Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

ብአዴን የወልቃይት ጉዳይ የትግራይ ጉዳይ እንደሆነ በሙሉ ድምፅ ወስኗል – አለምነው መኮንን

$
0
0

የብአዴን ፅህፈት ቤት ሀላፊ እና የብአዴን/ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አቶ አለምነው መኮንን ከጋዜጠኛ ተስፋይ ሃይሉ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ከወይን መፅሄት የካቲት 2008 እትም።

ወይን፡- በትግራይ እና በአማራ ህዝቦች የነበረውና ያለው ግንኙነት እንዴት ይገልፁታል?

ኣቶ አለምነው፡- አገራችን የብዙ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሃገር ነች። የትግራይና የአማራ ክልል ህዝቦች ደግሞ በኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ውስጥ የየራሳቸው ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ወግ እና ልማድ ያላቸው ህዝቦች ናቸው። በዚህ መልካም ግብረ ገብነትና ትስስር ያሉ ጥንታዊ ህዝቦች መሆናቸው ነው የምገነዘበው። ይህ ብቻ ሳይሆን የትግራይና የአማራ ህዝቦች የዘመናት የአብሮነት ታሪካቸው በጣም ሰፊ መሰረት ያለው ነው። ለምሳሌ የክርስትና እና የእስልምና እምነትን በጋራ ተቀብለው በጋራ ተሳስሮ የመሄድ፣ ይህ ብቻ ሳይሆን የጋራ የሆነ ኣለባበስ፣ ወግ ልማድ ያላቸው ህዝቦች ናቸው። በዚህ የተወሰነም ኣይደለም፤ የጋራ ጠላታቸው የሆኑትን የባዕድ ወራሪዎች በተከታታይ በጋራ እየተፋለሙ አገራችንን ጠብቀው ያቆዩ ህዝቦች ናቸው።

በቋንቋ አንፃራዊ ልዩነት ቢኖርም በባህል፣ ስነ-ልቦና፣ ሀይማኖት፣ ኢኮኖሚ እና ማሕበራዊ መሰረት እጅግ ትስስር ያላቸው ናቸው። ድህነትንና ኋላቀርነትን በጋራ በመፋለም ባካሄዱት ጥረት የድህነትና የኋላቀርነት ጠበቃ የነበረው አምባገነኑን የደርግ ስርአት በማስወገድ ሂደት እጅግ ብርቱ ተባባሪነት፣ የአብሮነት ኣስተሳሰብና መንፈስ ይዘው የታገሉ ህዝቦች ናቸው። በ17 ዓመታት የትጥቅ ትግል ሂደት ውስጥ ሰፊው የትግራይ እና የአማራ ህዝብ ልጆች እጅና ጓንት ሆነው፣ “እኔ ቀድሜ መስዋእት ልክፈል” በሚል ፅኑ እምነት በአንድ ምሽግ እየወደቁ፣ በአንድ ጉድጓድ እየተቀበሩ መላ የኢትዮጵያ ህዝብን ነፃ በማውጣት ሂደት ታሪክ ሊዘነጋው የማይችል አኩሪ ገድልና አንፀባራቂ የተጋድሎ ታሪክ ያላቸው ህዝቦች ናቸው። የደርግ ስርአት በማስወገድ ብቻም ተወስነው ኣልቀሩም። ስርአቱን ለማስወገድ ያደረጉት የጋራ ትግል ድህነትንና ኋላቀርነትን ለማስወገድ በጣምራ ዘርፈ ብዙ ተጋድሎ ኣካሂዷል፤ እያካሄዱም ይገኛሉ።

በዚህ መሰረት የጋራ የልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ፖሊሲዎችን ነድፈው ከገጠር እስከ ከተማ በጋራ እና በአብሮነት መንፈስ ለመበልፀግ ላለፉት 25 ዓመታት ከፍተኛ ትግል ያካሄዱበት ነው። ይህ በመሆኑ ምክንያት የትግራይ እና የአማራ ህዝቦች እንዲሁም መሪ ድርጅቶቹ ህወሐትና የቀድሞው ኢህዴን የአሁኑ ብአዴን በጣምራ ትልልቅ የለውጥ አብዮቶችን አካሂደዋል። እነዚህ ድርጅቶች የለውጥ አብዮቶች አካሂደው ዘላቂ የሰላም፣ የልማትና ዴሞክራሲ በሮችን ከፍተዋል። በዚህ ደግሞ ለዴሞክራስያዊ ብሄርተኝነት መሰረት የሆነ የጋራ ህገ መንግስት እንዲኖር በአገር አቀፍ መድረኮች ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። በዚህ ሳይወሰኑ ለአብሮነታቸው እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን በቀጣይነት እየፈቱ ከጥንት ጀምሮ ኣብሮ ያደገውና የመጣው ብዙ ገፅታ ያለው መልካም ነገር ተጠናክሮና ዳብሮ በልማታዊና ዴሞክራስያዊ መልክ ጎልብቶና ፋፍቶ እንዲሄድ ብዙ ትግል እያካሄዱ ያሉ ህዝቦች ናቸው።

ወይን፡- ከጥቂት ወራት በፊት በአማራ ክልል አንድ አንድ ኣካባቢዎች በተለይም በሰሜን ጎንደር በትምክህተኞች የተፈፀመውን የጥፋት ድርጊት መነሻው እና ምንጩ ምንድ ነው?

አቶ ኣለምነው፡- በቅርቡ በአማራ ክልል አንድ አንድ ኣከባቢዎች የተፈጠሩ ኣለመግባባቶች የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች የማይወክሉ የተዛቡ የዘረኝነት ገፅታ ያላቸው መጥፎ ተግባራት ተስተውሏል። እነዚህ ችግሮች ስረ መሰረታቸው ምንድ ነው? የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው። እነዚህ ችግሮች ሰፊውን ህዝብ እንደማይወክሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ መገንዘብ አለበት። እነዚህ የትምክህት ሀይሎች ሰፊውን ህዝብ የሚወክሉ አይደሉም። ይሄ ደግሞ መላ የትግራይ እና የአማራ ህዝቦች ሊገነዘቡት ይገባል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን በጥቂት ሀይሎች አቀነባባሪነት የዘረኝነት መልክ ያለው ኣስነዋሪ ተግባር መከናወኑ ከህፃን እስከ ኣዋቂ አንገት የደፉበት፣ ሊወገዝ የሚገባው መጥፎ ተግባር እንደተከናወነ የቅርብ ትዝታ ነው። ታድያ እውነታው ይህ ከሆነ መነሻው እና የነገሩ ስረ መሰረት ምንድን ነው? ይሄ ነገር እንዴት ነው የጀመረው? የሚሉትን ነገሮች አሟልቶ መረዳት በጣም ጠቃሚ ነው።

እንደሚታወቀው በአገራችን ሰፊ የልማት በር ተከፍቶ ሁሉም በጥረቱና በድካሙ ጥሮግሮ የሚያድግበት የፖለቲካ ኢኮኖሚ ድባብ ተፈጥሯል። የተፈጠረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ድባብ ላይ ተመስርቶ የተፈጠረ መነሳሳትም አለ። ለምሳሌ ህዝብ በጥረቱ ልክ ተጠቃሚ መሆን የጀመረበት ሁኔታ አለ። ይሄ ደግሞ የሚበረታታ እና የሚያኮራ ለውጥ ነው። በእነዚህ የተፈጠሩ የለውጥ ተስፋዎች እና ተጨባጭ የዕለት ተዕለት ተጠቃሚነቶች የበለጠ ህብረተሰቡ እንዲነሳሳ፣ በለውጥ ማእበል እንዲበረታታ፣ የለውጥ ሀሳቦች ይዞ እንዲነሳ የሚያደርግ፣ ባገኘው ጥቅም ረክቶ የማይቀመጥ ህብረተሰብ ተበራክቷል። ከዚህ በመነሳት ብአዴን እና ያዋቀረው መንግስት በሚሰሯቸው ስራዎች የመደሰቱን ያክል በአንፃሩ ደግሞ የሚያስከፉት ብዙ ነገሮች አሉ። ከእነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹ ለመጥቀስ ያክል፤ አንደኛ ስራ አጥነት እየተበራከተ፣ በአንፃሩ የሚፈጠረው የስራ ዕድል ደግሞ አነስተኛ እየሆነ የመሄድ ጉዳይ ነው።

ሁለተኛ የግብርና ምርታማነት በሚፈለገው ደረጃ አላደገም። እድገት መጥቷል፤ ግን በሚፈለገው ደረጃ አላደገም። በተጨማሪ የኢንዳስትሪ ልማት እና የአምራች ኢንዳስትሪ መስኮች ልማት ህብረተሰቡ ብዙ እንዲስፋፉ ይጠብቃል። ይሁን እንጂ የኢንዳስትሪ ምርታማነትም ሆነ ራሳቸው የኢንዳስትሪ ቁጥሮች አልተበራከቱም። ይህ ብቻ ሳይሆን የልማት፣ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች እየተነሱ ግን በወቅቱ ያልተመለሱ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ነበሩ። ሌላው የዕለት ተዕለት የአገልግሎት አሰጣጥ መጓደል የፈጠረው የመልካም አስተዳደር እጦት ነው። እነዚህ ጥያቄዎች በቂ መልስ ባለማግኘታቸው ቅሬታና አለመግባባት እየፈጠሩ የመጡበት ሁኔታ ነበር። በተመሳሳይ የወሰንና የቅማንት የማንነት ጥያቄም ከዚህ ጋር ተያይዞ የነበረና በወቅቱ ያልተመለሰ ጉዳይ ነው የነበረው። እነዚህ ተደምሮ ህብረተሰቡ ቅር ያሰኙት ጉዳዮች ነበሩ። እነዚህን ቅሬታዎች የተገነዘቡ የተቃዋሚ ሀይሎች ቅሬታዎቹ በቅሬታነታቸው ብቻ እንዲፈቱ ሳይሆን ያዩዋቸው ይሄን ኣጋጣሚ ወደ ከፍታ ጎትተው “ይሄ የሆነው እኮ የህወሐት የበላይነት ስላለ ነው። የህወሐት አመራሮች እና በዛ ዙርያ ያሉ ሰዎች የላቀ ተጠቃሚ ይሆናሉ። በአንፃሩ ብአዴን ይህንን የመሟገት አቅም የለዉም፤ አቅመ ደካማ ነው። ስለዚህ የልማት አድሎ እየደረሰብህ ነው” ብለው ህብረተሰቡ ያነሳቸው የዕለት ተዕለት ጥያቄዎች አዛብተውና ከትክክለኛ መንፈሱ ውጭ አድርገው የመግለፅና የተዛባ ኣካሄድ የመሄድ ሁኔታ ነው የነበረው።

ስለዚህ የችግሩ መንስኤ የህብረተሰቡ ቅሬታዎች ሁነው ሲያበቁ እነዚህን ቅሬታዎች ግን ወደአልተገባ አቅጣጫ፣ ህዝብን ከህዝብ ወደ የሚያጋጭ አቅጣጫ ጎትተው በመውሰድ “የህወሐት የበላይነት አለ፤ ስለዚህ እነሱ ላይ እርምጃ በመውሰድ ከአካባቢያችን ብናስወጣቸው የፈለግነውን ማድረግ እንችላለን” ወደሚል መጥፎ አስተሳሰብ እንዲጎተት አደረጉት። በዚህ ምክንያት የጥፋት ሀይሎች እና የጥፋት ሀይሎቹ ያደናገሯቸው ጥቂት ግለሰቦች ተረዳድተው በአማራ ክልል አንድ አንድ አከባቢዎች ለምሳሌ በመተማ ዮሃንስ፣ በጎንደር አንድ አንድ ኣከባቢዎች፣ በአርማጮሆና በመሳሰሉት የተለያዩ ጥፋቶች ፈፅመዋል። ግርግሩ እና ሁከቱ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው በሰፊው የአማራ ህዝብና በክልሉ በሚኖሩ ህዝቦች ላይ ነው። ስለዚህ የትምክህት አስተሳሰብና ተግባር በጥፋት ሀይሎቹ ተጎትቶ ወደ ከፍታ ሲወጣ ከሁሉም በላይ ቀድሞ የሚጎዳው የራሱን ብሄር ነው የሚለው ፅንሰ ሀሳብ መሬት ላይ የታየበት ክስተት ነው ያጋጠመው። ከዚህ ባልተናነሰ ደግሞ በትግርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ጉዳት ደርሷል።

በዚህ ጉዳት ብአዴን እና የክልሉ መንግስት በከፍተኛ ደረጃ ሀዘን እና ቁጭት የፈጠረበት ሁኔታ ነው ያለው። ይሄ ብቻ ሳይሆን ሰፊው ህዝብ ያዘነበት ነው። ምክንያቱም ሰፊው የአማራ ህዝብ በጠቅላላ ከኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመልካም ግብረ ገብነት የመኖር ታሪክ ያለው ህዝብ ነው። በተለይም ደግሞ ከትግራይ ህዝብ ጋር በብዙ ገፅታ ክፉ ሲገጥመው በጋራ እየመከተ፣ ደግ ነገር ሲገጥመው ደግሞ በጋራ ደስታውን እያጣጣመ የኖረ ህዝብ ነው። በተጨማሪ በጋብቻና ቤተሰብነት የተሳሰረ ህዝብ ነው። ስለዚህ ይህን የመሰለ ህዝብ የመለያየት የጥፋት ሴራ ነው የተቀነባበረው። ዋናው መሰረቱ ግን መሪዎች ያልፈታናቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መኖራቸው እነዚህን ብሶቶች የጠላት ሀይሎች ጎትተው ወደ ሚፈልጉት አቅጣጫ መውሰዳቸው ነው። ከዚህ ተከትሎ ደግሞ የዘር ገፅታ አስይዘው የዘመናት ድንቅ የመግባባትና የአብሮነት ታሪክ ያለው ህዝብ የመለያየት ክፉ ተግባር የጥፋት ሀይሎች በማከናወናቸው የተፈፀመ ነው።

ወይን፡- ብአዴን በሚመራው ክልል የተፈጠረው ሁከት ከክልሉ መንግስት ቁጥጥር ውጪ የሆነበት ምክንያት ምንድ ነው? ሁኔታው ሲከሰት ብአዴን አስቸኳይ መፍትሄ ለማስቀመጥ እና እርምጃ ለመውሰድ ያስቸገረው ምክንያትስ ምንድ ነው?

አቶ አለምነው፡-እንደተገለፀው ህብረተሰቡ ቅሬታ ውስጥ እንዲገባ ያደረገው በግምገማ ላይ እንደተለየው የብአዴን አመራርና የመንግስት መዋቅር ህብረተሰቡ የሚያረኩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ካለማከናወን የተነሳ ነው። በዚህ ቅሬታ ውስጥ ያለ ህብረተሰብ ቅሬታው እስካልተፈታለት ድረስ መሪዎቹን በቀላሉ ሊሰማ አይችልም። መሪ እና ህዝብን የሚያገናኘው ድልድይ፣ የህዝብን ችግር የመፍታት ጥረትና ከዚህ ጥረት የሚመነጭ መተማመን ነው። ስለዚህ ህብረተሰቡ በአመራር አፈፃፀም ላይ ቅሬታ ፈጥሯል። በሌላ አገላለፅ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የጥፋት ሀይሎቹን አስተሳሰብ የመስማትና እንደ ትክክለኛ የመውሰድ በምትኩ ቦታ ይዘዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን በአመራሩ ሆነ በአባል ድርጅት መዋቅር ውስጥ እነዚህን የተዛቡ አስተሳሰቦች፣ የትምክህት እና ተጓዳኝ አስተሳሰቦች ተዛምተው ታይቷል። ስለሆነም በተፈጠረው የተዛባ አስተሳሰብና ህብረተሰቡ በሚያነሳቸው ጥያቄዎች እንደአመራር እነዚህ ጉዳዮች ለመፍታት ቁርጠኝነት ባለማሳየታችን የፈጠረው ቅሬታ ተደምሮ የማስተካከያ እርምጃ እንዳንወስድ እና የአቅም ማጣት እንዲያጋጥም ምክንያት ሁኗል።

ስለዚህ ችግሩን ያልተስተካከለበት ዋናው ምክንያት በአስተሳሰቡ የመበከል ሁኔታ በአመራር አካላት ውስጥ ታይቷል። ከዚህ አልፎም ችግሩን ለማስተካከል የመደማመጥ ጉድለት በየእርከኑ ነበር። ከዚህ በመነሳት በአንፃራዊነት የጥፋት ተግባር የተሻለ ተቀባይነት ነበረው ማለት ነው። ከዚህ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው ሁኔታውን ወደዚህ ደረጃ ያደረሰው።

አለምነው መኮንን

ወይን፡- ብአዴን እንደ ፖለቲካዊ ድርጅት ለዚህ ድርጊት ዘላቂ መፍትሄዎች ብሎ ያስቀመጣቸው ምንድን ናቸው?

አቶ አለምነው፡-እንደ መፍትሄ የተቀመጠው ከመስመር ለአብሮነታችንም ሆነ በአብሮነት ለመበልፀግ፣ በአብሮነት ለማደግ እና በጋራ ትልቅ አገር፣ የበለፀገ ህብረተሰብ፣ የህዝቦች ሁሉም አቀፍ መብት የተከበረባት አገር መገንባት የሚያስችል ምርጥ ህገ መንግስት አለ። ህገ መንግስቱ ብቻ ሳይሆን ከህገ መንግስቱ የተቀዱ እና የተስፋፉ ጥልቅ ምርምርና ጥናት የተካሄደባቸው የፖሊሲና የስትራቴጂ ሀሳቦች፣ የልማታዊ እና ዴሞክራስያዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አሉ።

ከዚህ ወደ ፊት ያለው ጉዳይ ልማት፣ ዴሞክራስያዊ አስተሳሰብና ተግባር በማፋጠን የሚወሰን ነው። ህብረተሰቡን ቅር ያሰኙት የአፈፃፀም ችግሮች ናቸው። የመስመር ችግሮች አይደሉም። እንዲሁም ህብረተሰቡ ቅሬታ ውስጥ የከተቱት የሀሳብ ጉድለቶች አይደሉም፤ የአፈፃፀም ጉድለቶች ናቸው። ስለዚህ እኛ መፍትሄ ያልነው ህብረተሰቡን ቅር ያሰኙ ችግሮች በሙሉ ፈልፍለን እና ለቅመን በመፍታት በህብረተሰቡና በድርጅታችን ብአዴን/ኢህአዴግ መካከል ያለው ድልድይ መጠገንና ማደስ የሚል ነው።

ከዚህ በመነሳት በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ ቀይሰን እየሰራን ነን። በብአዴን ደረጃ “በጥልቀት በመታደስ ክልላዊ እና አገራዊ ህዳሴያችን እናፋጥናለን” በሚል መሪ ሀሳብ ነው የንቅናቄ መድረክ ከፍተን ድርጅቱ በተዋረድ ህብረተሰቡን እያሳተፈ እያደሰ ያለው። ምክንያቱም መፍትሄ ያልነው ይህ ስለሆነ። ከዚህ አኳያ እንደ ችግር የለየናቸው አምስት ዋና ዋና ጉዳዮች አሉ። እነዚህ እስከ አምስቱ ተላላፊ እና ገዳይ ፖለቲካዊ በሽታዎች ብለን ነው የምንጠራቸው። ከእነዚህ ፖለቲካዊ በሽታዎች የአስተሳሰብ መዛነፍ አንዱ ነው። ልማታዊ እና ዴሞክራስያዊ መስመር ኣለ። ያንን የተሰመረ የልማት እና የዴሞክራሲ መስመር በትክክል ተግባራዊ አለማድረግ የሚለው አንደኛው ያስቀመጥነው ነው። ሁለተኛው ችግር ብለን የለየነው የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር ነው። በዚህ ዙርያ ብዙ የተለዩ ሁኔታዎች አሉ። የምንኖርበት ሁኔታ በጥረቱና ልፋቱ ጥሮ ግሮ ከማደግ በአቋራጭ የመክበር፣ ከባለ ስልጣን ጋር ተጠግቶ የማደግ፣ በትስስር የመበልፀግ፣ በትስስር የመጠቃቀም ሁኔታ ስለሆነ ይሄን የሚቀይር ትክክለኛ አማራጭ መፍጠር አለብን ብለናል።

በመሆኑም እስካሁንም የሰራነው ስራ አለ፤ ግን የበለጠ እዚህ ላይ ለውጥ ማምጣት አለብን የሚል ነው። ሶስተኛው እንደችግር የለየነው እና መረባረብ አለብን ያልነው የህዝብን አንገብጋቢ ችግሮች ነቅሶ የመፍታት ነው። ቅድም የተዘረዘሩትን የግብርና እና የኢንዳስትሪ ምርታማነት፣ የመሰረተ ልማት፣ የማህበራዊ ልማት ጥራትና ተደራሽነት፣ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች የዴሞክራሲ ጉዳዮች የመሳሰሉት በአግባቡ ለይተን መፍታት ብለን ያስቀመጥነው አለ። ስለዚህ እነዚህን ድርቅ በሚያጠቃቸው አከባቢዎች፣ ዝናብ በተሻለ የሚያገኙ አከባቢዎች ብለን ምርታማነትን የማሻሻል፣ የስራ አጥነት ችግርን የመፍታት፣ የመልካም አስተዳደር ማስፈን ማተኮር አለብን ብለን ይዘናል። አራተኛው ዴሞክራስን የማስፋት እና የማጥለቅ ጉዳይ ነው። ዴሞክራሲ ወደ ህብረተሰቡ እንዲሰፋና እንዲጠናከር ማድረግ ነው። ዴሞክራሲ በውስጠ ድርጅት ደረጃ የተመለከትነው እንደሆነ ከህብረተሰቡ የጠቅላላ የዴሞክራሲ ፍላጎት ሲታይ እንደ ሰርቶ ማሳያ የሚወሰድ ነው። የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ እንደ ሰርቶ ማሳያ ሁኖ ሲያበቃ ግን በውስጠ ድርጅት ብቻ ታጥሮ ዴሞክራሲው ከቀረ ዋጋ የለውም። መላ ህብረተሰቡ ደርሶ ሊያሰፋውና ሊያበለፅገው ሲችል ነው ዘላቂነት የሚኖረው።

ስለዚህ በዚህ ዙርያ የሚታዩ የፀረ- ዴሞክራሲ እና በተፅእኖ የማሰራት የመሳሰሉት ህዝቡን የሚያስቀይሙ መጥፎ ተግባራት መወገድ አለባቸው ብለን በዛ ዙርያ እየሰራን ነው። ሌላው አፅንኦት ሰጥተን መወገድ አለበትና ትግል ማካሄድ አለበት ብለን እየሰራነው ያለነው ለአብሮነታችን፣ ለዴሞክራስያዊ አንድነታችን እንቅፋት የሆኑ የትምክህትና የጠባብነት በተወሰነ ደረጃ በአንድ አንድ አካባቢዎች የጎጠኝነት እና የአክራሪነት ሀይማኖት ሽፋን እያደረጉ አክራሪነት እና መሰል ኋላቀር አስተሳሰቦች ለአብሮነታችን እና ለአንድነታችን እንቅፋት ናቸው። ሲጀመር ቀድመው የሚጎዱት ሰፊው የአማራ ህዝብ ነው። በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ ብሄር፣ ብሄረሰቦች ነው የሚጎዱት። ቀጥለው ደግሞ ወደ ሌሎች ህዝቦች የመሸጋገር ችግር አለባቸው። እዚህ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት አለብን። ይህም ሁሉም ለማድረግ የጠቀስኳቸውን አምስት ዋና ዋና ችግሮች በዘለቄታው ለመፍታት የአስተሳሰብ ችግርን፣ ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣ ከህዝብ ችግር አፈታት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከፀረ-ዴሞክራሲ ጋር የተያያዙ የተለዩ መፍታት ያለባቸው ጉዳዮች እንዲሁም አብሮነታችን የሚፈታተኑ የትምክህትና ኋላቀር አስተሳሰቦች በድምሩ ከአመራር አኳያ ሲታይ የስልጣን አያያዝና አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ነው።

ሀላፊነትን ለህዝብ ኑሮ መለወጫ አድርጎ ከማየት ይልቅ የኑሮ መሰረት አድርጎ በዛ ዙርያ የመሄድ ጋር የተያያዙ መንስኤዎች እንደሆኑ ተለይተዋል። እነዚህን በቋሚነትና በቀጣይነት በመዋጋት ዴሞክራስያዊ አንድነታችንን የሚያጠናክር ሁሉን አቀፍ ርብርብ እናደርጋለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው። በዚህ ረገድ ባለፉት አራት ወራት በተካሄደው ሰፊ ንቅናቄ ብዙ የመጡ ማሻሻሎች አሉት። ይህንን አጠናክረን ወደ ፊት እንራመዳለን ብለን ነው እየሄድን ያለነው።

ወይን፡- በኢህአዴግ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የ15 አመት ግምገማ (ተሃድሶ) ተከትሎ ብአዴን እንደ አንድ የኢህአዴግ አባል ድርጅት እንዴት ራሱ ገመገመ? በተፈለገው አቅጣጫ ውስጡን አይቷል ብለው ያምናሉ?

አቶ አለምነው፡- ቅድም እንደጠቀስኩት በብአዴን ሁኔታ የኢህአዴግን የግምገማ ሀሳብ መሰረት በማድረግ “በጥልቀት በመታደስ ክልላዊ እና ሃገራዊ ህዳሴያችን እናፋጥን” በሚል መሪ ሀሳብ ላይ ተመስርቶ ሰፋፊ የአስተሳሰብ ትግሎች ኣካሂዷል። በመጀመሪያ ያደረገው በኢህአዴግ የተዘጋጀውን በጥልቀት የመታደስ የንቅናቄ ሰነድ መሰረት በማድረግ በብአዴንና በአማራ ክልል ሁኔታ ሰነዱን በአግባቡ የማዘጋጀት ሁኔታና ገምግሞ ስምምነት ላይ የመድረስ ጉዳይ ነው።

በዚሁ ሰነድ እንደየአግባብነቱ እየተስተካከለ እስከ መላ ህዝቡ እንዲደርስ ተደርጓል። ይህ ማለት ለክልል አመራሩ፣ ለማእከላዊ ኮሚቴው እና ከፍተኛ አመራር፣ ለመካከለኛ አመራር፣ ለታችኛው አመራር እና ለጀማሪ አመራር፣ ለመላ አባላት፣ ብሎም ለገጠርና ለከተማ ህዝብ፣ ለመንግስት ሰራተኛው እና ለመሳሰሉት በዚህ የንቅናቄና በጥልቀት የመታደስ ሰነድ ላይ ተመስርቶ ሰፊ የውይይት መድረኮች አከሂደዋል። የሰነዱ ጭብጥ አንደኛ ባለፉት 25 አመታት በተለይም ደግሞ ላለፉት 15 ኣመታት የመጡ ለውጦች ይገመግማል። ይሄ ጉድለቶቹ ለማየት እንደ መስፈንጠርያ አቅም ሁኖ እንዲያገለግል ታስቦ የተደራጀ ነው።

ሁለተኛው ድክመቶቹና የድክመቶቹን መንስኤዎች ምንድን ናቸው? የሚለውን ቅድም መንስኤውን ይዳስሳል። ሶስተኛው ከዚህ በመነሳት ወደ ፊት ምን ይፈልጋል? የሚለውን የሚመለከትና በዛ ላይ በየደረጃው ያሉ ተሳታፊዎች ተጨማሪ ሀሳብ የሚሰጡበትና በቀረበው ጭብጥ ላይ የላቀ መግባባት በሚደርሱበት ሁኔታ የተደራጀ ነው የነበረው። በዚህ ላይ ብዙ ርቀት ሂደናል። ሆኖም ግን ሙሉ በሙሉ ችግሮች፣ አስተሳሰቦቹ ተፈቷል ብለን አላየንም። ግን ብዙ ርቀት ተጉዘናል ብለን አይተናል።

የመጀመሪያው ይሄ ነው የነበረው። ከዚህ ቀጥሎ በየደረጃው እንደገና የአካል ግምገማ ለምሳሌ የማእከላዊ ኮሚቴ የአካል ግምገማ፣ የከፍተኛ አመራር የአካል ግምገማ ወዘተ እያለ ከጠቅላላ ሰነዱ ተነስቶ በድክመትና ጥንካሬ በተለይም ደግሞ ድክመቶች ላይ በማተኮር ድክመቶችና የድክመቶቹ ምንጮች ላይ በማተኮር የአካል ግምገማ ሂስና ግለ ሂስ በማካሄድ በዛ ላይ ተመስርቶ ውሳኔ የመስጠት ተግባራት ተከናውነዋል። በዚህ መሰረት የተሰጡት ውሳኔዎች በሂስ ከማለፍ ጀምሮ የማስጠንቀቂያ፣ ከደረጃ የማውረድ፣ ከሀላፊነት የማንሳት፣ በሙስና እና በተለያዩ ጥፋቶች የሚጠረጠሩ ካሉ ደግሞ ወደዛ የመውሰድ ጭምር በሚያካልል ነው እየተካሄደ ያለው።

በዚህ ሂደት እስካሁን ባለፍንበት ጉዞ በአጠቃላይ ሲወሰድ በክልል ደረጃ 55 በመቶ የሚሆኑ የካቢኔ አባላት በአዲስ ካቢኔ አባላት እንዲተኩ ተደርጓል። በዞን ደረጃ እስከ 44 በመቶ የሚሆኑ የካቢኔ አባላት በአዲስ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል። በወረዳ ደረጃ ደግሞ እስከ 47 በመቶ የሚደርሱ አመራሮች በአዳዲስ አመራሮች የተተኩበት ሁኔታ ነው የታየው። በዚህ ደረጃ ችግሮችን በመፈተሽ የማስተካከል፣ ለውጥ የማምጣት፣ በአዲስ መልክ፣ በአዲስ መንፈስ አሻሽሎ የመሄድ ሁኔታዎች ናቸው የተሰሩት ማለት ነው። ይሄም ሁኖ የተደረጉ ማሻሻዎች በዚህ ሳይወሰኑ ህዝብን አስተያየት እንዲሰጥባቸው መሪዎች አንዱን አንስቶ ሌላው በመቀየር ሳይሆን በሂደቱ ህብረተሰቡ እንዲሳተፍበት አስተያየት እንዲሰጥበት፣ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ እየተከራከሩ መቀጠል የሌለባቸው እንዳይቀጥሉ መቀጠል ያለባቸው እንዲቀጥሉ የማድረግ ስራ ነው የተሰራው። በሂደቱ እኛ ትኩረት የሰጠነው በጥልቀት መታደስ ሲባል ድርጅቱን በድምር ተጠናክሮ እንዲወጣ የማድረግ አቅጣጫ ነው እንጂ በልዩነትና የድርጅቱን አቅም በመከፋፈልም ሊፈታ ይችላል።

ይሄኛው መንገድ እኛው አልመረጥነውም። ምክንያቱም ሰው ድክመቱን እስካየ ድረስ፣ በወሳኝነት በጥፋቱ እስከ ተፀፀተ ድረስ፣ የጎላ ወንጀል ካልፈፀመ፣ አሻሽሎ ወይም ዝቅ ባለ ደረጃ ወይም ባለበት የሚቀጥልበት ሁኔታ ነው ያየነው። በአጠቃላይ ሂደቱ ድርጅቱን አጠናክሮ እንዲወጣ ነው እንጂ ሌላ ቁርሾ እና ሌላ ንትርክ በሚፈጥር እንዳይሆን ብርቱ ጥንቃቄ ተደርጓል።

ስለዚህ በእኛ አተያይ በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄው በሂደት ላይ ቢሆንም እስካሁን ባለፍንበት ሂደት እንደኛ በችግሮቹና በመፍትሄ ቀመሮቹ ላይ ጥሩ መግባባት ፈጥሯል። ይሄ ደግሞ አንድ ጥቅም ነው። በዚህ መሰረት ድርጅቱን አንዣብቦበት ከነበረው የመናጋት አደጋ አትርፎ አጠናክሮ በተሻለ ቁመና አመራር ሊሰጥ በሚችልበት ሁኔታ ላይ አደራጅቶታል። ስለሆነም የችግሮቹ አደጋዎች በብቃት መፍትሄ ካልሰጠናቸው በስተቀር ችግሮቹ ተመልሰው ሊወጡ እንደሚችሉና ከዚህ አደጋ ለመውጣት ጠንክረን መስራት እንዳለብን መነሻ መግባባት ተፈጥሯል። ይሄ በሂደት የሚዳብር መሆን አለበት። ይሄ ብቻ ሳይሆን፤ በኪራይ ሰብሳቢነት በአስተሳሰብና በተግባር በምን ደረጃ ላይ ነው ያለው የሚለውን ለመረዳትና የመፍትሄ እርምጃዎች ለመውሰድም የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል። ስለዚህ በብዙ መገለጫዎች ወደ ፊት የሚያራምድ ሁኔታ ፈጥሯል። እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ጠንክረን ካልሰራን የማይቀለበስ አይደለም። ምክንያቱም የተጀመረው ንቅናቄ ወደ ኋላ ሊመለስ ይችላል። ስለዚህ እንዳይመለስ አሁን በተግባርና በልማት፣ በዴሞክራስያዊ ተግባራት፣ በመልካም አስተዳደር መሰረት አድርገን ችግሮቹን እየፈታን የበለጠ እያጠናከርን እንሄዳለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው።

ወይን፡- ከተሃድሶ በፊት እና በኋላ ብአዴን ያለው ሁኔታ እንዴት ተገመገመ? ውጤቱስ ምን ይመስላል? የተካሄደውን የተሃድሶ መድረክ ተከትሎ በጠቅላላ ህዝቡ፣ አባሉና አመራሩ የተፈጠረውን ስሜት እንዴት ይገልፁታል?

አቶ አለምነው፡- እስካሁን በቆየንበት ሂደት ስናይ ከሞላ ጎደል በውስጠ ድርጅቱ ታጥሮ የቆየ ነው። ህብረተሰቡ ሙሉ ይዘቱን እስከ ቅርብ ጊዜ ሰነዱ አልቀረበበትም ነበር። ግን በተለያዩ መገናኛ ብዙኋን እና በተለያዩ መድረኮች በሚያዳምጠው፣ ድርጅቱ የጠፋውን ጥፋት ለማስተካከል ራሱ ወደ ውስጥ እያየ እንደሆነ ግንዛቤ ነበረው። ያልተሟላ መረጃም ቢሆን የሚገነዘባቸው ጉዳዮች ነበሩ። በዚህ ጉዳይ የበለጠ ግልፅ የሆነለት አሁን ነው። አሁን ወደ ህብረተሰብ እየቀረበ ነው። ወደታች እየቀረበ ለአስተያየት ክፍት እየሆነ ነው።

እስካሁን ባለው ሁኔታ ሲታይም “ድርጅቱ ወደ ቀድሞው ይዞታው እየመጣ ነው” የሚል አዝማሚያዎች እየመጡ ናቸው። ሆኖም ግን ሙሉ በሙሉ ወደዛ ደርሷል ማለት አይቻልም። በአጠቃላይ ሲታይ ብአዴን ወደ ድሮ ይዞታው እየመጣ ነው። ምክንያቱም መሪዎችን ቀርበውልን ከገመገምን፣ የማንስማማባቸው መሪዎች ከተቀየሩ፣ ጥሩ መሪዎች ካገኘን ይሄ አንዱን የሚያስማማን መሰረታዊ ጉዳይ መጣ የሚል ተስፋ የማሳደር ሁኔታዎች አሉ፡፡

ይሄ ግን የበለጠ ሊጠናከር የሚችለው በተጨባጭ ተግባር ሲደገፍ ነው። ዞሮ ዞሮ ህብረተሰብ የሚለካው ተጨባጭ ወደ ግል ሂወቱና ወደ አከባቢው ልማት ባመጣው ነገር ነው። ስለዚህ ለውጡን የሚለካው በግል ሂወቴ ምን ለውጥ መጣ? በአከባቢው ልማት ምን ለውጥ መጣ? ብሎ ነው የሚለካው። በዚህ መለኪያ ሲታይ ገና ብዙ መስራት ይጠይቃል። ገና ወደ ስራ እንገባለን ያለነው አሁን ነው። የበለጠ መተማመኑ ከዚህ በኋላ ባለው ሂደት ሊመጣ የሚችል ነው። እስካሁን በመጣንበት ርቀት ግን ይሄ ድርጅት ታድሶ ወደ ተሻለ ቁመናው ይመጣል የሚል ተስፋ ማሳደር እየጀመረ እንዳለ ነው።

ወይን፡- በክልሉ በትምክህተኞች የተከሰተውን ህገ ወጥ ድርጊት ለማስቆምና ህዝቡ በተረጋጋ ሁኔታ ልማቱን እንዲያካሂድ ታስቦ የወጣው አስቸኳይ የጊዜ አዋጅ እንዴት እየተተገበረ ነው? በተለይም በዚህ ህገ ወጥ ድርጊት የተሳተፉ እና የመሩ ሰዎች በህግ ስር ለመዋል ምን ተሰርቷል? ውጤቱስ?

አቶ አለምነው፡- በእኛ እምነት እንደ ብአዴን ትልቁ ማረጋጋት አስተዋፅኦ አደረገ የምንለው የተጀመረው የተሃድሶ ንቅናቄ ነው። ዋናው ይሄ በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ የሚለው ነው። ይሄ እንደተጠበቀ ሁኖ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደግሞ የማይተካ ሚና ተጫውቷል ብለን እናምናለን። እነዚህን ተደጋግፈው ያመጡት መረጋጋት ነው ብለን እናምናለን። ይህንን ታሳቢ አድርገን እስካሁን ወደ ሁለት ነጥብ አራት ሚልዮን ህዝብ ኣከባቢ በገጠር በከተማ በአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ላይ ውይይት አድርጓል። በአጠቃላይ ድምዳሜው ሲታይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል፣ ሰላም አረጋግቷል፣ የልማት እንቅስቃሴ እንዲጀመር አድርጓል፣ ሰዎች በተረጋጋና በሰከነ ሁኔታ የዕለት ተዕለት ሂወታቸው እንዲመሩ ዕድል ፈጥሯል። ስለዚህ ይሄ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የሚል አስተሳሰብ አለ። በሌላ በኩል ደግሞ የሚያሳስቡት ነገሮች አሉ። በዚህ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አድርጎ የቂም በቀል መወጣጫ እና መጠቃቅያ እንዳይሆን፣ ሰዎች በድብቁ እየጠቆሙ የግል ቅሬታቸውን የሚገልፁበት እንዳይሆን ጥንቃቄ ይደረግ የሚል የጥንቃቄ ሀሳብ አምጥቷል።

ይሄ ሁሉ ሁኖ ግን በድምሩ ሲታይ በክልሉ በፊትም የተረጋጋ አካባቢ የበለጠ መረጋጋትና ጥንካሬ እንዲኖራቸው አስችለዋል። ከዚህ ባለፈ አንድ አንድ ሁከት እና ግርግር የነበረባቸው አካባቢዎች ደግሞ ሁከት እና ግርግር አቁሞ የተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖር ህገ ወጦችን ህብረተሰቡ ባደረገው ትግል ወደ ህግ እየቀረቡ እንዲታረሙ እና መደበኛ የልማት፣ የሰላም፣ የዴሞክራሲ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅም የፈጠረ ነው። ከዚህ በበለጠ ለማጠናከር ደግሞ በጥልቀት ከመታደስ ንቅናቄው ጋር አስተሳስረን በላቀ ደረጃ ወደ ፊት እንወስዳለን ብለን እየሰራን ነው።

ወይን፡- በህገ ወጥ ስራዎች የተሳተፉ ሰዎች እና አመራሮች በቁጥጥር ስር ለማዋል የህዝቡ ተሳትፎ እንዴት ይገልፃል?

አቶ አለምነው፡- በመጀመሪያ አካባቢ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዝርዝር ይዞታና ሀሳብ እስኪረዳ ድረስ ጉዳዩን ለመረዳት ጊዜ የመውሰድ ሁኔታ ነበረ። እኛም በጥልቀት መታደስ ላይ አተኩረን ስለነበረ ፈጥነን አላወያየነውም። እዛ ላይ የተወሰነ ግር የማለት ወይም ግራ የመጋባት ነገር ነበረ። ከዚህ የተነሳ የህብረተሰቡ የራሱ ሚና ምን መሆን እንዳለበት በብቃት አልተሰራም ነበር። በኋላ ወደ ህዝቡ እየወረድን የሚጠበቅብንን እየሰራን ስንሄድ መጀመሪያ ራሱን የበለጠ የሰላም ፣ የልማት፣ የዴሞክራሲ ሀይል አድርጎ አጠናክሮ የመሰለፍ ሲጀምር ራሱን አሻሽሎ የመሰለፍ ሁኔታ ነው የነበረው። በዚህ ሳይወሰን ግን ከዛ ቀጥሎ ያደረገው ጥፋትን የመጠቆም እና ጥፋተኞች እንዲጠየቁም ድጋፍ እንደሚሰጥ የመግለፅ ሁኔታ አለ። እዚህ ላይ ሲገለፅ ግን ከጥንቃቄ ጋር ነው። ያለ ስራቸውና ያለ ጥፋታቸው የሚጠየቁ ሰዎች እንዳይኖሩ ጥንቃቄ ይደረግ የሚለውንም በደንብ ያሰምርበታል። ስለዚህ ህብረተሰቡ ውስጥ በድምሩ ያለው ሁኔታ ሰላማዊ ሁኔታው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይፈልጋል። እንዲሁም ህገ ወጦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ይፈልጋል። ይሄ እንደተጠበቀ ሁኖ ሂደቱ በመጠቃቃትና ቂመኝነት ያለው እንዳይሆን ጥንቃቄ እንዲደረግ ደግሞ ያሳስባል።

ወይን፡- ሌላው የወልቃይት ጉዳይ ነው “ወልቃይት የአማራ ነው” የሚሉ የተወሰኑ ግለሶቦች አሉ። ደጋግመው ጥያቄዎች ሲያነሱም ይሰማሉ። ጥያቄው ማንሳት ያለበት ግን የወልቃይት ህዝብ ኣይደለም? ይሄ እንደ ብአዴን አመራርና የብአዴን /ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዴት ያዩቷል? እንደ ድርጅት ስንመለከትስ ለምን ዘላቂ መፍትሄ አላስቀመጠም?

አቶ አለምነው፡- በዚህ ጉዳይ ብአዴን ከምስረታው ጀምሮ ግልፅ አቋም ኣለው። በወልቃይት ወይም የሆነ አካባቢ ብሎ ሳይሆን አጠቃላይ የብአዴን አቋም ምንድ ነው? ህዝቦችን ማንነታቸው የብሄር፣ ቋንቋ፣ የባህል፣ የስነ-ልቦና ማንነታቸው ተከብሮ፣ በመከባበር ላይ የተመሰረተ ዴሞክራስያዊ አንድነት መኖር አለበት የሚል ከምስረታው ጀምሮ ፅኑ አቋም ይዞ የታገለበት ነው። ድርጅቱ አሁን 36ኛ አመቱ አክብሯል፤ ባለፈባቸው ጉዞዎች ውስጥ የድርጅቱ አቋም ይሄ ነው። በቅርቡ በወልቃይት የማንነት ጥያቄ ተነሳ በተባለበት ወቅት የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የካቲት 2008 ዓ/ም ተሰብስቦ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጉዳይ ላይ ምንድ ነው ያለን ሀሳብ? ይሄ ጥያቄ እየተነሳ ነው የሚለው ከማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሲነሳ ጉዳዩን የበለጠ ግልፅ አድርጎ አቋም ወስዷል። አቋሙ የባለፉት 36 አመታት አቋሙን የሚያጠናክር ነው የነበረው። የወሰደው አቋም የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ካነሳ በሚተዳደርበት ክልል ከአካባቢው ጀምሮ በተዋረድ ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በሚፈቅደው አኳኃን ጥያቄ ማንሳት ይችላል። በዚህ መሰረት ህገ መንግስቱ መፍትሄ ይሰጧል። ብአዴን ክልላዊ ድርጅት ነው። የአማራ ክልል ህዝቦችን የሚያንቀሳቅስ ድርጅት ነው። ስለሆነም በዚህ ጉዳይ ቀጥታ ተሳትፎ የለውም። በወልቃይት ውስጥ ገብቶ ቀጥተኛ ተሳትፎ ሊያደርግ አይችልም። በአገር ደረጃ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በመሳሰሉት ጉዳዩ ከተነሳ እንደ አንድ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ከመርሁ ተነስቶ አቋም ሊይዝ ይችላል።

ከዛ ውጭ ግን ይሄ ጉዳይ በህወሓትና በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ነው የሚፈታው ብሎ ያለ ልዩነት በሙሉ ድምፅ ነው ማእከላዊ ኮሚቴው የወሰነው። ይህ ማለት የባለፉት 36 ኣመታት አቋሙ በ2008 ዓ/ም የካቲት ላይም ተደግሟል ማለት ነው። ይሄን አቋም ይዞ ነው ሲሰራ የቆየው። ይህ እንደተጠበቀ ሁኖ ግን ጉዳዩን በአጠቃላይ ቅድም እንደጠቀስኩት በእኛ አካባቢ ህብረተሰቡ ቅር የተሰኘባቸው የስራ አጥነት ችግሮች የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከመበራከታቸው የተነሳ የተለያዩ ሰበቦች ይፈለጉ ስለነበር የወልቃይት የማንነት ጥያቄም በእኛ አካባቢ አንድ የሁከትና ግርግር መነሻ ምክንያት ሁኖ አገልግሏል። ይሄም ሁኖ ግን የጥፋት ሀይሎቹ ሁሉንም ጉዳዮች ወደ ላቀ ከፍታ ወስደው የማጋጨትና ህዝብን ከህዝብ የማነታረክ አላማ ስለነበራቸው ያንን አላማ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ማሳካት ችለዋል። አሁን አሁን ጉዳዩ ግልፅ እየሆነ ነው ያለው።

አሁን በጥልቀት መታደስ ንቅናቄው ላይ የበለጠ ፍንትው ያለው ነገር ምንድ ነው? በ2008 ዓ.ም የካቲት ላይ ብአዴን የወሰነው ውሳኔ በኋላም በተሃድሶ መድረክ በግልፅ የተቀመጠ ጉዳይ ነው። ያ ማለት የወልቃይት አካባቢ ህዝብ ጥያቄ ካለው ጥያቄዎችን በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሊያቀርብ ይችላል። የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ይህንን የመመለስ አቅምም ችሎታውም አለዉ። ብአዴን በዚህ በኩል ቀጥተኛ ተሳትፎና ሚና የለውም። በአማራ ክልል ሁኔታም ቢሆን ቀጥተኛ የሆነ ሚና የለውም። ይሄ ህገ መንግስቱ እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱ መሰረት ያደረገ ጉዳይ ነው ብለን ነው ለህብረተሰቡ እያስረዳን ያለነው። አሁን ሁኔታውን የመረዳት ሁኔታ አለ። ይሄ ጉዳይ የበለጠ ወደ ጥፋት የሚጎትቱ ሀይሎች የሉም እያልኩ አይደለም፤ አሉ። ግን በአብዛኛው ጉዳዩን ህብረተሰቡ እየተገነዘበው ያለ ጉዳይ ነው። የብአዴን አቋም ደግሞ በዝርዝር የገለፅኩት አቋም ነው።

ወይን፡- የግጨው ሁኔታስ እንዴት ነው? ለምን እስካሁን ሁለቱም ድርጅቶች ተወያይተው ዘላቂ መፍትሄ አላስቀመጡለትም?

አቶ አለምነው፡- የአማራ ጠገዴ እና የትግራይ ፀገዴ ኩታ ገጠም ያሉ አካባቢዎች ጉዳይ ከመጀመሪያው ጉዳዩ መዘግየት አልነበረበትም። ጉዳዩን የሚነሳ መሆን አልነበረበትም ኣይባልም። ሊነሳ የሚችል ነው የነበረው። በየቦታው የወሰን የመሳሰሉት ጥያቄዎች በብዛት አሉ። ዋናው እዚህ ላይ እኛ እንደ ጉድለት የምናየው ጊዜ መውሰድ አልነበረበትም። አፈታቱ ጊዜ መውሰድ አልነበረበትም። ለምንድነው ጊዜ የወሰደው? የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው። ይሄ ችግር ጊዜ የወሰደበት ዋነኛ ምክንያት በሁለታችን እህት ድርጅቶች ውስጥ የአስተሳሰብ መዛነፍ አጋጥመዋል። ከዚህ በመነሳት የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ እና ተግባር ውስጥ የመግባት ሁኔታ ታይቷል። እዚህ ላይ የህዝብን አንገብጋቢ ችግሮችን ሳይፈቱ በትንንሽ አጀንዳዎች ችግር ፈች መስለው መታየት አመለካከት ነበረ። ከዚህ አልፎም የትምክህት አስተሳሰብና ተግባር በየደረጃው ያለው አመራር ተስተውሏል። ስለዚህ ይሄ ችግር ከመኖሩ ተያይዞ የወሰኑ ጉዳይ በአማራ ጠገዴ እና በትግራይ ፀገዴ መካከል ያለውን የወሰን ጉዳይ አንደኛው ከአቅሙና ከደረጃው በላይ አጋኖ የመረዳት ጉዳይ ነው።

ይሄ በሁለት ጠባብ አካባቢዎች ያለው የወሰን ጉዳይ ነው። ስለሆነ ጤናማ አስተሳሰብ ቢኖር ኑሮ በቀላሉ ሊፈታ የሚችል ነው። ነገር ግን የአስተሳሰብ መዛነፍ ስላለ ከአቅሙና ከደረጃው በላይ ተጋኖ እንዲታይ አድርጓል። ሁለተኛው ሌላ ትልልቅ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራ ሞልቶ ይሄ ጉዳይ ከሚገባው ጊዜና ቦታ የወሰደ አስተሳሰብ መዛነፍ ስላለ በዚህ ጉዳይ አልባሌ ጊዜ ማሳለፍ ታይቷል። ስለዚህ አሁን ጉዳዩ በአጭር ጊዜ መፈታት አለበት።

ምክንያቱም ዞሮ ዞሮ መሬቱ ያለው ከሁለቱም ህዝቦች የሚያልፍ አይደለም። እዛ ኩታ ገጠም ብቻ ያሉት ህዝቦች የሚጠቀሙበት ነው። እና ይሄ ሁሉ በአስተሳሰብ እና በአተገባበር ብልሽት የተፈጠረ ነው። በዚህ ምክንያት ከልክ በላይ ተጓትቷል። ህብረተሰቡም አመራሩ የተዛባ አስተሳሰብ በያዘ ቁጥር ትልቅ ነገር ያለ መስሎት በዛው ልክ ቀላል ያልሆነ ቁጥር ያለው ሰው የተደናገረበት ሁኔታ ታይቷል። አሁን እየሰራነው ያለነው ምንድ ነው? መጀመሪያ በአስተሳሰብ የተበላሸን ነገር እናስተካክል ብለን ለአስተሳሰብ ጊዜ ሰጥተን እየፈታን ነን። ጥሩ ስራ የጥሩ አስተሳሰብ ውጤት ነው። መጥፎ ስራ የመጥፎ አስተሳሰብ ውጤት ነው። ስለዚህ በትግራይ ፀገዴ እና በአማራ ጠገዴ መካከል ያለውን የወሰን ጉዳይ በአስተማማኝነት መፍታት የሚቻለው የተስተካከለ አስተሳሰብ ስያዝ ነው። ይሄን አስተሳሰብ ለመፍጠር የሰውን ትክክለኛ የስነ-ልቦና የማስተካከል ስራ እየሰራን ነን፤ በተሃድሶ መንፈስ። ትክክለኛ አስተሳሰብ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ከያዝን በኋላ በቀጥታ የወሰን ጉዳይ ይፈታል። የወሰን ጉዳይ የሚፈቱት ራሳቸው የሚያርሱት ሰዎች ናቸው። ማሳው ላይ የሚያርሱት ሰዎች ነው የሚፈቱት። ምክንያቱም መሬቱም ጋ ያሉ እነሱ ናቸው፤ አለመግባባትም የተፈጠረው በሁለቱ መሪዎች ነው። ስለዚህ መሪዎቹ በትክክለኛ አስተሳሰብ ውስጥ ከገቡ ችግሩን እየፈቱት ይሄዳሉ ብለን ነው የምናምነው።

ወይን፡- በመጨረሻ ለሁለቱም ህዝቦች እና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝቦች የሚያስተላለፉት መልእክት ካለ

አቶ አለምነው፡- መጀመሪያ ለመላው የትግራይ ህዝብና ለህወሓት ታጋዮች እንኳን ለ42ኛው አመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ! እንኳን አብሮ አደረሰን እላለሁ። አሁን በምንገኝበት ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች በዋናነት በውስጣዊ ምክንያቶች በተደራቢ ደግሞ በውጭ ወይም በጥፋት ሀይሎች አቀነባባሪነት ጣምራ እንቅስቃሴ ለዘመናት በአብሮነት የሚታወቁ ህዝቦች እጅግ የሚያስቀና የጋራ ትግል፣ የጋራ መስዋእትነትና የጋራ ድል ታሪክ ያላቸው ህዝቦች ልያለያይ የሚችል የዘረኝነት አስተሳሰብና ተግባር በጥፋት ሀይሎች ተሰንዝሮ ዕድል አግኝቷል። ነገር ግን ይሄ ጊዚያዊ ችግር ነው እንጂ የማናልፈው ችግር አይደለም። ምክንያቱም ሰፊው የትግራይ እና የአማራ ህዝቦች እጅግ ዘርፈ ብዙ የአብሮነት ታሪክ ያላቸው ህዝቦች ናቸው። መሰረታዊ ጥቅሞቹ በአብሮነት የሚያስቀጥሉ እንጂ የሚያለያዩ አይደሉም። የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ አጀንዳዎቹ የአብሮነት ጉዞ የሚጠይቁ ናቸው።

ስለዚህ የማስተላልፈው መልእክት የጋራ እሴቶቻችንን ጠብቀን የጋራ ጠላቶቻችንን እና ዕንቅፋቶቻችን በመመከት እና በመጥረግ ተባብረን የህዳሴ ጉዟችንን የጋራ ቤታችንን ለማሳካትና ጠላትን ድል ለማንሳት ተባብረን መነቃነቅ አለብን። ስለዚህ ለሁለቱም ህዝቦች በጋራ መስራት አለብን የሚለውን መልእክትን ነው የማስተላልፈው። በመጨረሻ ለአገራችን ህዝቦች ከዘመናት የማሽቆልቆል ጉዞ በኋላ አገራችን የለውጥ ጎዳና ይዛለች። ትልቅ የህዳሴ ፕሮጀክት አለን። ጠቅላላ የለውጥ ጉዟችን የህዳሴ ፕሮጀክት ነው። ይሄ ፕሮጀክት ከተሳካ አገራችን ድሮ ትልቅ ነበረች፤ አንድ ወቅት አሽቆልቁላ ነበረች፤ ትልቅ ትሆናለች። በዚህ ደግሞ ህዝባችን ከድህነትና ኋላቀርነት ወጥቶ፣ ከጉስቁልና ወጥቶ እድገትና ብልፅግና ውስጥ የገባ ህብረተሰብ ይሆናል። ይሄ ሊሆን የሚችለው ሰላም ሲጠበቅ ነው። ይሄ ሊሆን የሚችለው የልማት ጥረታችን ተጠናክሮ ሲቀጥል ነው። ይሄ ሊሆን የሚችለው የዴሞክራሲ ጉዟችን ሲጠልቅና ሲስፋፋ ነው። ይሄ ሊሆን የሚችለው ህዝብና መሪዎች እጅና ጓንት ሆነው የመልካም አስተዳደር ችግር ሲፈቱ ነው። ስለሆነም የመጀመርነው የለውጥ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ እንቅፋት እንዳይገጥመው እጅ ለእጅ ተያይዘን መልካም ሁኔታዎችን እንድናጠናክር፣ እንቅፋቶችን ደግሞ ተባብረን እንድናስወግድና የህዳሴው ጉዞ እንድናፋጥን ነው ጥሪየን ማስተላለፍ የምፈልገው።

ወይን፦ ዘርዘር ያለ እና ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ማብራሪያ ስለሰጡን እናመሰግናለን።

አቶ አለምነው፦ እኔም ለተሰጠኝ ዕድል አመሰግናለሁ!

Source – hornaffairs.com

 


የአድዋ ድል የቀለም ትርጓሜ እና  በአምስቱ ዓመት ጦርነት ውስጥ በውጪ የነበረው እንቅስቃሴ – ከዓለሙ ተበጀ

$
0
0

ለኢትዮጵያ እነማን ምን ዋሉባት ወይም ዋሉላት?

ከዓለሙ ተበጀ

ከ1928 እስከ 1933 ባለው ጊዜ ኢትዮጵያ ከጣሊያን ወረራ ጋይል ጋር ያካሄደችው ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የቀለም ፍትጊያ በግልጽ አፍጥጦ እንዲያይ አድርጓል። ቀድሞውኑም አድዋን ትከትሎ ዋናዎቹ የአውሮፓ መንግስታት የነጭ ሃይል በጥቁር ሕዝብ የደረሰበት ሽንፈት አስቆጭቷቸውና በነሱም ቅኝ ተገዥዎች ላይ የሚያስከትለው መነሳሳት አስግቷቸው ከተሸናፊዋ ጣልያን ጎን ቆመዋል።

ዶ/ር ሹመት ሲሻኝ እንደገለጹት፣ ጣሊያን የጦር ኋይሏንና መሳሪያዎቿን ታግዝባቸው ዘንድ በእንፋሎት የሚሰሩ መርከቦች ብሪታንያ እረድታለች። ከሰላ ላይ በመሃዲሲቶች ተከቦ የነበረውን 2 ሺህ ገደማ የጣሊያን ሃይል ነጻ ለማድረግም ወታደር ልካለች። የዚህም ዓላማ የመሃዲስቶቹን ሃይል ከጣሊያን ግለል በማድረግ ኢትዮጵያን ዳግመኛ የምትወጋበት ፋታ እንድታገኝ ለማድረግ ነበር። የጀርመን ንጉስም በሃገሩ ወደነበረው የጣሊያን ኢምባሲ በመሄድ በአድዋው ሽንፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል። አንድ የጀርመንን የውጭ ጉዳይ ቢሮ አመለካከት የሚያንፀባርቅ ጋዜጣ  “የአውሮፓ ክብር አፍሪካ ውስጥ ውርደት ደርሶበታል። ይህን ክብር ከመንበሩ ለመመለስም ሌላ ዘመቻ መካሄድ አለበት” በማለት ጽፏል። የወቅቱ የአስትሮ . ህንጋሪያ አጼ ግዛት መንግስትም በደረሰው ሽንፈት መጸጸቱን ጠቅሶ የጣሊያን መንግስት ለ “እናት ሀገር ደህንነት ምንም ስጋት ሳይገባት” የሚያሻውን ያህል ጦር በኢትዮጵያ ላይ ማዝመት እንደምትችል አሳውቋል።

የባቲካኑ “ቅዱሱ” ካቶሊካዊ አባት ሳይቀሩ በጣሊያን ላይ በደረሰው ሽንፈት እጅግ አዝነዋል። በዚህ የተነሳም ለምሳሌ እ. ኤ. አ በመጋቢት 4/ 1996 እለት ሊካሄዱ ይገባቸው የነበሩ ቤተክርስቲያናዊ ስርዓተ ሁነቶች እንዲስተጓጎሉ አዘዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋ የተሻለ ወዳጅነት የነበራት ፈረንሳይም ብትሆን የኢትዮጵያ ድል አስደንግጧታል። አንድ የሃገሪቱ ጋዜጣ “ከአረመኔው ዓለም የውጣ ሃይል ባንድ የስለጠነ ሀገር ላይ ባደረሰው ሽንፈት ፈረንሳይ ተጸጽታለች” ብሏል። አጼ ምኒልክ ለፈረንሳዊው የጅቡቲ ገዥ በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንደጠቀሱት ከአድዋው ጦርነት በኋላ የአውሮፓ መንግስታት በጣሉት ማእቀብ ፈረንሳይም ተባብራለች። በአጠቃላይ በወቅቱ ካውሮፓዊያኑ መንግስታት ኦርቶዶክሳዊቷ ሩሲያ ብቻ ለኢትዮጵያ ወገናዊነትን አሳይታለች። በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ርቀት የዚህን ወገናዊነት ተግባራዊ ጠቀሜታ አሳጣው እንጂ።

ከ40 ዓመት በኋላም ጣሊያን የወታደራዊ ድል ገድል የለሽ ያደረጋትን የአድዋን ቂሙዋን ልትወጣ ፈለገች። ብዙም አልተሳካላት እንጂ ወታደራዊ ዝናዋን ለማድመቅ ተስፋ አድርጋ በአንደኛው የአለም ጦርነት ገብታ ነበር። እ. ኤ. አ በ1922 ሞሶሎኒና የፋሽስት ፓርቲው ስልጣን ላይ ሲወጡ ደግሞ የመስፋፋት በተለይም ኢትዮጵያን ወሮ ለመያዝ ፍላጎቷ ዳግም አገረሸባት እና በ1928 ወረራ አካሄደች።

ከአንደኛው የዓለም ጦርንት በሁዋላ የመንግስታትን ትብብር ለማጠናከርና ሌላ መስል ጦርነትን ለማስቀረት እንዲረዳ ታስቦ የተቋቋመውው የመንግስታቱ ማህበር ልባዊ ሙከራ አድርቶ ቢሆን ኖሮ ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን ከመውረር ድርጊቱ ይታቀብ ነበር የሚሉ አንዳንድ ትንታኞች አሉ። በወቅቱ አሜሪካን የማህበሩ አባል አልነበረችም። በናዚ ሂትለር የምትመራው ጀርመንም አባልነቱዋን ሰርዛ ነበር። ከማሃበሩ አባል መንግስታት ፈርጠም ያለ ጡንቻ የነበራቸው ብሪታ ንያና ፈረንሳይ ደግሞ ሞሶሎኒ ከሂትለር ጋር እንዳያብር የነበራቸው ፍርሃት ኢትየጵያን በተመለከተ በሚቀይሱት ፖሊሲ ላይ ተጸኖ አሳድሯል። ስለዚህም ሁለቱ ዋነኛ የምእራብ አውሮፓ “ዴሞክራሲያዊ” መንግስታት ጣሊያንን ላለማስቀየም ወሰኑ። ቅድሚያ የሰጡትም ከኢትዮጵያ ይልቅ አውሮፓ ነክ ለሆነው የራሳቸው ደህንነት ነው።

ፈረንሳይ እና ብርታንያ ጣልያንን ላለማስቀየም ከወሰዱዋቸው እርምዳዎች አንደኛው ኢትዮጵያ እራሱዋን ለመከላከል የሚያስችል መሳሪያ የመግዛት ጥያቄ ስታቀርብ እምቢ ማለት ነበር። እ.ኤ.አ በ1934 እና 1935 መጀመሪያ ላይ ጣሊያን ኤርትራና ሱማሌ ውስጥ የጦር ሃይልና መሳሪያ ስታክማች፣ አጼ ሃይለሥላሴ በብኩላቸው የጦር መሳሪያ ከአውሮፓ ለመግዛት ሞከሩ። በወቅቱም ቀደም ሲል የተጠቀሱት መንግስታት በሁለቱም ጠብኞች ላይ መሳሪያ ማእቀብ አድርገናል አሉ። በጊዜው ጣሊያን እራሱዋን የማስታጠቅ አቅሙ ያላት በቂ ዝግጅትም ያደረገች መሆኑ በግልጽ እንደመታወቁ ማእቀቡ ያነጻጸረው በኢትዮጵያ ላይ ነው ማለት ይቻላል።

ሁለተኛውን የግማሽ ልብ እርምጃቸውን የውሰዱት ደግሞ ወረራው የተጀመረ ሰሞን ነበር። ይህም የመንግስታቱ ማህበር አባላቱ ከጣሊያን ጋር እንዳይገበያዩ ብዛት ባላቸው ሸቀጣሸቀጦች ላይ የጣለው የንግድ ማእቀብ ነው። 51 መንግስታት ደግፈውት በተላለፈው በዚህ ማእቀብ ዝርዝር ውስጥ ለዘመናዊ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችና ለጣሊያን ወረራ መሳካት የግድ አስፈላጊ የነበሩት የነዳጅ እና የከስል ምርቶች እንዳይካተቱ መደረጉም እርምጃው ከሙሉ ልብ እንዳልነበር ይጠቁማል።

ጣልያንን ለማስደሰት ታስቦ ሶስተኛው እርምጃቸው የተውሰደው ደግሞ በህዳር ወር 1928 ላይ ነው። የብሪታንያው የውጭ ጉዳይ ሴክሬተሪ ሆሪ ፓሪስ ላይ ከፈረንሳዩ አቻቸው ከላቫል ጋር ተነጋግረው በደረሱበት ስምምነት መሰረት በታሪክ “የሆሪ..ላቫል እቅድ” ተብሎ የሚጠቀሰው የማስታረቂያ ሰነድ ተዘጋጀ። እቅዱ ሁለት መሰረታዊ ይዞታዋች ነበሩት። አንደኛው የቦታ ልውውጥ አደላደላቸው ነው። በዚህም መሰረት ከስሜን ምስራቅ የሚበዛው ትግራይን፣ በደቡብ ምስራቅ የኦጋደንና የድንከል በርሃን ጨምሮ 60.000 ስኮዬር ማይልስ ጣልያን ከኢትዮጵያ ስትቀበል በልዋጩ ደግሞ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህርና አሰብ የመተላለፊያ መስመር አክሎ በወራሪዋ ከተያዘባት ኤርትራ 3.000 ስኮየር

ማይልስ እንዲሰጣት ነበር የታሰበው። ሁለተኛ ደግሞ የመንግስታቱ ሊግ በሚነድፈው እቅድ መሰረት በጣሊያን ሹማምንት የሚተዳደር አንድ ሰፊ “የኢኮኖሚ ማስፋፊያና የሰፈራ እቅድ ማካሄጃ” ቀጠና ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ለጣሊያን እንደሚሰጣት መተማመኛ የምታገኝበት ሁነታ እንዲፈጠር ጥሪ ያቀርባል ስነዱ።

በዕቅዱ ላይ ከተመለከተው ትንሹ ክልል /ኤርትራ/ ብቻ በጣሊያን እጅ እንደመሆኑ፣ እና ግማሽ ያህሉ የሃገሪቱ አካል ያለምንም ውጊያ ለእሱዋ እንዲሰጣት እንደማሰባቸው ሆሪና ላቫል ለጣሊያን በጣም ቸር ነው የሆኑት። ሌላው የሚያስገርመው ነገር ደግሞ አካሉዋ ተቆርሶ ሊሰጠው የታሰበችው የኢትዮጵ እሺ ማለት እና የመንግስታቱ ማህበር የመስማማት ጥያቄ ገና ከወዲሁ ያለቅለት ሆኖ መወሰዱ ነበር። አጼ ሃይለስላሴ የሀገራቸውን መክፋፈል በደመነፍስ ይቀበላሉ፣ መኳንንቱን እና የጦር አበጋዞቻቸውንም ሃሳቡን እንዲቀበሉ ያግባባሉ ተብሎ መታሰቡ ደግሞ ይበልጥ የሚገርም ነው። ከተቃወሙም ከዚያ በሁዋላ ከመንግስታቱ ማህበር እርዳታ አገኛለሁ ብለው እንዳያስቡም እንደ ማስጠንቀቂያ ጭምር ነበር እቅዱ። ሃሳቡን ቢቀበሉ ኖሮ ግን ኢትዮጵያ ለበለጠ ጥቃትና ለሰፋ ወረራ መዳረኋን በማጉላት የመንግስታቱ ማህበር የጣሊያንን ሞግዚትነት እንዲቀበለው ነበር የታለመው።

የብሪታንያ ካቢኔ ጊዜ ሰጥቶት እንስከሚነጋገርበት ድረስ እቅዱ በጥብቅ ምስጢራዊ ሆኖ እንዲቆይ ነበር የታሰበው። ሁለቱ ባለስልጣናት ቅዳሜ፣ ህዳር 27/1928 እለት ከስምምነት በደረሱ ማግስት ግን የኢትዮጵያንና የጣሊያንን ውርክብ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት አንድ እርምጃ ስለመወሰዱ የሚያስገነዝብ አጭርና እጅግ ሚስጢራዊ የአንግሎ.-ፈረንሳይ የጋራ መግለጣ ከጋዜጠኞች እጅ ገባ። በቀጣዩ ቀን ጠዋት ላይ ሁለት የፈረንሳይ ጋዜጦች እቅዱን በሚገባ የሚተነትን ጽሁፍ ይዘው ወጡ። ዜናው እንደምን አፈትልኮ ከጋዜጦች እጅ እንደገባ እስካሁንም በደንብ አይታወቅም። ከሰዓት በሁዋላ ደግሞ ዜናው ለለንደን የዜና ምንጮች ደርሰ። የብሪታንያ መንግስትም የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብሎ ሊያልፈው ያልቻለ የህዝብ ተቃውሞ ተፈጠረበት።

በዚህም የተነሳ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ባልድዊን ፕርግራም የያዙበትን በለንደኑ የባህር ሃይል ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ የመገኘት ሃሳባቸውን ሰርዘው ህዳር 29 ቀን 1928 እለት የካቢኔ አባላታቸውን ለስብሰባ ጠሩ። አነጋጋሪ የሆነ የገነፈለ የህዝብ አስተያየት እስካለ ድረስ ለጉዳዩ አንድ እልባት መስጠት የግድ ሆነ። ነገሩን ሁሉ የሩጫ ነበር። ሌላው ቀርቶ የካቢኔ አባላቱ በተሰበሰቡበት ክፍል ውስጥ የኢትዮጵያ ካርታ አልነበረም ይባላል። ይህም እውነት ከሆነ ደግሞ ምን ያህሉ የሀገሪቱ አካል ለጣልያን እንዲተላለፍ እንደታቀደ እንኳን ተጨባጭ ግንዛቤ ሳይኖራቸው ነበር ማለት ነው የካቢኔ አባላቱ በኢትዮጵያ መጭ እድል ላይ የሚነጋገሩት።

የኢትዮጵያ መሪ አጼ ሃይለስላሴም እቅዱን በጥብቅ የተቃውሙት በኦፊሴል  እንዲያውቁት ከመደረጉ በፊት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ባልድዊን ካቢኔያቸውን በሰበሰቡበት እለት፣ ይህን ጠብ አጫሪ የሚሸልም እቅድ እንደማይቀበሉት እና ብሪታንያም በወሰደችው አቁዋም እንዳዘኑ በመግለጽ ንጉሱ የላኩት መልእክት ለብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ደረሰው። በታህሳስ 1/1928 እለትም ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ክቡር አክሊሉ ሃብተወልድ የፈረንሳይን የውጭ ጉዳይ ቢሮ በመጎብኘት ስለ እቅዱ ዝርዝር ማብራሪያ ጠየቁ። ለዜና ዘጋቢዎችም “በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለጣሊያን ጠብ አጫሪነት ሽልማት የሚሰጥ ወይም የመንግስታቱ ማህበር ቀደም ሲል ከስምምነት የደረሰባቸውን መሰረታዊ መርሆዎች በተለይም የኢትዮጵያን ፓለቲካዊና የግዛት አንድነት የሚጻረር..” ምንኛውንም እቅድ በመቃወም አቋሙ የኢትዮጵያ መንግስት የጸና መሆኑን ገለጹ። ከሳምንት በኋላም ማለትም ታህሳስ 8/1928 እለት ንጉሰ ነገስቱ ደሴ ላይ ካቋቋሙት ቤተመንግስታቸው ሆነው ቀደም ሲል የተገለፀውን እቅድ እንደማይቀበሉት ለዘጋቢዎች የመግለፃቸው ዜና የመንግስታቱ ማህበር ከነበረበት ጄኔቭ ከተማ ደረሰ።

በአጠቃላይ የብሪታንያ መንግስት ከፈረንሳይ ጋር በማበር ይህንን መሰል ጣሊያንን አባባይ ፖሊሲ ቢያራምድም የህዝቡ አቋም ባመዛኙ አፍቃሪ..ኢትዮጵያ ነበር ማለት ይቻላል። ይህ ግን መንግስታዊ ያልሆኑ አንዳንድ አካላት ወይም ግለሰቦች የጣሲያንን ወረረራ የሚደግፍ እንቅስቃሴ አላደረጉም ማለት እንዳልሆነ ሊታወስ ይገባል። ለምሳሌ በውቅቱ የኦቨዘርበር እትም አዘጋጅ ጀ.ኤል ጋርቪን “አብስኒያዊያን በነጭ ዘር ላይ ድልን ተቀዳጅተው ቢሆን ኖሮ በጨለማው አህጉርና በሌሎችም አህጉራት መፍትሄ የማይገኝለት ችግር” ይፈጠራል ባይ ነበሩ። የዚሁ አመለካከት ዋና አቀንቃኝ ዘ አርል ኦፍ ማንሰፊልድ “ጣልያን ብትሸነፍ በቀለም ህዝቦች መሃል ረብሻና አመጽን ለማነሳሳት ለሚጥሩት ታላቅ ማበረታቻ ይሆናል፣ በምስራቅ አፍሪካ ይዞታችንም ላይ ከፍተኛ ጥፋት ያስከትላል” በማለት አስጠንቅቀዋል። ለብሪታንያ ክስረትን እንደሚያስከትል የሚያስገነዝብ ንግግር በማድረግም ይከሰሳሉ። በጣሊያን ላይ የኢኮኖሚ ማእቀብ መጣሉም በብሪታንያ ምጣኔ ሃብት /ኢኮኖሚ/ ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤትም በወቅቱ የመነጋገሪያ ርእስ ኖኖ ነበር። ለዚህም ትኩረት ለመሳብና ማእቀቡን ከጣሊያን ላይ ለማስነሳት የሚጥር አንድ “በብሪታንያ ከጣሊያን አቃ አስመጭዎች ማህበር” የሚባል አካል ተቋቁሟል።

የቫቲካኑ ጳጳስ የነበሩት ፒዮስ 11ኛም ያሳሰባቸው የነበረው የኢትዮጵያ መወረር ሳይሆን ወረራው ባይሳካ የሚያስከትለው ውጤት ነበር። በወቅቱም የፈረንሳዩን አምባሳደር ተቀብለው ሲያነጋግሩ እንዲህ ነበር ያሉት፣

“ይህ ጠብ እጅግ እረፍት ነስቶኛል። ኢትዮጵያ እንዲያውም በጠቅላላው ጥቁር አፍሪካ ውስጥ ባሉን ካቶሊካዊ ፍላጎቶቻችን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ካሁኑ ታውቆኛል። ኢትዮጵያ ውስጥ ካቶሊክ ሚሲዮናዊያን ሰላይ ተብለው እየተወነጀሉ ነው። ሁኔታው ኔግሮዎችን በነጮች ላይ ለማነሳሳት ጥቁሮች እየተጠቀሙበት ነው። የጣሊያን መሸነፍ በአፍሪካ የአውሮፓ ቅኝ ግዛቶቻችንን እጣ ፈንታ የሚወስን ይሆናል።”

ወረራው ከመጀመሩ በፊት ነሀሴ፣ 21 ቀን 1927 በአለም አቀፍ የካቶሊካዊያን ነርሶች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ደግሞ፣

“…በፍርደ ገምድል ጦርነት ልናምን አንሻም። በሌላ በኩል ጣሊያን እያሰበችው ያለው ጦርነት ያለማቋረጥ በተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ የግንባር ክልሎችን ደህንነት በማስከበር እራስን ለመከላከል የታለመ፣ በየቀኑ እየጨመረ በመጣው የህዝብ ብዛት የተነሳ አስፈላጊ እየሆነ የመጣ እና ስለዚህም የሀገሪቱን /የጣሊያንን/ ቁሳቂ ደህንነት ለማስጠበቅ ወይም ለመከላከል የሚካሄድ ጣርነት ስለሆነ ፍትሃዊ ነው። በመሆኑም የዚህ አይነቱ ጦርነት እራሱን በራሱ ስለፍትሃዊነቱ ያረጋግጣል ይባላል። በሌላ በኩል ግን አንድ ሃቅ አለ። በዚሁ ልንሸሸው በማንችለው እውነት ላይ ተመርኩዘን ይህ መስፋፋት አስፈላጊ ከሆነ ግንባር ክልሎችን መከላከልና ደህንነታቸውን ማስከበር አስፈላጊ ከሆነ እነኝህ ችግሮች ከጦርነት ይልቅ በሌላ መንገዶች እንዲፈቱ ብቻ ነው የምንሻው።”

ብለዋል። ከሶስት ቀን በሁላ ደግሞ ኦብስርቫቶሬ ሮማኖ ጋዜጣ ላይ “የጳጳሱ አመለካከት ግልጽ ነው። የመስፋፋት አስፈላጊነት ክግምት ውስጥ መግባት ያለበት እንጅ በራሱ መብት አይደለም። በሌላ በኩል ግን ይህ መብት ተግባራዊ ሲሆን የተወሰኑ ገደቦችን ከላበጀና የተወሰነ ዘመናዊነትን ካልተላበሰ ጎጅ ሊሆን ይችላል” የሚለው ጽሁፋቸው ተነቧል። ለካቶሊካዊያን ቀደምት የጦር ወታደሮች ስብስብ ደግሞ ጳጉሜን 2/1927 እለት ባደረጉት ንግግር ለሰላም መስፈን እየጸለዩ አብረውም “የታላቁና የጥሩ ህዝባቸው ተስፋዎች ፍላጎቶችና አስፈላጊ ነገሮች በሌላ ሳይሆን ፍትሃዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተቀባይነት እንደሚያገኙና እንደሚሳኩ” የአላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

የጳጳሱ አቋም በአጽንዖት ሲታይ ውርክቡ ከጦርነት ይልቅ በድርድር አብሮም ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረራ ይዛ ለማግኘት ያለመቻቸውን ጥቅሞች በሚሳኩበት ሁኔታ እንዲፈታ መሆኑ ግልጽ ነው። ዞሮ ዞሮ ግን “ቅዱሱ አባት” ወራሪውን ሃይል አላወገዙም። ወይንም ነህሴ 30 ቀን 1927 ሰላም እንዲወርድ ሰለሚያደርጉት ጸሎት በማመስገን መልእክቱዋን ላስተላለፍችላቸውና በግፍ ለተወረረችው ኢትዮጵያ አላገዙም። አለዚያም በወቅቱ በሚበዛው የአለም ክፍል ተቀባይነት የነበራቸውን የአለማቀፍ ህግ መርሆዎች ተግባራዊነት ለማስከበር ወይንም ለማስታረቅ የተደረገውን የሽምግልና ጥረት ለማገዝ አልሞከሩም።  የስነምግባርና የዳኝነት መሰረቶቹ ከክርስትና መርሆዎች ጋር ይዛመዱ ለነበሩት የመንግስታቱ ማህበርም ማበረታቻ አልሰጡም።  ሌላው ቀርቶ በዓለም የተከለከለ መርዝ እስከመጠቀም በደረሰ ጭካኔ እርምጃ ኢትዮጵያዊያንን  በፍግ የጨፈጨፈውን ወራሪ ሃይል ባለማውገዟ ተጸጽታ ከጦርነቱ ፍጻሜ በኋላ እንኩዋ ቫቲካን እግዚአብሄርን ምህረት፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ስለመጠየቁዋ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ዋቤ አላገኘም። በአጠቃላይ የደርሃም ጳጳስ የነበሩት እና በጽናት ለኢትዮጵያ የተከራከሩት ኽርበርት ሄንስሌይ ጄንሰን በወቅቱ.

“…አሁን ያሉት ጳጳስ ለአለም አቀፍ ህግ፣ ለፍትህ፣ ለሰብዓዊነት መከበረ ምን አስተዋጽኦ አድርገዋል? ጳጳሱ ጣሊያናዊ እንደመሆናቸው እንደማንም የህገራቸው ሰው ሁሉ የአርበኝነት ስሜት ያድርባቸዋል ብለን እናስብ ይሆናል። እዚህ ላይ ግን ልዩነት አለ። እሳቸው እንደሌላው ሰው አይተው እንዳላዩ ሊሆኑ አይገባቸውም። ድርጊታቸው ሁሉ በእውነት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል። ቫቲካን በየቦታው ወኪሎች ያሉት፣ መረጃ በሚገባ የሚያገኝና ሙሉ ነጻነት ያለው የዲፖሎማሲ አገልግሎት አላት። ሞሎሎኒ ከጳጳሱ በስተቀር ሁሉንም ጣሊያናዊያን ሊያታልል  ይችል ሆናል። በዚህ  አሳዛኝ የአብስንያ ጦርነት ከሃምሳ በላይ ሀገሮች ጣሊያንን በጠብ አጫሪነት ፈርጀው ሲቃወሙዋት፣ ጳጳሱ ምን አሉ? በሚያሳፍር ሁኔታ ውሎች ሲፈርሱ፣ ተቀባይነት የነበራቸው የጦርነት ህግጋት ሲጣሱ ከጳጳሱ አንደበት ምን ተቃውሞ ተደመጠ? የሀገራቸውን ሰዎች ዓይን ለመግለጥ፣ ህሊናቸውን ለመቀስቀስ፣ ስሜታዊነታቸውን ለመግታት በጳጳሱ ምን ጥረት ተደረገ? አዎ! በየጊዜው ጳጳሱ በተናገሩ ቁጥር ግልጽ ያልሆነ (አሻሚ) እና በዚህም የተነሳ ንግግሮቻቸው ከተግሳጽ ይልቅ ይሁንታን የሚያስመላክቱ ነበሩ። ሁልጊዜ የሚናገሩትም ስለሰላም ነበር። ሰላምን ተቀባይነት ያለው እና አስተማማኝ ስለሚያደርገው ብቸኛ መንገድ ስለ እውነት ድርጊት ግን ትንፍሽ አላሉም። ከእውነተኛ ድርጊት የተፋታ ሰላም የክርስቲያንን ከናፍርት ሊመርዝ ይችላልን? … ግን አንድ ያልታጠቁና እድሜያቸው የገፋ አዛውንት የጣሊያንን አምባገነን እንደምን ከድረጊቱ እንዲቆጠብ አደርገዋለሁ ብለው ተስፋ ሊያደርጉ ይችላሉ? ጳጳስ የኢየሱስ ገበዝ ናቸው፡ የኢየሱስ ሃይል ደግሞ በደካማነት ውስጥ ተገልጦ ጽናቱን ይገልጣል። መንፈሳዊ ስልጣኑም አለማዊ ሃይል በሌለበት ሁኔታ በሚገለጥበት ወቅት የበለጠ ደምቆ ይታያል። ምንም እንኩዋን ረዳት የለሽ ምርኮኛ ሆነው ሞሶሎኒ ፊት ለፊት ይህን ያህል አላደረጉም ይሆናል? ቅዱስ አባት ከሃላፊነታቸው ጋር የሚያያዝ ሲሆን ሃይለኛና ፈጣን ናቸው። አንድ የፈረንሳይ ሊቀ ጳጳስ አንድ የቤተክርሲያን ህግ ቢተላለፉ፣ እንደሚወገዙ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የጣሊያኑ አምባገነን ግን አለምን በአመጽ እና በሽፍጥ ሲያናውጥ ገና አልተነቀፈም። አልተገሰጸም። ልክ እየሱስ እንዳወገዛቸው ፈሪሳዊያን፣ ጳጳሱም “ትንኙን አጣርተው ሲያወጡ፣ ግመሉን ይውጣሉ”

በማለት የጻፉት አባባል የጳጳሱን አቁዋም አጠቃሎ ሳይገልጸው አይቀርም።

አሜሪካ ያራመደችው ፖሊሲም ቢሆን ጣሊያንን የሚጠቅም ቢያንስ የማይጎዱ እርምጃዎችን ያካተተ ነው። ሃምሌ ነሃሴ 1927 ላይ ብቻ ውርክቡን በተመለከተ የአሜሪካ መንግስት ሶስት እርምጃዎችን ወስዱዋል። አንደኛው የሃገሪቱ  ፕሬዚዴንት ሮዝቤልት  ለሞሶሎኒ የላኩት መልእክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ነሃሴ መጀመሪያ ላይ ህግ ሆኖ የተደነገገው የመጀመሪያው የገለልተኛነት አቋም ነው። ሶስተኛው ደግሞ የአሚሪካ መንግስት “የሪኬት ውል” (ሪኬት ኮንሰሽን) የተባለው እቅድ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ እንዳይሆን ያደረገው ግፊት/ጫና  ነበር።

ብርታኒያ እና ፈረንሳይ ለሆራላሻል እቅድ መሳካት አሜሪካ ግፊት እንዲታደርግ ባደረጉት ዲፕሎማሲያዎ ጥረትም ጭምር ነበር ሮዝቤልት ለሞሶሊነ መልእክት የላኩት። ሮም ውስጥ የነበረው ጉዳይ አስፈጽሚያቸው አሌክሳንደር ኪርክ ባቀረበው ሃሳብ መሰረት መልእክቱ ለህዝብ ይፋ አልተደረገም። በውስጡ ግን ፕሬዘዴንቱ የኢትዮጵያንና የጣሊያን ውርክብ በሰላም እልባት እንደሚያገኝ ያላቸውን ቅን ምኞት ግልጸው ጦርነት በሁሉም ሀገሮች ፍላጎት ላይ ጉዳት የሚያስከትል የዓለም አደጋ ይሆናል ብለዋል። ነሃሴ 13 1927 ከሰዓት በሁዋላ ሞሶሎኒ ኪርክርን አነጋግሮ መልእክት ሲቀበለው ግን የሆራላቫል እቅድ ውድቅ ከሆነ የአንድ ቀን ተኩል እድሜ አስቆጥሮ ነበር።

ነሃሴ 24 1927 ደግሞ ሮዝቤልት የመጀመሪያውን የገልልትኛነት አቋም በፊርማቸው ደንግገው አውጡ። ይህንንም ያደርጉት አሜሪካ ከኢትዮጵያና ከጣሊያን ጦርነት፣ ባጠቃላይ ደግሞ የመንግስታቱ ማህበር በጣሊያን ላይ ማእቀብ ቢጥል አውሮፓ ውስጥ ሊከተል ይችላል ተብሎ ከተገመተው ጦርነት እንዳትነካካ ይርዳል በሚል ተስፋ ነው። ድንጋጌው በእንደዚህ አይነት ጦርነት ወቅት ለማንኛውም ተፋላሚ ወገን የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ እንዳይደረግ የሚከለከል ህግ የማውጣት ስልጣንን ለፕሬዚዴንቱ ይሰጣል። በዚህም ፕሬዚዳንታዊ ስልጣን መሰረትም መስከረም 15፣ 1928 ላይ ሮዝቤልት ታንክ አውሮፕላንና የጦር መርከቦችን ጨምሮ ማንኛቸውን መሳሪያ ለተወራሪዋ ኢትዮጵያም ሆነ ለወራሪዋ ጣሊያን እንዳይሸጥ የሚያቅብ ድንጋጌ አወጁ። ማዕቀቡ የተጣለባቸው እቃውች ዝርዝር ሲታይ ጠባብና የጦር ማሳሪያዎችን ያካተተ ነበር።

እርግጥ ነው ፕሬዚዴንቱ የጣሊያን ሸቀጦች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የማድረግ ስልጣን አልተሰጣቸውም፣ አለዚያም ዲፕሎማሲያዊ ወኪሎች ከጣሊያን እንዲወጡ በማድረግ፣ የጣሊያንን ወረራ እውቀና ባለመስጠት፣ የጣሊያንን የባህር ሃይል ለማገድና ሱዊዝ ካናልን ለመዝጋት በመስማማት፣ እንዲሁም ተመሳሳይ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ማእቀቦችን በመጣል የመንግስታቱ ማህበር በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 16 መሰረት ሊወስዳቸው ይችላቸው በነበሩ እርምጃዎች ሙሉ በሙሉ የመተባበር ስልጣን ፕሬዚዴንቱ አልነበራቸውም። በሌላ በኩል ግን ቀደም ሲል ያነሳነው የነሀሴ 24/1927ቱ የገለልተኛነት አቋም ድንጋጌ የመንግስታቱ ማህበር ጦርነትን አስመልክቶ ከሚወስዳቸው እርምጃዎች ጋር በተያያዘ የአሜሪካን አቋም ምን እንደሚሆን ምንም የሚለው ነገር የለም። በጣሊያያን ላይ የሚጣሉ ማእቀቦችን በተመለከተ አሜሪካ የምትወስደውን አቋም የመወሰኑ ሃላፊነት ባብዛኛው የተተወዉ ለፕሬዚዴንቱ ነበር። ስለዚህም የዚህ ድንጋጌ አተረጓጎም ልቅ የመሆኑን እድል በመጠቀም ወይንም በማእቀቡ ውስጥ በነበረውና “የጦርነት ማካሄጃ ቁሳቁሶች” በሚለው አባብል ላይ በመመርኮዝ ጠብ አጫሪዋ ጣሊይንን በሚጎዳ መልኩ የእቃዎቹ ዝርዝር ሊያሰፉት ይችሉ ነበር።

አዎ አንዳንድ ሰዎች የገለልተኛነቱ ውሳኔ ሲደነገግና ማእቀቡም ሲጣል ጣሊያን ከአሜርካ የጦር መሳሪያዎችን ለማስገባት ገንዘቡም ሆነ በመርከብ የማጓጓዝ አቅሙ ሲኖራት፣ ኢትዮጵያ ግን ስላልነበራት የምትጎዳው ወራሪዋ ነች ብለው ያሰቡ ነበር። ጉዳዩን በአጽንኦት ላስተዋለው ግን ነገሩ የተገላቢጦሽ ነው። በነሃሴ 1927 መጨረሻ ላይ የነበረውን የሁለቱን ሀገሮች የጦር ሃይል አቅም ላነጻጸረ የወራሪዋ የጣሊያን ሃይል የበለጠ የታጠቀ ነበር። እንደ ነዳጅ ዘይት ብረት የምግብ ሸቀጦች ቃጫና ሎሎችም ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ቁሳቁሶችን ያለችግር ከውጭ ማስገብት እስከቻለች ድረስ ጣሊያን የራስዋ የጦር መሳሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎች ነበሩዋት። እናም ማእቀቡ ጣሊያንን ከማበሳጨት ባለፍ የሚያስከትልባት ጉዳት ኢምንት ሲሆን ለኢትዮጵያ ግን ከፍተኛ መርዶ ነው። የማምረት አቅሙ ላልነበራት ለኢትዮጵያ ከሁሉም በላይ የሚያስፈልጋት ማእቀቡ የተጣለበት የጦር መሳሪያ ነበርና። ፈርንሳይ፣ ብሪታንያ፣ የተቀረውም አብዛኛው አውሮፓ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማእቀብ እንደመጣላቸው የገልልተኛነት ድንጋጌው እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ለኢትዮጵያ ከቀሩዋት አማራጭ የግዢ ቦታዎች አንዷ አሜሪካ ነበረች።

አውሮፓ ውስጥም አሜሪካ የወሰድችው የገለልተኛነት አቋም ጣሊያን ላይ በሚጣል ማእቀብ ለመተባበር ፈቃደኛነቱ እንደለሌላት አመላካች ተደርጎ ተወሰደ። በሌላ በኩል ግን የመንግስታቱ ማህበር አባል የሆኑት የአውሮፓ መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ የተሰነዘረውን የጠብ አጫሪነት እርምጃ ለመቋቋም፣ ለመቅጣትና ለመከላከል አቅሙ ነበራቸው። ለውጤቱ መሳካት ፍቃደኛነቱ ቢኖር ኖሮ ፈረንሳይና ብሪታንያ በዲፕሎማሲያዊ ጫና ሞሶሎኒን ከእርምጃው ሊገታው፣ የኢትዮጵያን የመከላከል አቅም ሊያጎለብትና የመንግስታቱን ማህበር ከመፈራረስ ለማዳን በቂ ነበሩ የሚሉ ጽሀፍት አሉ።

የመንግስታቱ ማህበር በምክር ቤት ከመሰብሰቡ ከጥቂት ቀናት በፊት ማለትም ነሀሴ 25/1927 እለት አንድ የአሜሪካ ኩባንያ በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ለ75 ዓመት ያህል የነዳጅ ዘይት ፍለጋና ልማት ስራ እንዲያካሂድ የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት የመፈራረም ዜና ሲሰማ የመላው ዓለም ልብ ራደ። የዚያ ጭራሹን ያልተጠበቀ ሁነት ተዋናይ የብሪታንያዊው የንግድ ሥራ ደላላ የሪኬት ውል ሥራ ላይ ሊውል ሳይታሰብ አልቀረም የሚል ግምት በሰፊው ተናፈሰ። በመላው አውሮፓና ሜሪካ በተለይም ጣሊያን ውስጥ ብሪታንያና አሜሪካ ጣሊያንን ከኢትዮጵያ ማስወጣት የፈለጉት ሀገሪቱን ለራሳቸው ማቆየት ስለፈለጉ ነው ከሚል ፈጣን መደምደሚያ ላይ ተደረሰ። ጣና ሃይቅም በተመለከተ ሪኬት ስምምነት ለመፈራረም እየሞከሩ ነው የሚሉ ዘገባዎች ይህንኑ የብሪታንያን የቅኝ አገዛዝ መስፋፋት ፍላጎት አስመልክቶ የሚሰነዘረውን ክስ አባባሱት። የኢትዮጵያ የነዳጅ ዘይት ሀብት ክምችት ክፍተኛ ስለመሆኑ የተጋነነ እምነት መኖሩም ባጠቃላይ ታሪኩን እውነት አስመሰለው።

የብሪታንያ መንግስትም ሪኬት ለዚሁ ጉዳይ የሚውል ገንዘብ ከሀገሩ ስለማሻገሩ የማያውቅ መሆኑን በማስተባበል ወዲያዉኑ መግለጫ አወጣ። “ብሪቲያንያም ጣና ሃይቅን በተመለከተ ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያን ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ፍልጎት እንደሌላት፣ ይህንንም የሚመለከት ጉዳይ ቢሆን እንኳ የጣሊያንንና የኢትዮጵያን ውርክብ ላለማባባስ ማንኛውንም ስምምነት ለሌላ ጊዜ እያሸጋገረ መሆኑን አስታወቀ። ከዚህም አልፎ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ስምምነቱን ተግባራዊ ከማድረግ ይታቀቡ ዘንድ እንዲመክራቸው በኢትዮጵያ ያለው ወኪሉን ማዘዙን ገለጸ። ከሦስት ቀን በኋላ ማለትም ነሃሴ 28 ቀን1927 የብሪታንያ መንግሥት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጁን አለማስገባቱን የሚያሳውቅ መግለጫ አወጡ።

 

በሪኬት ጉጉ አስተያየት ተገፋፍቶ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነቱን አድርጎ  የነበረው አሜሪካዊው እስታንዳርድ ቫኩዩም ዖይል ካምፓኒ የተባለ ድርጅት ነበር።  አፄ ኃይለሥላሴም ለሁለት ምክንያቶች ከዚሁ ድርጅት ጋር ስምምነቱን አደረጉ። አንዱ ምክንያት የኢትዮጵያ  መንግሥት ሀገር ለመከላከል ጥረት ገንዘብ በጣም ያስፈልገው የነበረ መሆኑና ከኩባንያው እቅድ ጋር በተያያዘ ሊገኝ የሚችለው ገቢ በዚያ ሀገር ቀውጢ ላይ በነበረችበት ወቅት ተስፋ ማጫሩ ነበር።  ሁለተኛው ደግሞ  የአሜሪካ ምጣኔ ሃብታዊ ጥቅም በኢትዮጵያ መኖሩ የሚያስገኘው ዲፕሎማሲያዊና  ፖለቲካዊ  ጠቀሜታ ነው።  ይህም ወራሪው ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ሊረዳ ይችላል የሚል ተስፋ ማሳደሩ አይቀርም።

 

የተደረገው ስምምነትና በኢትዮጵያ ያጫረው ተሰፋ ግን በጦርነት ላለመነካካት ፖሊሲ ከቀየሰችው ከአሜሪካ ፖሊሲ ጋር የሚቃረን ነበር።  በወቅቱ ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ልክ በመስመጥ ላይ እንዳለች ጀልባ ነበረች።  ስለዚህም የአሜሪካ ስቴት ድፓርትመንት ለኦይል ካምፓኒው ወኪሎች መንግሥታቸው ምንም የደህንነት ዋስትና እንደማይሰጣቸው በማስገንዘብ የነዳጅ ዘይት ፍለጋና ልማት ሥራው የቱንም ያህል ትርፋማ ቢሆን በቅርቡ ጦርነት መካሄዱ ከማይቀርባት ሀገር ከበኢትዮጵያ  የገቡትን ውል እንዲሰርዙ መከራቸው።  ይኸው የአሜሪካ መንግሥታዊ አቋምም በጽሁፍ  ነሃሴ 28 ቀን 1927 ለለንደን፣ ለፓሪስ እና ለሮም ተላከ።  ኩባንያውም ውሉን ሰረዘ።  የኢትዮጵያ ተሥፋም በኖ ጠፋ።

 

አፄ ኃይለሥላሴም በኢትዮጵያ  ለአሜሪካው  ጉዳይ አስፈፃሚ በነገሩ የተሰማቸውን ጥልቅ ቅሬታ አሳወቁት።  አሜሪካ  ለሀገራቸው ምጣኔ ሃብታዊ  እድገት ሊረዳ  የሚችል የቴክኒክ ክሂልና የባለሙያ አቅም ቢኖራትም በኢትዮጵያ  ላይ ፖለቲካዊ ፍላጎት  እንደሌላት መገንዘባቸውን  ገለጹለት።  ወዳጅነታቸውን  ለማረጋገጥና አሜሪካ ለኢትዮጵያ ያላትን በጎ  ዝንባሌ ለማሳየት  ውሉን ተዋውለው እንደነበር አስገነዘቡት።  ይህ ሁሉ  እውነት እንደሆነ ጥርጥር የለውም።  ግን እንደ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ሁሉ የአሜሪካ መንግሥት  ቀዳሚ ፍላጎት ኢትዮጵያን መከላከል ወይም ማሻሻል ሳይሆን  እራሱን  ከውርክቡ በማግለል ከጠቡ አለመነካካት፣ ጣሊያንን አዋዝቶ  መያዝ ነበር።

 

 

የኢትዮጵያ ደጋፊዎችን ስንመለከት ደግሞ፣ ቀድሞም የአድዋ ድል ለጥቁር  ህዝቦች ታላቅ የምሥራች ነበር። ከበፊቱም ባርነት በህግ ሳይታገድ እንዲቆይ የሚሟገቱ ወገኖች ከጥቁር ህዝብ ጋር የተያያዘ ማንኛውንም የሰብዓዊነትና የስልጣኔ ዋቢ አሻራ ዋጋ ለማሳጣት በሚጥሩበት በዚያን ወቅት በመዳፋቸው ስር ላሉት ጥቁሮች ከኔነት መጽናኛ ምርኩዛቸው አንዱ ስለኢትዮጵያ የሚሰሙት ታላቅ አፈ ታሪክ ነበር።  የምዕራቡን የባርነት ሥርዓት ለማቆየት ግብ ታሪክን የሚያጣምሙ የኃይማኖት፣ የፍልስፍናና የሳይንስ ሰባኪዎች በበዙበት በዚያ በ19ኛው ከፍለ ዘመን፣  ጥቁር ሰባኪዎች በቀላሉ በእጃቸው ሊገባ ከቻለው አስረጂ ምንጭ ከመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ  ስለአፍሪካዊያኑ ስለኢትዮጵያ እና ግብፅ ስልጣኔና ገናና ታሪክ አነበቡ።

መዝሙረ ዳዊት 67፡31 ላይ “መኳንንት ከግብፅ ይወጣሉ፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ተዘረጋለች”፣ መጽሀፈ  ኤርምያስ 13፡23 ላይ ደግም “በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን፣ ወይስ ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?”  የሚሉትን መሰል አባባሎች በጥልቀት እየተረጎሙ ሰበኩ።  ኢየሱስ በተሰቀለበት ዕለት መስቀል ተሸክሞ  የረዳውንን የሰመዖንን አፍሪካዊነት፣ በሀዋርያት ስራ ውስጥ  የተገለጸው አማኝ ሞገስ ያለው ኢትዮጵያዊ ባለሥልጣን መሆኑን አስተማሩ። ጥቁር ዘርን በተመለከተ የነኝህ የነኝህ ዋቢዎች መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ  መኖራቸው ሁዋላ ላይ በእንግሊዝኛው “ኢትዮጵያኒዝም ተብሎ ለተሰየመውና  በዚያ ባርነት በተንሰራፋበት ጨለማ ወቅት ጥቁሮች በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ፣ በሰበዓዊነታቸው እንዲያምኑ ላገዘው አፍቃሪ ኢትዮጵያ ተራማጅ እንቅስቃሴ ዋና ምንጭ ሳይሆን አልቀረም።

 

አፍቃሪ ኢትዮጵያዊነት ከደቡብ አፍሪካ አንስቶ  እስከ ካሪቢያን፣ አልፎም እስከ ደቡብ አሜሪካ ድረስ በመዝለቅ አንዱ የጥቁሮች ኃይማኖታዊ አላባ ወይም በፈረንጅኛው ኤለመንት ሆኖ ቆይቷል።  በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ  ያሉ ሰብዕናዎችንና ክስተቶችን በአፍሪካዊነት መነጸር የሚያይ ማህበራዊ፣ ኃይማኖታዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ነው። በወቅቱ ተንሰራፍቶ የነበረውን የክርስትና ሰበካም የጥቁሮችን የበታችነት አስፍኖ ለማቆየት ዓላማ እውነታው የተጣመመበት ትምህርት እንደሆነም አድርጎ  ይቆጥረው ነበር። እንደ የልቪናግተን አባባል “ኢትዮጵያኒዝም የጥቁሮችን መገበር ተገቢነት ለማስረገጥ በአስረጂነት ከሚቀርቡት የመጽሀፍ ቅዱስ የሃም ልጆች እና የኖህ እርግማን አፈ ታሪኮች በተቃራኒ የቆመ ዕይታ ነበር ማለት ይቻላል። ባጠቃላይ ሊዮናርድ ባረት:

 

“ኢትዮጵያዊን የመጀመሪያዎቹ የሰው ልጆች ነን ብለው ያምናሉ። ለዚህም ማስረጃቸውን ይጠቅሳሉ። በተጨማሪም አምልኮዎችን፣ ክብረ በዓላትን፣ ቅዱስ የሰበካ ጉባኤዎችን፣ መስዋዕት ማቅረብን ባጭሩ ሰለአማልክት ክብር የሚከወኑ ሁሉንም ድርጊቶች የጀመርን ነን ይላሉ። ስለዚህ ከሰው ልጆች ሁሉ የበለጡ ሃይማኖተኞች፣ የሚያቀርቡትም መስዋዕት ከሁሉም በላይ አማልክትን የሚያስደስት ነው ብለው ያምናሉ።  ከሃይማኖተኛነታቸው የተነሳም በማንም ባዕድ አገዛዝ ስር እንዳይወድቁ ማድረግን በመሳሰሉት ጸጋዎች አማልክት እንደባረኳቸው ያስረዳሉ። ምንጊዜም በመካከላቸው ላለው ህብረት ምስጋና ይግባውና ሁልጊዜም ነፃነታቸውን እንዳስከበሩ ይኖራሉ።”

 

በማለት የጠቀሱት፣ የሲሲሊው ጸሀፊ የዲዮደሩስ አባባል ስለ ኢትዮጵያና ህዝቧ የነበረውን ጥንታዊ ግንዛቤ ባጭሩ ሳያስቀምጠው አይቀርም።

 

ይህን መሰሉ ግንዛቤ የወለደው የኢትዮጵያኒዝም እሳቤም በማርቆስ ጋርቬይ ጊዜ  ከርዕዮተ  ዓለምነት አልፎ በተግባር የሚገለጽ እንቅስቃሴ ሆኗል።  በእሳቸው እንቅስቃሴ  የሚታመንበት አምላክ የኢትዮጵያ አምላክ ነው። እ; ኤ፡አ በ1920  ኒዮርክ ውስጥ  ዓለም አቀፍ የጥቁር ዘር ዕድገት ማህበር  /ዘ ዩንቨርሳል ኔግሮ  ኢምፕሮቭመንት አሶሲዬሽን/  ጉባኤ የዓለም ጥቁር መብቶች አዋጅን /ድክላሬሽን ኦፍ ዘ ራይትስ ኦፍ ዘ ኔግሮ ፒዩፕልስ ኦፍ ዘ ወርልድ/  ባጸደቀበት ወቅት ያወጣውና  ሁሉን አቀፍ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በማለት የሰየመው መዝሙር ስንኞች ወደ አማርኛ ሲመለሱ እንዲህ ይላሉ:

 

ኢትዮጵያ የአባቶቻችን ምድር፣

አማልክት ሊጎበኙሽ፣ የሚመርጡሽ በፍቅር፣

በሌሊት ድንገት ሲመጣ፣

ማዕበል የተቀላቀለበት ደመና፣

ጦራችን ገንፍሎ ወጣ፣

ድል ማድረግ አለብን በውጊያው፣

ጎራዴዎች ሲያበለጨለጩ፣

ሲመዘዙ ካፎቴያቸው፣

ድል ለኛ ሞገስ ነው፣

በቀይ፣ በጥቁርና ባረንጓዴው ለምንመራው፣

_ አዝማች _

ገስግሱ፣

ወደ ድል ገስግሱ፣

አፍሪካን ነፃነት አልብሱ፣

ጠላትን ለመግጠም ተነሱ፣

ከቀዩ፣ ከጥቁሩና ካረንጓዴው ሃይል ጋር ገስግሱ፣

ኢትዮጵያ ጠላቶችሽ ወድቀው፣

ተፍረከረኩ፣

በሃይል ተመተው፣

በጉልበታቸው ተንበረከኩ፣

ልጆችሽ በጋለ ፍቅር፣

ተናገሩ፣

ርቀት ካላቸው ባህር፣

ማዶዎች መሰከሩ፣

ዬሆ! ታላቁ እኛን ሰምቶናል፣

ለቅሶአችንን፣ እንባችንን አይቶልናል፣

በፍቅሩ መንፈስ አንቀሳቅሶናል፣

በመጭዎቹ ዓመታት፣

አንድ ላይ ያሰባስበናል።

ማርቆስ ጋርቬይም በጽሁፋቸው ውስጥ “እኛ ጥቁሮች አንድ ዓይነት አርአያ አግኝተናል።  ምንም እንኳ የእኛ አምላክ ቀለም የሌለው ቢሆንም ሰው የሚያየው በራሱ መነፀር ነው። ነጮች አምላካቸውን የሚያዩት በነጭ  መነፀር ነውና  እኛም በኢትዮጵያ  መነፀር እያየን እናመልካዋለን”  ብለዋል።  በአፂ ምኒልክ መሪነት የኢትዮጵያ  ሃይል በጣሊያን ወራሪ ላይ በአድዋ የተቀዳጀው ድልም ድልድይ ሆኖ የጥንታዊቷን ኢትዮጵያ የታላቅነት ክብር ከዘመናዊ ዓለም ጋር አገናኘው። ታዲያ  ይህ የማገናኛ  ድልድይ ስራ እ፡ኤ፡አ  በ1890 ዎቹ ከፍፃሜ  ይድረስ እንጂ ግንባታው የተጀመረው የተቀረው የአፍሪካ ክፍል በውጭ ሃይላት አገዛዝ ቀንበር ስር ሲወድቅ ኢትዮጵያዊያን ብቻ በተከታታይ የተሰነዘረባቸውን ወረራ በድል ሲመልሱ ነበር።  በዚያው ክፍለ ዘመን እንኳ በ1870ዎቹ የግብፃዊያንን፣ በ1880ዎቹ የመሃዲስቶችን ተደጋጋሚ ጥቃቶች መክተው መልሰዋል።  የአድዋ ድል ደግሞ ይህን የነፃነት ቀናዒነት ይበልጥ  አደመቀው። የዓለምንም ቀልብ ሳበ።  የአውሮፓ መንግሥታት ዲፕሎማቶቻቸውን  ወደ አዲስ አበባ እንዲልኩ፣ ከኢትዮጵያ ጋር 19  ድንበርን የሚመለከቱ ስምምነቶችን እንዲፈራረሙ አደረጋቸው።

 

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ  ለነበሩት የአፍቃሪ ኢትዮጵያዊነት እንቅስቃሴ መሪዎችም የአድዋው ድል የሞራል እርሾ  ሆኗቸዋል።  ከእንቅስቃሴው ግንባር ቀደም መሪዎች አንዱ ጀምስ ድዋኔ ግብጽና ሱዳን ውስጥ ያሉትን ክርስቲያን አፍሪካዊያን ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው መፍትሄ ይፈልጉለት ዘንድ ለምኒልክ ደብዳቤ የፃፉት የአድዋውን ድል ተከትሎ ነበር። ለዚህም ጉዳይ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ ሞክረዋል። የነፃዋ  ኢትዮጵያ ተምሳሌትነት በዙሉ እና በሌሎቹ የደቡብ አፍሪካ ክፍሎች ውስጥ ጠንክሮ  ሠርጾ ነበር። እ፡ኤ፡አ፡ በ1935 _1936  ናታልና ዙሉ ክፍላተ ሀገራት ውስጥ  ስለኢትዮጵያ ይደረግ የነበረውን የአዳር ጸሎት ለመከታተል የሚጎርፉት አዳዲስ መዕመናን ቁጥር እጅግ የትዬ ለሌ ነበር።  መልከ ፃዲቅ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያን  እና የአብስኒያ ኮፕቲክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሚለው ስያሜ የተሰጣቸው ገናና አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ።

እ፡ኤ፡አ፡ በ1930ዎቹ ከጀማይካ፣ ምዕራብ ኪንግስተን ደሳሳ ጎጆዎች ሲፈልቅ የአልባሌ ሰዎች ስብስብ ከመባል አልፎ፣ በተጀመረበት ሀገር ህዝብ ውስጥ  የማይነቃነቅ መሰረት የጣለ ብቻ ሳይሆን ከካሪቢያን ወጥቶ በሰሜን አሜሪካ፣ በብሪትሽ አይልስ፣ በአፍሪካ  ውስጥ መስፋፋት የቻለው የራስ ተፈሪያዊያን እንቅስቃሴ አመጣጥም ውልዴቱ ከዚህ የኢትዮጵያና የጥቁሮች ህዝባዊ እንቅስቃሴ ትስስር ጋር የተያያዘ ነው።  በሌላ አባባል የአፄ ኃይለሥላሴ መንገስ ወይም የእሳቸው የጀማይካ ጉዞና  የዝናብ መዝነብ ያመጣው ድንገቴ ክስተት አይደለም ለማለት ነው።

ከሃይማኖቱ ውጭም በአርነት ትግሉ መስክ በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩት እህት የአፍሪካ ሀገሮች ታጋዮችም ኢትዮጵያ ፋና ወጊ መብራታቸውና የራዕይ ምንጫቸው ነበረች። ለዚህም ነው የናይጀሪያ ድኀረ ነፃነት የመጀመሪታ ፕሬዚዴንት የነበሩት ዶክተር አዚኪዊ:

“ኢትዮጵያ ጥቁር ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርባት የመጨረሻው ሀገር ነች። በዚህ ክፍለ  አህጉር ላይ የአፍሪካ ቀደም አባቶች የመሰረቱት መንግሥት የታሪክ ዋቢ ነች።  ኢትዮጵያ  ከዘመን ወደ ዘመን እየተሸጋገረች ህልውናዋን ጠብቃ መኖሯ የሚደነቅና መደነቅም ያለበት ነው።”

በማለት ተናግረው የነበረው።  ከአድዋው ድል አርባ ዓመት በሁዋላ ጣሊያን ቂሟን ልትወጣ የመላው ጥቁር ህዝብ ዕንቁ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ወረራ ስታካሂድ በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ የአውሮፓና የአሜሪካ መንግሥታት ከእሷ ጎን ቆመዋል። በተቃራኒው ግን በአፍሪካም ይሁን በተቀረው ዓለም የተቀጣጠለውን አፍቃሪ አፍሪካዊነት የትግል ስሜት አነስቷል። እልህ አጭሯል። በአጠቃላይ መላው ጥቁር ህዝብ፣ በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም ለፍትህ የታመኑ አውሮፓዊያን ነጮችም ለኢትዮጵያ ያላቸውን ወገናዊነት አጠናክሯል። የነኝህም ጥረት በውጭ የነበረውን ህዝባዊ ድጋፍ ወደ ኢትዮጵያ ያደላ እንዲሆን አድርጎታል።

ባህላዊ እሴቶቻቸውን  ያልጣሉ  የአፍሪካ ምሁራን ተሰባስበው ከነበሩባቸው  የአህጉሩ ከተሞች፣ ከካርቢያን ደሴቶች፣ ከጥቁር አሜሪካዊያን በኩል ወረራው ያጫረው የመጠቃት ስሜት ተስተውሏል።  በጀማይካ ኪንግስተን ከተማ፣በኩባ ስኳር አምራች ክፍለ ሀገራት፣በማዕከላዊ አሜሪካ ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎች፣ በነቁጧ በግሪናዳ እና በሃርለም ጥቁሮች ከኢ ትዮጵያ ጎን ቆሞ ለመዋጋት የሚጠይቅ ፊርማ አሰባስበው ለባለሥልጣን አቅርበዋል።   የሃርለም ጥቁሮች ዕድሉ ሳይሰጣቸ  ሲቀርም በኒዮ ርክ እና በኒውጀርሲ ከተሞች  መነገዶች ላይ በአካባቢው  ከነበሩ ጣሊያናዊያን ጋር ተጋጭተዋል።  ለብዙ ጥቁሮች፣  ኢትዮጵያ የአፍሪካ ክፍለ አህጉርን ፖለቲካዊ ነፃነት ለመታደግ የመጨረሻው የመከላከያ  ግንባር ነበረች።  በአንድ አውሮፓዊ ሀገር ላይ አስገራሚ ድልን ያስመዘገበች ባለድንቅ ታሪክ ሀገር።  እናም የዚህች ብቸኛ ነፃ ጥቁር ሃገር በድጋሚ በጣሊያን መወረር፣ በጥቁር ምሁራን ዘንድ ያጫረውን እልህ ለመገንዘብ የሚከተሉትን ክስተቶች  ማስተዋል ብቻ በቂ ነው።

አንድ ለትምህርት ወደ አሜሪካ ይጓዝ የነበረ ጋናዊ ወጣት  ለንደን ውስጥ በጋዜጣ ላይ “ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን ወረረ”  የሚለው ዜና ተጽፎ  ሲያነብ የተሰማውን ሲገልጽ:

“መላው ለንደን በእኔ ላይ በተናጠል  ጦርነት ያወጀብኝ ሆ ኖ ተሰማኝ።  ከዚያም ለጥቂት ደቂቃዎች ዕቁብም የሌለው እያንዳንዱ መንገደኛ ላይ አፍጥጨ እነኛ  ሰዎች የቅኝ አገዛዝ መራራነትን ሊገነዘቡ ይችሉ እንደሆነ እያሰላሰልኩ ከመደመም፣ ለእንደዚህ ዓይነቱ ሥርዓት መውደቅ የበኩሌን ትግል ላበረክት የምችልበት ዕለት እንዲመጣ ከመጸለይ  ሌላ  ምንም ማድረግ አልቻልኩም። ”

ብሏል።

ይህን የተናገሩት ከነፃነት በኋላ የጋና የመጀመሪያ  መሪ የሆኑትና የአሜሪካ  የስላላ ድርጅት ደመወዝተኛ በነበረ የራሳቸው ወታደራዊ መኮንን መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደባቸው  ከዋሜ ንኩርማ ነበሩ።  ከሴራሊዮን ዋላስ ጆንሰንም የጣሊያንን ወረራ በመቃወም አፍሪካን ሞርኒግ ፖስት ላይ ባወጡት ጽሁፍ ሰበብ እ  ኤ አ  በ1936 ታስረው 50 ፓውንድ ተቀጥተዋል።  የተከሰሱበት ወንጀል ብጥብጥ ለማነሳሳት መሞከር የሚል ሲሆን ከጽሁፋቸው ለመጥቀስ:

“አውሮፓዊ የሚያምንበት፣ አፍሪካ ውስጥ  ባሉ ቤተክርስቲያኖቹ የሚቆምለት አንድ አምላክ አለው።  ስሙ ማታለል ተብሎ  በሚጻፈው አምላክ ያምናል።  ህጉ እናንተ የሰለጣናችሁ  አውሮፓውያን ያልሰለጠኑትን አፍሪካውያን በማሽንገን ማሰልጠን አለባችሁ። እናንተ  ክርስቲያን አውሮፓውያን አረመናውያኑን  አፍሪካውያን  በቦምብ፣ በመርዝ ጋዝና በመሳሰለው ክርስቲያን ማድረግ አለባችሁ በሚለው ያምናል።”

የሚል  ይገኝበታል።  የዌስት ኤንድ፣ የአፍሪካ ምሁራንንና ቀስቃሾችን አካቶ  የያዘው የዋላስ ጆንሰንና  የጓደኞቹ ቡድን በአባላቱ ቁጥር ትንሽ፣ በሂደት ግን ተከታዮችን ያፈራና ውጤታማ  ሥራ የሰራ ነበር።  ቡድኑ ከቅኝ አገዛዝ ለመላቀቅ የሚያስችል ርዕዮተ ዓለም የመ ቅረጽ ትግል በፋና ወጊነት  ጀምሯል።

አፍቃሪ ኢትዮጵያው ቁጭት ባስከተለው መነሳሳትም ድጋፋቸውን ለኢትዮጵያ  ህዝብ ለመስጠት ብዛት ያላቸው ኮሚቴዎች በየቦታው ተቋቁመዋል። በብሪታንያ the International African Friends of Ethiopia (IAFE)፣ በአሜሪካ the American Committee for Ethiopia (ACE)፣ በትሪናዳ the Afro-West Indian League, the West Indian Youth Welfare League, the Negro Welfare Cultural and Social Association, the National Association of the African Progeny፣ በብሪትሽ ጉያና ጆርጅ ታውን the Afro-American Association, the League of Coloured Races፣ በሃይቲ the Ligue  haitienne pour la Defense du Peuple Ethiopien፣ በማርቲኒኪ the Group Jean, the Front Commun፣ በፓሪስ the Ligue de la Defense de la Race Negre በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ።

በምሳሌነት ከተመለከቱት ውስጥ የ IAFE ዋና ዋና ዓላማዎች 1ኛ/ በፋሽስት ጣሊያን  ወረራ ለተካሄደባት ኢትዮጵያ የብሪታንያን ህዝብ ድጋፍ ማስገኘት  እና 2ኛ/ በሚቻለው አቅምና በማንኛውም መንገድ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ፖለቲካዊ ነጻነትን ለመስጠበቅ እገዛ መስጠት ነበር።  የኮሚቴ ሊቀመንበር ሮበርት ጀምስ ሲሆኑ ጸሀፊው ደግሞ  ጆሞ ኬንያታ ነበሩ። ጆሞ  ኬንያታ Labour Monthly ላይ ”ከአብስኒያ ላይ እጃችሁን አንሱ!“  በሚል ርዕስ ባወጡት ጽሁፍ ኢትዮጵያን መርዳት ፋሽዝምን መዋጋት መሆኑን አስገንዝበዋል። “ኢትዮጵያ ለወራሪው ሃይል የሚኖራትን ምላሽ ሲያስገነዝቡም:

”ኢትዮጵያ በንጉሠ ነገስቷ መሪነት፣ በወታደሮቿ፣ በጀግንነቷና  በባህላዊ እሴቶቿ ትመካለች።  መንበርከክ የማይታሰብ ነው።  ሁልጊዜም እንደምታደርገው ይህን ወሰን ያጣ የኢምፔሪያሊዝም ድፍረት በመመከት ነፃነቷን ለመጠበቅ አሁንም ትዋጋለች።”

ያሉት።  የዚሁ ኮሚቴ ገንዘብ ያዥ  የነበሩት ደግሞ የማርቆስ ጋርቤይ ባለቤት ወ/ሮ  አሚ አሸውድ ጋርቤይ  ናቸው። ከስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላቱም ጆርጅ ፓድመር፣  ከትሪናዳ ሳሚ ማኒንግ፣ ከሶማሊያ  ማሃመድ ሰይድ ይጠቀሳሉ።

በ1921  በተካሄደው አፍቃሪ አፍሪካ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የግሪናዳው አልበርት መሪይሰው፣  እንግሊዝ ማንሸስተር ውስጥ የነበረው የኔግሮ  ዌልፌር  ማህበር ፐሬዚዴንት ዶከተር ፒተር ማክዶናልድ ሚሊያርድም ሌሎቹ የኮሚቴው አባላት ናቸው።

እ ኤ አ በ1936  መጀመሪያ ላይም የክብር ጸሃፊው  ፐሮፌሰር ኤች ኤስ ጀብንስ የሆኑት የአብስኒያ ማህበር የሚባል ተቋቋመ።  ማህበሩ ለንደን ውስጥ  ቢሮ  በመክፈት ለኢትዮጵያ እገዛ ለማስገኘት በቀየሰው ዓላማ መሰረት አንድ ሺህ  ፓውንድ የማሰባሰብ ጥሪ አቀረበ።  ከዚህም ሌላ ለኢትዮጵያ  የገንዘብ ብድር፣ እንዲሁም በመንግሥታቱ ማህበር ሊወሰዱ ይችሉ ለነበሩ ማዕቀቦች እና እርምጃዎች ህዝባዊ ድጋፍ የማሰገኘት እቅድ ነበረው።  ካባላቱም ውስጥ  ለኢትዮጵያ በነበራቸው ያላሰለሰ ድጋፍ ከታወቁት ያፓርላማ አባላት ራ ቨይቭያን አዳምስና ጀፈሪ ማንደር  በተጨማሪ፣ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን አስመልክቶ  በመጻፍ የታወቁት ጌታው ኖርማን ኤንጅል ይገኙበታል።

ከዚያም በፊት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1935  ላይ  የአምስተርዳሙ የዓለም ጸረ ጦርነት ጉባኤ ለኢትዮጵያ ያለውን ድጋፍ የሚገልጥና  የወራሪውን ጠበ አጫሪነት የሚኮንን መግለጫ አውጥቶ  ነበር።  በዚሁ ዓመት ሚያዝያ ወር ውስጥ  ካርሎ ሮሰሊ የተባሉ ሰው  Giustizia Liberta  ላይ  በተከታታይ ባወጧቸው ጽሁፎች ጣሊያንን  በጥብቅ ተቃውመዋል።  እነኝህም መጣጥፎቻቸው How to Conduct the Campaign Against the War in Africa በሚል ርዕስ በመጽሀፍነት ለህትመት በቅተዋል።  ሌላው  የኢትዮጵያ ባለውለታ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ  ፕሬዚዴንት የነበሩት  ቪክቶር ባሻ ናቸው።  የለንደኗ  ሲልብያ  ፓንክረስም እንደዚያው።

የካርቢያን ጥቁሮችም ከፍተኛ በሆነ ድርጅታዊ ቅንብር ኢትዮጵያን ለማገዝ እጅግ ደክመዋል።  በእያንዳንዱ ደሴት ቢያንስ  አንድ ለኢትዮጵያ  ተዋጊ አርበኞች መዲሃኒትና ሌሎች ቁሳቁሶች መግዣ የሚውል ገንዘብ የሚያሰባስብ ድርጅት ነበር።   ጥቁር ሴቶችም በበኩላቸው ከፍተኛ  ሚና  ተጫውተዋል።  የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀን የሚል ዝግጅት እያደረጉም ገንዘብ ለማሰባሰብ ጥረዋል።  ከውስጣቸውም የ the Negro Welfare Cultural and Social Association መሪ የነበሩት ኢልማ ፍራንኮስ በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሱ ናቸው።  ማህበራቸው የተቃውሞ ስልፎችን አደራጅቷል፣  የመደብ ብዝበዛን ከዘር/ጎሳ ብዝበዛ ጋር  በማገናዘብ ከፍተኛ ቅስቀሳ አካሂዷል። የ New Times እና የ Ethiopian News ቅጂዎችም  በብዛት እንዲሰራጩ አድርጓል።  ማርቲኒኪ ውስጥም አፍቃሪ የሰራተኛው መደብ  የሆኑ የፖለቲካ አቀነባባሪዎችን የያዘው the Comite de Defense du Peuple Ethiopien ተመስርቶ  “ኢትዮጵያውያን በዘሮቻቸው ወንድሞቻችን ናቸው። እንደኛ  የተጨቆነ ዘር፣ የጥቁር ዘር’’ የሚል የድጋፍ ጥሪ ያስተላልፍ ነበር።  በትሪናዳም ዕቃ አውራጅና ጫኝ ሠራተኞች  በጣሊያን መርከቦች ላይ ላለመሥራት እምቢ  ብለው ነበር።  በጀማይካ፣ ኪንግስተን የUniversal Negro Improvement Association ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤትም በ “ዘር ተዋረድ  የሃም ልጅነታቸው  ወደ ኢትዮጵያ  ገብተው ለመዋጋት ብዙ ሰዎች ፊርማቸውን በማሳረፍ የጠየቁበት ወረቀት ለባለሥልጣናት ቀርቧል።  በሌሎች የብሪታንያ ቅኝ ግዛቶችም የተለያዩ  ቡድኖችና ግለሰቦች ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል።  አንድ ሰው ከሆንዱራስ በጀማይካ  ለቅኝ አገዛዙ ባለሥልጣ በጻፉት ደብዳቤ ”ለመዝመት ዝግጁ ነንና ፈጣን ምላሽ ይስጡን።  እኛ እዚያ ከመድረሳችን በፊት የመጨረሻው  ጣሊያናዊ  እንዲሞት አንሻም።“  ብለዋል።

በኩቫም ሳልባዶር ግራሲያ አ ጉዬሮ እና ሌሎችም አፍሪካ ኩባዊያን የኮምኒስት ፓርቲውን ይሁንታ አግኝተው አፍቃሪ ኢትዮጵያ የሆነ ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁመዋል።  La Voz de Ethiopia የሚል የሬዲዮ  ስርጭትም ጀምረዋል።  አደላንቴ የሚባለው አፍሪካ ኩባዊ ጋዜጣም ባወጣቸው መጣጥፎችም በኢትዮጵያ የተካሄደውን ወረራ ከኩባ ዳግም ቅኝ አገዛዝ ጋር በማገናዘብ በስልጣኔ ስም ቅኝ አገዛዝን ለማጠናከር የታለመ መሆኑን ተንትኗል።  2000 ኩባዊያንም ከኢትዮጵያ ጎን ሆነው ለመዋጋት ፈቃደኛ እንደነበሩ ተዘገቧል። 60 ምርጥ ነርሶችም ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድና ሙያዊ ግልጋሎታቸውን ለማበርከት ፈቃደኛ ነበሩ። በአጭሩ ኩባዊ ገጣሚ ኒኮላስ ጉዮሊን በሞሶሎኒ ላይ:

ምኑ የባህር ወንበደ ሰይጣን ነው!

ይህ ሞሶሎኒ!

ከዚያ ባልጩት መሳይ የፊት ትይታው!

እና ከነኛ ስግብግብ ጥፍሮቹ ጋር!

 

በማለት የገለጹት የእልህ ስሜት በብዙ የሀገራቸው ዜጎች ልቦና ውስጥ  ይንበለበል ነበር።

የኢትዮጵያ ወዳጆች እና ኢትዮጵያዊያን የጥበብ አርበኞች ለምሳሌ ዮፍታሄ ንጉሴ “አጥንቱን ልልቀመው” እያሉ
በብዕራቸው ጥላትን ሲዋጉ፣ ወራሪው ደግሞ ከአድዋ ሽንፈቱ አርባ ዓመት በሁዋላ ቂሙን ለመወጣት በአደረገው ጦርነት ያገኘውን ድል እንዲህ እያለ አሞግሶ ነበር – አድዋ በሚል ርዕስ በኒኖ ራስተሊ
ተጽፈው፣ ዲኖ ኦሊቪሪ በሙዚቃ በተቀናበሩት ስንኞች፡

 

አሸነፈ ተመመ፣ ሄደ በርምጃ ጦሩ፣

ድልን ካድማስ አድማስ፣ እያስተጋባ አየሩ፣

በሚሊዮን የሚቆጠሩ፣

ጥፍሮች በምርኮ ተንጰረጰሩ፣

ባደባባይ በአካል ታዩ፣ መሠከሩ፣

አልቻሉም ሊያመልጡ፣ ሊሰወሩ፣

ቦታውን ጣሊያኖቹ፣

በ እጃቸው አስገቡ፣ ተቆጣጣሩ፣ ወንዶቹ፣

በፊታቸው ፈገግታ እያስነበቡ፣

በስሜት እየዘመሩ!

አድዋ ነፃ ወጣች፣

በ እጃችን ተመልሳ ገባች፣

በአድዋ ድል ተመዘገበች፣

ተወለዱ ዳግም ጀግኖች፣

ለድል ገሥግሱ፣ ገሥግሱ …

መላው ዓለም አወቀ፣

የአድዋ የበቀል ፍሬያችንን አደነቀ፣

የ እኛም ነፍስ በደስታ ጩኸት ፈነደቀ፣

አታሞው ተሰማ አስተጋብቶ፣

የምድሩን ጩኸት ተክቶ፣

የደስታ እምባና ልባዊ ምኞት ፈንቅሎ።

ይህ መሬት፣

አንድ ዕለት፣

አፈረ የሆኑበት፣

ሠማዕታት ከሥሩ አሉበት፣

ጥላዎች

የደም ቀለም አሻራዎች፣

በልህ ይቃጠሉ የነበሩ፣

በደስታ እየዘመሩ።

አድዋ ነፃ ወጣች፣

በ እጃችን ተመልሳ ገባች፣

በ አድዋ ድል ተመዘገበች፣

ተወለዱ ዳግም ጀግኖች፣

ለድል ገሥግሱ፣ ገሥግሱ …

መላው ዓለም አወቀ፣

የ አድዋ የበቀል ፍሬያችንን አደነቀ፣

የ እኛም ነፍስ፣ በደስታ ጩኸት ፈነደቀ።

 

ያን ጊዜስ እንደዚህ ቢሉም በአባት እናቶቻችን ተጋድሎ አድዋ ተመልሳ ከሕጋዊው ባለቤቷ ከኢትዮጵያ
ሕዝብ እጅ ካምስት ዓመት በሁዋላ ገብታለች።  ዛሬስ?  የታሪክ ምፀቱ፣ ከአድዋ በበቀሉ፣ ካርባ ዓመት በሁዋላ ጣሊያን ቂሟን ለመወጣት ስትመጣ ባንዳ ሆነው ባገለገሉ ሰዎች ልጆች እና የልጅ ልጆች በሆኑ የራሳችን  ሰዎች
የአድዋ   ድል ሲንኳሰስ፣ ሲያሻቸውም በደም   የተገነባው የጋራ   ታሪክነቱ           ሲካድ፣ በዚያ ከአራቱም ማዕዘናት የሀገራችን ክፍሎች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊን በአንድነትና በወኔ ቆመው ጠላትን እየተፋለሙ
በወደቁበት የአድዋ አፈር ላይ የቋንቋ መስመር ዘርግተው እየመተሩ ብሄር ብሄረሰቦች ወካይ የሚሏቸውን ቤቶች ሲሰሩ ምን ይሰማን ይሆን?  ደም የተቃቡን ባዕዳንስ  ምን ይሰማቸው ይሆን?  ኢትዮጵያ እስካለች ነው ኢትዮጵያዊያን በጋራ ተሰባስበን አድዋን በጋራነቱ ልናከብረው የምንችለው።  ታሪክ      ላንድ     ማህበረሰብ        ምርኩዙ ነው። ምርኩዛችንን በዝምታ አሳልፎ መስጠቱ ያለውን አደጋ ተገንዝበን የአድዋ ድልን ማሰብ ብቻ ሳይሆን፣ ክብሩን ማስከበርም ግዴታችን ይመስለኛል። ዝነኛው ገጣሚና ጠሀፊ ተውኔት ዮፍታሄ ንጉሴ በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት በጣፉት እላይ በገለጥኩት “አጥንቱን ልልቀመው”  ግጥማቸው  ውስጥ:

 

አጥንቱን ልልቀመው _ መቃብር  ቆፍሬ፣

ጎበናን ከሸዋ _  አሉላን ከትግሬ፣

ስመኝ አድሪያለሁ _ ትላንትና ዛሬ፣

አሉላን ለጥይት _ ጎበናን ለጭሬ::

ተሰበሰቡና _ ተማማሉ  ማላ፣

አሉላ ተትግሬ _ ጎበና ተጋላ::

ጎበና ሴት ልጁን _ ሊያስተምር ፈረስ፣

አሉላ ሴት ልጁን _ ጥይት ሊያስተኩስ::

አገሬ ተባብራ _ ካልፈጠረች እርካብ፣

ነገራችን ሁሉ _ የእንቧይ ካብ የእንቧይ ካብ::

ትምህርት እንዲስፋፋ _ ጉልበት እንዲጠና፣

አራቱ ጉባዔ _ ይነሱልንና፣

መኮንን ደረሶ _ አሉላ ጎበና፣

አገራችን ትማር _ አሁን እንደገና፣

ጎበና ተፈረስህ _ ጋር ተነሳ እንደገና::

 

ያሉት ጥሪ  አሁንም በሀገራችን ፈፋ ሜዳ፣ ከተማ ገጠር  እያስተጋባ  ይመስለኛል::  ምን ያህሎቻችን
በእዝነ ህሊናችን  ጥሪውን እያዳመጥነው እና  ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠነው እንደሆነ እራሳችን ለራሳችን ጠይቀን  መልስ እንዲንሰጥ በመጠየቅ፣ ጽሁፌን በጥያቄ እዘጋለሁ::

 

ክብር ለአድዋ ሰማዕታት!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

 

ሰንደቅ – ከጅምሩ ሂደቱ ላይ ጥላ ያጠላበት የፓርቲዎች ድርድር ሂደት እና ቀጣይ ጉዞ

$
0
0

ሰንደቅ – ከጅምሩ ሂደቱ ላይ ጥላ ያጠላበት የፓርቲዎች ድርድር ሂደት እና ቀጣይ ጉዞ

ለ26 ዓመታት በአገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች የመንግስት ስልጣን የዞ የቆየው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በወቅታዊ የአገሪቱ ችግር ዙሪያ ከተቃዋሚ (ተቀናቃኝ ወይም ተፎካካሪ በሉን ይላሉ) ፓርቲዎች ለመወያየት ግብዣ አቅርቦላቸው ወደ ውይይት ለመግባት ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ። ኢህአዴግን ጨምሮ ሰማያዊ፣ መኢአድ፣ መድረክ፣ ኢራፓ፣ ኢዴፓና ሌሎች 22 ፓርቲዎች የሚያደርጉት ውይይት ዓላማው ከ2008 ዓም ኅዳር ወር ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አማራ ክልል በተዛመተው ህዝባዊ ተቃውሞ (አንዳንዶች ቁጣ ይሉታል ኢህአዴግ ደግሞ ልማቱ ያመጣው ተቃውሞ ሲል ይጠራዋል) በመንግስትና በአገር ላይ ስጋት በማሳረፉ መፍትሔ ለመፈለግ ነው። ከፓርቲዎቹ ውይይት (ተቃዋሚዎች ድርድር እንጂ ውይይት አና ክርክር ብሎ ነገረ የለም። ኢህአዴገ የጠራን እንድንደራደር ካልሆነ ጥሪውን መቀበል አንፈልግም ሲሉ ይገልጻሉ) ቀደም ብሎ ደግሞ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአገሪቱ ላይ መታወጁ የሚታወስ ነው።

ኢትዮጵያ ላለፉት 26 ዓመታት በአንድ ፓርቲ አመራርነትና አስተሳሰብ ብቻ እየተመራች መቆየቷ ይታወቃል። በ2002 ዓም በተካሄደው አራተኛው ዙር ምርጫ በኋላ ራሱን አውራ ፓርቲ (dominant party) ብሎ መጥራት የጀመረው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በ2007 ዓም የተካሄደውን ምርጫም ሙሉ በሙሉ የፌዴራልና የክልል ፓርላማ መቀመጫ ወንበሮችነ ጠቅልሎ ያሸነፈ መሆኑን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወቃል። ሆኖም ከአምስተኛው ዙር ምርጫ ማግስት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በገዥው ፓርቲ ላይ ተቃውሞዎቸ መነሳታቸውን ተከተሎ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ የአገሪቱ የምርጫ ህግ እንደሚሻሻል የፌዴሬሽን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶችን የስራ ዘመን መክፈቻ ሲያበስሩ አስታወቀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትረ ኃይለማሪያም ደሳለኝም ቢሆኑ የምርጫ ህጉ መስተካከል እንዳለበት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገለጹ ሲሆን ለአገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ሲባልም ህገ መንግስቱ ሳይቀር መሻሻል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተው ነበር።

ከኦሮሚያና አማራ ክልሎች ግጭት ማግስት ጀምሮ አገራቀፍ የውይይትና የምክክር ጉባኤ እንዲካሄድ አገር ወዳድ ምሁራንና የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሲያስታውቁ ቆየተው ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለሁሉም አገረ አቀፍ መዋቅር ላላቸው ፓርቲዎች የድርድር የምክክር ወይም የውይይት ጥሪ አቅርቦ በጥር 10 ቀን 2009 ዓም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ መገናኛ ብዙሃን ባልታደሙበት (ኢቢሲ እና ሌሎች መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ብቻ ታድመዋል) መልኩ የድርድሩ፣ የክርክሩ ወይም የውይይቱ ቅድመ ሁኔታ ላይ ምክክር ሲያደርጉ ውለው ለጥር 25 ቀን 2009 ዓም ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ። ፓርቲዎቹ ለድርድሩ ለውይይቱ ወይም ለክርክሩ አስፈላጊ ነው የሚሏቸውን ነጥቦች ዘርዝረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ለሆኑት አስመላሽ ገብረስላሴ እንዲሰጡ በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ሃሳቦቻቸውን ገልጸው አስታወቁ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየሳምንቱና በየ15 ቀኑ ፓርቲዎቹ እየተገናኙ ወይይት ድርድር ወይም ክርክር እያካሄዱ ይገኛሉ።

መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓም የተካሄደውን ውይይት አስመልክቶ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮችና የኢህአዴግ ተወካዮች ጋር የሰጡንን አስተያየት ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

የድርድሩ ጊዜ መራዘም

ኢህአዴግና የተወሰኑ ፓርቲዎች ድርድር ውይይትና ክርክር በሚል ርዕስ እንዲወያዩ ሀሳብ ሲያቀርቡ መድረክ ሰማያዊ ኢዴፓ መኢአድና ኢራፓን ጨምሮ ሰባት ፓርቲዎች በአንድ ሰነድ ሶስት አይነት የመወያያ ርዕስ አያስፈልግም የተጠራነው ለድርድር እስከሆነ ድረስ ከድርድር ውጭ በሌላ ርዕስ ዙሪያ አንሰበሰብም ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። በርዕስ አለመግባባት ምክንያት የአንድ ቀን ጉባኤው የተቋረጠው የፓርቲዎቹ ውይይት ወደ ድርድር በቀጥታ ለመግባት የመጓተት ነገር ይታይበታል ሲሉ የቅድመ ድርድር ሂደቱን የሚገልጹ ሰዎች አሉ። ይህን በተመለከተ ለሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየታቸውን የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ “እኛ ወደ ድርድሩ የገባነው ከድርድሩ አንዳች ረብ ያለው ውጤት አናገኛለን ብለን ተስፋ አድርገን ነበር። ነገር ግን ቃላትን እየሰነጠቁ ሂደቱን ማራዘም የምንጠብቀውን ተስፋ እንዲመነምን እያደረገው ሲሆን በፓርቲያችን ላይም ችግር እየፈጠረብን ይገኛል። ለድርድር ከተጠራንበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ወራት ብቻ 12 የፓርቲያችን አባላት ታስረው የት እንዳሉ አናውቅም” ሲሉ የድርድሩ ሂደት መራዘሙን በቅሬታ ገለጸዋል።

የኢዴፓው ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው ቅድመ ድርድር ሂደቱ መራዘሙ የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸው ምክንያቱን ሲያስቀምጡም “22 ፓርቲዎች የሚሳተፉ በመሆኑ እና ሁሉም ሀሳቡን የሚያቀርብ በመሆኑ ጊዜ መውሰዱ አይቀርም። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከምንም በላይ አስፈላጊ የሆነውና ሁላችንንም ሊገዛን የሚችለው የስነ ስርዓት ደንቡ ስለሆነ በዚያ ላይ ሰፊ ውይይት አድርገን መቅረጽ ይኖርብናል” ሲሉ ተናግረዋል። ዶክተር ጫኔ አክለውም “በድርድር መልኩ እስከተሰበሰብን ድረስ ጊዜ መውሰዱ አይቀርም” ሲሉ የድርድሩ ስነ ስርዓት ደንብ ዝግጅት ጊዜ ወሰደ የሚባለው ለተሻለ ውጤት መሆኑን ገለጸዋል።

የመኢአዱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ አበበ ደግሞ የድርድሩ ቅድመ ዝግጅት ሂደት ዘግይቷል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። አቶ ሙሉጌታ “ዋናው ነገር መፍጠኑ ሳይሆን መግባባቱ ስለሆነ ለዚህ ደግሞ ሰፊ ውይይት እያደረግንበት እንገኛለን። ስለዚህ ዘግይቷል ብሎ ለመናገር ጊዜው ገና ነው” ብለዋል።

ርዕሱ ያላግባባቸው ተደራዳሪዎች

“ኢህአዴግ እንደራደር ብሎ ጠርቶ ውይይትና ክርክርም በሰነዱ ላይ ይካተት ብሎ መቅረቡ ለማደናበር ነው” ሲሉ የሚገልጹት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመነበር አቶ የሽዋስ አሰፋ ሀሳባቸውነ ሲያጠናክሩ “በመሰረቱ አሁን የመጣውን የውይይት ክርክርና ድርድር የሚል ርዕስ ኢህአዴግ ለማደናገር ያመጣው እንጂ አነሳሱ ለድርድር ነበር። እንደሚታወቀው ድርድርም ሆነ ክርክር ወይም ውይይት የየራሳቸው የሆነ ስርዓት አላቸው። ሶስቱም በአንድ ሰነድ ሊሆኑ አይችሉም። ኢህአዴግ በመጀመሪ ሲጠራን ለድርድር ብሎ ቢሆንም አሁን የሚታየው አዝማሚያ ግን ወደኋላ የማፈግፈግ ሰሜት ነው” ብለዋል።

የአቶ የሽዋስን ሀሳብ የሚያጠናክሩት የኢዴፓው ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው “አርብ ባደረግነው ውይይት ሰፋ ያለጊዜ ወስደን የተነጋገርነው በርዕሱ ላይ ነበር። እኛን ጨምሮ የተወሰኑ ፓርቲዎች ድርድር እንጂ ክርክርም ሆነ ውይይት የማንቀበል መሆናችንን ገልጸናል። ኢህአዴግና ሌሎች ደግሞ ሶስቱም ሀሳቦች እንዲካተቱ ጠይቀዋል። ሌሎቹ ደግሞ ድርድርና ክርክር የሚሉትን ነጥቦች ይዘው መሄድ ይፈልጋሉ። በዚህም ምክንያት መግባባት ባለመቻላችን በሰነዱ ይዘት ላይ እንድንወያይ ተደርጎ ከዚያ በኋላ ርዕሱ እንዲወሰን ነው ተነጋግረን የተለያየነው” ሲሉ ሶስት ጉዳዮችን የያዘውን ሰነድ ፓርቲያቸው እንደማይቀበለው ገልጸዋል።

ዶክተር ጫኔ ከመወያያ ሰነዱ ርዕስ በተጨማሪም በዓላማውና ዓላማውን ለመቅረጽ በወጡ ሀሳቦች ላይ አንዳንድ ቃላትና ሀረጎች ትርጉማቸው አሻሚ በመሆናቸው እንዲሻሻሉ ለማድረግ ውይይት መካሄዱን ገልጸዋል። የኢዴፓው ሊቀመንበር “አሻሚ ትርጉም ያላቸው ቃላት” ያሏቸውን ሲገልጹም “ለምሳሌ በኢህአዴግ ከቀረበው ሀሳበ ላይ የሚሻሻሉ ህጎች ካሉ ማሻሻል የሚል ይገኝበታል። እኛም ይህን ሀሳብ ስንመለከተው መሻሻል ያለባቸው ህጎች እንዲሻሻሉ ተብሎ ይስተካከል እንጂ “ካሉ” የሚለው ቃል የገባው ለማደናገር ካለሆነ በስተቀር ህጎች እንዲሻሻሉ እኮ ነው የተሰበሰብነው ብለን አቋማችንን ገልጸናል። በእኛ በኩል የቀረበውንና ኢህአዴግ ሃሳብ የሰጠበት ደግሞ አሳሪ የሆኑ ህጎቸ ሁሉ ይሻሻሉ የሚለውን ሲሆን አሳሪ የሚለውን ገላጭ ቃል መጠቀማችን ገና ወደ ድርድር ከመግባታቸሁ በፊት አቋመ እየወሰዳችሁ ይመስላል ሲል ተከራክሯል። በሌላ በኩል ደግሞ የብሔራዊ መግባባት እውን እንዲሆን የሚለው ሀረግ ላይ “እውን መሆን” በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ሰፊ ውይይትና ንግግር አካሂደንበታል” ሲሉ የካቲት 24 ቀን 2009 ዓም ፓርቲዎቹ ያካሄዱትን ውይይት ውሎ ገልጸዋል።

መኢአድም በድርድር እንጂ በውይይትና ክርክር በሚሉ ርዕሶች ላይ መወያየት እንደማይፈልግ አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል።

በመርፌ ቀደዳ እንደመሹለክ

“ኢህአዴግ ለይስሙላ ካልሆነ በቀር በሰጥቶ መቀበል የማያምን ፓርቲ ስለሆነ አሁን የተጠራው የድርድር ሂደትም ውጤት ሊያመጣ አይችልም” ሲሉ ስጋታቸውን የሚገልጹ ወገኖች አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ “በጥልቅ ተሃድሶ” ውስጥ የሰነበተው ኢህአዴግ “ለአገር ሰላምና ለህዝብ ደህንነት አልፎ ተርፎም ለራሱ ህልውናም ሲል ድርድሩን ከልቡ ያደርገዋል” ሲሉ ሀሳባቸውን የሚሰነዝሩ ወገኖች አሉ። የመጀመሪያውን ሀሳብ የሚያራምዱት ወገኖች ሀሳባቸውን ሲያጠናክሩም “ኢህአዴግ ሰጥቶ በመቀበል አምኖ ለተቀናቃኞቹ ስልጣንን እስከማጋራት የሚያደርስ ድርድር ያደርጋል ማለት ዘበት ነው። ለተቀናቃኞቹ ጥረታቸው ግመልን በመርፌ ቀዳዳ እንደማሾለክ ነው” ይላሉ።

በዚህ ዙሪያ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የመኢአድ፣ የሰማያዊና የኢዴፓ አመራሮች “ሂደቱ የቱንም ያህል የተጓተተ ቢሆን እና ኢህአዴግ የቱንም ያህል የራሱን ጥቅም ብቻ የሚያሳድድ ፓርቲ ቢሆንም ዳር ላይ ቆሞ ከመመልከት ተሳትፎ አድረጎ ማየት የተሻለ ነው” ሲሉ ገልጸዋል። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ “ከአስር ዓመት በኋላ ከጋራ ምክር ቤቱ አባል ፓርቲዎች ስብስብ ውጭ የሆኑ ፓርቲዎችንም ለድርድር መጋበዙ ይሁንታ የምንሰጠው ጅምር ነው” ያሉ ሲሆን የድርድርን አስገዳጅነት ሲገልጹም “ይህ በፍላጎት (በኢህአዴገ ፍላጎት ላይ ለማለት ነው) ላይ ብቻ የተመሰረተ ሳይሆን አገርን ህዝብንና ራስነ (ኢህአዴገን) ለማዳን የመጨረሻው አማራጭ ነው። ምንም እንኳ እስካሁን ያሉት ሂደቶች መልካም የሚባሉ ባይሆንም ኢህአዴግ ለራሱ ህልውና ሲል ከልቡ ሊያካሂደው ይችላል ብለን እናስባለን” በማለት የፓርቲያቸውን እምነት ገልጸዋል።

የመኢአዱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ በበኩላቸው “ከድርድሩ ቅድመ ዝግጅት የታዘብነው ተስፋ አስቆራጭነት ሳይሆን ተስፋ ሰጭ መሆኑን ነው። ለ11 ዓመታት የተዘጋውን በር ከፍቶ ከተፈካካሪ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ለማድረግ መጀመሩ በራሱ ተስፋ ሰጭ ሂደት ነው።” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “የታሰበውን ያህል ውጤት ሊመጣ ይችላል ወይ? ለሚለው እሱን ወደፊት የምናየው ነው። የታሰበውን ያህል ውጤት ባይመጣ እንኳ ፈፅሞ ውጤት አይመጣም (አታመጡም) ማለት ስህተት ነው” ሲሉ ከድርድሩ ተስፋ የሚያደርጉትን ተናግረዋል።

የመድረኩ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ደግሞ እስካሁን የተካሄደው ስብሰባ ብዙም ተስፋ ሰጪ አለመሆኑን ተናግረዋል። ሆኖም ከነገው ስብሰባ በኋላ ነገሮች ሊለወጡ እንደሚችሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል። የኢዴፓው ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ በበኩላቸው የድርድሩን አስፈላጊነት ገልጸው ሆኖም በተለይ እንደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያሉ ጉዳዮች በፓርቲዎቹ እንቅስቃሴ እና በፖለቲካ ምህዳሩ ላይ የሚያሳርፈው አሉታዊ ተጽእኖ ከፍተኛ ስለሆነ ሊታሰብበት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የህወሓት ተለጣፊው ብአዴን እና ህወሓት አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸው ተሰማ፣- ሚኒልሊክ ሳልሳዊ

$
0
0

መላው የአማራ ህዝብ ባነሳቸው የማንነት ጥያቄወች ዙሪያ መላ ህዝቡ በውስጥም በውጭም እየተደራጀ በሚያካሂደው ተጋድሎ የተርበደበደው ህወሓት የብአዴንን አመራርና አባላት በጠላትነት ፈርጇል።

እርግጥ ነው እንደምንሰማው ብአዴን ውስጥ ቀላል የማይባል ቁጥር የህወሓትን ረጅም እጅ ለመቁረጥ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውንና ህዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄወች በመልካም ነገር እንደሚመለከቱት እየታወቀ መጥቷል። ህወሃት ይህንን የገጠመውን ተጨማሪ ፈተና ለማለፍ በህወሃት አገልጋይነታቸው የታወቁትን እነ በረከት፣ አዲሱ ለገሰ፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ታደሰ ካሳ፣ ካሳ ተክለብርሃን፣ ከበደ ካሳና ደመቀ መኮነንን በዋነኛት በመያዝ ሰሞኑን የክልሉን ብአዴን አመራርና አባላት በስብሰባ ሲያምሱ ሰንብተዋል።በተካሄደው ስብሰባም ጸረ-ህወሓት አቋሞች በስፋት የተንጸባረቁ ሲሆን የወልቃይትና የራያ ጉዳይም በሸወርዋራው ተነስተዋል።የህወሃትን ተልዕኮ ለማስረጽ የመጣው ቅጥረኛ ጉጅሌም በመድረኩ ሙቀት በመደናገጥ የማባበልና የማሸማገል ስራ ላይ አተኩረው መሰንበታቸው ታውቋል።ስብሰባወቹ ሳይግባቡ ተግባብተው የተጠናቀቀ ቢሆንም ከስብሰባ በኋላ የወጡ የጹሁፍና የተሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫወች በህወሃት ጫና የቀረቡ እንጅ የብአዴንን የአባላትና የአመራር የስብሰባ ውጤት የተመለከቱ እንዳልሆነ ከውስጥ የሚወጡ መረጃወች አረጋግጠዋል።
ህወሃት በጸጥታ መዋቅሩም ማለትም በመከላከያ፣ በፖሊስና በደህንነቱም አካባቢ አስተማማኝ ያልሆነ ሁኔታ እንደተፈጠረበት ቅርብ የሆነ መረጃወች እያረጋገጡ ነው።እናም ህወሃት አጋሬና አሽከሬ የሚላቸው ድርጅቶች በምግባሩ በደንብ እየጠሉትና እየከዱት መሆናቸው ሲታወቅ የጸጥታ ሃይሉም ውስጥም እየተፈጠረ ያለ ትርምስ ተደማምሮ ለከፍተኛ ስጋት ተደርጓል።

በዚህ የህወሃት ቁስል ላይ የትምህርት ተቋሞች፣ በገጠርና በከተማ የሚኖረው ህዝብ አመጽ ሲደመርበት የነጻነታችን ቀን የመጀመሪያው መጨረሻ ላይ መሆናችን እንረዳለን።የሚጎለን ነገር ቢኖር!በአገር ቤት እየተካሄዱ ያሉ የማንነት ተጋድሎወችን በአግባቡ መደገፍና በተለይም የአማራ የፖለቲካ ሃይሎች ልዩነቶቻቸውን አጣበው ድክመቶቻቸውን አርመው በዋና ጠላታችን ላይ ማተኩር መቻል ነው።

ወያኔ የቆመበት አዲስ የኮንቬንሽናል ጦርነት ዋዜማ የለም፤ ለዋዜማ ሬዲዮ – መስቀሉ አየለ

$
0
0

ዋዜማ ራዲዮ፡ “የኢትዮጵያ መንግስት “የደህንነት አደጋ ደቅነውብኛል በሀገሪቱ ስላምና መረጋጋትን አናግተዋል” ያላቸውን ሀይሎች ለመፋለም እየተዘጋጀ መሆኑን በገዥው ፓርቲ ዙሪያ ላሉ ቁልፍ ሹማምንትና ለደህንነት አካላት ሹክ ብሏል።

ኢህአዴግ በተለይ በአማራና ኦሮምያ ክልሎች ተከስቶ የነበረው ህዝባዊ አመፅ እንዳይደገም ይረዱኛል ያላቸውን እርምጃዎች በሁለት ዘርፍ ከፍሎ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰናዳ መሆኑንም ለዋዜማ የደረሰ መረጃ ያመለክታል። ከእርምጃዎቹ አንዱ በኤርትራ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ መለወጥና በአስመራ ላይ ስልታዊ እርምጃ መውሰድ እንዲሁም በውጪ ሀገር ያሉ ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎችን በህግ ፊት ማቅረብና ማዘጋትን ያካትታል። አርበኞች ግንቦት ሰባትና ኦነግ እንዲሁም ኢሳትና ኦ ኤም ኤን የአዲሱ የመንግስት ጥቃት ኢላማ መሆናቸውን የመንግስት የቅርብ ምንጮች አረጋግጠዋል። በኤርትራ ላይ የተዘጋጀው አዲስ ዕቅድ በቅርቡ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ሲሆን በሌሎቹ ጉዳዮች ላይ አለማቀፍ አማካሪ ለመቅጠርና የምዕራባዉያንን ትብብር ለመጠየቅ ዕቅድ ተይዟልዕ ሲል በዚህ ሳምንት ዘግቧል።

ይህን ዘገባ ተከትሎ በማህበራዊ ድህረገጽ ላይ የተንሸራሸሩ የተለያዩ መላ ምቶችን የያን ሲሆን በጉዳዩ ላይ የተጨነቁም አልጠፉም። የብዙዎቹ የጭንቀት ምክንያት ግን በዋነኛነት የአዲሱ የትራምፕ አስተዳደር በባህሪው ነገሮችን የሚያይበት መንገድ ከተለመደው ወጣ ያለና ነጮቹ “አንፕሪዲክተብል” የሚሉት አይነት በመሆኑ ምናልባት በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የገባውን ቃል አጥፎ ከወያኔ ጋር መዳራቱን ከቀጠለ እንደ ገና በትራምፕ አስተዳደር ድጋፍ የእድሜ ማራዘሚያውን ትኬት በመቁረጥ ተጨማሪ የስቃይ አመታት እንገፋ ይሆናል ከሚል ስጋት ነው።

በኔ እምነት ግን እንዲህ ያሉ ነገሮች እንደወረዱ መታየት የለባቸውም ባይ ነኝ።ምክንያቱም በተደጋጋሚ እንደ ታየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና የፖለቲካው ዳይናሚክስ ወደየት እያመራ እንደሆነ ማሰብ ሲሳነው እንዲህ አይነት አጀንዳዎችን በመፍጠርና ወደ ሰው በመወርወር የህዝቡን ቀልብ ወደ አንድ አቅጣጫ የመሳብና ብዥታ የመፍጠር ስልት ይጠቀማል። የእሩቁን ትተን ባለፈው ሃምሌ ወር አካባቢ የነበረውን እንኳን ብናስታውስ አሁን ከነደፈው እቅድ የበለጠ የተጨበጠና የምር የሚመስል እቅድ ወጣ በተባለ በጥቂት ግዜ ውስጥ እቅዱን የእውነት ለማስመሰል በኤርትራ ድንበር በኩል ወረራ የሚመስል ነገር ለማካሄድ ሞክሮ እንደ ነበረ የሚታወስ ነው።
እቅዱም “የሻቢያን አከርካሪ እስከ መጨረሻው የሚሰብርና ሻቢያን በታማኝ ቡድኖች ለመተካት እንዲያስችል የሻቢያን ተቃዋሚዎች ያሳተፈና እግረ መንገዱንም በኤርትራ የመሸጉትን ጸረ ወያኔ ተቃዋሚዎች እግር ሳያወጡ በእንጭጩ ቆርጦ በማስቀረት አስተማማኝ ሰላም መፍጠር” የሚል አላማን የያዘ ነውም ተብሎ ነበረ። ይኽንን ነገር ተከትሎ በኢሳት ቴለቪዥን ጭምር ባለሙያዎች እየቀረቡ “ጦርነቱ ወይ አስመራ ወይንም አዲስ አበባ ይጠናቀቃል” የሚል ትንታኔ ሲስጡበት የነበረ ቢሆንም በሁለት የተለያየ ግንባር እጁን የሰደደው ወያኔ ለመጨበጥ የሞከረው አለሎ ምን ያህል አደገኛ እረመጥ እንደ ነበር እሳት ውስጥ እንደገባ ላስቲክ በጥቂት ግዜያት ውስጥ ተኮማትሮ የቀረው በመቶዎች የሚቆጠረው የአጋዚ ሰራዊት ማስረጃ ነው። ባጭሩ የትም ያልደረሰ ድንፋታ እንደነበርና ያ ሁሉ ዝርዝር ፕላን ባዶ ምኞቱን በወረቀት ላይ ከማስፈር በላይ ተሻግሮ የመሄድ ብቃትም ሆነ አላማ እንዳልነበረው አስመስክሮ ያለፈበት ዲስኩር እንደ ነበር ይልቁንም ወያኔ አሁን ያለበትን ቁመና ከፍቶ በማየት ይኽ የወጣው ሰነድ ዛሬም እንደ ትናንቱ ባዶ ፊኛ መሆኑን ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል:;

፩ በብዙ መመዘኛ ወያኔ ከአምናው ይልቅ ዘንድሮ የተዳከመ ቁመና ላይ መሆኑ እሙን ነው። ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ወደ ህዝባዊ ተጋድሎ ተሸጋግሮ በብዙ የአማራው ከፍተኛ ቦታዎች አካባቢ ነውጡ በመሳሪያ ሃይል መታገዝ የጀመረበት፣
፪ ብዙ ገጠራማ ቦታዎች ከወያኔ ቁጥጥር ውጭ በመሆናቸው ስልጠናው በዚሁ አካባቢ ስልጠና የሚሰጠጥበት;
፫ ትግሉ እየበሰለ፣ ህዝቡ ይበልጥ ወደ በረሃ እየተመመና ለመረረ መስዋእትነት እራሱን እያዘጋጀ ያለበት;
፬ ቀሪውም ህዝብ ነጻ አውጭ ከመጠበቅ ይልቅ ትግሉ እቤቱ በር ላይ እስኪ ደርስለትና እራሱም የድርሻውን ለመወጣት በጥፍሩ ቆሞ የሚጠብቅበት
፭ ኢህአዴግ የሚባለው የወያኔ ጭምብል ወልቆ TPLF እርቃኑን የቆመበት ብቻ ሳይሆን እራሱ በአንጃ የተከፈለበትና ማእከላዊነት የጠፋበት;
፮ በአለም ላይ ይኽ ነው የሚባል የውጭ ፖሊሲ የሌለው መንግስት ቢኖር የወያኔ መንግስት እንደመሆኑ ለሩብ ምእተ ዓመት ያህል ኢትዮጵያን ታህል አግር እየገዛ ኢትዮጵያዊ መሆን ያልቻለና ከትግራይ ውጭ ማሰብ የተሳነው እና ለግዜው እስከጠቀመው ድረስ የአገሪቱን ብሔርዊ ጥቅም እጅ መንሻ ሲያደርግ መኖሩ ይልቁንም ከአገሪቱ መዳከም እጠቀማለሁ ብሎ በቆሻሻ ስሌት ውስጥ እንዳልኖረ ዛሬ ያ ሁሉ ኑፋቄ ተጠራቅሞ ወደ አንዳች መርገምት መቀየር የጀመረበትና የእጁን ለማፈስ የተቃረበበት አካባቢያዊ ሁኔታ መፈጠሩን የአለም መገናኛ ብዙሃን የዘገቡት ሃቅ ነው። እንደ ሴተኛ አዳሪ ቀሚሱን እየገለበ ከማንም ሴረኛ መንግስታት ጋር አንሶላ ሲጋፈፍበት የነበረበት ዘመን አልቆ በሶስት መቶ ዲግሪ ወታደራዊ ከበባ ላይ የወደቀው ወያኔ የትናንቱዋን ደቡብ ሱዳን እንኩዋን ማስፈራራት ያልቻለበት፤ብሎም አዲሱ የትራምፕ አስተዳደር ይወስዳል በሚባለው የበጀት ድጎማ ፖሊስ ስረዛ የተደናገጠበት፤
፯ በማይናወጽ አለት ላይ “በሁለት እግሩ ተከልነው” ሲሉት የነበረው “ህገ መንግስታችን” የሚሉት ድሪቶ አቅም አልባ ሆኖ አገሪቱ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ውስጥ ለመንፈቅ ያህል የቆየችበት ብቻ ሳይሆን ዛሬም ድረስ ድፍረት ኖሮት ይኽን አዋጅ ለማንሳት በራሱ ላይ እምነት ባጣበት በዚህ አጣብቂኝ ሰዓት በምን ስሌት ነው በሻቢያና በዚያው ምድር ላይ አሉ በሚላቸው የታጠቁ ጸረ ወያኔ ሃይላት ላይ ደፍሮ ጦር የሚሰብቀው?

በእርግጥ አንጻራዊ በሆነ መልኩ ወያኔ መለስ በነበረበት ግዜ ማእከላዊ አመራር የነበረው ሲሆን የፖለቲካውም ሃይል በስለላ ክንፉም ሆነ በወታደራዊው መዋቅር ላይ ከፍ ያለ ጉልበት እንደነበረው ያም ሆኖ ግን ሻቢያንም ሆነ ድንበር ተሻግሮ ተቃዋሚዎቹን ለመምታት የሚያስችል ቁመና እንዳልነበረ የሚያውቀው መለስ ከሻቢያ ጋር ለመታረቅ ሰባ ሁለት ግዜ ያህል አማላጅ መንግስታት፣ ታዋቂ የአገር ሽማግለዎችን እና በሚስጥር ደግሞ የታሸገ ፖስታ ለአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ በማስያዝ ናይሮቢ ለሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ መላኩን እናውቃለን።ያም ሆኖ ግን ያ ሁሉ ደጅ ጥናት ውሃ ነበረ የበላው።

ለማጠቃለል ያህል ወጣ የተባለው ዘገባ አሁንም እንደ ባለፈው ላንድ ሰሞን የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሆነ ተብሎ በሳሞራው አገዛዝ የተለቀቀ ባዶ ዲስኩር ብቻ ነው። ዛሬ የወያኔ የፖለቲካና የስለላ ክንፍ ከሳሞራ ተገንጥሎ በራሱ ዛቢያ በሚሽከረከርበት፣ ሳሞራ ከመከላከያ ቢሮ ባሻገር የአራት ኪሎውን ምንጣፍ መጎተት በጀመረበት ሁኔታ ድንበር ተሻጋሪ ጦርነት መክፈትና ያሰበውን ማሳካት ቀርቶ በሰላማዊ መንገድ ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችል አጀንዳ ለመቅረጽ አቅም እንደ ሌለው እግር ጥሎት ወያኔን የወረሰውን የቁምጥና ደዌ መጠኑን የታዘበ መንገደኛ ሁሉ ያውቀዋል። ወያኔ እኮ በባድመ ዘመቻ ወቅት በተሻለ የህዝብ ድጋፍና ቁመና አንድ ሆኖ ዘምቶ ሶስት ሆኖ ነበር የተመለሰው። ዛሬ ያ ቁመና ላይ አይደለም።ዛሬ ከውስጥም ከውጭም ምንነቱ እንደ ሽንፊላ ተገልብጦ እንደ እንዝርት ተፈርቅጦ የታወቀው ይሕ ቡድን መረብን መሻገርና ኮንቬንሽናል ጦርነት ማካሄድ ቀርቶ ከጎንደር ከተሞች ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገዛው የገጠር ቀበሌ እንደሌለ ያውቀዋል። ዛሬም እንደ ባለፈው ሁሉ እንዲሁ አለሁ ለማለት ያህል ብቻ በባድመማን በጾረና ድንበር አካባቢ መጠነኛ ትንኮሳ ሊያደርግ ከሚችል በቀር።

ውይይቱ በተቀደው መስመር እየሄደ ነው፡- ግርማ ሰይፉ ማሩ

$
0
0

ወዳጆቼ እንግዲህ ውይይቱ በተቀደው መስመር እየሄደ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ በአካሄዱ ላይ ከግምታችን ውጭ የሆነ ነገር የለም፡፡ ውይይቱ በሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መካካል ነው ሲባል ቆይቶ ኢህአዴግ ለበዓሉ ድምቀት በሚል የክልል ሀጋሮች ይግቡ፤ የሚል ሃሳብ ጫር ማድረጉን ሰምተናል፡፡ ለምን? ብለን ጠይቀን ማለፍ ይኖርብናል፡፡ የመድረኩ ፕሮፌሰር በየነ ቀደም ሲል አቅረበውት የነበረውን ሃሳብ (መሪ ተደራዳሪ መሆን አለብን የሚል ነው፡፡) አጥበቀው ለመሞገት ከሌሎቹም “ተቃዋሚ” ተብዬዎች ጋር እሰጥ አገባ ለመግጠም አልቦዘኑም፡፡ ከዚህ የተረዳሁት ነገር ቢኖር፤ መድረኮች ሃሳቡን በመጀመሪያ ካቀረቡበት ቀን ጀምሮ ከሌሎች አባላት እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ያለማድረጋቸውን፤ እንደተለመደው ፕሮፌሰሩ አብዛኛውን ጊዚያቸውን በላቦራቶሪ ጥናት ላይ አሳልፈው ካቆሙበት ለመቀጠል ወደ ስብሰባ መምጣታቸውን የሚያሳብቅ ነው፡፡ በመድረክ ውስጥ ቢያንስ በጉልዕ የምናውቃቸው እነ ገብሩ አስራት ይህን ሃሳብ አምነውበት ከሆነ ፕሮፌሰሩን የላኳቸው፤ በግሌ ገብሩ አስራት ህወሓትን ረስቷል ብዬ መሳሳት ስለማልፈልግ፣ ፕሮፌሰሩን ባወጣው ያውጣው ብሎ ሊማግዳቸው ቆርጧል ብል ይቀለኛል፡፡ ከዚህ ውጭ መድረክ ውስጥ ይህ ነው የሚባል የፖለቲካ ሀሁ ገብቶት ፕሮፌሰሩን አይ የሚላቸው ስለማይኖር በቀጣዩ ዙር ስብሰባውን ረግጠው እንደሚወጡ ይጠበቃል፡፡

በእኔ እምነት ኢህአዴግ በሚያሳዝን ሁኔታ ውይይቱ በገለልተኛ አደራደሪ ይመራ የሚለውን የፈለገው አይመስልም፡፡ ምክንያቱም በውይይቱ ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ ለአንድ ቀን እንኳን ቢሆን፤ በሰብሳቢ ወንበርነት መቀመጥ ብርቃቸው ስለሆነ ለዚህ ሲሉ ይህን እንደሚደግፉት ያውቃል፡፡ በድምፅ ብልጫ ከሆነ የኢህአዴግ ሃሳብ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ ስብሰባውም አይረቤ መሆኑ ሰለሚረጋገጥ ይህን ጊዜ በቃኝ ማለት የጨዋ ስራ ይመስለኛል፡፡ የዚህ ስብሰባ ሌላው አስቸጋሪው ክፍል በስብሰባው የሚሳተፉት በዋነኝነት በኢህአዴግ እነ አቶ አስመላሽ፤ በተቃዋሚዎች ደግሞ እነ ፕሮፌሰር በየነ መሆናቸው ነው፡፡ በሁለቱም ወገን ሰጥቶ ለመቀበል ሳይሆን ለመቀማት የተዘጋጁ ናቸው፡፡ እነዚህ ተደራዳሪዎች የባህሪ ለውጥ ባላመጡበት ሁኔታ የቀድሞ ጉዳይ እያሰላሰሉ ወደ አዲስ ውጤት መጓዝ አስቸጋሪ ነው፡፡ ኢህአዴግ የካቲት 30 በነበረው ስብሰባ ዘና ብሎ ተቃዋሚዎችን ሲያቧጭቅ ከዋለ በኋላ ከፈለጋችሁ በነጠላ (21 ችሁም) ፤ ከፈለጋችሁ ደግሞ በሃሳብ ተደራጅታችሁ በቡድን፤ ካልሆነ ደግሞ ሁላችሁም በአንድ ላይ ሆናችሁ ልገጥማችሁ ተዘጋጅቻለሁ ብሎ፤ በማላገጥ ውይይቱን አጠናቋል፡፡ አንድ ሆነው እንደማይቀርቡ ይታወቃል፡፡ በእኔ እምነት አሁን ባለው ተቃዋሚዎች ሶሰት ቡድን ከቻሉ በራሱ እጅግ መልካም ይሆናል፡፡ ለማነኛውም ውይይቱ መቀጠል የሚኖርበት ከሆነ ወሳኙ ጉዳይ ተቃዋሚዎች ቆም ብለው ማሰብ ይኖርባቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ኢህአዴግ አሁን ከሚያሳየው ሁኔታ ቀርጠኛ እንዳልሆነ ይሰማኛል፡፡

ይህ ውይይት አንዳች ውጤት እንዲያመጣ ከታሰበ ከፍተኛ ሃላፊነት የሚሰጠው አደራዳሪ አካል እንዲቋቋም ማድረግ የግድ ነው፡፡ ይህን አካል ለማቋቋም ለኢህአዴግም ለተቃዋሚዎችም የጋራ የሆኑ ሰዎች በበቂ ሁኔታ ማግኘት አሰቸጋሪ ስለሆነ (እንደ አገር እዚህ ደረጃ መድረሳችን ያሳፍራል)፤ ከኢህአዴግ የሚመረጡ 2 ሰዎች፣ ከተቃዋሚ የሚመረጡ 2 ሰዎች እና አንድ በጋራ የሚመረጥ ሰብሳቢ መሰየም ያስፈልጋል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የሚመርጧቸው ሰዎች የፖርቲ አባል ያልሆኑ፤ ይህች ሀገር የገባችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ የተረዱ እና ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጡ የሚችሉ፤ ሃሳቦችን ማመንጨት የሚችሉ ግለሰቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ አደራዳሪ አካል ሌሎች ተግባራትንም ለማከናወን ሃላፊነት የሚሰጠው ቢሆን ደግሞ ሁኔታውን የተሻለ ያደርገዋል፡፡ በዙር በሚደረግ የሰብሳቢነት ውይይት የፓርቲዎች ምክር ቤት የሚባለው ሲያደርግ እንደነበረው ቀልድ ለመቀለድ ብቻ የሚደረግ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ ሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ትናንትና ዛሬ – ፋሲካ ገ/ጻዲቅ ወ/ሰንበት

$
0
0

ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ተ/ምሊቀመንበር የነበሩት

ሰላም ክቡራትና ክቡራን ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፤ በዛሬው ዕለት የምናገርበት ርእስ ስለሴቶች በብዛት ወደ ነጻነት ትግሉ ጎራ አለመቀላቀል ቢሆንም እግረመንገዴን በወንዶች የተመላው እና የሴት ያለህ የሚለው የትግል ጉዞአችን ለምን እንደሚጠየቀው ጾታዊ ስብጥር የለውም የሚለውን ሃሳቤን አካፍላችሁዋለሁ። እንደመንደመሪያ፤ የሴቶች ሚና በሃገራችን የታሪክ ሂደት ውስጥ ምን ይመስል እንደነበረ ጥቂት እውነታዎችን፤ እንዲሁም ባለፉት 25 ዓመታት በተደራጁትና ህወሃት መራሹን ስርዓት በሚቃወሙት ድርጅቶች ውስጥ፡ የሴቶች ተሳትፎ ለምን ሊበረታታ እንዳልቻለ የበኩሌን እይታ እገልጻለሁ። ዓላማዬም ካለፉት ድክመትና ጥንካሬዎቻችንን ተምረን ነገን ብሩህ ለማድረግ፤ ፍትህ እኩልነት፤ ሰብዓዊትና የዜግነት መብት የተከበረባት ኢትዮጵያን፡ እኔ እንደማልማት እንድታልሟት ራዕዬን ማካፈል ነው።

ሴት ልጅ በጡንቻ ካልሆነ በቀር በማንኛውም ነገር ከወንድ ልጅ አታንስም፤ እሱንም ስፖርት ካዘወተረች ትደርስበታለች። ሴት ልጅ ተፈጥሮዋ ሆኖ ሊሆን ይችላል፡ ትራራለች፤ ትሳሳለች፤ ላመነበችበት ዓላማ መስዋዕትነት ትከፍላለች፤ እጅግ ትታገሳለች፤ ሲበቃት ደግሞ አራስ ነብርን ታስንቃለች። ሴት ልጅ እቤት የምትውለው ሳታውቅ ቀርታ፤ ዝም የምትለው ፈርታ፤ አይዞህ የምትለው ሳይከፋት ቀርታ፤ ዝቅ የምትለው መከበር ጠልታ አይደለም። ኑሮዋን፤ ልጆችዋን፤ ዓላማዋን፤ ከፍ ሲልም የማህበረሰቧን ሰላምና ደህንነት ቅድሚያ ሰጥታ እንጂ።  በአንድ ወቅት በካናዳ የቀድሞዋ የሚሲሳጋ ከንቲባ ሄዘር ማካሊዮን፡ በቅጽል ስማቸው ኸሪኬን ሄዘር፤ 12 ጊዜ በህዝብ ተመርጠውና ለ36 ዓመታት በከንቲባነት አገልግለው በ93 አመታቸው በበቃኝ ለምርጫ መወዳደር ከማቆማቸው በፊት CBC ሬድዮ ላይ ቀርበው በስራ ዘመናቸው ከወንዶች በኩል ምን ያህል ፈተና እንደደረሰባቸው ሲጠየቁ የሰጡት መልስ፤ የሳቸውን የሃላፊነት ተግባር ለመቀበል የሚያንገራግሩት ከወንዶች ይልቅ ብዙ ጊዜ ሴቶች እንደነበሩ ተናግረው ነበር። እምነታችንም፤ ትምህርታችንም፤ ማህበረሰባችንም ስለ ሴት ልጅ ክብር፤ እኩልነትና አስተዋጽኦ እዚህም እዚያም

ቢጠቃቅስም፡ በተግባር ግን ሴት ከወንድ እኩል መሰለፍ መቻሏን ለመቀበል፡ ዲሞክራቲክ የሚባለው ካናዳ ውስጥ እንኳን መቸገራቸውን የኸሪኬን ሄዘር ተሞክሮ አንድ ምሳሌ ነው።

ወደ ሃገራችን ጉዳይ ስንመለስ፤ በኮ/ል አሌኸንድሮ ዴል ባዬ ተጽፎ በ ዶ/ር ተስፋዬ መኮንን ባይለየኝ በተተረጎመው ቀይ አንበሳ በሚባለው መጽሃፍ ውስጥ (1992፤ ገጽ 183፤84) ጸሃፊው የአለማየሁ ባሪያ ወይም “ማሚቴ” ብሎ እንደሚጠራት የትግራይ ሴት፤ በታሪካችን ሂደት ለሃገራቸው የተለያዩ አስተዋጽኦዎችን ያበረከቱ እንዲሁም ሃገራቸውን ከጠላት ወረራ  ለመታደግ በተደረጉ የጦርሜዳ ውሎዎች የተሳተፉ ነገር ግን ስማቸውን እንኳ በውል የማናውቃቸው ብዙ ባለውለታ ሴቶች ነበሯት፤ ዛሬም ከመጋረጃው ጀርባ  ብዙ ስራዎችን እንደሚሰሩ ጥርጥር የለኝም።

በአንጻሩ፤ ገድላቸው ከተከተበላቸው ነገስታት መሃከል፡ በቅድሚያ ንግስት እሌኒን ለማንሳት እወዳለሁ። ንግስት እሌኒ በፖለቲካና ዲፕሎማቲክ ብስለታቸው የሚደነቁ፡ በ16ኛው ክ/ዘመን ሊፈቱ የሞከሩት ችግር ዛሬም ያልተፈታ፡ የምስራቅ አፍሪካንና የመካከለኛው ምስራቅን አካባቢያዊ ቅራኔ እንዲሁም የአውሮፓዊያንን አሰላለፍ ያስተዋሉና የአለምአቀፍ ግንኙነት አካሄዱ ጠንቅቆ የገባቸው ሴት ነበሩ። ንግስት እሌኒ አባታቸው ገራድ አህመድ የተባሉ የደዋሮ ሰው ነበሩ። በዚያን ጊዜ ደዋሮ ተብሎ የሚጠራው ከሸዋ በስተምስራቅና በስተሰሜን፤ የዛሬውን አዳማን ጨምሮ፤ በስተምስራቅ ከአዳል ሡልጣናዊ ግዛት በኩል እያጠቃለለ የሚዋሰን የነበረው ስፍራ ሲሆን፤ አብዛኛው ህብረተሰብ የእስልምና  እምነት ተከታይ ነበረ ይሉናል አቶ ይልማ ደሬሳ (የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን 1959፤ ገጽ 13፤14)።

እሌኒ አጼ በዕደ ማሪያምን አግብተው ንግስት የሆኑ ሲሆን፡ ባለቤታችው በሞት ከተለዩዋቸው በኋላ፡ ለዐጼ እስክንድርና አጼ ያዕቆብ በእንደራሴነት፤ ልጃቸው ዳግማዊ ዐምደ ጺዮን ነግሶ ህይወቱ ሲያልፍ ደግሞ፡ ለልጃቸው አጎት ለዐጼ ናዖድ የበላይ አማካሪ ሆነው በወቅቱ በቱርኮች የተቃጣውንና ለኢትዮጵያ ህልውና

አስጊ የነበረውን ሁኔታ፡ ፖርቹጋሎችን እርዳታ በመጠየቅ፤ ከአካባቢያችን አረብ ሃገሮች ጋር ጥሩ ጉርብትና  እንዲኖር በመስራት፤ እንዲሁም ከአዳል ሱልጣኔቶችና ከሌሎችም አሚሮች ጋር ቤተሰባዊ ዝምድና ስለነበራቸው፡ ከማዕከላዊ መንግስቱ ጋር የአስታራቂነትና የዲፕሎማቲክ ሚና በመጫወት፤ ለ400 አመታት የቆየን ግጭት ወደ ሰላማዊ ግንኙነት ለመቀየር አስችለዋል (ይልማ ደሬሳ የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን 1959፤ ገጽ 18፤19፤21፤24፤25)። ንግስት እሌኒ የሃይማኖት ልዩነት ሳይበግራቸው እስላሙን፤ ኦርቶዶክስና ካቶሊክ ክርስቲያኖችን፤ ሃገራቸውን ከጎረቤት አፍሪካ ሃገሮችና ከአረቦች እንዲሁም ከአውሮፓዊያንን ጋር አግባብተው መስራት የቻሉ ተራማጅና፤ አርቆ አሳቢ ሴት ነበሩ።

በመቀጠል፡ የዐጼ  ባካፋ  ባለቤት የነበሩት የቋራ ተወላጅዋ እቴጌ ምንትዋብን ብንወስድ፡ በጣና ደሴት ላይ ዛሬ  የቱሪስት መስህብ የሆኑትን፡ የወንዶች ብቻ የሆነውን ክብራን ገብርኤልን ጨምሮ፤ ትልልቅ አድባራትና ገዳማትን ያሰሩ ሲሆን፤ በልጃቸው በዐጼ እያሱ ብርሀን ሰገድ ዘመንም በሞግዚትነት ነግሰው ትምህርት እንዲስፋፋ ለማድረግ ከአረቢኛ ወደ ግእዝ ያስተረጎሟቸውን መጽሃፍት፡ ተማሪዎች ከሸዋ፤ ከትግሬና ከጎንደር ወደ ደሴቷ መጥተው ለቀለባቸው ሳያስቡ ለዓመታት መጽሃፍቶቹን እንዲያጠኑ አስችለዋል (ተክለጻዲቅ መኩሪያ የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐጼ ልብነድንግል እስከ ዐጼ ቴዎድሮስ 1961፤ 4ኛ ዕትም ገጽ 256 እና 281)።

በሌላ በኩል፤ እቴጌ ጣይቱም በበኩላቸው ከአድዋ  ጦርነት በፊት ኮንት አንቶኔሊን “ማን የሚደነግጥልህ አለ ጦርነቱን በፈቀድክ ጊዜ አድርገው እኛም ከዛው እንቆይሃለን” ብለው በመለሱለት መልስና በሌሎች ቆራጥና ብልህ ምክራቸው የበለጠ የሚወደሱ ቢሆንም፡ አፈወርቅ ገብረየሱስ እንደጻፉት፡ ኮንት አንቶኔሊ የውጫሌ ውል ተርጓሚውን ግራዝማች ዮሴፍን እፊታቸው መሳደቡን በመቃወም፤ ስህተት ካለ የመገሰጽ መብት የኢትዮጵያዊያን ብቻ መሆኑን ማስገንዘባቸው ስለዜጎች መብት ያላቸውን የህግ ግንዛቤ

ሲያሳይ፤ በአንጻሩ ደግሞ፡ ዛሬ በሃገራችን ለዜጎች መብት የሚቆም መንግስት አለመኖሩ ምን ያህል ጉዞአችን የኋልዮሽ እየሄደ እንደሆነ ያመለክተናል (አጤ ሚኒሊክ 1901፤ገጽ 76፤77)።

በተጨማሪም፤ ምንም እንኳ ከ1909-1922 በንግስና ቢቆዩም፡ እምብዛም ታሪካቸው ሲነገር የማንሰማው ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ፤ በ7 ዓመታቸው ለ12 ዓመቱ የአጼ ዮሃንስ ልጅ፡ ራስ አርአያ ዮሃንስ፡ ለሃገር አንድነትና ደህንነት ሲባል  ልጅነታቸው መስዋዕት ተደርጎ ነበር የተዳሩት። በንግስናቸውም ዘመን ዛሬ ለተለያዩ  የእምነት ተከታዮች አገልግሎት በቀብር ስፍራነቱ የሚታወቀውን የአዲስ አበባውን ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ እጅግ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጸዋል። እንዲሁም ዘውዲቱ ሆስፒታልን የሴቶች ማዋለጃ አገልግሎት እንዲሰጥ ያሰሩትም እኒህ ንግስት ነበሩ። በዘመኑ የፊታውራሪ ሃ/ጊዮርጊስና የአልጋ ወራሽ ወገን እየተባባለ የነበረውን መካረር ሰላም ወዳዷ ንግስት ዘውዲቱ፡ በማስማማትና በታላቅ ትእግስት ያበርዱት እንደ ነበረ የዓይን ምስክርነት ቃላቸውን ደጃዝማች ከበደ ተሰማ በጽሁፍ አኑረዋል (የታሪክ ማስታወሻ  1962 ገጽ 31፤36፤39፤43)።

ሌላዋና፡ የሃገራችን የመጨረሻዋ ንግስት ሆነው ያለፉት እቴጌ መነን፤ በየካቲት 3 1938፤ የእቴጌ መነን የሴቶች ትምህርት ቤትን የመሰረት ድንጋይ በማኖር፡ የሃገራችን ሴቶች ዘመናዊ ትምህርትን እንድንቀስም የሚያበረታታ መሰረት ጥለዋል። በ1942 ደግሞ 14 ቅዱሳን መጽሃፍት እንዲተረጎሙ እና 3800 ቅጂዎች እንዲሸጡ አርገው $12 ሺህ ብር፡ አቅም ለሌላቸው ህጻናት መማሪያ እንዲሆን  ለቅዱስ ጳውሎስ የስዋስው ትምህርት ቤት አበርክተዋል። እቴጌ መነን በሃገራችን የመጀመሪያው የህክምና ትምህርት ቤት፤ ልእልት ጸሃይ ሆስፒታል እንዲሰራ፡ የእናታቸውን ርስት በስጦታ የሰጡ ሲሆን፤ ልጃቸው ልእልት ጸሃይ እንግሊዝ ሃገር የነርስነት ትምህርት ሲከታተሉ የተዋወቋቸው የኢትዮጵያ ባለውለታ ወ/ሮ ሲልቪያ ፓንክረስትም

ለሆስፒታሉ ገንዘብ በማሰባሰብ ተባብረዋቸው፤ የእቴጌዋ የበጎ አድራጎት ተግባር እንደታቀደው ሊከናወን ችሏል። በነገራችን ላይ የእቴጌ መነን እናት፡ የወ/ሮ ስህን አባት፡ ንጉስ ሚካኤል፤ የነቢዩ መሃመድ 5ኛ ትውልድ ከሆኑት ከአብዱላህ ቢን ሙሃመድ አል ባኪር የዘር ሃረጋቸውን እንደሚስቡ Anjahli Parnell ጽፈዋል (The Biography of Empress Menen Asfaw: The Mother of the Ethiopian Nation 2011፤ ገጽ 101፤105፤174)።

ሌላዋ ተደናቂ ሴት ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ሲሆኑ፡ ወ/ሮዋ የጣሊያን ወታደሮችን ዕቅድ ለአርበኞች በማድረስ፤ የከተማ ውስጥ አርበኞችን በማስተባበር፤ ለአርበኞች ጠመንጃ፤ ጥይትና ስንቅ በማቀበል የታገሉ ስመ ጥር አርበኛ ሴት መሆናቸውን ጀ/ራል ጃጋማ ኬሎ መስክረውላቸዋል። ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ፡ በወቅቱ የሚናቀውን የንግድ ስራ በትጋት በማከናወን፡ የዘይት ማምረቻ፤ የአልኮል ፋብሪካ፤ የእንጨት ስራ፤ የአትክልትና  ፍራፍሬ ምርት በመሳሰሉ የንግድ ስራዎች ላይ በግላቸውም ሆነ  ከግሪኮች ጋር በሽርክና በመስራት፡ ስራ ፈጣሪ እና ባለሃብት ሴት መሆናቸውን ደራሲ ሺበሺ ለማ ጽፈዋል (ሸዋረገድ ገድሌ  የአኩሪ ገድላት ባለቤት የህይወት ታሪክ 1878-1942  2007፤ ገጽ 200፤201፤206፤207)።

እነዚህ የጠቀስኳቸው መልካም ስራን ሰርተው ያለፉ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ታሪክ እንደሚያሳየንም ሆነ፤ የሰላም ጥናት አባት ተብለው የሚወደሱት ኖርዌጂያዊው ዮሃን ገልታንግ እንደጻፉት፤ አርክቴክቶችና ኢንጅነሮች በትምህርትና በስልጠና የሚያገኙትን፡ ልዩነቶችን አቻችሎ፤ ቅራኔዎችን ፈቶ የማለፍን ጥበብ፤ ሴቶች ግን በተፈጥሮ እንደታደሉት ጽፈዋል (Peace, and Development: Theories and Methodologies 2015፤ ገጽ 31፤ 32) ። የቀደምት ሴቶች ኢትዮጵያዊያንን ገድል የዘረዘርኩት ለመመጻደቅ፤ ለመበላለጥና ከወንዶች ጋር ለመፎካከር ሳይሆን፡ የእኛም ሆኑ የሌሎች ዓለም ማህበረሰቦች፡

ይህንን የሴትን ልጅ ልዩ ክህሎትና ተፈጥሮ፡ የተሻለ፤ መፈቃቀርና መከባበር የነገሰባት ሰላማዊ ዓለም ለመገንባት አለመጠቀማችን፡ “ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” የሚለውን ብሂልን እንዲያስታውሰን ብዬ ነው።

         ወደ ዘመናችን የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ስንመጣ ደግሞ፡ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የኢህአዲግ ቀይ እስኪብርቶ በሚል ርዕስ በ2004 ዓም ባሳተመችው መጽሃፍ፤ የሴቶች ተሳትፎ በሃገራችን የፖለቲካ ማህበረሰብ ዘንድ፡ በህወሃትም ሆነ በተቃዋሚዎች መንደር ባዶ መሆኑን ጠቁማለች። ከዚህ በተለየ መልኩ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ብቻ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ለፓርቲ ሊቀመንበርነት በመምረጥ ፈር ቀዳጅ ቢሆንም፤ ይኸው ፓርቲ በወቅቱ 20 ከሚሆኑት የስራ አመራሮቹ መሃል 2ቱ ብቻ ሴቶች እንደደሆኑ ጽፋለች (ገጽ 201፤202)። በበኩሌ የወያኔን ስርዓት መብት በመንፈግ የሚያክለው ባይኖርም፡ “የድርጅቱን” ሚስት፤ አዜብ መስፍንን ግን፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እንድትነግስ ለክፉ ስራም ቢሆን ዕድል መስጠቱ፡ ከተቃዋሚዎች አሰላለፍ እጅግ በጥቂቱም ቢሆን ለየት ያደርገዋል እላለሁ። የኢትዮጵያን ፖለቲካ ነፍስ ካወቅኩባቸው አመታት ጀምሮ በርቀት፤ ላለፉት አስራ ሁለት ዓመታት ደግሞ በቅርበት እንዳስተዋልኩት፤ በነጻነት ጥማትና በአልገዛም ባይነት ትግል የማህበረሰባችንን ትብትብ አመለካከት ጥሰው ከወጡትና ከማደንቃቸው እህቶቼ፡ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ውጪ፤ የዘመናችን የፖለቲካ ማህበረሰብ አበረታቶ፤ መርጦ፤ እደጉ ተመንደጉ ብሎና ፈቅዶ ያፈራቸው፡ ለሌሎቻችን አርአያ የሚሆኑ፤ ትውልዱን ሊቀርጹ የሚችሉ ሴቶችን፡ ለመቁጠር ብፈልግ እምብዛም ላገኝ አልቻልኩም።

ለዚህም ምክንያቱ ምን ይሆን ብዬ ራሴን ስጠይቅ ያገኘሁት መልስ፤ በህወሃትም ሆነ በተቃዋሚ ጎራ ያላችሁት “አብላጫዎቹ” ወንዶቻችን የኋላውን አሰራራችንን ሁሉ ኋላቀር ብላችሁ፤ በዘመናዊ ትምህርት ጫና ከበጎ ባህላችን ጋር ጭምር ቅራኔ ውስጥ ገብታችሁ፤ ራሳችሁም ገና ከአውሮፓዊያን የበላይና የበታች

አስተምህሮ ነጻ ስላልወጣችሁና የሃገራችሁን ነባር የአስተዳደር ጥበብ፤ ባህልና አሰራር፡ በተወሳሰበና መተማመን በጎደለው፡ የፓርቲና የድርጅት የተውሶ አወቃቀር፤ ሙሉ በሙሉ በመተካታቹ ነው። በሌላ በኩል ማህበረሰባዊ ፍትህንና እኩልነትን ለማስፈን፤ ነጻ አስተሳሰብና አመለካከት መጀመሪያ ከራስ፡ ብሎም ከቤታችን ይጀምራል። ለሌሎች መብት ለመጮህ፡ መጀመሪያ የግል ህይወታችን የሰው ልጆችን ሁሉ መብት በማክበር ጽንሰ ሃሳብ የተዋቀረ ሊሆን ይገባዋል። በየግል ህይወታችን ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ቅጥፈት፤ ተንኮልና አድሎ የተመላበት ከሆነ፤ በሸንጎ ስለፍትህ ብንመክር፡ በአደባባይ ስለ መብት ብንጯጯህ፤ ባዶ የመንፈስ ርካታን ካልሆነ በቀር፡ ማህበራዊ ፍትህንና እኩልነትን አያጎናጽፈንም። የሃገራችን የፖለቲካ መድረክ እኔነትና ራስወዳድነት የነገሰበት የዓለማችን ነጸብራቅ ነውና ወደ ማንነታችን ካልተመለስን ችግራችን ይቀጥላል። ከአውሮፓ በፊት ስልጣኔን ያጣጣመች፤ የነሉሲ መገኛ፤ የአክሱም፤ የላሊበላ፤ የፋሲለደስና፤ የሶፍ ሁመር ዋሻ ባለቤቷ ኢትዮጵያ ውስጥ፤ ለዛሬ ትውልድ የሚበጅ የአስተዳደር ጥበብ ተፈልጎ ይጠፋል ብዬ አላምንም።

በዚህ አጋጣሚ ይልማ ደሬሳ በገዳ ስርዓት መሰረት፡ የኦሮሞ ሴቶች ካገቡ በኋላ እንደ ወንድ በፈረስ ተቀምጠው እንደሚሄዱና ሃሳባቸውንም በነጻነት ሲናገሩ ተደማጭነት እንደሚያገኙ፤ በባላቸውም ትዳር የማዘዝና የማስተዳደር መብት እንዳላቸው ጽፈዋል (የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን 1959፤ ገጽ 247)። ዛሬ በዘመናችን የፖለቲካ ፈረስ ላይ የሚቀመጡ፡ በርካታ የኦሮሞ ሴት ወይዛዝርትን ማየት እፈልጋለሁ። የሃገር ውስጥና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮቻችን የደዋሮ ሴቶች ሆነው ማየትን እመኛለሁ። የእርዳታ ማስተባበሪያ ተቋም ወይም ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ ብዙ መነኖችን ለማየት እፈልጋለሁ። ኢትዮጵያን፤ ኤርትራን፤ ሱማሌን፤ ጅቡቲን፤ 2ቱን ሱዳኖች፤ ግብጽንና ኬኒያን አዋደው እና የተቃቃረውን አስማምተው፤ ለዓለማችን የሰላምን ዘር የሚዘሩ እሌኒዎችን ማየት ህልሜ ነው።

ለሃገራችን ጥቅምና አንድነት፤ ለዓለማችን ደህንነትና ሰላም፤ ለምድራችን ልምላሜና በረከት ሴቶች ከማጀታቸው እየወጡ አደባባዩን እንዲሞሉት ወንዶችም ሴቶችም ማገዝ፤ ማበረታታት፤ ጓዳቸው  እንዳይጎድል ዘመድ ወዳጅ እንዳይሰላች መተጋገዝ ይገባናል። በተመሳሳዩም ወንዶች ለሃገራዊ ጉዳይ አደባባይ ስትውሉ ሴቶችም ሆንን ሌሎች ወንዶች ለቤተሰባችሁ ልንሳሳላችሁ ይገባል። ውጤት አለመስዋዕትነት እንደማይገኝ የታወቀ ነው፤ ነገርግን አንዳንዴ መስዋዕትነቱ የግል፡ ወይም የቤተሰብ፤ ከፍ ሲልም የማህበረሰቡ ሊሆን ይችላል። ዳንኤል ፖ የተባሉ ጸሃፊ ሚሼል ናር ኦቤድ ስለተባለችው የሃገሯ የአሜሪካን መንግስት በውጪ ሃገራት የሚያደርገውን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት አምርራ ስለምትቃወመው ሴት ሲጽፉ፤ ሚሼል ማህበረሰባችን የእናትነትን ሚና ለእናት ብቻ  የሚተወውን አስተሳሰብ፤ ለጋራ ጥቅም ሲባል ሃላፊነትን በመውሰድ ለጎጆዋ ብቻ  ልታውለው የምትችለውን ልጇን በሰላምና በእንክብካቤ የማሳደግ እናታዊ ተግባር፡ ለፍጥረት ሁሉ አለኝታ ለመሆን፡ እየታሰረች እየተፈታች ስለ ዓለም ሰላም ስትታገል፤ በአንጻሩ ባሏና ማህበረሰቧ ሴት ልጇን ለማሳደግ እናታዊ ሚናን በጋራ በመወጣት ከዓላማዋ እንዳትደናቀፍ እንደተባበሯት ጽፈዋል (Danielle Poe “Woman, Mother, and Nonviolent Activism.” Positive Peace: Reflections on  Peace Education, Nonviolence, and Social Change 2010 P. 119, 130-31).

ስለዚህ ጥያቄው ሴቶች ለምን ከትግል ጎራ ታጡ ሳይሆን፡ ወደ ትግሉ ጎራ ሲወጡ በቂ ድጋፍ እንዲኖራቸው ማህበረሰባችንን ለማንቃት፤ ለማስተማር ምን ስራ ተሰርቷል? የትግሉ ጎራ እንደ ኮርማ  መጎሻሸሚያ መሆኑ፡ እንኳን ሴቶችን ወንዶችንም ስለሚያሸሽ፤ ለሃገር ጥቅም ሲባል ክብሬ ኩራቴ ተነካ በማለት መጎሻሸሙን ለማስቀረት በእናንተ ዘንድ ፈቃደኝነቱ አለ ወይ? ወደ ትግሉ ጎራ እንደምንም የመጡትንስ ሴቶች ከጓዳ ስራ ሌላ፤ ለማማከርና የመሪነት ድርሻ  እንዲኖራቸው ለማብቃት ዝግጁ ናችሁ

ወይ? ለሃገራችንስ ከህወሃት የተለየ ሴቶችን፤ ወጣቶችንና አነስተኛ የብሄር ቁጥር ያላቸውን የማህበረሰባችንን ክፍሎች የሚያሳትፍ ራዕይ ሰንቃችኋል ወይ? ራዕዩ ሲጠነሰስስ የሁሉም የህብረተሰብ አካላት ተሳትፎ አለበት ወይስ ለይስሙላና ብቻ ነው ተሳትፏችን የሚፈለገው?

ዶ/ር ታደሰ ወ/ጊዮርጊስ፤ “ኅብረተሰብ የሚፈጠረው፡ ኅብረተሰብ የሚደራጀው፤ የኅብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶች በኅብረተሰቡ እንቅስቃሴ ውስጥ በእኩልነት ደረጃ ሲሳተፉ ነው” ብለው ጽፈዋል (የምዕራባውያን ሥልጣኔና ኢትዮጵያዊያን በአሜሪካ ማህበራዊ እና ስነ ልቡናዊ ትንተና  2006፤ ገጽ 235)። “ዘመናዊ” ትምህርት ተምረናል በምንልበት በዚህ ዘመን፤ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የነበሩ ቀደምቶቻችንን ያህል እንኳን አስተውለን፤ ሴቶች በተፈጥሮ የተቸራቸውን የማማከር፤ የማግባባት፤ አርቆ የማየት ጥበብ ጥቅም ላይ ስናውለው አላየሁም። ፕ/ር ሃይሌ ገሪማ  እንዳሉት፡ “የኢትዮጵያ ጉዞ ሶስት ሺህ ዘመን ወደኋላ፤ ወደኋላ፤ ወደኋላ ሆኗል”። በሌላ በኩል ቴዲ አፍሮ “የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ” ቢለንም፤ ወደኋላ የምናየው ከበጎውም ከመጥፎውም ታሪካችን ለመማር እንጂ የነበረንና የገነባውን ሁሉ እያፈረስን የኋልዮሽ በመሄድ፤ አፍርሰን ለመስራት መሆን የለበትም። ስለዚህ፡ ምንም እንኳ ሴቶች ወደ ትግሉ ጎራ እንዳይገቡ ሌሎች ሴቶችም ሊያዳክሙ እንደሚችሉ ቢገለጽም፤ የዘመናችን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምህዳር የተጥለቀለቀው ግን በወንዶች ስለሆነ፤ የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲጨምርና የኋልዮሽ ጉዞአችን እንዲቆም እናንተስ ምን አቅዳችኋል? ብዬ ጥያቄውን ወደ ወንዶቻችን መልሸዋለሁ።

የአገር ፍቅር ልክፍት፤ በየትኛዉ ሰሚ ጠበል  ይፈታ ይሆን ?- በእስማኤል ዳውድ (ልጅ እያሱ)

$
0
0
 ኢትዮጵያ እያደባች አንቃ ከምትገላቸዉ የዘመን  አጋሮቼን ባሰብን ቁጥር ድብርቱም ፤ ሰቆቃዉም ይበረታል ።

ዳንኤል ሺበሺ

ከነዚህ ወንድሞቼ ዉስጥ  አንዱ ዳኒ ነዉ ።

ዳንኤል ሺበሺን የማዉቀዉ ተጋሪዎቼን ህያዉ መቃብሯን በአደረገችዉ  እናት ቤቴ < አንድነት > ነዉ ።   ዳኒ ጓዴ ፣ ወንድሜ ፣ አለቃዬ ፣ መካሪ መምህሬ  ጭምር ነበር አሁን ግን ላጣዉ ነዉ !   ልናጣዉ ነዉ ! ።
ቁጭት ከእልህ ደባል ሁና እና በሰዉ ነፍስ ህያዉ  ስትሆን በእሱ ታዝቤአለሁና ዝም አልልም ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~፣
ያለዉን ሁላ የቀይ ጥቁር ሁኖ ያፈራዉን ለዛች ሀገር   ያለስስት * ስለ ፍትህ* ሰጥቶአል ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ፣
 እነደ በቅሎ ለሰስ ብላ የምትሰግረዉን ነፃነት ግማሽ መንገድ ሂዶ ዲዮጋን ይመስል በጠራራ ፀሀይ ሲፈልጋት~~~~~~~~~~~፣ ድምም ያረገኝ ነበር ።
  እኩልነት የጠፈር  ሳይንስ በሆነባት ኢትዮጵያ እንደ ጉዱ ካሳ በየፌርማታዉ  የለፈፈ ዘመናይ እብድ ነበር ~~~~~~~~~~++++++++++ ፣ ነበር ። ። ።
 (ነበር )፦ እሩቅ አይምሰልህ ጉድ ጌጥ በሆነበት ሀገር ነገ ጉንፋን                           ገደለዉ ይሉሀልና።
በድራማ ህግ ተከሶ ተዉኔቱን ህዉሃት ሲተዉንበት ወገቡን አስሮ ፍትህ ይጠብቃል ያም ሆኖ በወረወሩት ታዛ ዉስጥም እንደ ህፃን ልጅ በየመጫወቻዉ { ሸለለ ፑቲካ} የሚቃጣዉ  ማፊያዉ ስረአት በረከሰ መንገድ ሲጎንጡት ፣ሲያታክቱት፣ ክብሩን የጃፓን ትሪ ሲያረጉበት ፤ ግዜ
      ያኔ ! !
እዛ ሲኦል ለሆነ ግቢ የወህኒዉ * አዛዥ * የሆነ ሁሉ ይመስለኝ ነበር።
እነ ዉሾም ታራሚዉን ሁላ አስገብተዉ የሚያረጉትን ሁላ ያለከልካይ አርገዉታል ።
አንድ ግዜ ትዝ የሚለኝ ከፍርድ ቤት መልስ (አራሚ) ተብዬዎቹ መረኖች ሲያመነጫጭቁን እና ካቴና   አንዳንዴ ( ምነዉ አየሀኝም) ምክንያት  ይሆናል እኔ (በግሌ) ጥፍር አክዬ ጥፍሬ ዉስጥ ስደበቅ ደረቱን የሚገለብጠዉ ብቸኛዉ ያ ጥርስ የለሽ አንበሳ እሱ ፦ ነበር
የማንንም ልጋጋም ካድሬ ፓሊስ መዳፍ መሞከሪያ ሲሆን ቃሊቲ ዉስጥ አይኔ በጥቁሩ አይቶታል ,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,”ያኔ” ደረቅ አረቄ ያምረኛል እናትና ልጅ !
ግና ( እሱም አይታክተዉ ) አቤት ፅየፋዉ !
አሁንም እንደ ድሮዉ እንደ ፦ አሻቸዉ ፧ –  እያረጉት ነዉ ።
እነሱ፦ ቅምጦቻቸዉን ለጉንፋን እና  ማድያት (ቺሻዝ ለአመጣባቸዉ) ሳይቀር ባንኮክና ሻንጋይ እየላኩ የኛ ወንድሞች ሰዉ የመሆንን *የፈጣሪን* ህግ እየተነፈጉ ፈጣሪ ያልበጠሰዉን ነፍሳቸዉን በጅምላ እየተቀጠፉ ነው
 በዚህ ሰአት እራሳቸዉን × የአሪያን× ዘር አርገዉ በሚቆጥሩ የወናፍ ልጆች የሰዉ ልጅ በታሪኩ ዉስጥ የማይጠረጥረዉን ሁላ እየተደረገበት ፤ የመጥረጊያ እንጨት ጀርባዉ ላይ እያለቀ ነዉ +++ እየተተ***።
የታወከዉን ወንድሜን ያልረባ አስፕሪን ከልክለዉ አመንምነዉ እየገደሉት ነዉ * በዝግታ* እያሸለበ ነዉ ።

  ዘጊቶ የደረሰ መረጃ ፣ – ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ፣

$
0
0

የትግራይ የበለሰ አብቃይ አርሶ አደሮችና  የመቀሌ ዩንቨርሲቲ  የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ተመራማራማሪዎች  እንዲሁም የዩንቨርስቲ ባለስልጣናት  ሆነው ስለ  የበለስ በቫይረስ  ከችሎኒያ  መውደሙ በሚመለከት በየካቲት 22 / 6 / 2009  ዓ ም  በአክሱም ሆቴል    ያካየዱት ስንፓዜም  ያለአንዳች ውጤት በአርሶአደሮችና በመቀሌ ዩንቨርስቲ የክንደያገብሪሂወት ቡዱን ሉዩነት ሳይግባቡ ተበታተኑ።

አስገደ ገብረስላሴ

በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች የጀመረው ለህዝብና ለእንስሳ አመት ከአመት ምግብ  የሆነው  በለስ  ሀላፍነት በጎደላቸው የመቀሌ ዩንቨርሲቲ ባለስልጣናትና ተመራማሪዎች  ነን ባዮች  ግለ ሰዎች በግብታውነት ተነሳስተው በአገር አቀፍ ተዋቂነት የለለው ምርምር በመካየዳቸው  በዚህ አመት  ይተካል  የማይባል  የሀገር ሀብት በማውደማቸው  የተጠቀሱት  ዞኖች ህዝብና እንስሳ  ለሞት ለስደት  እንደተዳረጉት  ከአስር አመት  በፊት ጀምሮ  በአገር ውስጥ  በፍትህ ጋዜጣ በፋክት መጽሄት ፣ በድህረገጽ ፣ በውጭ ሬድዮና  ተለብዥን  ተስተጋብቷል  ።   እንዳው የመቀሌ ዩንቨርሲቲ ፕረዝዳንቶች እና የትግራይ  ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት  ፣ የትግራይ ክልል እርሻ ምርምር ፣  እነዛ በተግባር  ያለአንዳች  መረጋገጫ ምርምሩ ያስፋፉ ግለሰዎች  ለፍርድ  ይቅረቡ ተብሎ ነበር ።

    በሌላ በኩል  እነዛ የመጀመሪያ  የውድመት ሰለባ የሆኑ  የራያና እንጣሎ ወጅራት ፤ ድድባ ደርጋዓጀን ፣ ዓዲጉዶም ወረዳዎች  አርሶ አደሮች  በተደጋጋሚ  ጊዜ ወደ ክልሉ ፕረዝዳንት አባይወልዱ ቢሮ አቤቱታ ለማቅረብ  ቢመላለሱም  ችግራቹ ምንድነው ብለው እንደማዳመጥ  ፈንታ ጆሮ ዳባ በማለት በፓሊስ አባረሩዋቸው ።  እንደገና  በቡዙ ሽ የሚቆጠሩ  አርሶ አደሮች በሰላማዊ ሰልፍ ወደ መቀሌ ሊመጡ ሲሉ  ገና መነሳት ሲጀምሩ  በልዩ ሀይል  እንደታገቱ  ይታወቃል ።
በአሁኑ  ጊዜ  በራያና በዋጅራት  የጀመረ የበለስ ውድመት  እየተስፋፋ ወደ ተንቤን  ሀገረሰላም  ገርዓልታ ስንቃጣ ፣ አጽቢ ወንበርታ  ፣ እዳጋ ሀሙስ  እና  አዲግራት አካባቢ ተስፋፍቶ ይገኛል ።

የመቀሌ ዩንቨርሲቲ እነ ደጉተር ክንደያ ገብሪሂወት ፣ደጉተር አብደርቃድር  የሚባሉ ፕረዝዳንቶች  በለሱ እየወደመ ለ10  አመት እየቀለዱ ነረው  ባለፈው ሳምንታት  ምን አይነት የተለዬ  አስጊ ሁኔታ እንደተነገራቸው አይታወቅም  ድንገት  ለዩንቨርሲቲው  የእርሻና  የተፈጥሮ ሀብት  ተማራማሪዎች  በመሰብሰብ   የበለስ ውድመቱ አዲስ እንደተከሰተ  አስመስለው  ተመራማሪዎች ሰብሰበው  ለምርምር  የሚሆን በቂ  ገንዘብና ተሽከርካሪዎች  ለምርምር  የሚሆን ማተርያል አለን  አሁንኑ   ዝመቱ እና አንድ  ውጤት አፈላልጉ ብለው ሸኝዋቸው ።  ተማራማሪዎችም  ሳይውሉ ሳያድሩ ወደ ሁሉም በለስ  የወደመባቸው አካባቢዎች ዘመቱ ።  ተመራመሪዎች  ከአንድ  ሳምንት በማይበልጥ ጊዜ የምርምር ዘመቻቸው አጠናቅቀው  ሪፖርት ይዘው ተመለሱ ። በአንድ ሳምንት  የሚደረግ ምርምር ምን ውጤት ይነረው መልሱ  የዘመቻው  አሳማሪዎች ።

ተመራማሪዎች  ሪፖርት ይዘው ከመጡ በኃላ  የመቀሌ ዩንቨርሲቲ ባለስልጣናት  በለስ ከወደመባቸው አከባቢ የተውጣጡ በርከት ያሉ አርሶ አደሮችና  የዩንቨርሲቲው በርከት ያሉ ሙሁራኖች  የተሳተፉበት ስንፖዜም በአክሱም ሆቴል  ተጧጧፈ ።

በስንፖዜሙ በዘመቻ ለጥናት ተሰማርተው  የሰነበቱ ተመራማሪዎች በደጉተር ክንደያ ገብሪሂዎትና በደጉተር አብደርቃድር ሊቀመንበርነት  ሪፖርት አቀረቡ ።ካቀረቡት  ሪፖርት  ውስጥ ፣ በለሱ የሁለቱ ዞኖች በለስ እንደወደመ ፣ እጅግ ቡዙ እንስሳ ዘቤት እንዳለቁ ፣ በሁሉም አከባቢ ያሉ ወጣቶች  የሚበሉት አጥተው እንደተሰደዱ ፣ አዛውንቶችና ህጻናት ፣ሴቶች እንደተጎሳቆሉ ፣   በለሱ በመውደሙ መሬቱ በዝናብ ተሸርሽሮ እንደተጠራረገ ፣የሁሉ ህዝብ ሞራል  እንደተነካ ፣ የወደፊት መጻኢ እድሉ ጨለማ ሆኖ እንደሚታይ  ወዘተ በህዝቡ  የደረሰው ችግር በሚገባ በሪፓርታቸው  አካትተው አቅርበዋል ።

በሌላ በኩል የበለስ አብቃይ አርሶአደሮች ንዴት በተሞላበት  ያነሱት ሮሮ  አንደኛ እድሜው የማይታወቅ የአሰር ምእተአመት የህዝብ ቀለብ ሆኖ የኖረ በለስ  ያወደመብን ጠላታችን ንገሩን  ። ሁለተኞ የወደመው ሀብታችን ካሳ ይሰጠን ። የተበታተኑ ልጆቻችን ፈልጉልን  ያለ  በለስ ለመኖር አንችልም  ፣ አገር የለን  ይመስል በጨለማ ተውጠናል ብለዋል ።

በመጨረሻው ስንፖዜሙ  ስለበለስ ወደ  ነበረበት ቦታ  የመመለስ ጉዳይ  የመቀሌ ዩንቨርሲቲ  ባለስልጣናት  መፍትሄው  ጨልሞባቸው ከአርሶ አደሮቹ ሳይስማሙ ወይ ሳይደሳሰቱ  ስንፓዜሙ ተጠናቀቀ ።

በመጨረሻ ግን በደጉተር ክንደያ ገብሪሂወት በአሁኑ ጊዜ የክችሎኒያ አውዳሚ  ቫይረስ አሁን  ተሰራጭቶበት ባለበት  ለመከላከል  ወይ ለማዳን እንደማይቻል ፣ ነገር ግን ወደ አጋሜና ሌሎች ቦታወች እንዳይዛመት ለማገት ብቻ ነው የምንችለው  ብሎ ቁርጡን ሲናገር አርሶ አደሮች  እጅጉን በመበሳጨት  እያዘኑ ወደየመጡበት  ሄደዋል ።   እዳውም  የክንደያ ገብሪሂወት አነጋገር ፖለቲካዊ  ትርጉም ሰጥተውት ሄደዋል ።

የተከበራችሁ የሀገራች ዜጎች ይህ በትገራይ በለስ ደርሶ  ያለው ውድመት  በዚሁ ታጥሮ የሚቀር  አይደለም ። እንዳው  በለስ እንደ አንድ የውሀና  የአፈር ጥበቃ ወነኛውን መፍትሄ ተብሎ  ከ15  አመት በፊት  ጀምሮ ወደ ጎንደር ፣ ጎጃም ፣ ሰሜን ሽዋ ፣ዋግ ላሊበላ፣ ደቡብ ህዝቦች ፣ ወደ አፋርና ሱማል  ከትግራይ   እየተቆረጠ እየተጫነ ተተክለዋል ፣ ይህ ሁሉ የተደከመበት  በትገራይ በተስፋፋ  ቫይረስ ተመልሶ ሲወድም እጅጉን  አሳዛኝ ነው ። ይህ  አደጋ  ከ70 %   በላይ በለስ ተመጋቢ የሆነ የኤርትራ  ህዝብም ለአደጋው   ሰለባ እንደሚሆን እገምታለሁ ።

በመጨረሻ ግን በትግራይ ህዝብ ተደቅኖበት ያለው ችግር  የፈደራል መንግስቲ  ከአስር አመት በላይ ዜጎች  እየተንጫጩ ለምን ዝምታ እንደመረጠ ያሳዝነኛል ። የመንግስት  ሚዲያዎች በተለይ ደግሞ  በትግራይና  በአመራ ክልሎች ያሉ  ሚዲያዎች በህዝብ ሀብት ተቋቁመው  እያሉ  የህዝብ ሮሮ ባለማስተጋባታቸው ምን  ያህል ከዳተኞች  መሆናቸው  ያመለክታል ።
ከአስገደ ገብረስላሴ  መቀለ ፣
30  / 6  / 2009  / ዓ ም

ዶ/ር መረራ የዋስ መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

$
0
0

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና የዋስ መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል፡፡ ፍርድ ቤቱ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩና የክሥ መቃወሚያ ካላቸውም እንዲያቀርቡ አዝዟል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና የዋስ መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል፡፡ ፍርድ ቤቱ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩና የክሥ መቃወሚያ ካላቸውም እንዲያቀርቡ አዝዟል፡፡ዶ/ር መረራ በፍርድ ቤቱ ውሣኔ ማዘናቸውን ለችሎቱ ገልፀዋል፡፡ ጠበቃቸው በውሣኔው ላይ ይግባኝ እንደሚሉ አስታውቀዋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ መድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀደም ሲል ዶ/ር መረራ ጉዲና በጠበቆቻቸው አማካኝነት የዋስ መብታቸው እንዲከበርና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው አንዲከታተሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀረ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

VOA

if(typeof(jQuery)==”function”){(function($){$.fn.fitVids=function(){}})(jQuery)};jwplayer(‘jwplayer-1’).setup({“file”:”http://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2017/03/5ffc50ec-f55b-4f74-ba53-72fb303cfc16_hq.mp3″});

በጅማ ዩኒቨርስቲ መምህራን ኮሌጅ:- በማዕተብ ጉዳይ ከመምህሩ ጋራ የተጋጨው ተማሪ ራሱን አጠፋ፤ መምህሩ ታሰረ፤ “ቤተ ክርስቲያን፥ የእምነት ነጻነታችንን ታስከብርልን”/ተማሪዎቹ/

$
0
0

ሐራ ዘተዋሕዶ

  • መምህሩ፣ በተመሳሳይ ጥፋት በተወሰደበት የዲስፕሊን ርምጃ ተባርሮ የተመለሰ ነው፤
  • ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች፣ የእምነት ነጻነታቸው እንዲከበር አቤቱታ አቅርበዋል፤ 
  • “በነጻነት መማር አልቻልንም፤ የእምነት ነጻነታችን ይከበር፤ የሕግ ከለላ ይሰጠን!”

*                    *                    *

(አዲስ አድማስ፤ ቅዳሜ፣ መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም.)

ተማሪ ተስፋዬ ገመዳ(ወልደ ገብርኤል)


በጅማ ዩኒቨርስቲ መምህራን ኮሌጅ፣ የኹለተኛ ዓመት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪ የነበረው ወጣት፣ በማዕተብ ጉዳይ ከመምህሩ ጋራ ተጋጭቶ የትምህርቱ ውጤት በመበላሸቱ ራሱን አጠፋ፡፡

ተስፋዬ ገመዳ የተባለው ተማሪው፣ የሥነ ልቡና ሳይንስ መምህሩ፣ በቡድን የሰጧቸውን የቤት ሥራ አዘጋጅተው በመድረክ ሊያቀርብ ሲል፣ መምህሩ፥ “በአንገትኽ ላይ ያደረግኽውን ማዕተብ አውልቅ ወይም ሸፍነው፤” ሲሉት ተማሪው፥ “ይኼ የእምነቴ መግለጫ ነው፤ ያዘዙኝን ማድረግ አልችልም፤” የሚል ምላሽ እንደሰጣቸውና መምህሩም፥ “ያዘዝኩኽን ማድረግ ካልቻልክ የሠራኸውንም ማቅረብ አትችልም፤” ስላሉት ከመድረኩ ወርዶ በእጁ የያዘውን የቡድን ሥራ ሪፖርት በብስጭት ቀድዶ መቀመጡን የዓይን እማኞች አስረድተዋል፡፡

በወቅቱ ተማሪው፣ ክፍለ ጊዜውን አቋርጦ መውጣቱንና ተመልሶ ሊገባ ሲል፣ መምህሩ፣ አትገባም ብለው እንደከለከሉት፤ ተማሪውም፣ ስሜታዊ ኾኖ ከመምህሩ ጋራ ለጠብ መጋበዙንና ሌሎች ተማሪዎች በመሀል ገብተው እንደገላገሏቸው፤ የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን፣ በቦታው ተገኝተው ስለተጠፈረው ችግር ተማሪዎችን በመጠየቅ ጠቡን ማረጋጋታቸውን፣ እማኞቹ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

በሌላ ቀን፣ ተማሪ ተስፋዬ እንደተለመደው፣ የሥነ ልቡና ትምህርቱን ለመከታተል ወደ ክፍል ሲገባ መምህሩ ከክፍል እንዳስወጡት፣ ለአካዳሚክ ዲኑ አቤቱታ ማቅረቡንና፣ “የትምህርቱ የመጨረሻ ክፍለ ጊዜ ስለኾነ በቃ ተወው፤ በውጤትኽ ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም፤” ብለው አረጋግተው እንደሸኙት የተማሪው የቅርብ ጓደኞች ገልጸዋል፡፡

በኋላም ለፈተናው የተቀመጠ ሲኾን፣ የተለጠፈው የፈተና ውጤት ግን “No Grade’’/ምንም ውጤት የለም/ የሚል ስለነበረ፣ ወዲያው በንዴት ወደተከራየበት ቤት በማምራት በግቢው በሚገኝ የማንጎ ዛፍ ላይ ራሱን ሰቅሎ መግደሉን ጓደኞቹ አስረድተዋል፡፡

ፖሊስና የአካባቢው ኅብረተሰብ ከቦታው ደርሰው ከተሰቀለበት ሲያወርዱት፣ ነፍሱ ከሥጋው እንዳልተለየችና ወደ ሆስፒታል ይዘውት በማምራት ላይ ሳሉ ሕይወቱ ማለፉን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ አስከሬኑ፣ ማክሰኞ፣ የካቲት 28 ቀን 2009 ዓ.ም. መሸኘቱንና የቀብር ሥነ ሥርዓቱም፣ በትውልድ ስፍራው በሰሜን ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ደገሞ ወረዳ ከትላንት በስቲያ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አስከሬኑን ለቤተ ሰዎቹ ያደረሱት መርማሪ ፖሊስ ዮሐንስ መገርሳ፣ ተማሪው ከመምህሩ ጋራ በመጣላቱ ራሱን እንዳጠፋ ጥርጣሬ መኖሩንና፣ የሆስፒታል የምርመራ ውጤት በመጠበቅ ላይ መኾኑን፤ ጉዳዩም ገና በመጣራት ላይ እንዳለ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡

[ተማሪው የደረሰበትን በደል ቀደም ብሎ ለጅማ ሀገረ ስብከትም በማስታወቅ እገዛ ጠይቆ እንደነበር ያወሱ ምንጮች፣ ጽ/ቤቱ ከትላንት በስቲያ ኃሙስ ጀምሮ ጉዳዩን እየተከታተለው መኾኑን ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርስቲው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችም፣ የሃይማኖት ነጻነታቸው እንዲከበር የሚጠይቅ አቤቱታ ተፈራርመው፣ ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት አስገብተዋል፤ ለሚመለከታቸው የኮሌጁና የመንግሥት ሓላፊዎችም በየደረጃው እንደሚያደርሱ ተነግሯል፡፡

በአቤቱታቸው፥ ከዚኽም በፊት፣ በአጽዋማት ወቅት ሥርዓተ እምነታቸውን በአግባቡ እንዳይፈጽሙ በሴኩላሪዝምና በአካዳሚክ ነጻነት ስም የተደረገባቸውን አድልዎ በማካተት፥ “በነጻነት መማር አልቻልንም፤ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ነጻነታችንን ታስከብርልን፤ የሕግ ከለላ ይሰጠን፤” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ለሀገረ ስብከቱ የደረሰው አቤቱታ፣ በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አማካይነት፣ ከዞን እስከ ፌዴራል መንግሥት አካላት ድረስ እንደሚቀርብ ተገልጿል፤ የሟች ቤተሰብም በሕግ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል፡፡]

******************

  • አካዳሚክ ዲኑ ግጭቱን ሲያጣሩ፣ መምህሩ፥ ሊደበድበኝ ነው፤ ብሎ ተማሪውን ከሦት ነበር፤ የክፍል ጓደኞቹን ሲጠይቁ ግን፥ ማዕተብኽን ካልበጠስክ፤ ብሎት በዚያ የተነሣ እንደኾነ ተረድተዋል፤ ጥፋቱም የመምህሩ እንደኾነ ነግረውና ይቅርታ ጠይቀው ልጁን አረጋግተውት ነበር፤ ከዚያ በኋላ በነበረ አንድ ክፍለ ጊዜ፣ ውጣ ብሎ እንዳይገባ ሲከለክለውም ለአካዳሚክ ዲኑ አስታውቋል፤ እርሳቸውም፣ ለኮርሱ፥ የመጨረሻ ክፍለ ጊዜ ነው፤ በሚል አባብለውታል፤ ፈተናውን ተፈትኖ ውጤቱን ሲያበላሽበትም ወደ አካዳሚክ ዲኑ ሊያመለክት ሔዶ ነበር፤ አላገኛቸውምና በየአንጻሩ፣ ለመምህሩ በሚታየው የአስተዳደሩ ከልክ ያለፈ
    መለሳለስ ምክንያት ነው የተበሳጨው፤
  • መምህሩ፣ ከዚኽም በፊት በተመሳሳይ የዲስፕሊን ችግር ከማስተማር ሥራው ተባርሮ የነበረ ሲኾን፣ በአንዳንድ ሓላፊዎች ልመና ከተመለሰ ገና አንድ ዓመቱ ነው፤ የአእምሮም እክል እንዳለበት ነው የሚነገረው፤ እብሪትም ይታይበታል፤ የዲኑ ቢሮ ገብቶ ወንበራቸው ላይ ተቀምጦ፣ ጸሐፊዋን፥ “ከዚኽ በኋላ ማንም ሰው እንዳይገባ፤ ዲኑ እኔ ነኝ” የሚልበት ጊዜ አለ፤
  • ተማሪው ራሱን ባጠፋበት ቀን ምሽት፣ መምህሩ በቁጥጥር ሥር ውሎ በእስር ላይ ነው ያለው፤ አስከሬኑ በተሸኘበት ዕለትም፣ በዩኒቨርስቲው በር ላይ ተማሪዎች ቁጣቸውን ሲገልጹ የነበረ ሲኾን፣ ፖሊስ በአስለቃሽ ጢስ በትኗቸዋል፤ ማምሻውንም ከዐሥር የማያንሱቱ ከየዶርሚተራቸው እየተያዙ ተወስደዋል፤
  • ተማሪው ከመሞቱ በፊት ለጓደኞቹ አራት ጊዜ በተከታታይ ደውሎ ነበር፤ ወደሚግባባው ጎረቤት ባለሱቅም ሔዶ ነበር፤ አላገኛቸውም፤ ብሶቱን የሚተነፍስበትና የሚያናግረው ሰው እየፈለገ ነበር፤ በርግጥ፣ የንስሐ አባቱን በዚያኑ ቀን ጠዋት አግኝቷቸው፣ ከመምህሩ ጋራ መጋጨቱን ነግሯቸው፣ እንደ መንፈሳዊ አባት አጽናንተውት ነው ወደ ቅዳሴ የገቡት፤ ከጸሎተ ቅዳሴው ሲወጡ የተረዱት ግን አሳዛኝ ኅልፈቱን ነበር፡፡
  • በጅማ ዩኒቨርስቲ መምህራን ኮሌጅ፣ በእንግሊዝኛ ዲፓርትመንት፣ የኹለተኛ ዓመት ተማሪ የነበረው ተስፋዬ ገመዳ(ወስመ ጥምቀቱ ወልደ ገብርኤል)ከ3.6 በላይ ድምር አጠቃላይ ውጤት ያለው ጎበዝ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ነበር፡፡

ሕወሃቶች አውሮፓና አሜሪካ ይታከማሉ ሕዝቡ ግን ….የሚሊዮኖች ድምጽ

$
0
0

ሕወሃቶች አውሮፓና አሜሪካ ይታከማሉ ሕዝቡ ግን ….የሚሊዮኖች ድምጽ

ሕወሃት ራሱን የትግራይ ነጻ አውጭ ብሎ በትግራይ ሕዝብ እየነገደ ያለ ድርጅት ስለመሆኑ አገር ሁሉ የሚያውቀው ነው። ሕወሃቶች ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ብቻ የሚጠቅሙ እንጂ  የድሃዉን የትግራይ ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል ሲደክሙ የታዩበት ሁኔታ የለም። ለሕዝቡ ያተረፉለት ነገር በሚኖር በሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ በጥርጥሬ  መታየተን ነው። በትግሬ ስም ፣ በብሄር ብሄረሰብ መብት በሚሉት ስም ሌላውን ማህበረሰብ እየበደሉና እየጨቆኑ ሕዝቡን ከሌላው ሕዝብ ጋር ለማቃቃር እየሞከሩ ነው።

በተለይም በወልቃይት ጠገዴ ዙሪያ ሕወሃቱ አባይ ዘዉዱ እያደረገ ያለው በጣም ሲበዛ አደገኛ የሆነ ተግባራትን ነው። በወልቃይት ሕዝቡ ትግሬ ፣ አማራ ሳይባባል ለዘመናት ተዋልዶ በፍቅር የኖረ ነው።  ትግሪኛም አማርኛም ሕዝቡ ይናገራል። ሲያሻው ሽሬ፣ ሲያሻው ጎንደር ሄዶ ይነገዳል። ሆኖም ሕወሃቶች ወልቃይት የትግሬ ነው በሚል በዚያ የሚኖረውን ሕዝብ በግድ ትግሬ ነህ እያሉ አሰቃዩትም አፈናቀሉት መሬቱን ወሰዱበት። አሁን በቅርብ እንኳን “ትግሬ አይደለንም የምትሉ ከሆነ፣ ለቃችሁ መሄድ ትችላላችሁ” የሚል ነዉረኛ አስተያየት ነበር አባይ ወልዱ የሰጠው። በዚህም ምክንያት ነገሮች መስመር እየሳቱ ነው የመጡት። ሁሉም የሕወሃት ዘረኛ የጥላቻ ፖለቲክ የወለደው።

ጦማሪ አርዓያ ተስፋማሪያም ምን ያህል የሕወሃት መንግስት ለሕዝብ ጥቅም እንዳልቆመ ለማሳየት ሲጽፍ ይሄን ብሏል፡

“አድዋ የሚገኘው ይህ የመንግስት ሆስፒታል የተገነባው በጃንሆይ ዘመን ነው። እድሳት ተደርጎለት አያውቅም። ውስጡ በከፊል ይህን ሲመስል የህወሀት ባለስልጣናት አውሮፓና አሜሪካ ስለሚታከሙ ስለህዝብ ህክምና እጦት ግድ አይሰጣቸውም። የዶ/ር ማርቆስ የግል ሆስፒታል ላይ የፖለቲካ ውሳኔ በማሳረፍ በሃይል ይዘጋሉ። አቶ ዳዊት የተባሉ ባለሃብት ከአሜሪካ ሄደው ሆስፒታሉን አይተው አልቅሰው ሲያበቁ “እድሳት ላድርግለት”? ብለው ሲጠይቁ መከልከላቸውን ገልፀዋል። ከ12 አመት በፊት የጀመሩት የሆስፒታል ግንባታ በነአባይ ወልዱ እንዲቆም ተደርጓል።”

የሌላው ሕዝብ በደል፣ የትግራይ ሕዝብም በደል ነው። የትግራይ ሕዝብ በደል የሌላውም ሕዝብ በደል ነው። በመሆኑ ለሕወሃት ዘረኛ የመከፋፈል ፖሊሲ ቦታ ሳንሰጥ እንደ አንድ ሕዝብ  ይሄን የሕዝብ ጠላት የሆነውን ስርዓት መቀየር አስፈላጊ ነው። አጼ ዮሐንስ እንዳሉት ሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ነን።በመሆኑ የጋራ የሆነችዋን አገራችን እጅ ለእጅ ተያይዘን ከመታደግ ዉጭ ሌላ አማራጭ አይኖረንም። ትግሬ፣ አማራ እየተባባልን መከፋፈላችን መከራችንን ፣ የሕወሃትን እድሜ የሚያራዝም ነው። እነርሱ የፈለጉት፣ የሚመቻቸው እኛ ስንከፋፈል ነው።  እኛ ግን በገባንበት ከነርሱ ወጥመንድ ዉስጥ መውጣት አለብን። በፍቅርም በሰላም፣ በሰለጠነ መንገድ  በመያያዝና በአንድነት እንነሳ። እነርሱ ጥቂቶች ናቸው። እኛ ሚሊዮኖች ነን።

 

 

የአጼ ዮሐንስ 4ኛ ዋና ዋና ፓለቲካዊ ድክመቶች – ከደረጀ ተፈራ

$
0
0
ከደረጀ ተፈራ
መጋቢት 2፣ 2009 ዓም
……………………………….
1). ዮሐንስ (ካሳ ምርጫ) አጼ ቴዎድሮስን አስገድለው ለመንገስ በነበራቸው የስልጣን ፍላጎት የተነሳ እንግሊዝን መንገድ መርተው በማምጣት ለአጼ ቴዎድሮስ ሞት ምክንያት ሆነዋል።
2). ከአጼ ቴዎድሮስ ቀጥሎ የነገሱትን አጼ ተክለ ጊዮርጊስን (ዋግ ሹም ጎበዜ) በጦርነት ከማረኳቸው በኋላ አስሮ ወይም በግዞት ማስቀመጥ ሲችሉ ሐይማኖት እንደሌለው አረመኔ ሁለቱንም ዓይናቸውን በወስፌ ጎልጉለው በማውጣት በጭካኔ አሰቃይተው ገድለዋቸዋል።
3). አጼ ዮሐንስ ቅድሚያ የሚሰጡት ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለስልጣን፣ ለዝናና ለሃብት (ለዘረፋ) ነበር። ለምሳሌ፦ (ሀ). አጼ ቴዎድሮስ ቢሞቱ እነግሳለሁ በማለት የባህር በር ለጠላት እንግሊዝ ክፍት በማድረግ የሃገራችንን ሉአላዊነቷን (Sovereignty) አስደፍረዋል። (ለ). የጎጃምን ህዝብ ከብቱንና እህሉን ዘርፈዋል።
4). አጼ ዮሐንስ በሃይማኖት እኩልነት አያምኑም። ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት የሚል አዋጅ በማስነገር የሙስሊም፣ የይሁዲና የሌሎች እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ዘንድ ቅሬታ በመፍጠር በኢትዮጵያ ላይ ቅሬታ እንዲኖራቸው አድርገዋል።
5). ዮሐንስ የወሎ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን በግድ እምነታችሁን ቀይሩ በማለት አዋጅ አስነግረዋል። አንጠመቅም ያሉትን ህፃንና ሽማግሌ ሳይለዩ በጅምላ ቁጥራቸው ከ30ሺህ በላይ የሆኑ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ቦሩ ሜዳ ላይ በጅምላ ጨፍጭፈዋል፣ ምላሳቸውን ቆርጠዋል፣ አፍንጫቸውን ፎንነዋል፣ ከንፈር ገሽልጠዋል።
6). በኢትዮጵያ ታሪክ ስደት የተጀመረው በዮሐንስ ጊዜ ነው። አጼ ዮሐንስ “እስላም ሃገር፣ አሞራ ቤት የለውም” የሚል አዋጅ ወሎ ላይ በማወጅ የወሎ ሙስሊም አማሮችን አሰድደዋል።
ወሎ ተጠመቅ እምቢ ካልክ ሃገር ለቀህ ውጣ በማለት አሳድደዋቸዋል።
በዮሐንስ ጭቆና የተነሳ በሩን ዘግቶ ከእናት አባቱ ሃገር በእምነቱ ብቻ በርካታ ህዝብ ከወሎ ወደ ሱዳንና ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ተሰዷል።
*ዮሐንስ ከሞቱ በኋላ አፄ ምኒልክ እንደነገሱ “ሁሉም እንደ እምነቱ ይኑር” የሚል አዋጅ በማወጃቸው ተሰደደው የነበሩ በርካታ የወሎ ሙስሊሞች ወደ ትውልድ አገራቸው ተመልሰዋል።
7). ዮሐንስ ቂመኛ፣ በቀለኛና እንደ ስማቸው “በዝብዝ ካሳ” በዝባዥ ነበሩ።
ለምሳሌ፦  የጎጃሙ ንጉስ ተ/ሃይማኖት አልታዘዘልኝም በሚል ምክንያት ቂም ቋጥረው የሚበቀልበትን ጊዜ ሲጠባበቁ ቆይቶ በጎጃም አካባቢ ተነስቶ የነበረውን ቅባት የተባለ ሃይማኖታዊ አስተምህሮን ምክንያት በማድረግ ጉዳዩን ከካህናቱና ከሃይማኖቱ አባቶች ጋር መነጋገር ሲችሉ፣ በትግሬ አገር እንደዚህ ዓይነት ነገር የለም እናንተ ከየት አመጣችሁት በማለት ተራውን የጎጃም ህዝብ በየ መንገዱና በየእርሻው ያገኙትን ሰው ሁሉ በጭካኔ በመግደል የጅምላ ጭፍጨፋና ፈጽመዋል። የጎጃምን ህዝብ ከብቱንና እህሉን ዘርፈው ወደ ትግራይ አግዘዋል።
8). ራስ አሉላን እንደ-መሾምና እንደ-መሸለም ለምን ያለኔ ፍቃድ ዶጋሊ ላይ ከጣሊያን ጋር ተዋጋህ በማለት ከስልጣን መሻራቸው (የቁም እስረኛ ማድረጋቸው)።
9). አጼ ዮሐንስ የምኒልክን ሃይል ለማዳከም በማሰብ የምኒልክ ግዛት የነበረውን የወሎን ክፍል ቀምተው ለልጃቸው ለማንገሻ ዮሐንስ መስጠታቸው።
10). አጼ ዮሐንስ 4ኛ ከእንግሊዝ ተወካይ ከሆነው ከአድሚራል ዊሊያም ሂዎት ጋር የሂዎት ውል / Hewett Treaty/ መፈራረማቸው። ይህ የሂዎት ውል በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ትልቅ ጠባሳ አስከተለ።
11). ኤርትራን እስከ መረብ ምላሽ ለጣሊያን አሳልፈው የሰጡት እራሳቸው አጼ ዮሐንስና ከሳቸውም ቀጥሎ ልጆቻቸው እነ መንገሻ ዮሐንስ መሆናቸው።
12). ዮሐንስ ለራሳቸውም ሆነ ለሃገራችን ደርቡሽ የሚባል የጎረቤት ጠላት አፍርተዋል።
ደርቡሾች (ሱዳኖች) መተማን በመውረር ጎንደርን ያወደሙት፣ ቤተክርስቲያን ያቃጠሉበት ምክንያት በዮሐንስ ላይ ቂም ስለነበራቸው ነው። ምክንያታቸው አጼ ዮሐንስ በጠብ ጫሪነት ለቀኝ ገዢዋ ለእንግሊዝ  አግዘው የሱዳንን ድንበር ጥሰውና ሉአላዊነታቸውን ደፍረው በጀብደኝነት በመውረር ህዝቡን በመጨፍጨፋቸው የተነሳ ነበር።
ወያኔ ከአሜሪካና ከምዕራባውያን በሚያገኘው ዶላር የተነሳ መሃል ሶማሌ ድረስ ወታደሮቹን በመላክ ህዝቡን እንደሚጨፈጭፍ ሁሉ አጼ ዮሐንስም ለእንግሊዝ ተላላኪ በመሆን በጀብደኝነት የደርቡሾችን ደም አፍሷል። የዮሐንስ ጣጣው ግን ለጎንደር ህዝብ ተረፈ።
13). አጼ ዮሐንስ የሱዳን የነጻነት ትግል ወደ ኋላ 72  ዓመት ጎትተዋል፣
የፓለቲካ ብስለት የሌላቸው ጀብደኛውና ጸብ ጫሪው ዮሐንስ ከእንግሊዝ ቀኝ አገዛዝ ሲታገሉ የነበሩትን ደርቡሾች (መሃዲስት) ማገዝ ሲገባቸው በተቃራኒው በመውረራቸው ሱዳኖች ያደርጉት የነበረውን የነጻነት ትግላቸው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ አፍሰዋል፣ አደናቅፈዋል።
ሱዳኖች ከእንግሊዝ ነጻ የወጡት ብዙ ቆይተው በ1956 ሲሆን የሂዎት ውልን ዮሐንስ ለእንግሊዝ በመፈረም ሱዳንን “በጀብደኝነት” የወረሩት በ1884 ነው። ስለዚህ አጼ ዮሐንስ የሱዳን ነጻነት ወደ ኋላ 72 ዓመት ጎትተዋል ማለት ነው። በሌላ አነጋገር ዮሐንስ የሱዳን ህዝብ ለተጨማሪ 72 ዓመታት በቀኝ ገዢዋ እንግሊዝና በተባባሪዋ ግብጽ ስር እንዲማቅቁ ያደረጉ የቀኝ ገዢዎች ተባባሪ ነበሩ።
14). አነሳሳቸው ከሽፍትነት፣ አስተዳደራቸው በዘፈቀደ፣ ውሳኔ አሰጣጣቸው የንጉስ ሳይሆን እንደ ሽፍታ ነበር፣
እንግሊዝ ካሳ ምርጫን (ዮሐንስን) ለመንገድ መሪነት ባይመርጣቸው ኖሮ፣ ዮሐንስ እንኳን ንጉስነት ቀርቶ ከሽፍትነትም የዘለለ ይህ ነው የሚባል ታሪክ አይኖራቸውም ነበር። ለንግስና የበቁበት አጋጣሚ አፋር በረሃ በሽፍታነት ሲንገላወዱ ሳለ ለእንግሊዝ ወራሪ ሰራዊት የመቅደላን መንገድ በመምራት በተሸለሙት የጦር መሳሪያ የንጹሃንን ደም አፍሰው ነው።
15). እና ሎሎችም።

ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች “ማን ያደራድር” በሚለው ላይ አልተስማሙም – አለማየሁ አንበሴ (አዲስ አድማስ)

$
0
0

በቀጣይ ቀጠሮ ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል

ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች በ4ኛ ቀን ቀጠሮአቸው በድርድር ስነ ምግባር ደንቡ ላይ ባደረጉት ውይይት ማን ያደራድር በሚለውና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ክርክር አድርገው ባለመስማማታቸው በይደር ለቀጣይ ቀጠሮ አስተላልፈውታል፡፡

ከትናንት በስቲያ በነበረው ቀጠሮ በቅድሚያ ውይይት የተደረገበት በድርድሩ እነማን ይሳተፉ በሚለው ጉዳይ ላይ ሲሆን ኢህአዴግ፤ “የሶማሌ፣ የአፋር፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የሐረርና የጋምቤላ ክልልን የሚመሩ 5 ፓርቲዎች መሳተፍ አለባቸው” የሚል ሀሳብ ያቀረበ ቢሆንም አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች “ፓርቲዎቹ የክልል ፓርቲዎች እንደመሆናቸው ሊደራደሩ የሚገባው ከክልል ፓርቲዎች ጋር ነው” በማለት ተከራክረዋል፡፡

ኢህአዴግ በበኩሉ፤ በድርድሩ የሚወሰነው ውሳኔ አምስቱን ፓርቲዎችንም የሚነካ በመሆኑና በፓርላማው 46 መቀመጫ ያላቸው በመሆኑ እንዲሳተፉ እፈልጋለሁ የሚል ሀሳብ ቢያቀርብም በአብዛኞቹ ፓርቲዎች ባለመደገፉ  ሀሳቤን ትቼዋለሁ ብሏል፡፡

በመድረክ በኩል ሁለት አማራጮች የቀረቡ ሲሆን ከኢህአዴግ ጋር በዋናነት መደራደር ያለበት ‹መድረክ› ነው የሚልና በተለያዩ ቡድኖች ተከፋፍለን እንደራደር የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ሁለቱም ሀሳቦቹ በአብዛኞቹ ፓርቲዎች ተቀባይነት አላገኙም፡፡

ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ የተደራዳሪዎች ቁጥር ቢመጠን እንደሚስማማ ያስታወቀው ኢዴፓ፤ ነገር ግን የሚመጠንበት መስፈርት በግልፅ የሚታወቅና ሁሉም ሊቀበለው የሚገባ መሆን እንዳለበት ሀሳብ አቅርቧል፡፡

የመድረክ ተወካይ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው፤ “ድርድር በሸንጎ አይቻልም፡፡” በማለት የተሳታፊ ፓርቲዎች ቁጥር መወሰን እንዳለበት አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
ኢህአዴግ በበኩሉ ሶስት አማራጮችን አቅርቧል። ሁሉም 21 ተቃዋሚ ፓርቲዎች በድርድሩ መሳተፍ አለባቸው፤ ተቃዋሚዎች እርስ በእርስ ተመካክረው በቡድን በቡድን ሆነው በተወካዮች መቅረብ ይችላሉ እንዲሁም ለብቻዬ ልዩ አጀንዳ አለኝ የሚል ወገን  ከሌሎች ጋር የተጀመረው ድርድር ሲያልቅ ለብቻው ከኢህአዴግ ጋር መደራደር ይችላል የሚሉ ናቸው፡፡
እነዚህን ሶስት አማራጮች ተቃዋሚዎች ተነጋግረውበት የሚስማማቸውን መርጠው ካሳወቁኝ እነሱ የተመቻቸውን እቀበላለሁ ብሏል – ኢህአዴግ፡፡ በቀጣይ ቀጠሮም ተቃዋሚዎች ውሳኔያቸውን እንዲያሳውቁት ጠይቋል፡፡

ከተሳታፊዎች ምን ያህሎች ሲገኙ ነው ድርድሩ መካሄድ የሚችለው የሚለውም ፓርቲዎቹን በርከት ላሉ ደቂቃዎች ያከራከረ ጉዳይ ሲሆን በመጨረሻም ከተደራዳሪ የፓርቲ ተወካዮች 2/3ኛ የሚሆኑት ሲገኙ ብቻ ድርድር እንደሚካሄድ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
ሰፊ ጊዜ የወሰደውና ሳይቋጭ በይደር የቆየው ጉዳይ ‹‹አደራዳሪ ማን ይሁን?›› የሚለው ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ‹‹ገለልተኛ አካል ይምራ›› እና ‹‹ራሳችን በዙር መድረኩን እንምራ›› የሚሉ ሀሳቦች ቀርበው ፓርቲዎቹ ተከራክረውበታል፡፡
የገዳ ስርአት አራማጅ ፓርቲ በበኩሉ፤ ቀላል ጉዳዮች ላይ በሚደረግ ድርድር ሌላ አደራዳሪ ሳያስፈልግ ራሳችን እንደራደር፣ ከባድ አጀንዳዎች ላይ ደግሞ በገለልተኛ አደራዳሪ መደራደር ይገባናል የሚል ሶስተኛ አማራጭ አቅርቧል፡፡
ኢህአዴግና በርከት ያሉ ፓርቲዎች ‹‹ድርድሩን ራሳችን በዙር እንምራው›› የሚል ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን መድረክ፣ መኢብን፣ መአህድ፣ ኢዴፓ እና 6ቱ ፓርቲዎች፤ ‹‹ድርድር በአደራዳሪና በተደራዳሪ አይመራም፤ ስለዚህ በገለልተኛ ወገን እንደራደር›› የሚል አቋም አንፀባርቀዋል፡፡
ገለልተኛ አካል ለመምረጥ አስቸጋሪ መሆኑንና ገለልተኛ የሚባል አካል ለማግኘት አዳጋች እንደሆነ በመግለፅም የተወሰኑ ፓርቲዎች ‹‹ድርድሩን በዙር መምራት አለብን›› ሲሉም ሞግተዋል፡፡
ኢህአዴግ በመጨረሻ ባቀረበው ሃሳብ፤ ሌላ ገለልተኛ አካል እንደማያስፈልግ በመግለፅ፣ በዙር ይመራ የሚለውን ሀሳብ እንደሚደግፍ ጠቁሞ ኢህአዴግ መድረክ እንዳይመራ ከተፈለገም ላለመምራት ፍቃደኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በነዚህ ሀሳቦች ላይ ሰፊ ክርክር ከተደረገም በኋላ ጉዳዩ መቋጫ ባለማግኘቱ የመድረኩ መሪ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ “ጉዳዩን በይደር አቆይተን በሚገባ አስበንበት በቀጣይ ቀጠሮ እንወስን” በሚል ያቀረቡት ሀሳብ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2009 ዓ.ም በድጋሚ ለመገናኘትና በእለቱ በሁሉም የስነ ምግባር ደንቡ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ ለማጠናቀቅ በማቀድ በቀጠሮ ተለያይተዋል፡፡

ፎረም 65፦ ከቅራኔ ወደ መግባባት (“የት ነበርሽ?”)


አዲስ አበባን ያቀፈ ሸዋ የሚባል ክልል ቢኖር ጥሩ ነው #ግርማ_ካሳ

$
0
0

 

“ኦሮሚያ/ሸዋ ውስጥ ያሉ በትምክተኝነት ምክንያት ኦሮምኛ ያልቻሉ ጥቂት ማህበረሰቦች ካሉ ሁለት እድል አላቸው። አንደኛ ኦሮምኛን ለምደው ተስማምተው የክልሉን ህግ አክብረው መኖር። ሁለተኛ ትምክተኝነት የሚወጥራቸው ከሆነ ደግሞ ወደመጡበት በፍላጒት ሄደው በክልላቸው እንደፈለጋቸው መሆን ይችላሉ። ከዚህ ውጭ ኦሮሞን በጎጥ ለመከፋፈል የምትጥሩትን የሚሰማቹ የለም። ኦሮሞ አንድ ነው።ሁሉም የቦረኔ ባረንቱ ልጅ ነው። ሸዋ ሲነካ ወለጋ ተነካ ፤ሀረር ሲነካ ጅማ አርሲ ፣ባሌ፣ሸዋ፣ጉጂ፣ቦረና ፣ኢሉ ፣ወሎ(ኦሮሞ)ን ያገባዋል። ኦሮሚያ ስትኖር ኢትዮጵያ ልትኖር ትችላለች። ኦሮሚያ ስትፈርስ ግን ኢትዮጸያ የምትባል ሀገር ቅዠት ትሆናለች “ ነው ያሉት እኝህ ጦማሪ።

ይሄ አስተሳሰብ እንደ ኦነግ ያሉ ብዙ የኦሮሞ አክራሪ ብሄረተኞች የሚጋሩት ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ። ለዚህም ነው ላለፉት 25 አመታት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢ አፍቃሪ ኦነጋዉያን የኦህዴድን ካባ ለብሰው፣  “ኦሮሞ አይደላችሁም፣ አገራችሁ አይደለም” በሚል ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ እያደረሱ ዜጎችን  ከቅያቸው ያፈናቀሉት።

እኝህ ጦማሪ ኦሮሚያ የሚባለው የመጣው ከ25 አመታት በፊት መሆኑ የረሱ ይመስላል። ኦሮሚያ ኦነግና ሕወሃት፣  “አማራ” የሚሉትን እና የኢትዮጵያ ብሄረተኞች የሆኑትን (ትምክህተኞች የሚሏቸዉን) ለማዳከምና ለመምታት ጠፍጥፈው የሰሩት ክልል ናት። በሌላ በኩል ደግሞ  ኢትዮጵያ  ለሺህ አመታት የነበረች ናት። ያ ማለት ያለኦሮሚያ ኢትዮጵያ ለዘመናት ኖራለች። እዚህ ላይ ኦሮሞን ከኦሮሚያ መለየት መቻል አለብን። ያለ ኦሮሞ ኢትዮጵያ የምትባል ልትኖር አትችልም። ኦሮሞ ዶር መራራ እንዳሉት የኢትዮጵያ ግንድ ነው።

አሁን ባለው ሁኔታ ኦሮሚያ ብቻ ሳትሆን አሁን በዘር ላይ የተሸነሸው ፌዴራል አወቃቀር ራሱ ሰላምን እና መረጋጋትን ሊፈጥር የሚችል እንዳልሆነ በገሃድ እየታየ ነው። በወልቃይት ጠገዴ ያለው፣  እንደ ሞያሌ፣  ጭናክሰን ባሉ በርካታ ወረዳዎች ፣ በአዲስ አባባና  በአዲስ አበባ ዙሪያ …. ያሉ ዉዝግቦች፣   ለምሳሌ ፣ “ ይሀ ግዛት የዚህ ዘር ነው፣ ያ ግዛት የዚያ ዘር ነው” ከሚለው አሁን ካለው አወቃቀር የመነጩ ችግሮችና ቁውሶች ናቸው።

በአዲስ አበባና አካባቢዋ፣ እንደ አዳማ/ናዝሬት ያሉትን ጨመሮ በርካታ አማርኛ ተናጋሪዎች ከተለያዩ ብሄረሰብ የሆኑ ወገኖች የሚኖሩባቸው ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትና ገዢዎች በአብዛኛው በዚህ አካባቢ የሚኖረውን ማህበረሰብ ስነልቦና የማይረዱ እንደውም፣ ይሄንን ሕዝብ በጥርጣሬ የሚያዩ ነው የሚመስሉት። በክልል መንግስት ደረጃም የሚያራምዷቸው ፖሊሲዎች በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩ ሌሎች ማህበረሰቦችን ጥቅም የሚያስከብር ሳይሆን መብታቸውን የሚረግጥ ነው። በአገራቸው ሁለተኛ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያደርግ።

ለምሳሌ በአዳማ ናዝሬት ያለውን ሁኔታ መመልከቱ ብቻ ይበቃል። በአዳማ ናዝረት አብዛኛው ነዋሪ ወደ 75% አማርኛ ተናጋሪ ነው። ሆኖም በአዳማ የከንቲባው ጽ/ቤት ሆነ በቀበሌዎች የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ብቻ ነው። የፖሊስ ጣቢያዎች የቀበሌ ሰራተኞች፣ አማርኛ እየተናገሩ፣ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ስለደነገገ ብቻ፣  እያስተረጎሙ  ነው በቁቤ ደብዳቤ የሚለዋወጡት። ይሄ አይነቱ አሰራር ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም። የአዲስ አበባ፣ የአዳማ፣ የቢሾፎቱ በአዲስ አበባና አካባቢው የሚኖሪው፣ ኦሮምኛ የማይናገረው በሚሊዮኖች የሚቆጠረው ማህበረሰብ፣   ጦማሪ መርጋ ኢብሳ እንዳሉት  “ኦሮምኛን ለምደው፣  የክልሉን ህግ አክብረው”  ካልኖሩ ወይንም ወደ “መጡበት” ወደሚላቸው ቦታዎች አዲስ አበባን እና ሸዋን ለቀው መሄድ እለባቸው የሚል አመለካከት ነው ያለው።

በዚህ መልኩ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ዙሪያ መካከል ያለው ችግር ሊፈታ አይችልም። ይሄ ደግሞ በምንም መልኩ ተቀባይነት አይኖረውም። ወደ ለየለለት  መተላለቅ  ነው የሚወስደን።

ብቸኛው አማራጭ፣  የሚያዋጣው አማራጭ፣ ኦሮሞዉን ሆነ ሌላው ሁሉ እኩል የሆኑበት፣ ለአስተዳደር በሚያመች መልኩ አካባቢዉን እንደገና ማዋቀር ነው።  በተለይም አዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖረው አብዛኛው የሸዋ ህዝብ ራሱን በራሱ ማስተዳደር መቻል አለበት። ለዚህም ነው አዲስ አበባን ያቀፈ ሸዋ የሚባል ክልል ቢኖር ጥሩ ነው የሚል ሐሳብ የማቀርበው።

አዲስ አበባ፣ የምስራቅ ሸዋ ዞን ሰሜኑ አካባቢ፣ እንዳለ የሰሜን እና የምእራብ ደቡብ ሸዋ ዞኖች፣ ከሆለታ በስተምስራቅ ያለው የምእራብ ሸዋ ዞን፣ በአማራው ክልል ያሉትን የሰሜን ሸዋ ዞንና ከሚሴን ዞኖች እንዳሉ ያጠቃለለ፣  አንድ እራሱን የቻለ ሸዋ የሚባል ክልል ቢኖር ጥሩ ነው። ከዚህም ጋር በተያያዘ፡

  1. የሸዋ የክልሉ የሥራ ቋንቋ አማርኛና አፋን ኦሮሞ ቢደረግ
  2. አማርኛና አፋን ኦሮሞ በሁሉም ት/ቤቶች ከእንግሊዘኛ ጋር እንደ subject ቢሰጥ (ይሄ ማለት የአዲስ አበባ ህዝብ ሳይቀር አፋን ኦሮሞን የመማርና የማወቅ እድል ይኖረዋል)

የበለጠ አዋጭ ይሆናል። ኦሮሞዎችም ሆነ ሌሎች የሚያጡት የሚጎድልባቸው ነገር አይኖርም። የሁሉም መብት ይከበራል። ሁሉም እኩል ይታያሉ። ሁሉም በፍቅር፣ ኦሮሞ፣ አማራ ሳይባባል ተከባብሮ፣ ተዋዶ ይኖራል።

ይሄን ሐሳብ ሳቀርብም፣ አንደኛ በአዲስ አበባ አካባቢዋ የሚኖረው ማህበረሰብ፣  የራሱ የሆነ ባህሪ ስላለው ነው። በመሆኑም  ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። ሁለተኛ ለአስተዳደር የሚያመች ነው። አንድ ክልል በጣም ትልቅ  ሲሆን ለአስተዳደር በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። ሶስተኛ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ መካከል ያለው ዉዝግብ ዘለቄታዊ መፍትሄ ያገኛል።

አፋን ኦሮሞ ብማር፣ ባውቅ ደስታዬ  ነው። እንኳን የአገሬ ህዝብ የሚናገረውን ቀርቶ የሌሎች አገሮችን ቋንቋ ለመናገር እንማር የለም እንዴ ? ቋንቋ ሃይል ነው። ቋንቋ የመግባቢያ መሳሪያ ነው። የአዲስ አበባ ተወላጅ እንደመሆኔ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖረው ገበሬ የሚናገረውን አለማወቄ ያሳዝነኛል። የአዲስ አበባ ልጆች አፋን ኦሮሞ እንድንማር መደረግ ነበረበት።

ሆኖም ግን በግድ የሚሆን ነገር የለም። በተለይም ኦሮምኛ የማትናገሩና የማትለምዱ ከሆነ ሸዋን ለቃችሁ ውጡ የሚለውን አነጋገር እንደ አዲስ አበባ ተወላጅ ልታገሰው የምችለው አነጋገር አይደለም። በተለይም ደግሞ የአዲስ አበባና የሽዋ ተወላጅ ያልሆኑ፣ የአዲስ አበባን የሸዋን ታሪካና ስነ-ልቦና የማይረዱ፣ በአዲስ አበባም ሆነ በሸዋ ጉዳይ ላይ ለመወሰን ሲሞክሩ ማየት ተቀባይነት አይኖረውም። ለዚህ ነው ያመንክኩበትን የምጽፈውና የምጦምረው። እዚህ ጽሁፍ ላይ ካቀረብኩ የተለየ፣ የተሻለ ሐሳብ ከቀረበ ለመማር ዝግጁ ነኝ። መመካከር፣ መከራከር እንችላለን። ግን በሰለጠነ መልኩ እናድርገው።

 

 

 

ማርች 8 የኢትዮጵያ ሴቶች የቃልኪዳን ቀን

$
0
0

ለመጀመሪያ ጊዜ እ.አ.አ. በ1911 በጀርመን፣ በአውስትሪያ፣ በዴንማርክና በስዊዘርላንድ የተከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በእኛ አቆጣጠር የካቲት 29 እነሆ 106 ዓመቱ። ሴቶች በሴትነታቸው ዝቅ ተደርገው በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸው የሚደርስባቸውን አድሎና የወንድ የበላይነትን ለመቋቋምና መብታቸውን ለማስከበር ድምጽ ያሰሙበት ዓለም አቀፋዊ የትግል ቀን 106ኛ ዓመት ማርች 8, 2017። በአጠቃላይ ሴቶች በፆታቸው ለሚደርስባቸው አድልዎ ድምጻቸውን ለማሰማትና የፆታ እኩልነት ተግባራዊ ይሆን ዘንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሰባሰቡበትና ትግላቸውም ዓለም አቀፋዊ አንድነት ይኖረው ዘንድ የተጀመረ ክብረ ባህል። ማርች 8 (የካቲት 29)። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

እኛ ወደ ትግሉ ካልሄድን ችግሩ ወደኛ መምጣቱ አይቀሬ ነው

$
0
0

እራስን ከጥቃት በመከላከል ሰላማዊ ህወት ለመምራት  ከሌሎች ሰዎች ጋር ተቻችሎና ተስማምቶ አብሮ የመሆን ባህርይ የሰው ልጅ በተፈጥሮ የሚያገኘውና በህወት ልምድም የሚያዳብር ችሎታ ነው ማለት ይቻላል። ይህ  አብሮ  የመሆን  ልምድ ከቤተሰብ  ጀምሮ በጉርብትና፤ በጎሳና ሀይማኖት መመሳሰል እያደገ  ሃገርን እስከ መመሥረት ይደርሳል። በሂደትም  አንድነት ሃይል መሆኑንም ያረጋግጣል። እነዚህ በየደረጃው ያሉት ስብስቦች በውስጣቸው ልዩነት መኖሩ አይካድም። ልዩነት በሀገር ደረጃ በተሰባሰቡ ሰዎች መሀከል ብቻ ሳይሆን በመንትዮች መሃከልም ይታያል። ህዝቦች ልዩነታቸው አንደተጠበቀ ሆኖ በጋራ በሚያስተሳስራቸው፤ በሚያቀራርባቸውና ባሳለፏቸው ታሪካዊ አብሮነት ተመስርተው  አንድነትን ፈጥረው  በድንበር የተከለሉ ሃገራትን መስረተው አብረው ይኖራሉ።

ከአንድነት የሚገኙ በርካታ ጥቅሞች መኖራቸው በጣም ግልጽ ሆኖ ሳለ የህዝቦችን አንደነት የሚጠላ ግለሰብም ይሁን ስብስብ መኖሩ ብዙዎቻችንን ግራ የሚያጋባ ክስተት ነው። ሀቁ ግን አንድነትን የሚጠላ በአንድነቱ የማይጠቀምና የሚጎዳ ብቻ ነው። እርግጥ ነው አንዳንድ ሰዎች ስብስብን የሚፈጥሩት ለክፉ ነገርም ሊሆን ይችላል። እንዲህ አይነት ስብስብ የሚፈጥሩት ግለሰቦች ግን ምንግዜም ቢሆን ሰው በዙሪያቸው የሚያሰባስቡት አንዱ ሌላውን እንዲጠላ በመስበክና ለሚቀሰቅሱት ህብረተሰብ ከነሱ ሌላ ወዳጃና መሪ እንደሌላቸ በመስበክ ነው። ለዚህም  እኛም መሀከል ለግል ጥቅም  ሲባል ህዝብ ከህዝብ እያናከሱ አንቱ ተብለው ለመኖር ልዩነትን የሚያሰፉ ፕሮፖጋንዳ በመርጨት የተጠመዱ ወገኖች ያሉን።

ህወሃት  የህዝቦችን  አንድነት የሚፈራበት  ዋነኛው  ምክንያት ከኢትዮጵያ ህብረተብ ውስጥ በመቶኛ ሲሰላ  “ውክልናው” ከአናሳ የህብረተሰብ ክፍል በመሆኑ እራሱ በሚያቀነቅነው የፓርላማ  ዴሞክራሲ ቦታ ስለሚያሳጣው ነው። ለዚህም  እድሜን ለማርዘም በከፋፍለህ ግዛ ዘይቤው ህዝቦችንን መከፋፈልን ዋና መሳሪያው አድርጎት ይኸው  ሀያአምስት አመት አለፈው። ይሀንን ዘይቤ ከሞላ ጎደል በስኬታማነት እስከዛሬ  ለመጠቀም  የቻለባቸው ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም  ዋንኛው ግን ቀደም ሲል ለዘመናት የነበረውንና በተለያዩ ጊዜያት ብቅ ባሉት የገዥ  ክፍሎች  ወቅታዊ  ምላሽ ያላገኙትን የብሄር ጥያቄዎችን በ1936-42 ጣሊያን በሀገራችን በወረረችበት ወቅት ለተመሳሳይ መሰሪ አላማ የተጠቀመችበትን ዘዴ (ከዚህ ቀደም ለማብራራት እንደሞከርትኩት) በመጠቀም የችግሩ ፈቺ  መስሎ በመቅረብ የአዞ እምባ በማንባት ነው።

ለዘመናት በአንድነት በመቆም ከውጭ ወራሪ ነጻነታችንን ጠብቀን የቆየን ብንሆንም ወያኔ  መከፋፈል ለእርሱ ስልጣን ላይ መቆያ ብቸኛ መፍትሄ እንደሚሆነ በመገመት ህዝባችንን የመከፋፈሉን ሴራ የጀመረው ጫካ ጠቅልሎ ከመግባቱ በፊት ነው። ታዲያ ለዚህ ከፋፋይ ሥራው እንቅፋት ሊሆንበት የሚችሉ ሁለት ሃይሎች የሃይማኖት አባቶችና ምሁራን ነበሩ ናቸውም። ሁለቱም ሃይሎች ህዝቡን በማንቃት ወደ ትክክለኛው መንገድ በመምራት ረገድ ተፅእኖ የመፍጠር አቅም ስላላቸው ውጥኑን ሊያከሽፉበት እንደሚችሉ ከጥዋቱ ተረድቶ ነበር። በመሆኑም እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች በጠላትነት በመፈረጅ ለማንበርከክና ለማጥፋት ጥረት የጀመረው ገና ከትግራይ በረሃ ሳይወጣ ነበር።

ለዚህም የህወሃት የመጀመሪያ ኢላማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ናት። በታሪክ አጋጣሚ ቤተክርስቲያኒቷ በነበራት ሥፍራ ከአማራው ብሄር ጋር በማያያዝ አማራውን በጥቅል እንደ ጨቋኝና በዳይ በማቅረብ ከማጥላላት አልፎ የቤተክርስቲያኒቷን መሬት በመንጠቅ ለደጋፊዎቹ አድሏል። መሪዎችንም ከአብተክርስትያን በማባረር ታዛዥ በሆኑት መሪዎች በመተካትና (ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ገጽ 302) እነሱንም ቢሆኑ የስለላ መዋቅሩን በቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ ገዳማት ሳይቀሩ በመዘርጋት ሰላዮችን በመነኩሴነት በማስቀመጥ ይየሰልላቸው ነበር።

በወቅቱ በትግራይ የነበረው የሙስሊሙ ህብረተሰብ በቁጥር አነስታኛ ከመሆኑም በላይ ከክርስትና እምነት ታካታዮች በተለየ ሁኔታ ላይ ነበር (ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ገጽ 318)። የመሬት ባለቤትነት የሌለው ከመሆኑም ሌላ አብዛኛው ሙስሊም በንግድ ሥራ ላይ የተሰማራና  በከተሞች ውስጥ የሚኖር ነበር። የሙስሊሙ ህብረተሰብ ህወሃት (ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ) ሃይማኖቱን ሊያዳክምበት እንደመጣ በመገንዘብ እርኩስ አላማውን ለመቋቋም በተለይም  ከአፋር የእስልምና ተከታዮች (ገብረመድህን አርአያ ) ባደረገው ተጋድሎ የተነሳ ሀወሃት ከጥፋት ዘመቻው ጋብ ቢልም  ኋላ ላይ ግን  ይህንን  የህብረተሰብ  ክፍል  በፋሽስቱ የጣሊያን ዘዴ “አዛኝ ቅቤ አንጓች” እንዲሉ አስመስሎ ከጎኑ ለማሰለፍ ስለመቻሉ መካድ ይከብዳል።

በተመሳሳይ መልኩ በምሁራን ላይም ዘመቻ በመክፈት በእንታረቅ ሰበብ በተኙበት ከመጨፍጨፍ አልፎ ውጊያ በመግጠም ብዙዎችን አስወግዷል። ለዚህም ከኢህአፓና ከኢዲዩ ጋር የነበሩትን ጦርነቶች መጥቀሱ ይበቃል። እነዚህ ግፎችና  ህወሃት ጫካ በነበረበት ወቅት የተከናወኑ ደባዎችና ፍጅቶች ሲሆኑ ያኔ አብሯቸው ከነበሩ የቀድሞ አባሎቻቸው ባይነገረን ወይም ባይፃፍ ኖሮ “ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ” እንዲሉ እንኳንስ ሌላው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ የትግራይም ህዝብ ባላወቀው ነበር።

በለስ ቀንቷቸው አዲስ አበባም ከገቡ በኋላ ይህንን እርኩስ አላማቸውን በመቀጠል እነዚህን ሁለቱን የህብረተሰብ ክፍሎችን በተጠናከረ ሁኔታ ኢላማቸው አድርገው እስከዛሬ ቀጥለውበታል። ለዚህም የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን ቃኖና በመጣስ ጳጳስ በህይወት እያለ በሌላ በመተካትና ሲኖዶሱን ለሁለት መክፈል፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠ/ምክር ቤትን (መጅሊስ) ለመቆጣጠር በ1987 በአንዋር መጂድ በየፀጥታ ሃይሎች የተፈጠረው እልቂትና እስካ እዛሬ ድረስ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ፈተና የሆነውና ለድምፃችን ይሰማ ንቅናቄ መፈጠር ምክንያት የሆነው፤ ብዙዎች የተሰውበት፤ ብዙዎች የታሰሩበትና የተሰቃዩበት “ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጋር ሊሄድ የሚችለውን የአህባሽ ሃይማኖት ተቀበሉ” ወከባ መጥቀሱ በቂ ነው። ህወሃት ለመሰሪ አላማው ያሰጉኛል ያላቸውን ምሁራንንም ለማስወገድ የመጀመሪያ ኢላማው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነበር።

ወያኔ/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶች ተዋህዶ ቤተክርስትያንና  በምሁራን ላይ ያደረሰውናን እያደረሰ ያለውን ጥቃትና ይህ ጥቃት በበኩሉ ለነፃነት በሚደረገው ትግል ላይ ያሳደረውን ተፅእኖ ከቀላል አይደለም። ይህንን በተመለከተ ሰፊ ሃተታ የሚያሻ በመሆኑ ለጊዜው በይደር ልለፈውና ሃሳቤ ላካፍላችሁ ወዳቀድኩበት ጉዳይ ላይ ብቻ ላትኩር።

በ1987 የተፈጠረው ሁኔታ በአንዋር መስጊድ 29 ምዕመናን በ”መንግስት” የፀጥታ ሀይሎች ሲገደሉ በሁኔታ በማሳበብ ወያኔ/ኢህአዴግ  የኢትዮጵያ እስልምና  ጉዳዬች ጠ/ምክር ቤት (መጅሊስ) በእጁ ከማስገባቱም ሌላ የተለያዩ የሙስልም በጎ አድራጎት ድርጅቶችን (NGO) በመዝጋት የሙስልሙን የእምነት ነጻነትን የማፈኑን ተግባር ተያያዘው። ቀደም ሲል በነበሩት 5 አመታት ለሙስሊሙ ማህበራሰብ የቆመ በመምሰል የሌላው ህብረተብ እምነት በተለይም የክርስትያኑን ለማዳከምና በጁ ላማስገባት ለጊዜ መግዢያነት ተጠቅሟል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ህወሃት እስልምናን ለማዳከም የተያያዘው ጥረት  ሙሉ በሙሉ ባለማሳካቱ ተስፋ ባለመቁረጥ ክፍፍሉን በማጠናከር በሁለቱ ተላላቅ ሃይማኖቶች መሃል ጥርጣሬን ማጠናከር ነበር። ለዚህም ሙስሊሞችን “እስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ ነው” ክርስትያኑን ደግሞ “የድሮውን ስርአት ሊመልሱ ነው” ብሎ “ለተለያያዩ” አድማጮቹ (Audiences)  ማሰማት ነበር። ይህም ለተውሰነ ጊዜ የሰራለት መስሎ ታይቶት ነበር። በእውነታ ላይ ያልተመሰረተ የፈጠራ ወሬ መልሶ ወረኛውን ስለሚጎዳ ወያኔ/ኢህአደግ የወረወረው ድንጋይ መልሶ መታው፤ እንግሊዞች (Pissing in the wind) እንደሚሉት፣ የበለጠ ጥላቻን አተረፈለት።

አምባገነኖች በህዝባቸው ጫንቃ ላይ በቆዮ ቁጥር የስልጣን ጥማት ስካራቸው እያየለ ይሄዳል በዚያው መጠን አሮጋንቲነታቸውና ለህዝባቸው ያላቸው ንቀት ይጨምራል። የሚገዙት ህዝብ እንዴት እንደሚበላ፤ እንዴት እንደሚናገርና ከማንጋር እንደሚናገር፤የትና ወዴት መሄድ እንዳለበት፤ መንፈሳዊ እምነቱ ምን መሆን እንዳለበት በአጠቃላይ በዚች አለም ላይ እንዴት መኖር እንዳለበት ሊወስኑለት ይቃጣቸዋል። ወያኔ/ኢህአዴግም ሁሉንም ለማድረግ ሞክሯል “እንደኛ ሃይማኖት አልባ መሆን ካልቻላችሁ ለኔ የሚስማማኝን ሃይማኖት (sect) ልጥመቃችሁ” ብሎ አህባሽ የተባለ ከእስልምና እምነት ፈር የለቀቀ  አምጥቶ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ በጉልበት ለመጫን ሞከረ።

ይህም ተገቢ አለምሆኑንና እሱ እራሱ የሚመጻደቅበት “ህገመንግስት” የመንግስት በሃይማኖት ጣልቃ መግባትን  የማይፈቅድ መሆኑን  የሙስሊሙ ህብርተሰብ ኮሚቴ በማቋቋም ችግሮቹን ለማስረዳት ቢሞክርም ህወሃት/ኢህአዴግ  የመናገርና የማዘዝ እንጂ የማዳመጥና “ህገመንግስቱ” የመተገበር በህርዪ ያልተካነ “መንግስት” በመሆኑ የመንግስታዊ ሃይማኖት ጫናውን ለማቆም ፍቃደኛ አልሆነም።

 ሰላማዊ ትግልን መታገል ለሚሹ አርአያ ለመሆን በሚችል አለም አቀፍ ተቋማት እውቅናን ባገኘው  ሰላማዊና መራር በሆነው ትግልሙስሊሞች ህወሃት/ኢህአዴግ ድምጻቸውን እንዲሰማና ለጥያቄያቸው መልስ እንዲሰጥ ግፊት ለመፍጠር ቢሞክሩም መልሱ ህዝቡ በፊርማው የመረጣቸው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የእስር ብቻ ሳይሆን የድብደባ፣ የግርፋት፣ የማዋረድ፣ የሰብዓዊ መብትም መገፈፍ ሰለባ ማድረግ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናንን ማሰር፣ መግረፍ፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ደግሞ ለሰደት መዳረግ ነበር። ከዚያም አልፎ ሰላማዊ ዜጎች በግፍ ጥይት እየተደበደቡ ለሞት መዳረጋቸው ሊካድ የማይችል የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

ምንም እንኳን  ከህወሃት/ኢህአዴግ ካንጋሩ ፍርድ ቤት ፍትሃዊነት ባይጠበቅም የህብረተሰቡን ለመደለል የተደረጉ ሞከራዎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው በራሱ ቴሌቪዢን ዘጋቢ ፊልሞችን አዘጋጅቶ ማሰራጨት ነበር፡፡ እነዚህ “ዘጋቢ” ፊልሞች ማለትም “አሸባሪው አል ሸባብ ኢትዮጵያ ውስጥ የራሱን ሕዋስ (cell) ለመዘርጋት ጥረት እያደረገ ነው” (አዲስ ግንባር)፤ “በኢትዮጵያ የተገኘው ሁለተኛው የአልቃይዳ ሕዋስ” (ጂሃዳዊ ሃራካት)፤ “ሸህ ኑሩን ወሃቢስቶች  ገደሏቸው” (ሀዘን ለመድረስ … ጉዞ ወደ ደሴ )፤ ከእስልምና እና ከሽብርተኝነት ጋር ተያይዘው የቀረቡት የጥፋት መልዕክተኞችና የማንቂያ ደወል የህዝብ ገንዘብ አለአግባብ ከማባከን በስተቀር ለህወሃት/ኢህአዴግ ያተረፈለት ነገር የለም ይልቁንም የስርአቱ ማንነት የበለጠ የተጋለጠበት አጋጣሚ ነው ማለት ይቻላል። ከህወሃት/ኢህአዴግ ባዚሁ ሳያበቃ በትግሉ ላማዳከም   የይቅርታና የእርቅ ኮሚቴ “የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ” የሚባል አካል አዋቅሮ በሙስሊማን ላይ  ከጅምሩ የከሸፈ “ተጸዕኖ” ለማሳደርም ሞክሯል።

በርግጥ የስርአቱ ሰለባ የሆንነው እኛ ሙሊሞች ብቻ ሳንሆን በዚያች ምድር የሚኖር ክርስትያኑም፤ አይሁዲውም፤ ዋቄፈቻውም፤ ኢ-አማኑ፤ ኦሮሞውም፤ አማራውም፤ ጉራጌውም፤ ኦጋዴኒውም፤ትግሬውም፤ ከምባታውም፤ ሃዲያውም፤ ወላይታውም. . . ነው። ለሙስሊሙም ሆነ ለሌላው መብት መከበር አንድ ላይ ሆኖ ለሥርአት ለውጥ መታገል ወሳኝ ነው። የእያንዳንዳችን ነጻነት ሲከበር እንደሙስሊም ወይም እንደሌላው የህበረተሰብ ክፍል አባልነታችን ልዩነታችን እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ ነጻነታችን ይከበራል። ለነጻነት የሚደረገውን ትግል የፖለቲካ ሥራ ነው ብለን ካልን፤ ከፖሊቲካ ነጻ የሆነ ግለሰብ ወይም ማህበረስብ አለ ለማለት ባያስደፍርም አላህ (ሱ.ወ) የሰጠንን አንጻራዊ ነጻነትን የነፈገንን አካል መታገል ሃይማኖታችን (42:39) የሚፈቅድልን ይመስልኛል። የ”ድምጻችን የሰማ” እንቅስቃሴም የመብትና የነጻነት ጥያቄ ነውና። የህዝብን ድምጽ የማይሰማ አካል ካለ እንዲሰማ መገደድ ይኖርበታል። አሊያም ቦታውን ለቆ ህዝብ በሚመርጠው መተካት አለበት። አንድ የመንግስት አካል የሚመረጠው ህዝቡን ሊያገልግል እንጂ በህዝቡ አንዲገለገል ከዚያም አልፎ መብቱንና ነጻነቱን እንዲነፍገው አይደለም። በአጭሩ መንግስት የህዝብ ተቀጣሪ አገልጋይ ደሞዝተኛ ነው።

አንድ ሙስልም የመጀምሪያ ግዴታው ከሁሉም በላይ  ሃይማኖቱ (ዲኑ)የሚያዘውን ተግባራዊ  ማድረግ ነው። በመሆኑም ከሌሎች ጋር አብሮ ለመስራት በጋራ ሊተገበሩ የሚችሉ ጉዳዮች ከዚህ ከየ እለቱ የሃይማኖት (ዲን) ግዴእታዎች ጋር የሚጋጩ ከሆነ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ከነዚህም ከብዙ በጥቂቱ፤የየ እለት የሰላት ሰአታት፤ የአርብ (ጁምአሰላት)፤ የረማዳን ወር ጾም፤ የወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ  መሰባሰብና የመሳሰሉት ናቸው። የሁሉንም የተለያዩ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያንን ተሳትፎ ለማጎልበት የጋራ መድረኮች ከቤተ እምነቶች ሰበካ ቢፀዱ መልካም ነው የሚሉም አሉ። ስብስቦቻችን በነሱ ባይባረኩ ምንም የሚጎላቸው ነገር አይኖርም። የእምነት አባቶች ከምዕመናን ጋር በየሚሰበሰቡበት ስፍራና ቤተኢምነቶች ለህዝባችን የሚያደርጉት ፀሎት በቂ ነው ይላሉ።

 እነዚህን አንደየ ሁኔታቸው ማስተናገድ (Accommodate) የሚቻል የመስለኛል። ከዚህ ውጭ መሰራታዊ የሆኑና ለአብሮ መስራት እንቅፋት የሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ያሉ አይመስለኝም። ካሉ ግን ፊትለፊት መነጋገር መፍትሄ ለማግኘት የበጃል ብዬ አምናለሁ። ይህ ካልሆነ ግን እርስበርሳችን እየተጠራጠርን ሁላችንም ነጻነታችንን እንደ ተነፈግን ኖረን ለልጆቻችን “ባርነትን” አስረክበን እናልፋለን። ይህ ደግሞ የማንንም አባት ወይም እናት ፍላጎት አለመሆኑ ግልጽ ነው።

እስልምና አብሮመስራትን ነው የሚያስተምረን። የሃገራችንን ሁኔታ ስንመልከት ዘርና ጾታን ሳይለይ ምስራቅ ያለው ለምዕራቡ፤ ደቡብ ያለው ለሰሜኑ፤ እንዲሁም ለመሃል አገሩ ሙስሊምና ሌሎች የሃገሩ ህዝቦች መብት መከበር ተቆርቋሪና ለተግባራዊነቱ መታገል ይኖርበታል። አንዱ የህብረተሰብ ክፍል ነጻነት ከተነፈገ የሁሉም ነጻነት እንደተነፈገ ይቆጠራል። በአንድ ሃገር ያሉ ህዝቦች የሚኖራቸው ነጻነት እኩል መሆን የኖርበታል። ከታሪክ እንደምንረዳው እስልምና የሚያስተምረን ይህንኑ ነው።

ይህ  ከሆነ ታዲያ ለነፃነት በሚደረገው ትግል እኛ ሙስልማን እያደረግን ያለው አስተዋጽኦ በቂ ነው ማለት ይቻላል? ይህንን ጥያቄ የማቀርበው ለራሴ ጭምር ነው።

ኢትዮጵያ እስልምናን ከተቀበለች ለአስራ አራት ምዕተ-አመት ቢሆንም የቀድሞ ገዢዎቻችን 30% (በዚህ ቁጥር የሚከራከሩም አሉ) ሙስልም ወደ ጎን በመተው ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት ናት ይሉ ነበር ዛሬ ግን ወያኔ ህንን ቀይሯል ብለን ከሆነ ተሳስተናል። ይልቁንስ ሃይማቶት የለሹ ወያኔ ሁሉም ሃይማኖቶች የተደፈጠጡባት የመከራና የአፈና ደሴት ነው ያረጋት። እርግጥ እድሜ ለቴክኖሎጂ ወጣቱ ትውልድ የእስልምና መጽሃፎችን በሃገራዊ ቋንቋ በቀላሉ ማግኘት በመቻሉ እራሱ ለማስተማር ችሏል። ወያኔ ቀደም ሲል እንደተገለጸው ለራሱ ጊዜ መግዢያ  እስከ 1987 ድረስ ለቀቅ ባደረገው አንጻራዊ ነፃነት መስድጂዶችና የመማሪያ ተቋማት ሊገነቡ ቢችሉም በኋላ ላይ  ግን በመጅሊሱ አማካይነት አህባሾች እንዲቆጣጠሯቸው ተደርጓል። ይህ ማለት ደግሞ ሁሉም በወየኔ ቁጥጥር ሥር  ነው።

በኢትዮጵያ በእስልምና ተቋም (Institution) ደረጃ ባይሆንም በመካሄድ ላይ ባለው የነፃነት ትግል ውስጥ በግልም ሆነ ሃይማኖታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በመሳተፍ ላይ ያሉ ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን  አሉ። ለዚህም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተደረጉና እየተደረጉ ያሉ ትግሎች በቂ ምሳሌዎች ናቸው።

መሪዎች በግልም ሆነ በስብስብ (Congregational) ሌላው ቢቀር እየተፈጸመ ያለውን ግፍና ሰቆቃ በማውገዝ ረገድ በሀገር ውስጥ ባለው የወየኔ/ኢህአዴግ ጫና ከባድ ቢሆንም ያ ስጋት በሌለበት በውጭ አለም በምንኖር በጋራም ሆነ በግል ለነፃነትና ለፍትህ ለሚደረገው ትግል ተሳትፎአችን በጣም አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ምክንያቶቹ ግን ከመላምት ባሻገር (በግልጽ ሥርአቱን የሚደግፉ እንዳሉ ሆነው) ይህ ነው ማለት ያስቸግራል።

ከመላምቶቹ መሃከል የተሻለች የሁሉም መብት የተከበረባት ኢትዮጵያን ለመገምባት በመታገል ላይ ያሉትን ሃይሎች በቅርበት ካለማወቅ የተነሳ በጥርጣሬ አይን የማየት፤የወያኔን መሰሪነት ካለመረዳትና ከትናንቱ መገፋት (marginalization) በመነሳት ከልብ ስርአቱ እስልምና የቆመ አድርጎ መውሰድ፤ “የባሰ ይመጣ ይሁን?” ጥርጣሬ፤ “እኔ ምናገባኝ ድሮም አልነበርኩበትም”፤ እያወቁ ለጊዜያዊ ጥቅም መሸነፍን…….የመሳሉትን ያጠቃልላል።

ሃይማኖታችን ለሃቅና ለፍትህ እንድንቆም ያስገድደናል። በጎሳና በነገድ ሳይሆን እንደ ህዝብ አንድ ላይ ሆነን በደልን እንድናወግዝና ከተበዳዮች ጎን እንዲንቆም ያዘናል።

አላህ (ሱ.ወ) የሰጠንን አንፃራዊ ነፃነት የሱ ፍጡር በሆኑት አምባገነኖች ተነጥቀን ሲያዋክቡን፤ ሲያሰድዱን፤ ሲያስሩን፤ ሲያሰቃዮንና ሲገሉን መሪዎቻችን ምንም እንዳልተፈጠረ ፈታቸውን ወደ ሌላ አቅጣጫ በማዞር ዝምታን መምረጣቸውና አዳንዳንዶቹም ከነዚህ አምባገነኖች ጎን  መሰላፋቸው ተገቢ አይመስለኝም።

የዛሬ 77 አመት የጣሊያ ወራሪዎች መጠቀሚያ እንዳደረጉን ህወሃት/ኢህአዴግ እንዲደግም መፍቀድ የለብንም። የግለሰቦች ነፃነት ሲረጋገጥ የሁላችንም  ነፃነት እንደ ግለሰብም ሆነ አንደ ሰብሰብ ሰለሚረጋገጥ የነፃነት ትግሉ የሙስሊሞችም ነው። ዛሬ በትግሉ መሳተፍ ስንችል ነው ነግ “ይህ የዛሬ ነፃነት እኔም ትናንት የታገልኩለትና ወንድሞቼ፤ እህቶቼ፤ አባቴና እናቴ መስዋእትነት የከፈሉበት ነው” ብለን በሙሉ ልብ መናገርና የነፃነቱ ባለቤትነት ሊሰማን የሚችለው።

ትግሉን መቀላቀል የሚንችለው እኛ ወደ ትግሉ በመሄድ እንጂ ብቻ ነው፤እኛ ወደ ትግሉ ካልሄድን ችግሩ ወደኛ መምጣቱ አይቀሬ ነውና። ቀደም ሲል የተጠቀሱት የሃይማኖታችን የዕለት ተዕለት ተግባራት (ዕባዳ) ጋር የተያያዙ የጊዜና ቦታ ጉዳዮችን ማስተናገድ የሚቻል ከሆነ ከዚህ ውጭ ያሉ እንዳንቀራረብ የሚያደርጉን ጉዳዮች ካሉም በግልፅ በመወያየት መፍትሄ ማግኘት ይቻላል። ከዛም ባለፈ ባጋራ ሊያስማሙን በሚችሉ ጉዳዮች ላይ አብሮ በመስራት ለነፃነት መብቃት የሚቻል ይመስለኛል።

ሓይማኖታችንን ፈጣሪያችን ባዘዘን መልኩ በትክክል መተግበር ያሚቻለው ነፃነት ሲኖር ነው። ነፃነትና ሀገር ደግሞ ተለያይተው አይታዩም፤ አንዱ ከሌለ ሌላኛው  ትርጉም ያጣልና።

ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት የተለያዩ ሃይማኖቶች በተለይም በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች መሃከል በጥርጠሬ መተያየቱ ሊኖር ይችላል። እርግጥ በተለያዩ ዘመናት በሌላው የዓለም ክፍሎች ከታዮትና እየታዩ ካሉት የሃይማኖት ግጭቶች  የራሱ በሆኑ ምክንያቶች  በባህሪየም ሆነ በይዘቱ የተለየ ቢሆንም ግጭቶችም ሆኑ በጥርጣሬ መተያየቱ የነበረና ዛሬም ያለ መሆኑን መካድ አይቻልም።ይህም ዝምብሎ በአንድ ጀምበር የተከሰተ ሳይሆን ለብዙ ዘመናት አብረን የኖርን ቢሆንም በዚያው መጠን በተለያዩ ጊዚያት በሃገሩቷ ውስጥ የተነሱት ገዚዎች ለስልጣን መቆናጠጫና ስልጣኑ ላይ ለመቆያ ሁለቱን ታላልቅ ሃይማኖቶችን በመሳሪያነት በመጠቀማቸው እርስ በርስ ጦርነት መሳበቅ የተደረሰባቸው ጊዚያት መኖራቸውና የበላይነትን የተቀዳጀው ክፍል በዚያው ለመቀጠል ያደረጋቸው  ጥረት የወለደው የማግለልናን የመገለል ሂደቶች የጥርጣሬ ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ።

ወያኔ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች  ፅንፈኛች ፤መሪዎችን ደግሞ (እጅ የሰጡትን ሳይጨምር) አሸባሪዎች እንደሚላቸው ሳይሆን፤ በተለይም የወጣቱ ትውልድ መሰረታዊ ባልሆኑ (ሰለፊ፤ ሱኒ፤ ተብሊጊ…)ላይ ከማተኮር ቁርአንና የነቢዩን (ሠ.አ.ወ) ሱናን በመከተል ትክክለኛና ጥሩ ሙስሊም መሆንን የመረጠ በመሆኑ በጥቅሉ መጠርጠር ተገቢ አይሆንም።

እርግጥ በማንኛውም ሃይማኖት ሆነ የፖለቲካ እምነት ውስጥ ካለማወቅም ሆነ አውቀው ለተለየ አላማ  ከትክክላኛው መንገድ ወጣ ያለ የፅንፈኝነትን አቋም የሚያቀነቅኑ አንዳሉ ሁሉ በሙስሊሙም ህብረተብ ከላይ ከተጠቀሰው ባልተለየ ምክንያት መኖራቸው መካድ አይቻለም። ሆኖም እነዚህቡድኖች ጥቂቶች በመሆናቸው የስጋትና የጥሪጣሪ ምንጭ መሆን የለባቸውም። እንዚህንም የመወጋት የሙስሊሙ ህብረተሰብ መሰረታዊ ተግባር ነው።

የመልእክቴ መሰረታዊ አላማ ችግሮች ካሉ ለችግሮቹ መፍትሄ ለመሻት እንዲቻል ለውይይት ለመጋበዝ እንጂ  ስለ እስልማና እውቀት አለኝ ብዬ በድፍረት ያልቀረብኩ መሆኔና ተሳስቼም ከሆነ ፈጣሪዬን ይቅርታ እየለመንኩ ለመታረምም ዝግጁ መሆኔን ላንባቢያንም ለመግለፅ እወዳለሁ።

ምንም እንኳን እንደ ህወሃት ላሉት (የዶክተር መረራ ቃል ልዋስና) እነሱ ከጫካ ቢወጡም ጫካ ከነሱ ውስጥ ላልወጣ ቡድኖች የማይሰራ ቢሆንም  ዛሬ አለም በደረሰበት ዘመን መነጋገር፤ መወያየትና በሰጥቶ መቀበል መርህ ላይ የተመረኮዘ የችግር አፍታት ዘይቤ ከፍተኛ ሥፍራ አለው ብዬ ስለማምንም ጭምር ነው። እንኳንስ ሃገርን የሚያህል ግዙፍና የህልውና ጉዳይ ቀርቶ በቤተሰብ መሃከል  ለሚፈጠረው ችግር እንኳን በመነጋገርና በጋራ በመስራት ነው መፍትሄ የሚገኘው። በተናጠል ለጠላት ከመመቸት በስተቀር  የትም አንደርስም።

አላህ ወደተቃናው መንገድ ይምራን።

አላህ ኢትዮጵያን ከነ ህዝቦቿ ይጠብቃት።አሚን።

ባህር ከማል

bahirk@hotmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Ethiopia: detained journalists denied justice

$
0
0

Ethiopian authorities should immediately release journalists Ananiya Sori and Elias Gebru or respect their right to due process. Since their arrest, on 18 November 2016, neither journalist, has been prosecuted or formally charged with any offense.

Elias Gebru and Ananiya Sori were arrested on 18 November 2016, together with their colleague and former leader of opposition party, UDJ (Unity for Democracy and Justice), Daneil Shibeshi by security forces. Outspoken journalist and former political activist Ananiya Sori was arrested following his recent criticism of government policies in reaction to widespread protests in the country during a radio debate organized by the pro-government media, Fana Broadcasting, in October 2016. In addition, Elias Gebru who is a freelance journalist and social media activist was apparently arrested in relation to his political analysis and published articles on social media.

Neither journalists have been informed of any formal charges against them and have been denied access to legal consultation or medical treatments. Both Elias Gebru and Anania Sori are also reportedly experiencing serious health problems due to the harsh detention conditions in several police stations across the capital, Addis Ababa. Elias Gebru is reportedly suffering from losing his olfaction senses. Together with Anania and Daneil, Elias was originally held in Bole Woreda police station for three months before being transferred to Qirqos Woreda Police station.  Anania Sori has also been transferred to the 6th Police station, currently called the Qirqos Sub-City Police Division.     .

The Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) has documented and reported the arrest of several journalists, human rights defenders and political activists since the State of Emergency was declared on 8 October 2016. “The Ethiopian authority is using the decreed state of emergency as a pretext for escalating grave human rights violations, dismantling dissent and a political crackdown in the country” said Yared Hailemariam, Director of the Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE).

Background

Since the State of Emergency was declared in October 2016, thousands have been arbitrarily arrested in relation with widespread protests in the country, mainly throughout Oromia and Amhara regions. Even though different credible sources confirmed that more than 30,000 people have been detained under the State of Emergency, Ethiopian authorities have confirmed only the release of nearly 20,000 detainees after months spent in different military training centres located in different regions of the country. The authorities also claimed that the detainees were released after receiving rehabilitation training, despite the allegation that many of the detainees were reportedly tortured and subjected to inhuman, degrading and ill-treatments, and denied to healthcare, legal representation and due process.

The African Commission on Human and Peoples Rights (ACHPR) called for an international, independent, and impartial investigation into allegations of the security forces’ use of excessive and unnecessary lethal force to disperse and suppress peaceful protests in November 2016.

The state of emergency directive gives sweeping powers to the Command Post that has been appointed by the House of Representatives to enforce the decree, including suspending fundamental and non-derogable political and democratic rights granted under the constitution of the country, the African Charter on Human and People Rights and international standards of human rights.

AHRE strongly urges the UN Human Rights Council to address the deteriorating political environment of Ethiopia and the grave violation of fundamental rights. The UN HRC should takes a strong position and urging Ethiopian authority:

  • to lift the ban on basic freedoms and fundamental rights that are enforced by the authorities and Command Post following the declaration of the State of Emergency;
  • to immediately and unconditionally release all political prisoners, journalists, bloggers, human rights activists and opposition leaders;
  • to ensure due process of law for those who were arrested before and during the time of the State of Emergency and to respect basic rights of prisoners,
  • to allow independent and impartial investigation into allegations of gross human rights violations during the enforcement of the state of emergency and since November 2015 when the protest were began.

For further information, please contact:

Yared Hailemariam

Executive Director
yaredh@ahrethio.org,
+32 486 336 367, AHRE, Facebook.

(Photo: Elias Gebru, Anania Sorie and Daniel Shibeshi)

ከቅራኔ ወደ መግባባት (“የት ነበርሽ?”)

$
0
0

ቅራኔ ምንድን ነው? ቅራኔ ለምን ይፈጠራል? እንዴት ይገለፃል? ቅራኔን ለመፍታት መነጋገር ጥቅሙ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎች ከቅራኔ ጋር የተያያዙ ነጥቦች ላይ ለመወያየት እንግዳችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ (Conflict Resolution Expert) ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱ ናቸው።

ዶ/ር ብርሃኑ በኦልድ ዶሚኒዮን ዩኒቨርሲቲ የፐብሊክ አድሚንስትሬሽን ፕሮፌሰር ሲሆኑ፡ የ”መንግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ” ሰብሳቢ ናቸው።

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live