍቅር ወይም ርኅራኄ  ስሜት በዉስጣቸዉ አልፈጠረባቸዉም::

9ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች ራሳቸዉን ፍፁም አርገዉ ነዉ የሚቆጥሩት:: በነሱ አመለካከት ስህተት የሚባል ፈጽሞ አያቃቸዉም:: በዚህም ምክንያት ማስረጃ ቢደረደርላቸዉም እንኳ ፈፅሞ የጥፋተኝነት ስሜት አይሰማቸዉም:: ለሌላ ሰዉ ስተትም ሆነ ለራሳቸዉ ስተት ይቅርታ አያውቁም::ባጠቃላይ አዕምሯቸው ጥፋተኝነትን፣ ይቅርታንና መሸነፍን የሚያከናዉን ክፍል ይጎለዋል ማለት ይቻላል::

10ኛ) የማህበረሰብ ጠንቅ ግለሰቦች የተነፈሱት ወይም የተናገሩት ሁሉ፣ በነሱ አንደበት ስለተነገረ ብቻ፣ አዉነት ነዉ ብለዉ ያምናሉ::

http://www.cnn.com/2013/09/30/us/manson-family-murders-fast-facts/

እናም ወደኛ ወቅታዊ ጉዳይ ስንመለስ  በርግጥም በጅጉ በሚያሳስብ ደርጃ  በህብረተሳባችን ዉስጥ እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን ባህርያት የሚያንፀባርቁ ግለሰቦች በቁጥር ከግዜ ወደግዜ እየጨመረ መምጣቱን በግልፅ የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች በተጨባጭ እየታዩ ሲሆን ለግዜዉ  ከንደዚህ የማህበረሰብ ጠንቅነት ባህሪ እያንፀባረቁ ካሉት መካከል እንደ አይነተኛ ምሳሌ (typical)ሆኖ ያገኘሁት በቅርቡ በፌስቡክ ላይ በሚያደረገዉ አደገኛ፣ከፋፋይና ለሕዝባችን ጠንቅ የሆነ እንቅስቃሴዉና ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ የሚስተዋለዉ ፀጋዬ አራርሳ የተባለዉ ሲሆን ይህ ግለሰብ ከፌስቡክ ገፁ ለማወቅ እንደቻልኩት በትምህርት ከፍተኛ  ደረጃ የደረሰ(ዶ/ር)፣ የኦሮሞ  ሕዝብ ሰባዊ መብት ተከራካሪ ነኝ የሚል፣ የኦሮምኛ ቋንቋ የማይናገር(የማይችል)፣ራሱ(አሁንም በማህበራዊ ድረ-ገፅ በሚያሰራጨዉ መረጃ ነዉ-እኔ በአካል ግለሰቡ መፈጠሩንም አላቅም) እንደሚለዉ ኦሮምኛ  ቋንቋ ገና እየተማረ እንደሆነ  ይልቁንም አማረኛ  ጠንቅቆ እንደሚናገር(ለግንዛቤ እንጂ ቋንቋ የማንኛዉም ሰባዊ መብት ተከራካሪነት ቅድመ ሁኔት አይሆንም) ወዘት በማለት ይቀጥላል ::በዚሁ የፌስቡክ ገፁ እኔን ያስደመመኝ/የገረመኝ ደሞ በየቀኑ የኦሮሞን ሕዝብ በተለይ ከአማራዉ ለመለያየት ለማቃቃር በሚፈለስፋቸዉና ፖስት አድርጎ ያልጠረጠሩና የዋህ አንባቢዎቹ በሚለግሱት ላይክ፣ ኮመንትና ሼር እንደታዳጊ ወጣት ሲቦርቅና ሲፈነድቅ መታዘቤ ነዉ::

እዚህ ላይ ማሳሰብ ያለብኝ ነገር ደግሞ ብዙ ግዜ እንደዚህ አይነት ትችቶች ሲነሱ ብዙዎች  ተከፋፍሎ ያለ ሕብረተሰብን ለበለጠ ክፍፍል አስተዋፅኦ ማበርከት ይሆናል የሚሉ አሉ ነገር ግን እኔ እላለሁ የችግሮችን መንስዔ በግልፅ አዉጥቶ ሳያደባብሱ መወያየት በፍፁም ችግሮችን አያባብስም እንደዉም የችግሩን ምንጭ ለማድረቅ ከመርዳት በስተቀር ::እናም ይህ አስተያየቴ ተጨማሪ ልዩነት ለመፍጠርና ግለሰቦችን ለመወንጀል/ለመተቸት/ለመኮነን ሳይሆን  የችግሮችን መነሻ አዉቆ መፍትሄ ለመሻት ይረዳ ይሆናል ከሚል ሃሳብ  የመነጨ ነዉ::

ለመንደርደሪያ ይሆነን ዘንድ ግን ለቀባርዉ ማርዳት ቢሆንም  በአሁኑ ሰዓት ዶ/ር ፀጋዬ አራርሳና  የኦዔምን(OMN) ባልደረቦቹ ለሰብአዊ መብቱ በብቸኝነት እንታገልለታለን ወይም ቆመንለታል (አትንኩብን ለኛ የተመደበ የግል ስራችን ነዉ የሚሉ በሚመስል መልኩ) የሚሉንን የኦሮሞን ሕዝብ ባሁኑ ሰዓት ያለበትን ሁኔታ በአጭሩ እናንሳ፤ በሽዎች የሚቆጠሩ የኦሮም ብሔር ተወላጆች በወያኔ እስርቤትና ማጎሪያ ቤቶች ዉስጥ እየማቀቁ እንደሚገኙ ያደባባይ ሚስጥር ነዉ፣  የዛኑ ያህል ደግሞ በቅርቡ ከነዚሁ እስር ቤቶችና ማጎሪያዎች ዉስጥ ሰባዊነትን በሚያኮሥስና በሚያሸማቅቅ ሁኔታ ይቅርታ ተደረገላቸዉ ተብሎ የወያኔ አራዊቶች ሲመፃደቁባቸዉ ሁላችንም ያየነዉና ከንፈር ያስመጠጠን ሃቅ ነዉ፣ በሙሉ ለማለት በሚያስችል የኦሮሞ ተቃዋሚ ሃይሎች መሪዎች ፣ እነ አቶ  በቀለ ገርባና ዶ/ር  መራራን ጨምሮ አሁንም በዚሁ በወያኔ ማጎሪያና ማሰቃያ  እስር ቤቶች ዉስጥ አየተጉላሉ መሆናቸዉ ይታወቃል:: በዚህ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለን ሰቆቃ ዘርዝሮ መጨረስ የሚቻል አይመስለኝም፤ የኢሬቻዉ ፍጅት፣ በግብፅና በሜድትራኒያን ባህረ ዉስጥ የሚያልቁና በኬንያና ሌሎች ጎረቤት ሃገራት ዉስጥ የሚደርሱባቸዉም መከራዎች መቋጫ አልተበጀላቸዉም:: እንደዉ በኦሮምያ ክልል ያለዉን ሁኔታ ለፅሁፌ ተዛማጅነት አነሳውሁት እንጂ  ይህ ሁኔታ  በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎችና ህዝቦች ማለትም በአማራዉ ክልል በሶማልዉ እንዲሁም በደቡቡ ያለዉ ሁኔታ እንደሚታወቀዉ ተመሳሳይ ነዉ.: የኦሮምያዉን ላተኩርበት የፈለኩት የኦሮሞ ብሄረሰብ መብት ተከራካሪ ነን እያሉ ጠዋት ማታ የምያደርቁን እንደ ዶ/ር ፀጋዬ አራርሳና ኦዔምን(OMN) ያሉ ጓደኞቹ ከላይ የጠቀስኳቸዉን የኦሮሞ ህዝብ በአሁኑ ሰዓት እየደረሱበት ያለዉን አበሳና ሰቆቃ ችላ በማለት ይልቁንም እስካሁን አንዲት መረጃ ባልተገኘለትና ይልቁንም ከጥላቻ፣ ከግለሰብ አጀንዳና የፖለቲካ ግብ የመነጨዉን ስለሚኒሊክ የኦሮሞ ሕዝብ ጭፍጨፋና የአማራ ህዝብ በሌላዉ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ላይ ስለነበረዉ የበላነት የወያኔ ፈጠራ ታሪክ ለኦሮሞ ወጣቶችና ላልጠረጠሩ የዋህ ተከታዮቻቸዉ ሲያስተምሩና ግራ ሲያጋቡ በመታዘቤ ነዉ::

የኦሮሞ ሕዝብ በዚህ ሁኔታ ላይ  ሆኖ እያለ፣ ከግል አጀንዳና ጥቅም በስተቅር፣ ለማንም ለምንም በማይጠቅም ጉዳይ ላይ ያለ የሌለ እዉቀት፣ ግዜና ሃይላቸዉን ተጠቅመዉ በዚህ ሕዝብ ደም ላይ በመረማመድ ዝናንና ሌላም ሌላም ግላዊና ሰዋዊ ፍላጎታቸዉን ለማሟላት ብቻ ሲራወጡ እያየን እንዳላየ ወይም ዝም ካልን ሰባዊነታችንን መካድና የእነዚህ በኦሮሞ ሕዝብ ደም ላይ አንደዋዛ የሚረማመዱትና የሚነግዱት ስተት ብቻ ሳይሆን የኛም ከዳር ቆመን ተመልካቾቹም ለዚህ ሕዝብ ስቃይ እኩል አስተዋፅኦ እያበረከትን እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል:: ምክንያቱም ዛሬ  ሀገርን በዉሸትና በፈጠራ ሲያፈርሱ ፣ ሕዝቦች አብሮ የመኖር ፍላጎትና መብታቸዉ በአጭበርባሪና አካበትነዉ በሚሉት እዉቀት ሽፋን  በየዋሁ ህዝባችን ላይ ሲነግዱበት በግልፅ እያየን፣ የታሪክ ወይም የሕግ  ዶ/ር፣ ፕሮፌሰር ወዘት ነን እያሉ በወያኔ ስር የሚማቅቀዉን የኦሮሞና ሌላዉንም ሕዝባችንን ለነፃነቱ ባንድነት እንዳይታገልና ለሕብረቱ ደንቃራ በመሆን፣ ይልቁንም  የገጠመዉ ሀገር በቀል ጠላት ልጆቹን፣ እናቶችን፣ አባቶችን፣ወንድም፣ እህቶቹንና አጠቃላይ ወገኑን ፊት ለፊት እየገደለበት ያለዉን የወያኔ ቅጥረኛ ገዳይ  ወደኅላ ችላ በማለት ከወቅቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለዉና ለወቅቱ ጥያቄ መልስ ሊሆን የማይችልና ማስረጃ ተፈልጎ ያልተገኘለት የነዚሁ የገዳይ ወያኔና ተመሳሳይ ድርጅቶች ፈጠራና ዉሃ የማይቋጥር ልብወለድ ታሪክ በወጣቱና ባልጠረጠሩ የዋህ የሕብረተሰባችን ክፍሎች  ዉስጥ  እንደመርዝ መርጨት/መስበክ ከማህበረሰብ ጠንቅነት በሺታ ሌላ ምን ብለን ልንጠራዉ እንችላለን?

ህዝቡ የጋራ ጠላቱን ተባብሮ አንዳይታገል በመሃሉ ልዩነቶችን ለማጥበብ ከመሞከር ይልቅ በየቀኑ አዳዲስ ልዩነት ማጉያ ዘዴዎችን እየፈለሰፉ ህዝቡ ከዋና ጠላቱ ይልቅ በተመሳሳይ በደል ስር ካለ ዜጋዉ ጋር እንዲቃረንና በጥርጣሬ እንዲተያይ ማድረግ ምን አይነት የሰብዓዊ መብት ተከራካሪነት(human right activism) ብለን እንጥራዉ? ይህ ታዲያ ከማኅበረሰብ ጠንቅነት ባህሪ ሌላ ምን አይነት የሰዉ ባህሪ እንበለዉ?  ይሄን የሰብዓዊ ፍጡር ባህሪ የህብረተሰብ በሽታ/ጠንቅ ብሎ ለመፈረጅ ደግሞ የግድ የስነልቦና ዶክተር ወይም ጠበብት መሆን ያስፈልጋል ብዬ አላምንም:: በኔ በኩል እነዚህ ግለሰቦች ታመዋል ህዝባችንንም በዚህ በሽታ አየበከሉ ነዉ ::

ሕዝባችን በወያኔ የምድር ላይ ገሃነም እስርቤቶች ታጉሮ እየተሰቃየ፣ እናትን በገደለዉ የልጇ እሬሳ ላይ ተቀመጭ የሚል አዉሬ የወያኔ ስርዓት ከፊታችን ተደቅኖ ፣ ለተራበ ሕዝብ እያለ ባለማቅፍ  ደረጃ በልመና ንግድ ላይ የተሰማራ ስርዓት ህዝባችን ጫንቃ ላይ ተዘፍዝፎ ሳለ ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ መብት ተከራካሪ ነን የሚሉት እነ ዶ/ር አራርሳ እና የኦኤምን(OMN) ጓደኞቹ ጠዋትና ማታ የሚኒሊክ ፍጅትና የአማራ የበላይነት የስማ በለዉ  የልብወለድ ታሪክ መስበክና የወጣቱን አዕምሮ በጥላቻ መመረዝ፣ የመማሩን ነገር ችላ እንበለዉና፣ የጤነኛ ሰዉ አእምሮ አመለካከት መሆኑን የሚያስርዳኝ ሰዉ ለኔ ትልቅ ባለዉለታዬ  አርጌ ነዉ የምቆጥረዉ:: ለኔ የነዚህ ሰዎች (የነ ዶ/ር አራርሳና የኦዔምን(OMN) ጋንጎች) ነገር ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲህ ነዉ የሆነብኝ:: ምክንያቱም ባሁኑ ሰዓት የኦሮሞ ህዝብና በተመሳሳይ የጭቆና ቀምበር ዉስጥ ያሉት ኢትዮጵያኖች እያሉ ያሉት እኮ  “ጠላታችን፤ ልጆቻችንን፣ እናቶቻችንን፣ አባቶቻችንን፣ እህት ወንድሞቻችንንና ባጠቃላይ ወገኖቻችንን እፊት-ለፊታችን እየገደለ ያለዉ ወያኔ ነው፣ ከዚህ በሃያላን መንግሥታት እየተደገፈ እየገደለንና የልጅ ልጆቻችን መኖሪያ ሀገር ጭምር እያጠፋና እየሸጠ ያለዉ ቅጥረኛዉ ወያኔ ነዉ ::” ነዉ ::  ብዙዎችን ግራ ያጋባዉና እኔንም በፍፁም ሊገባኝ ያልቻለዉ ደግሞ እነ ኦዔምን(OMN gangs) እና ዶ/ር አራርሳ በተፃራሪዉ  ጠዋትና ማታ በተለይ የኦሮሞን  ሕዝብ ለብቻ በመለየት የሚሉት ደግሞ  “አንገብጋቢዉና አፋጣኝ መልስ የሚሻዉ ከላይ ያላችሁት ሳይሆን እኛ የተማርነዉና የተመራመርነዉ የምንለዉና ወያኔ(ያሁኑ ገዳያቹ) ለ40+ አመታት አስረግጦ የሰበከን፣ ከሺ አመታት በፊት ተከስቷል ብለን ያመንበት፣  የምኒልክ ፍጅትና ያማራ ሕዝብ የበላይነት ነዉ ::” ነዉ:: ለኔም ፐዝል የሆነብኝም ይሄዉ ነዉ፤ የኦሮሞ ሕዝብ(በመሰረቱ የሁሉም የኢትዮጵያዉያን  ሕዝብ ጥያቄ ) እና የዳያስፖራ ኦሮሞ መብት ተከራካሪዎች መልስ::  እነዚህ ሁለት ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲህ ነገሮች እንዴት እንደሚጣጣሙ በቀላል ቋንቋ የሚያስረዳኝ ሰዉ ነዉ ያጣሁት::  እናም እንዚህ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲህ ፈፅሞ እርስበርሱ የማይጣጣም ፍልስፍና እንበለዉ ሃሳብ(idea)ተዋኒዎችን እንዴት እንርዳቸዉ?፣ ዋናዉ ቁም ነገር ደግሞ እራሳችነንና ዉድ ወገናችንን በተለይ ወጣቱን ከዚህ ተላላፊ በሽታ እንዴት እንጠብቅ?  እንደማህበረሰብ እንደ አንድ ሀገር እንደሚጋራ ሕዝብ እነዚህ ለህዝባቸዉ ጤናማ አመለካከት የሌላቸዉ(ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ሕብረተሰብ) ከኛዉ ሕብረተሰብ ዉስጥ የወጡ ወገኖቻችን እንደመሆናቸዉ መጠን የሚረዱበትንና በዛዉም  የራሳችንንም የወደፊት እጣፈንታ በተለይ ወጣቱን ከዚህ አደገኛ ዝንባሌ መከላከል  የምንችልበትን መንገድ መቀየስ የግድ ይላል:: ሆኖም ብዙ ሥራ ይጠይቃል ፣ ትግስት አስጨራሽ አሰልችና  አስቸጋሪም ነዉ :: በተለይ መፍትሄዉን ዉስብስብ የሚያደርገዉ፤

1ኛ) እነዚህ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ነን ባዮች በትክክል ግን የማህበረሰብ ጠንቆች ሁኔታዉን ከዘርና ከተፈለሰፈ ታሪክ ጋር ለማያያዝ መጣራቸዉ፣

2ኛ) እነዚሁ ዘርን ያተኮረ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ነን ባዮች የማህበረሰብ ጠንቆች በሚያሳስብ ሁኔታ የተማሩ እያልን ሁሌ እሽሩሩ ከምንላቸዉ የሕብረተሰባችን ክፍሎች በብዛት እየተፈለፈሉ መምጣታቸዉና

3ኛ) እኛዉ እራሳችን የነዚህ የማህበረሰብ ጠንቆች አጀንዳቸዉ ፈፅሞ ለሕዝባችን ፋይዳቢስ ቅዥት እንደሆነ አለመረዳትና እዉነትና ዉሸትን ለመለየት ጥረት (fact finding effort) ባለማረግ ዝም ብለን እንደቦይ ዉሃ መነዳታችን ሲሆነ የተረዳነውም ብንሆን ይሄን አፍራሽ ጠንቅ ሃሳባቸዉን ሙሉ በሙሉ  ላለመቀበል ወይም ለማስወገድ (to refuse and reject) የሚችል ኮስታራ ሃሞት አጥተን አብረን ለመልፈስፈስ በመምረጥ  ቦታ፣ ግዜና ድጋፍ መቸራችን ነዉ::

“የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል” – ያሬድ ጥበቡ

$
0
0

“ምን ይሻላል?”በሚል ርእስ ያሬድ ጥበቡ ከ2 አመታት በፊት ታዋቂ የታሪክ ሰዎችን በመጥቀስ የአዲስ አበባ ፊንፊኔን ታሪክ ካስረዳ በኋላ፣ አዲስ አበባን ያካተተ አንድ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እንዲፈጠር ጥሪ አቅርቦ ነበር። አቶ ያሬድ ጥበቡ ያኔ ያቀረቡትን ጽሁፍ እንዳለ እንደሚከተለው አቅበነዋል፡
***********
( ያሬድ ጥበቡ )

የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች በብዙ ጉዳዮች የሚለያዩ ቢሆንም፣ ፊንፊኔ መናገሻችን ናት በሚለው ጉዳይ ግን ይስማማሉ ። ለመሆኑ ፊንፊኔ የኦሮሞ መናገሻ ነበረች? ኦሮሞዎች ከየት መጡ? የኦሮሞን አፈታሪክና መዝሙሮች ፣ የታሪክ ተመራማሪዎችም ከፃፉዋቸው፣ ከሱማሌና ሐረሪ ህዝቦች አፈታሪክ በማጥናት፣ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ይልማ ዴሬሳ “የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን” የሚል መፅሀፍ በ1959 አም ፅፈዋል ። የታላቁ የኦሮሞ አፈታሪክ ቁንጮ፣ የብላታ ዴሬሳ ልጅ በመሆናቸው ልናዳምጣቸው የግድ ነው ። የመጨረሻው የሌቃ ነቀምቴ ንጉስ የሞቲ ሞረዳ በከሬ የቅርብ ዘመድም ስለሆኑ ( cousin) ታሪካቸውን ልቅም አድርገው ያውቃሉ ። እንዲህ ይሉናል ።
” ይህ ምዕራፍ የተፃፈው፣ የኦሮሞን ወይም አማሮች ጋላ የሚሉትን ነገድ ታሪክ በዝርዝር ለማስረዳት አይደለም ። ስለሆነ በ16ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ይህ ነገድ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ሰሜንና ወደ ምስራቅ ጎርፎ የሚበዛውን ደጋ አገር ይዞ ስለሰፈረበት በዘመኑ ታሪክ ውስጥ የኦሮሞን ነገድ ፈንታ ሳናነሳው ያለፍን እንደሆነ የ16ኛው መቶ የኢትዮጵያ ታሪክ ሙሉ ሆኖ አይገኝም ።…

… ታሪክ ሲነጋጋ የኦሮሞ ህዝብ ከአደን ሰላጤና እስከ ቅርብ የእንግሊዝ ሱማሌ በሚባለው የሱማሌ ሪፐብሊክ አውራጃ መካከል ከሚገኘው የአፍሪካ ቀንድ በተባለው አገር ሲኖሩ ታዩ ። ኦሮሞዎች በየትኛው የታሪክ ዘመን በዚህ ምድር እንደሰፈሩ ግልፅ አይደለም ። … ይሁንና ከ10ኛው መቶ ዘመን በፊት ሱማሌ የተባለው ነገድ ከታጁራ ቤይ አቅጣጫ ተንቀሳቅሶ በኦሮሞዎች ላይ ጦርነት ባደረገ ጊዜ፣ መጀመሪያ የእንግሊዝ ሱማሌ የነበረውን አገር ለቀው ወደ ምስራቅ ደቡብ መጓዝ እንደጀመሩ ታውቋል ። ኋላም የአፍሪካ ቀንድ ከምትባለው ሶስት ማእዘን ወረዳ ተነስተው በዋቢ ሸበሌና በጁባ ወንዞች መካከል ቤናዲር በተባለው አውራጃ ሰፍረው በዚያ ብዙ ዘመን እንደኖሩ በጋሎች አፈታሪክ ሲነገር የኖረ ነው ። …

… ከሰሜን የሱማሌዎች ከደቡብ ባንቱዎች የሚያደርጉባቸው ጦርነት ምንም ጊዜም ሰላም የሰጣቸው አይመስልም ። ስለዚህ ከዚህም ከአዲሱ አገራቸው እንደገና መሰደድ ግዴታ ሆነባቸው ።

…ጋሎች ወላቡ፣ አበያ፣ ባሕርና ሕዲ ዳዲ ከሚባሉት አቅጣጫ የሰፈሩት በአስረኛው መቶ በዛጕዌዎች ዘመነ መንግስት መጀመሪያ ላይ ይመስላል ። … የኦሮሞ ህዝብ በሥጋና በወተት የሚመገብ ዘላን ስለነበር ድርቅ ከሆነው ከቤናዲር አውራጃ ተጉዞ ወላቡ ወይናደጋ በገባ ጊዜ ይህች ምድር ማርና ወተት ታፈሳለች እንደተባለችው እንደ ምድረ ከነአን የምትቆጠር ሁና አገኙዋት ። … በወላቡ ተራራና በአበያ ባህር አጥቢያ በኖሩበት ጊዜያት የሰላምና የጥጋብ የዕድገት ዘመን መሆኑን ሲወርድ ስዋረድ የመጣው የጋሎች አፈታሪክ አጋኖ ይገልፅልናል ። …

ኦሮሞዎች እላይ በተመለከተው አኳኋን በወላቡ ዙሪያ ብዙ ትውልድ ካሳለፉ በኋላ ከልክ ያለፈ ተራብተው ምድር ጠበባቸው ። … ከዚህም ሌላ በጥንት ዘመን ከቀድሞው መኖሪያቸው ከአፍሪካ ቀንድ ወግቶ ያስወጣቸው የሱማሌ ህዝብ፣ አስራ አምስተኛው መቶ ሲጋመስ ወይናደጋው ድረስ እየመጣ አዲሱን አገራቸውን መውረር ጀመረ ። በዚህ አኳኋን የኦሮሞ ህዝብ ለመከላከልና ለግጦሽ የሚፈልገውን መሬት አስፍቶ ለመያዝ ከሰላማዊ አኗኗር ወደ አርበኝነት ሃሳቡን መለሰ ። …ከወላቡ ሳይነሱ በገዳ ድርጅት ውስጥ የጦር ሠራዊትን ማከናወን ዋና ጉዳይ አድርገው ያዙት ። …በዚህ ዘመን ኦሮሞዎች ከረዩ፣ ቱለማ፣ ሜጫና፣ ወሎ በሚባል ባራት ትልልቅ ነገድ ተከፍለው ይገኙ ነበረ ። ስለዚህ ከረዩ የተባለው ነገድ፣ ባሌን ፈጠጋርንና ደዋሮን እንዲወር፣ ቱለማ ወደ ሰሜን ተጉዞ ዛሬ የሸዋ ጋላ ምድር የተባለውን እንዲይዝ፣ ሜጫ በስተ ምእራብና በስተደቡብ የሚገኘውን የእናሪያዎችን አገር እንዲወስድና፣ ወሎ የተባለው ነገድ በሸዋ በስተምስራቅ ተጉዞ ከወሎ አውራጃ እስከ ትግሬ የተዘረጋውን አንጎት የተባለውን አውራጃ እንዲይዝ የተቀየሰው ኦዳ ነቤ በነበሩ ጊዜ ነው ። …

ለጦርነት የተደረገው ድርጅት ከአለቀ በኋላ ኦሮሞዎች ዘመቻውን ፈጥነው አልጀመሩትም ። [ ዛሬ ኢሳያስ ወያኔን ለመበቀል የሚያሳየውን አይነት ትእግስት ይመስላል * የኔ] ይልቁንም በነዚህ ዘመናት ውስጥ ሱማሌዎች ክርስቲያናዊውን ኢትዮጵያ ለመውረር በትልቁ በመዘጋጀት ላይ ስለነበሩ፣ ምቹ ጊዜ ለማግኘት ኦሮሞዎች በትእግስት ጠበቁ ። በ1506 አም አነስተኛ ወረራ ወደሰሜን በሚገኘው ወረዳ ላይ ከአደረጉ በኋላ ጥቂት ገፍተው ቆሙ እንጂ ውጊያውን አልቀጠሉም ። … ስለዚህ በ1520ና በ1532 አም መካከል ግራኝ የኢትዮጵያን ደጋ ወሮ በአማራና በሱማሌዎች መካከል ሃይለኛ የሆነ ትግል ሲደረግ ጋሎች ያሰቡትን ለመፈፀም በፀጥታ ሲጠባበቁ ቆዩ ። …

እስከ 16ኛው መቶ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ድምፁን ሳያሰማ የቆየው የጋላ ነገድ በ1524 አም ከደቡባዊ መኖሪያው መንቀሳቀስ ጀመረ ። የዚህም እንቅስቃሴ አላማ ከዚህ በላይ እንደተመለከተው ሁሉ በደጋው የኢትዮጵያ አወራጃዎች ላይ ለመስፈር ነበር ። “

እንግዲህ ከላይ በታላቁ ሰው ብእር ያነበብነው፣ ኦሮሞዎች ከየት ተነስተው ዛሬ የሚኖሩባቸውን ግዛቶች እንደያዙ ነው ። ገና 500 አመታት እንኳ ያላደረገ ታሪካዊ ክንዋኔ ነው ። ታዲያ የሶስት ሺህ አመት መንግስታዊ ታሪክ ባላት ሃገር ላይ፣ ታሪክ የሚጀምረው ከምንሊክ መስፋፋት ወዲህ ያለው ብቻ ነው የሚል ክርክር የት ያደርሳል? ፊንፊኔስ ብትሆን ከከብት አርቢዎች ሆራነት ወጥታ የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ መናገሻ የሆነችው በመላ ኢትዮጵያውያን ትጋትና ድካም መሆኑ እየታወቀ፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ውስጥ ናት የሚል ወያኔአዊ ደባ ምን ይጠቅማል? የአምስት ሚሊዮን ነዋሪዎቿስ መብት ለምን ታገደ? ብዙ ጥያቄዎች አሉ ። መፍትሄዎችም እንዲሁ ።

አንዱ የሚታየኝ መፍትሄ ፣ አሁን ባለው ፌዴራላዊ አወቃቀር ውስጥ የአዲስ አበባ ነዋሪ ዜግነቱን የሚያገኝበት መንገድ ማፈላለግ ነው ። ለዚህም፣ ማዘጋጃ ቤቱን እንደ ማእከል ወይም መነሻ በመውሰድ፣ 150 ኪሎ ሜትር ሬዲየስ ያለውን ግዛት “የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል” ብሎ 10ኛ ክልል መጨመርና፣ ይህም ክልል በፌዴራል ምክርቤት ድምፅ እንዲኖረው ማድረግ ። ይህ ክልል የሁሉም ብሄረሰቦች የጋራ ክልል በመሆኑ፣ በምክርቤቱ ውስጥ ያለው ድምፅም ቢያንስ አንድ ሶስተኛውን የያዘ ቢሆን፣ ሃገሪቱን ማረጋገት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረው ይመስለኛል ።

ይህ እቅድ ሶስት ችግሮች ይገጥሙታል ። አንዱ የሸዋን አማራ ከአማራ ክልል ያወጣዋል ። ሁለተኛው ችግር የኦሮሞን ክልል በምእራብና ምስራቅ ሁለት ቦታ ይከፍለዋል ። ሦስተኛው ችግር ደግሞ ጉራጌው የሚኖርበትን ከደቡብ ክልል ያስወጣዋል ። የአማራና ኦሮሞ ክልሎች ግን በወያኔ የፖለቲካ ፕሮዤ የተወጠኑ እንጂ፣ በታሪካዊ ወይም ውስጣዊ ፍላጎታቸው የተከለሉ አይደሉም ። ኦነግ ውስጥ የፖለቲካ ችግር በተነሳ ቁጥር፣ እስላምና ክርስቲያን፣ አርሲና ወለጋ እየተባባለ እንደሚቧደን ሁሌም የምንታዘበው ነው ። የአማራ ክልል ውስጥ የተካተቱም ህዝቦች፣ ከአማራነት ይልቅ ወሎዬነታቸው፣ ጎጃሜነታቸው፣ ጎንደሬነታቸውን ይበልጥ ያፈቅሩታል፣ ይወዱታልም። የወያኔ የዘር መድልኦ መባባስ ገና ወደፊት ይመስለኛል አማራ የሚባለውን ብሄር ቀጥቅጦ የሚፈጥረው ።

ጉራጌው አዲስ አበባን ደክመው ከሰሯት ቀዳሚ በመሆኑ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ ከልል ውስጥ ግባ ቢባል፣ ያን ቆንጆ ጭፈራውን ሲያቀልጠው በአይነ ህሊና ይታየኛል ። ሸዌው የኢትዮጵያ ማንነቱን አስቀዳሚ ሰለሆነ፣ ከኦሮሞና አማርነቱ በላይ ኢትዮጵያዊነቱን ያስቀድማል ብዬ መከራከር እወዳለሁ ። ስለሆነም ዜግነቱን የሚያሰከብርለት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቢያገኝ የሚያሰማው እልልታና ሆታ፣ የፈረሱ ኮቴ በእዝነ ህሊናዬ እያደመጥኩት ነው ።

ስለሆነም የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መፈጠር፣ ኦሮሞውን ቢያንስ ወደ ሁለት ክልል፣ አማራውን ደግሞ ወደ ሶስት ሊከፍለው ይችላል ። ይህ ግን ለተሻለ አስተዳደርና ልማት ጥርጊያውን ሰለሚከፍት ጥሩ ሃሳብ መስሎ ይሰማኛል ። አሁን ያለውንም የአዲስ አበባ ማሰተር ፕላን ችግር ከስር መሰረቱ ይፈታዋል ብዬ አስባለሁ ። አዲስ አበባንም ለፖለቲካ ተንኮል ተብሎ ከተጣለባት የአንድ ብሄር ክልል ውስጥ የመወርወር አደጋ ይታደጋታል ። የኢትዮጵያ ብሄርተኝነትም ዙሪያውን በከበቡት የኦሮም፣ የጉራጌ፣ የአማራ ገበሬዎች እየታገዘ፣ ከሸገር በሚፈልቀው የመላ ኢትዮጵያውያን ባህላዊ መስተጋብርና ፍቅር እየተመራ፣ የኢትዮጵያን ቀጣይነት ያረጋግጣል ብዬ አስባለሁ ። ይህ ለብዙ ወራት ተጨንቄ ያቀረብኩት ሃሳብ በመሆኑ ለማውገዝ አትቻኮሉ ። እሰኪ እንደኔ ተጨነቁበት ።

በተለይ አዲስ በቀል የሆናችሁት የትግራይ ከበርቴዎች፣ የሃገር መረጋጋት የሚፈጥረው ጥቅም ተጠቃሚ ስለሆናችሁ ፣ ከመለስ የስልጣን ተንኮሎች ባሻገር፣ ለልጆቻችሁ የምታወርሱት ሃገርና ንብረት እንዲኖራችሁ፣ የሚቀርቧችሁን የወያኔ መሪዎች ከሃገር ማጥፋት እኩይ ተግባርና ከዘረኝነት እንዲርቁ ምከሩ ። ይህን ማድረግ አቅቷችሁ እስካሁን እንደተያዘው ተቃውሞን በጥይት ማጥፋት ይቻላል ብላችሁ ከገፋችሁበት፣ እንኳንስ ሃገር፣ መሰደጃ ስንኳ አታገኙም ። ከቀዬው የነቀላችሁት ስደተኛ “የኒዮ ሊበራሊዝም ጠበቆች” እያላችሁ በምታወግዟቸው አለምአቀፍ መያዶች እየታገዘ ያድናችኋል። ከዚህ ይሰውራችሁ ። ለሃገር የሚበጅ መላ ምቱ። ይህችን ቅድስት ድሃ ሃገር የሁላችን እናድርጋት ። ታላቁ ትግራዋይ ኢትዮጵያዊ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ከመቶ አመታት በፊት እንደፃፈው “ጠንካራ መንግስት ከህዝብ ልብ ይቀዳል”

“ጠለምት የጎንደር አማራ እንጂ የትርጋይ አይደለችም ሆናም አታውቅም” – ከዓለም አቀፍ የጠለምት ማሕበር የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

መጋቢት 4ቀን 209ዓ/ም

ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በመበታተን፥ ህዝቧን እርስበርስ እያናቆረ በማጥፋት ታላቋን ትግራይ ለመመሥረት በሚል ኣጉል ቅዥት እየዋዥቀ ይገኛል። በፀረ ኢትዮጵያ አቋም የተመረዘው ወያኔ ኢትዮጵያን በጠመንጃ ሃይል ስልጣን ከተቆጣጠረበት ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ ተፈጥሮ ያደላቸዉን ለምና ወሃ-ገብ የሆኑትን የጎንደር ወረዳዎች፣ ወልቃይት፣ ጠገዴንና ጠለምትን ከወሎ ክ/ሃገር ደግሞ ወደ አራት የሚሆኑ ወረዳዎችን በትግራይ ክ/ሃገር ሥር እንዲሆኑ የዛሬ 44 ዓመት ደደቢት ላይ የጠነሰሰው ሴራ በጠመንጃ ሃይል ወደትግራይ እንዲካለሉ ከአደረገ ዓመታት ተቆጥሯል።

ከአምስት ምዕተ ዓመታት በላይ የታሪክ ባለቤት የሆነችው ጠለምት በጎንደር ክ/ሃገር የምትገኝ አማርኛ ተናጋሪና የአማራ ባህልና ወግ የሚከተል ሕዝብ የሚኖርባት ስለመሆኑ በቀደምት የታሪክ መዛግብት ዉስጥ ሰፍሮ ይገኛል። የጠለምትን መልከዓ-ምድር አቀማመጥን ስንመለከት፤ በሰሜን ተከዜ ወንዝን ተከትሎ ትግራይ፤ ክ/ሃገርን በምሥራቅ እንዲሁ ተከዜን ወንዝን ተከትሎ ተንቤን አውራጃ(ትግራይ) እና ዋግ አውራጃ(ወሎን)፤ በምዕራብ ወልቃይትና ጠገዴ፤ በደቡብ በተፈጥሮ ሃብት የበለጸጉ በጎንደር ክፍለ-ሃገር የሚገኙ እንደ ሰንሰለት የተጠላለፉ የሰሜን ተራራዎች ጋር ይዋስናል።

የወያኔ አገዛዝ ተከዜን ወንዝ የተሻገረው “ታላቋን ትግራይ” ለመመሥረት ባቀደው እቅድ መሠረት፤ ለምና ወሃ-ገብ የሆኑትን የጎንደር ወረዳዎችን ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምትን በተቆጣጠሩበት በ17 ዓመት የሽፍትነት ጊዜና ከ25ዓመት በፊት መላ ኢትዮጵያን በሃይል በመዳፉ ሥር ባሰገባበት ወቅት፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ይወያኔ ታጋይዮች የነበሩና ደጋፊዎቻችወን አምጥቶ በወልቃይት፣ በጠገዴና በጠለምት አስፍሮ ለዘመናት በጋራ አብሮ ይኖር የነበረን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና እንዲጠላላ እያደረገ ይገኛል።

ወያኔ ካለፉት 25 ዓመታት ጀምሮ፤ የጠለምትን ሕዝብ በመዳፉ ሥር ካስገባ በኋላ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እንዲሁም የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ባለው እቅድ መሠረት፤
1ኛ) በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከትግራይ በማምጣት ኣስፍሯል።

2ኛ) ከ25,000 በላይ የሚሆኑ የኤርትራ ስደተኞችን በማይ ኣይኒና በኣዲሃሮሽ በተባሉ መንደሮች በማስፈር ለፖለቲካ ፍጆታ እየተጠቀመባቸው እንደሆነና ለዚሁም ማረጋገጫ የዛሬ ኣንድ ወር ገደማ የትግራይና የኤርትራ ባህላዊ ባንድ በጋራ በመሆን አመታዊ የህወሃት በዓል ላይ መጫወታቸዉንና በኤርትራና በትግራይ ህዝብ ላይ ምንም አይነት ልዩነት ኣለመኖሩንና አንድ ሕዝብ መሆኑን በግልፅ ባደባባይ መናገራቸው ላለሙት ዓላማ ገላጭ መሆኑን ያስረዳል።

ሰፋሪዎቹም ባአገሬው ሐዝብ ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል ግፍና መከራ እየፈፀሙ ይገኛሉ። ተወልደው ባደጉበትና እትብታቸዉ በተቀበረብት አገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ በመቆጠራቸው ግፍና መከራው ከሚገባው በላይ መሸከም ሲያቅታቸው በህወሃት ከተወሰደባቸው ህብት ንብረት የተረፈዉን እንኳን ለመውሰድ እድሉን ባለማግኘታቸው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ስፍር ቁጥር የለላቸው ያገሬው ተወላጅ ባላባቶች ቀያቸዉን እየተዉ ወደ ጎረቤት አገር(ሱዳን)፥ወደ ጫካና ወደ ተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ተሰደዋል። ያሠፈራቸውን ቅጥረኞችን በማስታጠቅ፤ በጠለምት ሕዝብ ላይ ወደር የሌለው ጭፍጨፋ (genocide) እና የዘር ማጥፋት (ethnic cleansing) በማያቋርጥ ሁኔታ አካሂዷል። እያካሄደም ነው።

ይኽ ሁሉ ዘግናኝ ግፍ የተካሄደበትና በመካሄድ ላይ ያለው ፤ የጠለምት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በማንሳቱና እኛ አማራ፤ ቋንቋችን አማርኛ ነው፤ ክልላችንም ከላይ በታሪክ ተደግፎ እንደተገለፀው ጎንደር ነው ብሎ ያለፍርሃት በቀጣይነት መጠየቁ ያሳሰበውና ክፉኛ ያስደነገጠው የወያኔው ቁንጮና የትግራይ ክልል እስተዳዳሪ ተብየው አቶ አባይ ወልዱ ባሳልፍነው ወር ወደ ማይፀብሪ በመዝለቅ ሕዝቡን ሰብስቦ ለማባበል የሞከረ ቢሆንም ባከባቢው ያሰፈሯቸው የትግራይ ተወላጆችና ኣንዳንድ በጊዜያዊ ጥቅማጥቅም የተታለሉና ለሆዳቸው ያደሩ ባንዳዎች ሲገኙ ጀግናው የጠለምት ሕዝብ ግን እምቢኝ ኣሻፈረኝ በማለት በስብሰባው ላይ ሳይገኝ ቀርቷል። በሕዝቡ ምላሽ የተደናገጠው አባይ ወልዱ ላከባቢው የወያኔ ባላስልጣኖች መላው የጠለምት ሕዝብ ከሊማሊሞ በታች ራስ ዳሸንን ጨምሮ የትግራይ ክልል መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ የሚል ቀጭን ትእዛዝ ኣስተላልፎ በመሄዱ ያከባቢው ባለስልጣኖችም ያለቃቸዉን ትዕዛዝ ለመፈፅም ሕዝቡን ሳይወድ በግድና ሳያምንበት በጠመንጃ ኣፈ ሙዝ ኣስገድዶ ለማስወጣት ትልቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ባለን ውስጣዊ መረጃ መሠረት ደርሰንበታል።

ስለሆነም ጀግናው የጠለምት ሕዝብ ዛሬም እንደ ቀደምቱ ወያኔ የሸረበዉን ሴራ ለማክሸፍ “ጠለምት ጎንደር እንጂ ትግራይ አይደለችም፥ ሆናም አታውቅም” የሚለውን የጠለምት ታሪካዊ ምንነት አስረግጠህ ንገራቸው። ጠለምት የትግራይ ነው በሚል እነሱ ሊጠሩት ባስቡት የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመገኘት እውቅና እንዳትሰጥዋቸው። ጀግናው የጠለምት ሕዝብ ሆይ! የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) አገዛዝን አሽቀንጥረህ በማጣል የአማራ ማንነትህንና የመሬት ባለቤትነትህን ለማስመለስ የጀምርከውን ትግል እንዳንተው ለአምራ ማንነቱንና የመሬት ባለቤትነቱን ለማስመለስና መብቱን ለማስከበር ዉድ ህይወቱን እየገበረ ካለው ጀግናው የወልቃት ጠገዴ እንቅስቃሴ ጋር በማቀናጀት ትግሉን አጠናክረህ ቀጥል። እኛም በውጭ የምንኖር የጠለምት፥ወልቃይትና፥ጠገዴ ተወላጆች በሙሉ በያለንበት በመሰባሰብና በመደራጀት፤ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) በወገኖቻችን ላይ የሚያካሂደውን ጭፍጨፋ (genocide) እና የዘር ማጥፋት (ethnic cleansing) በማጋለጥና፤ ከወያኔ ጨቋኝ አገዛዝ ቀንበር ነፃ ለመውጣት የምታደርጉትን ትግል በማንኛው መልክ ለመርዳት እስከመጨረሻው ድረስ ከጎናችሁ መሆናችንን ለማረጋገጥ እንወዳለን።
የጠለምት፥ወልቃይትና የጠገዴ የማንነት ጥያቄ በሃቀኛ የሕዝብ ትግል ይረጋገጣል!
የኢትዮጵያ እንድነት ለዘላለም በክብር ይኑር!!
telemtgondar@gmail.com

The post “ጠለምት የጎንደር አማራ እንጂ የትርጋይ አይደለችም ሆናም አታውቅም” – ከዓለም አቀፍ የጠለምት ማሕበር የተሰጠ መግለጫ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News 24/7- Your right to know!.

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live