Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

ሉሉ የጃንሆይ ድንክ ውሻ – ምንጭ ፦ የአቶ ጥላሁን ብርሃነስላሴ

$
0
0

ሉሉ!!!!

ሉሉ የጃንሆይ ድንክ ውሻ ነበረች ፤ ይቺ ድንክ ውሻ አቶ ጀማነህ አላብሰው ተማሪ በነበሩበት ጊዜ በ1942 ዓ.ም ለጃንሆይ ያበረከቷት ነች ።በተበረከተችበት ጊዜ ጃንሆይ ስሟ ማነው ብለው ቢጠይቁ ግለሰቡ ያልተዘጋጁበት ጉዳይ ስለነበር አፋቸው ላይ እንደመጣ ” ሉሉ ነው” ብለው መለሱላቸው ።ከዚህ ወቅት አንስቶ የውሻዋ ስም ሉሉ ሆኖ ቀረ ።

ይህች ድንክ ውሻ የተለየችና አቶ ጀማነህ ከየት አምጥተው እንዳሰደጔት በእርግጥ የሚያውቅ ሰው አልተገኘም ። ይሁንና የነቃችና ብልህ ውሻ ስለነበረች ለብዙ ጊዜ ሉሉን ከውጭ ሀገር ጉብኝታቸው ጭምር ሣያስቀድሙ ንጉሰ ነገስቱ አይሄዱም ነበር ። ጃንሆይ ሉሉን ሳያስከትሉ የሚሄዱበት ቦታ ቤተክርስቲያን ብቻ ነበር ።ጃንሆይ አውስትራሊያን ለመጉብኘት ሲሄዱ የሀገሩ ህግ እንሰሳ እንዲገባ ስለማይፈቅድ ሉሉ ልትገባ ባለመቻልዋ አንድ የቤተመንግስት ባለሥልጣን ሉሉን ይዞ ወደሚቀጥለው የጉብኝት ሀገር ደቡብ ኮሪያ ሄዳ ጃንሆይ እዛ ሲደርሱ አስረክቧል ።

ጃንሆይ ከአውሮፓላን ከመውረዳቸው በፊት ሉሉ ትወርድና የራሷን ጉብኝት ታደርጋለች ።ውድድር ለመመልከት ወደ ስታዲየም ሲመጡ ቀጥ ብላ ኳስ ሜዳ መካከሉ ትሄድና ተመልሣ እስራቸው ትተኛለች ። በተለይ በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል በ 1954 ዓ.ም በተደረገው በ3ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ግጥሚያ ዕለት ሜዳው ውስጥ ገብታ እንዲያውም ጉል መግቢያው ድረስ መመለሷን እንደ ትልቅ ነገር የሚያወሱ ሰዋች አሉ ፤ይህንን ሁሉ የሚመለከት ሰው ይህች ውሻ ነገር ያላት ናት እያለ ይናገራል ።

Azeb Ataro saved to Ethiopia: Hagere

ሉሉን የሚወዷት ሰዋች የመኖራቸውን ያህል የሚጠሏትም ብዙዋች ነበሩ ፤ በተለይ የዮኒቨርቲቱ ተማሪዎች ጃንሆይ ለምርቃት በዓል ሲመጡ የእሷ አብሮ መምጣት አይጥማቸውም ነበር።እሷም ከመካከላቸው እየገባች ታነፈንፍ ስለነበር አንድ አመት ላይ አንድ ምሩቅ ሰው ረገጣትና ጮህች ፤ በዚህ ጊዜ አጃቢዎች ረጋጩን ተማሪ ለመለየት ብዙ ቢሞክሩም ሌሎች ተማሪዎች ስለሸፈኑለት ተማሪው ሳይለይ ነገሩ እንዲሁ በቅሬታ ታለፈ፤ ” ባለቤቱን ካልናቁ ውሻውን አይነኩም ” እንደሚባለው ጃንሆይን ካልናቁ ወይም ካልጠሉ ውሻውን አይነኩም በሚል ውሻዎን ሁሉ ሰው ያከብር ነበር።

አንድ ጊዜ ኮረኔል ተክሉ ገብሩ ሻምበል በነበሩበት ወቅት ተግባረዕድ ትምህርት ቤት የራዲዮ ኮሙኒኬሽን ትምህርት ሲማሩ ጃንሄይ ትምህርት ቤቱን ለመጉብኘት ሲመጡ መኮንኑ እግር ስር ሉሉ መጥታ ስላስቸገረቻቸውና ጃንሆይም በቅርቡ ስለነበር ውሻዋን ” ወይጅ ” ማለት ስለፈሩ “ወይዱ” ስላሉ ጔደኛቻቸው ” ወይዱ ” የሚል ቅፅል ስም ሰጥተዋቸው ነበር ።
ሉሉ የወር ደሞዝ ተቆርጦላት በወር የአንድ ሻምበል ደምወዝ ብር 175 ታገኝ እንደነበር የታወቀው ጀነራል መንግስቱ ነዋይ ለገሃር በነበረው የጦር ካምፕ እስር ላይ በነበሩበት ወቅት ለአንድ ሻንበል ” እኔ እዚህ ችግር ላይ የገባሁት ያንተን ደምወዝ ከአንድ የውሻ ደሞዝ እንዲሻል ለማረግ ብዬ ነበር ” ብለው በመናገራቸው ነበር ።

ሞት አይቀርምና ሉሉ ስትሞት ቤተመንግስት ውስጥ ተቀብራ መቃብሯም በእብነበረድ ስለተሰራ ጃንሆይ ከተወቀሱበት ነገር አንዱ ሆኗል ።

ምንጭ ፦ የአቶ ጥላሁን ብርሃነስላሴ ” የ20ኛው ክፍለዘመን ኢትዮጲያ ” የተሰኘው መጽሀፍ


ከዐድዋ እና ከማይጨዉ ጦርነቶችና ድሎች ምን እንማራለን? መማር ከቻልን – ከበቀለ ገሠሠ (ዶ/ር)

$
0
0

፩ኛ/  መንደርደሪያ፤

የአድዋ ጦርነት ድላችን ከፍተኛ ክብርና ኩራት ያጎናፀፈን ከመሆኑም በላይ ለዓለም ጭቁኖች በሙሉ የነፃነት ትግሎች ከፍተኛ ምሣሌ ጥሎ ያለፈ ተዓምራዊ ክንዋኔ ነበር። የማይጨዉም እልህ አስጨራሽ ትግልና ነፃነት እንደዚሁ። ጣሊያ እኮ በሁለቱም ጦርነቶች ወደአገራችን የዘመተችዉ የራሷን ጥቅም ለማስፋፋት ነበር። ይሄን ደግሞ የተማረችዉ ከርሷ በፊት የአፍሪቃን፤ የኢስያን፣  የፓሲፊክንና የአሜሪካን አገሮች ከተቀራመቱት እንግሊዞች፤ ጀርመኖች፤ እስፓኛዎችና ፖርቹጋሎች በመማር ነበር። የቤርሊን ጉባኤ በመባል በሚታወቀዉ ሴይጣናዊ ስምምነት ላይ የተደረሰ ዉሳኔ በመሆኑ ጣሊያም እንዳበደች ዉሻ እያለከለከች ወደ እኛ አገር ያቀናችዉ ድርሻዋን ልትቀራምት ነበር። በዓለም ላይ ይሄን ቅርምት ያልፈቀደች፤ ያልተበገረችና ነፃነቷን ጠብቃ እስካሁን የቆየችዋ አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት።

የአድዋ ድል ለኢትዮጵያ ነፃነትና ኩራት ብቻ ሳይሆን ሌሎቹም የሦስተኛዉ ዓለም አገሮች የኢትዮጵያን ፈለግ በመከተል ለነፃነታቸዉ እንዲታገሉ ሞራል በመስጠት ሕያዉ ምሣሌ ሆኖ ለዘለዓለም የሚኖር ብቸኛ ታሪክ ነዉ። ኢትዮጵያ በነዚያ ጀግኖች አያቶቻችን ስትኮራ ለዘለዓለም ትኖራለች።

ዛሬ አልሞትንም እያልን እራሳችንን እያታለልን በደመ ነፍስ የምንንቀሳቀስ የቁም ማዉታን ግን በነዚያ አርበኞች አያቶቻችንና ቅድመ አያቶቻችን ጀግንነት ደምና አጥንት በተገኙት ድሎች ከመኩራራት ባሻገር ዛሬ በአብዛኛዉ ተመሳሳይ አስተዋጽኦ ስናደርግ አንታይም። የቀደሙት አያቶቻችን በዘር፤ በጎሣ፤ በዕድሜና በጾታ ሳይከፋፈሉ በዐራቱም ማዕዘኖች በተባበረና በተቀናጀ መልክ የአገራቸዉን ነፃነትና የህዝባቸዉን ደህንነት ያስከብሩ ነበር፤ የአሁኖቹ ደግሞ የዉጪ ጠላቶቻችንን እየጋበዙ ድምበሮቻችንና መሬቶቻችንን ይቸበችቡላቸዋል፤ ይሰጧቸዋል። ህዝባችን ግን ዛሬ በገዛ አገሩም ሆነ በስደት ላይ እንደሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠረ በምን ዓይነት ባርነት፤ መከራና ሰቆቃ ላይ እንደሚገኝ የማያዉቅ ዜጋ ይኖራል ብዬ አልገምትም። ዛሬ ካለፉት ታሪኮች መማር የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ ነዉ፤ በጣም ያሳዝናል። ካለፉት ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችን መማር ካልቻልን ወይም ካልፈለግን ሰዎች አይደለንም፤ ከእንስሳትም በታች እንሆናለን። እንስሳት እንኳን ተመክሮአቸዉንና አካባቢያቸዉን ደህና አድርገዉ ይጠቀሙበታል፤ ለመኖር ያህል።

፪ኛ/ ከዐድዋ ጦርነትና ድል ምን እንማራለን?

ጣሊያን በፈረንጆች አቆጣጠር በ1885 ዓ/ም አካባቢ በምፅዋ ላይ መደራጀት ጀመረች። ከዚያም ቀስ በቀስ ወደ ምዕራብ እየገፋች ባህር ነጋሲ በመባል የሚታወቀዉን ሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል ይዛ ‘ኤርትራ’ የሚል ስም በመስጠት ሰፈረችበት። በዚያን ጊዜ የትግራይ ገዥ ራስ መንገሻ ነበሩ። ዐፄ ዮሃንስ በመተማ ጦርነት ላይ ከተገደሉ በኋላ የመንገሥ ፍላጎት ስለነበራቸዉና ለዚህም የጣሊያኖችን ድጋፍ ይሹ ስለነበር በመጀመሪያ ከዐፄ ምኒልክ ጋር ተባብረዉ ጣሊያንን ከሰሜኑ ክፍል ለማባረር ፍላጎት እንዳልነበራቸዉ ታሪክ ይናገራል። ደጃዝማች ባህታ ሃጎስ ከአከለጉዛይ ተነስተዉ ጣሊያኖችን ለመዉጋት ገጥመመዉ ሲገደሉ ከራስ መንገሻ በኩል ምንም ድጋፍ እንዳልነበራቸዉ ይነገራል። ከመጀመሪያዉ ተደጋግፈዉ  አብረዉ ቢሰለፉ ኖሮ ጣሊያ በይበልጥ ተደራጅታ ወደ ደቡብ በቀላሉ ለመዝለቅ ባልቻለች ነበር።

ዳሩ ግን ጣሊያ በትግራይ በኩል እየገፋች ወደደቡብ የመጣችበቱ ዓላማ ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ለመያዝ እንደሆነ ሲረዱ ራስ መንገሻ ገስግሰዉ ሄደዉ ድንጋይ ተሸክመዉ ዐፄ መኒልክ ፊት በመቅረብ ይቅርታ ጠይቀዉ እጎናቸዉ ተሰለፍ።

በዐፄ መኒልክና በጣሊያ ምንግሥት መካከል ዉጫሌ በመባል የሚታወቀዉ ‘የወዳጅነት’ ስምምነት በፈረንጆች አቆጣጠር በ1889 ዓ/ም ተፈርሞ ነበር። የዚህ ስምምነት አንቀጽ 17 እንነደሚለዉ ንጉሠ ነገሥቱ (ማለት ዐፄ መኒልክ) ከፈለጉ ከዉጪ አገሮች ጋር ስለሚኖራቸዉ ግንኙነት  በጣሊያን መሥሪያ ቤቶች ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ነበር። ጣሊያኖቹ ግን ሁን ብለዉ ይሄን ስምምነት በማጣመም ኢትዮጵያ የዉጪ ግንኙነቶችን በሙሉ በጣሊያ ባለሥልጣኖች በኩል እንድታደረግ ትገደዳለች ብለዉ ቁጭ አሉ። በዚህ መልክ ነበር እንግዲህ የአድዋ ጦርነት የተጀመረዉ።

የዐፄ ምኒልክ አዋጅ ተነገረ፤ ልብ የሚነካ ነበር። መልእክታቸዉ አጭር ነበር፤ አገር የሚያጠፋና ሃይማኖት የሚለዉጥ ጠላት ስለመምጣቱና በእግዚአብሔር ረዳትነት አገራቸዉን አሳልፈዉ እንደማይሰጡ በመግለፅ ጉልበት ያለዉ በጉልበቱ፤ ጉልበት የሌለዉ ደግሞ በሃዘንና በፀሎት እንዲረዳቸዉ ተማፀኑ።

በዚህም ጥሪ መሠረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዐራቱም ማዕዘናት ተንቀሳቀሰ። የመሃል አገሩ ሕዝብ በርሳቸዉ ሥር ተሰለፈ። የስሜን ጦር በእቴጌ ጣይቱ ሥር፤ የጎጃም ጦር በንጉሥ ተክለ ኃይማኖት ሥር፤ የሃረር ጦር በራስ መኮንን ወ/ሚካዔል ጉዲሣ (የ/ቀ/ ኃይለ ሥላሴ አባት) ሥር፤ የትግራይና የሃማሴን ጦር በራስ መንገሻና (የዐፄ ዮሃንስ ወንድም ልጅ) በራስ አሉላ ሥር ሲሰለፍ የወሎ ጦር በራስ ሚካኤል ሥር ነበር። ጣሊያን ዘመናዊ መሣሪያ ይዛ ስትመጣ የእኛዎቹ ግን ታቦት ይዘዉ በፊሉቤር፤ በጥቂት ጠብመንጃዎች፤ በእጅ ጦርና ጋሻ ብቻ ነበር የገጠሙት። ፈረስ የነበረዉ በፈረሱ፤ የሌለዉ ደግሞ በእግሩ ነበር የዘመተዉ።

ቸሩ እግዚአብሔር ይመስገን ድሉ ለአርበኞቻችን ሆነ። ሶላቶዎች ቅስማቸዉ ተሰበረ። የነጫጭባዉ ዓለም በሙሉ በከባድ ትካዜ ዉስጥ ወደቀ። በአዎሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩት ነጮች የጣሊያንን ክፉኛ መቸነፍ ማመንም ሲያቅታቸዉ ጊዜ ኢትዮጵያኖች እኮ ጥቁሮች አይደሉም፤ ከኛ ርቀዉ የሚኖሩ ነጮች ናቸዉ እስከማለት ደርሰዉ ነበር። ጣሊያን በአፍሪቃ ጥቁር አገር መቸነፏን ላለመቀበል።

፫ና/  ከማይጨዉ ጦርነትና ድል ምን እንማራለን?

የላይኛዉን ጦርነት ታሪኮች የሰማሁት ከትምህርት ቤቶችና ከጽሑፎች ሲሆን ስለማይጨዉ ጦርነት ግን ከአርበኛዉ አባቴ አፍ ጭምር ነበር፤ በወጣትነቱ ጦርነቱ ዉስጥ የገባ አርበኛና  የዐይን ምስክር ነበርና።

ጣሊያ በአድዋ ከተቸነፈች ቀን ጀምሮ አርፋ አልተኛችም፤ ወራሪ ጓደኞችዋም ጭምር። ስለዚህ ለ40 ዓመታት ሙሉ ዝግጅት አድርጋ ልትወርረንና ቂሟን ልትበቀል ተመልሳ መጣች። ወገኖቻችን እንደገና በተለመደዉ ህብረታቸዉ ዘመቱ። ጀግናዉና አርበኛዉ አባቴ እንዳስተማረኝ፤ አሁንስ ዓላማቸዉ አቸንፈዉ ከአገር ማባረር ብቻ ሳይሆን እስከ ሮማ ድረስ ተከትሎ በመሄድ ጥሩ ትምህርት ለመስጠት ጭምር እንደነበረ ነዉ። በእዉነትም ወደ መጀመሪያዉ ላይ  ጥልቅ ጉዳት አድርሰን ነበር። የአድዋ ሽንፈቷ እንዳይደገም  ክፉኛ ተጨነቀች። የደረሰባትን ከባድ ጉዳት ለፋሺስቱ መሪ ለሙሶሎኒ አስታወቀች። ከቫቲካን ጭምር የሮማ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የገንዘብ መዋጮ አደረገ፤ ሴቶቹ እስከጋብቻ ቀለበታቸዉ ድረስ።

ከአንደኛዉ የዓለም ጦርነት በኋላ የተከለከለዉን የመርዝ ጪስ ከጦር አይሮፕላኖች ላይ ረጨችብን። ቤቶች ተቃጠሉ፤ ከብቶች አለቁ፤ የአርበኞቻችን ዐይኖች ተቃጠሉ። ጉዳዩን ለማመንም አስቸጋሪ ነበር። ለጊዜዉ ማፈግፈጉ የግድ ሆነ።

ታሪኩ ረዥምና እልህ አስጨራሽ በመሆኑ አሳጥረዋለሁ። ንጉሣችን (ቀ/ኃ/ሥ)  ለሊግ ኦፍ ኔሽን ሊያመለክቱ ወደ ዠኔቫ ሄዱ። አፍንጫ ሲመታ ዐይን ያለቅሳል እንዲሉ የአዉሮፓ መሪዎች በሙሉ ለጣሊያን አዳሉ፤ በኛ ላይ አፌዙ። ንጉሣችን ተስፋ ቆርጠዉ በዚያዉ ወደ እንግሊዝ አገር አቀኑ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን እንደገና በጦር መሪዎችና በጎበዝ አለቆች ሥር እተደራጀ ለ5 ዓመታት ያላሰለሰ ትግል በማካሄድ ጣሊያኖችን ዕረፍት አሳጣቸዉ።

አርበኞቻችን ለነፃነታችንና ለክብራችን ደማቸዉን ሲያፈሱና አጥንታቸዉን ሲከሰክሱ ባንዳዎች ግን ለሆዳቸዉ በማደር ጣሊያኖችን እያገለገሉ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸዉ የሚረሳ ታሪክ አይደለም። ያ ሁሉ አለፈና ጣሊያም እንደገና ተደመሰሰች፤ አገራችንን በቅኝ ሳትይዝ እንደባነነች መጥታ እንደባነነች በሃፍረትና በቅሌት ወደ አገሯ ተመለሰች። እግዚአብሔር ይመስገን።

፬ኛ/ ጥፋቶቻችንን አምነን ንሥሐ ገብተን ወደፊት ልንራመድ እንችላለን?

ሁል ጊዜ ዉድ አገራችንን በይበልጥ የሚያሰቃዩት የዉጪ ጠላቶች ሳይሆኑ የዉስጥ ባንዳዎች ናቸዉ። ይሄም በጣሊያን ወረራዎች ዘመናት ታይተዋል፤ በደርግ አስተዳደር ዘመን ዐይተናል፤ ዛሬም በወያኔ/ኢሕአደግ ሥር እየተመለከትን ነዉ። ‘ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ’ የተባለዉ ለዚህ ነበር።

ሞት ላይቀር ነገር ብኩኖች ይስገበገባሉ። በልተዉ የሚጠግቡ አይመስላቸዉም፤ ለሺህ ዓመታት የሚኖሩ ይመስላቸዋል፤ ግብዞች።

ዛሬ ዉድ አገራችን በከባድ ጣጣ ዉስጥ ትገኛለች። ማንነታቸዉን ያጡ ወገኖች በተለይ በአማራዉ ነገድ አካባቢ ይታያሉ። የአማራዉ፡ የኦሮሞዉ፤ የጋምቤላዉ፤ የደቡቡ ሆነ የአፋር ሕዝባችን መሬቱን እየተነጠቀና እተፈናቀለ ይገኛል፡ ይታሰራል፤ ይገደላል፤ በገፍ ይሰደዳል።

የወያኔ/ኢሕአደግ አንቀጽ 39 ሥራዉን እየሠራ ነዉ። በአንድነት ምትክ ክፍፍሉ እየሰፋ ይታያል። ቻርተሩ ሲረቀቅ ሆነ የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ሲረቀቅ ከወያኔ ጎን በመሆን ድጋፍ የሰጡ ተለጣፊዎች ነበሩ።

አሥራ አምስት ተቃዋሚ ድርጅቶችን ያቀፈዉን ታላቁን ህብረት አፈረሱ። ድርጅቶች ፈለፈሉ። ገለልተኛ ታዛቢዎችና ነፃ የምርጫ ቦርድ ሳይኖር ምርጫ ዉስጥ መግባቱን እንዳታስቡት እያለ ሕዝቡ በነቂስ እያስጠነቀቃቸዉ ዘልለዉ ምርጫ ዉስጥ ገቡ። ከዚያ ምን ሆነ? ሁሉም የሚያቀዉ መሳቂያ ሆነዉ ቀሩ። ዛሬ በፓርላማ ተብዬዉ ዉስጥ አንድም ተቃዋሚ ድርጅት የለም። ይሄ ነዉ ዲሞክራሲ? ይሄ ነዉ ሰላም? ይሄ ነዉ እድገት?

ካለፉት ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችን መማር ከፈለግን አሁንም የዉድ አገራችንን ህልዉናና የመላዉን ሕዝባችንን ደህንነት ልናስጠብቅ እንችላለን። ዛሬም እንደገና አዳዲስ ፋሺስቶች እያንጃበቡብን ናቸዉ፤ አንዳንዶቹም ጠልቀዉ ገብተዋል፤ መሪታችንን ሊቀራመቱ፤ ህዝባችንን ሊከፋፍሉ፤ ኦርቶዶክስን ሊሰብሩ፤ ሙስሊሞችን ሊረግጡና ዉድ አገራችንን ሊያፈርሱ። የኢትዮጵያ መሬት የኢትዮጵያዉያን እንጂ የሱዳንም፤ የግብፅም፤ የቻይናም፤ የህንድም፤ የፓኪስታንም፤ የሳዑዲም ሆነ የቱርክ አይደለም፤ መሆንም የለበትም።

መፍትሔዉ ቀላል ነዉ። ከቀደሙት ጀግኖች፤ ቅዱሳንና ሰማዕታት እንማር። ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲያድርብን እንሞክር። ራስ ወዳድነትንና ሆድ አደርነትን እንቀንስ። ለአገር አንድነትና ነፃነት በህብረት እንፀለይ፤  እንታገል፤ ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን ያቺን የተረከብናትን ቆንጆ አገር እናዉርስ። አንዳንድ የዉስጥ ልዩነቶች እንኳን ቢኖሩን መጀመሪያ አገራችንን ከዉድቀት ካወጣናት በኋላ ዲሞክራሲያዊና ስልጡን በሆነ መልክ ተወያይተን መፍትሔ ልናገኝ የማንችልበት ምክንያት አይኖርም። በተለይ ባለፉት 40 ዓመታት ብዙ መቶ ሺህ ሕዝባችን (በተለይ ለጋ ወጣቶች) ለዲሞክራሲና ለእኩልነት ሲሉ ተቀጥቅጠዋል፤ ተሰቃይተዋል፤ ተገድለዋል፤ ተሰደናል። እስቲ አሁንም ለዲሞክራሲ ግንባታ አንድ ላይ ሆነን እንታገል። በዲሞክራሲ ጎዳና የሕዝባችን እኩልነት ከተጠበቀ፤ ሰላምና እርጋታ ከሰፈነ፤ የኢኮኖሚ እድገት ከታየና የአገሪቷ መዋዕለ ንዋይ ፍትሃዊና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ከተከፋፈለ ዋናዉ ችግራችን ተወገደ ማለት ነዉ። ከዚያ በላይ ያለዉ ቅንጦት ወይም ህልም ይመስለኛል።

ስማኝ ተዉ ስማኝ ሀገሬ፤ አንድነት ይበጀናል ዛሬ

ቸሩ ፈጣሪያችን የአገራችንን አንድነትና የሕዝባችንን ደህንነት ለዘለዓለሙ ይጠብቅልን፤ አሜን።

 

 

ሕወሃቶች ድርድሩ እንዲከሽፍ ዉስጥ ዉስጡን እየሰሩ ነው #ግርማ_ካሳ

$
0
0

ሕወሃቶች

ገዢው ፓርቲ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመደራደር ዝግጅት ላይ እንዳለ ይታወቃል። ወደ 21 የሚሆኑ ተቃዋሚዎች ናቸው ቢባል አብዛኞቹ ፣ መሪዎቻቸው የምርጫ ቦርድ ስርተፊኬት በኪሳቸው ይዘው የሚዞሩ ናቸው። ግብስብስ ድርጅቶች። እንደ አየለ ጫሚሶ፣ ትግስቱ አወሉ የመሳሰሉ።

ሆኖም በአንጻራዊነት በአገሪቷ ተቀባይነት ያላቸው ወይም ጠንካራ የሆኑ እንደ መኢአድ፣ ሰማያዊ፣ መድረክ፣ ኢዴፓ ያሉ ድርጅቶችም አሉ። (ስለዚህ ተቃዋሚዎች በምልበት ዝም ብለው በተቃዋሚ ስም የተቀመጡ ግብስብሶችን ሳይሆን እንደነ ሰማያዊ፣ መኢአድ አይነቶቹን ነው)

እነዚህ ተቃዋሚዎች በቅንነት የአገርን ችግር በዉይይት ለመፍታት ሕዝብን ባይወክሉም የሕዝብን ጥያቄዎች ይዘው ለመቅረብ ነው የተዘጋጁት። የሕሊና እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ፣ የፖለቲክ ምህዳሩ እንዲሰፋ፣ የዴሞክራሲት ተቋማት (ምርጫ ቢርድ፣ ፍርድ ቤት፣ሜዴያን..) ገለልተኛ ሆነው እንዲዋቀሩ ….የመሳሰሉትን።
ይሄ ይደረጋል የተባለው ድርድር በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ እምነት የተጣለበት ስላልሆነ፣ አገዛዙ ለሂደቱ ሕዝብ አመኔታ ይኖረው ዘንድ አንዳንድ ጠቃሚ እርምጃዎችን (እስረኞችን መፍታት የመሳሰሉ) እንዲወስድ ከብዙ ማእዘናት ጥሪ ቀርቦለታል።

ሆኖም ግን አገዛዙ ያን ለማድረግ ፍቃደኛ ሲሆን አይታይም። የመድረክ ከፍተኛ አመራር አባል ዶር መራራ ጉዲና እንኳን ሊፈቱ፣ የፈጠራ አስቂኝ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ዛሬ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል የነበሩት አቶ ነገሰ ተፈረደኝ፣ ወደ ወህኒ በደህንነቶች ታፍነው ተወስደዋል። አቶ ነገሰ የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ምክር ቤት አባል፣ የአንድንት ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ የነበሩ ሲሆን፣ አንድነት ፓርቲ ሰርተፊኬቱን በሕወሃት የፖለቲክ ዉሳኔ ተወስዶበት ሲዘጋ ሰማያዊን በመቀላቀል ሲታገሉ የነበሩ ናቸው።፡ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የፓርቲው ሊቀመንበር የነበሩ ጊዜ አቶ ነገሰ የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን አሁን የብሄራዊ ምክር ቤት አባል ናቸው። በቀድሞ የአንድነት ፓርቲ እንዲሁም አሁን ደግሞ የሰማያዊ አባላትን ዘንድ በጣም የተከበሩና የተወደዱ ሰካማዊ ታጋይ ናቸው።

የነ አቶ ነገሰ ተፈረደኝ በዚህ ወቅት መታሰር፣ የነ ዶር መራራ መከሰስ፣ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ፣ መድረክ ያሉ ከድርድሩ እንዲወጡ ለማድረግ፣ ድርድሩም ከወዲሁ የከሸፈ እንዲሆን ሆን ተብሎ፣ በምንም አይነት ድርድር እንዲኖር በማይፈልጉ፣ ድርድርን እንደ ድክመትና ሽንፈት በሚቆጠሩ ፣ ከልካይና አዛዥ በሌላቸው፣ ለማንም ተጠያቂ ባልሆኑ፣ እንደነ ስብሐት ነጋ ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ሳሞራ የኑስ ባሉ ጥቂት አክራሪ ሕወሃቶች የተቀነባበረ እንደሆነ መገመት አያስቸግረም።

ኢትዮጵያዉያን እስረኞች እንዲፈቱ እየጠየቁ ዘጎች ማሰር አገር እንድትረበሽ፣ በአገር መረጋጋት እንዳይኖር፣ የአገር ችግር በዉይይትህ እንዳይፈታ መፈለግ ነው።

የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ ሊቀመነበር አሁን የምክር ቤት አባል አቶ ነገሠ ተፋረደኝ ታሰሩ !

$
0
0


የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ፤ አሁን ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት ፤ አቶ ነገሠ ተፋረደኝ በማዕከላዊ ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል ።

አቶ ነገሠ በትላንትናው ዕለት ፣ አራዳ ጊዬርጊስ ቤተ የክርስቲያን፣ እብስተ መና ካፊ ውስጥ በደህንነቶች ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አብሯቸው የነበረ የዓይን ምስክር የገለፀ ሲሆን፤ ደህንነቶቹ በተንቀሳቃሽ የእጅ ስልካቸው ፎቶ ግራፍ ካነሳቸው በኋል ፤ ከካፊው ወጥተው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ፣ መንገድ ላይ አስቁመው ይዞቸዋል ። አቶ ነገሠ የታሰሩበት ምክንያት እስካሁን ያልተገለጸ ሲሆን ፣ይህ መረጃ ይፋ እስከ ሆነበት ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ታስረው ይገኛሉ።

‹‹ስለ እኔ አታልቅሱ!›› – ሙሉቀን ተስፋው

$
0
0

የሚፈግ እሳት፤ የማይጠፋ ፋና! አርበኛ ሰማዕት ጎቤ መልኬ (ከ1958 – 2009 ዓ/ም)

ምን ብየ እንደምጀምር አላውቅም፤ ግን እኛ ‹‹ዋዋ›› እያልን ለምንጠራው አባታችን ቤተሰቦቹ ደግሞ ‹ጃውይ› እያሉ በፍቅር ለሚጠሩት የዘመናችን ታላቅ ሰማዕት የ51 ዓመቱ ጎቤ መልኬ መናገር አለበኝ፡፡ አዎ! ማክሰኞ የካቲት 21 ቀን 2009 ዓ.ም ከሕይወቴ እኩይ ቀኖች በቅድሚያ እመድባታለሁ፤ ተደጋግሞ የተደወለ የስልክ ጥሪ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ፤ ከስልኩ የሰማሁት ነገር መንቃቴን መልሼ እንድጠራጠር አደረገኝ፤ ምናለ በሕልሜ በሆነ አልኩ!

የአንዳንድ ሰዎች የወገን ፍቅር ይገርመኛል! ሀብትና ንብረት ግድ የማይሰጣቸው ጥቂት ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ሕይወታቸውን ለወገን አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለእኔ አርበኛው ጎቤ መልኬ እንደዚያ ነው፡፡

ጃውይ ጎቤ መልኬ! የሚፈግ እሳት የማይጠፋ ፋና!
ትውልዱ እንዲህ ነው፡፡ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በጠገዴ ወረዳ አዴት ቊስቋም ከአባቱ አቶ መልኬ ተገኘ ከናቱ ይሳለም ደምለው በ1958 ዓ.ም ተወለደ፡፡ ለዋዋ ሕይወት አልጋ በአልጋ አልነበረችም፡፡ አባቱን በለጋ እድሜው በሞት ተነጠቀ፤ የቤተሰብ ኃላፊነት ገና በ17 ዓመቱ ተጣለበት፤ ግን ኃላፊነቱን የማይወጣ ዋልጌ አልነበረም፤ በድፍን አርማጭሆና ጠገዴ ስሙ የገነነ ገበሬ ሲሆን ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ ጃውይ ፈጣን ንቁ የወገን ያገር መከታ ሁኖ አደገ፡፡ መንጠሩነን መንጥሮ ዳጉሳ ከጅሆላ እያመረተ ከቤተሰብ አልፎ በሰኔ በሐምሌ ድፍን ጠገዴ ከእነርሱ ቤት ሲበላ ሲጠጣ ስሙ ከአጽናፍ አጽፍ ገነነ፡፡

በግብርናው ወደር የሌለው አራሽ አደፋራሽ ሆነ፤ ላሙ ቦራ ቦራ፣ በሬው ዛጎላ፣ እቦሳው ሶራ፣ ፍየሉ ወያይ፣ ማንም ደራሽ የሌለው ስለመሆኑ ዋሕብቴ ጀጀቢት በርሃ ይመስክር! ዋዋ ጎቤ ላገር መከታ ልበሙሉ ዘመን ባመጣው ቴክኖለጅ ቀዳሚ ተራማጅ ብቻም ሳይሆን ተፈላሳሚ ነበር፤ ሳይማር ያወቀ የወንዶች ወንድ፣ ካልነኩት የማይነካ አንበሳ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ጃውይ የተጣላ አስታራቂ፣ የተገፋ ጠያቂ፣ የታሰረ አስፈች፣ የተራበ መጋቢ፣ አግዳሚው አላፊው ዘወትር እንደ አብርሃም ቤት ቤቱ ከእግዳ የማይለየው ጃውይ ጎቤ ነበር፡፡ ጃውይ በአገሩ ሰው እጅግ የተወደደ ወደር የሌለውም ጀግና ነበር፤ በሃይማኖቱ እና በአገሩ ቀልድ የማያውቅ ወደፊት እጅ ወደኋላ የማይል ጀግናዎች መካከል ሰው ቢፈለግ ጎቤ መልኬ ቅድሚ ስሙ አለ፡፡

ጃውይ ማለት ልቡ የማይደነግጥ ደፋር ለወዳጁ ማር ለጠላቱ ኮሶ ነው፤ ዋሽ ከሆነ ድፍን አርማጭሆና ወልቃይት ጠገዴ ይመስክር፡፡ ተቆጥቶ ካያችሁት እንደአንበሳ ያስፈራል፤ ሲጫወት ሲስቅ ደግሞ ርግብ የዋኅ ነሰው ነበር፡፡

በንግዱ በኩል የተዋጣለት ነጋዴም ነበር፡፡ አርማጭሆ ሳንጃ ከተማ መካከል አላፊው አግዳሚው ድራፍት ከወይን ከፍየል ቁርጥ ጋር የሚያወራርድበት ሆቴል ነበረው፡፡ አርማጭሆ ጠገዴ የሚገናኝበት መስከረም ሲጠባ የሰባ ሰንጋ አርዶ የሚዘክርበት ጠላው በገምቦ የሚወርድበት ጥሎሹ ተዘርግቶ ቄስ ከመለኩሴ ዲያቆን ተሞሃይ የሚዘምርበት፣ የጃውይ ማጀቱ ወልወሉ የሚትረፈረፍበት አብልቶ አጥቶ ውሎ የሚያድርበት ጃውይ ቤቱ የእነአብርሃም የሳራ ዘመን ያለን የሚመስልበት ነበር፡፡ ይህን ሁሉ ለሰው ሲነግሩት ተረት ይመስል ይሆናል፤ ግን ከአርማጭሆ ሰው በላይ ምስክር የሚሆን የለም፡፡

ዘመናዊ ትምህርት ቤት አልገባም፤ ግን አስተሳሰቡ ዩንቨርሲቲ ገብተው ዲግሪ በጥሰው ከወጡ ሰዎች በላይ ነው፤ ከማንም በፊት መኪና ገዝቶ ራሱ ያሽከረክርም ነበር፡፡ የነበረው የፍየል ቁጥር በትክክል አይታወቅም፤ ሦስት ያክል መኪናዎችና የባለብዙ ሚሊዮን ብር ባለንብረትም ነበር፡፡ ግን ይህ ሁሉ ለዋዋ ከወገን ፍቅር በላይ አልበለጠበትም፡፡
አርበኛ ጎቤ እንዴት የወያኔ መንግሥት ላይ ነፍጥ ሊያነሳ ቻለ?

የዋዋ እና የወያኔ ጠብ አሁን የተጀመረ አይደለም፤ ከ1983 ዓ.ም በፊትም ይቀድማል፡፡ ወያኔዎች ገና ሥልጣን ሳይዙ በወልቃይትና በጠገዴ አካባቢ በዐማሮች ላይ የሚያደርሱት ጥፋት ያሳስበው ነበር፡፡ አስቦም ዝም አላለም፡፡ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የወያኔ መንግሥት ክልሎችን ሲያዋቅር የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ወደ ትግራይ መከለልን ተቃውሞ ከወንድሞቹ ጋር ነፍጥ አንስቶ ነበር፡፡ በጊዜው በመረጃ እጥረት ሌላው የዐማራ ሕዝብ በአካባቢው የሚሆነውን ባለመዋቁ ምክንያት እንቅስቃሴው ያን ያክል ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም፡፡

ጃውይ ጎቤ መልኬ ከወያኔ ጋር እርቅ ሰላም የሚባል ነገር ኖሮት አያውቅም፤ በ2006/7 በወያኔዎች የማስፋት እቅድ ግጨው አካባቢን አልፈው ለመያዝ ባደረጉት ጦርነት እነ ጎቤ መልኬ ተሳታፊ ብቻም ሳይሆን የጦርነቱ መሪዎች ነበሩ፡፡ አቶ ዓባይ ወልዱ የክልላቸውን የፖሊስ አባላት እስካ አፍንጫቸው አስታጥቀው ሲቪል አልብሰው ነበር ወደ ግጨው የላኳቸው፡፡ የወንዶች ቁና ጎቤ መልኬ ከአርማጭሆና ከጠገዴ ወጣቶች ጋር በመሆን ነበር ከነትጥቃቸው በጫካዎች ውስጥ አመድ ያደረጋቸው፡፡ ወያኔዎች ቀንዳቸውን ተብለው ፖሊሶቹም በጫካዎች ውስጥ ረግፈው ነው እቅዳቸው የተኮላሸው፡፡

የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ብሔርተኛነት የማንነጥ ጥያቄ እዚህ እንዲደርስ ከታገሉት ሰዎች መካከልም ቅድሚያ ከሚጠቀሱት ሰዎች መካከል ጎቤ አለ፡፡ በሕግ አግባብ እንዲያልቅ የሚችለውን አደረገ፤ ወያኔ ግን በኃይል ሊደፍቀው ፈለገ፡፡

ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ/ም ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ እነ አታላይን፣ እነ ጌታቸው አደመን እና ሌሎች የኮሚቴ አባላት ወያኔ ሲያፍን ጎንደር ከተማን ያጨናነቀው የጎቤ ጦር ነበር፡፡ ከብልኮ እስከ አውቶ ፓርኮ ድረስ እስከ አፍንጫው የታጠቀው የጎቤ ጦር ተሰልፎ ሲመለከቱት አጼ ኃይለ ሥላሴ ከስደት መልስ ቤተ መንግሥት ሲገቡ የነበረውን ግርማ ሞገስ የተላበሰ ትርኢት ይመስል ነበር፡፡ በዚህ ቀን ጎቤ አንድ ትልቅ ንግግር አደረገ፡፡ ‹‹ብአዴን የሕወሓትን የበላይነት ጥሎ ለሕዝብ ከቆመ መልካም፤ ካልሆነ ግን እኛ የምናደርገውን እናውቃለን›› አለ ጎቤ፡፡
ለቃሉ ሟቹ ጎቤ የተናገረውን በተግባር ነው ያሳየው፡፡ ጎቤ ከዚያን ቀን በኋላ በአርማጭሆና በቆላ ወገራ ያደረጋቸው የጦር ሜዳ ውሎዎች በሌላ ክፍል እመለስባቸዋለሁ፡፡
እንግዲህ የካቲት 21 ቀን 2009 ዓ.ም በጠዋት የዚህ ጀግና መስዋት መሆን ነበር የሰማሁት፡፡ እንደሰማሁ ዝም አላልኩም፤ ደጋግሜ ከወንድሞቼ ጋር ተነጋገርንበት፡፡ ጀግናው ሞቷል፤ ግን ደግሞ ጀግናው አለ፡፡ ማክሰኞ ዕለት ብቻ እስከ አንድ ሺህ የሚደርስ ጎቤን በተመለከተ በሕይወት ስለመኖሩ እንደነግራቸው ጠየቁኝ፡፡ ምን ብየ ልመልስላቸው? ወንዱ ሞተ ልበል?
ዋዋ እኮ በአካሉ የሞተው ገና ያን ሁሉ ሀብት ንብረት ጥሎ ጫካ የገባ ዕለት ነው፤ ግን ጀግንነቱ እንደ ዓድዋ ጀግኖች በዘመን ሁሉ ሲታወስ እንደሚኖር ግልጽ ነው፡፡ አንዳንዶች ስለሞቱ ብዙ ጻፉ፤ ብዙም አለቀሱ፡፡ ዋዋን አሁን አግኝቼ ብጠይቀው ‹‹ስለ እኔ አታልቅሱ›› እንደሚለኝ አልጠራጠርም፡፡ የእርሱ ፍቅር እኮ ሕይወትን አሳልፎ እስከ መስጠት ነው፡፡
የጎቤ ታላቅነት በጀግንነቱ ብቻ የተገደበ አልነበረም፡፡ የአንድ መሪ ታላቅነት የሚለካው ተተኪ መፍጠር ሲችል ነው፡፡ በዚህ ጎቤ የሚታማ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ብቻ አይደለም፤ ብዙ ጎቤዎች ተፈጥረዋል፡፡
በመጨረሻም በጎቤ የቅርብ ዘመድ ናትናኤል ሞላ የተገጠመ የሚከተለውን ግጥም በማስከተል ለጊዜው ጽሑፌን ልጨርስ፡፡
ወልቃይት ጠገዴ የሚወለደው፡
ጪልቋና አርማጪሆ የሚወለደው
ያባ ደፋር ልጅ አገር ያወቀው!
ያባደፋር ልጅ ጃዊ ሚሉት!
ባለ መኪና ባለ ጥገት፡
ትውልዱ አመራ ትውልዱ አዴት፡፡
አረ ዋዋየን የነካው ማነው?
ያገሬ ኩራት መመኪያችን ነው!
ታንክ መትረጊሥ የማይበግረው፡
ባንዳ ወያኔ ፈርቶት ሚኖረው፡
ላገር ነፃነት ጫካ የሄደው!
ያለ ነፃነት ሀብት ምን አለው?
ቆራጡ ጀግና ዋዋ ነው ያለው!
ምኑን አውርቸ ምኑን ልተወው፡
ድንበር ጠባቂ ያገር ኩራት ነው!
የከብቱን ብዛት ያየ ይናገር!
የበጉን ብዛት ያየ ይናገር!
የመኪናውን ያየ ይናገር!
የጠገዴው ወንድ የናጅሬ ዘር
ይቅርብኝ ብሎ ገባ ወደዱር፡፡
ሊሠርቅ አይደለም ሊቀማ አይደለም!
የነ ሥጦታው የናይቶ ወንድም!
መልመጥመጥና መፍራት አይወድም!

(ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው የአርበኛ ሰማዕት ጎቤ መልኬ የቅርብ ዘመድ ናትናኤል ሞላ በሰጠን መረጃ መሠረት ነው፤ እናመሰግናለ፡፡ የጎቤን የጦር ሜዳ ጀብዱዎች በቀጣይ እናቀርባለን)፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን ይቅርታ ልትጠየቅ እንደሚገባ ተገለጸ – በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው

$
0
0

በዐድዋ ጦርነት ጊዜ በአገሩ ላይ የደረሰውን ሽንፈት ለመበቀል ሲል የኢጣልያ ፋሽስት መንግሥት በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትና አድባራት ላይ ላደረሰው ቃጠሎ፤ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአባቶች ቀሳውስት፣ ዲያቆናትና መነኮሳት እንደዚሁም በምእመናን ላይ በግፍ ላደረሰው ጭፍጨፋ የጣልያን መንግሥት እና የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያን ይቅርታ መጠየቅ፤ የኢጣልያ ፋሽስት መንግሥት ከየገዳማቱና አድባራቱ የዘረፋቸውን ንዋያተ ቅድሳት፣ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍትን እና አገራዊ ቅርሶቻችንንም ለኢትዮጵያ መመለስ እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

የጥናቱ አቅራቢዎች እና የጥናቱ አወያይ

ይህ ሐሳብ የተገለጸው በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል አዘጋጅነት የማኅበሩ አባላት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአጠቃላይ በርከት ያሉ ምእመናንና ምእመናት በታደሙበት በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል አዳራሽ የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም በተካሔደው የጥናት መርሐ ግብር ላይ ሲኾን፣ በዕለቱ ‹‹በኢትዮጵያ ላይ የፋሽስት ኢጣልያ ወረራ እና የሮሙ ፖፕ ፒዮስ ፲፩ኛ አቋም›› እና ‹‹ቅኔ ዘዝክረ ዐድዋ›› በሚሉ አርእስት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል፤ በጥናቶቹ ዙሪያ ከታዳሚዎች ለተነሡ ጥያቄዎችም በጥናት አቅራቢዎቹ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

img_0723

የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ አባቶች እና ወንድሞች በከፊል

‹‹በኢትዮጵያ ላይ የፋሽስት ኢጣልያ ወረራ እና የሮሙ ፖፕ ፒዮስ ፲፩ኛ አቋም›› የሚለው ርእሰ ጉዳይ አቅራቢ ቀሲስ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገብረ አማኑኤል ፋሽስት ኢጣልያ አገራችን ኢትዮጵያን በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም በወረረበት ወቅት የጊዜው የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ወረራውን እና በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመውን ግፍ በዝምታ መመልከታቸው ተገቢ አለመኾኑን አስታውሰው ፖፑ ወረራውን ሊያወግዙ ያልቻሉበት ምክንያትም፡- በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና በኢጣልያ መንግሥት መካከል ጥላቻ እንዳይፈጠር በመስጋታቸው፤ በዘመኑ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና በካህናቱ መካከል ከባድ ተቃውሞ ስለነበር በመካከላቸው ግጭት እንዳይፈጠር በማሰባቸው እንደኾነና ዋነኛው ምክንያት ግን የኢጣልያ ኢትዮጵያን መውረር የካቶሊክ ሃይማኖትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት መልካም ዕድል ይፈጥራል ብለው በማመናቸው እንደኾነ በጥናታቸው አትተዋል፡፡

img_0729

ቀሲስ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገብረ አማኑኤል

ቀሲስ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ አያይዘውም ፖፑ የወቅቱ የኢጣልያ ፋሽስት መንግሥት ‹‹በእግዚአብሔር ፈቃድ የተነሣ፣ በሊበራሊዝም አስተሳሰብ ያልተሞኘ መንግሥት ነው›› ብለው ያምኑ እንደነበር፤ በወቅቱ ስለወረራው ሲጠየቁ ለሚድያዎች የሰጡት ምላሽም ፖፑ ለጦርነቱ የነበራቸውን ጥሩ አቋም እንደሚያመለክት፣ ለአብነትም በአንድ ወቅት ‹‹ራስን የመከላከል ጦርነት ነው›› ሲሉ ስለ ወረራው አስፈላጊነት እንደተናገሩ፤ የአገሪቱ መንግሥት ኢትዮጵያን ሊወርር ሲዘጋጅ ሙሶሎኒ በሮም ከተማ ንግግር በሚያደርግበት ጊዜ መላው የሮም ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ደወሎች ለረጅም ሰዓት ሲደወሉ እንደነበር፤ ይህም የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያ በኢጣልያ እንድትወረር የነበራትን ፍላጎት እንደሚያመለክት ባለጥናቱ ጠቁመዋል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወረራውን በገንዘብ ደግፋለች ተብላ ቤተ ክርስቲያኗ ተከሳ እንደነበር ያወሱት ቀሲስ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ፣ ፋሽስት ኢጣልያ ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላም ‹‹እጅግ የሚያስደስት ድል›› በማለት ፖፕ ፒዮስ ፲፩ኛ ጦርነቱን ማድነቃቸው ፖፑ የፋሽስት መንግሥት እና የወረራው ደጋፊ እንደነበሩ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ ልዩ ልዩ ምንጮችን ዋቢ አድርገው የፖፑን አቋም ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡

img_0724

የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ እናቶች እና እኅቶች በከፊል

የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለፋሽስቱ ሠራዊት በስውር የሞራል ድጋፍ ከማድረጓ ባሻገር የኢጣልያ ፋሽስት መንግሥት በየጊዜው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አድባራትና ገዳማት ላይ ቃጠሎና የቅርስ ዘረፋ ሲያካሒድ፤ እንደዚሁም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን እና ብፁዕ አቡነ ሚካኤልን በግፍ ሲረሽን፤ በአባቶች ቀሳውስት፣ ዲያቆናትና ምእመናን ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ሲፈጽም በዝምታ መመልከቷ (ድርጊቱን አለማውገዟ) የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የወረራው ደጋፊ እንደነበረች የሚያስገነዝብ ሌላኛው ነጥብ መኾኑን በመጥቀስ ለዚህ ዅሉ በደልም የጣልያን መንግሥት እና የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅና ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ ካሣ መክፈል፤ ከየገዳማቱና አድባራቱ የተዘረፉ ንዋያተ ቅድሳትን፣ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍትን እና አገራዊ ቅርሶቻችንንም ለአገራችን መመለስ እንደሚገባቸው ቀሲስ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ሐሳብ መሳካትም የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች እና መላው ሕዝበ ክርስቲያን ድጋፍ እንዲያደርጉ በማሳሰብ ቀሲስ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ጥናታዊ ጽሑፋቸውን አጠቃለዋል፡፡

img_0735

ቀሲስ ኃይለ ኢየሱስ አለባቸው

‹‹ቅኔ ዘዝክረ ዐድዋ›› የሚለው ጥናታዊ ጽሑፍ አቅራቢ ቀሲስ ኃይለ ኢየሱስ አለባቸው ደግሞ ከአድዋ ጦርነት በፊት፣ በጦርነቱ ወቅት እና ከድሉ በኋላ የተደረጉ አንዳንድ የግእዝ ቅኔያትን ትርጕምና ምሥጢር ከታሪክ መጻሕፍት ጋር አነጻጽረው በማቅረብ በቅኔአቸው ንጉሡንና ሠራዊቱን በማበረታታት ለአገራችን ድል ማግኘት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋጽዖ በጥናታቸው አመላክተዋል፡፡

በመጨረሻም በጥናታዊ ጽሑፎቹ ላይ ውይይት ከተደረገ እና ከመርሐ ግብሩ ታዳሚዎች ለተነሡ ጥያቄዎች በጥናት አቅራቢዎቹ ምላሽ ከተሰጠ በኋላ መርሐ ግብሩ በአባቶች ጸሎት ተፈጽሟል፡፡

የተከሰሰው መረራ ብቻውን ነው! አታምታቱ ጀዋርና ብርሀኑ የሉበትም! – ሰርፀ ደስታ

$
0
0

ሰሞኑን የወያኔ ቡድን ኢትዮጵያዊውን እውነተኛ የሕዝብ ልጅ ፕ/ሮ መረራ ጉዲናን ከአክራሪ እስልምና አቀንቃኙ ከጀዋርና (ክርስቲያንን ሁሉ በሜጫ ቢከትፈው የሚመኝ) በሻቢያ በኩል ኢትዮጵያን ነጻ አወጣለሁ እያለ የሚያላግጥብንን ብርሀኑ በአንድ ላይ ከሰሰ በሚል የወያኔ ሚዲያዎች ማናፈሳቸው ሳያንስ ሌሎችም ይህንን ተቀብለው እያዛመቱለት ነው፡፡ እውነታው ግን ከመረራ በቀር ለወያኔ በአሁኑ ወቅት አደገኛ ሆኖ የታያት የለም፡፡ እውነታው ጀዋርና ተከታዮቹ ባይኖሩ ወያኔ አደጋ ላይ በወደቀ ነበር፡፡ ጀዋርና ተከታዮቹ ለወያኔ የጠቀሟትን ያህል አለኝ የምትለው አጋዚም አልጠቀማትም፡፡ ጀዋርና ተከታዮቹ መስለውኝ ሕዝብ ወሳኝ ተጋድሎ ላይ እያለ ኢትዮጵያን ማፍረስ ሚናቸው እንደሆነ ከወያኔ የተሰጣቸውን ሥራ ለንደን ላይ ሲናገሩ የሰማናቸው፡፡ ጀዋርና ተከታዮቹ እኮ መሰሉኝ በወሳኝ የትግል ወቅት የሕዝብን ትኩረት ወደሌላ ለመቀየር አትላንታ ላይ የኦሮሞ ቻርተር በሚል ልዩ ሕዝብን የሚከልስ ሥራ ሲሰሩ የነበሩ፡፡ የለንደኑም ንግግር የአትላንታውም ጉባዔ እኮ እንደተባለውም ከምር አልነበረም፡፡ ሆን ተብሎ ወያኔ የገባችበትን አጣብቂኝ ፋታ እንዲሰጣት ትኩረት ለማስቀየር እንጂ፡፡ ለመሆኑ ጀዋር ከመቼ ወዲህ ነው የወያኔ ጠላት የሆነው፡፡ ከተከሰስ ለምን ድሮ አልተከሰሰም፡፡ ዛሬ ከመረራ ጋር ጀዋርን መክሰስ ለምን ተፈለገ; የወያኔው ቡድን ጀዋር በሕዝብ ዘንድ እንደተጠላ ስለተረዳ እንደገና የወያኔ ጠላት በማስመሰል የሕዝብ ትኩረት እንዲያገኝ ስለሚፈልግ ነው፡፡  ምክነያቱም ገና ብዙ ለወያኔ የሚሰራላት ሥራ አለውና ነው፡፡ ይህ ግለሰብ እያደረገ ያለውን ብዙ የኦሮሞ ልጆች ዛሬ ላይ ነቅተውበታል፡፡ እሱና ቡድኑ ወሳኝ የወያኔ የቁርጥ ቀን  ተዋናይ ናቸው፡፡ እባብ ሞኝን ሁለት ጊዜ ነደፈው ይባላል፡፡ ድሮ የኦነግ ባለስልጣናት ከወያኔ ጋር እየሰሩ የኦሮሞ ልጅ ኦነግ ነህ እየተባለ ሥንቱ የደረሰበት እንኳን ሳይታወቅ ቀርቷል፡፡ አሁን የኦነግ ባለሥልጣናት ብዙም ሚና የላቸውም፡፡ ወያኔ ትብብሯ ትልቅ ሚና አላቸው ከተባሉት ከእነጀዋርና ቡድኑ ጋር ነው፡፡ አስተውሉ ጀዋርና ቡድኑ ምን እያደረጉ እንዳለ፡፡ ዛሬ ጀዋርና ቡድኑ የአረጀውንና ከሕዝብም ትኩረት እየደበዘዘ የመጣውን ኦነግን በአዲስ መልክ እንዲያስቀጥሉት ወያኔ ትፈልጋለች፡፡ ይህ ከአልሆነ የኦሮሞ ሕዝብ ከእጇ መውጣቱ ነው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ አመለጠ ማለት ደግሞ በቃ ሁሉም ነገር አከተመ፡፡ እነ መረራ ዛሬ ላይ እንዲህ ሥጋት የሆኑባት ወያኔ ኦነጋውያን ጥሩ ሥም በነበራቸው ጊዜ እንደምንም አልቆጠረቻቸውም ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ከጥቂት የጀዋር ተከታይ የሙስሊም አክራሪ ኦሮሞዎች በቀር የኦሮሞ ሕዝብ ትኩረቱን ወደነመረራ አዙሯል፡፡ ይህ ወያኔን ከአስደነገጣት ነገር አንዱ ነው፡፡ በእርግጥም እነጀዋርንም እጅግ አስደንግጧል፡፡ ዛሬ የኦሮሞ አክቲቪስት ነን የሚሉት እንዲህ አቅላቸውን የጣሉ እስከሚመስል ድረስ የሚያንቀዠቅዣቸው ይሄው የኦሮሞ ሕዝብ ኦነጋውያኑን(የዛሬዎቹ አክቲቪስት ተብዬዎቹ እነጀዋር) ገሸሽ አድርጎ መረራንና ቡድኑ መመልከቱ ነው፡፡ ለዘመናት መረራን ሊያደምጥ የፈለገ አልነበረም፡፡ እንደውም የነፍጠኛ ተላላኪ በሚል ሥም ጭራሽ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖረው ተደርጓል፡፡ ሌላ ቀርቶ እነ ተስፋዬ ገብረዓብም እነሱ ከመረራ በላይ ኦሮሞ ሆነው በመረራ ሲያፌዙ ነበር፡፡ በአንድ ፕ/ር ሕዝቅዬል የመድረክ መሪ በሆነበት የኦሮሞ ዲያስፖራ ጉባዔ ላይ ሕዝቅኤልና መሰሎቹ የሰጡትን ኦሮሞነት ተሰፋዬ ሲጠቀምበት መረራን በመንቀፍ አፉን ሲያሟሽ የተደረገለት ጭብጨባ እናስታውሳለን፡፡  ዛሬ ላይ መረራን በኦሮሞ ሕዝብ ፊት አንዳች ክፉ መናገር አይቻልም! ዘግይቶም ቢሆን ሕዝብ አሁን ገብቶታል!

ወያኔ አሁን እያደረገች ያለችው ይህን አፍጥጦ የመጣባትን የመረራና ቡድኑ የኢትዮጵያዊነትና ኦሮሞነት ፍልስፍና እንዲምታታ ሥለፈለገች ነው የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጠላት የሆኑትን እንደነጀዋር የመሳሰሉትን ከመረራ ጎራ ያደረገቻቸው፡፡ ወያኔን ከኢትዮጵያዊነት በላይ የሚያስፈራት የለም፡፡ ይህ ኢትዮጵያዊነት በሙሉ ወኔ ወደ ኦሮሞ ሕዝብ ገባ ማለት ነገሩ ሁሉ ያበቃል፡፡ እንኳን አዲስ አበባ ወያኔ ተነሳሁበት የምትለው ደደቢትም ከዚያ በኋላ መመሸጊያዋ አይሆንም፡፡ ይህችን አገር የሠሯት ባለቤቶቿ በግዛታቸው የባንዳ ልጆች መጨረሻቸው ነው፡፡ ዛሬ የኦሮሞ ጀግኖች ልዮ ታሪክ የሆነውን የሚኒሊክን ታሪክ ጥላሸት ለመቀባት የሚዘመትበት ቁልፍ ሚስጥሩም ይሄው ነው፡፡ እነ የኦሮሞ አክቲቪስት ነን የሚሉ የወያኔ ቅጥረኞች እድል አግኝተው ያልተፈጠረ ታሪክ እየፈጠሩ የሚያወሩበት ሚስጢር ይሄ ነው፡፡ እምዬ ሚኒሊክ ሲባል ሁሉም ይበረግጋል፡፡ ጀግኖቹ ኦሮሞዎች ሚኒሊክ የልብ ወዳጃቸው ነው፡፡ የሚኒሊክ ታሪክ አደዋ ቢቻም አደለም፡፡ እወነት ነው ሚኒሊክና ኦሮሞዎች ብል ይቀለኛል እሽ ያለውን በውድ እምቢ ያለውን በግድ አስገብረው ኢትዮጵያ የምትባልን አገር ከዘመናት መፍረስ በኋላ መልሰዋታል፡፡ የኦሮሞ አክቲቪስቶችን ይህ ታሪክ የሚያስፈራቸው ከባንዳዎቹ ጋር ባላቸው ወዳጅነት እንጂ አንድም እነሱ የሚሉት ታሪክ በሚኒሊክ ተፈጽሞ አደለም፡፡ እንነጋገር ከተባለ በአፍሪካ አደለም በአለም ላይ ሥኬታማና ልዩ ታሪክ ፈጣሪ የነበረው ኦሮሞዎች በዋናነት የተሳተፉበት የሚኒሊክ ሥርዓት ነው! አገርን አንድ ማድረግ፣ አገርን በእድገት ጎዳና በታላቅ ፍጥነት ማስገስገሰ፣ ዓለም በወቅቱ ያልደፈራቸውን ቅኝ ገዥዎችን ማሸነፍና የአገርን ዳር ድንበር ማስጠበቅ ለየትኛውም የአለም መሪ አልተሳካለትም፡፡ ሊያውም አፍሪካዊነት በራሱ ታላቅ ክብደት በሆነበት ወቅት፡፡

ሰሞኑን የሄው ጀዋር የሚባለው ግለሰብ በሚመራው ሚዲያ የኦሮሞ ምሁር ነን የሚሉት ሶስት ግለሰቦች ፕ/ር ሕዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶ/ር አባስና ሀብቴ ኢታና ለሚኒሊክ ኃጥያት የሚሆን የውሸት ታሪክ በመፍጠር እውነተኛውን የማየወዱት ሳይቀሩ እየመረራቸውም ቢሆን የተጎነጩትን የአደዋን ታሪክ በማጥላላትና በማኮሰስ ሊነግሩን ብቅ ብለው ነበር፡፡ ምሁርነት በራሱ ትልቅ ሀላፊነት ነው፣ እድሜ ሌላው ትልቁ ሀላፊነት ነው፣ ከዚያ በተረፈ ግን ማንኛውም ተራ ሕጻን እንኳን  ቢሆን ሕሊናን የሚያጎድፍ ወሸት መናገር ውርደት ነው፡፡ ጥሩነቱ የኦሮሞ አክራሪዎቹ የሚይዙት የሚጨብጡት ስላጡ አሁን አሁን ማንነታቸውን እየገለጡት መሆኑ ነው፡፡ ለበርካታ ጊዜ የኢትዮጵያን ጉዳይ ዋና ተንታኝ የነበረው እሱ ራሱን እንደገለጸው “ዶ/ር” (ይቅርታ የሰውን ማዕረግ ለማሳነስ ሳይሆን ገና የ ዶክተሬት ተማሪ እንጂ ዶ/ር አደለም የሚል መረጃ ስላለ ነው) ጸጋዬ አራርሳ  የማንነት ጭምብሉ ሲወጣ ሲገለጥ ነው ዛሬ የምንሰማውን የጥላቻና የበቀል ንግግሮቹን መንዛት የጀመረው፡፡ እስከ ዛሬ ተደብቆ ነበርና፡፡ ልብ በሉ ጸጋዬ ግን በወያኔ የሲቪል ሰርቪስ ኮሌች የወያኔ ካድሬዎች አሰልጣኝ ነበር፡፡ ጀዋርና መላው የኦሮሞ አክቲቪስት ነኝ የሚለውን ወያኔ ሕዝብ እንዲቀበላቸው ትፈልጋለች፡፡ መረራን ከጀዋር ጋር የከሰሰችበት ዋና ምክነያቷ የመረራን ፍልስፍና ለመበረዝ ነው፡፡ የመረራ ፍልስፍና ከምንም በላይ ለወያኔ አደገኛ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት፣ ነፍጠኛ ከተባለ የኦሮሞም ነፍጠኛ ነበር ብሎ የሚናገረው ለዘመናት ተቀባይነት ያጣው የመረራ ፍልስፍና፡፡ ኢትዮጵያ ከማንም በላይ በኦሮሞ ልጆች ደም የተገነባች አገር ነች ብሎ የሚናገረው መረራና ጀዋር ናቸው እንግዲህ በአንድ ወንጀል የሚከሰሱት፡፡ ጀዋር ቢከሰስ እንኳን ምን አልባት ወደፊት ክርስቲያንን በሜጫ ጨርሶ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ምኞት እንዳለው ተጠርጥሮ ሊከሰስ ይችላል፡፡ ዛሬ እሱን የሚከሰው የለም፡፡ ዛሬ ግን  ጀዋር  አዲስ አበባ ቢሄድ ሻራተን ሶስት ቀን ቆይቶ ምን አልባት የታሰረ ወገን ካለው አስፈትቶ ሊመለስ ይችላል የቀድሞው የኦነግ መሪዎች እንዲህ እንደነበሩ እናስታውሳለንና፡፡ ሥንቱ የደሀ ልጅ ግን በኦነግ ሥም አልቋል፡፡ በአጭሩ ሌሎቻችሁ ደግሞ አታምታቱ ወይም አትጃጃሉ የተከሰሰው መረራ ብቻ ነው እንጂ ጀዋር እየተደረገለት ያለው ያጣውን የሕዝብ ድጋፍ እንዲያገኝ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ ባይሆን ጀዋር ትንሽ ቀሪ ደጋፊዎች ካሉት አገር ቤት ለወያኔ ፕሮፓጋንዳ የሚመች ሕዝብ የሚያልቀበትን የጎዳና አመጽ ያውጅ ይሆናል፡፡ ለእሱም ወሬ ያገኛል፡፡ እሱ የሚመራው ሚዲያ ይሄ ዛሬ ላይ በየቦታው የምንሰማው የኦሮሞ ሕዝብ ልጆች ሥቃይ ከአበቃ ወሬም ላይኖረው ነው፡፡ ሰሞኑን በሶማሊ ክልል ታጣቂዎች የሚደርሰው ግፍ ጥሩ ወሬ ሆኖለታል፡፡ እኛን ግን ያመናል፡ ይቆጫል፣ ያንገበግባል! ዛሬ ማንነቱን አጥቶ መክኖ አቅም ያጣው የኦሮሞ ሕዝብ ለጦርነት ለሌሎችም ጦርነትን ያስተማረ ነው፡፡ እድሜ ለወያኔና ኦነጋውያን፡፡ አሁን የነቃው የኦሮሞ ሕዝብ ፊቱን ወደነመረራ ማዘንበሉ ግን ከምንም በላይ ለወያኔና ኦነጋውያን(የዛሬዎቹ አክቲቪስቶች) ስጋት ነው፡፡  ይህ ነው እውነታው! አታምታቱ!

ሌላው በሻቢያ በኩል ኢትዮጵያን ነጻ አወጣለሁ ሲን ስንጃጃልለት የኖርነው ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ የተባለው ግለሰብ ነው፡፡ ድርጊቱ ሁሉ አንድም ቦታ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የነጻነት ትግል ጋር የሚመስል እንደሌለ ብናይም ብዙ ደጋፊ ስለነበረው ግራ ተጋብተን ቆይተናል፡፡ ለነጻነት እታገላለሁ የሚልን መደገፍ መልካም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን አንዳች የሚመስል ነገር የሌለውን መደገፍ በራሱ ሌላ ግራ መጋባት ነው፡፡ ዲያስፖራ ተብዬው በእርግጥ እንደነዱት የሚነዳ እንጂ ማስተዋል ያለው አይመስልም፡፡ ልብ በሉ ለነጻነት እዋጋለሁ የሚለው የብርሀኑ ቡድን የወያኔ የቁርጥ ቀን ወዳጅ በሆነው በሻቢያ በኩል ነው፡፡ ለመሆኑ ይሄ ቡድን አማራጭ አጥቶ ነው ወይ ብለን ስንጠይቅ መልስ የለም፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ከዳር እዳር ሕዝቧ አፈንግጦ እያለ ሻቢያ ጋር መልከስከስ ምንድነው; ብለን መጠየቅ ፈርተናል ወይም አዚም ተደርጎብናል፡፡ ባይሆን እንኳን ከምንም በላይ ደቡብ ሱዳን ጥሩ አማራጭ ነበር፡፡ ከሕዝብ ወጥተው ዛሬ እየታገሉ ያሉት ወገኖች እኮ ያሉበት እነ አርማጮ መሳሪያ የሚያገኙት ከሱዳን ነው፡፡ ያጠራቸው ገንዘብ እንጂ የተኛውንም አይነት መሣሪያ ሊያስገቡ እንደሚችሉ እናውቃለን፡፡ ማን ከልክሏቸው በገዛ መሬታቸው፡፡ የብርሀኑ ቡድን ግን ስንት አመቱ ነው;   ከባለፈው ዐመት የተሻለስ ትክክለኛ የነጻነት ታጋይ ከሆን ምን እድል ነበረው; ልብ ያለው ልብ ይበል ከማለት ውጭ አሁን ላይ ሰው ሊያምነው የማይቻለውን ነገር ብንናገር ማን ቢሰማ፡፡ ብርሀኑ ከመረራ ጋር የተከሰሰበት ሂደት ግን ጀዋርን ከመረራ ጋር ከተከሰሰበት የተለየ አደለም፡፡ እነ በቀለ ገርባ ከታሰሩ ጀምሮ መረራን የሚያስሩበት ምክነያት እየፈለጉ ነበር፡፡ ከምንም በላይ ሕዝብን ሊያመው የሚገባው መረራ መታሰሩ ብቻም ሳይሆን እንደገና ከሕዝብ ጠላቶች ጋር ተባባሪ እንደሆነ ለማሳየት የተሞከረበት ሂደት ነው፡፡ ወያኔና ወዳጆቹ የመረራን ከእነዚህ ሁለት ግለሰቦች ጋር መከሰሱን አጉልተው ሊያወሩት ይፈልጋሉ ይሄ በትክክልም አጀንዳቸው ነውና፡፡ ሌሎች ግን አይምታታባችሁ፡፡ በዚህ ልዩ ክስ  ወያኔን የከሰሰቸው መረራና መረራ ብቻ ነው፡፡ ጀዋር ብርሀኑ የምትሏቸው ወያኔ ሕዝብ ትኩረት እንዲሰጣቸው ስለፈለገች ነው ከመረራ ጋር የደባለቀቻቸው፡፡ ዲያስፖራ ሆይ ተምታቶብህ ሌሎችን አታምታታ፡፡ ሁሉንም ቆይተህ ታየዋለህ፡፡   ዲያስፖራን ሌላ የታዘብነው አለ መረራ ሲታሰር አንድም እንቅስቃሴ አለማድረጉ የዲያስፖራው ነገር የተያዘው በነጋዴዎች እንጂ በእውነተኛ የሕዝብ አጋሮች እንዳልሆነ ነው፡፡

 

እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን!

 

 

ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ! አሜን

“በስህተት ነው ፍ/ቤት ያቀረብንህ” – ወሰንሰገድ ገብረኪዳን

$
0
0

#MALAAN_JIRA
“በስህተት ነው ፍ/ቤት ያቀረብንህ” – ወሰንሰገድ ገብረኪዳን
============
“MALAAN JIRA” “ማለን ጅራ” የሀጫሉ ሁንዴሳ Hacaaluu Hundessaa ዘፈን ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ነው የተለቀቀው፡፡ ኦሮምኛ አልችልም፡፡ ለምን እንደሆን እንጃ የሀጫሉን “ማለን ጅራ” ግን እወደዋለሁ፡፡ በእኔ ዕይታ የዜማው ፍሰት፣ የክሊፑ ቅንብር … ወዘተ የተዋጣለት ነው፡፡ መልዕክቱ ባይገባኝም ዘፈኑ የሆነ የሚመስጥ፣ የሚወዘውዝ ነገር አለው፡፡ ይሁን እንጂ የዘፈኑን ርዕሱስ እንኳ አላውቅም፡፡ በኋላ ግን ወደ ኢንተርኔት ጎራ ብዬ ርዕሱን አየሁ፡፡ እስረኛውን ጠይቄ ስመለስ ዜማውን ብቻ እያንጎራጎርኩ ነበር፡፡ እናም የዘፈኑን መልዕክት የመረዳት ጉጉት አደረብኝ፡፡ ጥቂት ካሰብኩ በኋላ ከፌስቡክ ጓደኞቼ አንዱን በውስጥ መስመር ጥያቄ ሰደድኩለት፡፡
.
“ከዘፈኑ መሃል አንድ አራት መስመር ተርጉመህ ንገረኝ?” አልኩት፡፡
“ዘፈኑ ቃል በቃል ሲተረጎም ደረቅ ነው ሚሆነው፤ ብዙም አይጥምም” አለና ጥቂት ስንኞችን ተርጉሞ ላከልኝ፡፡
.
“Gasraa abbichu turii
አብቹ ጋራ ቆዪኝ
Galaan Finfinnee marsee
ገላን ፊንፊኔን ከቦ ነው ያለው
Silaa akka jallalaa wal-irraa fadaannu jaratu nu fagaeesse
እንደፍቅራችን መራራቅ የለብንም ነበር ሰዎች ናቸው ያራራቁን
Diiganii gaara sanaa diigamuu hin mallee,
ያ ሊናድ የማይችለው ተራራ አፍርሰው አፈራርሰው
Baasani nu addaan baanee
ለይተው እኛን ለያዩን
nuti addaan bahu hin mallee.
ልንለያይ የማይገባንን
መፍረስ የሌለበት ያንን ጋራ (ተራራ) አፈረሱት ተለያየን ለያዩን እንጂ እኛ መራራቅ አልነበረብንም
Soreetti haadha sooree
ሃብታሟ የሃብታሙ እናት
irbaan irra buusa qaba,
እራት ጭማሪ አለው
seeqanii sesseeqanii
ጋፍተው ገፋፍተው
kan addaan nu baasan jara….
ሰዎቹ ናቸው የለያዩን
.

የዘፈኑን ትርጉም በከፊል በተረዳሁ ጊዜ ከሳምንት በፊት የሴት አያቴ ወንድም መጥቶ ያወጋነው ታወሰኝ፡፡ እህቱን (ሴት አያቴን) ሊጠይቅ መጥቶ ነበር በዚያው ወደእኛ ቤት ጎራ ያለው፡፡ ከፍቼ /ኮማንዶ/ ትንሽ ወጣ ብሎ “ቦሴ” የሚባል መንደር ነው የሚኖረው፡፡ ቆፍጣና ገበሬ ነው፡፡ እስከዚህ ዕድሜዬ ድረስ አንድ ጊዜ ብቻ ነው ቦሴ ሄጄ የጠየቅኩት፡፡ እሱንም የልጁን ሠርግ ተጠርቼ መሰለኝ፡፡ እሱ ግን (የሴት አያቴን ወንድም አንተ የምለው እሱ ራሱ “አንተ” በለኝ ብሎ ነው) በየዓመቱ ወይ በየሁለት ዓመቱ አዲስአበባ መጥቶ ይጠይቀናል፡፡ በመጣ ቁጥር “እናንተማ ዘመድ አትጠይቁም፤ ተለያይተን መቅረታችን ነው” እያለ ይወቅሰናል፡፡ (መቼም የሀጫሉን ዘፈን ሰምቶ አይመስለኝም ሁሌም “ተለያይተን ልንቀር” የሚለው)
የሆነ ሆኖ እንዳየሁት “አረጀህ እኮ” አልኩት፡፡
“ምን እኔን አረጀህ ትለኛለህ? አንተ ራሱ ጨርጭሰህ የለ እንዴ” አለኝ፡፡ ሳቅኩኝ፡፡ እውነቱን ሳይሆን አይቀርም፡፡ እሱ አሁንም ጠንካራ ነው፡፡
“እንደዚህ ያገረጀፈህ የከተማ ኑሮ አስንፎህ ስራ ስለማትሰራ ነው፤ እኔ ጋ ብትመጣ እንደገና ልጅ ትሆናለህ”
“እዛ መጥቼ ምን እሰራለሁ?”
“መቼም እርሻ ማረስ አትችልም፡፡ ሁለት ላም እሰጥሃለሁ፤ ከብት ታረባለህ” አለኝ፡፡
ገበሬ ስሆን ታየኝና ሳቅኩ፡፡
.
እና ….. ይህንን ትውስታዬን እያመነዥግኩ “አሁን ፍቼ/ቦሴ አያቶቼ መንደር ብሄድ ኮማንድ ፖስቱ የሃጫሉን ዘፈን ሰምተህ ነው ሊለኝ ነው?” ብዬ ራሴን ጠየቅኩ፡፡ እዚህ አገር መቼም እፍረት የሚባል የለ፤ እንደዛ ይሉ ይሆናል፡፡
.
ምክንያቱም መዝናኛ ቤት (መጠጥ ቤት) ይህንኑ የሀጫሉን ዘፈን እንዲከፈት ጠይቀሃል ተብሎ ጋዜጠኛ ኢዩኤል ፍሰሃ እስር ቤት ተወርውሯል፡፡ ከወራት በፊት፡፡ ኢዩኤል ከእስር የተፈታ መስሎኝ ነበር፡፡ አንዳንዴ እንዲህ ይሆናል፡፡ የተፈታ የመሰለኝ ነገሩን (የታሰረበትን ምክንያት) አቅልዬው ይሆናል፡፡ እነ አናንያ እና ኤልያስ ናቸው አሁንም በእስር ላይ መሆኑን ነግረው ያስታወሱኝ፡፡ ስለዚህ ልጠይቀው ችሎት ተብሎ ወደሚታወቀው አካባቢ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሄድኩ፡፡
.
ወደፖሊስ ጣቢያው የሚያዘልቀውን ኮረኮንች ይዤ ትንሽ እንደተጓዝኩ ያየሁት ነገር አጠራጥሮኝ ቆም አልኩ፡፡ የተሳሳትኩ መሰለኝ፡፡ በሩ አናት ላይ ትልቁ “የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ክሊኒክ” የሚል ፅሁፍ ይታያል፡፡ እንደመጠራጠር አልኩኝና በአጠገቤ የሚያልፉ ሰዎችን “እስረኞች ያሉት እዚህ ነው አይደል?” ስል ጠየቅኩ፡፡ “አዎ” አሉና አረጋጡልኝ፡፡ “ክሊኒክ” የሚለውን እንደገና ፈገግ አልኩ፡፡ ወደው አይስቁ አለ ያገሬ ሰው፡፡
.
ገባሁ፡፡ ኢዩኤልን አስጠራሁት፡፡ መጣ፡፡ የተደነቀ ይመስላል፡፡ በእጁ መፅሐፍ ይዟል፡፡ ተጨባበጥን፡፡
“እዚህ መፅሐፍ ይገባል እንዴ?”
“አዎ፤ ይገባል”
“እኔ ምልህ፤ ከታሰርክ ስንት ጊዜ ሆነህ”
“አራት ወር ከ4 ቀን….ዛሬ 124 ቀኔ እዚህ ከተጣልኩ”
“ፍ/ቤት ቀርበህ…ዋስትና እንደተፈቀደልህ ያነበብኩ መስሎኝ ነበር”
“አዎ እንደታሰርኩ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍ/ቤት ቀርቤ የሁለት ሺህ ብር ዋስትና እንዳቀርብ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር”
“እና…?”
” ዋስትናውንም አስይዤ መፈቻ መጥቶ ነበር፡፡ እዚህ መፈቻው ላይ አንፈርምም ብለው ይኸው እስካሁን አለሁ”
“ለምን? ለምን እንዳለቀቁህ አልጠየቅክም”
“መጠየቅማ ጠይቄአለሁ፡፡ መጀመሪያውኑ ፍ/ቤት መቀረብ አልነበረብህም፡፡ በስህተት ነው ፍ/ቤት የቀረብከው …አሉኝ”
“ምን ማለት ነው?”
“እኔም ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም….” አለኝ ግራ በተጋባ ስሜት፡፡
.
እነሆ ጥቂት ደቂቃ እንዲህና እንዲያ አውግተን ተለያየን፡፡ እናም ተመለስኩ፡፡ “ማለን ጅራ”ን እያንጎራጎርኩ፡፡ አሁን ማለት የምችለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ እሱም ሰሚ ከተገኘ!
.
#ኢዩኤል_ፍሰሃ_ዳምጤን_ፍቱት!


አድዋን የመሰለ ወታደራዊ ድል ስለምን ወደ ፖለቲካዊ ድል መቀየር ተሳነን?

$
0
0

እንደ መግቢያ

በታወቀ ምክንያት የኢትዮጵያ ታሪክ አወዛጋቢነት ቀጥሏል፡፡ “ታሪክ የሞተ ፖለቲካ ነው” የሚለው አባባል ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን አይሰራም፡፡ ይልቁንስ “ታሪክ የነበረ፣ ያለና ወደፊትም ሊቀጥል የሚችል ፖለቲካ ነው” በስሜት በሚነዳ የዘውግ (የዘር፣ የጎሣ) ፖለቲካ ውስጥ ታሪክ ትልቅ ማገዶ ሆኖ ቀርቧል፡፡ እንዲህ ባሉ የታሪክ ውርክቦች ውስጥ ይበልጥ አትራፊው ገዥዉ ኃይል መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

ታሪክ የአሸናፊዎች ደንገ-ጡር በሆነችባት ኢትዮጵያ ገዥው ኃይል ለአገዛዙ በሚያመቸው መልኩ ታሪክን በርዞና ከልሶ ሲያቀርብ ታሪክን ሳያላምጡ የሚመጡ ደቃቅ “ፖለቲከኞች” በርክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታሪክ አተራረክ በአጥቂነትና በተከላካይነት የሚበየን የውዝግብ መድረክ ሆኗል፡፡ የአንድ ዘውግ ጉዳይን ሁልግዜ በተጠቂ ስሜት፤ ሌላኛውን ዘውግ በአጥቂነት የማየት ዝንባሌም በታሪክ ትንተና ውስጥ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ከታሪካችን የሚያግባባንን ማግኘት ተስኖናል፡፡ ጭራሹን ጉልህ የልዩነታችን መስክ ሆኖ ቀርቧል፡፡

ከሰሞኑ በምኒልክና በአድዋ ድል ዙሪያ ሶስት ጠርዞች፤ በሁለት ጐራ የተከፈለ ዱላ ቀረሽ  “ክርክር” (እንደ እውነቱ “ዘለፋ” ማለት ይቀላል) በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲንፀባረቅ እየተስተዋለ ነው፡፡ የአገራዊ የጋራ ማንነታችንና የብሄራዊ እሴቶቻችን ንጣፍ መሰራት ሊሆን የሚችለው የዓድዋ ድል በዓል በዚህን ያህል መጠን የልዩነታችን ቀይ መስመር አስማሪ መሆኑ የሰከነ የውይይት ባህል እየራቀን ለመሄዱ አንዱ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡

ብዙዎቹን የአካዳሚውን መስመር ሰዎች እንደሚያስማማው “የኢትዮጵያ አገራዊ ታሪክ ዘመንና መቼትን ተሻግሮ የሚጠቀስ ሰፊ እና ረጅም ዕድሜ አለው” ከአናሳ ዘውግ በመምጣታቸው ሁሌም ቢሆን የበታችነት ስሜት በሚያሰቃያቸው የህወሓት ስዎች ሲገለፅ እንደኖረው የኢትዮጵያ ታሪክ በአንድ መቶ ዓመት ብቻ የሚቀነበብ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ የተዋለደው ወጥ ይዘት ባጀበው ቀጣይ ተግባር ሳይሆን ውስጣዊና ውጫዊ በሆኑ የኃይል ግፊቶች የግዛት ወሰኑን በማጥበብና በማስፋት ሂደቶች መሀከል የተፈጠረ ነው፡፡ ዘመናዊት ኢትዮጵያ ሲባልም የትላንቷ ኢትዮጵያ ቅጥያ እንጅ ከጠፈር የመጣች ማለት አይደለም፡፡ ከዚህ አኳያ የህወሓት “ኢትዮጵያ የአንድ መቶ ዓመት ታሪክ ነው ያላት” የሚለው የጉርምስና ሀተታ  ከፖለቲካ ፍጆታነት የሚሻገር አይደለም፡፡

የታሪክ ሊቃውንቱ “ታሪክ የትውልዶች መገናኛ ድልድይ ነው” ሲሉ ቢደመጥም፤ ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን ታሪክ የትውልዱ የልዩነት ማስመሪያ ቀይ ቀለም ነው፡፡ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ለዘውግ ፖለቲካ ማፋፋሚያ አይነተኛ ማገዶ ነው፡፡ ታሪክ ለየዘውጉ (በ“ጨቋኝ” “ተጨቋኝ” ትርክት) ዘውጋዊ ንቃት መፍጠሪያነት አንጂ ከዚህ በተሻገረ መልኩ የአገራዊ ውህድ ህላዌ መጋቢና ደጋፊ ሆኖ ሲገለፅ አይስተዋልም፡፡

የማንነት ፖለቲካን የታከከ የታሪክ ትርጓሜ ጐልቶ በሚታይበት ኢትዮጵያ፤ በአገር ግንባታ ሂደቶች የታዩ ክስተቶችን በተመለከተ የሦስት ዘውጐች ሊሂቃንና ተከታዮቻቸው የበረታ ፉክክር ይስተዋልበታል፡፡

ባሳለፍነው ሩብ ክፍለ ዘመን ጉልህ የመገፋት ሂደት ውስጥ እየተዋለደ የመጣውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን ለማቅናት እየተውተረተረ የሚገኘው የአማራ ብሄርተኝነት፤ ግማሽ ክፍለ ዘመንን በሚሻገር መልኩ ተደክሞበት ዛሬም በውል ያልፀናው የኦሮሞ ብሄርተኝነት እና “የብቻ ሥልጣኔያችን ነው” የሚሉትን ሥልጣኔ ከአክሱም ሃውልት ፍርስራሽ ግርጌ መፈለግ የሚቀላቸው የአፄ ዮሐንስ ዘውድ አስመላሽ የትግራይ ብሄርተኞች በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ጫፍና ጫፍ የተወጠረውን የታሪክ ውርክብ በማጦዝ ወደረኛ የታሪክ ዘውግ ሙዚቃዊ ድርሰት /genre/ ፈጥረዋል፡፡

የምስራቅና የደቡብ ኢትዮጵያ የወል ማህበረሰቦች (Cultural communities) በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ አገር ግንባታ ሂደቶች የታዩ ውስን ማህበራዊ መለንቀጦችን እያስታወሱ ቢያኮርፉም፤ ከላይ እንደተጠቀሱት ሦስቱ (የኦሮሞ፣ አማራና የትግራይ) ዘውጐች በታሪክ ውርክቡ ውስጥ ሚዛኑን የሳተ የጉርምስና ሀተታ ሲያቀርቡ አይስተዋልም፡፡ አልፎ አልፎ ከሲዳማና ከወላይታ የሚመዘዙ ብሄረተኞች የሚኒልክን አገር ግንባታ ሂደት ሲነቅፉ መስተዋላቸውን ሳንዘነጋ፡፡ ከሚኒልክ የደቡብ ዘመቻዎች ተጠቃሹ የጉራጌ ዘመቻ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያመለክታሉ፡፡ ይሁንና የምኒልክን የአገር ግንባታ ሂደት የጉራጌ ልሂቃን እንደ ሌሎቹ ብሄረተኞች አግንነው ስብከት ሲያሰሙ አይስተዋልም፡፡

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ከአፄ ቴዎድሮስ የንግሥና ዘመን ይጀምራል፡፡ የዳግማዊ ቴዎድሮስ የአንድነት ህሳቤ ባልተጠበቀ መልኩ የተቀጣጠለው አገራዊ ራዕይ (አንድነቷ የተጠበቀ፣ ማዕከላዊ መንግስቷ የተጠናከረ ዘመናዊት ኢትዮጵያ የመመስረት ህልሙ) በመሳፍንቱ እምቢተኝነት፣ በካህናት ልግመት፣ በቴዎድሮስ የበዛ የቅጣት በትር፣ . . . በመጨረሻም በናፒየር በተመራው የእንግሊዝ ወታደራዊ ዘመቻ ቢመክንም በቀጣይ በነገሡት ነገሥታት (የውስጥ ሽኩቻቸው እንደተጠበቀ ሆኖ) ሊቀጥል ችሏል፡፡ በአፄ ዮሐንስ የዳር ድንበር ተከላካይነት ለጥቆም በንጉሰነገሥት ምኒሊክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ አገር ግንባታ ሂደት ከነሳንካዎቹ እውን መሆን ችሏል፡፡

ትውልድ የሚረግመው ጀግና!

ከምኒልክ የቀደሙት ሁለት ነገሥታት የተቻላቸውን ያህል ቢጥሩም ማዕከላዊ መንግስቱን በሚቆምና አገሪቷን ወደ ዘመናዊነት በማሻገር አፄ ምኒልክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ መስራች ነው፡፡ አፄው የግዛት አንድነትን ለማስጠበቅ ዘመኑ ያስገደደውን አማራጭ ሲወስደ የተጐዱ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳሉ የማይካድ እውነት ነው፡፡

ይሁንና የአገር ግንባታ ሂደት ከደምና ከላብ ውጪ ከቶውንም ተከውኖ አያውቅም፡፡ ዛሬ ላይ እንደ ሰማይ ከዋክብት በሥልጣኔና በምርምር ስርጸት የራቁን የምዕራቡ ዓለም አገራት እንደ አገር ለመቆም የበዛ የደም ዋጋ ከፍለዋል፡፡

የዘመናዊት ኢትዮጵያ አፈጣጠርም አብርሃም ሊንከን ከደከመላት አሜሪካ፣ ኦቶማን ቢስማርክ “ነፍጥና መስዋዕትነት” በሚል ከተዋደቀላት ጀርመን አልያም ከጣልያን ወይም ፈረንሳይ . . . አፈጣጠር የተለየ ክስተት አላስተናገደም፡፡ የፈሰሰው የደም መጠን ይለያይ እንደሆን እንጂ አገራቱ በነፍጥና በመስዋዕትነት የመቆማቸው እውነት ለመካድ የማይመች ዓለምአቀፋዊ ጉዳይ ነው፡፡

እርግማን አንድ፤ “ምኒልክ ሂትለር ነው”

ከኦሮሞና አማራ ፊውዳል ቤተሰብ እንደተወለደ በህይወት ታሪኩ ዙሪያ የተሰናዱ ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡ አፄው የሸዋ ንጉሣዊያን የዘር ግንድ ውስጥ የተገኘ በመሆኑ በመሬት ማስፋት /land power/ የሚያምን፤ ይህን ተከትሎ በሚገኘው የሰውም ሆነ የተፈጥሮ ሐብት የተሻለ ሥርዓተ-መንግስት እንደሚያነብር የተረዳ መሪ ነበር፡፡

በአፄው የንግስና ዘመንም ሆነ የንጉሠ ነገሥትነት ጊዜ በአገር ማቅናቱም ሆነ የውጪ ወራሪ ኃይልን በመመከቱ ዘመቻ የድል ከፋች አውራ የጦር አበጋዞቹ ውስጥ የኦሮሞ ራሶች ቀዳሚ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በብዙዎቹ አክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኞች የምኒልክን ጨካኝነት አጉልተው ለማውጣት የሚጠቀሙባቸው ዘመቻዎች ሁለት ናቸው፡፡ የአርሲና የጨለንቆ ዘመቻዎች፡፡ ቀሪ የኦሮሞ ግዛቶች (ወለጋ (ኩምሳ ሞረዳ)፣ ጅማ-ግቤ (አባ ጅፋር) . . . ) በተበጣጠሰ መልኩም ቢሆን በገዛ ፈቃዳቸው ለምኒልክ የገበሩ መሆናቸው ይሰመርበት፡፡

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ከዘውግ ፖለቲካ የታሪክ አተረጓጎም አኳያ በአጨቃጫቂነቱ የሚነሳውን የአፄ ምኒልክ የግዛት ማስፋፋት እና ለስድስት ተከታታይ ዓመታት (1872-1878/79) የዘለቀው የአርሲ የመከላከል ፍልሚያ ነው፡፡ ከዓመታት ፍልሚያ በኋላ በራስ ዳርጌ እና በራስ ወልደ ገብርኤል የበረታ ዘመቻ አርሲዎች በራቸው ተሰበረ፡፡ ከዚህ በኋላ ያለውን ክስተት “የኢትዮጵያ ታሪክ የዘነጋው ነው” የሚሉን የኦሮሞ ብሄርተኛ ልሂቃን ፕሮፌሰር አባስ ገናሞ (The history of Arsi, 1880-1935) በሚል ሥራው ላይ “የአርሲ ህዝብ በራስ ዳርጌ ጦር አልቆ ኃይሉ ከተዳከመ በኋላ ዳግመኛ እንዳይነካና ለነፃነቱ እንዳይዋጋ ለመቀጣጫ ብለው ወንዶችና ሴቶችን ከአሰላ በስተ ሰሜን በሚገኝ አኖሌ በተባለ ሥፍራ ላይ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ወንዶች በራስ ዳርጌ ትዕዛዝ የቀኝ እጃቸው እንዲቆረጥ ታዘዘ፡፡ ወራሪዎች የቆረጧቸውን እጅ በወንዶቹ አንገት ላይ እንዲንጠለጠል ተደረገ፡፡ በዚሁ መሰረት ሴቶችም ቀኝ ጡታቸውም እየተቆረጠ እንደወንዶቹ በአንገታቸው ላይ እንዲንጠለጠል ተደረገ፡፡ (ገጽ 45) ትርጉም” እያለ ይተርክልናል፡፡ ፕሮፌሰሩ ይህን ሲተርክልን አንድም የታሪክ ሰነድ በማስረጃነት አይጠቅስም፡፡ የታሪክ ማስረጃዬ የሚለውም ሥነ – ቃላዊ ትውፊትን ብቻ ነው፡፡ በታሪክ ሙያ መስፈርቶች ተቀባይነት የሚኖረው ታሪካዊ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ የምኒልክ “የጡት ቆረጣ” ተረክ ዛሬ ላይ ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ ከአዲስ አበባ 150 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው ውሃና መብራት በሌለባት አኖሌ ሃያ ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሐውልት ተገንብቷል፡፡

“በአርሲ ዘመቻ ራስ ዳርጌ ቄጤማ እየበተነ መላ አርሲን ተቆጣጠረ” የሚል ትርከት (narrative) የለም፡፡ ምንም በማይካድ መልኩ በአርሲ ዘመቻ ራስ ዳርጌ እና ራስ ወልደ ገብርኤል የአርሲ ጀብደኛ ተዋጊዎችን ለመቅጣት በአንድ ቀን አራት መቶ የሚደርሱ አርሲዎችን ቀኝ እጃቸውን እንደቆረጡ በአያሌው ቀኖ ከፈረንሳይኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጐመው የፋዘር ማርሻል ዲ.ሳልቫይች /The Oromo, an Ancient people, Great African Nation/ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ይህ መፅሐፍ አፍቃሪ ኦሮሞ የሆነው ፈረንሳዊው የኃይማኖት ሰው ከአርሲ ዘመቻ ጥቂት ዓመታት በኋላ አርሲ ደርሶ ከነዋሪዎቹ የሰበሰበውን መረጃ አካቶ የፃፈው መፅሐፍ ነው፡፡ በሰውየው መፅሐፍ ውስጥ “የሴቶች ቀኝ ጡት ተቆረጠ” የሚል መረጃ ፈፅሞ የለም፡፡ በጊዜው ይህ ድርጊት ተፈፅሞ ቢሆን ኖሮ ይህ የኃይማኖት ሰው ድርጊቱን ከመፃፍ ምን የሚያግደው ኃይል ነበር?

ሰውየው ጽፎት ተርጓሚው ዘለለው የሚል መከራከሪያ እንዳይቀርብ እንኳን ከፈረንሳይኛ ወደ እንግሊዝኛ የትርጉም ሥራውን የሰራው አያሌው ቀኖ ኦሮሞ በመሆኑ ለክርክር አይመችም፡፡

የአርሲ ዘመቻ ከተፈፀመ ከሰማንያ አመታት በኋላ አርሲ ላይ የወለደው ፕሮፌሰር አባስ ገናሞ ግን ሥነ ቃላዊ ትውፊትን ብቻ መነሻ በማድረግ የምኒልክ ጦር በአርሲ ዘመቻ ጊዜ “የሴቶችን ጡት ቆርጧል” ይለናል፡፡ መቼም ለታሪክ ምርምር ዋና ወሳኝነት ያለው አስተማማኝ መረጃ ወይም የታሪክ ምንጭ ሰነዶች (በሙያው መስፈርቶች ተቀባይነት ያላቸው ታሪካዊ ማስረጃዎች) መሆናቸውን መካድ ያስተዛዝባል፡፡

በጊዜው የአገር ቤት ፀሐፍት የነበሩትን እነ ፀሐፊ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴንም ሆነ ዘግይተው የደረሱትን ህዝባዊ ታሪክ ፀሐፍትን “የተጉለት ደብተራ” ማለት የሚቀላቸው የዘውገ ብሔርተኞቹ “እውነት ከእኛ ዘንድ ብቻ ነች” በሚል “ለቅኝ ግዛት” ሃቲት በሚያመች መልኩ ዝግና የተመረጠ የታሪክ ግንዛቤ በመያዝ ትውልዱን መራር ትውስታዎችን ከብዜት (ፈጠራ) ታሪክ ጋር በመጋት የተነጠለ ምልከታ ማስረፅ እንደ ስትራቴጂ ተያይዘውታል፡፡ ውጤቱም ሐውልትን ያዋለደው ጥላቻና እልህ የተጫነው ፖለቲካዊ እርግማን በሚኒልክ ላይ ማዝነብ ሆኗል፡፡

የግማሽ ቀኑ የጨለንቆ ጦርነት …

“ከ1855 ጀምሮ ሐረርንና አካባቢዉን ይገዛ የነበረው ሼክ ሙሐመድ ኢብን ዓሊ ኢብን አብድል አል ሽኩር ይባል ነበር፡፡ እርሱም ለመጀመሪያ ጊዜ ራውፋ ፓሻ ከዘይላ መጥቶ ሐረርጌ ግዛት በገባ ጊዜ ተዋግቶ ነበር፡፡ ዳሩ ግን የግብፆቹ ትጥቅ ዘመናዊ ስለነበረ መመከት ባለመቻሉ ልጁን ሐጂ የሱፍን በቅድሚያ ልኮ ለግብፅ ከዲቭ ገባርነቱን መግለጽ ግዴታ ሆነበት፡፡ ነገር ግን የግብፅ ጦር ወደ ሐረር ከተማ ለመግባት ሲጓዝ በዙሪያው ያሉት ኦሮሞዎች የአላ፣ የጀርሲ፣ የባሊሌ፣ የአቡራ . . . ነገዶች ተሰብስበውና ጠንክረው በእግርም በፈረስም እየጋለቡ በጦርና በቀስት ሰባት ሰዓት ያህል ከግብፆች ጋር ተዋግተው በመጨረሻ ሲሸነፉ እነሱም እንደአገር ልማድ ሴቶቻቸውን ልከው መገበራቸውን አስታወቁ፡፡ ቀጥለውም መሪዎቹ በየተራ እየመጡ ለራውፋ ፓሻ እጃቸውን ሲሰጡ፤ የግብፅ ባንዲራ አሚሩ ቤት ላይ በገሃድ ተሰቅሎ ሐረር በግብፅ አገዛዝ ሥር መሆኑ ታወጀ” (ተክለ ፃዲቅ ፣ አፄ ዮሐንስና የኢትዮጵያ አንድነት ገጽ 287)፡፡

ሐረር በዚህ መልኩ በግብፅ ከተያዘች በኋላ ለአስር አመታት ያህል በግብፆች ተገዝታለች፡፡ በዚህ ጊዜ ምኒልክ በወሎ በኩል የጀመረውን አገር የማቅናት ዘመቻ ወደ ደቡብ ፊቱን እያዞረ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆንም ምኒልክ የሸዋ ንጉስ እንጂ ንጉስ ነገስት አልነበረም፡፡

በተክለፃዲቅ አገላለፅ ፍሬያማ በሆነው አየሩ ለሰውነት ተስማሚ በሆነው ሰፊ የሐረር ግዛት ላይ ፈረንሳይም ጣሊያንም የቅኝ ግዛት ምኞታቸውን ዓይን ሳይወረውሩ አልቀረም፡፡ ምኒልክ ስትጠብና ስትሰፋ የኖረችውን ኢትዮጵያን እያሰበ፣ መሐመድ ኢብን አሊ ጋዝ አህመድ (ግራኝ አህመድ) ከምስራቅ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ለ15/16 ዓመታት ጠቅልሎ የገዛትን ኢትዮጵያ እያስታወሰ ፊቱን ወደ ሐረር ቢያዞር በምን መለኪያ እንደ ግብፆች “ቅኝ ግዛት” ሊባል ይችላል?

ግብፆች በሐረርም በዘይላም በሌላውም የኢትዮጵያ ዙሪያ ግዛታቸውን ለአስር ዓመታት ቢያስፋፉም በሱዳን የመሃዲስቶች አጥቂነትና በኩፊት የኢትዮጵያዊያዉን አሸናፊነት የተነሳ ከፍ ያለ የኢኮኖሚ ውድቀት ስለገጠማቸው ያለ አስገዳጅ ጦርነት ሐረርን ለመልቀቅ ተገደዱ ፡፡ (ተክለፃዲቅን ያጤኗል)

በዚህ ጊዜ (ግንቦት 1878) የሐረር ተወላጅ ባላባቱ አሚር አብዱላሂ የሐረር ገዥ ሆነ፡፡ ጣሊያን ሐረር ላይ ዓይኗን ጥላ ነበርና ምኒልክ ጣሊያንን መቅደም ግድ አለው፡፡ አሚሩ ገዥ በሆነ በሰባተኛው ወር በወርሃ ታህሳስ 1879 የሚኒልክ አገር የማቅናት ዘመቻ ወደ ሐረር ፊቱን አዞረ፡፡

የአፄው የጦር ሜዳ ውሎ ዘጋቢ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ የጨለንቆን ጦርነት እንዲህ ይተርከዋል “. . . አሚር አብዱላሂ ዛሬ (ታህሳስ 29) በዓለ ልደት (ገና) ነውና ክርስቲያኖች አይሰለፉም /አይዋጉም/ ብሎ መክሮ ጦሩን ጠቅልሎ ሰናድሩን /ባለጠመንጃውን/ ከፊት መድፎቹን ከመካከል፣ ቀስተኛውን ከኋላ ከዚያ ቀጥሎ ፈረሰኛውን ጋሻኛውን አሰልፎ በአምስት ሰዓት ወደ ሰፈር መጣ ንጉሡ መነጥራቸውን ከዙፋናቸው ፊት አቁመው ሲመለከቱት ከሰፈር ማዶ ያለውን ቁልቁለት ወርዶ ከደኑ ለጅሐድ /ለቅዱስ ጦርነት/ ሲመጣ አዩት፡፡

በዚህ ጊዜ በቁጣ . . . ሰራዊታቸውን “ሄደህ በለው” ብለው አሰልፈው ሰደዱት፡፡ . . . አሚር አብዱላሂም መድፎቹን ማስተኮስ ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ከመኳንንትም ከቤት አሽከሮችም ከሰራዊትም አጫሪው ፈረሰኛ ሄዶ ገጠመው በዚያ ጊዜ ፅኑ ውጊያ ሆነ፡፡ የንጉሱ ሰራዊት መድፎቹን እጅ አድርጐ /ማርኮ/ አዞረበት፡፡ የግንባሩም ሲዘልቅና ሲገጥመው አሚር አብዱላሂ ድል ሆነ (ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምንልክ፤ ገጽ 145)”

“የተደበቁ የግፍ ታሪኮችን ፈልፍለን አውጥተናል” የሚሉን እነ ገመቹ መልካ እና ወልደ ዮሐንስ ወርቅነህ በውጊያው “አጤ ምኒልክ በእጃቸው በገባው የአውሮፓ ነፍጥ እንደልባቸው ቢጠቀሙም የኦሮሞ ልጆች ለሐገራቸው ነፃነትና ለክብራቸው ሞትን ሳይፈሩ እየተፋለሙ የጀግና ሞት ሞተዋል፡፡ ቅኝ ገዥዎች የኦሮሞን ልጆች ደም ረግጠው በማለፍ በድዋንበር ፈረስ መጋላ በሚባለው አደባባይና በአምስቱም (የሐረር) በር የንጉሱን ባንዲራ (የአቢሲንያን ባንዲራ) ሰቀሉ” (ኦሮሚያ የተደበቀው የግፍ ታሪክ፤ ገጽ 82) ይሉናል፡፡ እዚህ ላይ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ሐረር ላይ የግብፅ ባንዲራ ለአስር ዓመታት መውለብለቡን በቁጭት ስሜት ቀርቶ በለዘብተኝነት እንኳ በመፅሐፋቸው ውስጥ ያልገለፁልን እነ ገመቹ መልካ የንጉሱ (የአቢሲንያ) ባንዲራ ሐረር ላይ መውለብለቡን እጅግ በቁጭት ስሜት ይተርኩልናል፡፡ ሐቁ ግን የምኒልክን የደቡብም ሆነ የምስራቁን ዘመቻ በድል ፋና ወጊነት የተወጡት የመንዝ ገበሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ፈረሰኞቹ የሸዋ ኦሮሞዎችም ጭምር መሆናቸው ነው፡፡

ገመቹ መልካና ወልደ ዮሐንስ ወርቅነህ ከላይ በተጠቀሰ የጋራ መፅሐፋቸው የጨለንቆ ጦርነት ላይ 4000 (አራት ሺህ) ተዋጊ በአሚሩ በኩል እንደነበረ ይገልፃሉ፡፡ እውነት ነው፡፡ ሌሎች የታሪክ ፀሐፊዎችም የተሳታፊው ቁጥር ላይ ልዩነት አይስተዋልባቸውም፡፡ በጨለንቆ ጦርነት ላይ “አልቋል” የተባለው የሰው ህይወት መጠን ግን ዛሬም ድረስ አከራካሪ ነው፡፡ ኮብላዩ “ሚኒስተር” ጁነዲን ሳዶ “በጨለንቆ ጦርነት አንድ መቶ ሺህ የሀረር ሰዉ አልቋል” ይለናል፡፡ የሚጠቅሰዉ ታሪካዊ ሰነድ ግን የለም፡፡ ከርሱ የተሻለ የተቆርቋሪነት ስሜት ያላቸዉ እነ ገመቹ መልካ እንኳ ይህን በድፍረት አልጻፉም፡፡ ምኒልክ በድል አድራጊነት ሐረር እንደገባ አንድ አዋጅ አስነግሯል፡፡ “እስላሙና ኦሮሞው እንደ አባቱ ይደር” ይላል፡፡ ከዚህ አዋጅ ተነስተን በጦርነቱ ተሳታፊ ከነበሩት የአሚሩ ወታደሮች ባለፈ የከተማው ነዋሪ ላይ የደረሰ ውድመት ያለ አይመስልም፡፡ የከፋ ውድመት ቢደርስ በጊዜው ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ቦረሊ የተባለው የፈረንሳይ መንገደኛ ኢትዮጵያን በተመለከተ በፃፈው መፅሐፍ ውስጥ ጉዳዩን ለማካተት የሚቀድመው አልነበረም፡፡ ግማሽ ቀን ያልተሻገረው የጨለንቆ ጦርነት ወራትና አመታትን ከተሻገሩት የደቡብ (በተለይም የጉራጌ፣ የከፋ፣ የወላይታ፣ የሲዳማ . . .) ዘመቻዎች አኳያ (በንጽጽር ሲታይ) እዚህ ግባ የሚባል አይደለም (“የአንድ ሰው ሞት አሳዛኝ (ትራጄዲ) የብዙዎች ግን ቁጥር (ስታቲስቲክ)” ነውእያልን እንዳልሆነ ልብ ይሏል)፡፡ መቼም ኢትዮጵያ በጦርነት የተፈጠረች አገር ነችና ጦርነትን ከጦርነት ማነፃፀር ለኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ የመንግሥት ምስረታ (የስቴት ፎርሜሽንን) ባህርይን እዚህ ላይ ያጤኗል፡፡ ለዚህ ጦርነት መታሰቢያ በሚል ለነገ አገራዊ ዕዳ ሊያመጣ የሚችል “የመታሰቢያ ሐውልት” ሐረር ላይ በሃያ አምስት ሚሊዮን ብር ተገንብቷል፡፡ ያው የብሄርተኝነት መቀሰቻ ከሆነው አንዱ ከትላትን የሚጐተቱ መራር የጦርነት ታሪኮችን  በብዜት መልኩ ለትውልዱ መጋት ነው፡፡ (እ)የተገነቡ ያሉ ሐውልቶችም ከዚህ የተሻገሩ አላማ የላቸውም፡፡

የነገሩ ምፀት ደግሞ ከምኒልክ አገር የማቅናት ዘመቻ በኋላ አድዋ ላይ ወራሪውን የጣሊያን ኃይል በተባበረ ክንድ ድል የነሱት ኢትዮጵያውያን ከአርሲና ከሐረር የተውጣጡ ፈረሰኞች ፣ ቀስተኞች እና ጋሻኛ የድሉ ባለቤት (ተሳታፊ) መሆናቸው ነው፡፡

የእነዚህ ከሐረር – ዓድዋ ፣ ከአርሲ – ዓድዋ. . . በባዶ እግራቸው ዘምተው ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው የተዋደቁ የኦሮሞ አባቶችን የዓድዋ ተጋድሎ በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ ማወደስ አልሆንልህ ያላቸው የኦሮሞኛ ሙዚቃ  አርቲስቶች (ቀመር የሱፍና ሹክሪ ጀማል) “ምኒልክ የአፍሪካ ሂትለር” ብሎ ለመዝፈን ግን አይሰንፉም፡፡ ነገሩ ግልፅ ነው! ዓድዋ ላይ ከአዋጊነት እስከ ጭፈራ ከፈረሰኛ እስከ እግረኛ ድረስ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በመዋደቅ ኮከብ ሆነው የዋሉትን የኦሮሞ አባቶች በኦሮምኛ ሙዚቃ ማወደስ ጠርዘኛው የኦሮሞ ብሄርተኝነት ዋነኛ ማጠንጠኛ የኦሮሞን ጥያቄ በፀረ ቅኝ ግዛት ትግል ውስጥ የሚቀነብበው በመሆኑ ከ“ቅኝ ግዛት” ሃቲቱ ጋር በቀጥታ የሚላተም በመሆኑ ዓድዋን የሚያስታውሱ (የሚዘክሩ) የኦሮምኛ ሙዚቃዎችን ልናዳምጥ አልታደልንም፡፡

ለጠርዘኞቹ የኦሮሞ ብሄርተኞች ፕሮፌሰር ሬይሞንድ ጀናስ የኦሮሞዎች የዓድዋ ተሳትፎ ራሱን በቻለ ሬጅመንት የሚታይ እንደሆነ “The Battle of Adwa, African victory in the age of Empire” ሲል በሰየመው መፅሐፉ የሚገልፀው ነገር አይዋጥላቸውም፡፡ የኦሮሞ ፈረሰኞች በዓድዋ ጦርነት ጊዜ “ወደ ሸለቆው ሲወርዱ በድንገት የገነፈለ ጥቁር ባህር ይመስላሉ” በማለት ጀግንነታቸውን የገለጹበት መንገድ ለእነርሱ “የአቢሲንያ ተረት ተረት ነው”፡፡

አለመታደል ሆነና ለጠርዘኞቹ የኦሮሞ ብሄርተኞች ዓድዋ ላይ የዘመቱት የቀደሙት የኦሮሞ ተዋጊ አባቶች፤ ምኒልክ በርቀት መቆጣጠሪያ እያሽከረከረ የሚያፋልማቸው ሮቦት እንጂ ራሳቸውን ችለው፤ ማንነታቸውን ጠብቀው የተዋደቁ ብርቱዎች አይመስሏቸውም፡፡ በራሳቸው የቆሙ ብርቱዎች እንደነበሩ ቢያምኑማ የ“ቅኝ ግዛት” ሃቲትን ሲያነበንቡ ባልኖሩ ነበር፡፡ ይሄው ውድቅ አመለካከት አድዋን የመሰለ ወታደራዊ ድል ወደ ፖለቲካዊ ድል እንዳንቀይረው እንቅፋት ሆነብን!! ዛሬም በየጥጉ “የእኛስ የጉድ ነው” እያልን እናላዝናለን፡፡

የእርግማን አንድ፡ ማሳረጊያ

አርሲና ሐረር ሌሎችም የደቡብ አገር የማቅናት ዘመቻዎች በሁለቱም ወገን የደም ዋጋ ባስከፈሉ ውጊያዎች የተጠቃለሉ እንጂ በብላሽ ስጦታ (ወደው የገቡትን ሳንዘነጋ) ወይም በህዝብ ውሳኔ ወደ ምኒልክ ግዛት የተጠቃለሉ አይደሉም፡፡ በወቅቱም ሰብዓዊ ጥሰቶች በገባሪው ወገን አልደረሱም ብሎ መከራከር ትርፉ ጉንጭን ማልፋት ነው፡፡ ምኒልክ በደቡብ ዘመቻ እጅ/እግር አልቆረጠም ብሎ በጨበጣ መከራከር የትም አያደርስም፡፡ ቀርቶ የታሪክ መዛግብት ማገላበጥ፤ በትንሹም ቢሆን “ፍትሐ-ነገስት”ን ማስታወስ የአባት ነው፡፡

የወደረኛውንና ጭፍራውን እጅ/እግር መቁረጥ በምኒልክ ጊዜ የተጀመረ ድርጊት ሳይሆን የዘመናዊት ኢትዮጵያ የታሪክ አባት የሆኑትን ሁለቱን የቀደሙ ነገስታት (ቴዎድሮስና ዮሐንስ) ጨምሮ የፊት መሳፍንትም ሆኑ ነገሥታት ፈጽመውታል፡፡ ከቶም አንዳንዶች አፍንጫ እስከ መፎነን፣ ምላስ እስከ መቁረጥ ደርሰዋል፡፡ (መስለብማ በየትኛውም መሳፍንት “የወግ” ነበር)፡፡

በጉልበት ሌላውን ማስገበር በመፈራረቅ የተከወነ ድርጊት ነው፡፡ በመስመር መሐል በመካከለኛው ዘመን የተካሄደውን የኦሮሞ መስፋፋት የፈጠረውን እልቂት የአባ ባህሪን፣ የአለቃ አጸሜንና የአለቃ ታየን ሥራዎች እያጣቀሱ ሁኔታዎችን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ የታሪክ ሰነድ ባለሃብቱ ዶ/ር መርዕድ ወልደ አረጋይ ከዛሬ 45 ዓመት በፊት ለሦስተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ማሟያው ያዘጋጀውን ጽሁፍ “Southern Ethiopia and the Christian kingdom 1508 – 1708, with special Reference to the Galla Migration and Their consequences” ላይ የተካተቱትን ወሳኝ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጦች መገምገሙ ለጋራ ቤታችን ይበጃል፡፡

“ሞጋሳ” እና “ጉዲፈቻ” በተሰኙ ማህበራዊ ሥርዓቶች የባህል ቅቤ ማቅለጫ ድስት (melting pot) ውስጥ የገቡትን የህብረተሰብ ክፍሎች ማሰብ ልንዘነጋው አይገባም፡፡ ኦሮሞ በመካከለኛዉ ዘመን ሲስፋፋ የተዋጡ የማህበረብ ክፍሎችን ክዶ መከራከር የሚያዋጣ አይደለም፡፡

በነዚህና መሰል ጉዳዮች ውስጥ ኦሮሞ ገዥም ተገዥም ነበር፡፡ አስገባሪም ገባሪም ነበር፡፡ ቀላጭም አቅላጭም ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ዛሬ ላይ ኦሮሞ መስፋፋቱን ተከትሎ ከሟሟበት የገዳ ሥርዓ ውጪ ሌሎች የዘውጉ ማንነቶች ከሞላ ጐደል ህያው ናቸው፡፡ ይልቁንስ ኢትዮጵያን ቀስቶ በማዋቀሩ ረገድ በማህበራዊውና በኢኮኖሚያዊው መስክ ይበልጥ አቃፊ ደጋፊ ሆኗል፡፡ ተጠቃሚነቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ቢወድቅም ቅሉ፡፡ ፖለቲካዊ ተሳትፎው ግን ዛሬም ድረስ የዛለው ጠርዝ የታከከው የልሂቃኑ ጉዞ ውጤት ነው፡፡ መቼም በጥንቸሎች የታሰረው ዝሆኑ ኦህዴድን እንደ ወሳኝ የፖለቲካ ድርጅት የመቁጠር ግዴታ የለብንም፡፡

አሜሪካውያን ከሚያከብሯቸው መሪዎቻቸው መካከል አብርሃም ሊንከን አንደኛው ነው፡፡ ጭራሹኑ እስከ መመለክ የደረሰ መሪ ነው፡፡ ይሁንና የደቡብ ግዛቶች ከሰሜኑ ለመገንጠል ጦርነት በከፈቱበት ወቀት አብርሃም ሊንከን የአንድነቱ ጠበቃና መሪ በመሆን ከፍተኛ ጦርነት መርቷል፡፡ በዚህ ጦርነት ስፍር ቁጥር የሌለው ህዝብ አልቋል፡፡ አብርሃም ሊንከንን ግን አሜሪካዊያን በፀረ ህዝብነት አለያም በጨፍጫፊነት ሲያነሱት አይታይም፡፡

ለማናቸውም የኢትዮጵያ ዘመናዊ አገር ግንባት ሂደትና ፈተናዎች በዚያን ጊዜዋ ኢትዮጵያ መቼት ውስጥ ተቀምጣ መታየትና መመዘን ይኖርባታል፡፡ አባ ዳኘው-ምኒልክም የዛሬ ዘመን መሪ ሳይሆን የራሱ ዘመን መሪ ነው፡፡ የንግስና ዘመኑ የሚመዘነው በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች መመዘኛ ነጥቦችን በተንተራሰ ሳይሆን እንደ ጊዜው ማዕቀፍ መታየት ግድ ይለዋል፡፡

ቻርለስ ቲሊ “ጦርነት አገርን ይወልዳል፤ አገርም ጦርነት ይወልዳል” ሲል የተናገረውን ኃይለ ቃል መምዘዙ እንድንግባባ ዕድል ይሰጠን ይሆናል፡፡ ካልሆነም የጀርመን አባት ቢስማርክ (አገራት በብረትና በደም ይመሠረታሉ) “states are formed by iron and blood” በማለት በተግባር አገሩን ለማዋሃድ የተጓዘበትን መንገድ ማስታወሱ የምኒልክን አገር የማቅናት ዘመቻ ግልፅ ያደርግልናል፡፡

በዚህ አግባብ ምኒልክ ከአገር መሃንዲስነቱ አኳያ “ነፍጥና መስዋዕትነትን” የአገር ማዋሃጃ ስልት አድርጎ የተጠቀመበትን መንገድ በትይዩ አስቀምጠን ስናይ ምኒልክ ለ“ሂትለር” ሳይሆን ለቢስማርክና ለአብርሃም ሊንከን ይቀርባል፡፡ ቆራጥ ዘመቻዎቹን ስንመረምር ደግሞ “እምዬ” የሚለውን የቁልምጫ ሥሙን ለመቀበል ይቸግረን ይሆናል፡፡ ምኒልክ “እምዬ” ቢቀርበት እንኳ የአገር ምህንድስና ዉሉ በደንብ የገባው states Man ነው፡፡ በምኒልክ ሃውልት ላይ ተጽፎ እንደሚነበበው ጽሁፍ “ከትልቅ ወይም ከትንሽ ቢሆን መወለድ ሙያ አይደለም ራስን ለታላቅ ታሪክ መውለድ ግን ሙያ ነው”፡፡

እናም ሊንከን በአንድነት ጠበቃ ደግፎ ባቆያት አሜሪካን አገር ሚኒሶታ ግዛት አልያም ቢስማርክ በተዋደቀላት ጀርመን፤ በርሊን ውስጥ ሆት ዶግ እየበሉ፤ የካልዲስን ቡና እንደ ወረደ እያጣጣሙ ምኒልክ በነፍጥና በመስዋዕትነት ያቆማትን አገር ቢሳካ ለመግዛት ካልሆነም ለመገንጠል እየታገሉ “ምኒልክ ሂትለር ነው” ቢሉ አንድም ርባና ቢስ የትውልድ ፖለቲካዊ ርግማን ነው፤ ሌላም አላዋቂነትን በአደባባይ መግለጥ ነው፡፡

እርግማን ሁለት፡ “ምኒልክ ኤርትራን ሸጠ፤ ትግራይን በደለ”

በቀጣይ ዕትማችን የምንዳስሰው ጉዳይ ይሆናል!!


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

121ኛው የአድዋ ድል በአል በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ። – ዘላለም ደበበ

$
0
0
በአውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ማርች 4 ቀን 2017 በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ የሚገኙ የፖለቲካና የሲቪክ ማህበራት በጋራ በመሆን ባዘጋጁት የአድዋ ድል መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ከሁሉም እድሜና ፆታ የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን በቦታው በመገኘት በጋራ አክብረዋል። ዝግጅቱ ከቀኑ 15:00 ሰዐት ላይ የጀመረ ሲሆን አቶ የወንድወሰን አናጋው ለታዳሚዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ የእለቱ ዝግጅት መጀመሩን አብስረዋል። በመቀጠልም የአድዋ ድልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ እጅግ መሳጭ እና ስሜት ቀስቃሽ የሆነ ዶክመንተሪ ፊልም በስክሪን ለታዳሚው ተለቆ የአድዋ ድል የመላው ኢትዮጵያውያን ብሎም የጥቁር ህዝቦች ትልቅ ድል መሆኑ ታይቷል። በማስከተልም የዚህ ታላቅ ድልን የሚዘክሩ እና ተመልካቹን በኩራት ያስፈነደቁ ግጥሞች በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ገጣምያን አቅርበው የሻይ እረፍት ተደርጓል። ከእረፍት መልስም ኮንት አንቶኖሊ ከወራሪው የኢጣልያ መንግስት ይዞት የመጣውንና ንግስት ጣይቱ በኩራት ልበሙሉነቷን ያሳየችበትን የውጫሌ ውል አንቀፅ 17 የተመለከተው አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ በብቃት የተወነችበት ቲያትር ተቀንጭቦ ቀርቦ ለታዳሚው ትልቅ መንቃቃትን ፈጥሯል። በማስከተልም ሀገሩን ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ ባንዳ ዛሬ በወያኔ መንግስት ብቻ ሳይሆን ቀድሞም የነበረ መሆኑን የሚያሳይ በማስረጃ የተደገፈ ፅሁፍ በአቶ ጥላሁን ቀርቦ የእለቱ የመወያያ አጀንዳ የሆነው እና ለውይይት የተመረጠው ፅሁፍ ” የአድዋ ድል በአል ቀጣይነት ኖሮት ለመጪው ትውልድ እንዴት ይተላለፍ? ከእኛስ ምን ይጠበቃል? የተናጠል እንቅስቃሴያችንንስ ወደ አንድ ለማምጣት በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ምን ማድረግ አለብን?” የሚል የመወያያ ፅሁፍ በወይዘሮ አሳየሽ ታምሩ ቀርቦ መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆኗል። ታዳሚዎቹም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ድንቅ ውይይት አድርገውበት የእለቱ ፕሮግራም ፍፃሜውን አግኝቷል።

የመረጃ ግብአት …. ሳውዲ አሰሪዎች የሰራተኞቻቸውን ፖስፖርት በ1 ወር እንዲመልሱ ተጠየቀ ! – ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* ” አሰሪዎች በአንድ ወር ጊዜ ፖስፖርትን ለሰራተኞች ያስረክቡ ”
* ማስጠንቀቂያና ጥያቄውን ያቀረበው የሰራተኛ ሚኒስቴር ነው
* ባሳለፍነው ሐምሌ አሰሪዎች የሰራተኞችን ፖስፖርት እንዲያስረክቡ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር
* ያላስረከበ 2,000 የሳውዲ ሪያል መቀጫ የተጣለ ቢሆንም የወጣውን ደንብ በርካቶች መተላለፋቸው ተደርሶበታል
* አዲስ በወጣው የአንድ ወር ገደብ ለሰራተኞች ካላስረከቡ “የከበደ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ” ይላል የወጣው መረጃ
* የሳውዲ መንግሰት “ከፋላ ” ተብሎ የሚጠራውን የአሰሪ የቆየ አሰራር ለመቀየር ጥናት እያደረግ መሆኑ ተጠቁሟል

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ ቀደም ከአሰሪዎቻቸው የጠፉ ሰራተኞች ፖስፖር ለሪያድ ኢንባሲና ለጅዳ ቆንስል የተሰጠ ቢሆንም በርካታ ኢትዮጵያውያን የግል መለያ ሰነዳቸው የሆነውን ፖስፖር ለማግኘት ችግር እንደገጠናቸው በምሬት ይናገራሉ ። ፖስፖርትን በመመለሱ ረገድ የሪያድ ኢንባሲ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረጉ ሲጠቀስ የጅዳ ቆንስል ግን በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ይዞ ለባለቤት ዜጎች ለማከፋፈል ተደጋጋሚ ቃል ገብቶ ነበር ። ያም ሆኖ ላለፉት በርካታ ወራት ፖስፖር ማከፋፈል አልመጀምሩን ዜጎች በምሬት ይናገራሉ ።

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
የካቲት 26 ቀን 2009 ዓም

ዛሬ ለ 52ኛ ጊዜ ተቀጥሮ የነበረው የዞኝ ዘጠኝ ጦማሪያን የተጠየቀውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል

$
0
0

ዛሬ ለ 52ኛ ጊዜ ተቀጥሮ የነበረው የዞኝ ዘጠኝ ጦማሪያን በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት) የአቃቤ ሕግ ይግባኝ የክስ ሂደት በበፍቃዱ ኃይሉ ላይ የተጠየቀውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል፣ በፍቃዱ ኃይሉ የሽብርተኝነት ክሱ ወደ አመጽ ማነሳሳት መቀየሩ የሚታወስ ነው በዚህም መሰረት የቀሪዎቹ ጦማሪያን ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለ53ኛ ጊዜ ለመጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
የበፍቃዱ ኃይሉ የክስ ሂደት በከፍተኛው ፍርድቤት እንዲከላከል በተወሰነው መሠረት ይቀጥላል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ክስ ሲጠናቀቅ አጠቃላይ ሂደቱ ላይ አቃቢ ሕግ ይግባኝ መጠየቅ እንደሚችል የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በይኗል።

Zone9
·

 

የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ደኅንነት ጉባኤ አማካሪ ዴቪድ ሽታይንማን የኢትዮጵያ መንግሥት ሹማምንት ሥልጣን ከተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ 30 ቢሊዮን ዶላር መዝብረዋል

$
0
0

DW – Amharic

የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ደኅንነት ጉባኤ አማካሪ ዴቪድ ሽታይንማን የኢትዮጵያ መንግሥት ሹማምንት ሥልጣን ከተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ 30 ቢሊዮን ዶላር መዝብረዋል ሲሉ ወነጀሉ። ዴቪድ ሽታይንማን ፎርብስ በተሰኘው የቢዝነስ ጋዜጣ በእንግድነት በፃፉት ሰፊ ኃተታ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ የተመዘበረውን እኩሌታ 30 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ከዩናይትድ ስቴትስ ተቀብሏል ብለዋል። አሜሪካ እና የተቀረው ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጉዳዩን ቸል ብሎታል ያሉት ሽታይንማን ችግሩ ከተጠያቂነት እጦት ይመነጫል ብለዋል። ትናንት አርብ በፎርብስ ጋዜጣ ላይ ለንባብ የበቃው ይኸው ፅሁፍ ፌስቡክ እና ትዊተርን በመሳሰሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በስፋት እየተሰራጨ ነው።

 

” ሕወሃት ከደርግ የባሰ ነው ” የቀድሞ የሕወሃት ታጋይ #ግርማ_ካሳ

$
0
0

ሕወሃት ሕዝብን የሚያገለግል ሆስፒታ እንዳይሰራ ማገዱን መረጃዎችን እየሰማን ነው። ምክንያት የሆስፒታሉ ባለቤት፣ ዶር ማርቆስ ገሰሰ የህወሓትን ዛቻና ማስፈራርያ ሳይበግራቸው፣ በሕወሃት ለየተበደሉትን የሚደገፍ፣ ሕወሃት ለሕዝብ ተጠያቂ እንዲሆን የሚታገሉትን እድነ አራና ያሉትን የሚደግፉ ኢትዮጵያዊ ናቸው። የአረና ሊቀመነበር አብርሃ ደስታ እንደ ጦንመረው ዶር ማርቆስ “ከተበደለ ህዝብ ጎን የሚቆሙ፣ ለዓረና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የሚሆን ክፍል በነፃ የሰጡና ገንዘብ ለሌላቸው ዜጎችም ነፃ ህክምና ያደርጉ የነበሩ ዜጋ ናቸው።

በዉጭ አገር የአረና ደጋፊ የኩኑ መስፍን፣ በዶር ማርቆስ ላይ የተወሰደዉን እርምጃ፣ በአንዲት የቀድሞ የሕወሃት ሴት ላይ የደረሰውን ግፍን እንዳስታወሰው ገለጾ፣ የአሁኑ የሕወሃት ስርዓት ከደርግ የባሰ መሆኑንም ለማሳየት ሞክሯል። የይኩኖን ጽፉ እንደሚከተለው አስፍሪያለሁ

=========
የኩኖ መስፍን)(
ዶ/ር ማርቆስ ገሰሰ ላይ የደረሰው ጥቃት፣ ዓረናን ለማስቆም ብሎም ለማጥፋት እየተደረገ ያለ የነበረ ፍፁም ፀረ ህዝብ ፀረ አገር ፀረ እድገት እርምጃ ነው።

በአንዱ የትግራይ ዞን የሆነ ታሪክ ልንገራቹ። አንዲት ህወሓት ታጋይ የነበረች ሴት ተገፍታ ከተጣለች በኋላ፣ በቤተሰብ እርዳታና በራስዋ ብርታት ምግብ ቤት ታቋቁማለች። ስራዋ ጥሩ ስለነበር ደህና መንቀሳቀስ ጀመረች።

ከጊዜ በኋላ አንድ ቀን እነዚ ገቢዎች የሚባሉ ይመጡና ግብር ክፈይ ይሉዋታል። እሷም “ግብር መክፈል ጀግንነት ነው” ትላለች ፣ ለመክፈል ተዘጋጅታ። “መቶ አምሳ ሺህ ብር መክፈል አለብሽ” ይሏታል። ሴትየዋ ደንግጣ ማመን አቃታት። ” አይ ስለ ግብር መሰለኝ የምትጠይቁኝ። አጠቃላይ ገቢየ እና ንብረቱ ቢገመት እንኳ ይህን ያህል ገንዘብ አያወጣም” ትላለች።

ግድም አልሰጣቸው፣ ውሳኔ ያሳልፋሉ። በጭፍንና በእቢርት። “ካልከፈልሽ ይታሸጋል” ብለዋት ሄዱ።

ሴትየዋ ጨንቋት ወደ ሚመለከተው የበላይ ባለስልጣን ሄድች። ጉዳይዋን አቤት አለች። ጉዳይዋ ይታይላት ተብሎ አምሳ ሺህ ቀንሰው መቶ ሺህ ብር ክፈርይ አሏት። ሴትየዋ ” አሁን ይሄም ሊሆን አይችልም። የለኝም” አለች። ሰሚ ግን ዬም። “ይታሸጋል” ተብላ የመጨርሻ ውሳኔያቸዉን ሰጧት።

“የዞን ካብኔ በተሰበሰበበት፣ አናግሩኝ” ብላ ጥያቄ አቀረበች። እድልም ተሰጣት። ” በእውነት ከናንተ በደርግ ዘመን ይሻል ነበር” ብላ እቅጩን ነገረቻቸው። “ምን ማለትሽ ነው ? ትታሰሪያለሽ ” ስትባል፤ አዎን እሰሩኝ፤ ሌላም ማድረግ ትችላላቹ። ግን ልንገራቹ ደርግ ህዝብን ሲበድል ህዝቡ አቤት የሚልበት ሲያጣ ደርግ ወደ ማይቆጣጠረው ቦታ ይሄዳል። ለትግል ይወጣል። መሮት። አሁን ግን የት እንሂድ? በቃ ይኸዉላችሁ ቁልፉ፣ ዝረፉኝ፣ ውረሱት። ሌላ አቅም የለኝም” አለች።

መምህር ጎይቶም ፀጋይ እንይ በተምቤን የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነበር። እሱ በሌለበት ማስታወቅያ አውጥተው ከመማር እና ከማስተማር ጋር በፍፁም በማይገናኝ መልኩ አባረሩት። የአረና አመራር ስለሆነ ብቻ።

የአሁኑ የዓረና ምክትል ሊቀመንበር ጎይቶም ፀጋይ። አዲስ አበባ ማስተርስ ዲግሪውን እያጠናቀቀ ይገኛል። ሰነፍ መምህር የዓረና አባል አይሆንም። ሰነፍ ሃኪም የአረና አባል አይሆንም። ሰነፍ ነጋዴ ህወሓትን አይቃወምም። ሰነፍ ወደ መንግስት ይጠጋል። አባልነቱ ለህልውና እና ለስራው ዋስትናው ነው። በራሱ የሚተማመን ብቁ ሰው እንደነ ደ/ር ማርቆስ አይነተቹ። እንደነ ጎይቶም ፀጋይ ሌሎች በርካታ የዓረና አባላትና አመራር አይፈለጉም። በሰበብ አስባቡ ማራቅ ክህብረተሰብ መነጠል ማባረር ማሰር ነው። በደ/ር ማርቆስ ሆስፒታል የተደረገው ይህ ነው። በጣም ያሳፍራል። አሁንም ወደኋላ።

ሆስፒታል አቋቁመው ሕዝብን ሲያገለግሉ የነበሩ ዶር ማርቆስ እኝህ ናቸው።

ህ.ወ.ሓ.ት በዶ/ር ማርቆስ ላይ የተለመደውን የበቀል ብትሯ እንዳሳረፈች ዛሬ ሰማን፤ – ሴቭ አድና

$
0
0


በ15 ዐመት ለ15 ሺሀ መጠጥ ቤቶች፤ ለ3000 በላይ ጫትና ሺሻ ቤቶች ፍቃድ የሰጠች ህ.ወ.ሓ.ት መቐለ ውሽጥ ቀደምት ከሚባሉና በሕዝብ ዘንድ መልካም ስም ካተረፉ የግል ጤና ተቋማት አንድ የሆነውን የድሮ ዶ/ር ማርቆስ ሆስፒታል (የአሁን ማርቆስ የውስጥ ደዌ የሕክምና ማዕከል)ን ዛሬ መዝጋታቸውን ሰማን፡፡ እጅግ አሳፋሪና የስርዐቱ ዐይን ያወጣ ዕብሪት፣ ስሜታዊነት፣ አላዋቂነትና ድድብና ማሳያ ነው፡፡
ደ/ር ማርቆስ የዐረና አመራር አባል ሆኖ የተመረጠው ከጥቂት ሳምንታት በፊት በተደረገው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ነው፡፡ በንዴት የሚይዘው የሚጨብጠው ያጣው ህ.ወ.ሐ.ት የጤና ቢሮ ካድሬዎቹን ልኮ ሆስፒታሉን አዘጋ፡፡ ህ.ወ.ሐ.ት ያደረበትን ከፍተኛ ብስጭት ለመደበቅ እንኳ አልተቻለውም፤ ቢቻለውማ ኖሮ ሁለት ሶስት ወር ቆይቶና አረሳስቶ ይህንን ማድረግ ይችል ነበር፡፡ የህ.ወ.ሐ.ት አመራር ግን በአስተሳሰብ ያበሰሉና መቼም የማይበስሉ፣ ግብዝና ስሜታዊ ህጻናት መሆናቸውን ያሳዩበት ነው፡፡
የጤና ቢሮ ሰዎች ይህንን እርምጃ ለመውሰድ ሆኑን ብለው ያቀረቧቸው 4 ምክንያቶች ከእውነት የራቁ እንደሆኑ ነው ዶ/ር ማርቆስ የሚገልፁት፤

1. “21/06/09 ዐ.ም ላይ ድንገት ለኢንስፔክሽን ከጤና ተቋሙ በሄንድንበት አጋጣሚ ባለቤቱ ከቦታው አልነበሩም”፡፡ እጅግ አስቂኝ ምክንያት ነው፤ የክልሉ ጤና ቢሮ በመንግስት ሆስፒታል የሚሰሩ ሰዎች በትርፍ ሰዐታቸው በግል የጤና ተቋማቸው እንዲሰሩ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በማንኛውም ሰዐት በጤና ተቋሙ መገኘቱ ግድ አይደለም፤

2. “የሙያ ፍቃድሕን ለሌላ ሰው አከራየህ”- ዶ/ር ማርቆስ ይህ ፍጹም ሐሰት እንደሆነና የገዛ ሙያ ፍቃዳቸው ከዘከያው ከሆስፒታሉ ተንጠልጥሎ እንደሚገኝ ይህንንም ማንኛውም የመቐለ ነዋሪ ሄዶ ሊያረጋግጠው የሚችል ሐቅ እንደሆነ ይገልፃሉ፤

3. “ለላብራቶሪ አውለዋለሁ ያልከውን ክፍል ለተገቢው ግልጋሎት አላዋልከውም”፤ ዶ/ር ማርቆስ በቂ የላብራቶሪ ክፍል እንዳላቸውና መመሪያው የሚያዘው ሁሉ ከበቂ በላይ እንዳሟሉ ይገልፃሉ፤

4. “ድንገተኛ/ኢመርጀንሲ ክፍልህ ላይ ስሚንቶ አገኝን”፤ የዶ/ር ማርቆስ መልስ “ከበቂ በላይ የድንገተኛ ሕክምና ክፍል አለኝ፤ በማስፋፊያ ግንባታ ላይ ስላለሁ ከስቶር ክፍሌ ስሚንቶ መገኘቱ ምንም ወንጀል የለውም፤ ኢመርጀንሲ ክፍል ላይ የተቀመጠ ምንም ስሚንቶ የለም”፤

እነዚህ ምክንያቶች አንድም ውሸት ናቸው፤ ሁለትም እውነት ቢሆኑ እንኳ በማስጠንቀቂያ ሊታለፉ የሚችሉ እንጂ አንድ ትልቅ የሕክምና ተቋምን ለአንድ ዐመት የሚያዘጉ አይደሉም፡፡
በእውነት እንዴት ያለ ዐይን ያወጣ ዕብሪነት ነው!

የመቐለ የግል ጤና ዘርፍ በዋናነት ለአንድ የህ.ወ.ሐ.ት ሰው የተሰጠ እንደሆነ የመቐለ ሰው ያውቃል፡፡ ለዚህም ምስክሩ 33 የት.እ.ም.ት (EFFORT)፣ የመንግስት ደርጅቶች ላለፉት 20 ዐመታት ሁሉም ያለምንም ጨረታ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዚሁ የኢህአዴግ ቅርብ ሰው ጋር የሕክምና ውል እንዲያስሩ መደረጉ፤ ከመሬትና ከብድር ጋር ተያይዞ ያለው ነገር፣ ሌላ ብዙም ብዙም…እሱ እሱ አንድ ቀን የምንጠያየቅበት ጊዜ ይመጣል፡፡

በሕ.ወ.ሐ.ት ቤት ምንም ነገር ሊፈፀም እንደሚችል ሁላችንም እናውቀዋለን፤ እንዲህ ዐይነቱ ያፈጠጠ ያገጠጠ የአደባባይ ውንብድና፤ ሊያውም በሕክምናው ዘርፍ ላይ…ይህ ግን ፈፅሞ የማይታመንና ህ.ወ.ሐ.ት ያለበትን የውዥንብር ህይወት ፍንትወ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

ሆነም ቀረ ግን…በ15 ዐመታት ለ15 ሺህ መጠጥ ቤቶችና ለ3ሺህ ጫትና ሺሻ ቤቶች ፍቃድ የሰጠ የትግራይ ክልል አስተዳደር ዶ/ር ማርቆስ ሆስፒታልን ለአንድ ዐመት ዘግቷል ፤


ተቃዋሚዎች ለምን መጠንከር አቃታቸዉ? – ሸንቁጥ አየለ

$
0
0

ተቃዋሚዎች ትናንት ተዋቀሩ ሲባል ዛሬ ተበተኑ የሚል ዜና ይመጣል::ከአምሳ እና ስልሳ አመታት በላይ የተመሰረቱትም ዛሬም ፈንግል እንደሚያንገዳግዳት ጫጩት ይወዛወዛሉ::

ትናንት ሽቅብ ስማቸዉ የተተኮሰዉ ተቃዋሚዎች ዛሬ ስማቸዉ ወደ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ተወርዉሮ ማንም ዞር ብሎ እንዳያዬዉ የታደመበት ይመስላል::

መተማመን: መደማመጥ: በአንድ መርህ መመራት: ከግለሰባዊነት ይልቅ ሀገራዊነት ብሎም ከፓርቲያዊነት ይልቅ ህዝባዊነት ከተቃዋሚዎች አንባ ብትፈለግ አልገኝ ስትል ህዝቡ ተቃዋሚዎችን ይወቅሳል::ተቃዋሚዎች ትናንት ተመስርተዉ አምሳ አመት የታገለዉን ፓርቲ ሁሉ በቂጡ ዘጭ ያደርጉና ከኛ በላይ ላሳር ብለዉ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላሉ::ግን ላንድ ሰሞን ነዉ:: ከዚያማ ኩምሽሽ ነዉ::

ህዝቡ ተቃዋሚዎችን ይወቅሳል እንጅ እራሱን ወቅሶ አያዉቅም:: ወይም ደግሞ ተቃዋሚዎች እያነገቡት የሚነሱት ጥያቄ የራሱ የህዝብ ጥያቄ መሆኑን አምኖ አያዉቅም:: ዝም ብሎ ግን ከተቃዋሚዎች የሆነ ታምር ይጠብቃል:: ተቃዋሚዎች ለምን መጠንከር አቃታቸዉ? የሚል የለም::ህዝቡ አንድ የሚጠይቃት ጥያቄ አለች:: “ማንኛዉ ተቃዋሚ ነዉ ጠንካራዉ? እንድንደግፈዉ ጠንካራዉን ፓርቲ ማወቅ አለብን::” ይላል:: “የጠነከረዉን መደገፍ ምን ያስፈልጋል?” ብሎ ከህዝቡ መሃል የሚጠይቅ ግን የለም::

ህዝቡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የራሴ ጉዳይ ነዉ ብሎ እስኪቀበል እና በቀጥታ እራሱ መሳተፍ እስኪጀምር ድረስ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ እንደ ተረት ተረት ሆና ትቀራለች እንጅ ከቶም እዉን አትሆንም:: ይሄኛዉ ዘመን ከቀደመዉ ዘመን የተለዬ ነዉ:: ጥቂት አቢዮተኞች ተነስተዉ: ጥቂት ባለ አዕምሮዎች ፊታዉራሪ ሆነዉ: ወይም አንድ ድርጅት ህዝብን በፕሮፖጋንዳ አሳምኖ ለዉጥ የሚመጣበት ወቅት አይደለም:: ወይም ደግሞ የሶሻሊስት አቢዮት ዘመን ሲከተለዉ እንደነበረዉ ስልት ህዝብን በማስገደድ እና በመቀጥቀጥ ብሎም በተራቀቀ ፕሮፖጋንዳ ህዝቡን በአንድ ፓርቲ ስር ማሰባሰብ አይቻልም::

ብዙዉ ነገር ተወሳስቧል:: አለማቀፋዊ ትሥስሩ ጠንክሯል:: የቴክኖሎጅ ምጥቀቱ ለብዙ ቡድኖች እና ፓርቲዎች(ለመልካሞቹም : ለመጥፎዎቹም) እኩል እድል ፈጥሯል:: እንዲህ አይነቱን ዘመን በህዝብ ቁጥጥር ስር ካልገባ ለአጨናባሪዎች እና ሀብት በእጃቸዉ ላይ ለገባ አናሳ ተንኮለኛ ሀይሎች ምቹ ነዉ:: ህዝቡ የሀገሪቱ ፖለቲካ የራሴ ነዉ ካለ ብቻ የዲሞክራሲን ትሩፋት መመገብ ይቻላል:: አለዚያ ግን ዲሞክራሲ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ ነዉ::

አሁን ባለዉ ሁኔታ ህዝቡ እንኳን የኢትዮጵያን ፖለቲካ በባለቤትነት ለመያዝ ቀርቶ ፖለቲካ ለማራመድ የሚነሱ ያርቲዎችን በዝምታ ነዉ የሚያስተዉላቸዉ:: ከሁሉም የሚገርመዉ ደግሞ ከላይ እንደተባለዉ በርካታዉ ሰዉ :ማንኛዉ ቡድን ነዉ ጠንካራዉ?” እያለ ጠንካራ ቡድን በማነፍነፍ እራሱን ሲያደክም ይዉላል::

ጠንካራ ቡድን ከዬት ይመጣል? በህዝብ ያልተደገፈ ተቃዋሚ እንዴት ጠንክሮ መቆም ይችላል? ትግሉ የሰዉ ሀይል:የገንዘብ አቅም: የተቋማት ምስረታ: የመረጃ ሀብት እና ሌሎችም ብዙ የሚያስፈልጉት ግብአቶች አሉ:: ተቃዋሚ ፓርቲ የሚመሰርቱ ሀይሎች ጥቂት ወገኖች ተሰባስበዉ ባሊያዙት ግብዓት በጨበጣ ወደ ትግል ሜዳ ይገባሉ:: ሆኖም የሚያርፍባቸዉ ምት ብዙ ነዉ:: ሆኖም የሚረዳቸዉ የለም:: ከዉጭ ሀይላት እስከ አንባገነኑ ወያኔ ድረስ የሚበታትናቸዉ ነገር ብዙ ነዉ:: እርስ በእርሳቸዉ ያለዉን ግንኙነት በተቋማዊ ዲሲፕሊን ለማረቅ የተቋም ግንባታ ሂደቱ በአስፈላጊ ግብዓቶች የታገዘ አይደለም::

ይሄም ሁሉ ሆኖ የፖለቲካዉ ባለቤት የሆነዉ ህዝብ የሀገሪቱ ፖለቲካ እንደማያገባዉ ሁሉ ነገሮችን በዝምታ ይከታተላል:: ብዙሃኑንም የተቃዉሞዉን ፖለቲካ የሚቀላቀሉ ጥቂት ዜጎችን “አይ ! አሁን ይሆናል ብለዉ ነዉ? ” በማለት ያሽሟጥጣል:: እናም በዚህ ሁኔታ ዉስጥ የሚዳክሩ ተቃዋሚዎችን እንዴት መጠንከር አልቻሉም ብሎ ከመጠዬቅ ይልቅ እንዴት ተቃዋሚ ሊኖር ቻለ ብሎ መጠዬቅ ይሻላል:: በደንብ ለሚያስብበት ሰዉ ትክክለኛዉ ጥያቄም “እንዴት ተቃዋሚ ሊኖር ቻለ?” የሚለዉ ነዉ::

አንድ ተቃዋሚ ድርጅትን የተቀላቀለ በእጅጉ የተማረ አንድ ጓደኛዬን አንድ ጥያቄ ጠይቄዉ ነበር:: “ከምታቃቸዉ ጓደኞችህና ግለሰቦች እንዲሁም ከቤተሰብህ ዉስጥ ምን ያህሉ አላማህን ይደግፉልሃል?” ብዬ::

እርሱም ፈገግ ብሎ “እረ ይሄን ጥያቄ እራሴን ጠይቄ አላቅም !” ሲል መለሰልኝ:: እናም ከዚህ ጓደኛዬ ጋር ተነጋግረን በጣም አጭር ቃለ መጠይቅ አዘጋጀን እና ጥያቄዉን ለጓደኞቹ: ለሚያዉቃቸዉ ሰዎች እንዲሁም ለዘመዶቹ እና ለቤተሰቦቹ በተነዉ::

ያገኘዉን መልስ ስንተነትነዉ ዉጤቱ በጣም አስደነገጠዉ:: እርሱ ይገምት የነበረዉ “ለእኛ ይታገልልናል” ብለዉ የሚያዉቃቸዉ ሰዎች : ዘመዶቹ እና ቤተሰቦቹ የሚያስቡ ይመስለዉ ነበር:: ያገኘዉ መልስ ግን አስፈሪ እና አስደንጋጭ ነበር:: 99% ጥያቄዉን የመለሱ ተጠያቂዎች የሰጡት አንድ መልስ ” ዝም ብለህ ጊዜህን ታጠፋለህ::ከፖለቲካ እራቅ!” የሚል ነበር:: ይባስ ብሎም “ትግሉን በምን ማገዝ ትፈልጋለህ ?” ለሚለዉ ጥያቄ ሁሉም ሰዉ የሰጠዉ መልስ “በምንም ማገዝ አልፈልግም” የሚል ነበር::

እናም ህዝባችን ዲሞክራሲ በርግጥ የሚፈልግ ከሆነ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በፊት የሀገሪቱ ፖለቲካ የራሱ ጉዳይ መሆኑን አምኖ መቀበል አለበት:: አለዚያ ግን ተቃዋሚዎች ላይ ትችቱ እና ወቀሳዉ ከቴም ወንዝ አያሻግርም::ትናት ተሰብስበዉ ዛሬ መበተናቸዉ ሳይሆን የሚደንቀዉ የሀገሪቱ ፖለቲካ የራሱ ፖለቲካ መሆኑን አምኖ አልተቀበለ ህዝብ ዉስጥ ቁጭ ብለዉ ትናንት ለመሰብሰብ መድፈራቸዉ ብሎም ያለምንም ግብዓት ወደ ትግል መግባታቸዉ በራሱ ያስመሰግናቸዋል::

እናም ለህዝባችን የሚቀርበዉ ጥያቄ “ህዝብ ሆይ ምኞትህ ምንድን ነዉ? ዲሞክራሲ ነዉ? ዲሞክራሲ ነዉ ካልክስ የሀገሪቱን ፖለቲካ በባለቤትነት ይዘህዋል? ወይስ ለመያስ ፈቃደኛ ነህ?” የሚል ይሆናል::

ህዝቡ የፖለቲካዉ ጉዳይ ያገባኛል ብሎ ወደ ፖለቲካዉ በተወሰኑ አካባባዎች ወደ አደባባይ ሲወጣ እና የወያኔን አንባ ገነንነት ፊት ለፊት ሲገጥም እንዴት ምድር አንቀጥቅጥ ፍርሃትን በወያኔ ላይ እንዳመጣባት በቅርቡ አስተዉለናል::ህዝባዊዉ አመጽ እና ህዝባዊ ተጋድሎዎች የሚያስገነዙቡት አንድ ብቸኛ እዉነት ምንድን ነዉ? ለዉጡ የሚመጣዉም ሆነ ቀጣይነት ባለዉ መልክ ዲሞክራሲ ስር ሊይዝ የሚችለዉ ህዝቡ የሀገሪቱን ፖለቲካ በባለቤትነት ከገባበት ብቻ ነዉ::ህዝቡ የሀገሪቱን ፖለቲካ በባለቤትነት ሲገባበት የሚከተሉት ሶስት እዉነታዎች በአንድ ጊዜ ይከወናሉ:-1ኛ. ትክክለኛዉን ህዝባዊ አጀንዳ ያነገቡትን እና የህዝብ ወዳጅ የሆኑ የተቃዉሞ ሀይላትን በጉያዉ ደብቆ እና ተንከባክቦ ወያኔን ለመፈንገል የሚያስችላቸዉን ጉልበት: እና በራስ መታመን ያስታጥቃቸዋል::ሚስጥራቸዉን ሚስጢሩ አድርጎ ወያኔን የሚያስገብር ጉልበትን እንዲያፈሩ ያደርጋቸዋል::

2ኛ. አንዳንድ የተቃዋሚ ሀይላት ፖለቲካን የሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ እና የአዬር ባዬር ሽቀላ ከማድረግ እንዲቆጠቡ ብሎም ነገ ሀገሪቱን እና የሀገሪቱን ዲሞክራሲያዊ መጻኢ እድል የሚያኮሰምን ዉሳኔን እንዳይወስኑ ያስገድዳቸዋል::ምክንያቱም ከሀገር ቤት እስከ ዉጭ ሀገር ህዝቡ የሀገሪቱን ፖለቲካ የእኔ ብሎ ከያዘዉ ከህዝብ አይን የሚሰወር አይኖርም እና

3ኛ. የወያኔ መሳሪያ የሆኑ ፓርቲዎች እንዲጋለጡ: የወያኔ መሳሪያ እና የሀገሪቱ ጠላት የሆኑ ፓርቲዎች እንዲዋረዱ ብሎም አላስፈላጊ አራሙቻዎች መንገዱን እንዲለቁ ሲያስገድዳቸዉ ትክክለኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ከመፍረስ እንዲዲኑ ብሎም ቀጣይነት እድገታቸዉ በአስተማማኝ ደረጃ እንዲራመድ ማድረግ ይችላል:: የተዛባ እና የኢትዮጵያን አጠቃላይ ጥቅም የሚጎዳ ህሳቤን የሚያናፍሱትንም አደብ እንዲገዙ ይገፃል ብቻ ሳይሆን እርቃናቸዉን ያስቀራቸዋል::
በአጠቃልይ ህዝቡ የሀገሪቱን ፖለቲካ መረከቡ እና ያገባኛል ብሎ በፊታዉራሪነት መነሳቱ አማራጭ የሌለዉ ምርጫ ነዉ::ግን ይሄ እየሆነ ነወይ ነዉ ጥያቄዉ? በዚህ ሁኔታ ዉስጥ ቆመን ነዉ እንግዲህ ተቃዋሚዎች ለምን መጠንከር አቃታቸዉ እያልን የምንጠይቀዉ::የማይጠዬቅ ገሃድ የወጣ መልስ ያለዉ ጥያቄ::

የህብር ሬዲዮ  የካቲት 26 ቀን 2009 ፕሮግራም

$
0
0

<… ስርዓቱ ዛሬም ድረስ ስልጣን ላይ የቆየው ሕዝቡን እርስ በእርሱ በማጋጨት በተለይ የአገሪቱ ምሰሶዎች የሆኑትን የኦሮሞና የአማራ ሕዝብን በማጋጨት ነው ።እነሱ እሳትና ጭድ እንደሚሉት ሳይሆን የኦሮሞና የአማራ ሕዝቦች አንድ ላይ የኖሩ በጋራ የሚያስተሳስራቸው ብዙ ነገር አለ።…በአገር ቤት በሕዝቦች መካከል የሚታየው አንድነት ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል በውጭ የሚታዩት እርስ በእርስ የመራራቅ ነገሮችን ለማቀራረብ በዚህ በሰሜን አሜሪካ በአንዳንድ ቦታዎች የጋራ ፎረም በማድረግ አየተንቀሳቀሱ ያሉ አሉ ።እዚህ ያለው ሁኔታ ግን አገር ቤት ባለው ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ የለውም። ለወደፊቱም ቢሆን…> ዶ/ር ዲማ ነጎ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ  ከሰጡን ቃለ መጠይቅ  (ክፍል አንድን ያዳምጡት)

<…በምንኖርበት አገር የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ መብታችንን ተጠቅመን መሳተፍ የእኛ ፍላጎቶችን የሚወክሉ ስለእኛ የሚናገሩ የሕዝብ ወኪሎችን መምረጥ መሳተፍ አለብን። ቁጥራችን ብዙ ነው የፖለቲካው ተሳትፏችን ስለሌለ እኛ ላይ ተጽዕኖ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮችን እንኳ ማስለወጥ አንችልም። አሁንም አሽከርካሪዎችን ሊጠቅም የሚችል የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣንን አደረጃጀት የሚቀይር ህግ ተግባራዊ ሊሆን ነው ።ካልደገፍንና ካልተሳተፍን ግን…> አቶ አሌክሳንደር አሰፋ በቬጋስ በዲሞክራቲክ ፓርቲ ኢትዮጵያውያን ተሳትፏቸውን በማሳደግ ለመብታቸው እንዲቆሙ ስለሚያደርጉት ጥረት ከሰጡን ገለጻ(ቀሪውን ያዳምጡት)

<…አድዋን የሚያጥላሉት ብቅ ብቅ ያሉት እውነተኞቹ የታሪክ ምሁራን ዝምታን መርጠው የፈጠራውን የፖለቲካ ታሪክ  ማጋለጥ ስላልቻሉ ነው… ሻዕቢያና መሰሎቹ  አድዋን የሚያጥላሉት የራሳቸውን አገር ለመመስረት ድሉ የፈጠረው ስሜትና አንድነት እንቅፋት ይሆንብናል ብለው ስለሚፈሩ ነው… ብዙዎቹ አገሮች ወይ ቅኝ ግዛት  ገዝተዋል አሊያም በቅኝ ተገዝተዋል የእኛ አለመገዛት ምልክቱ ታላቁ የአድዋ ድል ነው… >

 

የአድዋን ድል ማጥላላት ለምን ተፈለገ ልዩ ቃለ መጠይቅ ከአክቲቪስት አቻምየለህ ታምሩና ከዶ/ር ተሾመ ሞገሴ ጋር (አድምጡት)

በኢትዪጵያ የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞች እየደረስባቸው ያለው የስራ እድል ተጽእኖ እና ያስከተለው ቀውስ ሲዳስስ (ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

የኢትዮጵያው አገዛዝ  የመከላከያ ሰራዊት በስምንት ተሽከርካሪዎች ታጅቦ ለውጊያ ከጅቡቲ ግዛትሰፈረ

አርበኞች ግንቦት ሰባት ትግሉም ስልጠናውም አገር ቤት ገብቷል ከዚህ በሁዋላ በኤርትራ ስልጠናአይሰጥም አለ

ትግሉን መቀላቀል የፈለገ ወደ ኤርትራ ሳይሆን የአገር ቤቱን ትግል ይቀላቀል ሲል ጥሪ አቀረበ

በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ስዎች በጭንቀት ህመም እንደሚስቃዩ አለማቀፍ ጥናት ይፋ አደረገ

ዶ/ር ዲማ ነጎ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኖረም አልኖረ በአገር ቤት ትግሉ እንደሚቀጥል ገለጹ

በሕዝቦች መካከል የተጀመረው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል

የአሜሪካው ፕ/ት ትራምፕ የቀድሞው ፕ/ት ባራክ ኦባማ ስልኬን ሲጠልፉ ነበር ማለታቸው ታላቅተቃውሞ አስነሳ

በዶላር ዕጥረት ሳቢያ በአዲስ አበባ ሆቴሎች ዋጋ እስከመቀነስ ሄደዋል

የህዳሴው ግድብን ለማጥቃት ኤርትራ ታጣቂዎችን አስታጥቃ ላከችብኝ ለሚለው የኢህአዲግ ስሞነኛውንጀላ የአስመራ መንግስት ምላሽ ስጠ

የኡጋንዳው ፕ/ት ሙሴቭኔ የአባይን ውሃ በጋራ ያለመጠቀሙ እንቆቅልሽ አልገባኝም ሲሉ ጠየቁ

በኢትዮጵያ ሁሉንም ያሳተፈ ከፍርሃት የሚያላቅቅ ቅንጅት ያስፈልጋል ተባለ

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ሌሎችንም በንቅናቄው ለማካተት እየሰራ መሆኑን ገለጹ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ስድስት የሙስሊም ትምህርት ቤቶች በፓለቲካ ጫና ተሸጡ

በኢህአዲግ ማጎሪያ ቤት ውስጥ ለሚማቅቁት ለግንቦት 7ቱ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የህግ እማካሪማመቻቸት ጠቀሜታ እንደሌለው አንድ ከፍተኛ የእንግሊዝ የህግ ባለሙያ አስጠነቀቁ

“እንግሊዝ በአንዳርጋቸው ዙሪያ ከኢህአዲግ ጋር ፊት ለፊት መነጋገር አለባት”የህግ ባለሙያው ኬንዶምኒክ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽንሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓትበህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል።ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁምበተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

ቴድሮስ ኣድሓኖም ለአለም የጤና ድርጅት መመረጥ የለበትም ስንል ሁለት ነገሮችን በመጥቀስ – ናትናኤል አስመላሽ

$
0
0

ቴድሮስ ኣድሓኖም ለአለም የጤና ድርጅት መመረጥ የለበትም ስንል ሁለት ነገሮችን በመጥቀስ ብቻ ነው፣ አንደኛው የመታከም መብት ያለው ወጣት እንዳይታከም ስላደረጉ፣ ከአገር የመውጣት መብት ያለው ወጣት እንዳይወጣ ስላደረጉ፣ ይህ ወጣት ወጣት ሃብታሙ አያለው ነው። በሁለተኛ ደረጃ እሳቸው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል በነበሩባት ክልል የጤና ባለሙያዎች የፖለቲካ አባላት ስለሆኑ ብቻ ንግድ ፍቃዳቸው ከህግ ውጭ ሲነጠቁ እና ሆስፒታላቸው እንዲዘጉ ስለሚገደዱ ብቻ ነው። እኝህ ዶ/ር, ዶ/ር ማርቆስ ይባላሉ።በትግራይ በተደረገው ጥልቅ ታሃድሶ የሸራሮ ነዋሪዎች እስካሁን ድረስ መንገድ ላይ እና ቤታቸው ውስጥ እንደሚወልዱ ተናግረዋል። ለዚህ ነው ዶ/ር ቴድሮስ የአለም ጤና ድርጅት መምራት አይችሉም የምንለው፣ ሌላው የአገሪቱ የጤና ደረጃ ሳንነካካ እና ተደራሽነት ሳንጠቅስ ማለቴ ነው።ዶር ቴድሮስ ከህውሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው የለቀቁት ለአለም ጤና ድርጅት ለመወዳደር እና ከእዳውም ነጻ ለመውጣት(ለማምለጥ) ስለሚፈልጉ ነው ግን አይሆንም።

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ትናንት የጀመረውን ስብሰባ ዛሬም ቀጥሏል |የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ውሳኔ ሊተላለፍ ይችላል

$
0
0

(ቢቢኤን) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት መደበኛ ስብሰባውን መጀመሩ ተገለጸ፡፡ የአራት ፓርቲዎች ውህድ የሆነው ፓርቲው በሚኖረው የሶስት ቀናት ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል፡፡ ፓርቲው ውሳኔ ያሳልፍባቸዋል ተብሎ ከተያዙ ጉዳዮች መካከል አንዱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደሚሆን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በመጪው መጋቢት 28 ቀን 2009 ስድስተኛ ወሩን የሚይዘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፣ ይነሳ ወይስ ይቀጥል በሚለው ጉዳይ ላይ መንግስት ወጥ አቋም ሳይዝ ቆይቷል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የኢህአዴግ ባለስልጣናት በአስቸኳይ አዋጁ ዙሪያ የተለያየ አቋም መያዛቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ አብዛኞቹ የህወሓት ባለስልጣናት አዋጁ ከስድስት ወርም በላይ እንዲቆይ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን፣ ከፊሎቹ ደግሞ የውጭ ለጋሾችን ተፅዕኖ በመፍራት አዋጁ ከስድስት ወር በላይ ባይቀጥል ፍላጎት እንዳላቸው ምንጮች ይገልጻሉ፡፡

አዋጁ እንደ አጠቃላይ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሲታይ ደግሞ፣ አዋጁ ይፋ ሲደረግ የተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ባይቀጥል የሚል በላጭ አመለካከት እንዳለም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላ ሀገሪቱ ‹‹መረጋጋቷን›› ሲገልጹ የሚደመጡት የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ሀገሪቱ መረጋጋቷን ለውጭ ዲፕሎማቶች እና ለጋሽ ሀገራት ለማሳየት አዋጁን የማንሳት ፍላጎታቸው አመዝኗል ተብሏል፡፡ ሆኖም በፓርቲው ውስጥ ያለው ወጥ ያልሆነ አቋም፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ በቀጣይ የስብሰባ ቀናት ምን ዓይነት ውሳኔ ሊተላለፍ እንደሚችል ከወዲሁ ለመገመት አዳጋች ሆኗል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይፋ ከተደረገ በኋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መታሰራቸው እና በርካቶችም ሀገር ጥለው መሰደዳቸው ይታወቃል፡፡

የፍትሐ ነገሥት ደራሲ ማነው? – ይትባረክ አምላክ አበዊነ!! ተክለጊዮርጊስ ዘአትላንታ

$
0
0

ሐሰትን ድምጽን ከፍ አድርጎ በመጮህ ወይም አሳምሮ በመናገር እውነት ማድረግ አይቻልም። ሆኖም ይህ አይነቱ ሙከራ በአትላንታ ሰአሊተ ምህረት ካቴድራል አውደ ምህረት ላይ በቀሲስ አለም እሸት አብርሃ አማካኝነት ተሞክሯል። ቀሲስ አለም እሸት ካቴድሯሏን በወያኔው ጉጀሌ በአባይ ጸሃይ በሚወዘወረው ሲኖዶስ ለመውሰድ የሚደረገውን ዘመቻ ከአባ ኃ/ሚካኤል ፊታውራራነቱን ወስዶ አደራውን ለመወጣት በመፈራገጥ ላይ ይገኛል። ይህ ግለሰብ ማኅበረ ቅዱሳን ከሚባለው የጎበዝ አለቆች ቡድን ፔይሮል ላይ የሚገኝ ሆድ አደር ነው። ልማታዊው ቄስ በከተማችን የወያኔ ባለስልጣኖች ብቅ ሲሉ አልጋ ከሚያነጠፍላቸው አቶ ቴዎድሮስ ጋር በመሆን ዲሲ በሚገኘው የወያኔ ኤምባሲ ውስጥ በተደረገው የሰሜን አሜሪካ ኮማንድ ፖስት ስብሰባ ተካፍሎ ከመጣ ወዲህ የበሬ ወለደ ዘመቻውን አጠናክሮቷል። በዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ የሀሰት መረጃን አቅርቦ

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

 

 

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live