Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

ሁለቱ ጋዜጠኞች ክስ ሳይመሰረትባቸው ከሦስት ወር በላይ መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለጹ

$
0
0

የአናኒያ ሶሪ ባለቤትና የኤልያስ ገብሩ እህት ጋዜጠኞቹ በጹሑፍ ሐሳባቸውን ከመግለጽ ውጭ የሠሩት ወንጀል የለም ብለዋል። መንግሥት በበኩሉ የታሰሩ ካሉ ወይ ሞያው የሚጠይቀውን የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ባለማክበራቸው ነው ወይም ጋዜጠኞች ባለመሆናቸው ነው ብሏል።

አናንያ ሶሪና ኤልያስ ገብሩ የተባሉ ሁለት ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች ክስ ሳይመሰረትባቸውና የታሰሩበትን ምክንያት በይፋ ሳይነገራቸው ከሦስት ወር በላይ በእስር ቤት እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። ወጣቶቹ በጹሑፍ ሐሳባቸውን ከመግለጽ ውጭ የሠሩት ወንጀል የለም ብለዋል – ቤተሰቦቻቸው።መንግሥት በበኩሉ የታሰሩ ካሉ ወይ ሞያው የሚጠይቀውን የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ባለማክበራቸው ነው ወይም ጋዜጠኞች ባለመሆናቸው ነው ብሏል።

የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ ሲፒጄ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያ የታሰሩት ስለፃፉ ብቻ ነው በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል ማለቱ ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

if(typeof(jQuery)==”function”){(function($){$.fn.fitVids=function(){}})(jQuery)};jwplayer(‘jwplayer-1’).setup({“image”:”http://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2017/02/VOA.jpg”,”file”:”http://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2017/03/2fe47afe-fc9c-47c9-b977-c8f3026fdc5c_hq.mp3″});


በአብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ 500 ሺ ስደተኞች በሱዳን እንደሚገኙ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ

$
0
0

ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2009)

አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ወደ 500ሺ አካባቢ የሚጠጉ የኤርትራና የሶማሊያ ስደተኞች በሱዳን እንደሚገኙ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ።

ሰሞኑን ሱዳን በኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ፈጽማዋለች የተባለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ተከትሎ ለሃገሪቱ የሚሰጠውን የስደተኞች የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቋርጥ የተጠየቀው ህብረቱ ለሃገሪቱ እስካሁን ድረስ የለቀቀው ድጋፍ አለመኖሩን ገልጿል።

የሱዳን የድንበር ተቆጣጣሪ ሃይሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ ወደ ሃገሪቱ ድንበርን እያቋረጡ የሚገቡ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ማስታወቁ ይታወሳል።

በሃገሪቱ በሚገኙ የጎረቤት ሃገራት ስደተኞች ዙሪያ ሪፖርትን ያወጣው የአውሮፓ ህብረት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የኤርትራና የሶማሌ ስደተኞች በሱዳን እንደሚገኙ ማመልከቱን ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል።

እነዚሁ ስደተኞች ሃገሪቱን መሸጋገሪያ በማድረግ ወደ አውሮፓ የመግባት እቅድ እንዳላቸው ተነግሯል።

ባለፈው የፈረንጆች አመት 2016 አም ብቻ ወደ 30ሺ የሚጠጉ ስደተኞች ከሱዳን ወደ ጣሊያን ያቀኑ ሲሆን፣ ድርጊቱ ስጋት ያሳደረበት የአውሮፓ ህብረት ሃገሪቱ የስደተኞች ቁጥጥሯን እንድታጠናክር በሚል የ100 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ በቅርቡ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። ይሁንና፣ የሱዳን መንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቅርቡ በኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች ፈጽመውታል የተባለ ድብደባና እስራት ተከትሎ የአውሮፓ ፓርላማ ህብረቱ ለሃገሪቱ ሊሰጥ ያቀደውን የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቋርጥ ጥያቄን አቅርቦ ይገኛል።

ለዚሁ ጥያቄ ምላሽን የሰጠው የአውሮፓ ህብረት እስከአሁን ድረስ ሃገሪቱ የተለቀቀ የገንዘብ ድጋፍ እንደሌለና ልገሳው በአለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ ተግባራዊ የሚደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ከአንድ ሳምንት በፊት በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሱዳን መንግስት በመኖሪያ ፈቃድ ክፍያ ላይ ያደረገውን የክፍያ ጭማሪ እንዲያጤነው ኢትዮጵያውያኑ ኤምባሲው ጥረት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ይሁንና ኢትዮጵያውያኑ ጥያቄያቸውን ባቀረቡ ጊዜ የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ከኤምባሲው የቀረበላቸው ጥሪ ተከትሎ ሰላማዊ ሰልፉን ለመበተን በወሰዱት ዕርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩት ለእስር መዳረጋቸው ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል።

ለእስር ከተዳረጉት መካከል 65 አካባቢ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በ40 የጅራፍ ግርፋት እንዲቀጡ መደረጉም ሲዘገብ ቆይቷል። የመረጃውን መውጣት ተከትሎም የአውሮፓ ፓርላማ ሱዳን በስደተኞቹ ላይ ፈጽማዋለች ያለውን ድርጊት በጽኑ ኮንኗል።

በርካታ የህብረቱ የፓርላማ አባላት የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች የፈጸሙት ድብደባና እስራት አስቸኳይ ማጣራት እንዲካሄድበት ጥያቄን ያቀረቡ የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች የፈጸሙት ድብደባና እስራት አስቸኳይ ማጣራት እንዲካሄድበት ጥያቄን ያቀረቡ ሲሆን፣ የሱዳን መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው ምላሽ የለም።

የአውሮፓ ህብረት ለእስር በተዳረጉና ታስረው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ማጣራት እንዲካሄድበት ጥያቄን ቢያቀርብም፣ የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ድረስ የገለጸው ነገር የለም።

በባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ፖሊ ግቢ የማስጠንቀቂያ ወረቀት ተብትኖ አድሯል- ሙሉቀን ተስፋው

$
0
0

ዛሬ የካቲት 22 ቀን 2009 ዓም ማለዳውን መረጃ የላኩልን ሰዎች እንዳመለከቱት የወያኔ ግፍ ደግፈው ለሚንቀሳቀሱ የትግራይ ተማሪዎች ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክት ተበትኖ ማደሩን ሰምተናል። በዩንቨርሲቲው ግቢ ሲበተን ያደረው ወረቀት የጽሑፍ ይዘት የሚከተለው ነው፤

ማስጠንቀቂያ ለትግራይ ተማሪዎች

በትግራይ የአገዛዝ ስር የወደቀችው አማራ በህዝቡ ላይ ህወሀት ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመበት መሆኑን ደጋግመን መናገራችን ይታወቃል፡፡ነገር ግን መናገራችን እንደ በደል ተቆጥሮብን በደሉ እየገፋ መምጣቱን ሆን ብሎ አሰቀጥሎታል፡፡ እኛም እናንተ የትግራይ ተማሪዎች አትዮጵያዊ ስሜት ይኖራችኋል ብለን በዝምታ ስንከታተላችሁ ብንቆይም እናንተ ግን የእኛ ሞት ለእናንተ ደስታ ሆኖላችሁ በ 19/06/09 ዓ.ም በባህር-ዳር ከተማ የሙዚቃ ድግስ አዘጋጅታችሁ ስትዘፍኑ መዋላችሁ የአማራ መሞት ለእናንተ ደስታ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ ከዚህ በኋላ በጎንደር እየተገደሉ ያሉ ገበሬዎች ሞት፤ በባህርዳር ቤት ለቤት እየተዞረ ሰው ለቀማ ካላቆመ፤ በአማራ ክልል የምትገኙ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ቅጣቱን እናንተ ላይ እንደምንጥለው እንድታውቁ፤ አንድም የትግራይ ተወላጅ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከግቢ ወጥቶ ሲዝናና ፣ ቤተ-ክርስቲያን ሲሄድ፤ በትግሬ ስም ስብሰባ የምትሰበሰቡ ከሆነ እየተከታተልን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
አማራ ወደፊት!!!!!

የሚድሮክ ሔሊኮፕተር ተከሰከሰ

$
0
0

በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር ከሚተዳደሩት በርካታ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ (ቲኤንኤ) ኩባንያ ንብረት የሆነ ቤል 222U ሔሊኮፕተር፣ ቅዳሜ የካቲት 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ አምስት መንገደኞች አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ወደ ሐዋሳ ለመብረር በመነሳት ላይ ሳለ ተመልሶ ወደ መሬት ወድቋል፡፡

በሔሊኮፕተሩ ውስጥ ዋና አብራሪና ረዳት አብራሪ፣ እንዲሁም አምስት የተለያዩ አገር ዜግነት ያላቸው ተሳፋሪዎች ነበሩ፡፡ በአብራሪዎቹ ላይም ሆነ በመንገደኞቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስ ከአደጋው መትረፋቸው ታውቋል፡፡ መንገደኞቹ ወደ ሐዋሳ ለስብሰባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ሚሲዮናዊያን እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በቅርቡ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ተገንጥሎ በትራንስፖርት ሚኒስቴር ሥር ከተቋቋመው የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፣ የምዝገባ ቁጥር ኢቲ-ኤ ኤም አር ንብረትነቱ የቲኤንኤ የሆነ ሔሊኮፕተር በሁለት አብራሪዎች አማካይነት ወደ ሐዋሳ ለመብረር ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የጄኔራል አቪዬሽን ራምፕ (አውሮፕላን ማቆሚያ) በመነሳት ላይ ሳለ ከመሬት ብዙም ሳይርቅ ተመልሶ ወደ መሬት ወድቋል፡፡ በአብራሪዎቹ ላይም ሆነ በመንገደኞች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ የገለጸው ቢሮው፣ በሔሊኮፕተሩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ አደጋው በተከሰተበት ወቅት እሳት አለመነሳቱን ቢሮው አረጋግጧል፡፡

ሁለት ሞተር ያለው ቤል222 ሔሊኮፕተር የወደቀው በኃይል መቋረጥ (ሞተር በመጥፋቱ) እንደሆነ የሪፖርተር ምንጮች የተናገሩ ቢሆንም፣ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ምርመራ በማካሄድ ላይ ስለሆነ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ የቢሮው ባለሙያዎች አደጋው እንደደረሰ ሥፍራው በመድረስ ከሔሊኮፕተሩና ከአብራሪዎቹ አስፈላጊውን መረጃ የሰበሰቡ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የተሰበሰቡትን መረጃዎች በመመርመር ላይ ናቸው፡፡ ቢሮው የአደጋውን ሪፖርት በቅርቡ አጠናክሮ ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡ ‹‹የአደጋ ምርመራ ሳይጠናቀቅ ምንም ማለት አይቻልም፤›› ብሏል ቢሮው፡፡

ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአውሮፕላን ምዝገባና የበረራ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ሪፖርተር ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፣ የቲኤንኤ ቤል222 ሔሊኮፕተር ተመዝግቦ የገባው እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2008 ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ1986 በአሜሪካ ቤል ሔሊኮፕተር ኩባንያ የተመረተው ሔሊኮፕተሩ እ.ኤ.አ. እስከ ሰኔ 2016 ድረስ 3,891 ሰዓት መብረሩ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የአውሮፕላን ምዝገባና የበረራ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት በየዓመቱ በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ሲቪል አውሮፕላኖችና ሔሊኮፕተሮች ላይ ምርመራ በማድረግ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት ይሰጣል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ በጥቅምት 2009 ዓ.ም. በቲኤንኤ ሔሊኮፕተር ላይ ምርመራ አድርጎ የብቃት ማረጋገጫ መስጠቱን፣ ሠርተፊኬቱም ለአንድ ዓመት የሚያገለግል መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ ‹‹ሔሊኮፕተሩ ለበረራ ብቁ ነበረ፡፡ ሠርተፊኬቱ ሔሊኮፕተሩ እስከ ጥቅምት 2010 ለበረራ ብቁ መሆኑን ያረጋግጣል፤›› ብለዋል፡፡

የቲኤንኤ ዋና ሥራ አስኪያጅ ካፒቴን ተረፈ ኃይሌ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ሔሊኮፕተሩ የቴክኒክ ብቃቱ የተጠበቀና በጥሩ ሁኔታ በማገልገል ላይ ነበረ፡፡ ‹‹አደጋ እንግዲህ በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት ይችላል፡፡ ያለ ነገር ነው፡፡ ዋናው ነገር አብራሪዎቻችንና ደንበኞቻችን ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም መውጣታቸው ነው፤›› ያሉት ካፒቴን ተረፈ፣ የአደጋ ምርመራው ሲጠናቀቅ የተሟላ መረጃ ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር የሚተዳደረው ቲኤንኤ እ.ኤ.አ. 2004 የተመሠረተ ሲሆን፣ በዋነኛነት የቻርተር በረራ አገልግሎት በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ይሰጣል፡፡ ኩባንያው ሁለት እያንዳንዳቸው 37 መቀመጫ ያላቸው ቦምባርዲየር ዳሽ8-200 አውሮፕላኖች ሲኖሩት፣ አውሮፕላኖቹ በአብዛኛው በሱዳንና በሌሎች አገሮች የቻርተር በረራ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ አውሮፕላኖቹ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና አስጎብኚ ድርጅቶች ይከራያሉ፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት ቲኤንኤ ወደ ጎንደርና ሁመራ መደበኛ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መስጠት ጀምሮ የነበር ቢሆንም ብዙም ሳይቆይ አገልግሎቱን አቋርጧል፡፡  ቲኤንኤ በተጨማሪ ሁለት አይረስ የተባሉ ቀላል አውሮፕላኖች በመጠቀም የፀረ አረምና አንበጣ መከላከያ መድኃኒት ርጭት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ቲኤንኤ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የሚጠይቀውን የበረራ ደኅንነት መመርያ ሰነድ አሟልቶ ባለማቅረቡ ባለሥልጣኑ የኩባንያውን ፈቃድ ለአጭር ጊዜ አግዶት ቆይቷል፡፡ ባለሥልጣኑና የኩባንያው ማኔጅመንት መስተካከል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ተነጋግረው ኩባንያው የተጠየቁትን ሰነዶች በማሟላቱ ዕግዱ እንደተነሳለት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቲኤንኤ ቤል222 ሔሊኮፕተርን የገዛው እ.ኤ.አ. በ2008 አሜሪካን ጄኔራል ሰፕላይስ ከተባለ ኩባንያ መሆኑን የሚናገሩት የሪፖርተር ምንጮች፣ ሔሊኮፕተሩ ረዥም ጊዜ ያገለገለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ባለሙያዎች በበኩላቸው ሔሊኮፕተሩ በየጊዜው መደበኛ ጥገና የሚደረግለት ለበረራ ብቁ የሚባል እንደበረ አስረድተዋል፡፡ ዋናው ነገር ለሔሊኮፕተርና ለአውሮፕላን የሚደረገው መደበኛ ጥገናና ክትትል ነው እንጂ ዕድሜው አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ ዕድሜ ያላቸው ሔሊኮፕተሮች አገራችን ውስጥ ይበራሉ ብለዋል፡፡

ባለሙያዎቹ ይህን ቢሉም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እ.ኤ.አ. ሰኔ 2013 ያወጣው የአቪዬሽን ሬጉሌሽን ዕድሜያቸው ከ22 ዓመት በላይ የሆኑ የመንገደኛ አውሮፕላኖች ወደ አገር እንዳይገቡ ይከለክላል፡፡ የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላኖች ዕድሜ ደግሞ ከ25 ዓመት እንዳይበልጥ መመርያው ያዛል፡፡

የቲኤንኤ ሔሊኮፕተር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በባለሥልጣኑ እ.ኤ.አ. በ2008 ዓ.ም. ሲመዘገብ 22 ዓመት ዕድሜ ነበረው፡፡ ‹‹ሬጉሌሽኑ የወጣው እ.ኤ.አ. በ2013 በመሆኑ በሔሊኮፕተሩ ላይ ተፈጻሚነት የለውም፡፡ 22 ዓመት የሚለው ወደ አገር ተመዝግበው ሲገቡ ያላቸው ዕድሜ እንጂ፣ ከተመዘገቡ በኋላ 50 ዓመትም ቢሞላቸው ከገበያ እንዲወጡ የሚያስገድድ ሕግ የለም፤›› ብለዋል ኃላፊው፡፡

በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የተመዘገቡ 15 የግል አየር መንገዶች ቢኖሩም፣ በሥራ ላይ የሚገኙት ሰባት ያህል ብቻ ናቸው፡፡

ዜና- ሪፖርተር

ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ አሳጥተዋል የተባሉ የቡና ነጋዴዎችና የመንግሥት ሠራተኞች ተከሰሱ

$
0
0

ሐሰተኛ ሰነድ ወይም ንግድ ፈቃድ በማቅረብና የብቃት ማረጋገጫ ባለሙያ ከሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ጋር በመመሳጠርና በጥቅም በመተሳሰር መንግሥት ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ እንዲያጣ አድርገዋል የተባሉ ቡና ነጋዴዎችና የመንግሥት ሠራተኞች፣ የካቲት 20 እና 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

በተከሳሾቹ ላይ ሁለት የተለያዩ የክስ መዝገቦች ቀርበዋል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የብቃት ማረጋገጫ ባለሙያዎቹ አቶ ታምራት ኃይሌና አቶ ሁምኔሳ አብደታ፣ በግል ሥራ የሚተዳደሩትና ያልተያዙት አቶ ተመስገን ማሞ፣ ቡና ነጋዴዎቹ አቶ በርሄ ሐጐስና አቶ ዳንኤል ወልዴ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡ በሌላ መዝገብ ደግሞ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የካቲት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ክስ የተመሠረተባቸውና በግል ሥራ እንደሚተዳደሩ የተገለጸው አቶ እስክንድር ፍቅሩ፣ አቶ ልዑል ሰገድ ግርማ፣ አቶ ኤሊያስ ጀማል፣ አቶ አብደላ ናስርና አቶ ዮናስ ታደሰ ደግሞ ሐሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀትና ቡና ገዝተው በመሰወር ተከሰዋል፡፡

የመንግሥት ሠራተኞቹ የብቃት ማረጋገጫ ሲሰጡ ግብርና ሚኒስቴር በ2004 ዓ.ም. ባወጣው መመርያ ቁጥር 66114 መሠረት ነጋዴው ማሟላት የሚገባቸውን መሥፈርቶችን ማለትም መጋዘንና ቢሮ መከራየቱን፣ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ባለሙያዎች መቀጠራቸውን በአካል ተገኝተው ማረጋገጥ ሲገባቸው ከአቶ በርሄና ከአቶ ዳንኤል ጋር ባላቸው ድብቅ የጥቅም ግንኙነት ምክንያት ሳያረጋግጡ፣ የብቃት ማረጋገጫ መስጠታቸውን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

ባለሙያዎቹ በቀረበላቸው ፎርም ላይ በመሙላትና የቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ ከመስጠታቸውም በተጨማሪ፣ በተሰጣቸው ፈቃድ መሠረት መላክ አለመላካቸውን ሳያረጋግጡ የፈቃድ ዕድሳት መስጠታቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል፡፡ በመሆኑም ነጋዴዎቹ (አቶ በርሄና አቶ ዳንኤል) በተሰጣቸው የብቃት ማረጋገጫ መሠረት በአቶ ተመስገን ማሞ ስም ንግድ ፈቃድ በማውጣት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ 274.3 ቶን (2,743 ኩንታል) ቡና መግዛታቸውንም አክሏል፡፡ ለመጋዘን ፍሳሽና እርጥበት ቅናሽ ተደርጎ የሚቀረውን 235.6 ቶን (2,356 ኩንታል) ቡና ወደ ውጭ በመላክ 894,179 ዶላር ወይም 14,655,604 ብር የውጭ ምንዛሪ መንግሥት እንዲያኝ ማድረግ ሲገባቸው፣ ቡናውን በመሰወር የውጭ ምንዛሪው እንዳይገኝ ማድረጋቸውንና ጉዳት ማድረሳቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ ሁለቱ የቡና ነጋዴዎች በሌላ ጊዜ ደግሞ ሰለሞን አርዓያ (ያልተያዘ) የተባለውን ተከሳሽ ስም ተጠቅመው ንግድ ፈቃድ በማውጣት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የገዙትን 1,905.36 ቶን (19,053.6 ኩንታል) ቡና ወደ ውጭ ሳይልኩ በመሰወር መንግሥት ሊያገኝ የሚገባውን 6,502,895 ዶላር ወይም 129,407,612 ብር የውጭ ምንዛሪ ማሳጣታቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡

አቶ እስክንድር፣ አቶ ልዑል ሰገድ፣ አቶ ኤልያስ፣ አቶ አብደላና አቶ ዮናስ የተባሉ ተከሳሾች ደግሞ ሐሰተኛ ሰነድ በማሠራት፣ ሐሰተኛ ሰነዱን በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት አቅርበው ውክልና በመውሰድና ከግብርና ሚኒስቴር ለንግድ ሚኒስቴር የተጻፈና ማርቆስ ሰለሞን አበበ ለተባለ ቡና ላኪ ድርጅት የተሰጠ የሚመስል ሐሰተኛ የቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ በማዘጋጀት፣ ሚካኤል ወርቁ መንገሻ ለሚባል ግለሰብ ውክልና መስጠታቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያም ግምቱ 211,011 ዶላር ወይም 4,091,519 ብር የሆነ ቡና ገዝተው ወደ ውጭ መላክ ሲገባቸው ሳይልኩ በመሰወራቸው፣ የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ የውጭ ምንዛሪ ማሳጣታቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጾ አቅርቧል፡፡

እስክንድር ፍቅሩ በተባለው ተከሳሽ ውክልና በሚንቀሳቀሰው ዮታ ኮፊ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ በተባለ ድርጅት ንግድ ፈቃድ በቡና ላኪነት ኤሊያስ ከተባለው ተከሳሽ ጋር ተስማምተው በጋራ ሲሠሩ፣ የቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅ ቁጥር 602/2000 አንቀጽ 8(3)ን እና አንቀጽ 14(5)ን በመተላለፍ ከምርት ገበያው የገዙትን 147.39 ቶን (1,473.9 ኩንታል) ቡና በመሰወር መንግሥት ማግኘት የሚገባውን 424,996 ዶላር ወይም 4,492,633 ብር የውጭ ምንዛሪ ማሳጣታቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በድምሩ 152,647,368 ብር የውጭ ምንዛሪ በማሳጣታቸው የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን መምራት ወንጀል፣ በከባድ አታላይነት ወንጀል፣ በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸም ወንጀል፣ ያላግባብ ፈቃድ መስጠትና ማፅደቅ ወንጀል፣ መንግሥታዊ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀትና መገልገል ወንጀል ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡

ችሎቶቹም ለቀረቡት ተከሳሾች ክሱ እንዲደርሳቸው ካደረጉ በኋላ በንባብ አሰምተው፣ የቅድመ ክስ መቃወሚያ ካላቸው ከጠበቆቻቸው ጋር ተመካክረው እንዲቀርቡ፣ ያልተያዙትን ፖሊስ ተከታትሎ በመያዝ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ በማስተላለፍ ለየካቲት 30 እና መጋቢት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

ዜና- ሪፖርተር

ለሞ ኢብራሒም ሽልማት የሚመጥን አፍሪካዊ መሪ አሁንም አልተገኘም

$
0
0

በአፍሪካ የአመራር ስኬት ሽልማት ለመስጠት በማቀድ እ.ኤ.አ. በ2016 በዚሁ ዘርፍ ከሥልጣን የለቀቁ የአፍሪካ መሪዎችን ቢያወዳድርም፣ የወጣውን ከፍ ያለ ደረጃ በማሟላት የሚያሸንፍ መሪ አለመገኘቱን ሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን ማክሰኞ የካቲት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡

በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ሳሊም አህመድ ሳሊም የሚመራው የሽልማት ኮሚቴና የፋውንዴሽኑ ቦርድ አባላት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት ተስብስበው እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውም ታውቋል፡፡

የሽልማት ኮሚቴውን ውሳኔ አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡት ዶ/ር ሳሊም፣ ‹‹ሽልማቱ እ.ኤ.አ. በ2006 በይፋ ሲከፈት ደረጃው ከፍ ያለ እንዲሆን የተደረገው ታስቦበት ነው፡፡ በርካታ የአፍሪካ አገሮች መሪዎች አገሮቻቸውን ለመቀየር ላደረጉት ጥረት ዕውቅና እንሰጣለን፡፡ ነገር ግን የሽልማቱ ዓላማ ያልተለመዱ ልዩ የአመራር ክህሎቶችን ማጉላት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ጉዳዩን በጥሞናና በጥንቃቄ ከመረመርን በኋላ ሽልማቱን እ.ኤ.አ. በ2016 ላለመስጠት ወስነናል፤›› ብለዋል፡፡

ለሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን ሽልማት ዕጩ በመሆን የሚቀርቡት የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎች ሲሆኑ፣ ሥልጣናቸውን ከመታጨታቸው በፊት ባሉት ሦስት ዓመታት የለቀቁ መሆን አለባቸው፡፡ የሥልጣን ዘመናቸውም በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተገኘ መሆን አለበት፡፡

እስካሁን ሽልማቱ ለአራት የአፍሪካ የቀድሞ መሪዎች ተሰጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2014 ለናሚቢያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሂፊኪፑንዬ ፓሃምባ፣ እ.ኤ.አ. በ2011 ለኬፕ ቨርዴ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፔድሮ ፒሬዝ፣ እ.ኤ.አ. በ2008 ለቦትስዋና የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፌስተስ ሞሃይና እ.ኤ.አ. በ2007 ለቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ጆአኪም ቺሳኖ ሽልማቱ መበርከቱ ይታወሳል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2007 ለቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላም በፋውንዴሽኑ የክብር ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

ሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን በሱዳናዊና እንግሊዛዊ ቢልየነር የንግድ ሰው ዶ/ር ሞሐመድ ሞ ኢብራሒም እ.ኤ.አ. በ2006 የተቋቋመ ሲሆን፣ ዋነኛ ዓላማውም በአፍሪካ አመራር ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ነው፡፡

የሞ ኢብራሒም የአመራር ሽልማት አሸናፊ በቅድሚያ አምስት ሚሊዮን ዶላር የሚያገኝ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ በሕይወት እስካለ ድረስ 200,000 ዶላር በየዓመቱ ያገኛል፡፡

ባለሀብቱ ዶ/ር መሐመድ ሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽኑን ለማቋቋም ስኬታማውን የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኩባንያቸውን ሴልቴልን በ3.4 ቢሊዮን ዶላር እ.ኤ.አ. በ2005 መሸጣቸው ይታወሳል፡፡

ዜና- ሪፖርተር

የታጋይ ጎቤ መልኬ ሞት፤ የነፃነታችን ኩራት! (ጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት)

$
0
0

ለመብትና ለነጻነት የሚደረግ ትግል ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍል የተማርነው፤ የታሪክ ማህደሮችን በማገላበጥ አይደለም። ክቡር ህይወትን፤ ለሕዝብ እና ለአገር ነፃነት አሳልፎ መሥጠት ከቅድመ አያቶቻችን፤ ጀምሮ፤ በኩራት እየወረስን ዘመኑን ዋጀን እንጂ። ለዘለዓለም በባርነት ከመገዛት፤ ለአገርና ለወገን ነጻነት፤ ህወታቸውን ሰጥተው፤ በኩራት እኛም ነፃነታችንን ጠብቀን በመኖር ለቀጣዩ ትውልድ እንድናሥተላልፍ፤ የውጭ ወራሪን፤ የውሥጥ ባፍንዳን አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ፤ አሁን ላይ አድርሰውናል።

ጎቤ መልኬም የነዚያ ጅግኖች አባቶቻችን፤ ታሪክ ወራሽ እና ለቀጣዩ ትውልድ ምሳሌ ይሆን ዘንድ፤ ጀግነንትን በሆዱ ያለወጠ፤ ለኃብቱ ቀርቶ ለንፍሱ ያልሳሳ፤ የኢትዮጵያ ኩራት የጎንደር ጀግና ነው።

ዛሬ፤ አርበኛ ጎቤ መልኬን በወያኔ ነብሰ በላዎች፤ በመነጠቃችን፤ አንጥፈን ሙሾ አንደረድርም፤ ታሪካችንንም በነበር አንደመድምም። አስተምሮን ያለፈው፤ ትናንት፤ እነ አበራ ጎባው፤ እነ ወጣት ሞላ አጃው፤ እነ ደጀኔ እና የመሳሰሉት ጀግኖች የጎንደር አርበኞች ሲቀጠፉ፤ በሃዘን ልቡን በመሥበር፤ ተሥፋ ቆርጦ፤ እጅ ለጠላት መሥጠትን ሳይሆን፤ በጀግንነት እና በቆራጥነት፤ ለነፃነት የሚከፈለውን ዋጋ ከፍሎ፤ የበለጠ ሺ የጎንደር ጀግኖች፤ እንዲከተሉት፤ ለሁላችን ኩራት የሆነውን መሥዋዕትነት ከፍሎ የጀግና ክብሩን አወጀ እንጂ።

አሥገራሚው እና አሥደናቂው የታሪካችን ገጽታ ደግሞ፤ አገራችን አንድነቷን፤ እኛም ነፃነታችን ጠብቀን በኩራት እንዳንኖር፤ ዘመናዊ መሳሪያውን በመተማመን፤ በትቢት ተወጥሮ፤ ለሆዳቸው ያደሩ ሆዳም አገር በቀል ባንዳዎችን መልምሎ፤ በባርነት ሊገዛን የመጣውን የጣሊያን ጦር፤ ጀግነት እንጂ የመሳሪያ ጥራት፤ ለድል አያበቃም ብለው፤ የነፃነት ተጋድሏቸው ታሪክ፤ በድል ተጠናቆ ለዘለዓለም በትውልድ እንዲዘከር ያደረጉት፤ በዚሁ ወርኃ የካቲ መሆኑ ነው።

ዛሬም ከነዚያ የባንዳ የልጅ ልጆችና፤ በገንዘብ ከተገዙ ምንደኞች ጋር፤ ለነጻነትና ለዴሞክራሲ ሲታገል መሰዋዕት የሆነው ታጋይ ጎቤ መልኬ፤ የካቲትን እንደ ቅደመ አያቶቹ እና አባቶቹ በደሙ ዋጅቷት አልፏል። ታጋይ ጎቤ የሰው ልጅን መብትን ለማስከበር ወደ ትግል ሲገባ ይህን ነብስን ያህል ክቡር ዋጋ እንደሚያስከፍለው አውቆና አምኖ ነበር፤ የወያኔን ጦር እና በገንዘብ የተገዙ ባንዳዎች ለመፋለም በርሃ የወረደው።

ወያኔ ታጋይ ጎቤን በማጥፋት ትግሉን ያደፈነ ሊመስለው ይችላል። ይህን ተሥፋ ሰንቆ፤ አርበኞቻችን በመጨፍጨፍ፤ የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም የጀመረው፤ ዛሬ፤ በአርበኛ ጎቤ መልኬ ላይ ብቻ አደለም። ወያኔ፤ በሺ የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን በእሥር ቤት እያማቀ ባለበት ሰዓት፤ የከተማው ትግል፤ ጭራሽ፤ መልኩን ቀይሮ እልህ አሥጨራሽ ትግሉ ቀጥሏል። በመቶ የሚቆጠሩትን፤ እየገደለ ቢቀጥልም፤ ከነ ታጋይ መልኬ በፊት የተጀመረው የትጥቅ ትግል የበለጠ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዛሬው የታጋይ ጎቤ መልኬ፤ መሥዋዕትነ፤ በጀግንነት ሊታገሉ ዱር በርሃ ከገቡት በመለስ፤ በዚህች ወርሃ የካቲት ሌላ ጀግኖችን የሚወልዱ ሺ ሴቶች፤ ሺ መልኬዎችን ፀንሰው እንደሚያድሩ ፈጽሞ አንጠራጠርም!!

ወያኔ፤ ግን የራሱ የእውር ጉዞ ባይታየውም፤ ከደርግ ውድቀት እንኳ ትንሽ መማር ያልቻለ፤ ሁለት እግር ያለው አውሬ ነው። ደርግ ሕዝባችን በጭካኔ በጨፈጨፈ መጠን፤ የበለጠ ሕዝባችን ልቡ እንዲሸፍት፤ እና አጋጣሚውን ሁሉ ተጠቅሞ ሥራዓቱን የሚያንኮታኩትበትን ጊዚ እንዲጠብቅ አዘጋጀው እንጂ። ለዚያም ነው ወያኔ ሲመጣ፤ የይሻል ይሆናልን ተሥፋ ሰንቆ፤ በሩን ከፍቶ ምኒልክ ቤተ መንግሥት እንዲገባ ያደረገው። ይህን ግን ልብ አላሉም!! እኛ ግን፤ “የሚያደርጉትን አያውቁም እና ይቅር በላቸው” አንልም። ከእግዚአብሔር በታች፤ የነ አቡነ ጵጥሮስን መሥዋዕትነት እየዘከርን፤ ታሪካቸውን በተግባር ለመድገም የበለጠ እንጠነክራለን እንጂ።

ይህ ከወያኔ ጋር የምናደርገው ትግል፤ አገርን እንደ አገር ሕዝብን በማንነቱ እና በነፃነት፤ የማሥቀጠል ጉዳይ በመሆኑ፤ ወያኔ፤ ሺ ሆዳም ባንዳዎችን፤ በዙሪያው ኮልኩሎ፤ በጭካኔ፤ ቢዘምትብንም፤ ባንዳ ለሆዱ እንጅ፤ ለክብሩ ቆራጥ አለመሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን። ትግላችን ግን የሚሊዮኖች ነው። የወያኔንም ጭካኔ፤ የምንሰብረው፤ እጥፍ ድርብ ምላሹን በመሥጠት ነው።

በመሆኑም፤ ዛሬ ወያኔ፤ በጎንደር አርበኞች ላይ፤ እየወሰደ ያለው፤ አረመኒያዊ ግድያ፤ ነገ ደግሞ፤ ጊዜውን ጠብቆ፤ በመላ ኢትዮጵያ በያላችሁበት በራችሁ ድርሥ እስኪመጣ በመላ አገራችን ያላችሁ አርበኞች፤ በዝምታ ተራችሁን አትጠብቁ!! በየአላችሁበት የነፃነት ተጋድሏችሁን አቀናጁ እና የወያኔን ፍፃሜ አሳጥሩ እንላለን።

ጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት በታጋይ ጎቤ መልኬ ሞት፤ ከፍተኛ ሐዝንና ቁጭት የተሰማው መሆኑን ይገልጻል። ይሁን እንጂ፤ በቀጣዩ ትግላችን፤ የጎቤን ደም እጥፍ ድርብ ለማሥከፈልም ይሁን ለነፃንታችን የከፈለውን የህይውት ዋጋ ከግብ ለማድረስ፤ ትግሉን እየቀጠሉ ካሉት የትግል ጓዶቹ ጎን በመቆም፤ የድርሻችን እንደምናበረክት ለመግለጽ እንወዳለን። ለነጻነት የቆረጠ ሕዝብ፤ ነጻነቱን እስኪ ጎናጽፈ ድረስ፤ ታጋይ ሲሰዋ ሌላ ታጋይ እየተካ ለግብ እንደበቃ የህብረተሰብ ሳይንስ ያስረዳናል። በደቡብ አፍሪካ፤ በቪትናም የተመለከትነው የቆራጥ ህብረተስብ ተጋድሎ የሚያስተምረን ይህንን ነው።

ለጎቤ ቤተሰቦች እና ለታጋይ ጓዶቹ መጽናናቱን እንመኛለን

ታጋይ እንጅ ትግል አይሞትም!!!!!!!

ጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

በአድዋ ጦርነት የመረጃ (Intelligence) ሚና (መስቀሉ አየለ)

$
0
0

በሃገርና በህዝብ ደህንነት ጥበቃ ሚኒስቴር ስር ፤ ሐምሌ 1973 ዓ.ም በታተመውና “ደህንነት” በተሰኘ መፅሄት ከገፅ 28 – 38 ከአድዋ ጦርነት በፊት ፣ በጦርነቱ ጊዜና ከጦርነቱ በኋላ በጣሊያንና በኢትዮጵያ ወገን የተካሄደውን የስለላ ስራ አስመልክቶ  “በአድዋ ጦርነት የኢንተለጀንስ ሚና” በሚል ርዕስ ስር የሚከተለውን ጽሁፍ አስፍሯል።

ሀ)የጠላት መረጃ

የኢጣሊያ መንግስት ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛቱ ለማድረግ ሲነሳ የራሱን ገንዘብና የወታደሮቹን ደም በብዛት ለማፍሰስ አልፈለገም። ኢትዮጵያን በቀላሉ ለመያዝ ይቻላል የማለት እምነት ያደረበት የኢትዮጵያን የፊውዳላዊ ፖለቲካ ጠባይ በእጅ አዙርም ሆነ በቀጥታ ከመገንዘቡ የተነሳ ነበር። የዒጣሊያ ተመራማሪዎች በብዛት ወደ ኢትዮጵያ ከመግባታቸው በፊት በአፄ ቴዎድሮስ ላይ የደረሰው ችግር ለኢጣሊያኖች ከፍተኛ ትምህርት ሆኗል። ኢጣሊያኖች በዝብዝ ካሳ (ዮሃንስ)፣ ዋግሹም ጎበዜና(ተክለጊዮርጊስ 2ኛ)የወሎ መኳንንት ቴዎድሮስን ባይክዱ ፣ ለእንግሊዞች መንገድ ባያሳዩና ስንቅ ባይሰጡ ኖሮ የብሪታኒያ ሠራዊት መቅደላ ገብቶ ቴዎድሮስን ማሸነፍ ቀርቶ ላስታ እንኳን ለመድረስ በተሳነው ነበር ብለው አመኑ። ከቴዎድሮስ በኋላ በመሳፍንቱ መካከል ስለቀጠለው ሽኩቻና አለመግባባት በሰሜን ከ“ሳፔቶ”ና ከሌሎች ሚሲዮናዊያን የኢጣሊያ መንግስት መረጃ ሲያገኝ በመሃልና ደቡብ ሃገር ደግሞ ኩማሳይና ከጭፍሮቹ እንዲሁም ከ“ነቼኪ” ብዙ ዕውቀት አግኝቷል። መጀመሪያ አሰብ ቀጥሎ ምፅዋ በኢጣሊያ እጅ ከገቡ በኋላ ደግሞ በስመ ሃገር ጎብኚዎችና ተመራማሪዎች ኢትዮጵያን በማጥለቅለቃቸው የኢጣሊያ መንግስት ስለ ሃገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታዎች ከኛ የበለጠ የሚያውቅ የለም ብሎ ተማመነ።

ለጎጃሙ መስፍን ለንጉስ ተክለሃይማኖትም ድልድይ እንዲሰራላቸው ተብሎ  ከኢጣሊያ መንግስት የተላከላቸው መሃንዲስ ሳሊምቤኒ በቅርብ አማካሪያቸው ነበር። ሳሊምቤኒ በጎጃም ጠጅና ቆነጃጅት በመማረኩ የኢጣሊያ መንግስት ቢናደድበትም ከዮሃንስ ከምኒሊክና ከሌሎች መሳፍንት ጋር ስለነበራቸው ጠብም ሆነ ወዳጅነት ብዙ ጠቃሚ መረጃ ሰጥቷል።

የዮሃንስ ቤተ መንግስት በብዙ የታወቁ የኢጣሊያ መልዕክተኞች ተጎብኝቷል። ከነዚህ መካከል አንቶኖሊ አንዱ ሲሆን ከተቀሩት መካከል ደግሞ ቢያንኪ ፣ ኔሪኪኒና ትራቬርሲ ይገኙባቸዋል። እነዚህን መልዕክተኞች ስለ ዮሃንስ የውስጥና የውጭ ፖለቲካ ብዙ ያስጠናቸው የነበረው የነበረው የንጉዙ መሐንዲስ ኢጣሊያዊው  ጃኮሞ ናሬቲ ነበር። ናሬቲ በዮሃንስ ከመቀጠሩ በፊት ከርታታ አናጢ ነበር። ንጉሱ ስራውን ወደው የቤታቸው ግንበኞች ፣ አናጢዎችና ወርቅ አፍሳሾች ተቆጣጣሪ አደረጉት። አክብረው ሸልመው ፣ ሾመው ቢያስቀምጡት የአንድ ጥቁር ንጉስ አሽከር መሆን ስላላስደሰተው የኢጣሊያ መንግስት ኢትዮጵያን ከያዘ በኋላ ይሾመኛል በማለት የጌታውን ምስጢር በየጊዜው ይዘከዝክባቸው ነበር። መሃይሙ ናሬቲ ከኢጣሊያ ንጉስ ኒሻንና ሽልማት በይፋ ሲላክለት ዮሃንስ ለምን ብለው አይጠይቁንም ኖሯል ? ናሬቲ ነገር ማቀበሉን ለነገ እንጀራ ማውጫ አስቦ መሆኑን እያወቁ ከቤታቸው ማግለል እንዴት አቃታቸው ? አሉላ በአስመራ የሚያልፉትን ኢጣሊያኖችና ከነሱ ጋር የተቀራረበውን ኢትዮጵያዊ ሲጠረጥሩና አንዳንዶቹን ከነዚህም አንዱ ሳሊምቤኒ ሲሆን ሲያሴሩ አጼ ዮሐንስ አማላጅ ሆነው ማስፈታታቸውን የሁል ጊዜ እንቆቅልሽ ነው። ከአሉላ በስተቀር የኢጣሊያ ፍላጎት ምን እንደሆነ የገባው ሌላ የኢትዮጵያ መኳንንት የለም የሚለው የጊዜው የኢጣሊያኖች እምነት ልክ ይመስላል።

አጼ ዮሐንስ በበኩላቸው ኢጣሊያ በምጽዋና በአካባቢው ስለሚያካሂደው ፖለቲካ መረጃ ለመሰብሰብ ሳይሞክሩ አልቀሩም ነገር ግን ያሰባሰባቸው ዘዴና የሰብሳቢዎቹ ስም ለናሬቲና ምጽዋ ለነበሩት የኢጣሊያ ሹማምንት በመታወቁ ብዙ ጠቃሚ መረጃ አላገኙም። ለምሳሌ በምጽዋ በኩል ለዮሐንስ ወይም ለሌላ መስፍን ኢጣሊያኖች ከፍተው ሳያነቡት አንድም ደብዳቤ አያልፍም ነበር። ዮሐንስ ወይም አሉላ እንዲያውቁት የተፈለገ ነገር በደብዳቤው ከተጠቀሰ ደብዳቤውና አድራሹ ከምጽዋ እንዲያልፍ ይደረጋል። ሌላው ደግሞ አንድ ቴዎድሮስ ጂዩርጂዩ የተባለ ኢትዮጵያዊ በምፅዋ በአስተርጓሚነት ለኢጣሊያኖች ይሰራ ነበር። ከትግራይ ብዙ ደብዳቤ ይላክልሃል ተብሎ ተከሶ ለዮሐንስ ወይም ለአሉላ መረጃ ይልካል ተብሎ በመጠርጠሩ ከስራው ተባሯል።

አጼ ዮሐንስ ለብሪታኒያ መንግስት ደብዳቤዎች ሲልክ የምፅዋ አስተዳዳሪዎች ይሰሙታል። የብሪታኒያ መንግስት ላለማስቀየም ሲሉ ከፍተው አያነቧቸውም ግን በለንደን የሚገኘው የኢጣሊያ አምባሳደር ወደ ብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሄዶ ጉዳዩን ምንድን ነው ብሎ ይጠይቅና ቁም ነገሩ ወዲያው ይነገረዋል። ትንሽ ቆይቶም የዮሃንስ ደብዳቤና የብሪታኒያ መንግስት መልስ ቅጂዎችን ወደ ሮማ እንዲያስተላልፍ ይሰጡታል። የብሪታኒያ መንግስት ለኢጣሊያ በኢትዮጵያ መስፋፋት ድጋፉን ያሳየው በዚህ ብቻ አልነበረም። የንግስት ቪክቶሪያን መልስ እንዲያደርስ የተላከው ሻምበል ሐሪሰን ስሚዝ የኢጣሊያንን ዕቅድ ለዮሐንስና ለአሉላ እንዳያወጣ ስለተፈራ ይቀርቡለታል ለተባሉ ጥያቄዎች ሁሉ በምፅዋ የኢጣሊያ ሹማምንት የሚሰጠውን መልስ ተደጋግሞ ከተነገረው በኋላ ነበር መንገዱን እንዲቀጥል የተፈቀደለት። ለዮሐንስ አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎች የሚገዙ ነጋዴዎች በኢጣሊያኖች በጣም በመጠራጠራቸውና በዓይነ ቁራኛ በመጠበቃቸው ምጽዋ ውስጥ ብዙ ችግር ይደርስባቸው ነበር። ከሃያ ሺ ጠገራ ብር በላይ የሚያወጡ ለዮሐንስ የተገዙ ዕቃዎች ይዞ በምፅዋ ወደ መቀሌ ማለፍ ስለፈራ በዜይላ አድርጎ አዲስ አበባ ደረሰ። ወደ ትግራይ ለማለፍ በመዘጋጀት ላይ እንዳለ አንቶኒሊ ነገሩን በመስማቱ  እስጢፋኖስን አስይዞ ለዮሐንስ የገዛቸውን እቃዎች በሙሉ ለሱ እንዲሸጥለት አስገደደው። ዮሐንስንና ምኒሊክን ይበልጥ ለማቀያየምና ለማቆራረጥ ዓላማው ነበርና አንቶኒሊ የዮሐንስን ዕቃዎች በሙሉ ከኢጣሊያ ንጉስ የተላከ ገፀ በረከት በማስመሰል ለምኒሊክና ለጣይቱ ሰጠ። የእስጥፋኖስ የግል ሻንጣዎች ሲፈተሹ አንድ በቱርክ ሃገር የታተመ ቦስፎ ኤጂፕሲየን የተባለ ጋዜጣ ተገኘበት በጋዜጣው ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ስለምታካሂደው ፣ በተለይ ደግሞ  እየጠበቀ ስለ ሄደው የኢጣሊያ መንግስትና የምኒሊክ ወዳጅነት ዘርዘር ያለፅሁፍ ጽሁፍ ስለነበር ጋዜጣው ተወረሰ። እስጢፋኖስ ጉዞውን አቋርጦ በመጣበት መንገድ ወደ ምጽዋ እንዲመለስ ተደረገ። ጥብቅ ክትትል  እንዲደረግበት አንቶኒሊ ወደ ምፅዋ ቴሌግራም አስተላለፈ።

ምኒሊክ በአንቶኒሊ ላይ የነበራቸው እምነት በመጨረሻ ወደ ውጫሌው ውል አደረሳቸው። የውሉ ረቂቅ ሮም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ መምጣቱን በደንብ ሳይገለፅላቸው ትርጉሙን አዘጋጅቶ ካማካሪዎቻቸው ጋር ሳይነጋገሩበት አስፈረማቸው። የአማርኛው ቅጂ ብቻ ተነቦላቸው 17 አንቀፅ የሚረባ ጉዳይ ስላላዘለ ደጋግመው ለምን ያስፈልጋል ይቅር ቢሉት ቢጨመርስ ምን ይጎዳል ስላላቸው በውሉ እንዲያሠፍረው የፈቀዱለት በነበረው የቀረበ ግንኙነት ነበር።

ምኒሊክ አንቶኒሊ የተጠቀመባቸውን ያህል የመሳሪያ ስጦታ እንዲያስመጣላቸው አድርገው ከተጠቀሙበት በኋላ ለክብራቸውና ላገራቸው ነፃነት ሲሉ የውጫሌን ውል ለመሰረዝ ወሰኑ። እ.ኤ.አ በየካቲት 1893 ውሉ ውድቅ መሆኑን በይፋ ለዓለም አስታወቁ። የኢጣሊያ መንግስትም የአንቶኒሊ ፖለቲካ የተባለው እቅድ የከሸፈበት ምክንያት በምንሊክ በቃል አለመርጋትና ከሐዲነት ነው ብሎ አስተባበለ። በ 17ኛው አንቀፅ ሳቢያ ያገኘው መብትና ስልጣን ግን በምንሊክ ቃል ብቻ አይቀርምና በጦር ኃይል ለማስከበር ተዘጋጀ።

የኢጣሊያ ወታደሮች መረብን ተሻግረው ትግራይን መውረራቸውን ምኒሊክ እንደሰሙ ክተት አወጁ። እ.ኤ.አ በመስከረም 1895 የምንሊክ ሠራዊት ወደ ሰሜን ጉዞ በመጀመሩ የኢጣሊያ መንግስት ከመጠን በላይ ተደስቶ ምንሊክ ትግራይ ደርሰውለት በጦር ሜዳ አሸንፎ ኢትዮጵያን በቀጥታ ለመያዝ ቸኮለ።

በ 17ኛው አንቀጽ ምክንያት ምኒልክ የውጫሌን ውል በመሰረዛቸው አንቶኒሊ ወደ ሃገሩ ቢመለስም በአዲስ አበባ ብዙ የኢጣሊያ መንግስት ወኪሎች ቀርተው ነበር። አንደኛው ኮፑቺ  የተባለው ወኪል ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ የኖረና የምኒልክን  ሠራዊት ጥንካሬ በየጊዜው የሚገመግምና ምኒልክ ከሌሎች መሳፍንት ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በመከታተል ብዙ ዘገባ ያስተላለፈ ነበር። ዮሐንስ ገና በህይወታቸው ሳሉ አንድ ጊዜ የከዳ ሁለተኛም ይከዳልና በመሳፍንቱ እርስ በእርስ አለመጣጣም ተጠቅመን አሁኑኑ ኢትዮጵያን በኃይል እንያዝ እያለ የኢጣሊያንን መንግስት ለመገፋፋት ሞክሯል።

ለእርቅና ለስምምነት የሚሆኑ ሃሳቦችን አምጥተናል በማለት በዚሁ እ.ኤ.አ በ1893 የገቡት ኮሎኔል ፒያኖና ዶክተር ትራቪርሲ ዋና ተልዕኮአቸው የምኒልክን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ለይቶ ማወቅ ነበር። ሁለቱም መልዕክተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ጊዜ የተቀመጡና ለምንሊክ የውስጥና የውጭ ፖለቲካ እንግዶች ባለመሆናቸው እ.ኤ.አ በህዳር 1894 ለኢጣሊያ መንግስት ያቀረቡት ዘገባ የማሸነፍ እምነቱን አረጋግጦለታል። በነዚህና በሌሎች ወኪሎቻቸው ምንሊክ ወደ ሰሜን መጓዝ እስከ ጀመሩበት ጊዜ ድረስ የሠራዊታቸው ብዛት ፣ የመሳሪያቸው ጥራትና መጠን ለኢጣሊያኖች ገልጾ ነበር።

የኢጣሊያ መንግስት ምኒልክንና መንገሻን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹን መሳፍንትም በቅርብ ተከታትሏል። በሐረር የቢየነንፌልድ ኩባንያ የስለላ ተግባሩን ቀጠለ። በሳኮኒ ሞት ምክንያት የሐረር ቅርንጫፍ ኃላፊ ሆኖ የተተካው ፌልተር የራስ መኮንን ጥሩ ወዳጅ ሆነ። ራስ መኮንን ፌልተር የኢጣሊያ መንግስት ወኪልና ሰላይ መሆኑን አውቀዋል። የፌልተር ተልዕኮ መኮንን ምን ፍንጭ እንደሰጡት ለጊዜው አይታወቅ እንጂ እሱ እንዳግባባቸው እስከ አድዋ ጦርነት ዋዜማ ድረስ ጨርሶ አልተጠራጠረም። የኢጣሊያ መንግስት ከምኒሊክ ጋር ገና ከመጋጠሙ በፊት እንዳሸነፈ ያመነበት ዋናው ምክንያት ይህ ነበር።

በወሎና በአውሳ አውራጃ የኢጣሊያ ወኪልና ሰላይ ፔርሲኮ ሲሆን የርሱ ረዳትና አማካሪ ደግሞ አብዱራህማን ቤን ዮሱፍ የተባለ ኢትዮጵያዊ ነበር። አንቶኔሊ ከአውሳ ባላባቶች ጋር ጥሩ ግንኙነት ፈጥሮ ነበርና ፔርሲኮ የስለላና የማስከዳት ተግባሩን ለመፈፀም የጣረው አውሳ ተቀምጦ ነበር። በአብዱራህማን አማካኝነት ፔርሲኮ ከብዙ የአፋርና የሶማሊያ ባላባቶች ጋር ተዋውቆ በሃይማኖት ሳቢያ ኢትዮጵያውያንን  የከፋፈለ መስሎት ነበር። እንዲሁም በአብዱራህማን በኩል ከወሎው ገዥ ከራስ ሚካኤል ጋር ብዙ ጊዜ ስለተገናኘ ሚካኤል ምኒሊክን ይክዳሉ ብሎ አምኗል።

ሳሊምቤኒ ከጎጃም ከወጣ በኋላ ቋሚ የሆነ የኢጣሊያ ወኪል በደብረ ማርቆስ ባይኖርም ከተክለሃይማኖት ጋር የነበረው ግንኙነት አልተቋረጠም። በደብረ ማርቆስ ባለፉት ካንዳንድ የኢጣሊያ ዜጎችና እንዲሁም ከኢትዮጵያውያን መልዕክተኞች ባገኙት መረጃ ተክለሃይማኖት ምኒልክን በመፍራታቸውና በምኒልክ ትልቅነት በመቅናታቸው ከጎኑ እንደማይሰለፉ የኢጣሊያ መንግስት ተስፋ አድርጓል። የሽሬው ገዢ ራስ ሃጎስ ለመንገሻ ታማኝ በመሆናቸው በኢጣሊያኖች ቢታወቅም ሚኒልክን ይወጉልናል ብለው ተማምነዋል።

በመኮንን የሚመራው ጦር አምባላጌ ላይ መሽገው የነበሩትን ኢጣሊያኖች እ.ኤ.አ በታህሳስ 1895 ሲደመሰስ እንኳ መኮንንና መንገሻ ወደ እኛ ይዞራሉ የሚለው የኢጣሊያ እምነት ምንም አልቀነሰም። እንዲያውም ፌልተር ከሐረር በአስቸኳይ ተጠርቶ  በምፅዋ በኩል ወደ መቀሌ ተላከና በአንድ በኩል ምኒልክ የኢጣሊያንን መንግስት የበላይነት እንዲቀበሉ በሌላ በኩል ደግሞ መኮንን እንዲከዱ ለማድረግ ብዙ ጥረት አደረገ። መቀሌ ውስጥ የተከበቡት ኢጣሊያኖች ከሰንደቅ አላማቸውና ከመሳሪያቸው ጋር ወደ አዲግራት እንዲመለሱ ሚኒልክ ቢፈቅዱም የኢጣሊያ መንግስት ፈርተው ያደረጉ መስሎት ወዲያውኑ በማከታተል ያቀረበላቸው የሰላም ውል የሳቸውን ክብርና የኢትዮጵያን ነፃነት ጨርሶ የሚገፍ ሆነ። ባራቲየሪ የሰላም ውል ረቂቅ እያስያዘ ተራ በተራ የጦር መኮንንኖቹን የላከው ምኒልክ ያቀብሉታል በማለት ሳይሆን የሚኒልክን ሰፈርና የሠራዊታቸውን ወኔ በየ እለቱ ለመገምገም ሳይሆን አይቀርም። እ.ኤ.አ በ1896  በየካቲት ወር መጀመሪያ ገደማ ሚኒልክ መቀሌን ከለቀቁ በኋላ ግን በየት አቅጣጫ እንደሚያመሩ ባልታወቀበት ጊዜ ወደ ሰፈራቸው የላከው ሻለቃ ሳልሳ ዓላማው ውል ለመዋዋል ሳይሆን ወደ አዲግራት ያመሩ እንደሆን ለማወቅና የሠራዊታቸውን ስንቅ ሁኔታ ለማጥናት እንደነበረ አያጠራጥርም።

በምኒልክ በኩል ደግሞ የኢጣሊያኖች ኃይል ብቻ ሳይሆን አሰፋፈራቸውና የጦር ዕቅዳቸው ሁሉ በደንብ የታወቀ ይመስላል። ሚኒልክም ሆኑ መንገሻና አሉላ መረጃውን ያገኙት ከነ እገሌና እገሌ ነበር ለማለት የሚያስችል ምንጭ እስካሁን ባይገኝም ፤ ባራቲየሪ ደጋግሞ እንደፃፈው ሚኒልክ አንዳችም ነገር አላመለጣቸውም። ለዚህም ነው ኢጣሊያኖች እንደጠበቁት ሚኒልክ በዕዳጋ ሐሙስ አድርገው ወደ አዲግራት ያላመሩት። እስካሁን ድረስ የሚኒልክ ኃይልና የጦር ስልት ያላሰጋው የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስፒም የሚኒልክ ወደ ዓድዋ ማዝገም የኢጣሊያንን ጦር ከየምሽጉ ለማስወጣት የታቀደ ዘዴ መሆኑን መረዳት ጀመረ።

እ.ኤ.አ በ1895 ጥር ወር መጨረሻ እስከ ዓድዋ ጦርነት ዕለት ድረስ ሁለቱ ወገኖች የእያንዳንዳቸውን ጦር ሠፈር በብዙ መንገድ ሰልለዋል።  በመሰለል ብቻ ሳይወሰኑም አሳሳች መረጃዎችንም ነዝተዋል። የሚኒልክ ጦር ከመቀሌ ተነስቶ ዓድዋ እስኪገባ ድረስ የኢጣሊያ መኮንኖች መጠነኛ ርቀት በመጠበቅ ተከትለውታል። መረጃቸውንም በመስተዋት በማንፀባረቅ እስከ ባራቲየሪ ሠፈር ድረስ አስተላልፈዋል። በተጨማሪም ከሚኒልክ ጦር ጋር ከሚጓዙ ሠዎች መካከል ኢጣሊያኖች የተማመኑባቸው ሰላዮቻችን ናቸው የሚሏቸው ነበሩ። የነዚህ ሠዎች ተግባር የየዕለቱን ሁናቴ ከማስተላለፋቸውም በላይ የሚኒልክ የጦር ዕቅዶች ምን እንደነበሩ ማወቅም ነበር። በስም ከታወቁት አንዱ ፊታውራሪ ገብረዝጊ ነበሩ። በገብረዝጊ ይላክ የነበረው መረጃ ምኒልክ አሉላን መረብን ተሻግረው አዲኳላ የነበረውን የኢጣሊያኖች ምሽግ እንዲወጉ ልከዋቸዋል ፤ ራሳቸውም ከጦራቸው ጋር ይከተላሉ የሚል ነበር። ባራቲየሪና ጄነራሎቹ ምኒልክ አዲኳላ ዞረው ሊከቡን ነው ከአስመራ ጋር ያለንን መገናኛ ሊቆርጡብን ነው ብለው ስለሰጉ ዓድዋ ላይ ለመዋጋት ከተገደደበት ዋናው ምክንያት ይህ ነበር።

ኢጣሊያኖች የኛ ሰላዮች ናቸው ካሏቸው ሌሎች ሠዎች ብዙ ዓይነት መረጃ በዓድዋ ጦርነት ዋዜማ ደርሷቸዋል። አብዛኞቹ ሚኒልክን ዓድዋ ጦርነት ላይ መገፋፋት ብቻ  ሳ ይሆን የማሸነፍ እምነታቸውን የሚያጠናክሩ ነበር። ከሚኒልክ ሠፈር ደጋግመው የደረሱ መረጃዎች የሚኒልክ ጦር ስንቁን ጨርሶ ወደ ዝርፊያ ገብቷል በዝርፊያ ምክንያት እርስበርሱ እየተጨራረሰ ነው። በሠፈሩ ወረርሺኝ ገብቶ ወታደሩ እየረገፈ ነው የሚሉ ነበር። የነዚህ መለእክቶች አብሳሪዎች እነማን እንደነበሩ እስካሁን ከተገኙት ምንጮች ለማወቅ ያስቸግራል የምኒልክ ፀኃፊ የነበሩት ግራዝማች ዮሴፍ ለፈረንሳዊው ሞንዶን ቪያዩት ወዲያው ከአድዋ ጦርነት በኋላ ሲፅፉ መረጃዎቹን ለኢጣሊያ የጦር መሪዎች የሰጠ አንድ እጁ ሽባ የነበረ ሠው ነው ብለዋል።

ክሪስፒ በኢጣሊያ ምክር ቤት በተጠየቀበት ጊዜ እኛ አላጠፋንም ያጠፋው ምኒሊክ ነው ብሏል። አንቶኔሊ በ 17ኛው አንቀፅ ላይ ያጭበረበረው እንደማጭበርበር ሳይቆጠር ሚኒልክ ራሴንም አገሬንም ለባርነት አሳልፌ አልሰጥም ማለታቸው በክሪስፒና በባራቲየሪ ዓይን ክህደት ሆነ። በክሪስፒ አስተያየት ሚኒልክ የውጫሌ ውል ያፈረሱት በሃገርና በነፃነት ፍቅር ሳይሆን በኢጣሊያን ጠላቶች(ፈረንሳዮችን ማለቱ ይሆናል)ቀስቃሽነት ነው። ምኒልክ መንገሻ መኮንን ፣ ስብሐት ሐጎስ ተፈሪንና ሌሎችም ሁሉም በቃላቸው የማይረጉ ፣ ለኢጣሊያ መንግስት የሰጡትን ተስፋ የረሱ ናቸው ተብለው ተወቅሰዋል ፣ ተሰድበዋል። ይህ የሚያሳየው ኢጣሊያኖችና ፣ እንዲሁም ሌሎች ኤሮጳውያን በጥቁሮች ላይ የነበራቸውን ንቀት ምንኛ እንዳሳሳታቸው ነው። የኢጣሊያኖች ስህተት ሞኝ አገኘን ሲሉ በመሞኘታቸው ነው፡ አንድ ቀንደኛ ፋሺስት የአድዋ ጦርነት ጥናቱን “በውትድርናችንና በዘራችን በመመካታችን ፣ በተለይ ደግሞ ከፊታችን ስለነበረው ጠላታችን ምንም ነገር ባለማወቃችን የነዚያን ብጭቅጭቅ ለባሽ ሕዝብ እውነተኛ ዋጋ ለመገመት አልቻልንም። ብጭቅጭቅ ልብሳቸው እጅግ በጣም ከፍተኛ ደረጃ ያለው የውትድርና ጠባያቸውን ደብቆት ነበርና” ሲል ደምድሟል።

 

 

ለ)የወገን መረጃ

ከዓድዋ ድል በኋላ ከአፄ ምኒልክ ሠራዊት ያመለጡት ጥቂት የኢጣሊያን መኮንኖችና ወታደሮች “ሱማትራ” በምትባለው መርከብ ተጭነው እ.ኤ.አ መጋቢት 24 1888 ዓ.ም ናፖሊ ሲገቡ በጦርነቱ ጊዜ የደረሰውን ሁሉ በውነተኛ መልኩ ይገልጡ ጀመር። “ያየ ይናገር ፣ የቀበረ ያርዳ” እንዲሉ የጦርነቱ ወላፈን የገረፋቸው ሠዎች የሰጡት ምስክርነት በየፈርጁ ተሰብስቦ ቢሆን ኖሮ የኢጣሊያኖችና ተቆርቋቂዎቻቸው ስለ አድዋ ድል ከጊዜ በኋላ የለጣጠፉት የሐፍረት ምክንያት ከታሪክ ገፅ እየተቀረፈ እንደሚረግፍ አያጠራጥርም። ኢትዮጵያ አሸነፈች ሲባል የሞራል ድል የተመቱት ኢጣሊያኖች ብቻ ሳይሆኑ በዚያን ጊዜ አውሮፓን “ማን ያህልሻል” “ምን ተስኖሽ” እያሉ የካቡ አዝማሪዎችና የጣሊያንን ወራሪ ሠራዊ “ባሻህ ውረድ” በማለት የሸኙ አጫፋሪዎች ሁሉ ነበሩ።

ዓድዋ ላይ በዱብ ዕዳው እንደተደናገጡ አውሮጳውያን እውነት እውነቱን ተናገሩ። በኋላ ግን ልባቸው መለስ ሲል የኢጣሊያ ወራሪዎች ውርደት የነሱም መሆኑን በመገንዘብ የኢትዮጵያን ድል ለማወየብና ታሪኳንም ለማድበስበስ ፀሃፊዎቻቸው ያላውጠነጠኑት ዘዴ አልነበረም። በተለይም የታሪኩን ሐቅ ለማዛባት “ኢትዮጵያ ለምን አሸነፈች ?” በማለት ፈንታ “ኢጣሊያኖች ለምን ተሸነፉ ?” በሚል ጥያቄ ላይ በማተኮር:-

  • የሃበሻ ሠራዊት በብዛቱ ዋጣቸው
  • የኢጣሊያን ሠራዊት ወደ ዓድዋ ሲያመራ መንገድ ተሳሳተ
  • በኢትዮጵያ ሠራዊት ውስጥ አንድ መቶ ከሠላሳ ሦስት የመስኮብና ስድሳ የፈረንሳይ መኮንኖች ስለነበሩ ስትራቴጂውን የመሩት እነሱ ነበሩ።

በማለት እውነቱን ለማፋለስና ገመናቸውን ለመሸፈን ይጥሩ ነበር። ይኸ ሁሉ ሀበሻ ፈረንጅን በጀግንነቱና በጦር ስልቱ አሸነፈ እንዳይባል ነበር።

እኛ ግን በኢትዮጵያዊነታችን ያንን ሁሉ ወሬ ተመልክተን ተጨባብጠን ሁኔታ ከትክክለኛው ምክንያት ጋር ለማገናዘብና እውነቱን ለመሳት ስንሞክር የሚገጥመን የታሪክ ክስተት ሌላ ነው። የዓድዋ ድል በሠራዊት ንቃት በመሳሪያ ብዛትና በአመራር ጥራት ብቻ የተገኘ ሳይሆን የጀግንነትና የመስዋዕትነት ሚናም ተጫውተዋል። ከሁሉም የሚያስደንቀው ግን በዓድዋ ጦርነት ጊዜ የኢትዮጵያ የመረጃ ድርጅት በኢጣሊያ ላይ መረቡን ዘርግቶ ለድሉ ያደረገው አስተዋፅዎ ነበር።

የመረጃ ስራ ህቡዕ ስለሆነ በታሪክ ጉልህ ቦታ ተሰጥቶት አይታይም ነበር። የመረጃ ሠራተኞች በሙያቸው ጠባይ ምክንያት ስማቸው ሳይጠራ ማዕረጋቸው ሳይታወቅ ሲያልፉ እጅግ በጣም ጥቂቶቹ በይፋ ይታወቁ ይሆናሉ። ሌሎቹም ከጊዜ በኋላ ለመጪው ትውልድ ስም አውርሰው ይሆናል። በአጠቃላይ ህቡዕ ሠራዊት ግን መኖሩ ሳይታወቅ ፤ አለመታወቅ መመሪያው በመሆኑ ሠይፍ መዝዞ ገዳይ ሳይል ያልፋል።

በዓድዋ ጊዜ ይህ ህቡዕ ሠራዊት ኢጣሊያንን ምን ያህል አስቸግሮት እንደነበረና በተልእኮ ላይ የተያዘውም ቢሆን ሕይወቱን ከምንም ሳይቆጥር እንዴት መራሩን ፅዋ በጸጋ እንደተቀበለ ያዩ ኢጣሊያኖች ከአድዋ በኋላ ከሰጡት ምስክርነት አንዳንዱን እንጠቅሳለን።

የዓድዋ መነሻ ውጊያ ሁለት ቀን ሲቀረው የጦር ኃይሉ ጀነራሎች ከፍተኛ ውይይት ለማድረግ አዲግራት ውስጥ በተሰበሰቡ ጊዜ የበላይ መሪያቸው ጀነራል ባራቲየሪ ስለጦር ግንባሩ ጠቅላላ ሁኔታ ገለጣውን በማጠቃለል “የሁለት ቀን ስንቅ ቀርቷል። ከኋላ መንገዱ ተዘግቷል። ምርጫው መዋጋት ወይም ማፈግፈግ ነው። ያለን መውጫ አዲቀይህ ብቻ ነው። ምን ትመክራላቹ ?” ብሎ መድረኩን ለውይይት ከፈተ። በዕድሜ ከሁሉም ያንስ የነበረው ጀነራል ዳቦርሜዳ “ወደኋላ ማለትን ሃገራችን አትቀበለውም። ሁለትም ሶስትም ሺህ ሠው ቢሞትብንም ተዋግተን እንሸነፍ እንጂ አናፈገፍግም” አለ። ጀነራል አረሞንዲና ጀነራል አልቤርቶኒ ይህንኑ ሃሳብ ደገፉ።

በእድሜ የሁሉም ታላቅ የነበረው ጄነራል ኤሌና የተሰነዘሩትን አስተያየቶች በጥሞና ካዳመጠ በኋላ “የደረሱን መረጃዎች ምን ይላሉ ?” ብሎ ጥያቄ አቀረበ። እዚህ ላይ ታሪኩን የተረከው ሠው የባራቲየሪን መልስ መቅደምና የራሱን አስተያየት ጣልቃ በመግባት “ባራቲየሪ የኛን ብር በልተው በማይጠግቡ መረጃ አቅራቢ ሃበሾች ተከበዋል። ሠዎቹ ውስጥ ውስጡን ለጠላት እየሰለሉ ይጫወቱብናል” በማለት እውነቱን አጋልጧል።

አሁን ባራቲየሪ ለኤሊና የሰጠውን መልስ እንስማ

ከምኒሊክ ሠራዊት አንዱ ሲሶ ከድቶ እግረ መንገዱን አክሱምን ዘርፎ ወደ ሽሬ ዘልቋል። አንዱ ሲሶ  ደግሞ ወደ ሸዋ ተመልሷል። ንጉስ ተክለሃይማኖትና ራስ ሚካኤል ነገሩ እስኪለይለት አንቀሳቀስም ብለዋል የሚል መረጃ ደርሶናል

ሲል መልስ ይሰጠዋል። ጄኔራል ኤሊና ይህን መልስ ሲያገኝ “እንግዲያውማ የሚሻለው ያለንን ኃይል አስተባብረን ጠላትን መምታት ነው” ይልና የሌሎቹን ጄኔራሎች አስተያየት ያጠናክራል። ጀነራል ባራቲዬሪ “ሌላ የምጠብቃቸው መረጃዎች አሉ ሲደርሱኝ መጨረሻውን ውሳኔ አስታውቃችኋለው” ብሎ “ዛሬ ማታ ራታችን አድዋ ላይ ነው” በሚለው እንደ ተረት ሲጠቀስ በሚኖረው ዓረፍተ ነገር ውይይቱን ይዘጋል። ጄኔራል ኤሊና አሁንም የመረጃው ነገር ስለከነከነው ወደ  ጄኔራል ጋሊያኖ መለስ ብሎ በጆሮው “ይህ የራቱ ነገር ምን ይመስልሃል” ብሎ ሲለው “ጄኔራል እንዲህ ካሉ ጠላት አድዋን ለቆ  መሄዱን በእርግጥ ቢደርሱበት ነዋ” ብሎ መለሰለት። በዚሁ ጉባኤው ተበተነ።

በማግስቱ ሲጠበቅ የነበረው “ዓድዋ የሚገኙት ሃበሾች በየድንኳናቸው ተኝተው ያንቀላፋሉ” የሚለው መረጃ ደረሰ። መረጃው የተቀናበረው በምኒሊክ ድንኳን ውስጥ መሆኑን ሳይጠረጥር ፣ የላከው ሠው ምኒልክ ጦር ሠፈር ገብቶ መውጣቱ ብቻ ሙሉ ዕምነት ስላሳደረበት ጄኔራል ባራቲዬሪ የዓድዋን ውጊያ ከፈተ።

እንደ እውነቱ ከሆነ በዚያች ሌሌሊት በኢትዮጵያ ሠፈር ማንም አልተኛም። ቃፊሩም አድፍጦ ይጠብቃል ፤ ሠራዊቱም በተጠንቀቅ ላይ ነበር። በማለዳ ኢጣሊያኖች የተኮስኩት የመጀመሪያ ጥይት የራሳቸውን የጦር መርዶ የሚያበስር መሆኑን አያውቁትም ነበረ። በእውነቱ የባራቲዬሪ የመረጃ ማኅደር “ከባድ ምስጢር” የሚል ምልክት ተደርጎበት እንደሆነ ምስጢርነቱ ለኢጣሊያኖች እንጂ ለኢትዮጵያውያን አልነበረም። የባራቲዬሪ አዕምሮ በእኛ ሠዎች እጅ ወድቆ ነበር ማለት ነገሩን ማጋነን አይሆንም። ዓድዋ ላይ የመረጃው ቅድመ ውጊያ ለኢትዮጵያ ጀግኖች ሰፊውን የድል ጥርጊያ በመክፈት አስደናቂ ሚና ተጫውተዋል ማለትም ታሪካዊ ሁነት ነው። የወራሪው ተቆርቋሪዎች እንደሚሉት የኢትዮጵያ ድል የተገኘው በሠራዊት ብዛት ፣ በጠላት ስህተት ፣ በውጪ ዕርዳታ ወዘተ . . .  ብቻ ሳይሆን ሁኔታዎችን ቀድሞ በማወቅና ጠላትን ወጥመድ በማስገባት ኢትዮጵያውያን ባሳዩት የስልት ብልጫ ጭምር ነበር።

የኢትዮጵያ ጠላቶች በተለይም የሠራዊቱን ክንድ የቀመሱት ኢጣሊያኖች በኢትዮጵያ የመረጃ ድርጅት ላይ ያላቸው ጥላቻ መጠን የለውም። ሙያውን ሲያሳንሱ ወታደራዊ መረጃ ማለት ይቅርና በተለመደው አነጋገር “ስለላ” ለማለት እንኳ ይከብዳቸዋል። በኢጣሊያኖች አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መረጃ አባል የሚባል ነገር የለም። ይህን ተግባር ለሚፈፅሙ ሠዎች የሚሰጧቸው ቅፅል “ወንበዴ” “ከሃዲ” “ወሬ አቀባይ” ወዘተ . . . ነው። እንኳን ለኢትዮጵያ የሚሰሩትን ለራሳቸው አገልግሎት የቀጠሩአቸውንም ቢሆን “ወሬ አቀባዮች” ከማለት በተሻለ ስም አይጠሩአቸውም ነበር። ምነው ቢባል ፤ ሀበሻ ጥሬ ወሬ ማቅረብ ነው እንጂ ቅንብሩማ የነባራቲዬሪ ድርሻ ነውና።

በዓድዋ ጦርነት ላይ የኢትዮጵያ መረጃ የተጫወተው ሚና የጄኔራል ባራቲዬሪን አስተሳሰብ በማናጋት ብቻ አልተወሰነም፤ በጦር ሜዳውም ላይ እስከ መጨረሻው ደቂቃ የጠላትን የውጊያ አመራር አቃውሷል። ከዚህ አንፃር ፣ ከሁሉም ይልቅ የመረጃውን የመጨረሻ የበላይነት የሚያንፀባርቀው “ሊዚርቺቶ ኢታሊያና” (የኢጣሊያን ሠራዊት)የተባለው መጽሔት እ.ኤ.አ በሚያያዝያ  ቀን  1888 ዓ.ም ካሳተመው ረጂም ደብዳቤ የሚገኘው ፍሬ ነገር ነው።

አስተውል ፣ ዕለቱ ሰንበት ፣ ጊዜው ማለዳ ፣ ቦታው አድዋ ቀኑ ታሪካዊ ነው እነሆ አልቤርቶኒ ፣ ዳቦርሜዳ ፣ አሪሞንዴ እነዚህ ሶስት ጀነራሎች የተሰጣቸው ዓላማ ራዕዩ  የተባለውን ኮረብታ  ተባብረው መያዝ ነው። አንዱም ብርጌድ ጊዜውን ጠብቆ የተባለው ቦታ ደርሶ  የታዘዘውን ተግባር አልፈፀመም ፣ ሦስቱም ብርጌዶች ጎሕ ሲቀድ ውጊያውን እንዲጀምሩ ታዝዘው ነበር። አልቤርቶኒ ተኩስ ሊከፍት አስራ ሁለት ሠዓት ተኩል ይሆናል። አሪሞንዲ በበኩሉ ወደ ጦር ሜዳ የገባው ባልታወቀ ምክንያት በሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ ላይ ነው። ዳቦርሜዳ ደግሞ መዋጋት የጀመረው እስከ አምስት ሠዓት አርፍዶ ነው።

ባባራቲየሪ ማኅደር ከተሰገሰገው መረጃ አንዱ ረቢ አርአየኒ እና ኪዳነ ምህረት  በተባሉት ኮረብታዎች ላይ የኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ጦር ሠፍሯል የሚል ስለነበረ ፡ ዳቦርሜዳ ሲሆን በድብደባ ወይም በኃይል ረቢ አርአየኒን እንዲይዝ ፣ አልቤርቶኒም ኪዳነ ምህረትን በዚሁዘዴ ውንዲመታ ፣ አሪሞንዲ ደግሞ መካከሉን በስላች ገብቶ የዳቦርሜዳንና የአልቤርቶኒን ብርጌዶች በማገናኘት እንዲረዳ ነበር። ጉዞ ው ሲጀመር ዳቦርሜዳ ረቢ አርአየኒን በግራው ትቶ በማሪያም ሸዊቶ አምባ ስር ሸለቆውን እየተከተለ በመዞር ከረቢ አርአየኒ ይርቃል። “ምናልባት ይላል ደራሲው መንገድ ጠቋሚዎች አታለው ይሆናል . . .  እነሱም ልክ በዚያን ጊዜ ከመቅፅበት ተሰውረው አመለጡ . . .”

በነገራችን ላይ አልቤርቶኒም ያዝ የተባለውን የኪዳነ ምህረትን ኮረብታ ስቶ ለመያዝ ከታቀደው ከራዕዩ ተራራ በመራቅ ላይ ነው። አሪሞንዲ ደግሞ ወደ ራዕዩ ይገሰግሳል። “አውቆ ይሁን ተመርቶ አይታወቅም” ይላል ደራሲው። እንግዲህ የዓድዋ ዕለት ፣ “በተባለው ቦታ በታሰበው” የኢጣሊያን ብርጌዶች በመንገድ ጠቋሚዎች ምክንያት ለታላቁ ቀጠሮ ሳይደርሱ ቀሩ። መንገድ ጠቋሚዎቹ ግን ዓላማቸው መሟላቱን ከኢጣሊያን ጀነራሎች በፊት አውቀውት ስለነበረ  መልዕክታቸውን ፈፅመው ወደ መንደራቸው ተመልሰዋል። ይህ ያልገባው ወይም ያልተዋጠለት ኢጣሊያን ገና “መንገድ መሪዎቹ ወዴት ጠፉ” የሚል ገራገር ጥያቄ በልቦናው ያንገዋልለዋል። ነገሩን ለማሳጠር የዓድዋ ዕለት የኢጣሊያን ሠራዊት “ይመሩ” የነበሩት የኢትዮጵያ የመረጃ ሠዎች ናቸው ማለት ፌዝ አይደለም። ይህንኑ በመገንዘብ ተቆርቋሪዎች ባዕዳን ፀሃፊዎች የኢትዮጵያ የመረጃ ሠዎች የኢጣሊያንን ሠራዊት በዘዴ አሳስተው ገደል በመክተት ለሃገራቸው ድል አስገኙ ማለት ውርደት ስለሆነባቸው ፤ ዋናውን ጀብዱ በማለባበስ እንዲያው በደፈናው የኢጣሊያ ሠራዊት መንገድ በመሳሳት ተሸነፈ እያሉ ፀፀት የተመላ ፣ የእውነት ግማሽ ፣ የታሪክ ቅናሽ ከመለፍለፍ ተቆጥበው አያውቁም። ወይ እጅግ መቀነስ ወይ እጅግ ማብዛት እነዚህ ሁለቱ የተሪክ ጠላቶች ሲፈራረቁባት እውነት መልኳን ብትለውጥ እንጂ ጠባይዋን አትስትም።

ከአድዋ መልስ የኢትዮጵያ መረጃ ነገር ሲነሳ ኢጣሊያኖች ያንገበገባቸውና ያራዣቸው ጀመር። በተለይም የካቲት 23 ከተመቱት ምት ሳያገግሙ “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ” የመቀሌው አነሰና አሁንም በአዲግራት ሁለት ሺህ የሚሆኑ ሠዎች በእነ ራስ ስብሃት ተከበዋል። እዚያ የነበሩት ኢጣሊያኖች በነአሪሞንዲና በነ አልቤርቶኒ የደረሰውን ጉድ ሰምተው ሳሩም ቅጠሉም ሰላይ ይመስላቸው ጀመር።

ዓድዋ ላይ የኢትዮጵያ የመረጃ ድርጅት በኢጣሊያን የጦር አመራር ፣ በውጊያ ግንባርና በጠላት ምሽግ ውስጥ እየገባ ከፈፀመው ተግባር በቀር ከጦርነቱም በፊት የጠላትን እንቅስቃሴ በመከተል ፣ ኃይሉን በመገምገምና ፀረ ስለላ ጥንቃቄ በማድረግ ያበረከተው አገልግሎት ለመጨረሻው ድል ወሳኝ እንደነበረ ታሪክ ጸሃፊዎች ያረጋግጣሉ። ይህም በእኛ ደራሲያን ሳይሆን በውጪ ሠዎችና ሰነዶች የተረጋገጠ መሆኑ ታሪኩን ከአድሎ ነፃ በማድረግ ያጠናክረዋል።

የተነገረውንና የተፃፈውን ሁሉ መደርደር ትርፍ ቃል እንዳይሆንብን የአድዋ ድል በአውሮጳ እንደተሰማ ሰኔ 15 ቀን 1888 ዓ.ም በወጣው “ረሹ ዲ.ደ.ሞንድ” በተባለው የፈረንሳይ መፅሄት አልቤር ሐንስ የሚባል ደራሲ ከጻፈው ጥናት ውስጥ ፍሬ ነገሩን በአጭሩ ማስታወስ የኢትዮጵያ የመረጃ ድርጅት ደርሶበት የነበረውን የጥራት ደረጃ ለማስገንዘብ የሚበቃ ይመስለናል።

ሐንስ በትክክል እንዳመለከተው ከአድዋ ጦርነት በፊት የጄኔራል ባራቲየሪ ዕምነት “የሃበሻ ብሔረ ሰቦች ስለ ተቀያየሙና በውስጥ ቅራኔ ሆድና ዠርባ ሆነው ስለሚኖሩ ጦርነቱ ሲነሳ ይፍረከረካሉ” የሚል ስለነበር ፤ የኢትዮጵያን ኅዝብ ከግምት በታች በማስቀመጥ በጦርነቱ ጊዜ ተጨባጩን ሁኔታ ማወቅ አስፈላጊ መስሎ  አልታየውም። በዚህ ምክንያት የኢጣሊያን ብርጌዶች ወደ አድዋ እንዲዘምቱ ትዕዛዝ ሲሰጥ በተቀነባበረ ግብረ ኃይል አንድ የተወሰነ ቦታ በቀላሉ ለማስያዝ ከመፈለጉ በስተቀር ወሳኝ ውጊያ ሊገጥመው እንደሚችል አልገመተም። ከባራቲዬሪም ጋር የተሰለፉት ጄኔራሎች ውጊያው እንዲከፈት ሲገፋፉት ስለሚጠበቅባቸው ሁኔታ ከእርሱ የተሻለ የሚያውቁት ምንም ነገር አልነበራቸውም። በዚህ ላይ የጄኔራሉ ዋና መንገድ መሪ በአጉል ጊዜ ጠፍቷል  . . . በአንፃሩ ግን የኢትዮጵያ መረጃ በሚገባ ተደራጅቶ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል። ሚኒልክና የጦር መሪዎቹ በቅድሚያ የኢጣሊያንን ዝግጅትና ዓላማ በሙሉ ደርሰውበታል። ሮማ የሚሰጠው የመንግስት መግለጫና በኢጣሊያኖች ጋዜጦች የሚወጡት አስተያየቶች ሁሉ እየደረሷቸው ሚሲዮኖች ባሰለጠኑዋቸው ምሁራንና ቋንቋ በሚያውቁ ፈረንጆችም ይተረጉማሉ። እንዲሁም በኤርትራና በምፅዋ የሚኖሩ ታማኝ የውጭ ወዳጆችና በመረጃው ውስጥ የሚሰሩ የሃገር ተወላጆች በመርከብ የሚመጡትን የኢጣሊያን ወታደሮች ብዛትና እንቅስቃሴ በጥንቃቄ እየተከታተሉ ለሚኒልክ ወዲያው ያሳውቁ ነበር። በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን የሃገሪቱን አቀማመጥ በሚያስደንቅ ሁኔታ ጠንቅቀው ያውቁ ስለነበር መውጫ መግቢያውን በጥብቅ እያስጠበቁ ሠርገው ለመግባት የሚሞክሩትን ሰላዮች ፣ አጠራጣሪ ተላላፊዎችና ባልታወቀ ምክንያት ወደ ሠፈራቸው የሚመጡትን ሠዎች ሁሉ እየተከታተሉ ያለ ምህረት በመደምሰስ ጥቅጥቅ ያለ መጋረጃ በኢጣሊያኖች ፊት ዘርግተውባቸው ነበር። ኢትዮጵያውያን አልፈው ተርፈው የጠላታቸውን አድራጎትና እንቅስቃሴ በዝርዝር ከመከታተላቸውም በላይ አንዳንድ ምልክቶችንና የሌሉ ሁኔታዎችን አስመስለው እያቀረቡ ኢጣሊያኖችን አሳምነው እስከ መሸንገል ደርሰው ነበር።

 

 


ሸፍጠኛው ጥያቄ ! ኢትዮጵያዊው ማን ነው?- ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

 

ኢትዮጵያዊው ማን ነው? ፤ ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው?

እጅግ ይገርማል ይደንቃል ፤ ኢትዮጵያዊነት ምን እንደሆነ

ኢትዮጵያዊውም ማን እንደሆን ፤ አጠራጥሮ ደመነ?

የኢትዮጵያዊው ኢትዮጵያዊነት ፤ ማንነቱና ምንነቱ

ደብዝዞ እስኪያምታታ ፤ አስቸገረ መለየቱ ?

ለዚህም ተዳርሰናላ ፤ ጭራሽ ጥያቄ እስኪያስነሣ?

መሬት ሲያረጅ ምን ያበቅላል ፤ ይሉት ደርሷላ አበሳ

ኢትዮጵያዊው ማን ነው? ፤ ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው?

ኢትዮጵያዊነት ሲጎዳ ፤ ሲሸረሸር በነፋስ ሲታይ

ሲገፈተር ሲሽቀነጠር ፤ ሲወድቅ አደጋ ላይ

የተፈጠረ ጥያቄ ፤ የሀገር ፍቅርን አግላይ

ሀገር በቀል እሴቶችን ፤ ያለርሕራሄ ገዳይ

የተማረከ የተበነደ ፤ የሚያነሣው ሲሆን አባይ

ኢትዮጵያዊነትን ያስረጀ ፤ ክህደትን ያሠለጠነ

የተሠወረ ይመስል ፤ ድብቅ ምሥጢር የሆነ

የሐበሻነትን መለያ ፤ በአደባባይ ያኮሰመነ

የእንቢተኝነቱን ጽናት ፤ ከውስጥ ሰልቦ ያመነመነ

ብቁ ትጉ ዜጎቿን ፤ ጆሮ አስይዞ ያስመነነ

የቃል ኪዳን ልጅነትን ፤ እያስካደ ያስኮነነ

ታሪክ ቅርስ እሴታችንን ፤ ከል አልብሶ የከደነ

ሐሰት ሐሰቱን ያነገሠ ፤ እውነት እውነቱን ያዳፈነ

የራስን ወርቅ አስጥሎ ፤ መዳብ ጠጠር ያስለመነ

ሕዝብን የናቀ ያሳዘነ ፤የተዳፈረ ሉዓላዊነት

ወገናዊ ያልሆነ ፤ ባዕዳዊ ሸፍጥ ምጸት

በሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ፤ የተደበቀ እብለት

እውነቱ እየታወቀ ፤ በገሐድ በፋኖ ሕይዎት

የሀገራቸውን ጥቅሞች ፤ ለድርድር በማያቀርቡት

ለሉዓላዊነት ሲሉ ፤ ሞትን ገለው በሚሞቱት

ኢትዮጵያዊውን እሴት ፤ በጽናት በሚጠብቁት

በቀደመው በጥንት ዘመን ፤ ከሀገር አልፎ በአህጉራት

ኢትዮጵያዊነት በምልዓት ፤ ናኝቶ በነበረበት

በዚያ ዘመን ቢነሣ ፤ ሆኖ የሚታይ እብደት፡፡

በል እንግዲህ ወገኔ ፤ አውቀህም ይሁን ሳታውቅ

ጠይቀሀልና ጥያቄ ፤ በእጅጉ የሚያስደንቅ

ኢትዮጵያዊነት ማለት ፤ ሲተነተን ሲዘረዘር

ከአደኛኘት እስከ አሞጋገት ፤ ከአስተዛዘን እስከ አመራረር

ከአስተካከም እስከ አገነባብ ፤ ከአሣሣል እስከ አነጣጠር (አንጠረኛ)

ከአጠናን እስከ አፈለሳሰፍ ፤ ከአነባበብ እስከ አመሠጣጠር

ከአወጋግ እስከ አመራረክ ፤ ከአቀራረብ እስከ አመራመር

ከአጻጻፍ እስከ አቆጣጠር ፤ ከአስተሳሰብ እስከ አኗኗር

ከአከዋወን እስከ አቀጣጠር ፤ ከአዘገጃጀት እስከ አከባበር

ከአመጋገብ እስከ አለባበስ ፤ ከአስተዳደግ እስከ አነጋገር

ከአፈነጣጠዝ እስከ አለቃቀስ ፤ ከአዚያዚያም እስከ አደነካከር

ከአመራረቅ እስከ አረጋገም ፤ ከአመላለክ እስከ አሥተዳደር

ለዓለም የተገለጠ ፤ በመልከጼዴቅ በዮቶር

የራሱ መሠረት ያለው ፤ የሥልጣኔ ፈለግ

የራሱ ትውፊት ያለው ፤ እውነት የሆነ የሚታደግ

የራሱ ቀለም ያለው ፤ የብቻው መለያ ብልጹግ

የራሱ እምነት ያለው ፤ የተለየ ባሕልና ወግ

የራሱ ሥርዓት ያለው ፤ አከዋወን አደራረግ

የራሱ ይትበሀል ያለው ፤ የተወደዱ ደጋግ

ምዕራባዊ ያልሆነ ፤ ምሥራቃዊም ወዲያ ጥግ

ዓረባዊ ያልሆነ ፤ አውሮፓዊም አጭሉግ

ከማንም ያልተወረሰ ፤ ያልመጣ ተሻግሮ አፍላግ

ያወረሰ እንጅ የሰጠ ፤ ሁሉን ያረገ ዕዱግ

የራሱ ብቻ የሆነ ፤ ሉዓላዊ ማዕረግ

ይሄ ማለት ነው ወዳጀ ፤ የኢትዮጵያዊነት ድር ማግ

ይሄንንም የሚኖረው ነው ፤ ኢትዮጵያዊው ብትፈልግ፡፡

ወደ ኋላህ ተመልሰህ ፤ ማንነትህን ብትፈትሽ

ቱባውን ታገኘዋለህ ፤ ሳይበራረዝ ሳይበላሽ

ሲጠበቅላት የኖረውን ፤ በንግሥታት ነገሥታቷ

ከራሷው የበቀለውን ፤ የሆነውን የገዛ ሀብቷ

ኢትዮጵያዊ መሆን ካሻህ ፤ ጽዱ ንጥር ሐበሻ

አምጣውና ያንን ኑረው ፤ መደበላለቅ ሳትሻ

ያንን ተቀባ ተላበሰው ፤ አውልቀህ የሌላን ቆሻሻ

ዱካህ ብቻ ነው መድኅንህ ፤ ከጥፋት ማምለጫ መሸሻ

በልክህ የተሠራልህ ፤ አይጠብ አይሰፋህ ድርሻ

ይሄንን ሳታደርግ ግን ፤ ሳትመለስና ሳትረዳ

ኢትዮጵያዊ ነኝ እንዳትል ፤ እሷ አታውቅህም ነህ ባዳ

ምሁር ዐዋቂ ነኝ እንዳትል ፤ ጎሎሀል ዕውቀት የላቀ

ራስን የማወቅ ያህል ፤ አክብረህ መመስከር ላላወቀ

ጤነኛም ነኝ እንዳትል ፤ ይዞሀል የአእምሮ በሽታ

አንተነትህን አስጠፍቶህ ፤ ሌላ እንድትሆን የሚያምታታ

ይሄን በሚያህል ድንቁርና ፤ ወርቅ አንተነትህን ባስናቀ

ተውጠህ ሰምጠሀል ውጣ ፤ ዕውቀት አለልህ የመጠቀ

ይሄን በሚያህል በሽታ ፤ ሉዓላዊ ክብርህን ባስጣለ

ተለክፈህ አብደሀል ንቃ ፤ ጤና አለልህ ያማለለ

ድንቁርናው በርትቶብህ ፤ የለኝም ካልከኝ በር መውጫ

በሽታውም ጸንቶብህ ፤ አጣሁ ካልከኝ ፈውስ መስጫ

ከቶውንም ቃናው የለህ ፤ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ

ምንም እንደሆንክ አላውቅም ፤ ለምን ምንድን ነው ያንተ ምርጫ ?

ነጭ ነው ቢጫ ወይስ ዓረብ ፤ መልክህ ምንድን ነው ዓይነቱ ?

የማንነትህ ምንጭ አሻራ ፤ ወዴት ይመስልሀል መሠረቱ ?

አይደለም እንዳትሳሳት ፤ ያለህን አሳይ ሐቅ አውራ

እራስህን አታጃጅል ፤ ጆሮህን አትስጥ ለፈጠራ

የነጭ ቢጫ ዓረብ አይደለም ፤ ነው እንጅ የጥቁር አውራ

የተገፋው ሕዝብ መመኪያ ፤ መኩሪያ መከታ ባለአደራ

እራስህን ጠይቅ መርምረው ፤ ታሪክን አስመስክር ለእምነቱ

ልማዳዊ አይሁን መንገድህ ፤ ውስጥህ ምን ይልሀል ስሜቱ?

ራስህን ለእውነት አስገዛ ፤ ምክንያታዊ ይሁን ስሌቱ!

ወገናዊ ይሁን አድልኦህ ፤ ኢትዮጵያዊ ይሁን ቅኝቱ!

እራስህን ቅጥረኛ አርገህ ፤ የጠላት ሎሌ አትሁን ከንቱ!

ጠፍተህ ለማጥፋት አትትጋ ፤ ይሰማህ የክህደት ውርደቱ!

የማንም ምስክር አያሻህ ፤ ሕሊናህ ውስጥ አለ እውነቱ!

ከራስህ ተለይተህ ላትለይ ፤ ሆነህ ላትሆን ሌላ

ምንም አማራጭ የለህም ፤ ድመቅ በራስህ ገላ!

ተመለስ ከክህደትህ ፤ ሆነህ እንዳትቀር ሰንካላ!

አቅመቢስ ድኩም ሰባራ ፤ ለምንም የማይሆን ሰላላ!

ንቃ ከመተተኞች ፍዘትህ ፤ አዚሙን ሽረህ በኤላ

ተመለስ ወደአንተነህ ፤ እሱ ነው የሚያዋጣህ ከለላ፡፡

ሥራ በእናት አባትህ ትጋት ፤ በሰጠን ኃያሉን ዱላ!

ቀድሞ አንግሦህ በነበረው ፤ እስከ እስያ ሁላ!

ትጋ ተሯሯጥ ጽና ፤ ቅበር ስንፍናን ጥላ!

አሳድ ድህነትህን አባር ፤ አርቅ ከሀገርህም ክላ!

ባርክ በአንተው ጸሎት ፤ መርቅ ሕይዎት ለአንተ ታዳላ!

ፈትን በራስህ ጉልበት ፤ ዘይድ በራስህ መላ!

ኩራ በአንተው ማንነት ፤ ዝመት ወኔህን ሙላ!

ፎክር በአንተው ጋሻ ጦር ፤ ደንፋ በአንተው ሽለላ!

አቅራራ በአንተው ቀረርቶ ፤ ብረቅ እንደ እሳት ጎመራም ፍላ!

አውጅ ነጋሪት ጎስም ፤ ጨክን በሠይፍህ ቅላ!

ምጠቅ በራስህ ዕውቀት ፤ ጽና በራስህ መሐላ!

አውጋ በራስህ ቋንቋ ፤ ተቀኝ ቅኔህ ይራቀቅ ይስላ!

ፍረድ በራስህ ፍትሕ ፤ በዳይ እንዳይኖር ሚያጉላላ!

አንብብ በራስህ ፊደል ፤ ቀምር በቁጥርህ አስላ!

ብራና መጻሕፍትህን ፤ ሲሳይ ያወረዱትን ለሌላ!

እያንዳንዳቸውንም በዝብዝ ፤ ጥርግርግ አርግና ብላ!

አዚም በራስህ ዜማ ፤ አስንቅ ሌላን አስጠላ!

አዝምር በራስህ ሁዳድ ፤ መጽውት መዓድህን ሙላ!

አክብር የራስህን በዓላት ፤ መንፈስህ ይታደስ በተድላ!

ሙሉ ነውና ማንነትህ ፤ በራስህ እሴቶች ጉላ!

ከማንም ምንም አያሻህ ፤ ዕወቅ አትሁን ተላላ!

እንኳን ለራስህ ቀርቶ ፤ ብዙ ተርፈሀል ለሌላ፡፡

ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊነት ፤ በእነዚህ እሴቶች ካልተለካ

በምን ይመዘን ይመስልሀል ፤ ሀገርስ በምኗ የምትመካ ?

ከአማራ ኦሮሞ ትግሬ ፤ ከጉራጌ ወላይታ ሱማሌ

ከሁሉም ብሔረሰቦች ፤ እነዚህን እሴቶች ካለ አሌ

ኢትዮጵያዊነት ውስጡ የለም ፤ ሸጦ በልቶታል በአሞሌ!

ይማር ይመከር ይገራ ፤ እራሱን እስኪያውቅ ተላሌ፡፡

ብቻ የራሳችን ይሁን እንጅ ፤ የተገነባ በሐበሻ ዘየ

የአማራ እሴት ነው የተባለው ፤ የሱማሌውም ሆኖ ካልታየ

የወላይታው ሀብት የተባለው ፤ የትግሬውም መሆኑ ከታበለ

እሱ ደሞ እዚህ ምን አገባው ፤ የኔ ጉዳይ ነው ከተባለ

ይሄ ሰው ምኑም አልገባው ፤ ገና ገና ብዙ ችግር አለ፡፡

በል እስኪ ንገረኝ እኮ በል ፤ ኧረ እንዴት ሆኖ ነው ወገኔ

ሁላችንም እንዲህ እያልን ፤ ያሰብን ጊዜ ያኔ

አንድነት ያለው ጠንካራ ሕዝብ ፤ ያልተቃረጠ ሥልጣኔ

ሰላማዊት ምቹ ሀገር ፤ ሉዓላዊ ማንነት ውርስ

ዘመን ተሸጋሪ ታሪክ ፤ ሳይበረዝ ሳይከለስ

እንደምን ሆኖ ይኖርሀል ፤ መቸና ከወዴት ሊመጣ?

ምንስ ያሰመጠህ መሰለህ ፤ እዚህ ካለህበት ሁሉ ጣጣ?

መውደቅ የጀመርክበትን ዘመን ፤ መለስ ብለህ ብታየው

ሌላም ምክንያት አልነበር ፤ እንደዚህ ባሰብክ ጊዜ ነው፡፡

የኔ ነው ሌላው ምን አገባው? ፤ የምትለው ቅርስ የተጫነ

ተው ሲታወቅብህ ታፍራለህ ፤ ያ ቅርስ የአንተ እንዳልሆነ!

ነገሮች ተገለባብጠው ፤ የታሪክ አጋጣሚ ሆነና

የአንተ እንደሆነ እንድታወራ ፤ አረገህ ጊዜ ሳተና

ባለቤቱ ዝም ያለውን ፤ የሁሉም ነው ብሎ አስቦ

አንተም እያወክ እውነቱን ፤ ልትነጥቅ ከዳዳህ ከደቦ

እውነቱ ይነገርሀል ፤ ዋ ትዋረዳለህ በኋላ!

ዐርፈህ ተቀመጥ በአደብ ፤ በእናት ኢትዮጵያ እንዳትጠላ፡፡

ወገኔ እኔስ ልመርቅህ ፤ ነው ብለህ እንዳትንቀው የኩታራ

ልብ ይስጥህና ያድርግህ ፤ በማንነትህ የምትኮራ!

በፍቅር በመከባበር ፤ ተሳስበህ ጠባቂ አደራ!

የማይፈታ አንድነት ያለህ ፤ በእኩያን ጠላቶች ሴራ!

የማንነት እሴቶችህን ፤ በሉላዊነት ሽርሸራ

ለድርድር ያማታቀርብ ፤ ቆራጥ ሀሞተ ኮስታራ!

በራስህ ዱካ እሮጠህ ፤ ሌሎቹን ባረገው ሲራራ

ለስኬቶችህ የምትበቃ ፤ በመላው ዓለም የምትበራ!

የምትደምቅ የምትፈካ ፤ የምትነግሥ የምትፈራ!

አሜን! በለኛ ወገኔ ፤ ልሳንህ አሜንን ይጣራ!

ከአሜን ይቀራልና ፤ አሜን አሜን አሜን ምራ!

አሜን አሜን አሜን ምራ ፤ አሜን አሜን አሜን ምራ!

ጥቅምት 2004 ዓ.ም.
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

ዘመቻ አድዋ! (ፈትለ እና ወርቀ)  – አስራት አብርሃም

$
0
0
አስራት አብርሃም

አስራት አብርሃም

ፈትለ እና ወርቀ የተንቤን ገበሬዎች ናቸው። ሁለቱም አድዋ ዘምተዋል፣ ፈትለ እዚያ ሲሰዋ፣ ወርቀ በህይወት ተመልሰዋል። እንዴት ሊዘምንቱ እንደቻሉ እንዲህ በምናባዊ ወግ አምጥቼዋለሁ።

ወርቀ፦ “ደጃዝማች ‘ለዘመቻ ተዘጋጁ’ ብለዋል።”

ፈትለ፦ “ወየት ሊዘምቱ ነው?”

ወርቀ፦ “አድዋ! ጥሊያን የሚባል ጠላት ባህር ተሻግሮ መጥተዋል አሉ።”

ፈትለ፦  “እንዴት ያለ ነው ይሄ ጥሊያን  ደሞ? እንደ ድርቡሽ ነው?”

ወርቀ፦ “አይደለም እንደ ቱርክ ያለ ሳይሆን አይቀርም፣ ‘ኃይማኖቱ ግን ኮቶሊክ ነው’ ተብለዋል።”

ፈትለ፦ “ኮቶሊክ?! እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ! ታዲያ እኛ ብቻችን እንችለዋለን?” አለ በእጁ እያማተበ።

ወርቀ ፦ “ኧረ ንጉሰ ነገስቱ ራሳቸው ጦራቸውን ይዘው መጥተዋል ነው የሚባለው፣ ጦጲያ ሙሉ ነው

የተሰፈው አሉ። ራስ አሉላም፣ ራስ መንገሻም አብራችው ናቸው።”

ፈትለ፦ “አፄ ዮሃንስ?!”

ወርቀ፦ “ምን ሆነሃል አንተዬ፣ አፄ ዮሃንስማ መተማ ሲዋጉ ድርቡሽ ገደላቸውማ አይደለ! አፄ ምኒልክ ናቸው እንጂ!”

ፈትለ፦ “እንዲያ ነው?! ደግ። እንዘምታለን እንግዲያውስ ። ወለተኪዳንን ስንቅ እንድታዘገጃጅ አሁኑኑ ነግራታለሁ፣ የአጥቢያ ኮከቡ ብቅ ሲል፣ መጥተህ ጥራኝ፣ ፀሐዩ ሳይበረታ መገስገስ አለብን፤ አለ” የሕዳር ፅዮን አክሱም ሊሳለም ሄዶ ያያቸውን የአድዋ ተራሮች በምናቡ እያሰበ።

 

 

ጋን ቢሆን ምንቸቱ -የማን ነው ጥፋቱ ? – ይገረም አለሙ

$
0
0

አምባሳደር ተስፋዬ አብዲ ከኢሳት ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በኔት ወርክ ችግር  ምክንያት ዘግይቼ ነው ያዳመጥኩት፡፡ አምባሳደር ተብለው ይጠሩ አንጂ ያልዋሉበት ቦታ ያልሰሩት  የሥራ መስክ የለም፡፡ ከጀት አብራሪነት እስከ ደህንነት ሰርተዋል፣ከመከላከያ እስከ ውጪ ጉዳይ ብዙ ቦታዎችን አዳርሰዋል፡፡ በአብዮቱ አፍላ ወቅት ሶሻሊዝምን እናራምዳለን ያሉ፣ በርዕዮተ ዓለም ያልተለያዩ ርሳቸው “ሥልጣነኝነት” የሚል መጠሪያ ባወጡለትና ሌሎቻችን የሥልጣን ጥም በምንለው ሲገዳደሉ በቅርብ ነበሩ፡፡ ጠንቁ እስከ ዛሬም ያለቀቀን ነጭና ቀይ ሽብር በማንና እንዴት አንደተወጠነና እንደተፈጸመ ያውቃሉ፡፡ ከንጉሱ ቤተሰቦችና ባለሥልጣኖች የጅምላ ፍጅት  በመፈንቅለ መንግሥት እስከተረሸኑት ጀነራሎች ብሎም ኮ/ል መንግሥቱ በቀጭን ትዕዛዝ ማዕረግ ከመግፈፍ እስከ ርሸና ርምጃ ያስወሰዱባቸውን የጦር መከንኖች ከነምክንያቱ ያውቃሉ፡፡ ሌላም ሌላም፡፡ ማጋነና ካልሆነብኝ ከአዳመጥኩት ሶስት ክፍል ቃለ ምልልስ (ከዩቲዩብ)  እንደረዳሁት ከሚያውቁት የማያውቁት የሚያንስም የሚቀልም ይመስለኛል፡፡

ትንሽ ሰርተው ብዙ እንዲወራላቸው የሚሹና በትንሽ እውቀት መድረክ የሚጠባቸው በሞሉበት አምባሳደር ተስፋየ የሰሩትንም የሚያውቁትንም በጓዳቸው ከመያዝ አልፈው እስከ አሁን ድረስ ሲሰሩም እዩዩኝ እያሉ ሳይሆን  ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ውጤት እየናፈቁ መሆኑ በእውነቱ አድናቆትና  አክብሮት እንዲቸራቸው የሚያደርግ ነው፡፡ ርሳቸውም አንደተናገሩት ከሁኔታውም መገመት እንደሚቻለው በተለያየ ምክንያት ራሳቸውን ከአደባባይ ያቀቡ ለሀገራቸው ብዙ የሰሩና ብዙ የሚያውቁ እንደ አምባሳደር ተስፋየ አይነት ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ግን ምን ያደርጋል አልተገናኝቶም ሆነ፡፡

መድሀኒት ላጣው የሀገራችን የፖለቲካ በሽታ በቂ ህክምና ለመስጠትና ፈዋሽ መድሀኒት ለማዘዝም ሆነ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ ላስቸገረው ተላላፊ በሽታ ክትባት ለማዘጋጀት የሀገራችንን ችግር መንስኤ ምንነት፣ የበሽታውን ምልክት፣ የሚያስከትለውን ውጤት ወዘተ በደንብ የሚያውቁ ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሁሉን አይተው፤ የሚችሉትን ያህልም ጥረው ግረው አልሆን ሲላቸው ከበሽተኞች ጋር አልቀጥልም ብለው ከተለዩት አምባሳደር ተስፋየና መሰሎቻቸው የሚቀድም አልነበረም፡፡ ግና ምን ዋጋ አለው “ጋኖች አለቁና ምንቸት ጋን ሆኑ” የሚለውን አባባል ሥልጣኔ ለውጦት ጋኖቹ ባሉበት ምንቸቶች ጋን እየሆኑ ሀገር ከበሽታዋ ትፈወስ ዘንድ ህክምናውን መስጠት ትክክለኛውነ መድሀኒትም ማግኘት ክትባቱንም ማዘጋጀት የሚችሉት የሚገባቸውም ሰዎች ውሎአቸው ከመጋረጃ ጀርባ ሆነና በሽታችን ፈወስ አጥቶ ቀጥሏል፡፡

የአምባሰደርን ቃለ ምልልስ እያዳመጥኩ ከዚህ በላይ ያነሳሁትን  በአእምሮየ እወጣሁ እያወርድኩ ሀገርን ከበሽታዋ እንፈውሳለን፣ ከችግር እናላቅቃለን፣ ለዴሞክራሲ እናበቃለን ወዘተ ብለው በፖለቲካው መድረክ ላይ የሚታዩትንና አምባሳደር ተስፋየን ጨምሮ በተለያየ ግዜ ወደ መገናኛ ብዙኃን ብቅ ብለው ያወቅናቸውንና ከመጋረጃ ጀርባ አሉ ብየ የገመትኳቸውን በህሊና ሚዛን መመዘን ውስጥ ገባሁ፡፡፡ እስቲ ምዘናውን አግዙኝ፡፡ በሚዛኑ አንደኛው ወገን  ላይ የሚቀመጡትን ስም መዘርዘር ሳያስፈልግ እነ አምባሳር ተስፋየ አብዲ እንበልና በዛኛው ረድፍ ሰሩም አልሰሩ በገሀድ ያሉ ስለሆነ ስማቸውን መጥቀሱ የህግም የሞራልም ጥያቄ አያስከትልምና ከሰማያዊዎቹ ይልቃልና የሺዋስ እስከ መድረኩ በየነ ጰየጥሮስ፣ ከኢዴፓው ጫኔ ከበደ እስከ መኢአዱ በዛብህ ደምሴ፤ ከቅንጅቱ አየለ እስከ ጫሚሶ እስከ ኢፍዴኃግ  ግርማይ ሀደራ፣( ይህን ግንባሩም መሪም ብዙ የሚታወቅ አይመስለኝም፡፡ የማወቅ ጉዳይ ከተነሳ አንድ ጥያቄ አስቀምጬ ልለፍ፡፡ የፕ/ር በየነን ፓርቲ ሙሉ ስም ምን ያህል ሰው ያውቀው ይሆን ? መድረክን አይደለም፣፡ አለማወቅ ሀጢአትም ወንጀልም አይደለምና በሚያመቻችሁ መንገድ ተናገሩ፡፡ከሚያውቀው የማያውቀው ከበዛ በዚሁ መስመር ብቅ ስል ሹክ እላችኋላሁ እስከዛው ግን የቤት ሥራ ይሁን፡፡) ከኢሰዴፓው ይመር እስከ ኢአዴዱ አድማሱ ሀይሉ፣ ከመኢብኑ መስፍን ሽፈራው እስከ ራዕዩ ተሻለ ሰብሮ ወዘተ በሌላኛው የሚዛኑ ጫፍ ደርድሩና መዝኑዋቸው፡፡ ያለ ጥርጥር የሚገኘው ውጤተ ወይ ነዶ ነው ፡፡  (ማእረጋቸውና አንቱታው የቀረው ለአጠራር አንዲያመች እንጂ ሌላ ምክንያት የሌለው መሆኑን  በአክብሮት እገልጻለሁ፤ እንዲሁም የሀገር ቤቶቹን ብቻ የጠራሁት ስለ ውጪዎቹ ብዙም እውቀት ስለሌለኝና አውሮፓና አሜሪካ ተቀምጠው ስለሀገር ቤቶቹ ፓርቲዎች ከአባላቱ አይደለም ከመሪዎቹ በላይ እናውቃለን እንደሚሉት ድፍረቱ ስለሌለኝ ነው)

በዛኛው የሚዛኑ ጫፍ የደረደርናቸው ሀገሪቱን ከበሽታዋ እንፈውሳለን የሚሉን  “ፖለቲከኞች” ለሀያ አምስት አመት እንዳየናቸው አይደለም ሀገር ሊያድኑ ለስማቸው መጠሪያ የሆኑዋቸውን ድርጅቶቻቸውን በሽታ እንኳን ማወቅተስኖአቸው  የአልጋ ቁራኛ ያደረጉ ናቸውና ሚዛን  የሚደፉ ሆነው አልታዩኝም፡፡

ምንቸቶች ጋን ሆነው ጋኖቹ ቦታ አጥተው፤
መድሀኒቱ ጠፍቶ ስቃይ ሆነ ኑሮው፣
እስቲ አንነጋገር ከቶ በዚህ ጉዳይ  ተጠያቂው ማነው?

ምንቸቶቹ ያልሆኑትን አይደለም ሊሆኑ የማይችሉትን ጋን ነን ብለው አለቦታቸው በመገኘታቸው በድፍረታቸው በዚህም ባደረሱትና እያደረሱ ባሉት ጥፋት ተጠያቂ ናቸው ብንል እንዴ ቦታውን ባዶ ሲያገኙት፣ አረ እናንተ ምንቸት አንጂ ጋን አይደላችሁም፣ ካለ ቦታችሁ ምን ታደርጋላችሁ የሚላቸው ሲጠፋ እነርሱ ምን ማድረግ ነበረባቸው ክፍት የተገኘ ቤት ቀድሞ የደረሰ ነው የሚገባበት የሚል መከራከሪያ ሊቀርብ ይችላል፡፡

ጋኖቹ ቦታቸውን ማስጠበቅ ጋንነታቸውንም በተግባር ማሳየት ነበረባቸውና በጋኖች ቦታ ምንቸቶች እንዲፈነጩ በማድረጋቸው  እነርሱም ተጠያቂነት አለባቸው ብሎ ለመድፈር ደግሞ  ባልተገራ ምላስና በላሰላ ብእር የሚካሄደው የአየር በአየር የቃላት ተኩስ ጋኖቹን መች በቦታቸው የሚያቆይ ነውና የሚል ተቃራኒ ሀሳብ አእምሮ ያፈልቃል፡፡

ጋንና ምንቸትን መለየት የማይቸግረው ተገልጋዩ አንድም ምንቸቶች በጋን ቦታ አለን ሲሉ ወግዱ ይሄ ቦታችሁ አይደለም ማለት ሁለትም አቅማቸውን አውቀው በምንቸትነታቸው አገልግሎት አንዲሰጡ አንጂ ጋን ነን እያሉ አንዳይንጠራሩ ማድረግ ነበረበት ይህን ለማድረግ ደግሞ የማንም ወገን ፈቃድና ክልከላ የማያግደው የራሱ ግላዊ መብት ነው በማለት የተጠያቂነቱ ሚዛን ወደ ህዝቡ እንዳይገፋ ተቧድነው ብቅ በማለት ወኪልህ ነን ይላሉ አንጂ መች ወክለን ይሉታል፣የምንልህን ተቀበል ይሉታል እንጂ ምች ያዳምጡታል፣ወዘተ የሚለው ሀሳብ በተቃራኒ ይከሰታል፡፡ እንዲህ እንዲህ ቢባልም ይነስም ይብዛ ይክበድም ይቅለል እንጂ ሁላችንም የድርሻ ተጠያቂነት አለብን፡፡በሽታችንን ለማወቅ ያላስቻለን ትልቁ ችግርም ይሄ ነው፤ ጣትን ወደ ሌላው ለመቀሰር ያለንን ድፍረት እሩቡን ህል አንኳን ወደ ራስ ለማዞር አለመድፈር፡፡

ከድፍረት አይቆጠረብኝና በቦታቸው ያልተገኙትን ጋኖች ለመውቀስም ለመክሰስም ሳይሆን (ደሞስ ማን ሁኜ) ዝምታ ለምን በሚል ሶስት ጥያቄዎችን ላንሳ፡፡

  1. አንዳንዶቹ አንደ አምባሳደር ተስፋዬ ከነበረው መንግሥት በግዜ ቢፋቱም አንዳንዶቹም እስከ መጨረሻው አብረው ቢዘልቁም( እንደውም አንዳንዶቹ ከንጉሡ ዘመን ነው የሚጀምሩት) ዛሬ ሀገሪቱን የሚያብጠውና ትውልዱን ርስ በርስ የሚያባላው በሽታ ከእነርሱ የተላላፈ ነውና በሽታውን የማወቅም ሆነ መድሀኒቱን የመፈለግ ኃላፊነት አለባቸውና ዝምታ ለምን ማለት ከጀለኝ፡፡
  2. ሀገራቸው እንዳደረጉላት ባታደርግላቸውም ዜጎች ናቸው፡፡ በአምባገነን አገዛዝ የሚሰቃየው ህዝብ ወገናቸው ነው፡፡ የበሽታውን እንዴትነት የመድሀኒቱንም ምንነት የሚያውቁት እነርሱ ወደ ጎን ሆነው ፤ በአላዋቂ ሀኪም ሀገርና ህዝብ በበሽታ ሲሰቃይ ማየት አንዴት አስችሏቸው ነው ዝም የሚሉት ለማለትም ስሜቴ ገፋፋኝ፡፡
  3. የብዙዎቹ ልጆች ከሀገር ውጪ እንደሆኑ ቢገመትም ኢትዮጵያዊነታቸውን አውልቀው የሚጥሉት አይደለምና ሀገር ከበሽታዋ ተፈውሳ ጤናማ ብትሆን ሀገሬ ብለው ሊወጡ ሊገቡ እንዳም ሲል ጓዛቸውን ጠቅለው ሊመጡ ይችላሉ፡፡እናም ሀገራቸው ለእነርሱ ልትሆን ላለመቻሏ የእነርሱም ድርሻ አንዳለበት ሁሉ በተቃራኒው ለልጆቻቸው እንድትሆን በማድረጉ እጃቸው ሊኖርበት ይገባል ብዬም አሰብኩና ዝምታ ለምን ለማለት ደፈርኩ፡፡፡ “አባት ያበጀው ለልጁ በጀው ” አይደል የሚባለው ፡፡

ይህ ስሜት ኢሳት ከአምባሳደር ተስፋዬ ጋር ያደረገውን ውይይት በመስማቴ የተፈጠረ ሳይሆን የቆየ ነው፡፡ኢሳትና ቪዥን ኢትዮጵ በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን ሳይ ይሄው ስሜቴ ተቀስቅሶ  ግንቦት 2008 “መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ያላት የሰው ድሀ ሀገር ኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ  ብሽቀት ቁጭቴን ጽፌ ነበር፡፡ ያንን ጽሁፌን ያሳረኩበትን አንቀጽ ዛሬም ልድገመው፡፡

መቼ ይሆን! ኢትዮጵያ ልጆቿ  ቁጥራችን ብቻ ሳይሆን ቁም ነገራችንም በዝቶ ሰው እያላት የሌላት የሰው ድሀ ከመሆን የምትወጣው? መቼ ይሆን! በዘር፣ በሀይማኖት፣ በአመለካከት ልዩነት ተለያይተው የመቶ ሚሊዮኖች እናት ግን የሰው ድሀ ያደረጉዋት ልጇቿ ከምንም ነገር በፊት እናታችን ብለው እውቀታቸውን አቀናጅተው ሀይላቸውን አስተባብረው  ነጻነት የሚያቀዳጇት? መቼ ይሆን! ልጆቿ ከራስ በላይ ነፋስ አስተሳሰብ ተላቀው፣ ከመጠላለፍ አዙሪት ወጥተው፣ ከቁልቁለት ጉዞ የሚያቃኑዋትና  የነበረ ዝናና ክብሯን መልሰው የሚያቀዳጁዋት? አረ መቼ ይሆን! ልጆቿ  ዴሞክራሲ እየተረገዘ የሚጨነገፍበትን ሲወለድም   በአጭር የሚቀርበትን በሽታ ተርደተው መድሀኒትም አግኝተውለት ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ የሚበቁት ? አረ መቼ ይሆን! ልጆቿ የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ሀገር የሰው ድሀ የሆነችው እነርሱ ተለያይተው በመቆማቸው፤ በስልጣን ጥም በመታወራቸው፤ ከእኔ በላይ በሚል አስተሳሰብ በመታጠራቸው፣ለራስ እንጂ ለመጪው ትውልድ የማይጨነቁ በመሆናቸው ወዘተ መሆኑን ተረድተው ከየራሳቸው ታርቀው፣ ርስ በርሳቸው ፍቅር መስርተው፣ እንደ ብዛታቸው ቁም ነገራቸውም ለሀገርና ለወገን ሲበጅ የሚታየው ? መቼ አረ መቼ !

 

ብአዴን ባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካን መጠቅለሉንና ዳሸን ቢራ በኪሳራ እየማቀቀ መሆኑን አስታወቀ

$
0
0

የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብአዴን የልማት ድርጅት የሆነው ጥረት ከርፖሬት ሰሞኑን በዋና ስራ አስፈፀሚው አቶ ታደሰ ካሳ በሰጠው መግለጫ ፣ ኮርፖሬቱ በአሁኑ ስዓት በርካታ ፋብሪካዎችን በመያዝ በክልሉ ቀዳሚ መሆኑን እንዲሁም ከኢጣሊያ በኢትዮጵያውያን ለደረሰው ግፍ የደም ካሳ ክፍያ ተብሎ የተገነባውን የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን መጠቅለላቸውን ተናግረዋል። በዳሸን ቢራ ግን ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶብናል ብለዋል።

ጥረት በዳሸን ከደረሰበት ከፍተኛ ኪሳራ ውጭ በተለያዩ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ኪራይ እና አገልገሎት ከመንግስት ጋር በቀጥታ ያለ ጫረታ ባገኛቸው ድጋፎች 1 ቢልየን 442 ሚልየን 876 ሽህ ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።
ዳሽን ቢራን መጠጣት ደም እንደመጠጣት አድርጎ የሚያየውን ድርጅት ከመዘጋት ለማትረፍ በሚሊዮን የሚቀጠር ገንዘብ እየከፈለ የተለያዩ አርቲስቶችን በመጋበዝ ለማስተወዋቅ ቢሞክርም፣ ጥረቱ አድካሚ እና አሰልች እየሆነ መምጣቱን አቶ ታደሰ ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት ጥረት ላገኘው ትርፍ አስተዋጽኦ ያደረጉት አምባሰል የንግድ ስራዎች ድርጅት ፣ ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት ድርጅት እና ኮልቻ ትራንስፖርት አክሲዩን ማህበር ናቸው። በ2016 ኮርፖሬቱ ያለመውን ገቢ ያላገኝበት ፣ ያልተሳኩ ሽያጮች የተበራከቱበት፣ ህዝባዊ አመፁ ብትሩን ያሳረፈበት እንዲሁም የውጭ ምዛሬ እጥረት እና የግበዓት እጥረት በማጋጠሙ ነው ሲሉ ስራ ባለስልጣኑ ተናግረዋል።
አቶ ታደሰ ካሳ ከኢጣልያ መንግስት ለኢትዮጵያውን በደም ካሳነት የተበረከተውን የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን በሰባት መቶ ሚልየን ብር መግዛታቸውን ቢገልጹም፣ ሰራተኞችና ነዋሪዎች ግን ባዶ ቦታዎች ብቻ ሰባት መቶ ሚሊዮን ብር እንደሚያወጡና ብአዴን ጉልበቱን በመጠቀም የደም ካሳ የሆነውን የህዝብ ሃብት እንደዘረፈ ይናገራሉ።
በገበያ እጦት የተመታው ሌላው የድርጅቱ ኩባንያ የጣና ኮምንኬሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን ይህንን ለማካካስ በቀጣይ አመታት አርሶ አደሩ ከአንድ ሽህ ብር ጀምሮ አክሲዎን እንዲገዛ በማድረግ፣ የወረቀት ፣ የልብስ ስፊት እና የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ ነው፡፡

የአውሮፓ የስፖርት ሚዲያዎች የዘገቧቸው አበይት የዝውውርና ሌሎች ስፖርታዊ ወሬዎች

$
0
0

በ  ወንድወሰን ጥበቡ

በዕለተ ሃሙስ የአውሮፓ የስፖርት ሚዲያዎች የዘገቧቸው አበይት የዝውውርና ሌሎች ስፖርታዊ ወሬዎች ስለ ሃሪ ኬን፣ ሉኬ ሻው፣ ዲያባላ፣ አንቶኒዮ ኮንቴ፣  ጆን ቴሪ፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ አሌክሲ ሳንቼዝ ጉዳዮች እና ሌሎች ትኩስ የዝውውር ወሬዎች ተካተውበታል።

ሀሙስ የካቲት 23፣ 2009 ዓ.ም 

ኪን የማንችስተር ዩናይትድ የ80 ሚ.ፓ አማራጭ ሆኗል

ማንችስተር ዩናይትዶች አንቶኒ ግሪዝማንን ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በ80 ሚ.ፓ የዋጋ ስምምነት ለማስፈረም ፊታቸውን ወደቶተንሃሙ አትጥቂ ሃሪ ኬን ያዞራሉ።

ምንጭ: ደይሊ ስታር

ማን ዩናይትድ ለዲባላ የዝውውር ጥያቄ አቅርቧል

የጁቬንቱሱ የፊት ተጫዋች ፓውሎ ዲባላ ከማንችስተር ዩናይትድ በርካታ የዝውውር ጥያቄዎች ቀርበውለታል።

ምንጭ: ካልቾመርካቶ ድረገፅ

ኮንቴ ከቼልሲ ጋር እየተነጋገሩ ነው

የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከስታንፎትምርድ ብሪጁ ክለብ ጋር አዲስ ስምምነት ማድረግ ሰለሚችሉበት ሁኔታ እየተነጋገሩ ይገኛሉ።

ምንጭ: ደይሊ ኤክስፕሬስ

ስፐርሰች ሉኬ ሻውን ምርጫቸው አድርገውታል

ቶተንሃም ሆትስፐሮች ሉኬ ሻው በመጪው ክረምት ከማንችስተር ዩናይትድ እንዲወጣ የሚያድረገው የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርቡለት ይችላሉ።

ምንጭ: ደይሊ ሚረር

ኤልኤ ጋላክሲ ቴሪን ፈልጓል

የአሜሪካን ሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ በመጪው ክረምት ጆንቴሪን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል።

ምንጭ:  ዘ ሰን

የዩናይትዱ አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በኦልትራፎርድ የመቆየት ፍላጎት አለው። የ35 ዓመቱ ስዊድናዊ የእግርኳስ ህይወቱን መቀጠል የሚያስችሉት የዝውውር ጥያቄዎች ከወደቻይና፣ ዩናይትድ ስቴስትና አውሮፓ ቀርቦለታል።  (ደይሊ ሚረር)

 

Daily Mirror

የደይሊ ሚረር ጋዜጣ የዕለተ ሃሙስ ዕትም በጀርባ ገፁ ዝላታን ኢብራሂሞቪችን ይዞ ወጥቷል

ኢንተር ሚላን የ47 ዓመቱን የቼልሲ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከስታንፎርድ ብሪጅ እንዲለቁ የሚያደረጋቸው በዓመት 10 ሚ.ፓ ክፍያ አቅርቦላቸዋል። (ደይሊ ሚረር)

ምንም እንኳ የ26 ዓመቱ ቪክቶር ሞሰስ ከሰማያዊዎቹ ጋር አዲስ ስምምነት ለመፈራረም ቢስማማም አንቶኒዮ ኮንቴ ግን በመጪው ክረምት የክንፍ ተከላካይ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው።  (ደይሊ ቴሌግራፍ)

አርሰናል አማካኞቹን የ25 ዓመቱን ጃክ ዊልሼርና የ23 ዓመቱን አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይንን እንዲሁም የ27 ዓመቱን ተከላከዩን ኪራን ጊብስን የማጣት አደጋ ተደቅኖበታል። መድፈኞቹ የኮንትራት ስምምነታቸው በ2018 ክረምት ለሚጠናቀቀው ለእነዚህ ሶስት ተጫዋቾቹ እስካሁን መደበኛ የሆነ የኮንትራት ጥያቄ አላቀረበላቸውም። (ለንደን ኢቭኒንግ ስታንዳርድ)

ጁቬንቱስ የ28 ዓመቱን የአርሰናል አጥቂ፣ አሌክሲ ሳንቼዝን ለማሰፍረም ሲል የ25 ዓመቱን አጥቂውን፣ ሲሞኒ ዛዛን እና የ20 ዓመቱን ኪንግስሌይ ኮማንን ለመሸጥ ተዘጋጅቷል። (ቶክ ስፖርት ቱቶ ስፖርትን ጠቅሶ)

መድፈኞቹ “የወደፊቱ አሌክሲ ሳንቼዝ” ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን የ17 ዓመቱን ቺሊያዊ ተጫዋች ለማስፈረም የሙከራ ጊዜ ሰጥተውታል። ማርሴሎ አለንዴ የተሰኘው ይህ ተጫዋች የሁለተኛው ዲቪዮን ክለብ፣ ሳንታ ክሩዝ ተጫዋች ነው። (ሰን)

የሌስተር ሲቲ ደጋፊዎች ሮይ ሆጂሰን ቀጣዩ የክለባቸው አሰልጣኝ እንዲሆኑ አልፈለጉም። የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ክለብ ከ69 ዓመቱ የቀድሞ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋር መደበኛ ያልሆነ ንግግር እያደረገ ይገኛል። (ሌስተር ሜርኩሪ)

Daily Star

የዕለተ ሃሙስ የደይሊ ስታር ጋዜጣት ዕትም ማንችስተር ዩናይትድ ሃሪ ኬንን ሊያስፈርም እንደሚችል የሚገልፅ ዘገባ ይዞ ወጥቷል

ሊቨርፑል ለሳንቶሱ የ17 ዓመት ተጫዋች፣ ሮድሪጎ የዝውውር ጥያቄ ቢያቀርብም ታዳጊው ግን ወደአውሮፓ የመሄዱ ጉዳይ እያሳሰበው ይገኛል። (ግሎቦስፖርትን ጠቅሶ ደይሊ ኤክስፕሬስ)

የቀዮቹ አለቃ የርገን ክሎፕ የ25 ዓመቱ የፊት ተጫዋች ሎሬንዞ ኢንሲኚ ከናፖሊ ጋር ያለው ኮንትራት በእንጥልጥል መቆየቱን ተከትሎ የወደፊቱ የዝውውር ዕቅዳቸው ሊያደርጉት ይችላሉ። (ካልቾመርካቶ)

ዌስትሃሞች ለ26 ዓመቱ ሁለገብ አማካኝ ተጫዋች ሚካኤል አንቶኒዮ ሳምንታዊ ደመወዙ 70,000 ፓውንድ ሊደረስ የሚችል አዲስ ኮንትራት ሊያቀርቡለት ነው።  (ደይሊ ስታር)

የ31 ዓመቱ የማንችስተር ዩናይትድ የቀኝ መስመር ተከላካይ፣ አንቶኒዮ ቫሌንሺያ የሆዜ ሞሪንሆው ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን የሶስትዮሽ ዋንጫ ባለቤት ስለመሆን ማሰብ መጀመሩን ተናግሯል። (ደይሊ ቴሌግራፍ)

የ37 ዓመቱ የሊድስ ዩናይትድ አሰልጣኝ ጋሪ ሞንኮ የተሰናባቹ አሰልጣኛቸው ማርክ ዋርበርተን ምትክ ይሆኗቸው ዘንድ በሬንጀርሶች ተፈልገዋል።  (ደይሊ ስታር)

የ35 ዓመቱ የብሪስቶል ሲቲ አሰልጣኝ ሊ ጆንስ ቅዳሜ በአሽተን ጌት ስታዲየም በሚደረገው ጨዋታ ቡድናቸው የሻምፒዮንሺፑ ተቀናቃኛቸውን በርተንን የማያሸንፉ ከሆነ የስንብት ዕጣ ይገጥማቸዋል። (ብሪስቶል ሲቲ)

የ48 ዓመቱ የፉልሃም አሰልጣኝ ስላቪሳ ጆካኖቪች በክለቡ ስኬያማ የሚሆኑ ከሆነ በሻምፒዮንሺፑ ለ10 ዓመታት ሊቆዩ እንደሚችሉ ተናግረዋል። (ለንደን ኢቭኒንግ ስታንዳርድ)

በመጨረሻም

በዝቅተኛው ሊግ ተሳታፊ የሆነው ሊንኮን ሲቲ ደጋፊዎች በኤፍኤ ዋንጫው ሩብ ፍፃሜ ከአርሰናል ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ትኬት ለመቁረጥ ሲሉ ሽያጭ ከሚጀምርበት 7 ሰዓታት ቀድመው ሰልፍ ጀምረዋል። ሊንከኖች ቅዳሜ መጋቢት 2፣ 2009 ዓ.ም ለሚደረገው የኤመራት ጨዋታ 7,000 ትኬት ተመድቦላቸዋል። (ሊንከንሻየር ኢኮ)

የስፓርታ ሞስኮው ተከላካይ ዲሚትሪ ኮምባሮቭ ለአምስት አመቷ ሴት ልጁ የልደት ክብረ በዓል አንበሳ ቀጥሮላታል። (ደይሊ ሚረር)

ስለባንዳዎቹ እውነቱን ከጠየቃችሁማ ይሄው (ኤርሚያስ ቶኩማ)

$
0
0

ጀግናው ራስ አሉላ

ኢትዮጵያውያንን ለዘመናት ከውጭ ወራሪዎች እየመጡ እንደፈለጉ ህዝቧን እንዲጨፈጭፉ ታሪካዊ ቅርሶቿን እንደፈለጉ እንዲዘርፉ ረዳት በመሆን ያገለገለው ከተከዜ በስተሰሜን ይገኙ የነበሩ ባላባቶች በተለይም ነገስታቱ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ከተከዜ ማዶ ነገስታቶች መካከል አጤ ዮሐንስ ፣ ልጃቸው ራስ መንገሻ፣ ጀግናውን ራስ አሉላን የገደለው የተምቤኑ ራስ ሐጎስ እና ኃይለስላሴ ጉግሳ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ባላባቶችና ነገስታት ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ኢትዮጵያን ከውጭ ወራሪዎች ጋር በመሆን ያወደሙ ብዙም ያልተወራላቸው ባንዳዎች ናቸው ቢወራም ስለኃይለስላሴ ጉግሳ እንጂ ስለሌሎቹ ብዙም አይፃፍም አንድነትን ይጎዳል ተብሎ ስለሚታሰብም እንዲወራ አይፈልግም፡፡

አጤ ዮሐንስ የሌላኛው ባንዳ የእንደርታው ገዢ የራስ አርአያ እህት ወይዘሮ ወለተ ሥላሴ ልጅ ናቸው፡፡ አጤ ዮሐንስ በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩትን አጤ ቴዎድሮስን ከስልጣን አስወግደው የኢትዮጵያ ንጉስ ለመሆን ያልሞከሩት ነገር የለም ከእነዚህም ውስጥ የተሳካላቸው የኢትዮጵያና የእንግሊዝን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መቋረጥ በመጠቀም ለእንግሊዞች በማደር የሠሜኑ የኢትዮጵያ ክፍልን ለእንግሊዝ ወታደሮች ክፍት በማደረግ አጤ ቴዎድሮስ የሚገኙበት መቅደላ ድረስ የሚሸኙ ሰዎችን በማዘጋጀትና ወታደሮቹን መንገድ እንዲመሩ በማድረግ መቅደላ ድረስ ከአፍ እስከገደፉ የታጠቀውን የእንግሊዝ ወታደሮች ወስደው አጤ ቴዎድሮስ አማራጭ እንዲያጡና እራሳቸውን እንዲያጠፉ በማድረግ ከእንግሊዞች የተገባላቸውን ቃል ተቀብለው አክሱም ላይ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገስት ተብለው የተሾሙ ናቸው፡፡ አስገራሚው ነገር በንግስና ቀናቸው ለእንግሊዝ ወታደሮች እና መንግስት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ናቸው ለእንግሊዝ መንግስት የጻፉት ደብዳቤ አጤ ቴዎድሮስን ለመውጋት በመጣው ጦር ውስጥ የተሳተፉት ዌልሄምሰን በፃፉት የታሪክ ማስታወሻ ላይ ይገኛል፡፡ እንግሊዞችም ለአጤ ዮሐንስ ውለታ ኢትዮጵያውያንን ለመውጋት ይዘውት መጥተው የነበሩትን መሳሪያዎች ለንጉሱ ሠጥተው ሄደዋል፡፡

ሌላኛው ባንዳ የአጤ ዮሐንስ ልጅ የሆነው የትግሬው ገዢ ራስ መንገሻ ነው፡፡ ራስ መንገሻ የአድዋ ጦርነት ሊካሄዱ ወራቶች ሲቀሩት ከጣልያኖች ጋር በመስማማት የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጦር በተቃራኒ እንዲቆምና ለጣልያን እንዲያድር ጣልያንን የጠላ ጠላቴ በማለት የፋሺሽት ጣልያን ወታደሮች ከበሮ እየተደለቀላቸው ወደኢትዮጵያ ድንበር እንዲገቡ ምክንያት የነበረ ሰው ነው፡፡ ይህ ታሪኩ ግን ብዙም አይወራም የማይወራበት ምክንያት ሃሰቡን ቀይሮ የፈፀመው መልካም ተግባር ስላለ ሳይሆን ቢወራ እና እውነታው ቢታወቅ ህዝቦችን ከማራራቅ በተለየ ሊፈጠር የሚችል ነገር ስለማይኖር እውነታው እንዲደበቅ ተደርጓል፡፡

ሶስተኛው ባንዳ የተንቤን ተወላጁን ጀግናውን የእንግዳ እቁበን ልጅ የራስ አሉላን ህይወት የነጠቀው የተምቤን ገዢ የነበረው ራስ ሐጎስ ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ከጣልያኖች ብዙ ድጋፍና እርዳታ ይደረግለት የነበረ እና ራስ አሉላን እንዲበቀል ከፋሽሽት ኢጣልያ ትዕዛዝ የተሠጠው ህሊናው በገንዘብና በጥቅም የታወረ ግለሠብ ነበረ፡፡ ራስ አሉላ ከአድዋ ድል በኋላ ሐገር ሰላም ብለው በተቀመጡበት ወቅት ይህ ባንዳ ራስ ሐጎስ የሚባል የጣልያን ተላላኪ ወታደሮችን አዘጋጅቶ የራስ አሉላ ጦር ባልተዘጋጀበት ሁኔታ ጦርነት በመክፈት የራስ አሉላን እግር በጥይት በመምታት ጀግናው የኢትዮጵያ ባለውለታ ራስ አሉላ አባነጋ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር የካቲት 15 1897 ህይወታቸው እንዲያልፉ ያደረገ ታሪክ ሊረሳው የማይገባው የጣልያን ተላላኪ ነበረ፡፡

አራተኛው ባንዳ ብዙዎቻችን የምናውቀው ኃይለስላሴ ጉግሳ ነው፡፡ ኃይለስላሴ ጉግሳ የአጤ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ነው፡፡ ይህ ባንዳ ከራስ ስዩም ጋር በመሆን ትግራይን ለሁለት ከፍሎ ሲመራ የነበረ ግለሠብ ሲሆን በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት አጤ ኃይለስላሴ ልጃቸውን ዘነበወርቅን ገና በ13 ዓመት እድሜዋ የዳሩለት ግለሰብ ነው፡፡ ይህ እንሰሳ የ13 ዓመት ልጅ የነበረችውን ዘነበወርቅ በማስረገዝ በወሊድ ምክንያት ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረገ ነውረኛ ግለሠብ ነው፡፡ ባንዳው ኃይለስላሴ ጉግሳ እንደቀደምቶቹ ኢትዮጵያን ለመካድ ከነበረው ፍላጎት የተነሳ አጤ ኃይለስላሴን የምገዛው መሬት ስላነሰኝ ግዛት ይጨመርልኝ በማለት ቁርሾውን ከጀመረ በኋላ የ2ኛው የጣልያን ወረራ ሊነሳ አቅራቢያ መስከረም 28 ቀን ከአዲስ አበባ ጋር የሚገናኘውን የስልክ መስመር በሙሉ በጣጥሶ በወታደሮቹ ታጅቦ አስመራ በመግባት ለጣልያን ለማደር የተስማማ ነው፡፡ እዚህ ጋር እጅግ ልብ የሚነካው ተግባር የእርሱ ወታደሮች የፈፀሙት ተግባር ነው፡፡ ኃይለስላሴ ጉግሳ 12000 ወታደሮች የነበሩት ሲሆን ባንዳ ለመሆን መስማማቱን ሲያውቁ አስመራ ድረስ አብረውት ለመሄድ የተስማሙት አንድ ሺህ ብቻ መሆናቸውን ደቦና በመፅሃፉ ገልጧል፡፡ ኃይለስላሴ ጉግሳ ከባንዳነቱ በተጨማሪ አንዳንድ የትግራይ ሹማምንት ለኢጣልያ እንዲያድሩ በማድረግ ጣልያኖች በነፃነት የትግራይ ምድር ላይ እንዲጨፍሩና የትግራይ ህዝብ ላይ እንደፈለጋቸው እንዲፈነጩ ያደረገ ባንዳ ነበረ፡፡
ደንቆሮን ደንቆሮ ካላልከው ደንቆሮነቱን ሊረዳ አይችልም ይላሉ አባቶቻችን እውነት ነው ደንቆሮን ደንቆሮ ልንለው ይገባል ችግሩ የዘንድሮዎቹ ደንቆሮዎች ደንቆሮ ብንላቸውም ሊሠሙን አልቻሉም ምክንያቱም ደንቆሮ መስማት አይችልምና ሆኖም እውነታውን አሁንም ቢጠቅምም ባይጠቅምም ከዚህ በኋላም መፃፋችንን እንቀጥላለን፡፡

ቸር ያገናኘን
#ኤርሚያስ_ቶኩማ

ኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የተመዘዘዉ የወያኔ የበቀል በትር? – ሸንቁጥ አየለ

$
0
0

ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እየተነሳ ከ12 በላይ በሚሆኑ የኦሮሚያ ወረዳዎች ላይ የጥቃት እርምጃ ስለሚወስደዉ እና ወረዳዎቹን ስለሚወረዉ ህገወጥ ሀይል የጀርመን ድምጽ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል:: የጀርመን ድምጽ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣኖችን እያነጋገር ለመስማት የሚዘገንኑ ሀቆችን ሲያቀርብ ያደመጠ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በወያኔ በቀልተኛ እርምጃ መበሳጨቱም መገረሙም አይቀርም:: ይሄ ከሶማሌ ክልል የሚነሳዉ ወራሪ ሀይል በኦሮሚያ ክልል ያለዉን ማህበረሰብ የማፈናቀል: ወረዳዎችን የመዉረር ብሎም ወረዳዎቹን የሶማሌ ክልል ናቸዉ ብሎ የሶማሌ ክልል ባንዲራን በወረራቸዉ ወረዳዎች ላይ የማዉለብለብ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ተብራርቶ ቀርቧል::

ይሄዉ ህገወጥ ሀይል የኦሮሚያ ወረዳዎች የሶማሌ ወረዳዎች ናቸዉ የሚል መግለጫ እየሰጠ ኦሮሞዉን እያፈናቀለ ወረዳዎቹንም በቁጥጥሩ ስር እያደረገም እንደሆነ ያደመጠ ሁሉ ወያኔ በቀጣይነት ኢትዮጵያዉያንን እርስ በርሳቸዉ በክልል ግዛት ጉዳይ ሊያጫርሳቸዉ በሰፊዉ እንዴት እንዳቀደ ግልጽ ይሆንለታል::የሚያሳዝነዉ ደግሞ የፌደራል መንግስቱ እና የሶማሌ ክልል መንግስት በኦሮሚያ ክልል መንግስት አገላለጽ መሰረት ይሄ ከሶማሌ እየተነሳ ኦሮሞዉን እየፈጀ ስላለዉ ሀይል ሲጠየቁ ይሄ ሀይል ከመንግስት ቁጥጥር ዉጭ ነዉ እያሉ የፌዝ መልስ እየሰጡ ነዉ:: ሆኖም የኦሮሚያ ባለስልጣናት በመረጃ ለጀርመን ድምጽ እንዳቀረቡት ይሄ ከሶማሌ ክልል የሚነሳዉ ህገወጥ ሀይል የሰለጠነዉ እና የሚታዘዘዉ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ /ህዉሃት/ ነዉ::

የዚህ ሁሉ ዋና ማጠንጠኛዉ ግብ በቀል ነዉ::ኦሮሞው ለምን የዲሞክራሲያዊ መብቴ ይከበር የሚል ጥያቄ አነሳ የሚል ታሳቢ ነዉ::ወያኔ ስልጣን የያዘ አመታት ዉስጥ አንድ ሸዉራራ ታሳቢን አንግቦ ነበር ወደ ስልጣን የወጣዉ::ይሄዉም ኦሮሞዉን እያሞኘሁና እያስፈራራሁ ዘላለሜን እጋልበዋለሁ: አማራዉን ደግሞ በሌሎች ብሄሮች እያስቀጠቀጥሁና አከርካሪዉን ሰብሬ ለዘላለም እገዛዋለሁ የሚል ቀመርን ይዞ ነበር የተነሳዉ::

በወያኔ ቀመር መሰረት እነዚህን ሁለት ትልልቅ ብሄረሰቦች እርስ በእርስ ከፋፍለህ ግዛዉ ከተቆጣጠራቸዉ ሌላዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አስቸግሮም አያስቸግረዉም:: ሆኖም ወያኔ ያሰበዉ እና የቀመረዉ ስትራቴጅ ስህት መሆኑን ሀያ አምስት አመታት ሙሉ የኦሮሞ ህዝብ ወያኔን ተጋፍጦ ስለዲሞክራሲያዊ መብቱ እየሞገተዉ ይገኛል::በተለይም በመላዉ ኦሮሚያ ተነስቶ የነበረዉ የኦሮሞ ተቃዉሞ ወያኔን በኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የበቀል በትሩን እንዲያነሳ አድርጎታል::አንዱ የበቀል በትሩም ኦሮሞዉን ከሶማሌ ክልል በሚነሳ ህገወጥ ሀይል ማስቀጥቀጥ ማፈናቀል እና ማስጨረስ ሆኖ ተከስቷል::

ወያኔ ምናልባትም የኦሮሞን ማህበረሰብ በአራቱም አቅጣጫ ከልዩ ልዩ የሀገሪቱ ማህበረሰቦች ጋር በማጋጨት እና በማስጨረስ የመጨረሻዉን የበቀል እርምጃ ሊወስድበትም እየተዘጋጀ ሊሆን ይችላል::

የኢትዮጵያን ህዝብ በአጠቃላይ ለመታደግ እና ለመፈወስ ኢትዮጵያዉያን የተቃዉሞ ሀይላት አንዱ የአንድነት ሀይል: ሌላዉ የብሄር ሀይል ተባብለዉ ለዬብቻ ሳይሮጡ ቁጭ ብለዉ በጥበብ እና በሰከነ መልክ ቢመክሩ ብቻ ለሁሉም የምትመች እና ሁሉም የሚስማማባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መፍጠር ይቻላሉ:: የኦሮሞ ተቃዉሞ ሀያላትም ከወንድሞቻቸዉ የአማራ ተቃዉሞ ሀይላት ጋር ያለባቸዉን የልዩነት መሰረት ለሁለቱም ማህበረሰብ በሚበጅ መልክ ፈትተዉ እንዲሁም መላዉ የኢትዮጵያን ህዝብ በሚጠቅም መልክ ኢትዮጵያን ለማዳን ከአንድነት ሀይሉም ጋር ተባብረዉ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መፍጠር ላይ ቢተጉ መልካም ይመስለኛል::

ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በደንብ ሊረዱት የሚገባዉ የዲሞክራሲያዊነት ምርጫ እና የመጻኢዉ ጊዜ ምልዓታዊ የማህበረሰብ ብልጽግና ሁሉ በራሳቸዉ እጅ ብቻ እንደሚገኝ ቢረዱት መልካም ነዉ::ከዚያ ዉጭ ድጋፍ ከዚያ ወይም ከዚህ የዉጭ ሀይል ወይም ከዚህኛዉ ወገን ለዚህኛዉ ማህበረሰብ ተብሎ የሚሰጥ ድጋፍ ሁሉ ሁሉንም ማህበረሰብ የማያድን ስለሚሆን የመጨረሻዉ ጉዞ ወደ ጥልቁ መርዛማ ባህር ነዉ::መፍትሄዉ ኢትዮጵያዉያን ብቻቸዉን ቁጭ ብለዉ የማንንም የዉጭ ሀይል እጅ ሳያስገቡ ይነጋገሩ: ይመካከሩ: መወቃቀስም ካስፈለገ ይወቃቀሱ: ሀይለኛ እና ፍጹም የአማራጭ ሀሳቦች ላይ ይከራከሩ::

በመጨረሻም ለሁሉ ወገን የሚበጀዉን የተሻለ አማካይ እና አካታች መስመር በመከተል አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመፍጠር በመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ህዝብ ላይ እየተፈጠረ ያለዉን ያለመረጋጋት እና የመከራ አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቀረት ይስሩ:: ኢትዮጵያዉያን ከተባበሩ ወያኔን አንድም በድርድር ወይም በሀይል ከወንበሩ የማንሳት ስራም የሳምንታት ስራ ብቻ ይሆናል:: ሌላዉ ምርጫ ሁሉ የጨላማ ጉዞ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ አዙሪት ነዉ::


የትግራይ ብሄርተኞች የአማራ እና የምኒልክ ጥላቻቸው ምንጩ ምንድነው?

$
0
0

ሰሞኑን አንድ በግርድፍ የተፃፈ እና ለማንበብ እግር እግር የሚልና ቋቅ የሚያስብል ፅሁፍ ተፅፎ ተመለከትኩኝ ።
መቸም ከዛ አካባቢ ብቅ የሚሉት ሁሉ ፅሁፋቸው አይስብ ንግግራቸው Scratch እንዳደረገ ሲዲ ለጆሮ አይመች እነሱም አያፍሩም እኛም በይሉኝታ ዝም እያልናቸው ተቸገርን።
ፅሁፉ ” ትግሬዎች ለምን አፄ ምኒልክን ይጠሉታል ” የሚል ርእስ ያለውና ከስሩ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ተረት ተረትነት ፅሁፉን ዘላችሁት እንድታልፉ የሚያደርግ ቢሆንም ብዙ ሰዎችን የማሳሳት አጋጣሚ ሊፈጥር ስለሚችል ይሄን በመርዝ ተቦክቶ በተንኮል የተጠፈጠፈ አምባሻ ሌላው እንዳይበላው ማስጠንቀቅ እንዳለብኝ በመገንዘብ ማርከሻውን ለመፃፍ ወሰንኩኝ ።

በፅሁፉ መጀመሪያ ትግሬዎች አፄ ምኒልክን የጠሉት ኤርትሪያን እና ጅቡቲን ለጣሊያንና ለፈረንሳይ አሳልፎ ስለሰጠ የሚል የጠላ ቤት ወሬ አይነት ነገር ተፅፏል ።
ባለፈው መለስ ዜናዊ የሞተ ሰሞን አንድ የትግሬ ኮሌኔል “መለስ ዜናዊና የህውሃት የትግል ጉዞ ” በሚል ርእስ በፃፈው መፅሀፍ ላይ ” መለስ ዜናዊ በልጅነቱ ጠላ በጣም ስለሚወድ ጉሽ ጠላ ካልቀመሰ ትምህርት ቤት እሽ ብሎ አይሄድም ነበር ” :ብሎ ፅፎ ፈገግ አድርጎኝ ነበር ምናልባት ይሄን ተረት ተረት መለስና ስብሃት ነጋ ጠላ ቤት ፅፈውላቸው ሊሆን ይችላል ።

እስኪ ነገር መደረት ሳላበዛ ወደ ገደለው ልግባ ። ኤርትሪያን በተመለከተ መቼና በማን ዘመነ መንግስት ወደ ኢጣሊያ እንደገባች በዝርዝር ፅፌው በስፋት በተለያየ ድረገፆችም ጭምር (ስሜን ባለመጥቀሳቸው ቅር ቢለኝም ) ስለተሰራጨ እኔም ፔጅም ላይ ስላለ ማንበብ ይቻላል ።
..
ለማስታወስ ያክል በአጭሩ ኤርትሪያ አፄ ምኒልክ ከመንገሱ አንድ አመት በፊት በአፄ ዮሀንስ ዘመነ መንግስት የኢጣሊያ መንግስት በአፍሪካ የመጀመሪያውን ቅኝ ግዛት አገሩን “ኤርትሪያ ” ብሎ እንደሰየማትና አፄ ምኒልክ የተረከቧት ኢትዮጵያ ከመረብ ወንዝ ወድህ ያለውን ኢትዮጵያ እንደነበር መታወቅ አለበት ።

ጅቡቲን ወደተመለከተው ” በሬ ወለደ ፣ላም በሰማይ ሲበር ዋለ ” አይነት ተረት ተረት እንግባ ።
የጅቡቲው እና የምኒልክ ጉዳይ ሁሌ ሲገርመኝ ይኖራል ምክንያቱም ብዙ ሰው አዋቂ ናቸው ተብለው የሚገመቱ ሰዎች ይሄን ተረት ተረት ሲደግሙት መስማት ያሳፍራል ። ይሄ ተረት ” ምኒልክ ጅቡቲን ለፈረንሳይ ለ 99 አመት ሊዝ ሰጥተዋል ” የሚል ጉደኛ ተረት ነው።
የጅቡቲ እውነተኛ ታሪክ እንደሚከተለው በአጭሩ ላስቀምጥላችሁ :

ጅቡቲ በየትኛውም የኢትዮጵያ ታሪክ ዘመን የኢትዮጵያ ወደብ ሆኖ አያውቅም ።

ከ 1150 _ 1270 ድረስ የነገሱት ዛግዌ ነገስታት ጅቡቲን ከአካባቢው ገዥዎች ጋር በመዋዋል በኪራይ አልፎ አልፎ በወደብነት ይጠቀሙበት እንደ ነበር ተፅፎ ይገኛል ። በ 1270 ዛግዌዎች ስልጣናቸውን ሲያጠናቅቁ ጅቡቲን መጠቀም አቆሙ ። ይሄ ማለት ምኒልክ ወደዚህ አለም ከመምጣቱ 500 አመታት በፊት መሆኑ ነው ።ልብ በሉ ምኒልክ በጅቡቲ ጉዳይ በአላዋቂዎች የሚወቀሰው የእኛ ባልሆነ ወደብና ከ500 አመታት በፊት ኢትዮጵያ በኪራይ ትጠቀምበት በነበረው የሌላ ህዝብ ወደብ በሆነ ጉዳይ ነው።
በጣም ይገርማል የእነዚህ ሰዎች ድንቁርናና በማያውቁት ጉዳይ ላይ ለመፃፍ እና ለመናገር ያላቸው ድፍረት ሃጃኢብ የሚያስብል ነው።

አሁን በፍጥነት ወደ ዋናው ርእሴ ልግባና መልሱን በአጭሩ ለማስቀመጥ ልሞክር ። ትግሬዎች ምኒልክንና አማራን ለምን ይጠላሉ?
..
አፄ ዮሐንስ በጥይት መተማ ላይ ቆስለው በነበረ ጊዜ ዘውዴን ለልጄ ራስ መንገሻ አውርሻለሁ ብለው ተናዘው ቢሞቱም ቀድሞም ንጉስ የሚል መአረግ የነበረው እና ከዮሀንስ የበለጠ ሰፊ ግዛት ያስተዳድር የነበረው ምኒልክ በቀላሉ ካለምንም ደም መፋሰስ በሰላም የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መሆኑን በአዋጅ አስነገረ ። ዮሀንስ ሞቶ ዘውዱ በምኒልክ ሲተካ ትግሬዎቹ ከፍተኛ የሆነ ” የባዶነት ስሜት “Emlitiness ” ይሰማቸው ጀመረ ። ከ 1000 አመታት በኋላ በዮሀንስ አማካኝነት እጃችን ገባ ያሉት ስልጣን አፍታም ሳይቆይ እንደ ማለዳ ጤዛ ተስረባቸው ። እንቁልልጭ ብሏቸው በምኒልክ ወደ ተገቢው ቦታ ተመለሰ ።

የትግሬ ብሄርተኞች አፄ ዮሀንስ በመተማ ጦርነት ከተሰው በኋላ የዙፋኑን መንበር የተረከቡት ምኒልክ እንደ ጠላት እና ባእድ ንጉስ አድርገው በመመልከት ” የትግሬ ስልጣን ወደ አማራ ሄደብን ” በማለት በራስ መንገሻ አማካኝነት ትግራይ ውስጥ የምኒልክን ንጉስነት አንቀበልም በማለት እምቡር እምቡር ቢሉም በሀረሩ ገዥ ራስ መኮንን የሚመራ የምኒልክ ሰራዊት ትግራይ ዘምቶ አንድ 20 የሚሆኑ ጥይቶች እንደ ፈንድሻ ጠሽ ጠሽ አድርጎ ሙሉ ትግራይን ከተቆጣጠረ እና መንገሻን ከእነ ህይወቱ ከማረከ በኋላ የትግራይ አመፅ በዚሁ አከተመ ።

ይሄን ዘመን የትግሬ ብሄርተኞች በቁጭት የምኒልክ ዘመን በማለት ያስታውሱታል።
ሃቁ ይሄ ሆኖ እያለ በታሪክ ደላላዎች እና በአላዋቂ ብእር ማንም በሞነጫጨረ ቁጥር መታለል የለብንም።

ወሎ ነኝ

ህዝብ የወደደውን ውደዱ – ለገሠ ወ/ሃና

$
0
0

በድጋሚ እንኳን ለ121ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰን እንኳን በማግስቱ አመቱን ሙሉስ ብለውስ መቼ ይሰለቸኛል እኔ የምኒልክ ስለሆንኩ ዓመት አልጠብቅም ሁልጊዜው በውስጤ ኩራቴና ትምክህቴ አብሮኝ ነው የኔነቴ መሠረት ስለሆነ በኩራት አነሳዋለሁ የዘንድሮው የአድዋ ድል አከባበር በምድርም በሳይበርም ባስደናቂ ሁኔታ ተከብሯል ኦነጋውያንና ህውሃታውያን የሚተነፍሱበት አፋቸው ተዘግቶ የሚሞነጫጭሩበት እጃቸው ቀጠማ ሆኖ ምድር ጠቧቸው ምን ውስጥ እንግባ ብለው ሲጨነቁ ስመለከት እንዴት ደስ አለኝ አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ እኛ ጠጋ ጠጋ ለማለት የሞከሩ አሉ እኛ አይከፋንም የምንመኘው በሚቀጥለው ዓመት አንጎላቸው መሥራት ጀምሮ አብረውን እንዲያከብሩ ነው ፡፡
ባያከብሩም እነሱ ክብር ያጣሉ እንጂ እኛ ክብራችን አይጎድልብንም ፡፡
ጊዜ ሰጥቷቸው ምኒልክ ቤተመንግስት የገቡት ወንበዴዎች እና የባንዳ ልጆች የኢትዮጵያን ባለውለታ የሆኑትን እምየ ምኒልክን እንዲጠላ ብዙ ቢደክሙም አልተሳካላቸውም እንዲያውም የበለጠ እንድንወዳቸው ፣ እንድናደንቃቸውና እንድናከብራቸው አደረጉን የኢትዮጵያ ህዝብ ለምኒልክ እና ለአድዋ ድል ያለውን የላቀ ክብር መቼም አያስቀረውም ህዝብ ባለውለታውን ያውቃል ውለታ ለዋሉለት የላቀ ክብር ይሰጣል
በዓለም ታሪክ ህዝብ ተሳስቶ አያውቅም ህዝብ ምንጊዜም ትክክል ነው ፡፡
ወያኔና አጋሮቹ ለ40 ዓመት የነዙትን ፀረ አማራና ፀረ ምኒልክ ፕሮፓጋንዳ ቦታ አጣ ለጀግናው ለእምየ ምኒልክና አብረውት ድል ላስመዘገቡት ጀግኖች ያለውን አድናቆት እና አክብሮት ሁኔታዎች ባይመቹም የሚቻለውን መንገድ በመጠቀም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አወደሰ አከበረ ፡፡
ወደፊትም እያከበረ ይኖራል ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ህውሃት በፈጠረው አፈታሪክ ተታላችሁ ያከበራችሁን ያላከበራችሁ ወደ ህሊናችሁ ተመለሱና ባለውለታችሁን አክብሩ ህዝብ የወደደውን ውደዱ ተረቱን እርሱት ፡፡
ክብረቢሶቹ እና የባንዳ ልጆች ውለታ የማያውቁት ህውሃትና ጀሌዎቹ በምኒልክ ጀግንነት ሁልጊዜ እንደተሸማቀቁ ይኖራሉ ፡፡ እኛ ግን በክብር ቀና ብለ እንራመዳለን ፡፡
ክብር ለአድዋ ጀግኖች !!!

ከውስጥ አዋቂ የደርሰኝ መርጃ እንዲህ እንደሚከተለው ቀርቧል – ካርበኞች መንደር አሞራው ምንአለ ባሻ

$
0
0

ማፊያው ህወሀት ወያኔ የነጻነት አርበኞች ታጋዮችን በብአዴንና በመስሎቹ በብሔር አቀንቃኞች ሙሉ በሙሉ እጁን በማስገባት የማዳከም ሥራውን በመሥራት ላይ ይገኛል። ለምሳሌ ዱር ቤቲ ብለው የገቡትን ጀግኖች በተለያየ ዘመደ አዝማድጥቅማጥቅም በመደለል እርምጃውን አጥናክሮ ቀጥሎበታል፡በተለይ በሥራቱ ላይ ከፍተኛ ሥጋት ያመጡብኛ ብሎ የሚፈራቸውን ታጋይ ጀግኖች አይከፍሉ ከፍሎ የመደለል ሥራውን በበቂ የሥለላ መዋቅር መከናወን እንዳለበት በደህንነት መስሪያ ቤቱ ተወስኖ እየተሰራበት መሆኑን የውስጥ ዘጋቢያችን አረጋግጦልኛል።

በተለይ ከድህንነት መስሪያቢቱ አፍትልኮ የወጣው መርጃ ሰሜንኑን የሀገራችን ክፍል ለወያኔ ትልቁ ስጋት ሁኖ በስፋት መሰራት አለበት ብለው የማዳከም ሥራውን ለመስራት ከፍተኛ ወጭ ተደርጎ በስውር እየተሰራ መሆኑን መርጃው ደርሶኛል።ቦታዎችን ለመጠቀስ አስፈላጊ አይደልውም የነጻነት ኋይሎችን ይጎዳልና አያይዞም የአድዋን በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በዘንድሮው ለማክብር የወሰኑት ህወቶች የተበላሽውን ፖለቲካቸውን ለማደስ የተጠቀሙበትና የህዝቡን ስሜት ለመሳብ ያደርጉት ድርጊት እንጅ፡ ለአባቶች ተጋድሉ አስበው አይደለም ወያኔ ዘረኛው አጼ ምንሊክን ጡት ቆረጡ ብለው ኦሮሚያ ክልል የሰሩት ሀውልት ብሔርን ከብሔር ለማናከስ የሰሩት ሲራ እንዲት ቢቀልዱ ነው እምየ ምኒሊክን የጥቁር ህዝቦች አባት ተምሳሊ የሆኑትን እንዲት አፋቸውን ሞልተው ሊያከብርይት ቻሉ?
አወ የህዝብን ትኩርውት ወይም አቅጣጫ ለማስቀየር መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ቅድሚያ አውቆታል።

በአማራ ክልል አያሊ ሰዎች እየተረሽኑ በተለይ ሰሜን ጎንደር፡ አርማጭሆ፡ዳባት አጅሪጃኖሯ እንቃሺ፡በለሳ ወገራ፡ መተማ ቋራ ሽንፋ ደልጊ፡ አለፋጣቁሳ፡አይምባ ደንቢያ፡ ደቡብ ጎንደር ጋይንት ደብርብርሃን፡ ጎጃም በአጥቃላይ በነዚህ ቦታዎች በጠቀስኳቸው አያሉ ሰዎች በስውር እየተረሽኑ መሆኑን ከስፍራው ዘጋቢው መርጃውን አድርሶኛል።
በአንድ በኩል በሱማሊ ኦጋዴን በኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ህዝቦችን እረስበርሱ እያስጨፋጨፉ ኦሮሚያ ውስጥ አያሊ ሰዎች እየተገደሉ፡ በጋምቤላ ክልል ህጻናትና ሀብት ንብረታቸው የቀንድ ከብቶቻቸው ሳይቀርእየተዘረፉ፡ እየታፈኑ በየቀኑ ውደ ደቡብ ሱዳን እየተወሰዱ ባሉበት ሀገር ! እንዲት ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመሽወድ አፉን ሞልቶ ይናገራል፡ የኢትዮጵያ ዚጎች አብዛኛው ወጣቶች ተሰደዋል ታሰርዋል ተገልዋል፡በስደትም ስላም አግንተው እንዳይኖሩ አድርጓል፡በሱዳን ውስጥ በኢትዮጵያኖችና በኤርትራዎች፡ አሱማሊዎች ላይ አያሊ ስቃይ መድርሱን የአውሮፓ ፓርላማን የአቋም መግለጫ አውቷል ከነዚህ ውስጥ አብዛኝውን ግን ግፍና ስቃይ የሚበዛበት የኢትዮጵያ ሰደተኞች ናቸው።

በህዝባችን የሚቀለደውን ግፍና ስቃይ ህዝቡ ይወቅው!

ድል ለጭቁኑ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ።
ሞትና ውርደት ለዘረኞች የባንዳ ልጆች።
ካርበኞች መንደር አሞራው ምንአለ ባሻ ነኝ

የአድዋን ትርጉም ለሚያቃልሉት የሹምባሽ ልጆችና የቁቤ ዋቆ ትውልድ – መስቀሉ አየለ

$
0
0

አስራ አራት የአፍሪካ አገሮች ከኮሎኒያልዝም ነጻ ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ የባርነት ግብር [Slavery Tax] ይከፍላሉ።

ነገሩ እንዲህ ነው፤እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በአስራ ዘጠኝ መቶ አምሳ ስምንት ጊኒ “ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት መውጫው ግዜ አሁን ነው፤ጊኒ ለጊኒያውያን” ባለች ግዜ ይኽ እርምጃ የፈጠረው ድንጋጤ ባርነት ፍንገላውን ተፈጥሯዊ መብታቸው ላደረጉት ፈረንሳዮች የሚያዋጥ አልነበረም። በመሆኑም ነገሩ ወደኋላ እንደማይመለስ ሲያውቁት በአገሪቱ ውስጥ “አለን” የሚሉትንና ማንቀሳቀስ የቻሉትን ንብረት ሁሉ ወደ ፈረንሳይ ካጋዙ በኋላ መንቀሳቀስ የማይችሉትን እንደ ሆስፒታል፣መጻህፍት፣ ትምህርት ቤቶች፣ መኪኖች፣ ትራክተሮች፣ ትልልቅ ፤እርሻዎችን ወዘተ በፈንጅ ያጋዩ ሲሆን ከብቶችንና የጋማ ከብቶቹን በሙሉ ደግሞ ለቁጥር ሳያቀሩ ገድለው ወጡ። ይኽ የፈረንሳዮች የበቀል ሰይፍ አላማው ሌላ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ ለሚፈልጉ የቀሩት የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት አገሮች ምንም አይነት የነጻነት ጥቄው ከማንሳታቸው በፊት ሁለት ግዜ ማሰብ እንዳለባቸው ለማጠየቅ መሆኑ ነበር።

ሆኖም ግን በወቅቱ በድፍን አፍሪካ እየተቀታጠለ የመጣው የፓንአፍሪካኒዝምን ወላፈን በቀላሉ የሚጠፋ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን በገዛ አገራቸው ከእንስሳት በታች ቀን ለሚገፉት አፍሪካውያን ከዚያ የተሻለ አማራጭ ግዜ ሊመጣ ስለማይችል ትግሉን አጠናክረው ወደፊት ከመግፋት ውጭ ሌላ አማራጭም አልነበራቸውም።ነገር ግን ፈረንሳዮች ደግሞ ያንን ሁሉ ጥቅማቸውን አሳልፎ ላለመስጠት እየሄዱበት የነበረው የበቀል ደረጃ አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው የቶጎ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣን ላይ የወጡት ሲልቫኖስ ኦሊምፒዮ ለሁለቱም ሃይሎች ግማሽ መንገድ ድረስ የሄደ አንድ አማራጭ የመፍትሔ ሃሳብ አቀረቡ። ይኼውም ፈረንሳዮች አገራቸውን ከሚያወድሙባቸው “በየአመቱ የባርነት ታክስ (slavery tax ) እንከፍላለን” የሚል ሲሆን ባሪያ ፈንጋዮቹም በውሳኔ ሃሳቡ ተስማምተው “በሰላም” የወጡ ቢሆንም የክፍያው መጠን ግን ውሎ አድሮ ቶጎን ለመሳሰሉ ገና በቅጡ በሁለት እግራቸው ላልቆሙ ትናንሽ አገሮች እንዲህ በቀላሉ የሚገፋ ነገር አልነበረም።ለዚህም አንዱ ማሳያ በአስራ ዘጠኝ ስልሳ ሶስት ዓም ክፍያው የአገሪቱን አጠቃላይ በጀት አርባ በመቶ ያህል ደርሶ የነበረ በመሆኑ በአገሪቱ ውስጥ ፈጥሮ የነበረው አለመረጋግት ከፍተኛ መሆኑ ነው።

ፈረንሳዮች የእጅ አዙር ፍንገላውን የሚያቀላጥፉበት ዋነኛው መንገድ ለነዚህ የቀድሞ ኮሎኒዎች የሚሆን ፤እራሱን የቻለ “ፍራንክ” የሚባልና በፓሪስ ብሔራዊ ባንክ በሚታተም ከረነሲ እንዲጠቀሙ በማድረግ ክፍያውን ደግሞ በወርቅና በመሳሰሉት የሚያወራርዱ ሲሆን ጫናውን መቋቋም የከበዳቸው ፕሬዝዳንት ኦሎምፒዮ ከስምምነቱ በማፈንገጥ የራሳቸውን ብሄራዊ ገንዘብ ማተም ቢጀምሩም በአገሪቱ ውስጥ የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ አንድ ፊደል ላልቆጠረና በአገሪቱ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ በቅጡ ለማይረዳ ነገር ግን ጠመንጃ መተኮስ የማይሳነው ኢኔቴ ናሲንግቤ የተባለ ቅጥረኛ ነፈሰ ገዳይ ሹምባሽ ስድስት መቶ አምሳሁለት ዶላር በመክፈል አስገደላቸውና ህልማቸውን አጨነገፈው። በቅሎ አመልጣለሁ ብላ ማሰሪያዋን አሳጠረች ነው ነገሩ።

ቀጣይዋ ተረኛ ማሊ ነበረች። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የነበሩት ማዲባ ኬቴ ከስምምነቱ መውጣታቸውን ይፋ ባደረጉ በጥቂት ግዜያት ውስጥ የፈረንሳይ የወታደራዊ አታሸ ባቀናበረው መፈንቅለ መንግስት ተሰልቅጠው በታማኝ ባንዳው ኮሎኔል ሙሳ ትራዎሬ ተተኩ።

እንግዲህ አስራ ዘጠኝ ስልሳዎቹ ማለት አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት ቀንበር ወደ ነጻነቱ ጎራ ለመቀላቀል ደፋ ቀና በሚሉበት ሰዓት በአንጻሩ ደግሞ ፈረንሳዮች በያንዳንዱ አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሁሉንም ነገር ከቁጥጥራቸው ስር እንዳይወጣ ያልተከሉት እንቅፋት ያላፈሰሱት ደም አልነበረም።በጥር አስራ ዘጠኝ ስልሳ ስድስት የሴንትራል አፍሪካው ዴቪድ ዳኮ በነፍሰ በላው እና በስልጣን ዘመኑ የተቀናቃኝ ፓርቲ አባላቱን መሪዎች እየገደለ ስጋቸውን በማይክሮዌቭ ሳይቀር እየጠበሰ ይበላ እንደነበር በሚነገርለት ቦካሳ በተባለ ታማኝ አሽከራቸው እንዲገለበጥ አደረጉ። ነገሩን አጠናክረው በመቀጠል በሰኔ አስራ ዘጠኝ ስልሳ ስድስት በቡርኪናፋሶ እንዲሁም በአስራ ዘጠኝ ሰባ ሁለት በቤኒን የተፈጸሙት የመፈንቅለ መንግስት ክንዋኔዎች ሁሉ በፈነርሳይ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት የተመሩ ናቸው።

በአጠቃላይ በአለፉት አምሳ አመታት ብቻ በሃያ ስድስት የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ስልሳ ሰባት ያህል የመፈንቅለ መንግስት ሲፈጸም ከነዚህ ውስጥ ስልሳ ሁለት በመቶዎቹ የተካሄዱት የቀድሞ የፈንሳይ ቅኝ ግዛት በሆኑት አገሮች ውስጥ መሆኑ በራሱ የሚያሳየው ነገር አለ።

ይኽ ማብቂያው የማይታወቅ ውል ቀይ ቢላ ሆኖ አስራ አራት በሚያህሉ የቀድሞ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ቤተመንስቶች አልጋ ስር ዛሬም ድረስ ተቀምጧል። ወደነዚህ አልጋ የሚጠጋ አፍሪካዊ መሪ ይህንን ስውር ስለት እያወቀ የሚገባ ሲሆን ከዚህች አንድ እርምጃ የሚያፈገፍግ ማንም ቢኖር እጣ ፋንታው የሚያሻማ አይደለም። ባርነት ፍንገላው ዛሬም ድረስ እጁ እንደረዘመ ነው።

መሪራስ አማን በላይ በስድሳ አምስት ዓመታቸው አረፉ

$
0
0

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Mar. 3, 2017)፦ የተከበሩት ባለታሪክ፣ ፈላስፋ፣ ባለመድኃኒት፣ የነገረ-መለኮት አዋቂ እና የ24 መጻሕፍት ደራሲ የነበሩትመሪራስ አማን በላይ ባደረባቸው ሕመም የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 17 ቀን 2017) በሎስ አንጀለስ ከተማ በተወለዱ በ65 ዓመታቸው ከዚህዓለም ተለዩ።

መሪራስ አማን የተወለዱት መጋቢት ፳፫ ቀን ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. አፕሪል 1 ቀን 1951 ዓመተ ምህረት) ሲሆን፣ የትውልዳቸው ስፍራቸው በለሳ ተብሎበሚጠራና ጎንደር ውስጥ በሚገኘ አካባቢ ነበር። የአደጉትም በጎንደር እና በጎጃም ውስጥ እንደነበር ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ ዝግጅት ክፍል የደረሰው ዘገባ ያስረዳል።

ከልጅነታቸው ጀምሮ ትምህርታቸውን የቀሰሙት ከአባታቸው ከመምህር በላይ ድሉ፣ ከአባ ጼሄማ በጎንደር ተክለኃይማኖት፣ ከመሪጌታ መንክር ደብረኤልያስጎጃም፣ ከመሪጌታ ጉባኤ በጎጃም ነበር። መሪራስ አማን፤ ቅዳሴን፣ ቅኔን፣ ዜማን፣ ብሉይን፣ ሃዲስን፣ የእንጨት አዋጅን (የመድኃኒት እጽዋትን)፣ የሃረግ ስዕልን፣የኢትዮጵን ታሪክ፣ አቡሻህርን (ባህረሃሳብን) እና ሌሎችንም በአድባራት እና ገዳማት የሚሰጡ የኢትዮጵያ ትምህርቶችን ተምረዋል። በለተይ በቅኔ፣ በግስ ርባታ እናሰዋሰው ችሎታቸው በመምህራኖቻቸው እና የትምሀርት ባልንጀሮቻቸው ስማቸው የተጠራ ነበር። በዚህም ምክንያት በጎጃም በይስማ ደጀን በመሪጌታ መንክርዘንድ ቅኔ አስነጋሪ ነበሩ።

ተማሪ ሳሉ እና ትምህርታቸውንም ካጠናቀቁ በኋላ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተዘዋወሩ አያሌ ገዳማትን እና አድባራትን እየጎበኙ በውስጣቸው የአሉትን ምስጢራዊናጥንታዊ መጻሕፍቶቻችንን ለመመርመር እድል አግኝተዋል።

የ19 ዓመት ልጅ ኹነው ወደ ኑብያ (ሱዳን) ተጉዘው በነበረበት ወቅት በአንድ በፈራረሰ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቤተክተርስቲያን ቅጥር ግቢ በተቀበረ የድንጋይ ሳጥንውስጥ፣ ምናልባት ኢትዮጵያ ውስጥ የሌሉ የኢትዮጵያን ታሪክ ጨምሮ ስለተለያዩ ጉዳዮች የሚዘረዝሩ በግዕዝ የተጻፉ የብራና መጻሕፍትና ጥቅሎች አግኝተዋል።እነዚህን መጻሕፍት ያገኙት የዛሬ 50 ዓመት አካባቢ ነበር። መጻሕፈቱ በግዕዝ የተደረሱ ነበሩ። በእነዚህ መጻሕፍት ላይ ተመርኩዘው ይዘታቸውን እያሳጠሩ ከ24ያላነሱ መጻሕፍትን አሳትመው፣ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን በእውቀትና በጥበብ አንጸዋል።

መሪራስ አማን በላይ መጽሐፍ ከማንበብና ከመጻፍ በላይ ሌላ ሕይወት አልነበራቸውም። ሲጽፉም እጅግ ፈጣን እንደነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ወገኖችለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ ዝግጅት ክፍል ገልጠዋል። በራሳቸው የተመዘገቡት የመጻሕፍቱም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው።

  1. ምዕራፈ ሕያዋን ቃለ ሕይወት ዘወንጌላውያን የምሳሌው ምስጢር በሐተታና በትንተና
  2. የጥንትዋ ኢትዮጵያ ትንሳዔ ታሪክ
  3. የሱባ ቋንቋ መዝገበ-ቃላት
  4. መጽሐፈ ብሩክ (ብሩክ ዣንሽዋ)
  5. መጽሐፈ ክቡር
  6. መጽሐፈ ሱባኤ ዘበአማን ካልእ
  7. መጽሐፈ አብርሂት
  8. መክሰተ ምስጢር
  9. መጽሐፈ እንቆአእባን
  10. መጽሐፈ ሠረገላ ታቦር
  11. መርሐ ጽድቅ ወአሚን ወመርሐ ግብር
  12. መጽሐፈ ፈውስ
  13. መጽሐፈ አድህኖት
  14. ብርሃነ ሕይወት ዘበአማን

 

  1. መጽሀሠይፈ ኃይማኖት ተዋህዶ
  2. ሕይወት እንደገና በሦስት ዐለሞች
  3. በአንድ ሰውነት የሦስት አካላት ምስጢር
  4. መጽሐፈ ኤልያስ ነቢየ እግዚአብሔር
  5. የእውነትን ሕይወት ውደዱ
  6. አፍሪ-ካሁን
  7. ጥበብ ከእውቀት ትምህርት ከልጅነት
  8. የልቤ ወዳጅ የሰው ዘር ልጅ
  9. ጸሎት አሚን ዘበአማን ወጸሎተ ተዋህዶ
  10. ምክር ከእኔ ስማ አንተ ወገኔ

መሪራስ አማን በላይ፣ በሀገር ፍቅር የሚነዱ፣ ለኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ቀናኢ፣ ለኢትዮጵያ እውነተኛ ታሪክ መገለጥና መዛመት የሚተጉ እና በፍቅረ ንዋይያልተነደፉ ትልቅ ጠቢብ ነበሩ። ጥበብን ለአገራቸው ሕዝብ ለማቅሰም ወደኋላ አይሉም ነበር። ለአገራቸው እስከዛሬ ካበረከቱት በላይ ገና ብዙ አስተዋጽኦ ለማድረግቢያቅዱም የማይቀረው ሞት ቀደማቸው። ይህም በመሆኑ፣ ራሱ የእውቀት ዩኒቨርሲቲ የሆነ አንድ ትልቅ ሰው ኢትዮጵያ አጥታለች። 3

 

መሪራስ አማን በላይ የስድስት ልጆች አባት ነበሩ። በልጆቻቸው ውስጥ፣ በብርቅዬ መጻሕፍቶቸው እና በሚወዱአቸው ኢትዮጵያውያን ልቦች ውስጥ ይኖራሉ። እግዚአብሔር ነፍሳቸውንበገነት ያኑራት ዘንድ የዝግጅት ክፍላችን ይመኛል። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመድ ወዳጆቻቸው እና ለመላው አፍቃሪዎቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

 

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live