Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

“ሀገር በድርድር ነው የሚገነባው” የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አቤል ዋቤላ – የሚሊዮኖች ድምጽ

$
0
0


ሶስት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን ነገረ ኢትዮጵያ አዘጋጅ ጦማሪ፣  በተቃዋሚዎችና በገዢው ፓርቲ መካከል ስለሚደረገው ድርድር ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አራቱ ጦማሪያን ድርድሩን በገዢው ፓርቲ ላይ ያላቸውን ስጋት ገለጸው በመርህ ደረጃ ግን ድርድሩ ጥሩ ነገር እንደሆነ ነው የገለጹት።

” የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና ትንሽ መላወሻ ቦታ የሚያመጣ ከሆነ፣ ድርድሩን እንደ መልካም ውጤት አድርጌ ነው የምወስደው” ሲል ጦማሪ አጥናፍ ብርሃኔ፣  አቤል ዋቤል በበኩሉ “ሀገር በድርድር ነው የሚገነባው” ሲል ድርድሩን  በአዎንታዊነት ይገልጸዋል። ጦማሪ በላይ ማናዬ በበኩሉ “የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከልብ መነጋገር፣ መደራደር በየትኛውም ሁኔታ የሚደገፍ ነው” ሲል  አስተያየቱን ይሰጣል። ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ በድርድሩ መልካም ዉጤት ይመጣል ብሎ ባይጠበቅም፣ “መንግስት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊያደርግባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ አጠንክረው ቢደራደሩ ነው መልካም የሚሆነው” ሲልም ድርድሩ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ካተኮረ ጥሩ ሊሆን እንደሚችል ነው የገለጸው።

አዘጋጅ ና ጦማሪ በበአዲስ አድማስ ጋዜጣ #ጦማሪያን ሃባቸውን እንዲህ ገልጸዋል ….!

———
“የተቃዋሚዎችን የመደራደር አቅም እጠራጠራለሁ”

#አጥናፈ_ብርሃኔ
የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና ትንሽ መላወሻ ቦታ የሚያመጣ ከሆነ፣ ድርድሩን እንደ መልካም ውጤት አድርጌ ነው የምወስደው፡፡ አሁን የሚደራደሩት ፓርቲዎች ይሄን ለማድረግ ከቻሉ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ኢህአዴግስ እውነት የሚያምንበትን ነው እያደረገ ያለው? በሚለው ላይ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ከዚህ ቀደም የተደረጉ ድርድሮች አሉ፡፡ የምርጫ ስነ ምግባርን በተመለከተ ድርድር ተደርጓል፡፡ ግን ምን ውጤት አመጣ? ያ ድርድር ለማን ነው የጠቀመው? ከዚያ ድርድር በኋላ በምርጫ ምን ውጤት መጣ? ይሄ መመርመር አለበት፡፡ ይህ የምርጫ ስነ ምግባር ድርድር ላልተደራደሩ ፓርቲዎች ማነቆ ሆኖ ነበር። ብዙ ተጎድተውበታል። ችግሮችን ሲፈጥርባቸው ነበር፡፡ አሁን ላይም ተቃዋሚዎቹ የመደራደር አቅማቸውን እጠራጠራለሁ፡፡ ከዚያ ውጪ ገዥው ፓርቲ እስካሁን ምንም አይነት መለሳለስ እያሳየ አለመሆኑ ሌላው ተግዳሮት ነው። የአድርባይነት ስሜት የህዝብን አመኔታ የሸረሸረ በመሆኑ የገዥው ፓርቲ መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ነው የምሰጋው፡፡ አቅም ኖሯቸው መደራደር ቢችሉ እንዲደራደሩባቸው ከሚያስፈልጉ ጉዳዮች ዋናው፡- ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ ጉዳይ፣ የፖለቲካ መጫወቻ ሜዳው መጥበብ፣ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ዶ/ር መረራን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ የመድረክ አመራሮች ካሉ፣ እነሱ መፈታት በሚችሉበት ጉዳይ ላይ መደራደር አለባቸው፡፡ በግሌ ውጤት ያመጣል ብዬ ባልጠብቅም ውጤቱን ከሂደቱ መጠበቅ አለብን፡፡ ( Atnaf Brhane )
—————————————-
“ሀገር በድርድር ነው የሚገነባው”

#አቤል_ዋበላ
እንደ ሀገር ባለፉት ሁለት ስርአቶች የተፈፀሙ ስር ነቀል ለውጦች ብዙ ዋጋ አስከፍለውናል፡፡ ስር ነቀል ሲሆን ብዙ ነገር ወደ ኋላ ይመለሳል፡፡ አሁንም ቢሆን ስር ነቀል ለውጥ የሚታለም ከሆነ፣ለህዝቡ የተሻለ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም፡፡ ያለውን ስርአት ለማስተካከል ንግግሩ መጀመሩ በራሱ ጥሩ ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ ድርድር ሲባል የሚታወቀው በተመጣጣኝ ኃይሎች መካከል የሚደረግ ነገር ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ እውነታ፣ተቃዋሚው በመንግስት በደረሰበት ተደጋጋሚ ጫና በጣም ተዳክሞ ነው የሚገኘው፡፡ ድርድሩ የምር ችግር ፈቺ እንዲሆን ከተፈለገ፣ በተቃዋሚው ወገን ያለውን የኃይል መሳሳት የሚቀንስ መሆን አለበት፡፡ተቃዋሚው እንደፈለገ ህዝቡን በዙሪያው እንዲያሰባስብ ክፍት መሆን አለበት፡፡ መሪዎቻቸው የታሰሩባቸው ፓርቲዎች አሉ፡፡ እነዚህ መሪዎቻቸው እንዲለቀቁላቸው ያስፈልጋል፡፡ ይህ ከሆነ ተቃዋሚዎችም በህዝብ ዘንድ ያላቸው አመኔታ ስለሚጨምር ድርድሩ አቅምና ውጤት እንዲሁም ተአማኒነት ይኖረዋል፡፡ ድርድራቸውን በሚዲያዎች አጠቃቀም፣በፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ላይ ቢያደርጉ የበለጠ ውጤት ማምጣት ይቻላል፡፡
ኢህአዴግ ለፖለቲካ ትርፍ ሲል ብዙ ጥፋቶች ሰርቷል፡፡ አሁን ግን ስልጣንን የማዳን ሳይሆን ሀገርን የማዳን ስራ ነው መስራት ያለበት፡፡ ይህ ድርድር የዚህ አይነት ውጤት ይዞ መምጣት አለበት፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም እንደ ፊጋ በሬ ኢህአዴግን ሳያስደነግጡት፣ በአግባቡ በኃላፊነት ስሜት ሊደራደሩ ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ ኢህአዴግም ይሄን እድል ማባከን የለበትም፡፡ ሀገር በድርድር ነው የሚገነባው፡፡ ( Abel Wabella )
—————————————-
‹‹ድርድሩ በቅንነትና በቁርጠኝነት መካሄድ አለበት››

#በላይ_ማናዬ (ጦማሪና ጋዜጠኛ)

ድርድሩ ከልብ የሚካሄድ ከሆነ መልካም ነው። በተለያየ አጋጣሚ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ሆኑ ሌሎች በሃገራቸው ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ ሰዎች ሲጠይቁት የነበረው ይሄንኑ የድርድና የውይይት መንገድ ነው፡፡ የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከልብ መነጋገር፣ መደራደር በየትኛውም ሁኔታ የሚደገፍ ነው፡፡ እኔ በግልም በተደጋጋሚ በፅሁፎቼ ስጠይቅ የነበረው መነጋገር ወሳኝ እንደሆነ ነበር። ይሄ ድርድርና ውይይት ግን ቅንነት በተሞላበት መንገድ፣ በደንብ ችግሮችን እያነሱ በጥንቃቄ መካሄድ አለበት። እንዲሁ ለይስሙላ የአንድ ሰሞን ጫጫታ ብቻ ሆኖ እንዳያልፍ በአንክሮ መከታተል ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ድርድር ላይ በተቃዋሚዎች ቢነሳ ብዬ የማስበው፣ በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ለእስር ተዳርገውብናል ያሏቸው ሰዎች እንዲለቀቁ፣ የፓርቲ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች ታስረዋል፤ እነዚህ ተፈተው የድርድሩ አካል መሆን አለባቸው። በትክክል የድርድሩ አካል መሆን ያለባቸው የታሠሩ የፖለቲካ አመራሮች አሉ፤ እነሱ እንዲሳተፉ መጠየቅ አለባቸው፡፡ ሌላው ከህገ መንግስቱ ተፃራሪ ናቸው እየተባሉ በህግ ባለሙያዎች አስተያየት ይሰጥባቸው የነበሩ ህጎች ላይ ጠለቅ ያለ ድርድር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አንዳንዶቹ በህግ ባለሙያዎች ተጠንተው ቢሰረዙ ምኞቴ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ጋር በሚደረገው ድርድር ተቃዋሚዎች የህዝቡን ሃሳብና ስሜት በማንፀባረቅ ከልባቸው ሊሰሩ ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ መንግስት ቁርጠኝነቱን እስከ መጨረሻው የሚቀጥል ከሆነ ጥሩ ነው፡፡ ግን በተደጋጋሚ ካየነው ልምድ ስንነሳ፣ ቁርጠኝነቱ እስከ ምን ድረስ ነው በሚለው ላይ ጥርጣሬ ያድርብኛል። ግን ካለመነጋገር መነጋገሩ የተሻለ በመሆኑ ጠንክሮ መደራደሩ የተቃዋሚዎች ሚና ነው ብዬ አምናለሁ። በሌላ በኩል በድርድሩ የተገለሉ የፖለቲካ ሃይሎች እንዳይኖሩ ቢደረግና ሁሉንም አካታች ቢሆን መልካም ውጤት ያመጣል፡፡ የህዝቡ ድምፅ በሙሉ እንዲሠማ ከተፈለገ፣ አሁን ካሉት ፓርቲዎች በተጨማሪ ሌሎች ያገባናል የሚሉም መካተት አለባቸው፡፡ በዚህ መንገድ የሚካሄድ ከሆነ፣ ድርድሩና ውይይቱ ውጤት ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ አለኝ፡፡( Belay Manaye )
——————————
‹‹በድርድሩ ሁሉም እኩል መሆን አለባቸው››

#ናትናኤል_ፈለቀ
በአንድ አካል መልካም ፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ፣ ሌሎች ደግሞ ተለማማጭ ሆነው የሚካሄድ ድርድር ትክክለኛ ውጤት አያስገኝም ። ድርድር ከተባለ ሁሉም በእኩልነት መጥተው፣ ለሁሉም ምቹ የሆነ ውጤት እንዲኖረው ነው የሚፈለገው ፡፡ ነገር ግን አንዱ የፈለገውን ማድረግ የሚችል፤ ሌሎቹ ደግሞ አሉ ለመባል ያህል የሚገቡበት ድርድር የአንደኛውን ወገን ብቻ ፍላጎት ይዞ እንደሚጠናቀቅ መተንበይ ቀላል ነው። እኔ ለምሳሌ “ከዚህ ድርድር መልካም ውጤት ትጠብቃለህ ወይ?” ብባል፣እንድጠብቅ የሚያደርገኝ ነገር ስላላየሁ አልጠብቅም፡፡ ከዚህ በፊትም እንዲህ ያለው ነገር በተለያዩ ስሞችና ቅርፆች ተሞክሯል፤ ግን ምንም የተለየ ነገር አላመጣም፡፡ ይሄም ያመጣል ብዬ አልጠብቅም፡፡
በድርድሩ ለምሳሌ “ህገ መንግስቱ ይከበር ” የሚባል ከሆነ ምንም አዲስ ነገር የለውም፡፡ ዋናው ተግባር ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተደራድረው ቢለያዩ፣ አንደኛው ወገን ስልጣን ሁሉ በእጁ ያለ በመሆኑ ስምምነቱን እንደፈለገ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ግን ድርድሩ የታሠሩ ፖለቲከኞች ይፈቱ፣ ሚዲያው ነፃ ይሁን፣ የፖለቲካ ስልጣን እንጋራ ከሆነ ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ፓርቲዎቹ የምርጫ ስርአቱ ላይ ብቻ ተደራድረው ሊወጡም ይችላሉ፡፡ ይሄ ደግሞ ያን ያህል ውጤት የለውም፡፡ በየትኛውም ሥርዓት ውስጥ በሃቀኝነትና በቁርጠኝነት ከተሰራ ለውጥ ይመጣል፡፡ ስለዚህ መንግስት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊያደርግባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ አጠንክረው ቢደራደሩ ነው መልካም የሚሆነው።ኢትዮጵያ ውስጥ በፖለቲካ መሳተፍ አስፈሪ በሆነበት ሰዓት የተፈጠሩ ፓርቲዎች በመሆናቸው፣ይብዛም ይነስም በዚህ ድፍረት ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችን ልናበረታታ ይገባል፡፡ ሌላ ወካይ እስከሌለ ድረስ ህዝቡን ወክለው መደራደር ይችላሉ የሚል እምነትም አለኝ፡፡


በዓለማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመሰብሰብ የተላከው የብአዴን ልዑክ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው

$
0
0

ሙሉቀን ተስፋው

ተማሪዎችን ለማሰመን የተላከው የብአዴን ቡድን በዓለማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ገጥሞት ያለ ምንም ውጤት ተመልሷል። ተማሪዎቹ ያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ አልተሰጣቸውም። ሰሞኑን የኢሕአዴግ ተወካዮች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በዩንቨርሲቲው የተሃድሶ ግብዣ በሚል ሲጨፍሩ ሰንብተው መመለሳቸውንም ተማሪዎች አስታውቀዋል። በዩንቨርሲቲው የዐማራ ተማሪዎችን ወክሎ የላከልን መረጃ እንዳለ እንደሚከተለው ይቀርባል።

ወያኔዉ ብአደን ዛሬ በዓለማያ ዩኒቨርሲቲ ባካሀደዉ የታደሶ ስብሰባ በጀግኖቹ የአማራ ተሩሪዎች ቀንዱን ተመታ። ነገሩ እንድህ ነው ማለትም ዛሬ ጠዋት 2:30 አፍረንቀሎ አዳራሽ ተሰባስቡ ተልባን። ሁላችንም የአማራ ተማሪዎች ተሰበሰብን። ወያኔ ብአደን ተደሰተ፤ ደጋፌ አለኝ ማለት ነው አለና ደብተር እስክቶ ታደልን። ሰብሳቢው ተደሰቶ በወንበሩ ላይም ወደግራ ወደቀኝ እየተሽከረከረ ፈገግ ፈገግ ማለት ጀመረ። ተማሪዎቹ ቦታቦታቸውን መያዝ ጀመሩ፤ አይተዋቸው የማያውቋቸውን ተማሪዎች አንተ ከየት ነው የመጣሀው አንተስ መታወቂያ አሳይ ማለት ጀመሩ። በዚህን ጌዜ የተማሪዎቹ ፌት ተለዋወጠ። ምንድነው እናውቃቸዋለን የኛ ናቸው አሉ ከምሀል ተጠያቂው የጠራሁ አማራ ጎጃም የደንበጫ ልጅ ነኝ አለ። አሁን ተላላኪው ደንገጥ አለ። በቃ ወደ ርሳችን እንግባ ፀጥ በሉ አለና ከክልል የተላከ ያኔ በቆራርጠህ ግዛው መለሰ የተፃፈ ወረቀት የታደሶ መሰመር በሚል መነበብ ጀመረ። የተማሬዎች ፌት ወዳውኑ ነብር መሰለ። ወዳዉኑ ጥያቄ አለ አንበሳው ተማሪ። ቆይ እንጨርስ ሲል ዳር ስተዳር ቀፎው እንደተነካበት ንብ ህም ህም አለ መደረክ መሬው ደንገጥ በማለት ቀጥል እሽ ምንድን ነው አለ። የተማሬውን ስም ለጊዜው ልተው እድህ ሲልም ቀጠለ ታድሶ የምትሉት ለውጥ እንጅ እድገት ሲያመጣ አላየነውም እስኪ ቃል ቀይሩ እስከመቸ በሞተ ሰው ቃል እንገዛቸኋለን እዳለ ሁለተኛውን ጥያቄ ቀጠለ እና ባሁኑ ስአት ህዝባችን ሀሳቡን በነፃነት እየገለፀ አይደለም ብአደን ለትግራይ ወይስ ለአማራ ለማን ነው የቆመው በማለት ጨረሰ።
2ኛው ጥያቄ ተነሳ የወልቃይት ጉዳይ ከምን አደረሳችሁት ሸጣችሁት ወይሰ መተማስ ሽጣሽሁት ለዘመናት ተከብራ የኖረች ሀገር በናንተ ተደፈረች መጨረሻው ምንድን ነው መልስ እፈልጋለሁ አለ
3ኛዉ ጥያቄ ተነሳ እናንተ ውልቃይት መተማ ትላላችሁ በወሎ በኩል የተሸጠውሰ የአማራ መሬት አይደለም ምን ትላለህ አሉት መድረክ መሬው ከወሎ የመጣ ነበር እና ኩምሽሸ አለ ተማሬውም መልስ እፈልጋለሁ በማለት ጨረሠ
4ኛዉ ጠያቂ ደግሞ ወያኔ እኛን መዝረፍ ከጀመረች ቆይታለች ከጎንደር የተወሠደው ጀኒኒተርሰ ብአደን ምን ሲሰራ ነበር በቅርቡስ ከአማራ በጀት ተቀንሶ ወደ ትግራይ የተወሰደው 4.5 ቢሊየን ብር ሰው ስለለለን አይደል ለምንድን ተወሠደ መልስ በማለት ጨረሰ
5ኛ ጥያቄ ባማራ ክልል ኢንዱስትሬ የለም ኢንዱስትሬው ትግራይ ነው ችግሩ ምንድን ነዉ ሲል ጠየቀ ከጠለናም አማራ ማለት ባለታሬክ አገሩን አሰከባሬ ትልቅ ህዝብ ነው ነገር ግን ባሁኑ ሰአት እንደህዝብም አንደብሔርም አይታይ እንዳውም አላልቅ ብሏችሁ ነው እንጅ ገላችሁ ጨርሳችሁት ነበር እስካሁን ተበደል ልቀቁ በቃችሁ እሰከመቼ ነዉ አለ፦

ከስዐት በኋላ ቀጠለ ተመካከረ እና ጠዋት የነበረው በግማሽ ቀረ ይህንን የሰማ ቆራጥ ተማሬ ከሰዐት ያመጡትን ያምጡ አለና ገባ አዳድስ ፌት በዛባቸው ደነገጡ የጠዋቱ ሰው የለም ግራ ገባቸዉ አሁን የመጣችሁ ደብተር እና እስክርቢቶ ሌላቀን አሁን እንጀምር አለ ተማሬዎችም እኛም አንፈልግም በማለት ተጀመረ ወዳዉኑ ጠያቄ ቀጠለ
1ኛ አምና በተነሳው የዉልቃይት ማንነት ጥያቄ ጎንደር ላይ የተነሳው ተጋድሎ ህዝባችን አልቋል ችግሩ የመንግስት ነው ጥያቄውን ባግባቡ ቢመልስ ንሮ ይህ ባልተከሰተ ነበር አሁንም አፋጣኝ መልስ ይፈልጋል አለ
2ኛዉ ቀጠለ መንግስት በውጭ ያለውን ዲያስፖራ አሸባሬ ይላል አሸባሬ እራሱ ነው እነሱ ከሚያዉቁት እና ከአለም ህዝብ ጋር እያነፃፀሩ እኛ ጋ በደል እና ግፍ ሰለበዛ ድሞክራሴ ሰለለ ለአለም ህዝብ ለማሰማት ነው አለ
3ኛዉ ቀጠለ ህገመንግስታችን ላይ መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይገባም ይላል እናንተ ግን ሀይማኖት ውሰጥ ገብታችሁ የራሳችሁ ፓርቲ ደጋፌውን በሰልጣናችሁ ትሾማላችሁ ለምን ሌሎችም በርካታ የተቃውሞ ጥያቄውችን ተኮናንቦ ከመመለሱም በላይ ተማሬዎች በቆራጥነት በመታገል በሀሳብ ድል አደርገዋል
ድል ለአማራ ሕዝብ
ወንድሞቻችሀ ከዓለማያ ዩኒቨርሲቲ

የእማሆይ ነገር ! – ይድነቃቸው ከበደ

$
0
0

አንዲት መነኩሴ በታላቁ ኩዳዴ ጾም እንቁላል ያምራቸውና ፣ አንድ እንቁላል ይዘው ከገዳማቸው ወጣ ወዳ አለ ስፍራ ይሄዱሉ፡፡ የጋለ ድንጋይ ፈልገው እንቁላሉን ድንጋዩ ላይ ያፈርጡታል ።ብዙም ሳይቆይ፤ አንድ የገዳም አባት በዛ በኩል ለጉዳይ ብቅ ሲሉ፤ እማሆይ ድንጋይ ላይ እንቁላል ለመጥበስ ፀሀይን እና ድንጋይን ለማገናኘት ሲባክኑ ያገኙዋቸዋል፡፡ የገዳሙ አባት መነኩሴዎን ምነው እማሆይ ? ቢሏቸው “ሠይጣን አሳስቶኝ” ሲሉ። ሠይጣንም ቁጭ ብሎ ከእሟሆይ ሙያ እየተማረ ነበርና ብሽቅ ብሎት፤ “ የእውነት ይህን ዓይነት እንቁላል አጠባበስ ያለዛሬም አላዩሁት አለ” ይባላል፡፡

የማይገባንን ግን የምንፈልገውን ለማግኘት ደፋ ቀና ስንል፣ ለማይገባን ነገር መባከናችንን ታዝቦ ፤ እንዴትስ ይሆናል ? ብሎ ለሚጠይቀ የምንፈጥረው ሰበብ እና አላስፈላጊ ምክንያት ፤ መቼም ማለቂያ የለውም ። ምን ይሄ ብቻ የምንፈጥረው ሰበብ ወይም ምክንያት ፤ ሰበብ ወይም ምክንያት የምናደርገው ነገር ተሰምቶ ፣ ታይቶ የማይታወቅ ምን አልባትም ወደፊትም የማይኖር ጭምር ሊሆን ይችላል ። እማሆይ ሊበሉት ያሰብት እንቁላል ከምንም በላይ ደግሞ ያጠባበስ ዘዴያቸው ፤ እማሆይ ሰበብ ያደረጉት ሰበበኛው እራሱ አያውቀውም ፤ እንዳሁኹም ሰበበኛው ሰይጣን ቁጭ ብሎ ከእማሆይ ሙያ እየተማረ ነበር ። እሱም “ የእውነት ይህን ዓይነት እንቁላል አጠባበስ ያለዛሬም አላዩሁት አለ መባሉ ለዚህም አይደለ ። ሰኔ እና ሰኞ አይነት ሆነና ነገሩ ፣ ይህ ጽሁፍ እና የእማሆይ ነገር ! በኩዳዴ ጾም ገጠመ።


ከሰሞኑ የሚፃፈው ፣የሚወራው ለጉድ ነው። አንዱ ሌላውን ለመደገፈ እና ለመቃወም የሚወረወረው የነገር አንካሴ ፣የወርዋሪው ልክ-የለሽ ድፍረት ፍንትው አድርጎ የሚያስይ ነው። የራስ የሆነውን ነውርን ለሌላው ለመስጠት የምናመካኘው ሰበቡ ሲታይ ፣ እዚህ ላይ ፈጣሪ ጠብቀኝ የሚያስብል ነው ። ሌላውን መስደብ እና ማዋረድ፣ የተሳዳቢውን ጨዋነት የሚያረጋግጥ የሚመመስለን በዝተን መታየታችን አይጣል ነው። ይበልጥ ደግሞ ሰለ-ሚባለው ነገር ፣ ግራ ቀኙን መዝኖ የራስ የሆነ አቋም ለመያዝ ከመሞከር ይልቅ ፤ “ወሬ ሲንግሩህ ሃሳብ ጨምርበት” ይሉት አይነት ነገር ፣ ይሄን ሰሞን ወዲህ እና ወዲያ የሳይበር (የማህበራዊ ድረ-ገጽ) እና የመገናኛ ብዙሃን ሹኩቻው ለጉድ ነው።

ልብ ያልን እንደሆነ ፤ሰዎች ስለሌላው ጥሩ ነገር ሲነግሩን ፣ ደግመን ደጋግመን ማረጋገጫ እንፈልጋለ። ከዚያም የዛ ሰውን ጥሩነት ወይም ስኬት ቀስ ብለን ማንሻኮክ ሥራ ሆኖብን ምንዳ እንጠብቃለን ። ሆኖም ግን አንዱ ስለ ሌላው መጥፎነት ሲነግረን ምን አይነት ማረጋገጫ ሳያስፈልገን ፤ “ወሬ ሲነግሩህ ሃሳብ ጨምርበት” እንደሚባለው የራሳችንን ግምት ጨምረንበት ፍጽም ከእውነት የራቀውን የሐሰት ወሬ በመጮህ ለማሰማት እንሞክራለን ። ይህም አልበቃ ብሎን ለመቅበር ጉድጎድ እንምሳለን፣ በቆፈርነው ጉድጎዳ ማን ይቅደም ሳናውቅ። ይህ ሁሉ የአብዛኞቻችን ችግር ነው። ለዚህም የሚሻለው በጎ ልቦና ፈጣሪ እንዲሰጠን መጸለይ እና እራስንም ለበጎ ነገር ማትጋት ነው።

በጎ ልቦና ይታገሳል፣ በጎ ልቦና ይቅር ባይ ነው፣ በጎ ልቦና የተከለከለ እና የተፈቀደን ለይቶ ያመላክታል፣ በጎ ልቦና በእራስ ላይ እንዲሆን የማይፈለግ በሌላው ላይ እንዳይሆን ያስጠነቅቃል፣ በጎ ልቦና የወደቅውን ለማንሳት እንጂ የቆመውን ለመጣል አይባዝንም፣ በጎ ልቦና ለስህተት ሣይሆን ከስህተት ለመውጣት ምክንያት ይፈልጋል፣በጎ ልቦና ትላንት፣ዛሬ እና ነገን ያስባል፣ በጎ ልቦና ከፀብ እና ከሐሜት ይልቅ ፍቅርን ፣ሰላምን እና ተግሳጽን ያስቀድማል ፣ በጎ ልቦና የእማሆይ ነገር አስታውሶ ከሰበብ ይጠብቀናል። ምን ይሄ ብቻ ከዚህ በላይ የሆነውን ለማሰብና ለማድረግ የበጎ ልቦና አሰተዋአዖኦ ቀላል አይደለም ። እናም ፈጣሪ በጎ ልቦና ይስጠን፤ አሜን!!!

(ይድነቃቸው ከበደ)

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር፤ አሜን!!!

የማይፈራና የማይሸማቀቅ ታላቅ ሕዝብ – የሚሊዮኖች ድምጽ

$
0
0

ም/ጠ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጎንደር ሕዝቡን ሰብሰበው ማነጋገራቸው የሚታወቅ ነው። ጎልጉል በስብሰባው ከሕዝቡ ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል የተወሰኑትን ለአንባቢያኑ አቅርቧል።

ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል የሚከተሉትን አቅርበናል። አቶ ደመቀና አቶ ገዱ በርካታና በትህትና ሕዝቡን ለማነጋገር መዘጋጀታቸውን በአዎንታዊነት ሊወስድ የሚገባው ነገር ነው። አመራሮች በዚህ እመልኩ የሕዝቡን ስሜት መገንዘባቸው ምን አልባትም በዉስጥ ኢሓዴግ አመራሮች ስብሰባ ላይ ልፍስፍ ሳይሆን ጠንካራ ሆነው ሊወጡ የሚችሉበትን ሁኔታ ሊፈጥርላቸው ይችል ይሆናል። ህዝብ ያን ያህል አክብሯቸው በሰብሰባቸው ተገኝቶ ያለዉን ፍላጎት ገልጾላቸው ፣ እነርሱ ግን ሕዝብን ከማዳመጥና ሕዝብን ከማገለገል የነ አባይ ወልዱና የነ ስህተ ነጋ አሽከር መሆን ከፈለጉ፣ ከሕዝቡም ከሕወሃቶች ሳይሆን ሜዳ ላይ ተጥለው የሚቀሩ ነው የሚሆኑት። ሕወሃት በባዴን ላይ (አመራሮቹንም ሳይቀር) ጥርስ ነቅሷል። በጎንደር እንዳደረጉት ሕዝቡን ለማናገር መሞከራቸው ፣ ሕዝቡም የተሰማዉን እንዲናግቀር መፍቀዳቸው ፣ በራሱ ሕወሃቶችን የሚያናዳድ ነው። ሕወሃቶች ሕዝብ ሲዋረድም ሲሸበር እንጅ ህዝብ ሲከበር አይወዱምና።

የጎንደር ህዝብም ምን እንኳን የአጋዚ በትር በሚሰቀጠጥ ሁኔታ ቢያርፍበትም፣ ቀን ብሎ ከመሄድ የተገታበት ሁኔታ የለም።፡ ኮምንድ ፖስትና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጎንደርን አንገት አልስደፋም። የጎንደር ሕዝብ በድፍረትን በወኔ ነበር አስተያየቱን በስብሰባው ላይ ሲሰጥ የነበረ።

ከተሰጡ አስተያየቲች መካከል ጥቂቶቹ እንሆ፡

አንድ የከተማዋ ነዋሪ
“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳችሁት አላነሳችሁት ጎዳናዉ ላይ በጥይት የወደቁ ልጆቻችን ህይወት አይመልስም፤ እናንተም መግደላችሁን ላታቆሙ ለምን ታባብሉናላችሁ?” ያሉት የአገር ሽማግሌዉ ንግራቸዉን ሲጨርሱ “የደርግን መጨረሻ ማስታወስ ብልህነት ነዉ” ሲሉ ምክር አዘል ማስጠንቀቂያ ለግሰዋል፡፡

ታዋቂዉ የባህል ልብስ ነጋዴ ሐጅ ሐሰን አሊ፡
“የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ማዕከል የሆነዉ ቅዳሜ ገበያ ምክንያቱ ዛሬም ድረስ ባልተገለጸልን ሁኔታ 446 ሱቆች በእሳት ቃጠሎ ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል፡፡ በዚህ የተበሳጨ ነጋዴ ራሱን እንዳጠፋ እኔና የአካባቢዉ ሰዎች ምስክሮች ነን፤ ትዳር ፈርሷል፤ ልጆች ተበትነዋል፤ ጎንደር በቴሌቪዥን ዜና እንደሚነገርላት የተረጋጋች ከተማ አይደለችም፤ ማህበራዊ ቀዉሱ የከፋ ነዉ፤ ይሄን መላ ካላላችሁ ምኑ ላይ ነዉ መንግስትነታችሁ?”

የፊት አቦ አቡነ አረጋዊ ደብር አለቃ የሆኑት አለቃ መኮንን ወልዱ ፡
“አሁን በልዑል እግዚአብሔር ሥም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ ጎንደር በታሪኳ በደርቡሽ ወረራ ጊዜ አንድ ዘመን ብቻ ብርሃነ መስቀሉን በአደባባይ አላከበረችም፡፡ ከስንት እና ስንት ዘመናት በኋላ ዘንድሮ ጎንደር ላይ የመስቀል በዓል በአደባይ ሳይከበር ቀረ፡፡ እናስ እናንተን ከወራሪዉ ደርቡሽ ለይቶ ማየት ብንቸገር ትፈርዱብን ይሆን? የጥምቀት በዓልስ ቢሆን ከካህናቱ መስቀል በላይ ጠመንጃ አንጋቹ በዝቶብን ለክርስቶስ ከብር ዝቅ ብለን በዓለ ጥምቀቱን አከበርን፡፡ ሌላዉ ቢቀር አላፊ ነን ብላችሁ እንዴት ማሰብ ተሳናችሁ? ሁላችንም ስናልፍ “የምንቀበርባትን ቤተክርስቲያን እንዲህ ፈተና ማብዛት በጎ አይደለም ልጆቼ”

የብአዴን መካከለኛ አመራሮች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸዉን ጥያቄዎች ለከፍተኛ አመራሩ አቅርበዋል፡፡እነ ደመቀ ከሕዝቡ ፣ ከባዴን መካከለኛና ታችኛው አመራር ዉጭ ለመሆን ከሞከሩ ዘንዶ በአንገታቸው ላይ ጠመጠሙ ማለት ነው።

ፍረጃን የስህተት መሸፈኛ ያደረገው የተቃውሞ ጎራ (ምላሽ ለኢንጂነር ይልቃል) – ግሬስ አባተ

$
0
0

ኢ/ር ይልቃል ከSBS Amharic ጋር ያደረጉትን ቆይታ አደመጥኩት፤ በከዚህ ቀደም ፅሁፌ እንዳልኩት ‹በኢትዮጵያ የተቃውሞ ጎራ ፖለቲካ ውስጥ ለሚሰሩ ስህተቶች ሌሎችን ‹‹ወያኔ›› ማለት እራስን ከስህተት ነፃ የሚያድርግ ነው፡፡ ኢ/ር ይልቃል 22 ደቂቃዎችን በፈጀው ቆይታቸው ሌላው ሁሉ ቀርቶ በመሪነታቸው የነበራቸውን መድረኮች በመጠቀም ችግሮችን ለምን መፍታት እንዳልቻሉ እንኳ ትንፍሽ ሳይሉ ሌሎችን በባንዳነት መፈረጅ መርጠዋል፡፡ ይህ ብዙ የሚገርም አይደለም፡፡ የፓርቲው የስነስርአት ኮሚቴ እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አራት አባላትን የመጠየቅ አቅም መፍጠሩ በአፍራሽነት ነው ያስፈረጀው፡፡


ይህን አሮጌ የፍረጃ ፖለቲካ የሙጥኝ ብለው በዛው አንደበታቸው እንዲህ ይላሉ ‹‹ዋና ከምላቸው የሰማያዊ ፓርቲ አስተዋፅኦዎች ይህን ትውልድ ከ60ዎቹ ትውልድ ፖለቲካ አላቆ አዲስ እርሾ እንዲሆን አድርጓል›› ከዚህ በላይ ፌዝ የለም፡፡ ቁምነገሩ እኮ የተዋናዮቹ የእድሜ ለውጥ አይደለም፡፡ የአስተሳሰብና የተግባር ነው፡፡ ዛሬም ተቀናቃኝ የሆነውን አካል በጠላትነት እያዩ፣የሃሳብ ልዩነትን ከፍረጃ ተሻግረው ማስተናገድ እንኳ ሳይችሉ፣ተጠያቂነት ሲነሳ አሮጌውን ፍረጃ እየደገሙ ከ60ዎቹ ትውልድ ፖለቲካ ተላቀናል ይሉናል፡፡

ኢ/ሩ አሮጌውን ፍረጃቸውን ለማስረዳት አንድነት፣ቅንጅት፣ኦብኮ፣መኢአድ ላይ የሆነውን በድፍኑ እንደምሳሌ አቅርበዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ በሰማያዊና በመኢአድ ላይ የሆነው አንድ አይነት አይደለም፡፡ መቼም ሰርተፍኬቱን ለሰማያዊ ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ ጤና ጥበቃ ይስጥ ካልተባለ በስተቀር፡፡ ሰርተፍኬት ሰጪው አካል አንድ በመሆኑ የሰማያዊ ሁኔታ የሌሎች ተመሳሳይ እንደሆነ የፍረጃው ሞተሮችን ማሳመን ይቻል ይሆናል፡፡ ሂደቱን የተከታተለ ሰው ግን የ’ካፈርኩ አይመልሰኝ ፖለቲካ አስቀያሚ ምሳሌ መሆኑን አይስተውም፡፡ ገና ድርድሩ ሳይጀመር ቅድመ ውይይቱን አስመልክቶ በጥርጣሬ አይን የሚታይ እንደሆነ ስለሚያውቁ ብቻ ያን ለማጠንከር በተለይ የሰማያዊ እና መኢአድ እውቅና ከዛ ጋር እንደሚያያዝ ለማሳየት የሞከሩበት አገላለፅ በፍረጃ ተጠልሎ ለማለፍ የሚሞክሩበትን እርቀት ያሳያል፡፡

የሆነው ሆኖ የኔ ክርክር የግለሰቦች ጉዳይ አይደልም፡፡ ቁም ነገሬ በአመራር ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች በሚፈፅሙት ስህተት የሚፈጠሩትን ችግሮች እስከመቼ በፍረጃና በገዢዎች እያሳበብንና ስህተት የሰሩትን ነፃ እያደረግን እንቀጥላለን? ይህ ለተቃውሞ ጎራው ተዋናዮች የስህተት መደበቂያ ዋሻ ሆኖ አላገለገለም ወይ? እዚህ አገር በተለይ ፓርቲዎች ከመቋቋም ጀምሮ በገዢዎች ተፅእኖ እንደሚደርስባቸው እሙን ነው፡፡ ይህ ከሆነ ለዚህ መሻገሪያውን መንገድ ማዘጋጀት የእነሱ ተግባር አይደለም ወይ? ለዚህ ሀላፊነቱን መወሰድ የለባቸውም ወይ? ይህን ሳንመልስ አለባብሰን አሮጌውን ፖለቲካ መከተል የትም የማያደርስ ብቻም ሳይሆን አንድ እግር ወደፊት አንድ እግር ወደኋላ አይነት ነው፡፡

“በርበሬ አይሆንም ዕጣን ንግግር አይሆንም ሥልጣን” -መነበብ ያለበት የአዲስ አድማስ ርእስ አንቀጽ

$
0
0

አንዳንድ ጨዋታ የዕውነት ያህል አሳማኝ ነው፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ ላይ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ይነሳል፡፡ በኃይል ጭቅጭቁን ያካረሩት አራት አገሮች ናቸው፡-
1ኛ/ እንግሊዝ
2ኛ/ ፈረንሣይ
3ኛ/ እሥራኤል
4ኛ/ ሩማኒያ
እንዲያ በኃይል ያጨቃጨቃቸው አጀንዳ፤ “አዳምና ሔዋን የየት አገር ሰዎች ናቸው?” የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
በመጀመሪያ ሙግቷን ያቀረበችው እንግሊዝ ናት፡፡ እንዲህ ነው ያለችው፤ በተወካይዋ አማካኝነት፤
“አዳምና ሔዋን ያለጥርጥር እንግሊዞች ናቸው፡፡ ለምን ቢባል፤ እንግሊዛዊ ሰው ብቻ ነው አንዲት ሴት ትፈጠር ዘንድ በጨዋነት የገዛ ጎድኑን አሳልፎ የሚሰጥ”
ይሄኔ የፈረንሳዩ ተወካይ ከመቀመጫው ተፈናጥሮ ተነሳና፤
“በጭራሽ እንደዛ አይሆንም! እስቲ የአዳምን ቁመናና ቁንጅና ተመልከቱ፡፡ ራቁቱን ሆኖ እንኳን እንዴት እንደሚያምር ልብ – በሉ፡፡ ይሄ ሊኖረው የሚችለው ፈረንሳዊ ብቻ ነው” አለ፡፡
ቀጥሎ የቀረበው ተሟጋች እሥራኤላዊው ተወካይ ነበር፡፡ እንዲህ አለ፡-
“በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በትክክል እንደተቀመጠው፤ፍጥረት የተፈጠረው በቅድስቲቱ ምድር ነው፡፡ ስለዚህም አዳምና ሔዋን የተመረጡት ህዝቦች ናቸው! ስለሆነም አይሁዳውያን ናቸው!”
ይሄኔ የሩማኒያው ተወካይ ጭንቅላቱን እየነቀነቀ ብድግ አለና፤
“የለም! በእኛ በሩማንያን ዕምነት አዳምና ሔዋን ሊሆኑ የሚችሉት ሩሲያዊ ነው!”
“እንዴት? አስረዳና?” ብለው ሁሉም ጮሁበት፡፡
የሩማንያው ተወካይም፤
“ምክንያቴን ላቅርብላችሁ፡፡ በዓለም ላይ ሩሲያዊ ብቻ ነው በደንብ ሳይበላና በደምብ ሳይለብስ ገነት ውስጥ ነው ያለሁት የሚል!” ሲል ገለፀ፡፡
ተጨበጨበለት!!
*   *   *
አገርን ከሌላ አገር ማስበለጥ፣ የራስን ፓርቲ ከሌላው ፓርቲ የበላይ ነው ለማለት መሞከርና እኔ እሻል እኔ እሻል መባባል፣ ጥንትም ነበረ፣ አሁንም ያለ እና ወደፊትም የሚኖር ነው፡፡ ያም ሆኖ ያላንዳች ምክናዊነት፣ አንዱ ሌላውን መብለጥ አይችልም፡፡ አመክንዮ ይፈልጋል፡፡
በሀገር ደረጃ ሲታይ ከፖለቲካ ጥንካሬ እስከ ኢኮኖሚ ጥንካሬ፣ ከዚያም የወታደራዊ አቅም፣ እንዲሁም ማህበራዊ መሰረትን ይጠይቃል፡፡ እነዚህን ለማሟላት ብርቱ ድካም፣ የረዥም ጊዜ ባለታሪክ መሆንንም ይጠይቃል፡፡
በሀገራችን ያየናቸው ለውጦች ከወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት፣ እስከ ተማሪ እንቅስቃሴ፣ ውለው አድረውም የተደራጁ ወታደራዊ ኃይሎች አመራር ሥር የወደቁ ነበሩ፡፡ በዚሁ ዙሪያ የተደራጁ ፓርቲዎችና ድርጅቶች ተወልደዋል፡፡ ወደ ትጥቅ ትግልም ያደጉ ታይተዋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ግን እርስ በርስ ከመቆራቆስና ከመጠላለፍ፣ አልፎ ተርፎም ከመጨራረስ በስተቀር ሁነኛ የፖለቲካ መድረክ ፈጥረው፣ ሁነኛ ክርክርና ሀቀኛ ሙግት ተሟግተው፣ እዚህ ስምምነት ላይ ደረሱ የሚባልላቸውና የሚያኮሩ አልተገኙም፡፡ መንግሥትና ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣አይጥና ድመት ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ነበሩ፡፡ ክፍተቱ ሰፊ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ስናይ የኖርነው፤ የቂም በቀል፣ የደባና የሤራ፣ ከእኔ በላይ ላሣር እና የደም መፈላለግ ፍጥጫ በመሆኑ የሰላማዊ ትግል ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ፣በሰለጠነ መልክ ተነጋግሮ ዳር መድረስ ያልተሞከረ ነው፡፡ አንድ ፀሐፊ እንዳለው፤ “የኢትዮጵያ ፖለቲከኛ ሁሉ በየኪሱ ትናንሽ ዘውድ ይዞ ነው የሚዞረው!”
ከተማሪ እንቅስቃሴ ጊዜ ጀምሮ እንደመሪ መፈክር ሲያገለግል የኖረው፤
‹‹unity is power››
‹‹አንድነት ኃይል ነው›› የሚል ነበር፡፡
“United, we stand
Separated, we fall!›› የሚልም ነበር፡፡ (‹‹ከተባበርን እንቆማለን፤ከተነጣጠልን እንወድቃለን!›› እንደ ማለት ነው፡፡) በአጭሩና በተለመደው የአማርኛ አባባል፤‹‹ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር›› ማለት ነው፡፡ ይሄ ዛሬም ይሠራል፤በአግባቡ የሚጠቀምበት ከተገኘ፡፡ ጥበብ ይጠይቃል፡፡ በሆይ ሆይታና በግርግር፤ በችኮላ የሚፈጠር አካሄድ መጨረሻው አያምርም፡፡ የፖለቲካ ድርድር የአንድ ወገን ብልጠት አይደለም፡፡ የሀገር ጉዳይ ነውና ሁሉም ወገን በልባዊነት ሽንጡን ጠበቅ ሊያደርግበት የሚገባ ነገር ነው፡፡ በተንኮል ሽረባም የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን፤
‹‹ነገር በሆድ ማመቅ
ለትውልድ መርዝ መጥመቅ›› የሚለን ለዚህ ነው!
ከሁሉም በላይ መቻቻል የሚፈተንበት፣ሆደ-ሰፊውና አስተዋዩ የሚለይበት ነው። የፖለቲካ ብልህነት ጠርቶ የሚወጣበት ነው፡፡ ዲሞክራሲ የተሸናፊዎች መብት መሆኑን በእርግጥ የምናጣራበት ሂደትም ነው፡፡ ገዢው ዘራፍ ሳይል፣ተገዢው በቂምና በቅሬታ ሳይወጣ ማየት እንሻለን፡፡ ሰላማዊ ትግል የሰላም አገር መለያ ነውና፣ከትንቅንቁ ባሻገር ግልፅ ውይይት እንጠብቃለን፡፡ ስለታሰሩ የተቃዋሚ አባላት ምን ሀሳብ እንደሚነሳ ለመስማት እንጓጓለን፡፡ ስለምርጫ ህግጋት ለውጥ ምን እንደሚወሳ ለማዳመጥ እንተጋለን፡፡ በመጨረሻ ግን አንደበተ ርቱዕነት ብቻውን የአሸናፊነት መገለጫ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ቀናነት፣ ቁጡነትን ማስወገድ፣ የቤት ሥራን በሚገባ ሰርቶ መምጣት፣ ወቅታዊ (timely) የሆነውን ጉዳይ፤ ጊዜ ከማይሽረው (timeless) ጉዳይ ለይቶ ማየት ወሳኝነት አላቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን፤
‹‹በርበሬ አይሆንም ዕጣን
ንግግር አይሆንም ሥልጣን››
የሚለውን አባባል አለመዘንጋት ነው! ይሄን ልብ እንዲሉም አደራ ጭምር እናስታውሳለን፡፡

በጎንደር ችግር አለ – ብአዴን ህዝብን ሲያናግር፣ ሕወሃት ይተኩሳል – የሚሊዮኖች ድምጽ

$
0
0
 
ጎንደር ከተማ ከፍተኛ ተኩስ እንዳለ እየተገለጸ ነው። ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው “ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ፣ ከምሽተ 4.30 ጀምሮ መኖሩን መረጃዎች እየመጡ ነው። ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ሲኖር መንገዶች ሁሉ ተዘግተዋል ተብሏል” ሲል ጦምሯል።
 
ከጥቂት ቀናት በፊት የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባላት የከተማዋን ህዝብ በአክብሮት ማነጋገራቸውና ሕዝቡ አስተያየቱን በድፍረትና በወኔ መስጠቱን በተመለከተ በሰፊው መዘገቡ ይታወቃል። ሆኖም ግን፣ የብአዴን አመራሮች ሕዝቡን ለመስማት ባደረጉት ጥረት ያልተደሰቱት፣ ኮምንድ ፖስት ከሚባለው ጀርባ ያሉ የሕወሃት የደህነትና የመከላከያ ሃላፊዎች ” እነ ገዱ የፈለጉትን ስብሰባ ጠርተው ቢያወሩም ከኛ ዉጭ የትም አትሄዱም። ሃይሉ ያለው እኛ ጋር ነው” በሚል የደካሞችና የእብሪተኖችን መለስክት ለማስተላለፍ ፣ ሆን ብለው የጀመሩት ጠብ ጫሪነት ሊሆን እንደሚችል ተንታኞች ይናገራሉ።
 
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታዉጆ፣ በርካታ ታጣቂዎች በመላክ አገዛዙ መረጋጋትን ለመፍጠር የሞከረ ቢሆንም፣ እንደ ጎንደር ከተማና ባህር ዳር፣ ካሉ ትላልቅ ከተሞች ዉጭ፣ በሌሎች ገጠራማ አካባቢዎች ከአገዛዙ ቁጥጥር ዉጭ እንደሆኑና በጎበዝ አለቃ የሚመሩ፣ ከሕዝቡ የተወጣጡ በርካታ ተዋጊዎች፣ የሚንቀሳቀሱባቸው እንደሆነ ለአካባቢው ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ። አገዛዙ አካባቢውን ማረጋጋት ባለመቻሉም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአማራው ክልል እንደገና ለሶስት ወራት ለማስተላለፍ እቅድ እንዳለውም ታውቄል።
 
መሳሪያ፣ ሃይል ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መፍትሄ እንዳላመጣና እንደማያመጣ የገለጹትአንድ የቀድሞ ዝነኛው የአንድነት ፓርቲ ክፍተኛ አመራር አባል ” ያ ሁሉ ወታደር ተሰማርቶ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታዉጆም፣ መረጋጋት ካልመጣ፣ ኢሕአዴግ ከሃይልና ከእልህ ፖለቲክ ያለፈ ተሻለ አማራጫን መቀበል አለበት ” ሲሉ አገዛዙ መሰረታዊ የአካሄድ ለዉጥ ካላመጣ የከፋ ችግር ዉስጥ እንደሚወድቅ ነው የተናገሩት። እኝህ የሰላማዊ ታጋይ ሲያክሉም አሁን ተጀመረ የተባለውን ድርድርን፣ ኢሕአዴግ ለሰላም፣ ለአገር ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለራሱ ሲል እንዲጠቀምበት፣ በሕዝብ ተቀባይነት ያለው፣ የተጨበጠ ዉጤት የሚያመጣ ድርድር እንዲያደርገው ጠይቀዋል።
 
“ፍርሃት የወለደው ታጋሽነታችን ለብዙ ሕገ-ወጥ ድርጊት ጋብዞናል” የሚለው መፈክር በጎንደር ሲታይ የነበረ መፈክር ነበር። ” መንግስት ለኔ ሳይሆን በኔ ላይ ነው የቆመው” የሚል እምንት በዉስጡ ካዘለ፣ አገዛዙ የሚያወጣውን ሕግ በሙሉ አልቀበለም የሚል የእምቢተኝኘት አቋም መያዙ አይቀረም። ተጀምሯልም።
 
በመሆኑም አገዛዙ እንደከዚህ በፊቱ ሊቀጠል እንደማይችል ተገንዝቦ፣ የይስሙላን እና የማስመሰንልል የዉሸት “ተሃድሶዉን” ወደ ጎን ጥሎ፣ አንድ የጎንደር ነዋሪ እንዳሉት በድሪቶ ላይ ድሪቶ መደረቡን አቁሞ፣ ለትክክለኛና እዉነተኛ፡ለዉጥ ራሱን እንዲያዘጋጅ እንጠይቃለን።
 
ከተቃዋሚዎች ጋር የተጀመረዉ ድርድር እንደ አገር ከታሰርነበት ማነቋችን የምንወጣበት፣ የሰደዱ የሚመለሱትብት፣ ነፍጥ ያነሱ ነፍጥ የሚደፉበት፣ የታሰሩ የሚፈቱበት፣ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ የተበተኑ የሚሰባሰቡበት፣ በዘር አድሎ ሳይኖር ሁሉም እንደ ኢትዮጵያዊ በዜግነቱ የሚከበርባትና ሁሉ በሁሉም የአገሪቷ ግዛቶች በሰላም የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ትመጣ ዘንድ በሩን የሚከፍት ድርድር እንዲሆን ጸሎታችን ነው።

ዶ/ር መረራ የኦሮሚያን ብጥብጥ በማባባስና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ ክስ ተመሠረተባቸው – ታምሩ ጽጌ

$
0
0
  • በክሱ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ ጀዋር መሐመድ ተካተዋል

የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ ባደረገላቸው ጥሪ ቤልጂየም ብራሰልስ ደርሰው ሲመለሱ፣  ከመስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመጣስ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ብጥብጥና ሁከት ሲያባብሱ እንደነበር የሚገልጽ ክስ ሐሙስ የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ተመሠረተባቸው፡፡

የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀናለ)፣ 38(1)ን፣ 27(1)ን እና አንቀጽ 238 (1 እና 2)ን ተላልፈዋል ተብለው የመጀመሪያ ክስ የተመሠረተባቸው ዶ/ር መረራ፣ የግንቦት ሰባት አርበኞች ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ ጀዋር መሐመድ ናቸው፡፡ በፌዴራልና በክልል ሕገ መንግሥት የተቋቋመን ሥርዓት በሕገወጥ መንገድ ለማፍረስ መንቀሳቀሳቸውን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመሠረተው ክስ ያስረዳል፡፡ የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የአይዲዮሎጂ ዓላማን ለማራመድ፣ በመንግሥት ላይ ጫና ለመፍጠርና ኅብረተሰቡን ለማስፈራራት፣ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ የሁከትና የብጥብጥ ጥሪ በማስተላለፍ በአንዳንድ የአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ኅብረተሰቡ ወደ ሁከትና ብጥብጥ እንዲገባ ማድረጋቸውን፣ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው ክስ ገልጿል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንዳብራራው ዶ/ር መረራ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራርነትን እንደ ሽፋን ተጠቅመው፣ የአዲስ አበባ ከተማና የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን ተቃውሞን እንደ መነሻ በማድረግ ሁከትና ብጥብጥ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንዲቀጥል አድርገዋል፡፡

በ2006 ዓ.ም. ለኦፌኮ አባላት የሥራ ክፍፍል በማድረግ በመንግሥትና በሕዝብ ተቋማት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ላይ የንብረት ውድመት እንዲደርስ ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ በኢንቨስትመንት ላይ በተሰማሩ ባለሀብቶች ንብረቶች ላይም ውድመት መድረሱንም አክሏል፡፡ በሰውም ላይ ከባድ የአካል መጉደልና ሞት መከሰቱንም ጠቁሟል፡፡

ዶ/ር መረራ በ2008 ዓ.ም. በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች በተለይም በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ አካባቢ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ማለትም የአምቦ-ካራ የመንገድ ግንባታን በመቆራረጥ፣ ካምፕ በማቃጠል፣ በተሽከርካሪዎችና በማሽነሪዎች ላይ የ2,957,661 ብር ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ በቡራዩ ከተማም በ42,598,204 ብር ንብረቶች ላይ ጉዳትና ውድመት ማድረሳቸውንም አክሏል፡፡ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ፣ አመያ፣ ጎሮ፣ ቶሌ፣ ኢሉ፣ ቀርሳ፣ ወንጪ ወረዳዎችና ቀበሌ መስተዳድር የግለሰቦች መኖሪያ ቤቶችንና በኢንቨስትመንት የተሰማሩ ኢንቨስተሮችን የተለያዩ ንብረቶች ጉዳት በማድረስና በማውደም የ17,352,482 ብር ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት መሆናቸውንም ክሱ ያብራራል፡፡

ሐምሌ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ዶ/ር መረራ ባስተላለፉት የሁከት ጥሪ፣ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. በመላ ኦሮሚያ ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማካሄድ መታሰቡን በመግለጽና የሁከቱ ተካፋዮች እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

ዶ/ር መረራ ለዚሁ መገናኛ ብዙኃን መስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ኢሬቻ በዓል ላይ የተከሰተውን አደጋ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ የመንግሥት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ሕዝብ ላይ በወሰዱት ግድያ 678 ሰዎችን እንደተገደሉ በመግለጽ ባስተላለፉት ጥሪ፣ በክልሉ አንዳንድ ከተሞች ሁከትና ብጥብጡ እንዲቀጥል ማድረጋቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ በተነሳውም ብጥብጥና ሁከት የሰላማዊ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን፣ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ በመንግሥትና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ፣ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ላይ በተሰማሩ ባለሀብቶች ንብረቶች ላይ ጥቃት እንዲደርስና እንዲወድሙ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በኢሉአባቦራ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በምሥራቅ ሸዋ፣ በባሌ፣ በሰበታ ከተማ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ በአርሲ፣ በምዕራብ አርሲ ዞን በመንግሥት ንብረት ላይ የ215,468,309 ብር ውድመት እንዲደርስ ማድረጋቸውንም ገልጿል፡፡ ዶ/ር መረራ መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ንብረት ላይ የ1,168,293,498 ብር ንብረት እንዲወድም ምክንያት መሆናቸውንም በክሱ አብራርቷል፡፡

ሌላው ዶ/ር መረራ በቁጥጥር ሥር ውለው የታሰሩበት ምክንያት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመጣስ ተብለው ነው፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተፈረጀው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በብራሰልስ በመገናኘታቸው ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው መመርያ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር መገናኘት የተከለከለ መሆኑ ተገልጾ እያለ፣ ዶ/ር መረራ መመርያውን ጥሰው በመገናኘታቸውና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 01/2009 አንቀጽ 12(1)ን በመተላለፋቸው መሆኑን ክሱ ያብራራል፡፡

ዶ/ር መረራ ኅዳር 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ጋር በብራሰልስ የኦኤምኤን ሠራተኞችና የኦነግ አባላትና ደጋፊዎች ባዘጋጁት የስብሰባ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ስለነበረው ሁከትና ብጥብጥ በመግለጻቸው፣ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር የተያያዙ ግዴታዎችን የመተላለፍ ወንጀል በመፈጸም ክስ ዓቃቤ ሕግ አቅርቦባቸዋል፡፡

ዶ/ር መረራ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 486(ለ)ን በመተላለፍ በ2006 ዓ.ም የኢትዮጵያና ናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድኖች በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ የአልሸባብ አባላት የአጥፍቶ ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ባለመቻላቸውና የታጠቁት ፈንጂ ፈንድቶ መሞታቸው እየታወቀ፣ እሳቸው ግን ‹‹አሸባሪዎቹ አፈነዱ የተባለው የውሸትና የመንግሥት ድራማ ነው›› በማለት ሕዝቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዳይኖረው አድርገዋል ሲል ዓቃቤ ሕግ የሐሰት ወሬዎችን የማውራት ወንጀል ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡

ከዶ/ር መረራ ጋር በአንደኛ ክስ ተካተው ክስ የተመሠረተባቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ ጀዋር መሐመድ ናቸው፡፡ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በህቡዕ አባላትን በመመልመል እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ፣ ሁከቱ እንዲቀጥል በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) በተለይ በ2009 ዓ.ም. የሁከት ጥሪ ማድረጋቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ አርሶ አደር ከእንግዲህ ግብርና የማዳበሪያ ዕዳ አይከፍልም፤›› በማለት አርሶ አደሩ በመንግሥት ላይ እንዲያምፅና ለፍትሕ ሥርዓቱ እንዳይገዛ የሁከት ጥሪ ማቅረባቸውንም አክሏል፡፡ እሳቸውም ሆኑ ድርጅቱ አርበኞች ግንቦት ሰባት እስከ መጨረሻው የደም ጠብታ ድረስ እንደሚታገሉ በመግለጽና በሰላማዊ መንገድ መታገል ሞኝነት መሆኑን በመስበክ፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሚገኘው ሕዝብ መሣሪያውን እየወለወለ ወደ በረሃ እንዲገባም በኢሳት ቴሌቪዥን ንግግር በማድረግ፣ ሁከቱና ረብሻው በመላ አገሪቱ እንዲስፋፋ ጥሪ ማቅረባቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሯል፡፡ ፕሮፌሰሩ በተለያዩ ጊዜያት በአገር ውስጥ በህቡዕ የሚንቀሳቀሱ ባሉበት ጥቃት እንዲያደርሱ በመንገር፣ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የሽብር ቡድን አባላትም ተመሳሳይ ተግባር እንዲፈጽሙ ትዕዛዝ መስጠታቸውንም ክሱ ያብራራል፡፡

አቶ ጀዋር መሐመድም የአዲስ አበባ ከተማና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላንን ለሁከት መቀስቀሻ ምክንያት በማድረግ፣ በአገር ውስጥ ለሚገኙ የኦነግ የሽብር ቡድን አባላት ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የነበረውን ብጥብጥና ሁከት በኦኤምኤን በማስተላለፍ ሁከትና ብጥብጡ እንዲቀጥል ጥሪ ሲያደርጉ እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል፡፡ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ነጋዴዎች ለሕዝቡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን እንዳይሸጡ፣ እንዳያቀርቡና እንዳይገዙ፣ የትራንስፖርት አቅርቦት እንዳይኖር በማለት የሁከት ጥሪ መግለጫዎችን ሲያስተላልፉ እንደነበር በክሱ ተብራርቷል፡፡ አቶ ጀዋር ከላይ በዶ/ር መረራ ክስ ላይ የተገለጹ የንብረት ውድመቶች (በገንዘብ የተገለጹት) እንዲደርሱ ምክንያት መሆናቸውንም ክሱ ይጠቁማል፡፡

በመሆኑም ሦስቱም ተከሳሾች በፈጸሙት በሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ ወንጀል መከሰሳቸውን፣ የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ዓቃቤ ሕግ የጠቀሰውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 238 (1 እና 2)ን ተላልፈው ፈጽመውታል የተባለው ወንጀል በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ከተረጋገጠ፣ ከሦስት ዓመታት እስከ ሞት ሊያስቀጣቸው እንደሚችል ሕጉ ይገልጻል፡፡

በክሱ ውስጥ በሁለተኛ ክስ ላይ የተካተቱት ድርጅቶች ደግሞ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እና ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) ናቸው፡፡ ድርጅቶቹ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1)ሀ እና ለ፣ 38፣ 34 (1)እና የሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 5 (1) ለን በመተላለፍ፣ ዶ/ር መረራ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑና አቶ ጀዋር ደግሞ ‹‹ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሁከትና ብጥብጥ እናስወግዳለን፤›› በማለት ያቀረቡትን ጥሪ በማስተላለፍ ድጋፍ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አብራርቷል፡፡ መገናኛ ብዙኃኑ በተለያዩ ጊዜያት ያስተላለፉትን ጥሪ ዓቃቤ ሕግ በዝርዝር በክሱ አካቶ አብራርቷል፡፡ በአጠቃላይ ድርጅቶቹ የኦነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ልሳን በመሆንና ሚዲያንና ሙያን ሽፋን በማድረግ፣ ሦስቱ ግለሰቦች የሚያስተላልፉትን የብጥብጥ ጥሪ በመቀበልና የሽብር ቡድን ድጋፍ በማድረግ በዋና ወንጀል ላይ ተካፋይ በመሆናቸው፣ የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ እንደተመሠረተባቸው ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

ክሱ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ለዶ/ር መረራ ጉዲና ክሱን በመስጠት ለማንበብና ተከሳሹ በጠበቃ ተወክለው እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከስድስት ዓመታት በፊት ክስ ተመሥርቶባቸው በሌሉበት በሞት እንዲቀጡ ፍርድ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡


የአለቃ ጸጋየ በርሄና የህላዊ ዮሴፍ ወጎች፤ ከሹመት እስከ ሽረት፤

$
0
0
  • የህወሓት-እስራኤል ቀጣይ የፖለቲካ ቁማር!

አሁን ባለዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ለህወሓት/ኢህአዴግ ቁልፍ የስጋት ምንጩ የዲያስፖራዉ የተቃዉሞ ጎራ ነዉ፡፡ የድህረ-ምርጫ 97 ዉርስ ዕዳ የሆነዉ የዲያስፖራዉ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እንደ ሀገር ቤቱ ሁሉ በዘዉግ ፖለቲካ የሚታመስ ቢሆንም በጋራ ጠላት (ህወሓት/ኢህአዴግ) መዉደቅ ላይ ያለ አንዳች የልዩነት መስመር ይስማማል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ ሀገር ቤት ያሉት የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከሚያሰሙት ጩኅት በላይ ከባህር ማዶ የሚሰማዉ ሹክሹክታ እንቅልፍ ይነሳዋል፡፡ የህዝብ ድምጽና የዲያስፖራዉ የተቃዉሞ ፖለቲካ መሳ ለመሳ መሄድ የቆላ ቁስል ሆኖበታል፡፡ እናም የዲፕሎማሲ ታርጋን እንደ ሴራ ፖለቲካና ድርጅታዊ ጠቀሜታነት አብዝቶ ለመጠቀም የጨዋታዉን ህግ ያሻሻለ ይመስላል፡፡

የዲያስፖራ ፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪነት በማይካድ ደረጃ አይሎ በመዉጣቱ ወትሮዉንም ጥንቃቄ ይደረግበት የነበረዉ የአምባሳደሮች ሹመት ቁልፍ ቁልፍ በሆኑ ሀገራት የህወኃት ሰዎች አለያም ለድርጅቱ ቀይ ምንጣፍ ሊጎትቱ ለሚችሉ የኢህአዲግ አባል ድርጅቶች ዉስጥ አባላት መሆን እንዳለባቸዉ የህወሓት ነባር ታጋዮች የማይሻር ህግ ነዉ፡፡

አሁን ባለዉ ተጨባጭ ሁኔታ ብረት አከል ሁለገብ ትግል (ገጠር-ከተማ የሚያዳርስ የተጠና የትግል ስልት) በሚሹ ኃይሎችና በወታደራዊ ዕምቃ ሥልጣናቸዉን ሊያጸኑ በወሰኑ መንግስታዊ ሽፍቶች መሀከል የሚዋልል ፍትጊያ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መገለጫ ሆኗል፡፡

የሰላማዊ ትግል ጀምበር ባዘቀዘቀባት ኢትዮጵያ፤ ከወራት በፊት ተራዛሚነት ባሳየ መልኩ ለተቀጣጠሉት ህዝባዊ አመጾች የሞራልና የሎጀስቲክ ድጋፎችን በተናጠልና በግብረ-ኃይል ደረጃ በማድረግ የዲያስፖራዉ ሚና ላቅ ያለ ነዉ፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ላለፉት ሃያ አምስት አመታት ያለ መታከት እንቅልፍ አጥቶ ይሰራበት የነበረዉ ጸረ-ኢትዮጵያ አጀንዳ በድካሙ ልክ አልሆንለት ብሏል፡፡ ይህን አዉዳሚ ጸረ-ኢትዮጵያ አጀንዳዉን በማክሸፍ ረገድ የዲያስፖራዉ ሚና ከነችግሩም ቢሆን በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ በተለይም በሀገር ቤት የሚታየዉን የሰብዓዊና የዴሞክራሲ መብቶችን ረገጣ ለምዕራቡ ዓለም በማስተጋባት፤ ዘዉግን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን በማስረጃ አስደግፎ በማጋለጥ፤ “ትግራይ እስክትለማ ኢትዮጵያ ትድማ!” የሚለዉን ህወሓታዊ “የዘዉግ ኢኮኖሚክስ” ገመና አደባባይ ላይ በማስጣትና መሰል ጉዳዮችን በማንሳት የዲያስፖራዉ የተቃዉሞ ጎራ ተጽዕኖ ከቃላት በላይ ነዉ፡፡

ላለፉት ሃያ አምስት አመታት ስንሰማዉ ከኖርነዉ እዉነታ አኳያ በዉጭ ሀገራት በአምባሳደርነት የሚሾሙን፣ የደህንነትና የፖለቲካ አታሼዎችን እና የኢምባሲ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ምደባ በጌታቸዉ አሰፋ የሚመራዉ የደህንነት ቢሮዉና ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የሚሰሩት መሆኑን ነዉ፡፡ ህወሓት ከአናሳ ዘዉግ የተገኘ የፖለቲካ ቡድን እንደመሆኑ መጠን የሰዉ ኃይል ዉስንነት አለበት፡፡ ህወሓት የራሱን ሰዎች በሁሉም ቦታ ለመመደብ ዲፕሎማሲያዊ አካሄዶችና የሰዉ ኃይል ዉስንነት ቢያግደዉም በዋናዋና ሀገራት ከፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አኳያ የራሱን ሰዎች ቢቻል በአምባሳደርነት ቦታ ካልሆነም በኢምባሲ ዋና ጸሃፊነት፤ የፖለቲካና የደህንነት አታሼ ቦታዎች ላይ ማስቀመጥ ለድርድር የማያቀርበዉ አቋሙ ነዉ፡፡

እንዲህ ያለዉን ተሞክሮዉን ይበልጥ ለመረዳት በሰሜን አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አዉስትራሊያ፣ በአዉሮፓ ዋና ዋና ሀገራት (እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ኖርዌ፣ ቱርክ) በኤዥያ (ህንድ፣ ጃፓን፣ቻይና፣ ደቡብ ኮርያ፣ ሲንጋፖር) በመካከለኛዉ ምስራቅ (የተባበሩት አረብ ኢሜሬት፣ ኳታር፣ሳዉዲአረቢያ፣ ኩዌት፣ እስራኤል) በአፍሪካ (ሁለቱም ሱዳኖች፣ ኬንያ፣ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ) ባሉ ሀገራት የአምባሳደር ሹመቶችንና በታኮነት የተቀመጡትን ወሳኝ የኢምባሲዉን ሰራተኞች ማንነትና ፖለቲካዊ ስብዕና ማጤኑ ይበልጥ ግንዛቤ ይሰጣል፡፡ ተሹዋሚ አምባሳደሮቹ አንድም የህወሓት ሰዎች ናቸዉ ካልሆነም የድርጅቱ ቀይ ምንጣፍ ጎታቾች መሆናቸዉ ለክርክር የሚቀርብ ጉዳይ አይሆንም፡፡ እዚህ ላይ በአሜሪካና በእንግሊዝ ያሉትን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኞችን ለማሳያነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

ኃይለ ሚካኤል አበራ

ግርማ ብሩን በአምባሳደርነት ሹመዉ ከጽዳት እስከ ኢምባሲዉ ዋና ጸሃፊ ድረስ፣ ከሴፍቲ ማን እስከ ፖለቲካና ደህንነት አታሼዎች ድረስ ከቪዛ ጉዳዮችን ከሚመለከቱ ሰራተኞች እስከ የዲያስፖራ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊነት ቦታዎች በሙሉ የትግራይ ሰዎች ናቸዉ፡፡ፕሮፖጋዲስቶቹ የህወሓት ሰዎች በየቢሯቸዉ የ“ብሄር ብሄረሰቦች”ን ፎቶ ለጥፈዋል፡፡ የክልሎችን ባንዴራ በየቢሮዉ ተፈልጎ አይታጣም፡፡ በስጋ ህወሓት በመንፈስ ደግሞ “ብሄር ብሄረሰቦች” ዉክልና አላቸዉ፡፡ ለንደን ላይ ብርሀነ ሀጎስን የተካዉ የኤፈርትን ንግድ የሚያጧጥፈዉ ኃይለ ሚካኤል አበራ ኢምባሲዉን ከእግር እስከ ራሱ በትግራይ ሰዎች ሞልቶታል፡፡ ይሄዉ ከሰሞኑ በዉጭ አገራት ባሉ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች የህወሓት 42ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በከበሮ ድለቃ እየተከበረ እንደሆን በመገናኛ ብዙሃን የዜና ሽፋን ተሰጥቶት እያየን ነዉ፡፡ የብአዴንና የኦህዴድን የምስረታ በዓል ማን ዘወር ብሎ ያያል?

ከላይ ለማሳያነት በተጠቀሱት ሀገራት የሚመደቡት አምባሳደሮች ካልተጻፈዉ ቀዳሚ ሥራቸዉ አንዱ ለህወሓቱ ግዙፍ ድርጅት ኤፈርት የሚሆኑ የንግድ ልዉዉጥ ጉዳዮችን ማመቻቸት ሲሆን፤ በግልጽ ከተጻፈዉ ቀዳሚ ሥራቸዉ አንዱ ደግሞ እንደየሀገራቱ ተጨባጭ ሁኔታ ዲያስፖራዉን ቢቻል በአብዮታዊ ዴሞክራሲዉ “የዲያስፖራ ፖሊሲ” እንዲጠመቅ በማድረግ የድርጅቱን ማህበራዊ መሰረት ማስፋት ካልሆነም በዲያስፖራዉ መካከል የዘዉግ ክፍፍል በመፍጠር ኃይሉን ማዳከም አምባሳደሮቹ፣ የፖለቲካና የደህንነት አታሼዎቹ የሥራ አፈጻጸም ከሚገመገምባቸዉ ነጥቦች በቀዳሚነት ይጠቀሳል (እንደየ ሀገራቱ የዲያስፖራ የኃይል ሚዛን ቢለያይም)፡፡

የህላዊ ህልውና ማክተም

የመለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ የተፈጠረዉን የዲፕሎማሲ ክፍተት ለመድፈን በየዓመቱ መጨረሻ ወር ላይ በህወሓቱ ኢሳያስ አማካኝነት የዉጭ ገዳዮችን በሚከታተለዉ የደህንነት ቢሮዉ ዲፓርትመንት ሪፖርት አቅራቢነት በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስተባባሪነት መካሄድ የጀመረዉ የአምባሳደሮች ዓመታዊ ስብሰባ ቀዳሚ አጀንዳ “የጽንፈኞችን ኃይል ለማምከን የተደረጉ ጥረቶችን እና ልማታዊ ዲያስፖራ ለመፍጠር የተሰሩ ተግባራት” የተመለከቱ ጉዳዮችን በስፋት ይቃኛሉ፡፡ ቀናት በሚወስደዉ በዚሁ ስብሰባ የየኢምባሲዉ አምባሳደሮች በመዋቅር ደረጃ ከነርሱ በታች የፖለቲካና የደህንነት አታሼ ሆነዉ በተመደቡ የህወሓት ሰዎች ከፍና ዝቅ እየተደረጉ ይገመገማሉ፡፡ እንዲህ ያለዉ ግምገማ በብርቱ ከደረሰባቸዉ አምባሳደሮች ቀዳሚዉ ህላዊ ዮሴፍ ይገኝበታል፡፡

ህላዊ ዮሴፍ

ህላዊ ዮሴፍ በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለሙሉ አምባሳደር ሆኖ ከተሾመ አንስቶ ሁለት ዋና ዋና ተልዕኮዎችን ማሳካት ይጠበቅበት ነበር፡፡ የእስራኤል ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉበትን ሁኔታ ማመቻት በተለይም ከኤፈርት ጋር (የብአዴኑን “ጥረት” እንርሳዉ) የሚሰሩበትን ዕድል መፍጠር አንደኛዉ ተልእኮዉ ነበር፡፡ ሁለተኛዉ ተልዕኮ ደግሞ በእስራኤል የሚኖሩ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያንን (ቤተ እስራኤላዊያንን) የዲያስፖራ ፖሊሲ በማጥመቅ መዋዕለ ንዋያቸዉን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ ማግባባት ጎን ለጎን ከቅርብ አመታት ወዲህ በቤተእስራኤላዊያን ዘንድ እየተስተዋለ ያለዉን የአንድት ሃይሉን በገንዘብ የመደገፍ ስሜት ማስተንፈስ የህላዌ ዮሴፍ ቁልፍ ተልእኮዎች ነበሩ፡፡ በእርግጥ በእስራኤል የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዉስጥ ሶስተኛ ተልእኮም አለ፡፡ እስራኤል እንደ መንግስት ህወሃት እንደ ድርጅት በደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ከሞሳድ ጋር የሚሰሯቸዉ ተግባራት አሉ፡፡

እስራኤልና አሜሪካን ሶማሊያ ዉስጥ ከመሸገዉ የአልሸባብ የሽብር ጥቃት ለመጠበቅ በዉክልና የሚዋጋዉ ህወሃት ለዚህ ዉለታዉ ከቴክኖሎጂ አቅም ጋር በተያያዘ የደህንነትና ስለላ (በተለይም ከሽብተኝነት ጋር በተያያዘ) እንዲሁም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነትና ስለላ የተመለከቱ ስልጠናዎች ለህወሃት ምልምሎች ይሰጣል፡፡ የስልጠና ተሳታፊዎችን የስልጠና ሂደቱን የሚከታተለዉ በኢምባሲዉ በኩል የደህንነት አታሼ ቡድን አለ፡፡ ህላዌ ይህን ጉዳይ ዳር ቁሞ ከመታዘብ የዘለለ ሚና አልነበራዉም፡፡

ያም ሆኖ “የእስራኤል ባለሃብቶችን ወደ ኢትዮጵያ በሚገባ አልሳብክም፤ ለኤፈርት ይህ ነዉ የሚባል የገበያ ትስስር አልፈጠርክም፤ በቤተእስራኤላዊያን ዲያስፖራዎች መዋዕለ ንዋያቸዉን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ ማግባባት አልቻልክም፤ በተለይም በ2008ዓም ሃምሌ ወር ላይ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ በባህር-ዳር ከተማ በተከበረዉ የዲያስፖራ ቀን ከእስራኤል የመጡት ዲያስፖራዎች ሰባት ብቻ ነበሩ፡፡ በአንጻሩ ቴልአቪቭና ጎንደር ከተማን ለመለየት በሚያስቸግር መልኩ ቴልአቪቭ የትምክህተኞችና የፀረ- ሰላም ሃይሎች ማዕከል ስትሆን አንተ ቢሮህን ዘግተህ ልቦለድ ታነብ ነበር” በሚሉ ቅስም ሰባሪ ክሶች በመዋቅር ደረጃ የበታቾቹ በገቢር ግን አለቆቹ በሆኑት የኢምባሲዉ የፖለቲካና የደህንነት አታሼዎች ተገምግሞ በእነ ጌታቸዉ አሰፋ ይሁንታ ሰጪነት በኃይለማርያም ደሳለኝ ፈራሚነት ከአምባሰደርነቱ ተነስቷል፡፡ በምትኩም የምንግዜም የበላዩ የህወሃቱ አለቃ ፀጋዬ በርሄ ተሹሟል፡፡

“የህላዌ አዕምሮ ኢህአፓ ላይ ቁሟል፡፡ ከዚህ በኋላ አዕምሮዉን ለግጥም እንጂ ለፖለቲካ ሊያዉለዉ አልቻለም” የሚሉት የኢህዴን የቀድሞ ታጋዮች፤ የመጠሪያ ስሙን ከፍቅሩ ዮሴፍ ወደ ህላዊ ዮሴፍ ከቀየረ በኋላ ከርዕዮተ ዓለማዊ ምልከታ ይልቅ የግጥም ተመስጦዉ በረታ፡፡ በድህረ ደርግ የመጀመሪያዉ አዲስ ዓመት ማግስት የህላዊ ብቸኛ ወንድም በአዲስ አበባ አንድ ጥግ ቦታ ላይ ራሱን አጥፍቶ ተገኘ፡፡ ህላዊ ከዚያች ቀን ጀምሮ ግድየለሽና ዝርክርክ ሰዉ ሆነ፡፡ አልኮልን ዋኘበት፡፡ ሲጋራን ከብዕሩ በላይ ጨበጠ፡፡ በበረከት ስምኦንና በጥቂት ጓዶቹ ጥረት ህይወትን በሹፈት፤ ፖለቲካን በአስመሳይነት ቀጠለ፡፡

ለዚህም ይመስላል የርጅና ዘመኑ አስቀድሞ የመጣ፡፡ በአምባሳደርነት ግዜዉ የኢየሩሌምን ገዳማት አዘዉትሮ ይጎበኝ ነበር፡፡ ቴልአቪቭ ዉስጥ በሚገኘዉ አዲስ አበባ ሬስቶራንት በተደጋጋሚ  ከሚገኙ ደንበኞች ቀዳሚዉ እርሱ ነዉ፡፡ በህወሃት ሰዎች አጠራር “በአዝማሪ ድግስ/ኮንሰርት” መታደም ነፍሱ ነዉ፡፡ ጠርሙስ ባይወረወርበትም አሽሙር ተወርዉሮበት ወደ ቤቱ ይመለስ ነበር፡፡ ቢሮዉ ዉስጥ በአዳም ረታ የልቦለድ ስራዎች መዝናናት ይወድ የነበረዉ ህላዌ፤ “የስንብት ቀለማት” እና “መረቅ” የተሰኙ የደራሲዉ ስራዎች ቢሮዉ ጠረጴዛ ላይ አይጠፉም፡፡

በእነዚህና መሰል ድርጊቶቹ ለተከታታይ ሁለት አመታት “C” በስንብት ዘመኑ ደግሞ “D” የተሰኘ አሸማቃቂ የአምባሳደርነት ዉጤቱን ተቀብሎ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል፡፡ ህላዊ ከዚህ በኋላ የህይወት ዘመን አለቆቹ የህወሃት ሰዎች ቢፈቅዱለት ከነሠራዊት ፍቅሬ፣ ቴዎድሮስ ተሾመ ፣ሙሉአለም ታደሰ…ጋር ፈርሾ የሮማንስ አድቬንቸር ፊልም ስክሪፕት እና ባሩድ ባሩድ የሚሸቱ ግጥሞችን እየጻፈ ማምሻዉን ደግሞ በቀኝ እጁ ቮድካ በግራ እጁ የኮንከር ካርታዉን ታቅፎ በዝምታ ሞቱን ቢጠብቅ አይጠላም፤ ፈቃጅ የለም እንጂ! ከወራት በኋላ በብአዴኑ “ጥረት ኮርፖሬት” የቦርድ አባልነት ዉስጥ አልያም በኢህአዴግ ጽ/ቤት በኩል ብቅ እንደሚል እንጠብቃለን፡፡

የአለቃ ፀጋዬ በርሄ ሹመትና ቀጣይ የቤት ሥራዎች

ጸጋዬ በርሄ

ከስድስተኛ ክፍል ትምህርቱና ከድቁናዉ አቋርጦ 1968ዓም ላይ ደደቢት በረሃ የተገኘዉ የቤተክህነት ሰዉ – ፀጋዬ በርሄ፡፡ ከዓለማዊ ትምህርቱ ይልቅ መንፈሳዊ ትምህርት ላይ የገፋ ሰዉ ነዉ፡፡ አለቃ ጸጋዬ በርሄ ሰባት ዓለማዊ መጽሃፍትን ባያነብም ሰባት ጊዜ ዳዊት ደግሟል፡፡ “አለቃ” የሚለዉ “የማዕረግ” ስሙም ከቤተክህነት ትምህርቱ ጋር ተያይዞ ኮሚኒስት ጓዶቹ ሲያላግጡበት ያወጡለት ስሙ ነዉ፡፡

አለቃ ጸጋዬ በርሄ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ባይጀምርም ዛሬ ላይ በቢዝነስ አድሚስትሬሽን (MBA) የሁለተኛ ዲግሪ “ባለቤት” ነዉ፡፡ ጸጋዬ በርሄ ከትምህርት አኳያ ልክ እንደ ነጭ ወረቀት ንጹህ ነዉ፡፡ ከሴራ ፖለቲካ አኳያ ግን የሚናቅ ሰዉ አይደለም፡፡ እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ አለቃ ጸጋዬ በርሄ የሽማግሌዉ ስብሃት ነጋ ዋርሳ መሆኑ ነዉ፡፡ የስብሃት ነጋ እህት ቅዱሳን ነጋን አግብቷል፡፡ ተንኮሉም ቢሆን ከአምቻ ጋብቻ ዉህድ የተገኘ ይመስላል፡፡ ድንቁርናዉም እንደዛዉ፡፡ ጸጋዬ ላይ የተቀለዱ ቀልዶች ግነት ቢታይባቸዉም ከእዉነታዉ ብዙ የራቁ ግን አይደሉም፡፡ ለአብነት አለቃ ጸጋዬ በርሄ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት እያለ ዮሃንስ ቤተመንግስት ዉስጥ መለስ በሚመራዉ ስብስባ ላይ ጣልቃ እየገባ ሲያስቸግር መለስ በቁጣ ስሜት “አለቃ ጸጋዬ የስብሰባዉን ህግ ታከብር እንደሆነ አክብር ካልሆነ ግን ይሄን ስብሰባ በእንግሊዝኛ ነዉ የማደርገዉ” ብሎ አሸማቀቀዉ እየተባለ የሚወራዉ ቀልድ የሰዉዬዉን ነጭ ወረቀትነት ለማመላከት ነዉ፡፡

አለቃ ጸጋዬ ህወሓት ረግጦ በሚገዛት ኢትዮጵያ በዋናነት በድሀረ መለስ ከታዩት ፖለቲካዊ አፈናዎች ጀርባ እጁ አለበት፡፡ በመለስ ጊዜም ቢሆን የህወሃት ክፍፍልን ተከትሎ በተፈጠረዉ  የኃይል አሰላለፍ የመለስን ቡድን በመደገፍ የእግረ ረጅሙን ሰዉዬ (ገብሩ አስራት) ወንበር የተረከበ፤ በክልሉ ዉስጥ አኩራፊ እንጂ አንድም ተቃዋሚ እንዳይፈጠር ተግቶ የሰራ፤ የኢዲዩ እና የደርግ ርዝራዥ ናቸዉ ያላቸዉን የትግራይ ሰዎች “ባዶ ስድስት” የተባለ እስር ቤት ያለ ምክንያት በማጎር ያሰቃየ፤ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) መሪ የነበረዉ ፍሰሃ ኃይለማርያምን (ቀደም ሲል የህወሃት ሰዉ ነበር) ኤርትራ በረሃ ላይ በደህንነት ሰዎች ሲገደል ግድያዉን ካቀነባበሩት ግንባር ቀደም ሰዎች አንዱ አለቃ ጸጋዬ በርሄ ነበር፡፡

በድህረ መለሷ ኢትዮጵያ የአለቃ ጸጋዬ ስዉር የአፈና እጆች የከሸፈዉን የአንዳርጋቸዉ ፅጌን የግድያ ሙከራ (ኢሳት በዶክመንተሪ መልክ ሰርቶታል) በማቀነባበር፤ አንድነት ፓርቲን በትእግስቱ አወሉ በኩል እንዲሰነጠቅ በማድረግ፤ ሰማያዊ ፓርቲን በማስተንፈስ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ዉስጥ ገብቶ በመፈትፈት፤ መተማ ላይ የተፈናቀሉትን የትግራይ ሰዎች ድራማ በማቀነባበር፤ የወልቃይትን ጉዳይ ይበልጥ በማወሳሰብ ረገድ ሰዉዬዉ እጁ ረጅም ነዉ፡፡ደብረጽዮን የሚያከብረዉ፤ ጌታቸዉ አሰፋ የማይንቀዉ ሰዉ – አለቃ ጸጋዬ በርሄ አሁን ለየት ያለ ተልዕኮ ተሰጥቶታል፡፡

በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለሙሉ አምባሳደር ተሿሚ ሆኗል፡፡ በዚህ ሹመቱ ህላዊ ዮሴፍ ልቦለድ እያነበበ ያበላሻቸዉን ስራዎች ከኢምባሲዉ ነባር የህወሃት ተሿሚዎች ጋር ሆኖ ማስተካከል ይኖርበታል፡፡

  • ለኤፈርት የንግድ አጋር መሆን የሚችሉ ኩባንያዎችን ማፈላለግ
  • የቤተ እስራኤላዊያንን የከረረ የአንድነት ስሜትና ድጋፍ ማስተንፈስ
  • ሞሳድ ለህወሃት የሚሰጠዉን የደህንነትና ወታደራዊ ስልጠናዎች ሂደት መከታተል የአለቃ ጸጋዬ ተጠባቂ ተልዕኮዎች ናቸዉ፡፡

አለቃ ፀጋዬ ከትግረኛ እና ግዕዝ በመጠኑም ቢሆን ከአማርኛ ቋንቋ በስተቀር ሌላ ቋንቋ ጆሮውን  ቢቆርጡት አይስማም፡፡ የአለቃ ፀጋዬን የቋንቋ ችግር ቀድሞ የተረዳው የጌታቸው አሰፋ የደህንነት መስሪያ ቤት በእስራኤል የኢትዮጵያ ኢምባሲ ውስጥ ከሚሰሩት ሁለት የፖለቲካና ሶስት የደኅንነት አታሼዎች በተጨማሪ ለሁለቱም ዘርፍ ሁለት ሁለት ተጨማሪ ሙያተኞች ከአለቃ ፀጋዬ ጋር ወደ እስራኤል እንዲጓዙ አድርጓል፡፡

ስኳዱን አጠናክሮ የተጓዘው አለቃ ፀጋዬ “ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠር ፖለቲካውን ይቆጣጠራል” በሚለው ህወሃታዊ መመሪያ መሠረት ለግዙፉ ኤፈርት የንግድ ኢምፓየር ተጨማሪ ግብአት  ለመፍጠር በቻለው መጠን መትጋቱ ይጠበቃል፡፡ በተለይም በኮንስትራክሽን ዘርፍ (ከሱር ከንስትራክሽን ጋር)፤ በመድኃኒት ምርት (ከአዲስ የመድኃኒት ፋብሪካ ጋር)፤ በእርሻ መሳሪያዎች (ከህይወት ሜካናይዜሽን ጋር) በቴክኖሎጂ ዘርፍ (ከኮምፒዉተር ኔትወርኪንግ ቴክኖሎጅ ሶሉሽን ጋር) እንዲሁም በ“ትዕምት” ስር ካሉ ሌሎች በዝባዥ የንግድ ድርጅቶች ጋር የሚሰሩ የእስራኤል  ባለሀብቶችን በማፈላለጉ ረገድ የአለቃ ፀጋዬ ስኳድ ድርጅታዊ ተልዕኮ ይሆናል፡፡

በእስራኤል የሚኖሩ አብዛኞዎቹ ቤተ እስራኤላዊያን እጅግ ጥብቅ የሆነ የአንድነት ስሜት ያላቸውና የታወቀውሞ ጎራውን የሚደግፉ ናቸው፡፡ ኢሳት በተደጋጋሚ የገቢ ማስባሰቢያ አካሂዶ ከማያፍረባቸው ከተማዎች አንዷ ቴልአቪቭ ነች፡፡ ቤተ እስራኤላዊን በእስራኤል ውስጥ ያላቸው የአንድነት የፍቅር ስሜት ከሌላው አለም ለየት ያለ ነው፡፡ አብዛኞዎቹ ከአንድ አካባቢ (ከጎንደር) የሄዱ በመሆኑ በዘውግ የመከፋፈል ተጋላጭነታቸው ወደ ዜሮ የወረደ ነው፡፡

ቤተ እስራኤላዊያን ከቆይታ ብዛት በወታደራዊ መስክ እስከ መኮንንና የመስመር ኃይል መሪነት የደረሱ፤ በእስራኤል የሀገር ውስጥ የደህንነት መስሪያ ቤት “ሽንቤት” የደህንነት ኦፊሰር የሆኑ፤ በትህምርትና በንግድ የተሳካላቸው፤ በፖለቲካዉ መስክ የካዲማ ፓርቲ አባል በመሆን በእስራኤል  ፓርላማ “ክኔሴት” የፓርላማው ምክትል አፈጉባኤ የሆነውን ሸሎሞ ሞላን ጨምሮ በሊኩድ ፓርቲ በአመራር ደረጃ ቤተ እስራኤላዊያን አሉ፡፡

የጠንካራ ኮሚኒቲ ባለቤት የሆኑት ቤተ እስራኤላዊያን፤ የድህነት ጉዳይ ሆኖ እስራኤል ቢኖሩም ልባቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሆነች በኩራት ይናገራሉ፡፡ ቤተ እስራኤላዊያን ሀገር ቤት ባለው  ጨቋኝና ዘረኛ አገዛዝ ሁሌም እንደተከፉ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ተደጋጋሚ የተቃውሞ ስልፎችን በማዘጋጀትና ለተቃዋሚው ኃይል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የከረረ ተቃውሟቸዉን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

የጥንቱን ሰለሞናዊ ትርከት እንተወውና እስራኤል በአመዛኙ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት የተለሳለሰና ጥቅም ተኮር ነው፡፡ በኃይለሥላሴ ጊዜ ጽዮናዊነነትን አስታክካ ግንኙነቷን በይፋ  የጀመረችው እስራኤል፤ ጽዮናዊነነትን በአደባባይ “ማህበራዊ አደንዛዥ ዕጽ” እያለ ይነቅፍ የነበረው ደርግ ሲመጣም እርሱን ሳትዘልፍ የሽምቅ ተዋጊዎቹንም ሳትደግፍ በተለሳለስ መልኩ መንግሥቱ ኃይለማርያም ያበደበትን “ዘመቻ ሰለሞንን” አሳክታለች፡፡

ህወሓት ማዕከላዊ መንግሥቱን በተቆጣጠረ በወራት ልዩነት ባዘጋጀው የሽግግር መንግሥት ጉባኤ ላይ በተጋባዥነት የፍልስጤሙን ነፃ አውጪ መሪ ያሴር አራፋትን ሲጋብዝ፤ እስራኤል የደንቡን  ያህል ተቃወመች አንጂ አኩርፋ አልቀረችም፡፡ የማታ ማታም የደኅንነት አቅምን ከማሳደግና  የቴክኖሎጂ አቅምን ከማጎልበት አኳያ የሞሳድ ድጋፍ የተገለጠለት ህወሃት ከእስራኤል ጋር በፍቅር ወደቀ፡፡

እስራኤል ለየትኛውም ሀገር በደኅንነትና ወታደራዊ ሥልጠናዎች ዙሪያ ድጋፍ ለመስጠት ቀዳሚ መስፈርቷ ሰብዓዊ መብቶች አለያም ዴሞክራሲያዊ መብቶች የመከበር ያለመከበር ጉዳይ አይደለም፡፡ ይልቁንስ ከተሳካ ታሪካዊ መሰረት ያለው ጽዮናዊነት ካልሆነም ሽብርተኝነትን በተመለከተ ሀገራቱ ያላችውን የአደባባይ አቋምና መልካዊ ምድራዊ አቀማመጥ መገምገም ይቀላታል፡፡

በዚህ ስሌት ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ተመራጭ በተለይም በሶማሊያ ጸረ አሜሪካ-እስራኤል የሆነው አልሸባብ አከርካሪ አለመስበር፤ በኤርትራ ምጽዋ ወደብ ላይ ኢራን፤ ሳውዲ አረቢያና ግብጽ የጦር ቤዝ ለመመስረት ያላቸው ወታደራዊ ፍላጎት፤ የየመናዊያን የርስ በርስ ጦርነት እና ኢራንና የሳውዲ አረቢያ በየመን የውክልና ጦርነት መጀመራቸዉ በዚህ ክፍተት  የሚፈጥረው ኃይል ያሳስባት እስራኤል ኢትዮጵያን አጥብቃ እንድትይዝ አድርጓታል፡፡ መቼም አከራሪ የጽዮን ብሄረተኛው ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ያለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ጉብኝት በጠብታ መስኖ ልማት ዙሪያ ለመፈራረም እንዳልመጣ ግልጽ ነው፡፡

የህወሃት የደህንነት መስሪያ ቤት አቅም ይበልጥ እየፈረጠመ መምጣት ግብአቱ ከአሜሪካና ከእስራኤል የሚሻገር አይደለም፡፡ በተለይም በብርጋዴል ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ የሚመራው የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) የታቀዋሚ ፓርቲ መሪዎችን፣ የጋዜጠኞችን፣ የአክቲቪስቶችን፣ የተጽዕኖ ፈጣሪ አርቲስቶችን እና የታዋቂ ግለሰቦችን የዕለት ተዕለት የስልክ ግንኙነት በመጥለፍ፤ የኢይሜል እና የፌስቡክ አካውንታቸውን በመስበር መረጃዎችን ሲበረብር ውሎ የሚያድርበት የአቅም ምንጭ ከእስራኤል-አሜሪካ የተገኘ ነው፡፡

አለቃ ፀጋዬ፤ ቤተ እስራኤላውያን የአንድነት ኃይሉን የታወቀውሞ ጎራ የሚደግፉበትን ብሄራዊ ስሜት ማስተንፈስ የሚሳካለት ባይመስልም፤ የግዙፉን ኤፈርት የንግድ ኢምፓየር ይበልጥ ለማስፋትና በሞሳድ በኩል ለህወሃት ምልምል የደኅንነት ሰዎች የሚሰጠውን ስልጠና በምልክት ቋንቋ ቢሆን ተደግፎ የሥልጠናውን ሂደት ለመከታተል አይሰንፍም፡፡

የሀገር ቤቱ ህዝባዊ ተቃውሞ አይሎ ህወሓት ወደ መቃብር ቢወርድ እስራኤል አለቃ ፀጋዬን አሳልፋ ባትሰጥም ዴር ሱልጣን ገዳም ውስጥ የብህትውና ህይወት እንዲኖር ፈቃድ የምትነፍገው አትመስልም፡፡ ማን ያውቃል አለቃ ፀጋዬም በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የተካውን ዳዊት አንስቶ  ይደግመው ይሆናል፡፡ እስከዚያዉ ግን እስራኤል አንደ መንግሥት ለብሔራዊ ደህንነቷ፤ ህወሃት እንደ ድርጅት ለልዕለ ዘዉግ የበላይነት ወዳጅነታቸው ይቀጥላል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ያለ ማስረጃ ክፍያ ተፈጽሟል አለ

$
0
0

ረፓርተር ጋዜጣ

  • የኦዲት ግኝት የቀረበባቸው ተቋማት በአንድ ወር ውስጥ ምላሽ እንዲሰጡ ታዘዙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር ባቀረበው የስድስት ወራት ሪፖርት ለማን እንደሚከፈል ማስረጃ ያልቀረበለት 1.099 ቢሊዮን ብር ክፍያ እንደተፈጸመ ይፋ አደረገ፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የአንበሳውን ድርሻ ይዟል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ 89.9 ሚሊዮን ብር በጉድለት መገኘቱ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ በዚህ መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን 71.5 ሚሊዮን ብር፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት 18.5 ሚሊዮን ብር፣ በድምሩ 89.9 ሚሊዮን ብር ጉድለት ተመዝግቦባቸዋል፡፡

አዲስ ዙ ፓርክ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል፣ የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት 11 እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤቶች ግንባታ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ደግሞ 767.6 ሚሊዮን ብር በወቅቱ ፈሰስ አላደረጉም ይላል የኦዲት ግኝት ሪፖርቱ፡፡

የዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ደግሞ 2.7 ሚሊዮን ብር በማነስ የተመዘገበ ሒሳብ እንዳለው ታውቋል፡፡ የኦዲት ሪፖርቱ እንደሚለው ለማነስ ምክንያት በሥራ ተቋራጮች ቅድመ ክፍያ 2.7 ሚሊዮን ብር በእያንዳንዱ የክፍያ ሰርተፍኬት ተቀንሶ ሳይሰበሰብ መገኘቱ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቤቶች ግንባታ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና ዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል በድምሩ 168.09 ሚሊዮን ብር ማስረጃ ያልቀረበበትና ለማን እንደሚከፈል የማይታወቅ ክፍያ ፈጽመዋል ሲል ሪፖርቱ ገልጿል፡፡

በተጨማሪ ከግዢ ደንብና መመርያዎች ውጪ በጨረታ አሸናፊ ካልሆነ ድርጅት ግዢ መፈጸም፣ ውል ሳይገባ ግዥ መፈጸም፣ ያለ ጨረታ ግዥ መፈጸም፣ በቴክኒክ ኮሚቴ አስተያየት ሳይሰጥበት ግዥ መፈጸም በሪፖርቱ ቀርበዋል፡፡ በዚህ መሠረት 12.5 ሚሊዮን ብር ግዥ የፈጸሙ ተቋማት ተብለው በኦዲት ሪፖርቱ የተጠቀሱት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ አዲስ ዙ ፓርክ፣ የአዲስ አበባ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ቢሮ ናቸው፡፡

ተከታታይ ቁጥር በሌለውና ሕጋዊ ባልሆነ ደረሰኝ 87.2 ሚሊዮን ብር ክፍያ የፈጸሙት ደግሞ የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ፣ ዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል፣ ራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታልና ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት 11 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ናቸው ተብሏል፡፡

የመንግሥት የግዢ አፈጻጸም መመርያ ቁጥር 3/2002 ክፍያ መፈጸም ያለበት ሕጋዊ በሆነ የገቢ ክፍያ መለያ ቁጥር ባለው ደረሰኝ መሆን እንዳለበት ቢገልጽም፣ ተቋማቱ ይኼንን መመርያ መተላለፋቸውን የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር ሪፖርት ይገልጻል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ 107.6 ሚሊዮን ብር ንብረት ክፍል ገቢ ስለመደረጋቸው ማስረጃ ሳይያያዝ ክፍያ መፈጸሙን ሪፖርቱ ገልጿል፡፡

አስገራሚ ሆኖ የተገለጸው ክስተት ደግሞ፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በኮንትራክተሮች ስም የተሽከርካሪ ግዥ 34.5 ሚሊዮን ብር የፈጸመ መሆኑ በኦዲት ምርመራ ወቅት ተሽከርካሪዎቹ ወደ ባለሥልጣኑ ሳይዛወሩ መገኘታቸው ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር ወ/ሮ ጽጌ ወይን ካሳ ዓርብ የካቲት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባቀረቡት በዚህ የኦዲት ሪፖርት፣ የኦዲት ግኝት በተገኘባቸው ተቋማት ላይ የተጠያቂነት ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

ይኼ ሪፖርት በቀረበበት ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡

ከንቲባ ድሪባ ኩማና ምክትል ከንቲባ አባተ ስጦታው ይኼ ጉዳይ በአስቸኳይ ተጣርቶ ዕርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡ የኦዲት ግኝት ያለባቸው መሥሪያ ቤቶች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲሰጡ ከንቲባው ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

 

ድርድሩ – ይገረም አለሙ

$
0
0

መንደርደሪያ ፤ ብዙ ግዜ አዲስ ያልሆኑ ግን እኛ አዲስ የተፈጠሩ ያህል የምንጮህባቸው ነገሮች ሲከሰቱ ብዙዎች የሚያሳዩት ነገር “የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል” ይሉ አይነት ነው፡፡ ወያኔ ሥልጣኔን ያሰነብትልኛል ብሎ እስካመነ የማይቆፍረው ጉድጓድ እንደሌለ እየታወቀ  ድርድር ጠራ ተብሎ  ተቀዋሚ ተብየዎችም ጥሪውን ተቀብሉ  ተብሎ አዲስ ተአምር የተፈጠረ ይመስል ድጋፍና ተቃውሞ በተለመደው መንገድ እየተሰማ ነው ነው፡፡ ነገር ግን ከተለመደውና መረጃም ማስረጃም ፍለጋ ከማያደክመው የፍረጃና ውንጀላ ጉዞ ወጣ ብሎ ድርድር ለምን፣  ድርድር በእነማን መካከል፣ ድርድር እንዴትና በምን ሁኔታ? ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ የሚችል አስተያየት መጻፉ፣ ልምድ ማካፈሉ ነበር የሚበጀው፡፡ እኔ ይህን ለማድረግ የሚበቃ እውቀትም ልምድም የለኝም፡፡ ፍረጃና ውንጀላ ላይ በመሮጥም ሆነ ጭፍን ድጋፍ በመስጠት  ደግሞ አላምንም፣ በዚህ መካከል ሆኜ ስለ ድርድሩ የተሰማኝን  ልበል፡፡

ድረድር፣  ለድርደር ምክንያት የሆነው ጉዳይ ምንነት፣  የተደራዳሪዎቹ ማንነት፣ የድርድሩ ሂደት አንዴትነት ወዘተ ቢለያይም  ዙሪያ ጥምጥም ገለጻ ውስጥ ሳይገባ ድርድር ሰጥቶ መቀበል ነው፡፡ ትንሽ የያዘው ወይንም ምንም የሌለው የሚፈልግበት፣ ብዙ የያዘው የሚሰጥበት፡፡ በመሆኑም ያየዘውን ወዶና ፈቅዱ የሚሰጥ “ቅዱስ ፖለቲከኛ” የለምና   ያለ አስገዳጅ ሁኔታ በውዴታና በፈቃደኝነት ወደ ድርደር መድረስ አይቻልም፡፡ አሁን የሚወራለት ድርድር ይካሄዳል የሚባለው ሁሉንም ጠቅሎ በያዘውና የሚሰጠውም የማይሰጠውም በብዛት ባለው ወያኔና በየግልም በጋራም ምንም ባልያዙና ምንም የሚሰጡት ነገር በሌላቸው ተቀዋሚዎች መካከል ነው፡፡ (ይቅርታ ይደረግልኝና የድርድሩ ተካፋይ የተባሉትን ፓርቲ ብሎ ለመጥራት አንደበቴ፣ ለመጻፍ ጣቶቼ እሽ አይሉኝም፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ለድርጅቶቹ ወይንም ለመሪዎቹ ጥላቻ ኖሮኝ ሳይሆን ፓርቲ ለመባል የማይበቁ በመሆናቸው ነው፡፡) ስለ መስጠት መቀበሉ ከማየታችን ቀደም ግን እዚህ ደረጃ እንዴትና በምን ምክንያት ተደረሰ የሚለውን ማየቱ ይበጃል፡፡

የድርድሩ ምክንያት የህዝብ እንቢተኝነት፡፡  ወያኔ የድርድር ጥሪ ያቀረበው በመላ ሀገሪቱ በተለይ ደግሞ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች በተቀጣጠለው የህዝብ ቁጣና እንቢተኝነት በደረሰበት ድንጋጤ መሆኑን ወያኔዎችም ቢሆን የሚክዱት አይመስለኝም፡፡ በማሰር፣ በመግደል፣ በማስፈራራት አመጹን መግታት አልቻሉም፤ የሀያ አመስት አመት ብሶት ነውና ፡፡ የሚመጻደቁበትን ህገ መንግሥት ጣጥለው በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስም ወታደራዊ አገዛዝ አሰፈኑ፤ ለወያኔ ከሥልጣን የሚብስ ነገር የለምና፡፡ ይህን ሁሉ ቢያደርጉም የህዝቡን ተቃውሞ አጥፍተው ሥልጣናቸው ሲረጋጋ አልታይ አላቸውና “ጅብን ሲወጉ በአህያ ተከልሎ ነው” እንዲሉ ተቀዋሚ ተብየዎችን ተጠቅመው የህዝቡን ተቃውሞ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ እናጠፋለን ብለው ተነሱ፡፡ ይህን ሀሰት የሚል ይኖር ይሆን? ካለ በጽሞና እንነጋገር፡፡

ወያኔን ለድርደር ያንበረከከው የህዝብ ትግል በህይወትም በአካልም አያሌ መስዋዕትነት ተከፍሎበታል፡፡ የድርድሩ አብይ ፈተና የሚመጣው እዚህ ጋር ነው፡፡ ምክንያትም ወያኔ ህዝብ መስዋዕትነት የከፈለበትን ጥያቄ መመለስ አይችልም፣ተቀዋሚ ተብየዎቹ ደግሞ ( ስም አጣሁላቸውና ተቸገርኩ) ለህዝቡ ጥያቄ መልስ የማስገኘት ፖለቲካዊ አቅም አይደለም ጥያቄውን ይዞ ለመደራደር የሞራል ብቃት የላቸውም፡፡ አረ እኔ አለሁ የሚል ካለ በጩኸትና በዘለፋ ሳይሆን በሚታይ በሚዳሰስ ማስረጃ ያሳየን፡፡

ወያኔ ለምን ይደራደራል፡ ወያኔ ተገዶም ቢሆን ለምን ወደ ድርድር መምጣት እንደፈለገ ለሁሉም ሰው ግልጽ ነውና ብዙ የሚያነጋግር አይመስለኝም፡፡ አንደኛውና የመጀመሪያው ምክንያት ከአዋጅ በፊትም ሆነ በአዋጅ መግደል ማሳሩ የህዝቡን ተቃውሞ ሊያዳፍነው ካልሆነ በስተቀር ጨርሶ ሊያጠፋው እንዳልቻለ ማየቱ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የግዜ ጉዳይ ነው አንጂ ተቃውሞው በተመሳሳይ ሁኔታ መነሳቱ አይቀሬ ነው፡፡  ታዲያ በየግዜው የህዝብ ቁጣ እየተነሳበት በለመደው መንገድ እየገደለ በአንድ በኩል ውግዘትና ወቀሳ እያስተናገደ ከመኖር፣በሌላ በኩል ደግሞ ከሥልጣን ሲወርድ የሚጠየቅበትን የወንጀል ክምችት እየበዛ  ከሚቀጥል የህዝብን ተቀዋሞ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለማጥፋት ነው፡፡ ይሄ ይችላል? አሁን ከመተንበይ ግዜው አጭር ስለሆነ ጠብቆ ማየቱ ይሻላል፡፡ ሌላው በኃያላኑ መንግሥታት የገንዘብ እርዳታና ብድር እንዲሁም የዲፕሎማሲ ድጋፍ የቆመ በመሆኑ ሰላም ፈላጊ ችግርን፣ በዴሞክራሲያዊ አግባብ በሰላም የሚፈታ፣ ከተቀዋሚዎቹ ጋር የሚነጋገር መስሎ በመታየት ድጋፉን ማስቀጠል መቻል ነው፡፡ ድርድሩ ከቀጠለ ይህ እንደሚሳካለት የሚያጠራጥር አይመስለኝም፡፡ ሌላው ተቀዋሚዎችን አፍ ማስያዝ፣ ቁርጥ ያለ ዓላማ፣ እምነትና አቋም የሌላቸውን ተቀዋሚ ነን ባዮች ደግሞ (በውጪም በውስጥም ያሉ) ሲሆን በአባልነት፣ ካልሆነም በደጋፊነት ማሰልፍ መቻል የድርድሩ አንዱ ዓላማ ሊሆን ይችላል ብሎ መገመት ይቻላል፡፡

ተቀዋሚዎች ለምን ይደራደራሉ፤ የሚሰጡት የሌላቸው፣ ወያኔን ወደ ድርድር ባመጣው የህዝብ ትግል ውስጥ ጠብታ አስተዋጽኦ ያልነበራቸው፤ በተናጠል ፓርቲ ለመባል የማይበቁ፣ በጋራ፣ የጋራ የመደራደሪያ አጀንዳ ቀርጾ ለመቅረብ የሚያስችል የትግል አንድነትም ሆነ የአንድ ሀገር ልጅነት ፍቅር የሌላቸው ምን ለማትረፍ ነው ወደ ድርድሩ መድረክ ያመሩት ብሎ መጠየቁ ተገቢ ቢሆንም እንደ ስማቸው ፍላጎታቸው የበዛ እንደ ብዛታቸው መልካቸው የተዥጎረጎረ ነውና አንድ ወጥ የሆነ ምላሽ ማግኘት የዳግታል፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን ምላሽ መፈለግ ግድ ነውና ለመልሱ መንደርደሪያ ወይንም በር ከፋች ጥያቄ ይቅደም፡፡

የሚደራደሩት ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ለማስገኘት ወይንስ የየግል ፍላጎታቸውን ለማርካት? የመጀመሪያው ከባድ የሚባል ብቻ ሳይሆን የማይሞክሩት ነው፡፡ ምክንያቱም የህዝቡ ጥያቄ የሥርዓት ለውጥ ነውና፡፡ ሁለተኛው ግን በጣም ቀላል ነው፡፡ መለስ ፍለጋውን ከቀላሉ እንጀምር፡፡

ወያኔ በፓርላማው ስራ መጀመሪያ ቀን በፕሬዝዳንቱ አንደበት ያስነገረውን “የፓርላማ ወንበር በችሮታ አንሰጣለን” የሚል መልእክት ያለው ንግግር የሚረሳ ያለ አይመስለኝም፡፡ በተነገረው መሰረት የምርጫ ህጉን በማሻሻል ( ይህን ህግ ለማሻሻል ህገ መንግሥቱን ማሻሻል ቢያስፈልግም ወያኔ ለዚህ ግድ የለውም) ፓርላማ በመገኘት ባለመገኘታቸው በወያኔ ላይ ምንም የማያመጡትን ሰዎች ወደ ፓርላማ መግቢያ በር በድርድሩ ካሳያቸው፣ በጣም ቸር ልሁን ካለ ደግሞ የተወሰኑቱ የምኒስትርነትም ባይሆን የምክትልነት ሹመት በዚህ ድርድር ማትረፍ አንደሚችሉ ካሳያቸው በወያኔ ድርጎ የሚተዳደሩ ወትሮም ከህዝብ ጋር ጉዳይ የላቸውምና “ምኞቴ ተሳካ ያሰብኩት ደረሰ” የሚለውን የጥላሁን ገሰሰን ዜፈን እያዜሙ ድርድሩ በስኬት ተጠናቀቀ፣ ኢህዴግ ለሀገርና ለህዝብ አሳቢነቱን ”

ለድረድር ከቀረቡት መካከል  ሌላው ቢቀር ቤት ኪራይ የሚከፍልልንን ደጋፊ እንዳናጣ ብለው የሚሰጉና በእምቢተኝነት የፖለቲካ ትርፍም እናገኛለን ብለው የሚያስቡ ቢገኙና በዚህ መንገድ አንደራደርም፣ ይሄን ይሄን አንቀበልም ፣በዚህ መልክ ችግሩ በዘለቄታ  አይፈታም ወዘተ ለማለት ከቻሉ ብዙም አይሆኑምና በጸረ ሰላምነት ተወግዘው፣ በድርድር አደናቃፊነት ተከሰው፣ ከዛም አልፎ የሌሎችን ተልእኮ አንግበው የመጡ የሚል ሰም ተሰጥቶአቸው አፋቸውን ለጉመው፣ እግር ከወርች ታስረው በሚኖሩበት ቢሮአቸው መመሸግ ነው፡፡

አሁን ወደ ከባዱ ጥያቄ እንመለስ፡ ህዝቡ የጠየቀው የሥርዓት ለውጥ በመጀመሪያ በአጀንዳነት ሊመዘገብ አይችልም ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል፡ ከወያኔ ባህርይ አንጻር፡፡ ምክንያት ወያኔ ሰማይ መሬቱን የሚቧጥጠው ሥልጣኑን ለማጥበቅ እንጂ ለመልቀቅ ምን አደከመው፡፡ ተደራዳሪ ተብየዎቹስ ይህ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ  መጀመሪያ ፍላጎቱ፣ ቀጥሎ ዝግጅቱ፣ ከዛስ  አጀንዳ አንዲሆን የማስገደድ የተናጠል ብቃቱ የጋራ  ህብረቱ አላቸው? ከየት መጥቶ! እናም ጉዳይ እዚሁ ላይ ያበቃል፡፡የተደራዳሪዎችም ፍላጎትና ማንነት እዚሁ ጋር ይታወቃል፡፡ “የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል ይሉ አይነቱ ጭፍን ድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ፍረጃና ውንጀላው አሁን ተገቢ የማይሆነው ለዚህ ነው፡፡

የድርድሩ የመጨረሻ ውጤት ዜሮ ነው፡  ድርደሩ ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ለወያኔ  ርዳታና ብድሩ አንዳይነጥፍ፣ የዲፕሎማሲ ድጋፉ እንዳይቆም ሊያደርግለት ይችል ይሆናል፣ ችግሮችን በውይይት የሚፈታ፣ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ህገ መንግሥትን እስከ መሻሻል  ድረስ የሚሄድ፤ ለተቀዋሚዎቹ ወንበር ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ የመሳሰሉ ቅታያዎችና ማደመቂያዎች ተጨምረውበት  ገጽታ ግንባታ ለሚባለው  የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ፍጆታ ሊጠቅመው  ይችል ይሆናል፤ የትግላቸው መነሻም ሆነ መድረሻ የራስ ጥቅም ለሆኑ በተቀዋሚ ካባ ለሚንቀሳቀሱትም ትንሽ ትንሽ የሥልጣንም የገንዘብም ፍርፋሪ ሊያስገኝላቸው ይችል ይሆናል፡፡ (አሁን ከሚሰጣቸው ዳረጎት በተጨማሪ)

እንዲሁም የእነርሱ ፓርላማ መግባት የኢትዮጵያዉያን ችግር መፍትሄ ማግኘት ለሚመስላቸው ወይንም አድርገው ለሚያስቡ (ይህ ከዚህ ቀደም በተግባር ያየነው ነው)  በመጪው ምርጫ ተወዳድረው አሸንፈው ሳይሆን በችሮታ ፓርላማ የሚገቡበትን መንገድ ሊያመቻችላቸው ይችል ይሆናል፡፡ሌላም ሌላም ፤

ወያኔና ተደራዳሪዎች እንዲህ በየመጠናቸው ከድርድሩ ሊያተርፉ ይችላሉ ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ ትርፍ እናገኛለን ሳይባል ሳታሰብና ሳይታቀድ አይደከምምና፡፡ የድርድሩ ምክንያት የሆነው በህይወትና በአካል መስዋዕትነት ወያኔን ወደ ድርድር ያመጣው ህዝብ ግን ጥያቄውን የሚመልስለት አይደለም ለጉዳቱ ካሳ የሚሆነው አንዳችም ነገር አያገኝም፡፡ ይሄ ነው አንግዲህ የድርድሩን ውጤት ዜሮ የሚያደርገው፡፡  እንደ እስራት ግድያውና የአስቸኳይ አዋጁ ድርድሩም  የህዝቡን ጥያቄ መመለስም ተቃውሞን ከነአካቴው ማጥፋትም አያስችልምና፡፡

በመጨረሻ፤ ለመሆኑ ድርድር ከተባለ መደረግ ያለበት ከመንግሥት ጋር ነው ወይንስ ከኢህአዴግ ጋር፡፡ ወያኔ የመንግሥትና የድርጅት ኮፍውን ሲሻው የሚቀላቅለው ሲፈልግ የሚለያየው ለእኩይ ተግባሩ መጠቀሚያ ሲል ነው፡፡ እንደውም አቶ መለስ በተካኑበት የማደናገሪያ ስልት ተከታዮቻችውንም እኛንም ሊያደናግሩ የድርጅታቸው አንዱ ችግር የድርጅትና የፓርቲ ኮፍያ ማደባለቅ አንደሆነ ነግረውን ነበር፡፡ “ፖለቲከኞቻችንስ” ኢህዴግ ማለት መንግሥት፣ መንግሥት ማለት ኢህአዴግ ነው ብለው አምነው ተቀብለው ነው ፡፡

ትክክል የሚባል ነገር ከጠፋ አመታ ተቆጠሩ እንጂ ትክክለኛው ነገር ወያኔም እንበለው ኢህአዴግ ፓርቲ ነው፤ እውነተኛ (አቅም፣ ብቃት፣ የዓላማ ጽናትና ግልጽነት ያለው ) ተቀዋሚ ቢኖር ፓርቲ ከፓርቲ ጋር መፎካከር መወዳደር እንጂ መደራደር የለም፡፡መደራደር ከመንግሥት ጋር ነው፡፡ እዚህ ጋር ኢህዴግንና መንግሥትን ምን ለያቸው የምትለው የተለመደች  ነገር አንደምትነሳ እገምታለሁ ፡፡እኔም ጥያቄ አለኝ እነርሱ የሚሉትንና የሚያደርጉትን ነው መከተል ያለብን ወይንስ ትክክል የምንለውን?

ቸር አንሰንበት

አንድ ሚሊዮን ስንት ነው? – ነፃነት ዘለቀ

$
0
0

ይሄ የቁጥር ነገር አልገባኝ እያለ መቸገሬን የምገልጥላችሁ ሀገሬ ውስጥ በምታዘበው የሙስና ግዝፈት እያፈርኩና እያረርኩም ነው፡፡ ትሹም ትልቁም ከመሬት እየተነሣ “አንድ መቶ ሚሊዮን ከባንክ ተበድሬ…፣ አምስት መቶ ሚሊዮን ብር ከባንክ ተበድረን ስናበቃ …፣ ለእገሊት 30 ሚሊዮን አበድሬያት …” እያለ ሲያወራ አንደበቱን ያዝ እንኳን አያደርገውም፡፡ ስለዚህ ቁጥር እኔ ማይም ነኝ ወይም እነሱ የጣሱት አኃዛዊ ሕግና ሥርዓት መኖር አለበት፡፡ እንጂ የ18 ዓመትና የ20 ዓመት ታዳጊ ወያኔ የ5 ሚሊዮን ብር መኪና ሲነዳ ማየት ባልተቻለ ነበር፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ ብዙ ነገሮች አውሮፓና አሜሪካ ቢሆን ኖሮ ዕድሜ ልክ ዘብጥያ ያስወርዳሉ፡፡ “ከየት አመጣኸው?” ብሎ የሚጠይቅ እኮ የለም፡፡ ካጠገብህ ተነስቶ ላጥ ይልና በአንዲት ቀን አዳር ሚሊዮኔር ሲሆን ታየዋለህ፡፡ በትብታብ ይሁን በጥንቆላ ወይም ሰርቶ ይሁን ሰርቆ የሚታወቅ ነገር የለም – ተሰርቶ ደግሞ በቅጽበት ጠሀብ ጫፍ አይደረስም፤ ህግና ሥርዓት ከሌለ በስተቀር፡፡ ንግድ ዱሮም ነበር – ያኔ ተያይቶ ነበር ሰው የሚናገደው እንጂ እንዳኑ በደረቅ ምላጭ – በባልጩት – አይለጫጭም ነበር፡፡ ብቻ አነዳዱን እንኳን ላያውቅበት፣ አበላሉንና አጠጣጡን ሳይቀር ላያውቅበት በአንዴ የከበርቴዎችን ቡድን ሲቀላቀል ትታዘባለህ – ከዘሩ ውጪ ደግሞ የምታውቅለት የተለዬ ሥራም ይሁን የንግድ ተሰጥዖ የለውም፡፡ አጥፍቶ ጠፊ የኢኮኖሚ አልቃኢዳዎችና አይሲሶች ወርረውን እንደትኋን እያንገበገቡን ናቸው፡፡

ሚሊዮንን ዱሮ የማውቀው በሰው ስምነቱ ነበር፡፡ አሁን ግን በተለይ ወያኔዎች ጢባጢቤ የሚጫወቱበት የብር መጠን መግለጫ ሆኖኣል፡፡ ባለፈው ሰሞን የጎላጉል ሕንፃ ባለቤት ለአንድ ጨረታ ይቀርባል አሉ፡፡ ከዚያም ባንክ የመሠከረለት ቢያንስ ሦስት ሚሊዮን ብር የሚደርስ ተቀማጭ ገንዘብ እንዳለው የሚያሳይ ማስረጃ እንዲያቀርብ ይጠየቃል፡፡ ያ ወያኔ – እንዳትደነግጡ – ከአንድ ባንክ ብቻ ያመጣው የባንክ ደብተር 350 ሚሊዮን ብር ይነበብበታል፡፡ ይህቺ እንግዲህ ጥቂቷ ናት፡፡ ወያኔዎች ወሬያቸው ሚሊዮንንም አልፎ ቢሊዮን ከገባ ቆይተዋል፡፡ እኛ ለምደነዋል፡፡ የኔን ኪስ ሸረሪት ያደራበታል፤ የነሱን የባንክ ደብተር ዶላርና ብር ይዝመነመንበታል፡፡ ሆዳም ማይም ሲገን እንዲህ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ጉዷ ፈላ፡፡ ኢትዮጵያውያን ጉዳችን ተንተከተከ፡፡ ወያኔዎች መሬቱንም፣ የመንግሥትን የገቢ ምንጭም፣ የሀብት መገኛ የኢኮኖሚ አውታሮችንም ጥርግርግ አድርገው ለራሳቸው ወስደው ሌላውን ሙልጭ አውጥተውታል፡፡ አዲስ አበባ የትም ግባ ሕንፃና ቪላው በአብዛኛው የትግሬ ወያኔዎች ነው፡፡ ከጠቅላላው የሀገሪቱ የሕዝብ ቁጥር ስድስት መቶኛ የሚሆነው ማኅበረሰብ በምን ምትሃትና ተዓምር ይህን ሁሉ የሀገርና የሕዝብ ሀብት በ25 ዓመታት ውስጥ ሊቆጣጠር እንደቻለ ሲያስቡት ያስደነግጣል፡፡ ሆቴሉ፣ ሱፐርማርኬቱ፣ ነዳጅ ማደያው፣ ባንኩና ኢንሹንሱ፣ ኮንዶምኒየሙ፣ ሪል ኢስቴቱ፣ መስጂዱ፣ ቤተስኪያኑ፣ የመንግሥት ሥልጣንና የጥቅም ቦታዎች ሁሉ… ምን አለፋችሁ … ኢትዮጵያ እንዳለች በወያኔ ተይዛ ሌላው መለመላውን ቀርቶላችኋል – መለመላውን፡፡ ምን ዓይነት ጉድ ነው? እነዚህ ሰዎች ሌላው ቢቀር ፈጣሪን ረሱት ማለት ይሆን? ይህ የአሁን አልጠግብ ባይነት ወደፊት ሲያስታውካቸው/ ሲያስመልሳቸው እንደሚያድር ጠፍቷቸው ነው ልበል? የዶሮን የሚያህል አንጎል ያለው አንድ ትንሽ ሰው እንኳ የዚህን አፀያፊ ተግባራቸውን የዞረ ድምር ማሰብ አያቅተውም፡፡ ምን ዓይነት ጥርሱን ያገጠጠ ገብጋባነትና ስስታምነት ነው? እንዴ? ወያኔን ያጀበ ትግሬ በልቶ ሲያድር ሌላው በርሀብ ይለቅ ብሎ ያወጀው የየትኛው ሰማይ አዛዥ ነው? ኧረ እየተስተዋለ ይሁን! ኧረ አሁንና ዛሬ በ11ኛው ሰዓት ላይም ቢሆን እናንት ወያኔዎች ሶበር በሉ – በሆድ እያሰባችሁ ዘመነ መንግሥታችሁን ትጨርሱት? አንጎላችሁ እንዲሠራ በቻይና አኩምፓንክቸርም ቢሆን ወጋ ወጋ አድርጉት፤ አኩፕሬዠርንም ጨምሩበትና ዓይነ ኅሊናችሁን አሸት አድርጉ – ምናልባት የምትሠሩት ግፍ የሚያስከትልባችሁ የኋላ ጠንቅ ቢገለጥላችሁ፡፡ አሁን በተዘረፈ ሀብት ስለጠገባችሁና አእምሯችሁን የጥጋብ ሞራ ስለሸፈነባችሁ ያላችሁ ይመስላችኋል እንጂ ሞታችኋል እኮ፡፡ “ከገዳይና ከሟች ማንኛቸው ናቸው የሞቱ?” የሚለውን ፍልስፍና ነክ ጥያቄ ደግሞ ለጥቂት ጊዜ አመንዥኳት፡፡ ያኔ እኛን ገደልን ብላችሁ በባዶ ሜዳ ከምትፎክሩት ከእናንተና በእናንተ “ከተገደልነው” ከኛ ማንኛችን እንደሞትን ታውቃላችሁ፡፡ ከዚህ ቂልነታችሁ አሁኑኑ ካልባነናችሁና ወደሰውነት ደረጃ ካተመለሳች የምትሰምጡበት አዘቅት ከቬርሙዳም የጠለቀ ነው፡፡ ይህን አውነት መናገር ነቢይነትን አይጠይቅም – ሦስተኛዋን ዐይን ገርበብ ማድረግ ብቻ በቂ ነው፤ ያ ዐይን ደግሞ ጨፍናቸሁት ወይም አፍርጣችሁ ጥላችሁት ይሆናል እንጂ እናንተም ጋ አለ፡፡ ከሰው ማሕጸን ነዋ የተገኛችሁት!

ሙስና፡፡ ይህችን ሀገር – ኢትዮጵያን – መቀመቅ እየከተታት ያለው ሌላው ነገር – ከዘረኝነቱ ቀጥሎ – ሙስና ነው፡፡ ሙስና ብሎ መጥራቱም ያንሰዋል፡፡ ለሀገራችን የሙስና ደረጃ ይህ የሦስት ፊደላት ቅምር – ሙስና – የሚል ቃል አይመጥነውም፡፡ ሙስና እግር አውጥቶ ሲሄድ የሚታየው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ሙስና ግም ነው፤ ግማቱ ደግሞ አይል ነው፡፡ ሰውን ወደ ጅብነት የሚለውጥ ክርፋት፡፡ እንዴት እንደምንጸዳ እግዜር ይወቅ፡፡

አንድም ሥራ – በተለይ የመንግሥት ሥራ – ካለሙስና አይሠራም፡፡ ሙስና ውስጥ የማይገባ ሰው በመንግሥት መሥሪያ ቤት ሥርፋ የለውም – ሥርዓቱ ይተፋዋል፡፡ ለምን ቢባል – ሙሰኞችን ያደናቅፋልና፡፡ አብረህ ካልበላህ ያጠፉሃል- እንዲያውም ብሶ በሙስና ሲከሱህ አያፍሩም፡፡

የዱሮው ሙስና ይሉኝታ ነበረው፡፡ የዱሮው ሙስና በሀገር ፍቅር ስሜት የታሸ ነበር – ብዙም አይጨክንም፡፡ ለምሣሌ መቶ ብር ቢወጣ አምስቷ ወይ ስድስቷ ብር ነበረች በአዩኝ አላዩኝና በልመና በሚገኝ ሰነድ የምትሰረቀው፡፡ አሁን ግን ያ ዓይነቱ ሙስና የፋራ ነው፡፡ እውነት ነው የምላችሁ – በዚህ ዘመን ሙስናው ከ60 እና ከ70 በመቶ በላይ ነው፡፡ በገንዘባዊ ምሣሌ ቢገለጽ – አንድ የመንግሥት ፕሮጀክት በመቶ ሚሊዮን ሊሠራ ነው  እንበል፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 60 እና 70 ሚሊዮኑ ብር ከላይ እስከታች ያሉ ባለሥልጣናት እንደየደረጃቸው ይቃረጡትና ቀሪው 40 ወይ 30 ሚሊዮን እንደነገሩ ለዚያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያነት ይውላል – ያውም ከተሠራ ነው –  ገንዘቡ ተበልቶ ከናካቴው ላይሠራም ይችላል፡፡ ጠያቂ የለም፤ ተጠያቂም የለም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሌባና ሙሰኛ ነውና፡፡

በዚያ ላይ የጥራት ነገር አይነሳ፡፡ ማን ስለሀገር ይጨነቃል? ማን ስለነገው ትውልድ ያስባል? የጨረባ ተዝካር፡፡ ያባትህ አገር ሲወረር አብረህ ውረር፡፡ የሚታየው ዛሬ መክበር እንጂ የነገ የሀገሪቱ ዕጣ ፋንታ እንጦርጦስ መውረድ መሆኑ ለማንም ደንታ አይደለም፡፡ የምንገርም ዜጎች ፈልቀናል፡፡ መንገዱ ከመመረቁ ይቦዳደሳል፤ ሕንፃው ከመመረቁ ይሰነጣጠቃል፤ ማሽኑ ከመተከሉ ኃይሉ ይዝላል፤ “ምሁሩ” ከመመረቁ “ሀሁ”ን ከ”ለሉ”ና ትንሹዋን “a,b,c,d” ከትልቁ  “A,B,C.D” መለየት ያቅተዋል፤ የህክምና ዶክተሩ ከመመረቁ የህክምና መርፌን ከልበስ መስፊያ መርፌ መለየት ይሳነዋል፤ ወይ ጉዳችን – ጉዳችን እኮ ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ ምን ይዋጠን? “What swallow us?” ብዬ በ‹ቆንጆ› እንግሊዝኛ ባስፈግጋችሁስ ምን ይለኛል?

ሙስና ባህል ሆኖኣል፡፡ የማይሞስን የድህነቱ ጎርፍ አጥለቅልቆት እንደሚሞት ይታመናል፡፡ ስለሆነም አለመሞሰን የሚያስመሰግን ሳይሆን የሚያሰድብ እየሆነ ነው፡፡ አዲስ ማኅበራዊ “ኖርም” እያዳበርን ነው፡፡ የምሥራች!

ሙስና በዓለማዊ ብቻም ሣይሆን በእምነት ቦታዎችም የእስትንፋስ ያህል ነው፡፡ ከአንድ አነስተኛ ደብር ወደ ትልቅ ደብር ለመዛወር ለሀገረ ስብከቱ ባለሥልጣናት እስከ 80 ሺህ ብር ጉቦ እንደሚከፈል ሰምቻለሁ፡፡ አለበለዚያ በዚያው አነስተኛ ደብር እያከኩ መኖር ነው፡፡ ብዙ የሙስና ሥራ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲካሄድ እግዜሩም ታዝቦ ቁጭ እንጂ አንዳችም የሚፈጠርቅ መቅሰፍት አይልክም – ዱሮ ግን ቀልድ የለም፤ ቤቱን የሚደፍርን ባለጌ ካህን በመብረቅ ይሰነጥቀው ነበር – ዛሬ ግን ስንቱን ፈጥርቄ እዘልቀዋለሁ ብሎ ሳይን አይቀርም ትቶታል – ሒሣባቸውን ባንዴ እንዲያወራርዱ ፈቃዱ የሆነ ይመስለኛል፡፡ ምን ያለ ዘመን ውስጥ ገባን ግን ጎበዝ! (መሴሰኑን፣ መዋሸቱን፣ ሙዳየ ምጽዋት መገልበጡን፣ የሰው ሚስት ማባለጉን… ይህን ይህን “ተራ ወንጀል”ና ኃጢኣትማ ተውት – ሆድ ይፍጀው)፡፡ እንደሀገርም እንደማኅበረሰብም በቁም ሞተናል፡፡

እግዚአብሔር ካልተፈራ፣ የሀገር ፍቅር ስሜት ከጠፋ፣ ሰብኣዊነት ተንጠፍጥፎ ካለቀ፣ የሞራልና የባህል ክሮች ከተበጣጠሱ ሰው ዐውሬ ነው – ከዐውሬም የባሰ እንዲያውም፡፡ ዕውቀት ደግሞ ብቻውን ምንም አይሠራም፡፡ ማወቅማ ከፓትርያርካችን የበለጠ ዐዋቂ አለ እንዴ? የእግዚአብሔርን ቤት የሚደፍር እኮ የሚያውቃት ነው – ሊቀ ሣጥናኤል እኮ ከቤተኛነትም አልፎ የመላእክት አለቃ ነበር፡፡ ግን ማወቅ ብቻውንና በራሱ ዋጋ ስለሌለው ይህ መልአክ ከመረገምና የጨለማውን መንግሥት ከመውረስ – ወርሶም ርዕሰ-መስተዳድሩ ከመሆን – አላመለጠም፡፡

እኛም መሀገር ውስጥ ብዙ መኳንንትና መሣፍንት እንዲሁም በሃይማኖቱም ረገድ በርካታ ካህናትና ሊቃነ ጳጳሣት የዚሁ የጨለማው መንግሥት አጋፋሪዎች ናቸው – በጊዜው ንስሃ ካልገቡ፡፡ ወዮ ለቀኑ በሉ! ቀኑ ደርሷል፡፡ ምርትና ግርድ ሊለይ፣ ንፋሹ በሲዖላዊ የዘላለም እሳት ሊቃጠል ጊዜዋ ቀርባለች፡፡ ያወቀ ዳነ፤ ያላወቀ አልዳነም፡፡ ይብላኝ አእምሯቸው ለደነበሸ ትግሬ ወያኔዎችና አጫፋሪዎቻቸው፡፡ … ሰላም እጆቿን ወደፈጣሪዋ ለዘረጋችው ኢትዮጵያ፡፡

ለአስተምህሯዊ አስተያየት – nzeleke35@gmail.com

ዞን ዘጠኞችና ጋዜጠኞች በተገኙበት የሰማያዊ ፓርቲ መሰረታዊ መልሶችን ሰጠ – የሚሊዮኖች ድምጽ

$
0
0

“መሰረታዊ መልሶች!” በሚል የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢና የሕግ ባለሞያው አቶ ይድነቃቸው ከበደ ዛሬ የካቲቲ 19 ቀን ፓርቲው በውስጣዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጽ/ቤቱ  ስላደረገ ገለጻ  ማብራሪይ ሰጥተዋል።

የቀድሞ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል የፓርቲው የበላይ አካል የሆነውን የጠቅላላ ጉባዬ ውሳኔ አልቀበልም በማለት በተለያዩ ገፆች ላይ በመውጣት፣ “አሁንም የፓርቲው ሊቀመንበር እኔ ነኝ” እያሉ  የፓርቲውን እባላትና ደጋፊዎች ግራ በማጋባት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ከዛሬ ነገ የፓርቲውን ደንብ አክብረው ወደትግል እንዲቀላቀሉ ቢጠበቁም፣ በብዙ ወገኖችም ትልቅ ተማጽኖ ቢደረግላቸውም፣  “ሊቀመንበር ካልሆንኩኝ ትግሉ ዋጋ የለውም” በማለት ፣ በግል የሚያውቁዋቸዉን ጋዜጠኞች ጋር በመደወልና  ቃለምልልስ በማድረግ  የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን “ወያኔዎች ናቸው” ብሎ በመክሰስ አፍራሽ ተግባራታ ላይ እየተሰማሩ ነው።

“ነገሮች  በሂደት ሊሰተካከሉ ይችላሉ” በሚል ተስፋ ዝምታን መርጦ የነበረው የፓርቲው አመራር በድርጅቱ የዉስጥ ጉዳይ ያለውን ብዥታ ለማጥራት ነበር ዛሬ ገለጻዎች ያደረገው። የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን፣ እንደ ዶር ያእቆብ ሃይለማሪያም ያሉ አንጋፋ ኢትዮጵያዉያን የተገኙ ሲሆን ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችን ግልጽነት ባለው መልኩ ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል።

ኢንጂነር ይልቃል አሁን ካለው አመራር ጋር “ማንም አባል” የለም ብለው ከሰው የነበረ ቢሆንም በዛሬ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት፣ እንደ አቶ ይድነቃቸው ከበደ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ፣ አቶ አበራ ገብሩ የኦዲት ኮሚሽን ሰብሳቢ፣ ብሌን መስፍን፣ ሃና ዋለልኝ፣ አበባ አካሉ፣  ሰለሞን ተሰማ፣ አሮን ሰይፉ ..የመሳሰሉ ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተዋል።

በዛሬው ስብሰባ ዙሪያ  የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸው የሚከተለውን አቅርበዋል፡
=============================
በዛሬው ዕለት፣ የካቲት 19 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ፤ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የፓርቲው ውስጣዊ ጉዳይ አስመልክቶ ገለፃ ተደረገ።

” ብዙ እየተባለ እና እየተወራ ነው። በሚነገረው ልክ ምላሽ እንስጥ ብንል ትላንት የነበርን ወዳጅነት እና ጓዳዊ ግንኙነት ላለማበላሽት ፣ምን አልባትም አሁን ላይ መለስ ብለን የተሻለ እድል ካላ በሚል የቀናነት መንፈስ በዝምታ ነገሮችን ለማየት ሞክረናል። ይሁን እንጂ የመጀመሪያ ቃል ኪዳናችን (የጋራ አመራር፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት ከምንም በላይ ለፓርቲ ደንብ እና መርህ መገዛት) ሰብረው፤ ባልሆነው ነገር ብዙ እየተፃፈ እና እየተባለ ነው። የሚባለው እና የሚፃፈው ነገር ከዚህ በበለጠ ሰዎችን ማሳሳት ስለሌለበት ፤ በፓርቲያችን ውስጣዊ ጉዳይ ከዚህ በኋላ ተገቢውን ምላሽ እንሰጣለን።” በማለት አቶ የሺዋስ አሰፋ ንግግር አድርጓል ።

በእለቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጦች ፣ የፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት ፣የኦዲት እና ምርመራ ኮሚሽን ተጠሪዎች ፣የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና የሽምግልና ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ተገኝቷል።

በነበረው ገለፃ እና ማብራሪያ ሰፊ ሽፋን አግኝቶ ውይይት የተደረገበት፣
አቶ የሺዋስ አሰፋ በሊቀመንበርነት የተመረጡበት የጠቅላላ ጉባኤ ኮረም (ምላዕተ ጉባኤ) ፣ ለጉባኤው ወጪ የተደረገው ገንዝብ ምንጭ ፣ በፓርቲው ውስጥ ይታይ የነበረው የገንዘብ ምዝበራ በተመለከተ ፣ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ለመፍታት በብሔራዊ ምክር ቤቱ ይደረግ የነበረው ጥረት እና መሰል ጉዳዮችን አስመልክቶ ማብራሪያ እና ገለፃ የተደረገ ሲሆን። በዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ይመራ የነበረው የአሸማጋይ ቡድን በመገኘት ጥያቄዎችን በመጠየቅ ተሳትፎ አድርጓል ።

ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ከገለፃው እና ከማብራሪያው እንዲሁም አሉን ባሉን መረጃ መሠረት ፤ጥያቄዎች እና አሰተያየታቸው ያቀረቡ ሲሆን ፤ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ምላሽ ሰጥቷል። ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች የቀረበላቸውን ገለፃ መሠረት በማድረግ የራሳቸውን ግንዛቤ እንዳገኙ ለማወቅ ተችሏል ።

በተጨማሪ በመረጃ እና በእውነት ላይ የተመሰረት ሃቅ በመሞርከዝ፣ ከዚህ በኋል የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አስፈላጊ ናቸው ብሎ የሚያምናቸውን መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በእለቱ ተገልፃል።

“አንቱ አጤ ሚኒሊክ ምን ያሉት ሰው ነዎት ?… ” – አሌክስ አብርሃም

$
0
0

የዛሬ አመት በዚህ ወቅት ነው …..አዳራሹ ካፍ እስከገደፉ ግጥም ብሎ በተሰብሳቢወች ተሞልቷል ! የኢሃዴግ ወጣቶች ሊግ ..የሴቶች ሊግ …ጥቃቅንና አነስተኛ ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪ የቀረ የለም ! ለዩኒቨርስቲ ተማሪወች ከሚሰጠው ስልጠና ጎን ለጎን የአገሪቱን ‹‹ነባራዊ ሁኔታ›› ለነዋሪውም ለማስገንዘብ የተዘጋጀ የሶስት ቀን የመወያያ መድረክ ነው … አዳራሹ ዙሪያውን የአክሱም የላሊበላ ምስሎች ተስለውበታል በቀኝ በኩል የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ፎቶ በትልቁ ይታያል በስተግራ የአፄወቹ ምስል ተደርድሯል የአፄ ቴውድሮስ የአፀጼ ሚኒሊክና የአፄ ይኋንስ . . .

ስብሰባው ሶስተኛ ቀኑ ነበር ….ሰብሳቢው እንዳለፉት ሁለት ቀናት ሁሉ ዛሬም እንዲህ ሲል ቀጠለ ‹‹ እና ባለፉት ሁለት ቀናት በስፋት ታሪካችንን እንደዳሰስነው አሁን ላለው የብሄረሰቦች እርስ በእርስ መቃቃር መነሻው አፄ ሚኒሊክ ነበሩ …. አሁን ከኤርትራ ጋር ላለው አንዳንድ ተገቢ ያልሆነ የድንበርና ሌላም ውዝግብም ያው መነሻው የአጼው ስርአት ነበር … ›› እያለ ለድፍን ሶስት ቀናት የአፄ ሚኒሊክን ድክመት ደካማ አስተዳደር እና ፀረ ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ ያወገዘበትን ትንታኔ አገባደደ …… ከዛም ህዝቡ ጥያቄ ካለው እንዲያቀርብ እድል ሰጠ!

በስብሰባው ላይ የጥንቱ ሲወገዝ እና ሲገዘት የአሁኑ አገዛዝ የፅድቅ ዘይት ሲቀባና ሲሞካሽ ግራ ከገባቸው ታዳሚወች መካከል አንዲት እናት ከወንበራቸው ተነስተው በቀጥታ ወደሚኒሊክ ፎቶ ሄዱና አዳራሹን በሚያናውጥ ድምፅ ሚኒሊክን በጥያቄ አፋጠጧቸው

‹‹አንቱ አጤ ሚኒሊክ …. አሉ የሚኒሊክ ፎቶ ላይ አፍጥጠው …..እንግዲህ የዚች አገር ችግር ሁሉ መነሻ እርሰዎ ከሆኑ …ጥያቄ አለኝ ለእርሰዎ ! ምን ያሉት ሰው ነዎት ግን ?
ለምንድን ነው ላባችንን ጠብ አድርገን ግብር በምንከፍልበት አገር መብራት በየቀኑ የሚያጠፉብን ?
አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. ለምንድነው የስልክ ኔትወርኩን የማያስተካክሉልን ‹‹ያለዎት ቀሪ ሂሳብ ›› የምትለው እቴጌ ጣይቱ ናት ?›› ለምን አይመክሩልንም …?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. የውሃ ማማ በምትባል አገራችን ውሃ እንዲህ የሚያጠፉብን ለምንድን ነው ?
አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….ለምንድነው ልጆቻችን ስራ አጥ እንዲሆኑ ያደረጉብን? ያሰሩብን ”””’

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ””’እርሰዎና ጋሻጃግሬዎቾ በአውቶሞቢል እየፈሰሱ ስለምን ህዝብዎት በትራንስፖርት እጦት ፍዳውን እንዲበላ ፈረዱ ?ማንስ ነው ተጠያቂው?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….ለምንድነው የትምርት ጥራቱ ከእጅ አይሻል ዶማ የሆነው ለምን ልጆቻችንን በነቀዘ ቲወሪ ያነቅዙብናል? ››

አንቱ አጤ ሚኒሊክ …..ለምን ምርጫ በደረሰ ቁጥር አገር ምድሩን ያዋክቡታል ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ …. ለምን ሃሳባቸውን በነፃነት የሚገልፁትን ሁሉ አሸባሪ እያሉ እስር ቤት ይወረውራሉ? ያስደበድባሉ ያስገድላሉ ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. ለምን የህዝቡን የሰቆቃ ኑሮ በመስተዋት ህንፃወች በቀለበት መንገዶች ግርጌ ሊደብቁ ይፍገመገማሉ ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. ለምን መርፌ ያነሱ ሙሰኞችን እያሰሩና ከበሮ እያስደቁ በሬ የሚጎትቱትን በዝምታ ያልፋሉ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ …..ለምን በብሔራዊ ቴሌፊዥናችን ብሔራዊ ውሸት ያልኖርነውን ዝባዝንኬ እየተረቱ ያደነቁሩናል ?ለምን ብሔርን ከብሔር የሚያጋጭ የውሸት ታሪክ ይፈጥራሉ ህዝቦችን የሚያቃቅር ሀውልት ያቆማሉ ….ንፁህ ውሃ ያጣ ህዝብ ከጥላቻ ሃውልት ንፁህ ውሃ ይቅዳ ብለው ነው ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ ….. ለምን ፍትሃዊ ምርጫ አይኖርም … እስከመቸ ከዚህ ሁሉ ችግሮዎት ጋር ዙፋንዎት ላይ ይቆያሉ ?
አንቱ አጤ ሚኒሊክ ……እስከመቸ የከበረ ታሪክን በመንደር ቱሪናፋ ሲያራክሱና ዝቅ ሲያደርጉ ይኖራሉ ?

አንቱ አጤ ሚኒሊክ …..እርሰዎ የጀመሩትን እናስቀጥላለን ! በቃ ለመጭዋም ምርጫ እንመርጠዎታለን አሁን ሰብስበው አይነዝንዙን ….ሲሉ እንደእብድ ጮሁ

ሰብሳቢው
‹‹ሴትዮ ….. አካሄድ አካሄድ ……ከአጀንዳ ወጥተዋል›› ሲል ጮኸ
‹‹ አሃ አጀንዳው የሚኒሊክ መስሎኝ …አካሄድ የምትለኝ ታዲያ ወዴት ሂደን እንጩህ .›› ብለው ቀጠሉ ,,,,
አንቱ አጤ ሚኒሊክ ,,,,,,,,,,

ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን ይሁን እንጂ የትግራይ ባንዳዎችማ ለጣሊያን ባርነት አሳልፈው ሰተውን ነበር፣ – ከ ደረጀ ተፈራ

$
0
0
አጼ ዮሐንስ 4ኛ ከሞቱ በኋላ ልጆቻቸው አባታቸው ከእንግሊዝ ጋር በገቡት የሂወት ውል ምጽዋ ላይ እንግሊዞች የተከሉትን ጣሊያን የሚባል ወራሪ እንደ መንቀል ትኩረታቸው ጥቅምና ስልጣን ላይ ሆነ። ዮሐንስ ከእንግሊዝ ጋር በመመሳጠር ለአጼ ቴዎድሮስ ሞት ምክንያት እንደሆኑ ሁሉ ልጆቻቸውም በተራቸው ከጣሊያን ጋር በሚስጥር በመደራደር (Treaty በመፈራረም) ምኒሊክን አስገድለው ለመንገስ ይዶልቱ ነበር።
በልጅ ያልታደሉት አጼ ዮሐንስ የፓለቲካ ብስለት ይጉደላቸው፣ ግራ ቀኙን የማያስተውሉ ጀብደኛ ይሁኑ እንጂ በተዋጊነት አይታሙም። ልጆቻቸው ግን ከምንም ውስጥ የሌሉ ከንቱዎች ነበሩ። የሚገርመው ከአባታቸው ብሰው ለፈረንጅ በእጥፍ አጎብዳጅ ሆኑ። ሁሉን ነገር ትተውት ዋናው ዓላማቸው ከጣሊያን ጋር አብረን ምኒልክን አስወግደን ስልጣን እንያዝ የሚል ብቻ ሆነ። በመሆኑና ምኒልክ ይህን ተናገረ ይህን ሊያደርግ ነው በሚል የአሉባልታ ወሬ ተጠመዱ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት በፊት ኢትዮጵያን ከድተው እጃቸውን ለጣሊያን ሰተው ነበር ነገር ግን ከጣሊያኖች የሚፈልጉትን ማግኘት ስላልቻሉ ተመልሰው በመምጣት አጼ ምኒልክን ይቅርታ ጠየቁ። በይቅርታ የሚያምኑት ደጉ ንጉስ ምኒሊክም ይቅርታ አደረጉላቸው። በአድዋው ጦርነት ከጠላት ወገን ነው የመጣው ብለው ሳይጠራጠሯቸው በአድዋው ጦርነት ላይ እንዲሳተፉ አደረጓቸው። “ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይተውም” እንደሚባለው ከአድዋ ጦርነት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ንጉሱን ከድተው ሸፈቱ ይሁንና ንጉሱ ማርከው በማምጣት (መግደል ሲችሉ) በሸዋ አንኮበር የቁም እስረኛ አድርገው አስቀመጧቸው። ባጠቃላይ እነ ራስ መንገሻ ዮሐንስ በውትድርናውም ሆነ በዲፕሎማሲው ምንም ዓይነት ብቃት ያልነበራቸውም፣ በነገር (conspiracy) የተካኑ  ከንቱ ፍጥረት ነበሩ።
ዮሐንስ ልጆች ለጣሊያንና ለእንግሊዝ የነበራቸውን አጎብዳጅነት ከእነሱም አልፎ ወደ አሽከሮቻቸውና ወደ ተራው የትሬ ህዝብ እንደ ጉንፋን በሽታ በመተላለፉ በአድዋ ጦርነት ወቅት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የትግሬ ቅጥረኛ ወታደሮች መፈጠር ቻሉ። በመሆኑም ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ሲወሩ በርካታ ቅጥረኛ የትግሬ ተዋጊዎችን (Askaris) ከጎናቸው አሰልፈው በኢትዮጵያ አርበኞች ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት ማድረሳቸውን ታሪክ ይነግረናል።
የባንዳ ልጅ ባንዳ ነውና ይህ ለፈረንጅ ማጎብደድ በዘር እንደሚተላለፍ ተላላፊ ደዌ ከአባት ወደ ልጅ ሲተላለፍ ቆይቶ የአድዋ ጦርነት ከተደረገ ከ40 ዓመት በኋላ የአጼ ዮሐንስ የልጅ ልጅ የሆነው ኃ/ስላሴ ጉግሳ 20ሺህ በስሩ የነበሩትን ወታደሮች ይዞ ለጣሊያን እጁን ሰጠ (ገባ)። እጁን በመስጠት ሳያበቃ በርካታ የትግሬ መሳፍንትን ወደ ጣሊያን እንዲኮበልሉ በማድረግና የኢትዮጵያን አርበኞች በመውጋቱ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል።
አሁን ባለንበት ዓለም በሰለጠነበት ጊዜ ወደ ኋላ ሄደው ቀኝ ገዢዎች አፍሪካን ለመግዛት ይጠቀሙበት የነበረውን የከፋፍለህ ግዛ ፓሊሲያቸው ማስፈጸሚያ ስልት ሆኖ ሲያገለግላቸው የነበረውን Tribalism Politics  የጣሊያን ባንዳ ልጆች የሆኑት ወያኔ ትግሬዎች በብሔር ብሔረሰብ ስም እንደ አሜባ ቅርጻቸውን ቀይረው በመምጣት ጣሊያንንና ባንዳ አባቶቻቸውን አነባብሮ የመታውን የኢትዮጵያን ህዝብ እርስ በርሱ በማጋጨት ቂማቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።
ከፋሽስት ጣሊያን ጎን ተሰልፈው አርበኞቻችንን ሲገሉ የነበሩት የባንዳ ልጆች ዛሬ በለስ ቀንቷቸው ስልጣን ቢይዙ ጀግኖች አባቶቻችን የተሰውለትን ሰንደቅ አላማ ጨርቅ ነው፣ አክሱም ለወላይታው ምኑ ነው በማለትና፣ የኢትዮጵን ታሪክ የሚጀምረው ጣሊያን ከተሸነፈበት ከአድዋ ድል በኋላ እንደሆነ ያህል በመቶ አመት ገድበውና የሃገራችንን ታሪክ በማጠልሸት፣ የጥቁር ህዝብ ኩራት የሆኑትን ታላቁን የአድዋውን ጀግና ንጉስ አጼ ምኒልክንና ከእሳቸው ጎን የዘመቱትን ስም ጥር ጀግኖቻችንን በፈጠራ ወሬ ስማቸውን በማጥፋት ላይ ይገኛሉ። ይህ የሚያሳየው ወያኔና ደጋፊዎቹ በዘር የተላለፈ የማይለቅ በባንዳነት ደዌ የተለከፉ ድኩማን መሆናቸውን ነው።
ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን ይሁንና የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የጉራጌ፣ የሃድያ፣ የሲዳማ፣ የከንባታ፣ ባጠቃላይ ከመላው የሃገራችን ክፍል የዘመቱ አርበኛ አባቶቻችን የሃገራችንን አረንጎዴ፣ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ አንግበው በዱር በገደሉ በ5ቱ የአርበኞች የትግል ዓመታት ተንከራተው ነጻ ባያወጡን ኖሮ ትግሬዎችማ ለጣሊያን ባርነት አሳልፈው ሰተውን ነበር።
ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን!
አሜን!

ሰማያዊ ፓርቲ መሰንጠቅ አልገጠመኝም አለ

$
0
0

Yilkal Getnet, ousted Blue Party leader

ዋዜማ ራዲዮ- በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ያገኘው አዲሱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር በፓርቲ ውስጥ መስንጠቅ አለመከሰቱን ይልቁንም ፓርቲው በዲስፕሊንና በምዝበራ ጥፋተኛ ያላቸው የአመራር አባላት ላይ እርምጃ የወሰደበት እንደነበረ አስታወቀ።
ለፓርቲውና ለቀድሞ አመራሮች ክብር ሲባል ጉዳዩን በዝምታ ይዞት መቆየቱን የገለፀው አዲሲ የፓርቲው አመራር ችግሩን በፓርቲው ውስጥ ለመፍታት የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ጉዳዩ ወደ አደባባይ መውጣቱንና በአሁኑ ወቅት ፓርቲው በአብላጫው የቀድሞ አመራር አባላትን ይዞ ስራ መቀጠሉን ገልጿል። ዝርዝር ዘገባው የሚከተለው ነው።

የካቲት 8/2009 በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተቸረው የሰማያዊ ፓርቲ አዲሱ ሥራ አስፈፃሚ በዛሬው ዕለት (የካቲት 19/2009) በጽ/ቤቱ በሰጠው የፓርቲው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ፣ የፓርቲው የቀድሞ የፓርቲ መሥራችና የሥራ አስፈፃሚ አባላት የነበሩ፣ እንዲሁም አሁን የብሔራዊ ምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ጌታነህ ባልቻ “ተከስቶ የነበረው ችግር መከፋፈል ሊባል አይችልም” በማለት አስተባብለዋል። “ጥቂት ሰዎች በዲሲፕሊን እና በንብረት ምዝበራ ቢሰናበቱም፣ አሁንም 37 ቋሚ እና 13 ጊዜያዊ አባላት ያሉት ብሔራዊ ምክር ቤት አለ። ሥራ አስፈፃሚውም የጠቅላላውን ጉባዔ እና የምርጫ ቦርድን ዕውቅና አግኝቷል” ብለዋል።

በአዲሱ የፓርቲው ሊቀ መንበር አጭር የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው የማብራሪያ መድረክ፣ የተለያዩ ሰነዶችን በማቅረብ በቀድሞው ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል እና ደጋፊዎቻቸው፣ እንዲሁም በአቶ የሺዋስ አሰፋ የሚመራው አዲሱ ሥራ አስፈፃሚ መካከል የነበረው ችግር በቀድሞው ሥራ አስፈፃሚ ድክመት የተፈጠረ እና አሁን ግን እልባት ያገኘ መሆኑን ለማስረዳት ሞክሯል።

 

አቶ የሺዋስ በመክፈቻ ንግግራቸው “እስካሁን ዝም ያልነው፣ አንደኛ የሰውን ክብር ላለመንካት እና ሁለተኛ የመታረቅ ትንሽ ዕድል ካለ ብለን ነበር።” ብለዋል። አቶ ጌታነህም የቀድሞው ሊቀመንበር እና ሌሎች የተባረሩ አባላቱ ለሠላማዊ ትግሉ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ግምት ውስጥ በማስገባት ፓርቲው ጉዳዩን ይፋ ከማድረግ መቆጠቡን ገልጸዋል።

 

Yeshiwas Assafa, new leader of Blue Party

አቶ ጌታነህ ባልቻ “የችግሩ መነሻ የፓርቲው የቀድሞ ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት እና ሌሎቹም የድርጅቱን ንብረት መመዝበራቸው ነው” ብለዋል። “የንብረት መመዝበሩ ጥያቄ እንደተፈጠረ የሥነ ስርዓት አጣሪ ኮሚቴ ተዋቅሮ ጉዳዩን በመመርመር ያረጋገጠ ሲሆን፣ በዚሁ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ ነባሩን ሊቀመንበር በማውረድ አዲስ ምርጫ በማካሔድ አቶ የሺዋስ የሊቀ መንበርነቱን ቦታ በውስጠ ደንቡ መሠረት ወስደዋል” ብለዋል። አቶ የሺዋስም በመግቢያ ንግግራቸው ከሊቀ መንበር በስተቀር ቀሪው የሥራ አስፈፃሚው ኃላፊዎች ባሉበት መቀጠላቸውን አስረድተዋል።

 

ከፓርቲው አስራ አምስት መስራች አባላት መካከል አንዱ ብቻ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የቀድሞውን ሊቀመንበር ጨምሮ ሁለት ተጨማሪ መሥራች አባላት በሥነ ስርዓት ጉድለት በመታገዳቸው መሥራች ዐሥራ አንድ አባላት የፓርቲውን ሥራዎች ለማከናወን በሚጥሩበት ሰዓት ፓርቲው እንደተሰነጠቀ መነገሩ ትክክል አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል።

የድርጅቱን ንብረት መዝብረዋል የተባሉት 5 ሰዎች በድርጅቱ ደንብ መሠረት ክስ የቀረበባቸው እና በደንቡ መሠረት የተከራከሩ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ጥፋተኛ መሆናቸው ሲበየን፣ አቶ ይልቃልን ጨምሮ በይቅርታና በቅጣት ለመታለፍ ያልፈቀዱት አራቱ ከአባልነት ሲሰናበቱ አቶ ጌታነህ ባልቻ ግን በቅጣት ታልፈው የአዲሱ የሥራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ቀጥለዋል።

የአጣሪው ኮሚቴ ገለልተኝነት፣ የተመዘበረው ንብረት ግምት፣ የጠቅላላ ጉባዔው ምልዓትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባላት ሲመልሱ የሥነ ስርዓት አጣሪ ኮሚቴው ሦስት አባላት በምክር ቤቱ የፀደቁ በመሆናቸው ገለልተኛ ናቸው ብለዋል። ተመዘበረ የተባለውን ገንዘብ ትክክለኛ መጠን ለመግለጽ በተደጋጋሚ ያመነቱት አቶ ጌታነህ፣ በመጨረሻ “ከመጀመሪያ ጀምሮ ከተደረጉት 3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪዎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ በሰነድ ሳይወራረድ የቀረ ነው” ብለዋል። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር አስቸጋሪ ገጽታ ምክንያት ለቅስቀሳ የሚታተሙ በራሪዎች እና ተመሳሳይ ወጪዎች የሦስተኛ ወገንን ደኅንነት ከመጠበቅ አንፃር ያለ ደረሰኝ ሊሠሩ እንደሚችሉ እና ችግሩ በዚህ ሳቢያ ተፈጥሮ እንደሆነ እና የአሠራር ክፍተት ካለ የተጠየቁት አቶ ጌታነህ፣ “እንደዚህ ዓይነት ወጪዎች በልዩ ቃለ ጉባኤ የሚፈፀምበት አሠራር አለን” በማለት የአሠራር ክፍተት ለምዝበራ እንዳላጋለጣቸው አስረድተዋል።

የጠቅላላ ጉባዔውን ምልዓት በተመለከተ በመተዳደሪያ ደንቡ የተወሰነ ቁጥር ባይኖርም ሰማያዊ ፓርቲ መዋቅሮቹን በዘጋባቸው ወረዳዎች ቁጥር ልክ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት እንደሚኖረውና በ2007 አቶ ይልቃል ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ በፀደቀው እና ከዚያ ጀምሮ ለ3 ዓመታት በሚያገለግለው 226 አባላት ያሉት ጠቅላላ ጉባዔ ዳግም ጥሪ ተደርጎ፣ 129 አባላት ተገኝተው ኮረም በመሙላቱ በተደረገው ምርጫ አቶ ይልቃል ወርደው አቶ የሺዋስ በምትካቸው ተመርጠዋል።

 

በአቶ ይልቃል እና ደጋፊዎቻቸው ከተነሱ ቅሬታዎች መካከል፣ የፓርቲው አባላት ያልሆኑ ሰዎች መገኘታቸው አግባብ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ አቶ የሺዋስ “ታዛቢ እንዲኖር በማለት ከቀድሞው አንድነት ፓርቲ፣ ከመኢአድ እንዲሁም ከምርጫ ቦርድ ታዛቢ ጋብዘናል። እነዚህ ግን በደምፅ ቆጠራው አልተሳተፉም። የአቶ ይልቃል ደጋፊ የነበሩ 13 ሰዎች ከ129ኙ በተጨማሪ ቢገኙም ጉባዔውን ለማስተጓጎል እንጂ ለመሳተፍ ፊርማቸውን ለማኖር ስላልፈቀዱ በጠቅላላው ጉባዔ ውሳኔ እንዲወጡ ተደርገዋል” በማለት ተሳታፊዎቹ የፈረሙበትን ሰነድ አሳይተዋል።

 

ጠቅላላ ጉባዔው የተካሔደው ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ ነው በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የተራገበውን ዜና ሲያስተባብሉም፣ አቶ ጌታነህ ሁለት ደብዳቤዎችን አቅርበዋል። የመጀመሪያው ከፓርቲው ለሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ሰጪ ጉባዔውን ለማካሔድ የተጠየቀበት ደብዳቤ ሲሆን፣ ሁለተኛው የሰሜን አሜሪካው ድጋፍ ሰጪ ድጋፍ ማድረጉን የገለጸበት እና ለአቶ ይልቃል ጌትነትም ግልባጭ የተወበት የኢሜይል መልዕክት ነው።

 

ከቀድሞው ሊቀ መንበር እና ደጋፊዎቻቸው ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት፣ በወቅቱ ከሁለት ዓመት እስር በኋላ በነጻ የተፈቱት አቶ የሺዋስ አሰፋ በግንቦት ወር 2008 ልዩነቱን በእርቅ ለመፍታት ንግግር ላይ የነበሩ መሆናቸውን አስታውሰው፣ በዚህ ውይይት መሐል ሊቀ መንበሩ አቶ ይልቃል ወደካናዳ መሔዳቸውን የውይይቱ አካላት እንደማንኛውም ሰው ከሚዲያ መስማታቸውን ተናግረዋል። የቀድሞውም፣ የአሁኑም ሥራ አስፈፃሚ ውስጥ በውጭ ጉዳይ ኃላፊነት የሚያገለግሉት አቶ አበበ አካሉም “እኔ እንኳን አቶ ይልቃል በፓርቲው ሥም ሊሔዱ ስለመሆናቸው ምንም መረጃ አልነበረኝም። ፓርቲው የግለሰብ ንብረት የሆነ ያክል ነበር። እኔ የማገለግለው የኢትዮጵያ ሕዝብን እንጂ የፓርቲውን ሊቀመንበር አይደለም” በማለት በምሬት ተናግረዋል።

የገንዘብ ምዝበራው አሁንም እንደቀጠለ የተናገሩት አቶ ጌታነህ፣ “በቅርቡ ከሰሜን አሜሪካ ደጋፊዎቻችን የተላከልን 7,600 ዶላር ድጋፍ አቶ ይልቃል እጅ ከገባ በኋላ ወደ ፓርቲው ገቢ አልተደረገም። ደጋፊዎቹም እውነቱን ሲያውቁ ለማስመለስ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካላቸውም” ብለዋል። “ከዚህም ውጪ ሌሎች ምዝበራዎች አሉ” ያሉት አቶ ጌታነህ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊወስዱት እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

የቀድሞ የፓርቲ መሪ ይልቃል ጌትነት ግን የአዲሲ አመራር እርምጃ ፓርቲውን ለማፍረስ የተቀነባበረና ባልታወቁ ሀይሎች የተቀነባበረ ሴራ ነው ሲሉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ላይ 12 የቀድሞ የፓርቲ አባላትን የያዘ ሁለት ኮሚቴ መመሥረቱ ተነግሯል። የአቶ ይልቃል ደጋፊዎች የምርጫ ቦርዱን ውሳኔ በፍርድ ቤት ሊሞግቱት ይችላሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የኮሚቴው አባል እና ከሦስት ወራት የማዕከላዊ እስር  በኋላ በቅርቡ የተፈቱት፣ የሕግ ባለሙያው አቶ አዲሱ ጌታነህ በትላንትናው ዕለት አመሻሹ ላይ ባልታወቁ ሰዎች በጩቤ ተወግተው ሆስፒታል መግባታቸው ተነግሯል።

 

የደከመን መርገጥ ሳይሆን የደከመን ማገዝ ነው ትክክል – (ምላሽ ለአቶ ይገረም አለሙ)- ግርማ ካሳ

$
0
0

 

ይገረም አለሙ የተባሉ ጸሃፊ “ድርድሩ” በሚል ያቀረቡትን ጽሁፍ  ዘሃበሻ ላይ አነበብኩ። እኝህ ሰው ከሚጦምሩትና ከሚጽፉት ዉጭ ማን እንደሆኑ፣ አገር ቤት ይኑሩ፣ ዉጭ አገር፣ በእዉነተኛ ስማቸው ይጻፉ፣ በብእር ስም ብዙ የማውቀው ነገር የለም። ሆኖም ባቀረቡት ሐሳብ ዙሪያ እኔም የተሰማኝን አንዳንድ ምላሾሽ፣ በአክብሮት መስጠት ፈለኩ።

“ድርድር በእነማን መካከል፣ ድርድር እንዴትና በምን ሁኔታ? ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ የሚችል አስተያየት መጻፉ፣ ልምድ ማካፈሉ ነበር የሚበጀው፡፡ እኔ ይህን ለማድረግ የሚበቃ እውቀትም ልምድም የለኝም፡፡ ፍረጃና ውንጀላ ላይ በመሮጥም ሆነ ጭፍን ድጋፍ በመስጠት  ደግሞ አላምንም፣ በዚህ መካከል ሆኜ ስለ ድርድሩ የተሰማኝን  ልበል፡” ሲሉ ነው የጀመሩት ጽሁፋቸው። ሆኖም ግን እንዳለ ጽሁፋቸው፣ እንኳን ለድርዱሩ የሚጠቅሙ ሐሳቦችን ሊያቀርቡ ቀርቶ፣ ጭራሽ ፍረጃና ወገዛ የሞላበት፣  “ድርድሩ መደረግ የለበትም” የሚል አቋም ያንጸባረቀ ጽሁፍ ነው።

አቶ ይገረም “ወያኔ የድርድር ጥሪ ያቀረበው በመላ ሀገሪቱ በተለይ ደግሞ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች በተቀጣጠለው የህዝብ ቁጣና እንቢተኝነት በደረሰበት ድንጋጤ መሆኑን ወያኔዎችም ቢሆን የሚክዱት አይመስለኝም፡” ሲሉ የጻፉት ትክክለኛ አባባል ነው። በኦሮሚያና በአማራው ክልል የተከሰተው ተቃዉሞ ድንጋጤ ዉስጥ ከመክተትም ባለፈ፣ በዉስጣቸው ከፍተኛ የሆነ መከፋፈልን ነው የፈጠረው። በተለይም በብአዴን እና በሕወሃት መካከል ብዙዎች ያልተረዱት ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ነው ያለው። የብአዴን መካከለኛና ታችኛው አመራሮች ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል የሕወሃት የበላይነት መቆም አለበት ብለው የቆረጡና የተነሱ ናቸው።

አቶ ይገረም ድርድሩ የሕዝብ ትግል ዉጤት መሆኑን ከገለጹበት አባባል በስተቀር ግን፣ ሌሎች ያሰፈሯቸው ነጥቦች በድርዱሩ ላይ ከወዲሁ ዜጎች ጨለምተኛ አመለካካት እንዲኖራቸው የሚገፋፉ፣  ተስፋ አስቆራጭ የሆኑ ፣ በመፍትሄ ላይ ሳይሆን ብሶት በማሰማት ላይ ያተኮሩ ደካም ነጥቦች እንደሆኑ ነው ለማየት የቻልኩት።

እኝህ ሰው በተለይም ተቃዋሚዎችን የገለጹበት አገላለጽ ከማስገረም አልፎ አስቆኛል። “ይቅርታ ይደረግልኝና የድርድሩ ተካፋይ የተባሉትን ፓርቲ ብሎ ለመጥራት አንደበቴ፣ ለመጻፍ ጣቶቼ እሽ አይሉኝም፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ለድርጅቶቹ ወይንም ለመሪዎቹ ጥላቻ ኖሮኝ ሳይሆን ፓርቲ ለመባል የማይበቁ በመሆናቸው ነው” ይሉናል አቶ ይገረም። እርግጥ ነው ተቃዋሚዎች ጠንካራ ናቸው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው። እርግጥ ነው በተቃዋሚዎች ዉስጥ በየትኛውም ድርጅት ችግሮች እንዳሉ ችግሮች አሉ።  ሆኖም ግን ድርጅቶቹ የሚጠናከሩበትን መንገድ ከመፈለግና በዚያም ረገድ ሐሳቦችን ከመስጠት በዚህ መልኩ ፣ በትንሹም ቢሆን ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ወገኖችን እንቅስቃሴ ማሳነስና ዜሮ ማስገባት፣ በግሌ ሃላፊነት የጎደለው አድርጌ ነው የምወስደው።

በነገራችን ላይ አቶ አቶ ይገረም ተቃዋሚዎች ሲሉ ሁሉንም ጨፍልቀው ማየትቸው ራሱ አንዱ ትልቁ ድክመታቸው ነው። ሰማያዊ ፓርቲ፣ መኢአድ፣ መድረክና ኢዴፓ አሉ። እነዚህ አራት ድርጅቶች ሕዝብን እንወክላለን ያሉበት ሁኔታ የለም። ሊሉም አይችሉም። ሆኖም ግን የሕዝብን ጥያቄ ግን እንደ ድርጅት ማቅረብ ይችላሉ። ያንንም ነው እያደረጉ ያሉት። የእስረኞች መፈታት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መቆም፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኛ እንዲሆኑ፣ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ….የመሳስለኡት የሕዝብ ጥያቄ አይደሉም እንዴ ?

በአገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች በከባድ ሁኔታ ውስጥም ሆነው ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉ መሆናቸውን አቶ ይገረም፣ አዉቀው ላለማመን ካልፈለጉ በስተቀር፣  ያጡታል ብዬ አላስብም። ለምሳሌ ሁለት ምሳሌዎች ልጥቀስ፡

በአማራው ክልል ከፍተኛ እንቅስቃሴ ከመደረጉ፣ ከአንድም ሁለት አመታት በፊት በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደሴ በመሳሰሉ ቦታዎች ሕዝቡን ለማደራጀትና  ለማንቀሳቀስ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ ሥራ ሲሰራ እንደነበረ አገር ሁሉ የሚያወቀው ነው። የአንድነት ፓርቲ በምርጫ 2007 ወቅት ከ547  የፓርላም ወረዳዎች በ508 ተወዳዳሪዎች አሰልፎ ፣ በሰላሳ አራት ዞኖች ጽ/ቤት ከፍቶ በምርጫው ጠንካራ ፓርቲ ሆኖ ለመውጣት ዝግጁ የነበረ ፓርቲ ነበር። (ከአንድነት ቀጥሎ የብዙ ድርጅቶች ስብሰብ የሆነው መድረክ 270 ብቻ ነበር ያሰለፈው)   በድርጅቱ ዉስጥ ችግር የነበረ ቢሆንም፣ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ችግሩን ፈቶ፣ አዲስ አመራር መርጦ የተንቀሳቀሰ ፣ ከፓርቲው ምስረታ ጀመሮ አራት ሊቀመናብርትን ያስተናገደ የአንድ ሰው መፈንጫ ያልሆነ ዘመናዊ ፓርቲ ነበር። ብርሃንን ሰላምን ጨመሮ የግል ማተሚያ ቤቶች የአንድነት ልሳኖችን፣ ጋዜጦችን ፣ በደህንነቶች ትእዛዝ አናወጣም ቢሉም ፣ ፓርቲው የራሱ ማተሚያ ማሽን እና የራሱ ጀኔሬተር በመግዛት በሳምንት ሁለት ጋዜጦችን (ፍኖተ ነጻነት እና የሚሊዮኒች ድምጽ ) እያተመ ለሕዝብ ያቀርብ ነበር። በተለያዩ የአገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ አማራጭ ሐሳቦችን ያዘለ ዳንዲ የሚባል መጽሔት፣  በኦሮሚያ ላለው ማህበረሰብ በአፋን ኦርሞ ቶኩማ በቢሊሱማ በሚል ጋዜጣ መረጃዎች እንዲደርሰው ለማድረግ ዝግጁትን ጨርሶ ነበር።

አንድነት ጠንካራ ሆኖ በመውጣቱ ነው ሕወሃት የፖለቲካ ዉሳኔ፣ ጉልበቱና ጠመንጃው ስላላለው የወሰነው።  በድርጅቱ መድረክ ለሊቀመንበርነት ተወዳድሮ አንድ ድምጽ ብቻ (የራሱን ድምጽ) ያገኘውንና ለኑሮ ደሞዝ የሚፈልዉን ደካማ ግለሰብ በመጠቀም፣ ምርጫ ቦርድ አንድነት ሕጋዊ ሰርተፊኬቱን እንዲያጣ አደረገ። እዉነታው ይሄ ሆኖ እያለ፣  አቶ ይገረም ግን በጭራሽ የማይገናኝ ነጥቦች በማገናኘት፣ የተሳሳተና በእዉነት ላይ ያልተመሰረተ፣ ግን እርሳቸው ትክክል ነው ያሉትን ለመሸጥ ሲሉ ፓርቲዎችን ሲያሳንሱ ነው የሚታዩት። “ፓርቲዎች የሚፈርሱት በራሳቸው አባላት ነው” ብለው በጻፉት ጽሁፍ ላይ ከጥቂት ሳምንታት በፊት፡

ንድነት ህመሙ የጀመረው ሊቀመንበሩ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ስትታሰር ነው፡፡ መድሀኒት የሚፈልግለት አይደለም በሽታውን የሚያውቅለት ጠፍቶ ለአምስት አመታት ከተሰቃየ በኋላ በሀገር ቤትም በውጪም የሚኖሩ  ከአመራር እስከ አባል የነበሩ  የግዛቸው ነኝ፣ የበላይ ነኝ በማለት በፈጠሩት የሥልጣን ሽኩቻ በሽታው ተባብሶ ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡ በመቃብሩ ላይ የቆመው ትእግስቱ አዎሉም በየግዜው በሹመት ላይ ሹመት ሲሰጡት የነበረ ሰው ነው፡፡ ታዲያ ለአንድነት ሞት ቀዳሚው ተጠያቂ ወያኔ ወይንስ የሥልጣን ጥም ያናወዛቸው የአንድነት አመራሮችና የዲያስፖራ ብር ያናወዛቸው አጃቢዎቻቸው” ሲሉ እኝህ ሰው፣ የአንድነት ፓርቲ ከምርጫ 2007 የነበረዉን ጉልህ ተሳትፎ በመናቅ፣ በሚሊዮሞች ድምጽ የተሰሩ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ወደ ጎን በማድረግ ፣ አንድነት ከጨዋታ ዉጭ እንዲሆን 90% ድርሻው የወያኔ እንደሆነ እያወቁ በዚህ መልኩ ለተቃዋሚዎች መዳከም ወያኔ የለበትም ማለታቸው በራሱ አጠያያቂ ነው። በነገራችን ላይ የአንድነት ፓርቲ ሕጋዊ ሰርተፊኬቱን ቢነጠቅ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ ግን አሁን በትግል ዉስጥ ናቸው። የተወሰኑይ እንደ መኢአድ እና ሰማያዊ ተቀላልቀለውም እየታገሉ ናቸው። ወያኔ ሰርተፊኬቱን ቢነጥቅም፣ አባላቱን ደጋፊዎች፣ የአንድነት የለዉጥ ሃይል አሁንም አለ።

አቶ ይገረም፣ ትንሽ የነበረዉን ሁኔታ ይረዱ ዘንድ ከጥቂት አመታት በፊት፣ ከብዙ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል፣  በአማራው ክልል በባህር ዳር የተደረገን አንድ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲመለከቱ ልጋብዛቸው እፈልጋለሁ። የእምቢተኝነት መንፈስ፣ ለመብት የመቆም ስሜት፣ ድፍረት፣አገራዊ ወኔ እንዲኖር የአንድነት ፓርቲና የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቀ የነበረዉን አስተዋጾ ለማየት ይረዳቸዋል።

ሌላው የሰማያዊ ፓርቲን በተመለከተ ነው።ሰማያዊ ፓርት ከተመሰረተ ጀምሮ ለትግሉ ብዙ አስተዋጾ ያደረገ ፓርቲ ነው። በፓርቲው ውስጥ እንደ ማንም ድርጅት ልዩነቶች ይኖራሉ። ሆኖም ፓርቲው ከግለሰቦች ይልቅ በድርጅቱ ያሉ ተቋማት ጠንካራ እንደሆኑ ያስመሰከረ ድርጅት ሆኗል። አገዛዙ ልክ እንደ አንድነት ፓርቲ፣  ጠንካራ የሰማያዊ አመራሮች በሽብርተኝነት ክስ አስሮ አሰቃይቷል። እያሰቃየም ነው። የድርጅቱ የአሁኑ ሊቀመነበር ወደ 2 አመት ገደማ በወህኒ የተሰቃዩ ናቸው። እንደ ዮናታን ተስፋዬ ያሉ አንጋፋ ታጋዮችም በአሁኑ ወቅት በወህኒ ነው የሚገኙት። ሰማያዊ በከባድ ሁኔታ ዉስጥ ሆኖም ግን በከፍተኛ ተነሳሽነት ለትግል የተዘጋጀ ድርጅት ነው።

ይሀን ስል በፓርቲዎች ዉስጥ “ችግር አልነበረም፣ ድካም አልነበረም” ማለቴ አይደለም። ሆኖም ግን አቶ ይገረም ለማቅረብ እንደሞከሩት፣ አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች ምንም እንዳልሰሩ፣ “ስማቸውን መጥቀስ እስከማፈር ድረስ” የማይረቡ እንደሆኑ አድርጎ ማቅረብ ግን ፣ ያውም የሚረባ የሚሉትን ሳያሳዩን እና ሳያመላከቱን የደከመ፣ የሽንፈት፣ ጨለምተኛ ፖለቲካ ነው።

 

አቶ ይገረም በድርድሩ ዙሪያ ሲጽፉ  አሁንም በተስፋ መቆረጥ ውስጥ ተሞልተው ነው። ወያኔዎች የሚደራደሩት ጊዜ ለመግዛትና የአለም አቀፍ ድጋፍ እንዳይቀርባቸው ነው ከሚል ነው በሚል፣ ከድርድሩ ምንም ነገር እንደማይገኝ ነው የገለጹልን። ተቃዋሚዎችም ፓርላማ ለመግባትና ጥቅም ለማግኘት ብለው እንደሚደራደሩም አይናቸውን በጨው አጥበው ነው የጻፉት። አንደኛ የተቃዋሚ መሪዎች ጥቅም ቢፈልጉ ኖሮ አገዛዙን ተቀላቅለው ፣ ወያኔ ሆነው፣ ይሄን ጊዜ ሃብት በሃብት ይሆኑ ነበር። ሁለተኛ የምእራባዊያን መንግስታት ሁኔታም የመረዳት ችግር ያለባቸው መሰለኝ። ያን ቢረዱ ኖሮ ምእራባዉያን  ለሰብአዊ መብትና ለዲሞክራሲ ሳይሆን ለጥቅማቸው ብቻ የቆሙ እንደሆኑ ያወቁ ነበር።  ወያኔ ድርድር አደረገ አላደረገ ፣ ጥቅማቸውን እስካስጠበቀላቸው ድረስ የውጭ ድጋፍ እንደማይለየው  ይረዱ ነበር። “የዲፕሎማሲ ድጋፍ ቆመ” ያሉትን አቶ ይገረም፣ ስህተት ነው። አልቆመም። “ቆመ” ካሉ መረጃዎች ያቅረቡና ይከራከሩ።

ወያኔ ለድርድሩ የቀረበው እርሳቸው እንዳሉት በሕዝብ ተገዶ ነው። በሕዝብ ብቻ ሳይሆን በድርጅቱ ውስጥ ባሉ መካከለኛና አነስተኛ አመራሮች ግፊት ነው። አሁን ያለው አገዛዙ ከ5 ወይም 10 አመታት በፊት የነበረው አይደለም።በመሆኑም ይህ ድርድር በአንጻራዊነት የፖለቲክ ምህዳሩን እንዲሰፋ ሊረዳ ይችላል። ያም ባይሆን እንኳን  ያ እንዲሆን ሙከራ ማድረጉና መታገሉ አስፈላጊ ነው። አቶ ይገረም፣ አሁንም እላለሁ፣  ሌላ አማራጭ ሳያሳዩን ፣ ትንሽ ቢሆን የተሻለ ነገር እንዲመጣ ወደ ድርድር የመገባቱን ሂደት ማሳነሳቸው፣ ማጣጣላቸው ተገቢ አይደለም።

በግሌ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ አቤል ዋቤላ እንዳለው “አገር የሚገነባው በድርድር ነው” የሚል እምነት አለኝ። ከአሁን ለአሁን ትላንት አልተሳካምና ዛሬ መሞከር የለበትም የሚለው አነጋገር ፣  የትም አያስኬድም። ይልቅ ይሄ ድርድር ትንሽም ቢሆን ፍሬ እንዲያፈራ የድርሻችንን መወጣት ነው የሚጠበቅብን።

አሁንም ደግሜ የምለው አገር  ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች እንደ ማንም ድርጅት በውስጣቸው ችግሮች ይኖራሉ። ሆኖም ግን በዋናነት በገዢው ፓርቲ በኩል የደረሰባቸዉን የሚደርስባቸው ግፍና መከራ በጣም የከፋው። እዉነቱ ያ ሆኖ እያለ፣ እነርሱ ከማገዝና ከመደገፍ፣ እነርሱ ከድካማቸው እንዲወጡ የድርሻችንን ከማድረግ ፣ ወያኔ በነርሱ ላይ የሚያደርሰው ጫና ሳያንሳ እኛ ደግሞ “ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው” እንደሚባለው፣ እነዚህ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ላይ ጠጠር መወርወር ዘመናዊ ፖለቲካ አይደለም። ተቃዋሚዎች መተቸት ፣ መወቀስ አለባቸው። መሪዎቻቸው ተጠያቂ መሆን አለባቸው። ሆኖም ትችታችንን ወቀሳችን ፈረንጆች constructive  criticism ( ገንቢ ትችት) መሆን አለበት እንጂ  destructive criticism  (አፍራሽ ትችት) መሆን የለበትም። የአቶ ይገረም ጽሁፍ በኔ እይታ destructive የሆነ ትችት ነው።

“እኔም ጥያቄ አለኝ እነርሱ የሚሉትንና የሚያደርጉትን ነው መከተል ያለብን ወይንስ ትክክል የምንለውን? “ ነው ሲሉ በመጠየቅ ጽሁፋቸው ያጠቃላሉ አቶ ይገረም። ትክክል የሆነውን ነው መከተል ያለብን የሚል መልስ ነው ያለኝ። ሆኖም እርሳቸው የሚቃወሙት፣ ችግርን በዉይይት መፍታት ትክክል ብቻ ሳይሆን የሰለጠነ ፖለቲካ ነው። ከላይ ጠቅሼዋለሁ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ እንዳለው አገር የሚገነባው በድርድር ነው። ትክክል ሳይሆን ትክክል የተበላን ትክክል እንዲሆን መስራትና መድከም ያ ትክክል ነው። አቶ ይገረም እንደሚያደረጉት፣ ዜጎች ተስፋ ማስቆረጥ፣ የደከመዉን ደካማ ነው ብሎ መረጋገጥ ትክክል አይደለም። የደከመውን ማንሳትን ማበረታታት፣ የተሳሳተዉን እንዲታረም መምከርና መዉቀስ  ያ   ትክክል ነው።  የአቶ ይገረም ችግር ትክክል ያልሆነውን ያለመከተል ሳይሆን ትክክል የሆነውን ነገር አለመከተላቸው ነው።

(ይሄ ጽሁፍ የተጻፈው ምሉ በሙሉ አቶ ይገረም ባቀረቧቸው ሐሳቦች ዙሪያ ነው። በርሳቸው ላይ ምን እንደሆኑ ባላወቅም ችግር የለኝም። እርሳቸው ወደ ግለሰብ እንካ ሰላምቲያ ሳይገቡ በቀርቡ ሐሳቦች ዙሪያ ምላሽ የሚሰጡ ከሆነ እጠብቃለሁ)

 

 

እውን አማርኛ፤ ከኦሮምኛ የመጣ ቋንቋ ነውን?  (ለበፍቃዱ ዘ. ኃይሉ በኩል)

$
0
0

ከሁለት ሳምንት በፊት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር የካቲት 1፥ 2017፤ የፌስቡክ ጓደኛዬ በፍቃዱ ዘ. ኃይሉ በፌስቡክ ገጹ ላይ “ይህንን በድጋሜ ማጋራት አስፈላጊ ይመስለኛል” ከሚል ማሳሰቢያ ሥር የሚከተለውን አስፍሮ ነበር፡፡

«…ዶናልድ ሌቨን (ዶ/ር) በሠራው አንድ ጥናቱ ‹አማርኛ የተፈጠረው የኦሮሞ ተወላጆች ግዕዝ ለመናገር ሲሞክሩ ነው› በማለት ያትታል፡፡ የመርጌታ ግሩም ተፈራን ትርክት ማመን ከቻልን ይህ እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ ዶናልድ ሌቪን የአማርኛ ቋንቋ ቅርፅ (Syntax) የኩሽ ቋንቋዎች ባሕሪ ያለው መሆኑን ጠቅሶ ነው እንዲያ ያለው፡፡ ባሕሩ ዘውዴም ‹‹[አማርኛ] ተገንጥሎ ወጥቷል ተብሎ በጥቅሉ ከሚታመንበት ሴማዊው ግዕዝ ይልቅ ከኩሻዊው ኦሮምኛ ጋር ብዙ የሚጋራው ጠባይ አለው›› ብሎ ጽፏል፡፡…»

ገና ጽሑፉን እንዳየሁት ድካም ተሰማኝ፡፡ ለምን ማለት ጥሩ ነው፤ ገና ሳየው የሆነ ነገር ማለት እንዳለብኝ ስለገባኝ እና ማለት ያለብኝንም ዝም ብዬ በግምት እና በመሰለኝ መወርወር ሳይሆን እውነትን ብቻ ይዤ ማቅረብ ስለሚገባኝ፤ እውነትን የያዘ ነገር መጻፍ ደሞ ቀላል ባለመሆኑ ገና ከመጀመሪያው አድካሚ ሥራ  እንደሚጠብቀኝ በመረዳቴ ነበር መድከም ግድ የሆነብኝ፡፡ በመጨረሻ ግን የጻፍኩት ጽሑፍ አማርኛን በተመለከተ መታወቅ ካለባቸው ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹን በጥቂቱም ቢሆን የሚዳስስ በመሆኑ ድካሜ ወደ ብርታት ተቀይሮ ደስ ብሎኛል፡፡

በነገራችን ላይ እኔ አይደለም የኢትዮጵያ፤ የዓለም ቋንቋዎች ግንኙነት እና ዝምድና የሚስበኝ እና የሚያስደንቀኝ ሰው ነኝ፡፡ ሌላው ይቅርና “ምስጢር” የሚለው የግእዝ ቃል፤ በአማርኛ “ሚስጥር”፣ በግሪክ “ሚስቲሪዮ”፣ በላቲን “ሚስትሪዮ/ሚስተሪዩም”፣ በሮማንያ “ሚስጤር”፣ በጣሊያንኛ “ሚስተሮ”፣ በእንግሊዝኛ “ሚስትሪ” ከመሆኑም ሌላ በብዙ የአውሮፓ ቋንቋዎች ተቀራራቢ ቃል መያዙ ራሱ ባሰብኩት ቁጥር ያስደንቀኛል፣ ያስደስተኛል፡፡ ክርስትና ሲጀመር መለኮታዊውን ሚስጥር ወይም ሚስጥረ ስላሴ የምንለውን  ጉዳይ ለመግለጽ ስለተጠቀሙበትና ያኔ ክርስትናን የተቀበሉ ሁሉ ቃሉን ስለተጋሩት ይሆንን የሚል ሃሳብም ይመጣብኛል፡፡

ወዳገራችን ቋንቋዎች ስንመጣም፤ አማርኛና ኦሮምኛ ይቅርና ግእዝ እና ኦሮምኛ ብዙ የጋራ ቃሎች እንዳሏቸው አምናለሁ፡፡ ለምሳሌም ቁር (ብርድ)፣ ፈውስ፣ እምነት፣ባቄላ/ቡቃያ እና ሌሎችም አያሌ ቃሎች በግእዝና በኦሮምኛ አስገራሚ ተመሳሳይነት/አንድነት እንዳላቸው ተገንዝቤአለሁ ይሁንና ሰዎች የዘመኑን የታሪክ እና የፖለቲካ እብደት ተከትለው ስለቋንቋዎቻችን የሚጽፉትን ውሸት መቀበል አይሆንልኝም፤ ከመኮነንም ወደኋላ አልልም፡፡ ይህ ጽሑፍም የዚህ አስተሳሰቤ ነጸብራቅ እንደሆነ ይያዝልኝ፡፡

በመጀመሪያ በፍቃዱ የቋንቋ ቅርፅ (‘ሲንታክስ-syntax’) ሲል በአንድ ቋንቋ ዐረፍተ ነገር ውስጥ ያሉ ቃሎችን የአደራደር ቅደም ተከተል ሊል ፈልጎ መሆኑን ማረጋገጥ ነበረብኝ፡፡ በፍቃዱ የቋንቋ ቅርፅ (‘ሲንታክስ-syntax’) ሲል የጠራው ቃል በቋንቋው ዓለም ያለውን ትርጉም ለማየት ሞከርኩ፡፡ የአንድን ቋንቋ የዐረፍተ-ነገር አወቃቀር ሥርዐት በተለይም ቃሎች በዐረፍተ-ነገሩ ውስጥ ያላቸውን አደራደር (ቅደም ተከተል) እንደሚያመለክት ተረዳሁ፡፡ ታዲያ እንደዚህ ከሆነ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በአፍ መፍቻነት ከሚያገለግሉ ሴማዊ ቋንቋዎች ውስጥ የዐረፍተ ነገር አወቃቀር ሥርዐቱ ከኦሮምኛ የተለዬ ቋንቋ አለን? አማርኛን ብቻ ለይቶ መጥቀስ ለምን አስፈለገ? ጉዳዩ የዐረፍተ ነገር አወቃቀር ሥርዐት ከሆነ አማርኛ ብቻ ሳይሆን ከግእዝ ውጪ ያሉት የኢትዮጵያ ሴማዊ ቋንቋዎች በሙሉ ኦሮሞዎች ግእዝ ለመናገሩ ሲሞክሩ የተፈጠሩ ናቸው መባል አለበት ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በቋንቋ ሳይንስ መሠረት የኢትዮጵያ ሴማዊ ቋንቋዎች በመባል ከሚታወቁት 15 ቋንቋዎች ውስጥ ከኩሽ ቋንቋዎች የተለዬ የዐረፍተ ነገር አወቃቀር ያለው ግእዝ ብቻ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ለምን “ግዕዝ” ሳይሆን “ግእዝ” ብዬ እንደምጽፍ ሌላ ግዜ አብራራለሁና ላሁኑ ሳትቀየሙኝ እንዳላያችሁ እለፉት፡፡

ዝርዝሩን በሰፊው ማየታችንን እንቀጥል፡፡ በዓለማችን ላይ ሰባት ሺ የሚሆኑ ቋንቋዎች ይገኛሉ። በነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች ዐረፍተ ነገሮች የሚዋቀሩባቸው ስድስት ዋና ዋና የሚባሉ የቃል አደራደር መንገዶች አሉ። ይህ ክፍፍል የተዘጋጀው በዐረፍተ ነገር ውስጥ ያሉት ዋና ዋና የንግግር ክፍሎች ማለትም የድርጊት ባለቤት (አድራጊ)፣ ድርጊት ተቀባይ (ተደራጊ) እና ግስ ያላቸውን ቅደም ተከተል መሠረት በማድረግ ነው። ለምሳሌ “አበበ በሶ በላ” የሚለው የአማርኛ ዐረፍተ ነገር ‘አድራጊ-ድርጊት ተቀባይ-ግስ’ የሚለውን የአደራደር ሥርዐት የተከተለ ነው። የመጀመሪያው ቃል “አበበ” አድራጊውን ያመለክታል። ለጥቆ ያለው “በሶ” የሚለው ቃል ድርጊት ተቀባዩን ሲያመለክት “በላ” የሚለው ደሞ ግስ ሲሆን ድርጊት አመልካች ነው።

 

ያለማችን ቋንቋዎች የሚጠቀሟቸው ዋና ዋናዎቹ የዐረፍተ-ነገር አደራደር ሥርዐቶች የሚከተሉት ናቸው።

  • አድራጊ — ድርጊት ተቀባይ — ግስ (ምሳሌ ዐ.ነገር በአማርኛ-አበበ በሶ በላ፤ ቋንቋ-ኦሮምኛ)
  • አድራጊ — ግስ —ድርጊት ተቀባይ    (ምሳሌ ዐ.ነገር በአማርኛ-አበበ በላ በሶ፤ ቋንቋ-እንግሊዝኛ)
  • ግስ — አድራጊ — ድርጊት ተቀባይ (ምሳሌ ዐ.ነገር በአማርኛ-በላ አበበ በሶ፤ ቋንቋ-ግእዝ)
  • ግስ — ድርጊት ተቀባይ — አድራጊ (ምሳሌ ዐ.ነገር በአማርኛ-በላ በሶ አበበ)
  • ድርጊት ተቀባይ — ግስ — አድራጊ (ምሳሌ ዐ.ነገር በአማርኛ-በሶ በላ አበበ)
  • ድርጊት ተቀባይ — አድራጊ— ግስ    (ምሳሌ ዐ.ነገር በአማርኛ-በሶ አበበ በላ)

ከዓለማችን ቋንቋዎች ውስጥ፤ አርባ አምስት ከመቶ የሚሆኑት አንደኛውን መንገድ (አበበ-በሶ-በላ)፣ አርባ ሁለት ከመቶ የሚሆኑት ደሞ ሁለተኛውን መንገድ (አበበ-በላ-በሶ) ይከተላሉ።

የኩሽ፣ የኦሞ፣ እና በኢትዮ-ሴማዊ መደብ የሚካተቱት 14 ቋንቋዎች እንዲሁም ጥንታዊ ግሪክ እና አርመንያ ከላይ በቁጥር አንድ የተመለከተውን (አበበ-በሶ-በላ) የዐረፍተ ነገር አደራደር ሥልት ይጠቀማሉ፡፡ ከነዚህም በተጨማሪ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ3000 እስከ 1000 ዓመተ ዓለም በሜሶፖታሚያ ይነገር የነበረው አካዲያን የተባለው ሴማዊ ቋንቋ ይህንኑ መንገድ ይከተል እንደነበር ይታወቃል፡፡

የሴማዊ ቋንቋዎች መሠረታዊውና ዋናው የዐረፍተ-ነገር አደራደር መንገድ ሥወስተኛው (በላ-አበበ-በሶ) እንደሆነ የቋንቋ ሊቆች ይስማማሉ። ይሁንና ዛሬ ይኸን መንገድ የሚከተሉት ሴማዊ ቋንቋዎች ግእዝ እና ዐረብኛ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሌሎቹ ሴማዊ ቋንቋዎች ልክ እንደ ኩሽና ኦሞ አንደኛውን መንገድ (አበበ-በሶ-በላ) እንደሚከተሉ እስቲ በምሳሌ እንመልከት፡፡ በአማርኛ “እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” ብንል፤ “እግዚአብሔር” ባለቤት፣ “ሰማይና ምድር” ተደራጊ ወይም ድርጊት ተቀባይ ሲሆን “ፈጠረ” ደሞ ግስ (ድርጊት አመልካች) ነው፡፡ ይኸንኑ ዐረፍተ ነገር ወደ ትግርኛ ስንወስደው፤ “እግዚአብሔር ሰማይን ምድሪን ፈጢሩ” ይሆናል፡፡ በኦሮምኛ ደሞ “ዋቀዮ በንቲዋን ዋቃ ፊ ላፋ ኡሜ” ልንል እንችላለን፡፡ “ዋቀዮ” የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ሲሆን “በንቲዋን ዋቃ ፊ ላፋ” የሚለው ሐረግ “ሰማይንና ምድርን” ይወክላል፡፡ “ኡሜ” ማለት ደሞ “ፈጠረ” ማለት ነው፡፡ ይኸው ዐረፍተ ነገር በግእዝ ሲቀመጥ፤ “ፈጠረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድር” ወይም “ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድር” የሚል ይሆናል፡፡ ወደ ዐረብኛ ሲተረጎም ደሞ “ኸለቀ አላህ ሰማዋህቲ ወአል ኧርደ” የሚል ይሆናል፡፡በዐረብኛ “ኸለቀ” ማለት “ፈጠረ” ማለት ሲሆን፤ “ሰማዋህቲ ወአል ኧርደ” የሚለው ሐረግ “ሰማያትንና ምድርን” የሚል ትርጉም አለው፡፡ ጥንታዊው ዕብራይስጥ እንደ ግእዝና እንደ ዐረብኛ ይኸንኑ መንገድ ይከተል እንደነበር ይታወቃል፡፡ የዛሬው ዘመናዊው ዕብራይስጥ ግን ልክ እንደ ዘመናዊው ግሪክ እና እንደ እንግሊዝኛ በሁለት ቁጥር የተመለከተውን (አበበ-በላ-በሶ) መንገድ ይጠቀማል፡፡

እዚህ ላይ፤ ሌሎች ኢትዮ-ሴማዊ ቋንቋዎች በሙሉ (ዳሃላክ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ አማርኛ፣ አርጎባ፣ ሐረሪ፣ ስልጤ፣ ወለኔ፣ ክስታኔ፣ ኢኖር፣ ሜስሜስ፣ መስቃን፣ ሰባት ቤት ጉራጌ እና ዛይ) ከግእዝ ተለይተው እንዴት የኩሽና የኦሞ ቋንቋዎችን መንገድ ሊከተሉ ቻሉ የሚል ጥያቄ መነሳቱ ተገቢ ነው፡፡ ብዙ የቋንቋ ሊቆች በኩሽ ቋንቋዎች ተጽዕኖ ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ፡፡ ይሁንና ይህ ሐቅ በራሱ፤ አማርኛ፣ ትግርኛም ሆነ ሌሎች ዛሬ በኢትዮጵያ በአፍ መፍቻነት በማገልገል ላይ ያሉ ሴማዊ ቋንቋዎች ከኦሮምኛ ወይም ከሌሎች ኩሽ ቋንቋዎች የመጡ ናቸው ሊያሰኘን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንደተጠቆመው ዕብራይስጥ ራሱ ጥንት ይጠቀምበት የነበረውን “ግስ-ባለቤት-ድርጊት ተቀባይ (በላ-አበበ-በሶ)” ሥርዐት ትቶ በዘመን ሂደት “ባለቤት-ግስ-ድርጊት-ተቀባይ (አበበ-በላ-በሶ)” ወደሚለው ሥርዐት እንደተቀየረ ይታወቃልና፡፡ ዘመናዊው ግሪክም ጥንት የነበረውን የዐረፍተ-ነገር አወቃቀር ዘዴ ለውጧል፡፡ ዕብራይስጥና ግሪክ የዐረፍተ ነገር አወቃቀር መንገዳቸውን ቀየሩ ማለት የጥንቱ ዕብራይስጥ እና ዘመናዊው ዕብራይስጥ እንዲሁም የጥንቱ ግሪክኛ እና ያሁኑ ግሪክኛ የተለያዩ ቋንቋዎች ሆኑ ማለት አደለም፡፡ እነዚህ ሁለት ቋንቋዎች ያደረጉት የዐረፍተ-ነገር አወቃቀር ለውጥ ጥንት ከነበራቸው የዘር ግንድ አላወጣቸውም፡፡ ዕብራይስጥ እንደገና ከሌላ ቋንቋ መጣ አልተባለም፡፡ ግሪክም፤ የጥንቱ ግሪክ አልን የዛሬው ግሪክ ያው አንድ ቋንቋ ነው፡፡

እናም ምናልባት የኛም ሴማዊ ቋንቋዎች በተመሳሳይ መንገድ ባሳለፉት ዘመን ውስጥ የአወቃቀር ለውጥ አድርገው ሊሆን ቢችልስ? በነገራችን ላይ ግርማ አውግቸው ደመቀ “የአማርኛ አመጣጥ (The Origin of Amharic)” በሚል በጻፈልን የቅርብ ግዚ ሥራው ላይ ቀደም ባሉ ዘመናት የነበሩ የአማርኛ ጽሑፎችን በማጥናት የጥንቱ አማርኛ ልክ እንደ ግእዝ እና እንደ ዐረብኛ የ “ግስ-ባለቤት-ድርት ተቀባይ (በላ-አበበ-በሶ)” የዐረፍተ ነገር አወቃቀር ሥርዐትን ይከተል እንደነበር መስክሮልናል፡፡ መጽሐፉን በሙሉ የማንበብ ዕድል ባላገኝም ዕድሜ ለኢንተርኔት ዘመን ከላይ የጠቆምኩትን ሐቅ በመግቢያው እተሰጠ አስተያየት ላይ ተመልክቻለሁ፡፡ ለማንኛውም ስለ ዓለማችን ቋንቋዎች አመዳደብ እና የዐረፍተ ነገር አደራደር ሥርዐት ተጨማሪ ዝርዝር ማብራሪያ የፈለገ ሰው ‘ኢትኖሎግ (ethnologue)’ የተባለውን ድረ ገጽ መመልከት ይችላል፡፡

“አማርኛ ከኦሮምኛ መጣ ወይም አማርኛን ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግእዝ ለመናገሩ ሲሞክሩ ፈጠሩት” የሚለው በዶናልድ ሌቨን ተደርሶ በበፍቃዱ ዘ. ኃይሉ የቀረበው ቀልድ ባያስቀኝም አንድ አሳዛኝ ነገር አስታውሶኛል፡፡ ዛሬ ግዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች አማርኛን እና ሌሎችን ቋንቋዎች የሚያዩበት መንገድ የአራምባና የቆቦ፣ የመቀሌ እና የሞያሌ ብቻ ሳይሆን የሰማይና የመሬት ያህል ተራርቆ ይታየኛል፡፡ ብዙ ሰዎች ከአማርኛ ውጪ ያሉትን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በተመለከተ ትክክል ያልሆነ እና የመሰላቸውን ነገር ለመጻፍ ወይም አስተያየት ለመስጠት ይቅርና የቋንቋዎቹን ስም ለማንሳት እንኳ የብሔረ ብሔረሰቦች አምላክ እባክህ ይቅር በለን የሚል ልመና እንደሚያቀርቡ ሳንታዘብ ቀረን ብላችሁ ነው! ታዲያ አማርኛ ላይ ሲሆን ሰው ሁሉ ከመሬት እየተነሳ እንዴት ደፋር ይሆናል? ምክንያቱ ምን ይሆን ብዬ ስጠይቅ፤ ከጀርባ የሚያሸልም ያልተጻፈ ስምምነት አለ የሚል መልስ የሰማሁ መሰለኝና መላሹ ሰይጣን እንደሚሆን በመገመት ወግድልኝ፣ አርባ ክንድ ራቅ ብዬው ቀጠልኩ፡፡

ለማንኛውም አማርኛን በተመለከተ የሆነ ያልሆነውን ማለት ልክ እንደመተንፈስ ከመቆጠሩ የተነሳ ስለሱ የሚያወራው እና የሚጽፈው ሰው ቁጥር ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦቸ ብዛት በልጦ ጠቅላላ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብዛት እንዳያክል እና ለአቆጣጠር እንዳያስቸግር መስጋቴን ልደብቅ አልችልም፡፡ ብዙ ሰው ስለ አማርኛ መጻፉ ባልከፋ ነበር ከእውነት የራቀና መሠረት የሌለው ሲሆን ግን ያስጠይፋል፡፡ በተለይ ፌስቡክ ላይ አማርኛን ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር እያነጻጸሩ የሚጽፉ አንዳንድ ሰዎች አማርኛን በተመለከተ  የሚሰነዝሩት አስተያየት የኢትዮጵያን ቋንቋዎች “ሀ- ሁ” ሳይቆጥሩ በባዶው ሜዳ የሚደነፉ አላዋቂዎች መሆናቸውን ይመሰክራል፡፡

በፍቃዱ ዘ. ኃይሉ ከዐረፍተ-ነገር አወቃቀር ሥርዐት ጋር አያይዞ “አማርኛን ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግእዝ ለመናገር ሲሞክሩ ፈጠሩት” ሲል ያቀረበልን አስተሳሰብ ይሰራል ቢባል እንኳ ለአማርኛ ብቻ ተለይቶ እንደማይሠራ ለማረጋገጥ ከፈለገ ከአማርኛና ከኦሮምኛ ዘለቅ ብሎ የሌሎችን ቋንቋዎችም “ሀ-ሁ” እንዲቆጥር በወንድምነት እንመክረዋለን፡፡ ይኸ ሃሳብ ባጠቃላይ ከግእዝ ውጪ ያሉትን ሴማዊ ቋንቋዎች በተመለከተም እንደማያስኸድ እንዲሁም አማርኛ የቋንቋ አወቃቀሩ ሴማዊ እንደሆነ ለመገንዘብ የሴማዊ ቋንቋዎችን ወሳኝ ባህሪዎች መመልከት ግድ ይለናል፡፡

ሴማዊ ቋንቋዎች አንድ የጋራ የሆነ ባህሪ አላቸው-ከግስ ይነሣሉ (ግስን መሠረት ያደረጉ ናቸው)፡፡ በሴማዊ ቋንቋዎች ውስጥ ከንግግር (ከዐረፍተ-ነገር) ክፍሎች እንደ ግስ ወሳኝ ነገር የለም፡፡ በሴማዊ ቋንቋዎች ሌላ ምንም ቃል ሳይጨመርበት ግሱ ብቻ በቅጥያዎች መልኩን እየለዋወጠ የድርጊቱን ባለቤት፣ የድርጊቱን ጊዜ፣ አዎንታዊ/አሉታዊ መሆኑን ወዘተርፈ የማመልከት ብቃት አለው፡፡ “በላ” የሚለውን መነሻ ግስ ወስደን የሚከተሉትን መመልከት ጥሩ ፍንጭ የሚሰጥ ይመስለኛል፡፡

  • በላ = እሱ በላ፤ ባይገለጽም ባለቤቱ “እሱ” መሆኑን በግሱ ብቻ እናውቃለን
  • በላች= እሷ በላች
  • ልትበላ= እሷ ልትበላ፤ “ልትበላ” የሚለው ቃል የድርጊቱ ባለቤት “እሷ” መሆኗን ብቻ ሳይሆን ድርጊቱን ለመፈጸም ተቃርባ እንደነበር የሚያመለክተን ነገር አለ፡፡
  • ላይበላ፣ ሲበላ፣ እያበላ፣ በልተው፣ አባላ፣ ተበላላ……….

ሌላው የሴማዊ ቋንቋዎች መለያ ደሞ ብዙዎች ግሶች ባለ ሥወስት ሆሄ/ፊደል መሆናቸው እና በብዙዎች ሴማዊ ቋንቋዎች ተመሳሳይነት ያላቸው መሆኑ ነው፡፡ በአማርኛ ቋንቋም ባለ ሥወስት ፊደል ግሶች እጅግ በጣም የተለመዱ ናቸው፡፡ በ “ቀ” ፊደል ከሚጀምሩ ባለ ሥወስት ሆሄ ግሶች መካከል ልጥራ ብል፤ ቀበጠ፣ ቀበለ፣ ቀበረ፣ ቀደደ፣ ቀደመ፣ ቀደሰ፣ ቀወረ፣ ቀወጠ፣ ቀወሰ፣ ቀዘነ፣ ቀዘፈ፣ ቀጠጠ፣ ቀጠለ፣ ቀጠነ፣ ቀጠፈ፣ ቀጠረ፣ ቀጨጨ፣ ቀጨመ፣ ቀየሰ፣ ቀየረ፣ ቀየደ፣ ቀየጠ፣ ቀለለ፣ ቀለመ፣ ቀለደ፣ ቀለበ፣ ቀለዘ፣ ቀለጠ፣ ቀለሰ፣ ቀመመ፣ ቀመሰ፣ ቀመረ፣ ቀመለ፣ ቀነሰ፣ ቀነፈ፣ ቀነተ፣ ቀሰፈ፣ ቀሰረ፣ ቀሠሠ፣ ቀሰተ፣ ቀሸረ፣ ቀፈፈ፣ ቀፈተ፣ ቀሰጠ፣ ቀሰመ፣ ቀቀለ፣ ቀረረ፣ ቀረበ፣ ቀረጠ፣ ቀረፈ፣ ቀተለ፣ ቀተረ እያለ ይቀጥላል፡፡ አይበቃኝም? በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ያሉትን ባለ ሥወስት ሆሄ ቃሎች በሙሉ ልዘርዝር ብል እስክሪብቶና ወረቀት ብቻ ሳይሆን ዕድሜዬም ላይበቃኝ ይችላል፡፡

ይኸም ብቻ አደለም፤ ሴማዊ ቋንቋዎች ከግስ ተነስተው የሚራቡ እጅግ ብዙ ቃሎች አሏቸው፡፡ ለምሳሌ በአማርኛ ቋንቋ “በላ” ከሚለው ግስ በመነሳት አንድ ሺ የሚሆኑ ርቢ ቃሎችን ማግኘት እንችላለን፡፡ በዚህም መሠረት ከአንድ ቃል ተነስቶ በመራባት አማርኛ በጣም የታወቀ ሲሆን ግእዝ “እነሱ” በሚለው ተውላጠ ስም ለወንዶች እና ለሴቶች የተለያየ አጠቃቀም ቢኖረውም በጠቅላላ የርቢ ቃሎቹ የተወሰኑ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህልም “አበላ“ እና “አስበላ” የሚሉ ቃሎች “አብልዐ” በሚል አንድ ቃል ብቻ ይወከላሉ፡፡

አማርኛና ኦሮምኛ ልክ ዕቃ እንደሚዋዋሱ ጎረቤታሞች ግንኙነታቸው ቃሎችን በመዋዋስ ላይ የተመሰረተ ሲሆን አማርኛ እና ሌሎች ሴማዊ ቋንቋዎች ግን አንድ ቤት ውስ ያለውን ተካፍሎ በጋራ እንደሚበላ ቤተሰብ ከመዋዋስ የዘለቀ መሠረታዊ የቋንቋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸንንም ለመረዳት ግእዝን፣ አማርኛን እና ዐረብኛን እንደ ምሳሌ በመውሰድ ቀጥለን እንመለከታለን፡፡ እስቲ፤ ከበረ፣ ወለደ፣ ፈታ፣ ተዋሐደ፣ ሰማ እና ከተበ የሚሉት ቃሎች በግእዝ፣ በአማርና እና በዐረብኛ የሚያስተላልፉልንን መልክት እንከታተል፡፡ የሚነግሩንን በጥሞና እናዳምጣ!

የግእዝ እና የአማርኛ አረባብ (በቅንፍ ውስጥ ያለው አማርኛ ነው)፡-

  • ከብረ (ከበረ)፤ ተከብረ (ተከበረ)፤ አክበረ (አከበረ/አስከበረ)፤ ክቡር (የተከበረ)፤ ክብርት (የተከበረች)፤ ክብር (ክብር)፤ አክባሪ (አክባሪ/አስከባሪ)
  • ወለደ (ወለደ)፤ ወላዲ (ወላጂ)፤ አውለደ (አዋለደ/አስወለደ)፤ መወልድ (አዋላጂ)፤ ሙላድ (መውለጃ)፤ ተወልደ (ተወለደ)፤ ውሉድ (የተወለደ)፤ ተወላዲ (ተወላጂ)፤ ወለድ/ወለት (ሴት ልጅ)፤ ወልድ (ወንድ፣ ልጅ)፤ ወልድና (ልጅነት)፤ ልደት (ልደት)፤ ትውልድ (ትውልድ)
  • ፈትሐ (ፈታ)፤ ፈታሒ (ፈቺ)፤ መፍትሕ (መፍቻ፣ቁልፍ)፤ፍትሕ (ፍትሕ)፤ ፍትሐት (አፈታት)፤ ተፈትሐ (ተፈታ)፤ ፍቱሕ (የተፈታ)
  • ዋሐደ (ተዋሐደ)፤ አውሐደ (አዋሐደ፣ አንድ አደረገ)፤ መዋሕድ (የሚያዋሕድ)፤ ውሑድ (የተዋሐደ)፤ ዋሕድና (ውሕደት፣ አንድነት)፤ ተዋሕዶ (አንድ የሆነ)፤ ዋሕድ (አንድ)
  • ሰምዐ (ሰማ)፤ ሰማዒ (ሰሚ፣ የሚሰማ)፤ ተሰምዐ (ተሰማ)፤ ስሙዕ (የሰማ፣ የተሰማ)፤አስምዐ (አስሰማ፣ አስደመጠ)፤ መስምዕ (አስሰሚ)፤ምስማዕ (መስሚያ፣ ማሰሚያ)፤ ተሳምዐ (ተሰማማ)፤ ስምዕ (ስሞታ፣ ስሙልኝ)፤ ስማዔ (ስመ-ጥር፣ ዝነኛ፣ የተመሰከረለት) ፤ ስሙዓት (ዝና)፤ ስምዓት (ዝነኛነት፣ መስማት)
  • ከተበ (ከተበ፣ ጻፈ)፤ ከታቢ (ጸሐፊ)፤ ክታብ (ጽሕፈት)፤ ተከትበ (ተጻፈ)፤ ክቱብ (የተጻፈ)

ከላይ የተጠቀሱት ስድስት ቃሎች የዐረብኛ አረባብ ደሞ እንደሚከተለው ይሆናል (በቅንፍ ውስጥ የአማርኛው ትርጉም ተመልክቷል)፡፡

  • ካቢር (ክቡር)፤ አክባር (ክቡር፣ ኃያል)፤ ታክቢር (ከበሬታ)
  • ወለደ (ወለደ)፤ መውሊድ (ልደት)፤  ማውሉድ (ልጅ)፤ ዊላዳ (ውልደት)፤ ዋላድ (ልጅ)፤ ታውሊድ (ትውልድ)
  • ፈትሓ (ፈታ፣ ከፈተ)፤ ሚፍታሕ (መፍቻ፣ ቁልፍ)፤ ፈቲሓ (መግቢያ፣ መክፈቻ)፤ ሊፈታሕ (መፍታት፣ መክፈት)፤ ፈታሓ (ፈቺ፣ ከፋቺ)
  • ወሕዳ (ውሕደት)፤ ተዋሐድ (ማዋሐድ፣ አንድ ማድረግ)፤ ዋሒድ (አንድ)፤ ሙዋሐድ (የተዋሐደ)፤ ታውሒድ (አንድነት)
  • ሳማ (መስማት)፤ ሳሚ (ዝነኛ)፤ ኢስማ (መስማት)፤ ሰምዔተ (ሰማ)፤
  • ከተበ (ጻፈ)፤ ያክቱቡ (ይጽፋል)፤ ይክቱብ (መጻፍ)፤ ካቲብ (ጸሐፊ)፤ ኪታባ (አጻጻፍ)፤ ኪታብ (መጽሐፍ)፤ ማክቱብ (ደብዳቤ)፤ ማክታብ (ቢሮ፣ ጽሕፈት ቤት)፤ ኢክቲታብ (ምዝገባ)

እንደተባለው አማርኛን ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግእዝ ለመናገር ሲሞክሩ ከፈጠሩት ከመጀመሪያው ቋንቋቸው (ከኦሮምኛ) ወደ አማርኛ ያመጡት መሠረታዊ የቋንቋ ባህሪ ምንድነው ነው? ለመሆኑ የአማርኛ እና የኦሮምኛ ግንኙነትስ ምን ዐይነት ነው?  እንደኔ እንደኔ መሠረታዊ ግንኙነታቸው ቃሎችን መዋዋስ ነው፡፡ ይኸ ደሞ የቋንቋዎቹ ተናጋሪዎች በነበራቸው ግንኙነት የተፈጠረውን ቁርኝት እንጅ ከአንድ ቋንቋ ቤተሰብ መምጣታቸውን ወይም አንዱ ከሌላው መምጣቱን አያሳይም፡፡ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ተዋደው ቢጋቡ እና አንድ ቤት ውስጥ ቢኖሩ ወደላይ ዘራቸው አንድ ሆነ ወይም ከአንድ ቤተሰብ የመጡ ናቸው ማለት አይደለም፡፡

ግሪክ እና ግእዝ የቃል መዋዋስ ሲነሳ በጣም ጥሩ ምሳሌዎች ሊሆኑን ይችላሉ፡፡ ግእዝ በሕንዳዊ-አውሮፓዊ የቋንቋ መደብ ከሚካቱት ከግሪክ፣ ከሮማይስጥ እና ከላቲን የሚዛመዱ አያሌ ቃሎችን ይዟል፡፡ ስኳር፣ ነጭ ሽንኩርት፣ በርበሬ እና ጠረጴዛ በግሪክ እና በግእዝ ተመሳሳይነት ካላቸው ቃሎች መካከል ሲሆኑ፤ ደባል፣ ክብሪት እና ባንዲራ ደሞ ግእዝ ከሮማይስጥ የተዋሳቸው እንደሆኑ የሚጠቁሙ መረጃዎች አልጠፉም፡፡

የግእዝና የግሪክ የጋራ የሆኑ ቃሎችን መዘርዘር ራሱን የቻለ ሥራ ቢሆንም ጥቂት ቃሎችን በመመልከት ግንዛቤአችንን መገምገም እንችላለን፡፡

ግሪክ……ግእዝ………አማርኛ………..ትግርኛ……..ላቲን………ሮማኒያ……ጣሊያንኛ……እንግሊዝኛ

ፒፔሪ……ፕፕሬ………በርበሬ…….……በርበረ…….…ፒፔሪስ……..ጲጴር………….ፔፔ……….…..ፒፐር

ሳካሪ………ሶከር……….ስኳር/ሽኳር…….ሽኮር…………ሰካሮ…..……ሱከር……..……ዙገሮ……….…ሹገር

ላምፓስ……ለምፓ………ላምባ…………ላምባ………..ላምፓስ…..….ላምፐ…..ላምፓዳ/ላምፓዲና….ላምፕ

ሩዚ……….ሩዝ….….…ሩዝ……………ሩዝ…………..ሪቼ……………ኦሬዝ……….ሪዞ…………..ራይስ

ፓፓስ………ጳጳስ………ጳጳስ……………ጳጳስ…..…….ፖፔ…………..ጳጰ…………..ፓኣፓ………ፖፕ

ኦክያኖስ…ውቅያኖስ.…ውቅያኖስ…..……ውቅያኖስ……፤ኡቺያኑስ………ኦቺያን………ኦቺያኖ………ኦሺን

ሰጠናስ…..ሰይጣን .…..ሰይጣን……….ሰይጣን………….ሳታን………….ሳጣና………ሳተና………ሴተን

ዲፕሎ….ደባል…….…ደባል…..………ደባል…………..ዱፕሉስ………….ዱብሉ………ዱፕሊካቶ….ደብል

ፓስካ…ፓሲካ/ፋሲካ…ፋሲጋ/ፋሲካ…..ፋሲጋ/ፋሲካ.……ፓዚካ………….ጳሲቃ……….ፓዚካ……………….

ስጎርዶ……ስጒርድ…..(ነጪ)ሽንኩርት….(ጸዓዳ)ሽጉርቲ……………………………………………………………………….

ዲያቮሎስ….ዲያብሎስ……………………………………ዲያቦሊ……………ዲያቮል………………….ዴቭል

ግእዝና ግሪክ፤ በግዜው በነበረው ግንኙነት ምክንያት በተለይም ከክርስትና አመጣጥ እና የሃይማኖቱ መረጃዎች ከግሪክ ወደ ሌሎች ቋንቋዎች መስፋፋታቸውን ተከትሎ በግእዝና በግሪክ መካከል የቃሎች መወራረስ ተፈጠረ እንጅ ሰዋሰዋዊ ሥርዓታቸውም ሆነ አገሳሰሳቸው እና የቃል አረባባቸው የተለያየ ነው፡፡ በቅርቡ ዘመን እንኳ አማርኛ ከፈረንሳይኛ ሹፌር፣ ፓርላማ፣ ዳንቴል፣ ዲስኩር፣ አምፖል፤ ከጣሊያንኛ ፋብሪካ፣ ካልቾ፣ አልቤርጎ፣ ፌርማታ፣ ኩሽና፣ አውቶቡስ እና ባልኮኒ እንዲሁም ከእንግሊዝኛ፤ ደርዘን፣ ኮምፒውተር፣ ሶፋ፣ሆቴል የመሳሰሉትን ቃሎች ተውሷል፡፡ ይሁንና ሰው ሁሉ የአዳም ዘር ነው ወይም ቋንቋዎች ሁሉ መጀመሪያ አንድ ነበሩ የሚለውን ድፍን ያለ ሃሳብ እናራምድ ካላልን እና በዛሬው የቋንቋዎች አመዳደብ መንገድ መሠረት አንሂድ ካልን አማርኛ ከፈረንሳይኛ፣ ከጣሊንኛም ሆነ ከእንግሊዝኛ ጋር የቅርብ ዝምድና እንደሌለው የምንጠራጠር አይመስለኝም፡፡

የአማርኛ እና የኦሮምኛ ጉዳይም ይኸው ይመስለኛል፡፡ በነገራችን ላይ ሰዎች አማርኛ ከኦሮምኛ ስለተዋሳቸው ቃሎች እንጅ ኦሮምኛ ከአማርኛ ስለተዋሳቸው ሲያወሩ ብዙ ስላላጋጠመኝ ኦሮምኛ ከአማርኛ ስለተዋሳቸው ቃሎችም ጥቂት ማለት እፈልጋለሁ፡፡

“ኦሮምኔት” የተባለ ድርጅት በቁቤ መንገድ ያዘጋጀውን ኦሮምኛን ወደ አማርኛ የሚተረጉም የቃሎች ዝርዝር መዝገብ ለማየት ሞክሬ ነበር፡፡ በዝርዝሩ ካገኘኋቸው ቃሎች መካከል የሚከተሉት ከአማርኛ የተወረሱ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ከአማርኛ እንዳልመጡ የሚያሳይ አሳማኚ መረጃ የሚያመጣ ሰው ካለ ሃሳቡን ከመቀበል ወደኋላ አልልም፡፡ ቃሎችን አንያቸዋ! ከኦሮምኛው ቃል ቀጥሎ ለዚሁ ቃል መሠረት የሆነው ቃል እና ርቢዎቹ በግእዝ እና በአማርኛ (አማርኛው በቅንፍ ውስጥ) ተቀምጠዋል፡፡

  • ማረሻ (maarashaa)- ሐረሰ(አረሰ)፤ተሐርሰ (ታረሰ)፤ሐራሲ (አራሺ)፤ሕርስ (እርሻ)፤ማሕረስ (ማረሻ)
  • ኬላ (kellaa)- ከልአ(ከላ፣ከለከለ፣አገደ)፤ተከልአ(ተከለከለ)፤ከላኢ (ከልካዪ)፤ምክላእ (ኬላ፣ መከልከያ)
  • ፍልጥ (falaxa)- ፈለጸ (ፈለጠ)፤ ፈላጺ(ፈላጪ)፤ፍልጽ (ፍልጥ)
  • ክብሪት (kibriitii)-ክብሪት (ክብሪት)……..ችብሪት (ሮማይስጥ)
  • መለኩሴ (moloksee)- መንኰሰ(መለኮሰ፣ተለየ)፤መነኰስ (መለኩሴ)፤ ምንኩስና (ምልኩስና)
  • ርካሽ (rakasa)- ረኲሰ (ረከሰ፣ ዋጋ አጣ)፤ርኩስ (የረከሰ)፤ ርኲሰት(ርካሽነት፣ ርኩስነት)
  • ሚዛን (mizaana)-መዘነ(መዘነ)፤ መዛኒ (መዛኚ)፤ ሚዛን (ሚዛን)
  • ፈላስፋ (falaasama)- ፈልሰፈ (ፈለሰፈ፣ፈለሰመ)፤ ፍልሱፍ (ፈልሳፊ፣ ፈላስማ)፤ ፍልሳፌ (ፍልስፍና፣ ፍልስምና)…..ፊሎሶፊያ (ግሪክ)
  • በተስኪያን (bataskaana)- ቤተ-ክርስቲያን፣በተክሲያን፣በተስኪያን (“ቤት” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ፣ በግእዝ እና በአማርኛ አንድ ሲሆን፤ የግሪኩ ሁለተኛ ፊድል “ቤታ”፣ የዕብራይስጡ ሁለተኛ ፊደል “ቤት” እና የግእዙ ሁለተኛ ፊደል “በ” (መጀመሪያ ላይ ግእዝ አ፣ በ፣ ገ፣ ደ የሚል አደራደር እንደነበረው ልብ ይሏል) አመጣጣቸው “ቤት” ከሚለው ቃል ጋር የተገናኘ ሲሆን የ “በ” ቅርጽም የቤት ወይም የቤት መግቢያ በር ቅርጽ እንዲመስል ተደርጎ መቀረጹ በኔ በኩል ከግምትነት ያለፈ ጉዳይ ነው፡፡
  • መርፌ (marfe)- ረፍአ (ሰፋ፣ጠቀመ)፤ ረፋኢ (ሰፊ)፤ ርፍእ (ስፌት)፤ መርፍእ (መስፊያ፣ መርፌ)
  • ገበያ (gabaa)- ጋብአ (ሰበሰበ፣አከማቸ)፤ ተጋባአ (ተሰበሰበ)፤ መስተጋብእ (መሰብሰቢያ)፤ ጉባኤ (ጉባዬ፣ ገብያ፣ መሰብሰቢያ)
  • በርበሬ (barbaree)- በርበሬ (አማርኛ)፤ ፕፕሬ (ግእዝ)፤ ፒፔሪ (ግሪክ)
  • አረም (aramaa)-አረመ (አረመ)፤ አረም (አረም)
  • ባህር (baarii)-ብሕረ (ተንጣለለ፣ ተዘረጋ)፤ ብሔር (አገር፣ ምድር)፤ ባሕር (ባሕር፣ የውሀ መከማቻ፣ ውሃማ ምድር)
  • አበባ (abbaaoo)- አበበ (አበበ)፤ አበባ (አበባ)
  • መቀስ (maaqassi)-መቈሰ (ቆረጠ፣ቀጠፈ)፤ መቀስ (መቀስ፣ መቁረጪት)

አትደክሙም፣ እንቀጥል? በቃ፤ እኔን ደከመኝ፡፡

 

ሲ. ፉት የተባለው እንግሊዛዊ እንደ አውሮፓዊዎቹ አቆጣጠር በ1913 በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ባሳተመው የኦሮምኛ-እንግሊዝኛ የቃል መፍቻ መጽሐፍ ላይ በጣም ብዙ የአማርኛ መሠረት ያላቸው የኦሮምኛ ቃሎች ሠፍረዋል፡፡ እነዚህን ቃሎች እዛሬው ኦሮምኛ-እንግሊዝኛም ሆነ ኦሮምኛ-አማርኛ ቃል መፍቻ ላይ ሳጣቸው “አዲሱ የቁቤ ትውልድ እነዚያን የነፍጠኛ ቃሎች የት አደረሳቸው?” የሚል ተንኮለኛ ጥያቄ መጣብኝና ሰይጣንና ክፉ ነገር እንዲርቁ በሚል ጸሎት አደረስኩ፡፡

አማርኛ ከኦሮምኛ ከተዋሳቸው ብዙ ቃሎቸ መካከል ለዛሬው ጉዳያችን “አንጋፋ”፣ “ጨፌ” እና “አዱኛ” የሚሉትን እንመልከት፡፡ በነገራችን ላይ ድሮ “አዱኛ” ኦሮምኛ ቃል መሆኑን አላውቅም ነበር፡፡ በአማርኛ ግን ቃሉን ከልጅነቴ ጀምሮ ዐውቀው ነበር፡፡ ለምሳሌ ያላገባ ልጅ ሲሞት ገና አዱኛውን ሳያይ ተቀጬ ይባላል-ደስታን፣ የሕይወትን ጣም፣ ባጠቃላይ ዓለምን ሳያይ ለማለት ነው፡፡ በኋላ “አዱኛ” በኦሮምኛ “ዓለም” ማለት እንደሆነ ለማወቅ ችያለሁ፡፡ እነዚህ ቃሎች በተለመደው የአማርኛ አረባብ መንገድ ሲራቡ አይታይም፡፡ ከሮማይስጥ/ጣሊያንኛ የመጣው “ፋብሪካ” የሚለው ቃል እንኳ ባቅሙ፤ “ፈበረከ”፣ “አፈበራረክ” ለማለት ሲሞክር እንታዘባለን፡፡  “አንጋፋ” ከሚለው “አነገፈ”፣ “አነጋገፍ” ፣ “ንጋፌ”፣ “መንገፍ” እና “መናገፊያ” የሚሉ ቃሎችን እንደርድር ብንል ትርጉም የላቸውም፡፡  አንድን ቃል ነጥሎ መዋስማ በማንኛቸውም ቋንቋዎቸ መካከል ሁልግዜ ያለ ነው፡፡ ከእንግሊዝኛ የመጣው “ኮምፒውተር” የሚለው ቃልም እንዲሁ ነው፡፡ “ኮምፒውተር” ከሚለው ቃል ውጪ ያሉት ተዛማጅ ቃሎች በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ የሞያሌ እና የመቀሌ ያህል ይራራቃሉ፡፡ “ኮምፒውተር” የሚለው ቃል እናት፣ አባት፣ እህቶች እና ወንደሞች በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ አይገናኙም፡፡ የእንግሊዝኛወ “ኮምፒውቴሽን” እና የአማርኛ ትርጉሙ “አቀማመር” አንድ ሊሆኑ ቀርቶ አይመሳሰሉም፡፡ ይኸም የሆነው አማርኛን እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች ስላልፈጠሩት ብቻ ሳይሆን አማርኛ እና እንግሊዝኛ በቋንቋ ቤተሰብ ዝምድና ስለሌላቸው ነው፡፡ የኦሮምኛና የአማርኛ ጉዳይም ተመሳሳይ ነው፡፡ ትናንት ከኦሮምኛ ወደ አማርኛ የመጣው “አንጋፋ” ይቅርና ጥንት ከግሪክ በግእዝ በኩል ወደ አማርኛ የመጣው “በርበሬ” ም እንዲሁ ነው፡፡ “በረበረ”፣ “ብርበራ”፣ “አበራበር” እያልን በግድ እናራባ ብንል ከ“በርበሬ” ጋር ሊገናኙልን አይችሉም፡፡ ከመሠረቱ ባድ ቃል ስለሆነ እና አመጣጡ አንድን ነገር ወክሎ (ቀይ የሆነውን የሚያቃጥል ነገር) ስለሆነ አማርኛ ውስጥ ከጎኑ የሚሆን ዘመድ አጥቶ ብቸኝነት ሲሰማው ይታያል፡፡

“ወደላ” የሚለው የኦሮምኛ ቃል ከሌሎች ትንሽ የተለየ ነገር ይታይበታል፡፡ “ወደላ” በኦሮምኛ “ወንድ አህያ” የሚል ትርጉም አለው፡፡ አማርኛ ይኸን ቃል ከኦሮምኛ የወሰደው ይሆን? እኔ ርግጠኛ አደለሁም ሆኖም ግን “ወደል/ወደላ” በአማርኛ “ትልቅ/ግዙፍ” የሚል ትርጉም ሲኖረው “ወደለ”፣ “መወደል” እና “አወዳደል” የሚሉ ርቢዎችም አሉት፡፡ “ወደለ” ሲባል “አጠበደለ፣ ጠብደል ሆነ” ማለት ነው፡፡ ይኸ ልጅ እንዴት ወደለ እባካችሁ አቤት መወደሉ ሲባል እሰማ ነበር ድሮ-እንደዛሬው አዲስ አበባ ላይ በሚታወቁ የአማርኛ ቃሎች ብቻ በተወሰነ አማርኛ ከመታጠሬ በፊት፡፡ እናም አማርኛ ከኦሮምኛ ከወሰደው በኋላ ራሱ አራብቶት ይሁን አይሁን አላወቅኩም፡፡ በኦሮምኛ ግን ወደላ ከሚለው ቃል ጋር የሚዛመድ እና ወንድም፣እህት ፣ አባት ወይም እናት ነኝ የሚል ቃል አላጋጠመኝም፤ ከቤተሰብ ተለይቶ እንደጠፋበት ያመለከተም አልተመዘገበም፡፡

አማርኛ በወጣትነቱ ወይም በጎልማሳነቱ ዘመን የተዋሳቸው እና ራሱ ያሳደጋቸው እልቆ መሳፍርት የሌላቸው የግእዝ መሠረት ያላቸው ቃሎች የሚያሳዩን ሐቅ ግን ከኦሮምኛው እጅግ የተለየ ነው፡፡ የግእዝ መሠረት ያላቸው፤ “ገዛ”፣ “ገደለ”፣ እና “ተጓዘ” ከኦሮምኛዎቹ “አንጋፋ”፣ “ጨፌ”፣ እና “አዱኛ” እንዴት እንደሚለዩ ቀጥላችሁ ተመልከቱልኝ፡፡

  • አንጋፋ (ኦሮምኛ)-›አንጋፋ (አማርኛ)፤ አንጋፉታ (ኦሮምኛ)-›………
  • አዱኛ (ኦሮምኛ)-› አዱኛ (አማርኛ)…… አበቃ፣ ሌላ ቃል የለም
  • ጨፌ (ኦሮምኛ)-›ጨፌ (አማርኛ)
  • ገዝአ (ገዛ)፤ ገዛኢ (ገዢ፣ የሚገዛ)፤ አግዝአ (አስገዛ)፤ እግዚእ (ገዢ፣ ጌታ፣ አዛዢ)፤ እግዝእት (ሴት ገዢ፣ እመቤት)፤ እግዚኦ (ገዥ ሆይ፣ ጌታ ሆይ)፤ ተገዝአ (ተገዛ)፤ ግዙእ (የተገዛ)፤ ግዝአት (ግዛት፣ መገዛት)፤ እግዚአብሔር (የአገር ጌታ፣ የዓለም ጌታ፣ የዓለም ገዢ)
  • ገደለ (ገደለ)፤ ገዳሊ (ገዳዪ)፤ አግደለ (አስገደለ)፤ ተገድለ (ተገደለ)፤ ግዱል (ግዳይ፣ የተገደለ)፤ ገደላ (ሬሳ)፤ ገደል (ገደል፣ መጣያ)፤ ተጋደለ (ተጋደለ)፤ ተጋዳሊ (ተጋዳዪ)፤ ገድል (ገድል፣ ውጊያ)፤ አስተጋደለ (አጋደለ)፤ አስተጋዳሊ (አጋዳዪ)
  • ግዕዘ (ተጓዘ)፤ ገዓዚ (ተጓዢ)፤ ገዓዝ (ጉዞ)፤ ግዑዝ (የተጓዘ)፤ ግዕዘት (ግዞት፣ መጓጓዝ)፤ ምግዓዝ (መጓጓዣ)፤ ጋዕዝ (ጓዝ)፤ አግዐዘ (አጓዘ)፤ አግዓዚ (አጓዢ፣ አጓጓዢ)

 

ማጠቃለያ

የአማርኛ ቤተሰባዊ ዝምድና ከግእዝ ወይም ከኦሮምኛ እንደሆነ ለማሳየት የተቻለንን ሞክረናል፡፡ አማርኛን ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግእዝ ለመናገር ሲሞክሩ ከፈጠሩት ከድሮ ቋንቋቸው  (ከኦሮምኛ) የተወሰኑ ቃሎችን ከቤተሰቦቻቸው ነጥለው ከመዋስ ሌላ መሠረታዊ የቋንቋ ባህርይ ወደ አዲሱ ቋንቋ (ወደ አማርኛ) ያላመጡ ይልቁንም ገና መናገር ከሚሞክሩት ከግእዝ ለአማርኛ ብዙ ነገር ያወረሱት ለነፍሳቸው ብለው ነው? እስቲ እዚህ ላይ ጥቅሱን እንደገና እናምጣው፤ “…. አማርኛ የተፈጠረው የኦሮሞ ተወላጆች ግዕዝ ለመናገር ሲሞክሩ ነው” የኦሮሞ ተወላጆች ሲባል ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ለማለት እንደሆነ እገምታለሁ- የሚወራው ስለ ቋንቋ እንጅ ስለሰው ዘር ስላልሆነ፡፡ ይታያችሁ እንግዲህ ኦሮምኛ የሚናገሩ ሰዎች (የኦሮሞ ተወላጆች) ከሚናገሩት ከራሳቸው ቋንቋ ሳይሆን ገና ለመናገር ከሚሞክሩት ከግእዝ ብዙ ነገር አውርሰው አማርኛን ፈጠሩት! “ልሳቅ ባይኔ ጥርሴስ ልማዱ ነው” አለ ያገሬ ሰው፡፡

መቼም የመሰለንን መጻፍ ቀላል ነውና እኔም ኦሮምኛ ከአማርኛ የተዋሳቸው ቃሎች ስላሉ እና የአማርኛ እና የኦሮምኛ የዐረፍተ-ነገር አወቃቀር ሥርዐት ተመሳሳይ ስለሆነ ብቻ፤ ኦሮምኛ ከአማርኛ የመጣ ቋንቋ ነው ብዬ ብጽፍ ካስፈለገም እከሌ የተባለው ጸሐፊ እንደዚህ ብሏል፣ አለቃ እንተና ይኸን ጠቅሶታል እያልኩ ብደረድርስ? ያኔማ ብዙ ሰዎች ሲሳደቡ፣ ሲንጫጩ፣ ሲጮሁ ወይም ሲያለቅሱ ይታየኛል፡፡ ለማንኛውም ውሸት መጻፍ እና  መተረክ ገደብ እና ለከት ቢኖረው መልካም ነው በሚል ሃሳቤን እደመድማለሁ፡፡

 

የዘር ማጥፋት አይደረግብኝ ብሎ የተነሳዉን የአማራ ሀይል ለማጥፋት እየተጉ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት መዘመር ይቻላል? እንዴት?

$
0
0

ሸንቁጥ አየለ
——————
የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት ከታወጀበት ይሄዉ ከሃያ አምስት አመታት በላይ ሆነ::በተግባርም በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማሮች በወያኔ የዘር ማጥፋት ፖሊሲ እንዲጠፉ ተደርጓል::ይሄን አማራ ህዝብ ላይ እየተከናወነ ያለ የዘር ማጥፋት ፖሊሲ በተግባር ጮክ ብለዉ ሲቃወሙ የነበሩ የአንድነት ድርጅቶች ነበሩ::በግንባር ቀደምትነት መኢአድ ዋናዉ ነዉ:: በማስከተልም ሰማያዊ ፓርቲ አማራ ላይ የተደረገዉን የዘር ማጥፋት ድርጊት ሲቃወም አስተዉለናል::

ልዩ ልዩ ኢትዮጵያዊያኖች (አማራ የሆኑም ያልሆኑም) በአማራ ህዝብ ላይ የተደረገዉን እና እየተደረገ ያለዉን የዘር ማጥፋት ፖሊሲ በተግባር ተቃዉመዋል:: ለምሳሌ እንደ ዶክተር ያዕቆብ ሀይለማሪያም ያሉ የህግ ምሁራን በሞያቸዉ የአማራን ህዝብ የዘር ማጥፋት ወንጀል በተግባር ሲቃወሙ ነበር:: የተወሰኑ የግል ሚዲያዎችም የአማራን ህዝብ የዘር ማጥፋት ወንጀል በተግባር ለማጋለጥ ሰርተዋል::ብዙ የግል ሚዲያዎች እና በዉጭ ሀገር ያሉ ዌብሳይቶች ነገሩን እንደገባቸዉ እና እንደሚፈልጉት እያንሸዋረሩም ቢሆን ለህዝብ ለማሳወቅ ተግተዋል::

የሚያሳዝነዉ ግን ፊት ለፊ የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት አጀንዳችን አይደልም : ይሄን ጉዳይ ዜና አንሰራም : ስለ አማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት ከዘገብን የኢትዮጵያን አንድነት እንጎዳለን የሚሉ ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ሚዲያዎችም በታሪክ መዝገብ ተመዝግበዉ ተቀምጠዋል:: ዝርዝር ዉስጥ አልገባም:: ስለማይጠቅም ብቻ ሳይሆን አሁን ላነሳሁት ጭብጥ ስለማይበጅ::

ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን የአማራ ህዝብ የተደረገበት የዘር ማጥፋት ወንጀል በሀይል: በምልዓት እና በወኔ ከፊት ሆኖ የሚጋፈጥለት የተደራጀ ፓርቲ እና ሚዲያ አላገኘም ነበር:: በተለይም የመኢአድ መዳከም ከተከሰተ ብኋላ አማራ ህዝብ ላይ እየተከናወነ ያለዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል መድበስበሱ ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ የአማራ ህዝብ እራሱ ብሶት ገፍቶት አትግደሉኝ ብሎ ወደ አደባባይ ወጥቷል::ይሄን የአማራ ብሶት እና መገፋት ብሎም ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ የተጎነጎነ ወንጀል በተደራጀ መልክ ለመጋፈጥ የአማራ ወጣቶች ሆ ብለዉ ተነስተዋል::

ብዙዎቹ እጅግ ብዙዎቹ የአማራ ወጣቶች ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ጸብ የላቸዉም::አንዳንድ እጅግ ጥቂት ሰዎች በደም ፍላት ኢትዮጵያዊነት እርም የሚል ሀሳብ ሲያራምዱ ቢደመጡም በብዙሃኑ የአማራ ታጋይ ሀይል ዘንድ ግን ተቀባይነት አላገኙም::በመሆኑም የአማራ ወጣት የአማራ ህዝብ ላይ የተቃጣዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል ማስቆም ዋና ግቡ መሆኑን ደጋግሞ እየገለጸ ነዉ::ይሄም ይበል የሚያስብል ነዉ::የአማራን ህዝብ ማዳን የአማራ ወጣት ስራ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቅን ዜጋ ሁሉ አጀናዳ ሊሆን ይገባዋል::

የአማራ ወጣት ሀይል መነሳሳት በኢትዮጵያ አንድነት ዙሪያ የተሰለፉ ሀይሎችን ለጊዜዉ የሚያዳክማቸዉ ቢመስልም አሁን ህዝቤን አማራን ዘሩን አታጥፉብኝ ብለዉ የተነሱ የአማራ ወጣቶችን መቃወም እና መሳደብ ብሎም እንዲጠፉ ተንኮል መጎንጎን ግን ለአጠቃላይ የኢትዮጵያ አንድነት እና ደህንነት መፍተሄ አይሆንም::ከዚህ የአማራ ሀይል ጋር ፍትጊያ ዉስጥ: እልህ ዉስጥ እና መጠላለፍ ዉስጥ የገባችሁ የአንድነት ሀይሎች ወደ መጠፋፋት ወንዝ ዉስጥ ለመመሰግ ባትፋጠኑ ጥሩ ነዉ::

አንድነት ምንድን ነዉ? አማራን የሚያህል እጅግ ሰፊ ቁጥር ያለዉ ህዝብ የዘር ማጥፋት ታዉጆበት አትግደሉኝ ብሎ ሲነሳ አይዞህ ልትለዉ ይገባል እንጅ ልትሰድበዉ እና ልታንቋሽሸዉ ይገባል ወይ? ወይስ ስለተቃጣብህ የዘር ማጥፋት ወንጀል እራስህን አትከላከል ልትለዉ ይገባል ወይ? አንድነትስ ጽንሰ ሀሳቡ ይሄ ነወይ? አንድ ግለሰብ እንኳን በደል ተፈጸመብኝ ብሎ ቢያምጽ እና ለተቃዉሞ ቢነሳሳ ያን ግለሰብ ማንቋሸሽ እና መሳደብ ይገባል ወይ? የዲሞክራሲ ጽንሰ ሀሳብ የሌሎችን ብሶት ማድመጥ አይደለም ወይ?

ኢትዮጵያ በምልዓት የምትድነዉ በዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ቀመር መሆኑን እዉር አሞራ አይስተዉም::ሆኖም ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለማምጣት እንዴት እንደሚቻል ሰፊ ብሄራዊ ዉይይት ሊደረግ ይገባዋል እንጂ እኛ የቀመርነዉ መንገድ ብቻ ነዉ የሚያስኬደዉ የሚለዉ ስሌት አዋጭ እንዳልሆነ ብዙ ተምሳሌቶችን እያነሱ ማጣቀስ ይቻላል:: አንድ እና ሁለት የፖለቲካ ፓርቲ ብቻዉን አሁን ያለዉን የተወሳሰበ ሁኔታ ሊፈታዉ እንደማይችል ግልጽ ሆኗል::

ስለሆነም የአማራዉን ሀይል ብቻ ሳይሆን የኦሮሞዉንም እንዲሁም የሌሎችን ኢትዮጵያዊ የብሄር ሀይላትን (ኢትዮጵያ ትፍረስ የማይሉትን ሀይላት ሁሉ ) በሰፊ ሀገራዊ ዲሞክራሲያዊ ጉዳዮች ሊመክሩ የሚችሉበትን ስልት መቀዬስ እና ማወያዬት ብቸኛ አዋጭ መፍተሄ ነዉ::የአደረጃጀት ልዩነት ላይ ሳይሆን መተኮር ያለበት ኢትዮጵያን በምልዓት እንዴት ማዳን እንደሚቻል በሰፊ ሀገራዊ ህሳቤ ላይ አቻቻይ መሰረት ሊጣልለት ይገባል::

የዘር ማጥፋት አይደረግብኝ ብሎ የተነሳዉን የአማራ ሀይል እየተቃወሙ እና እየሰደቡ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት መዘመር ቀልድ ነዉ:: የአማራን ሀይላት ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የብሄር ሀይላት ያገናዘበ ሰፊ ሀገራዊ አጀንዳ ሊታሰብበት ይገባል:: የኦሮሞ የፖለቲካ ሀይላት አንግበዉት የተነሱት አጀንዳን እና የአማራ የፖለቲካ ሀይላት አንግበዉት የተነሱት የፖለቲካ አጀንዳ እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ የብሄር ድርጅቶች አንግበዉት የተነሱትን የፖለቲካ አጀንዳ በዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያዊነት ስርዓርት ዉስጥ እንዴት ሊመለስ እንደሚችል የሚያመላክት ሀገራዊ የዉይይት መድረኮችን በመፍጠር: ኢትዮጵያ ትቀጥል ዘንድ ልዩነቶችን በማቻቻል እና ሁሉንም ሀይል ሀሳቡን በማክበር የተሻለ ሀገራዊ አጀንዳን በአካታችነት መቅረጽ ከአንድነት ሀይሉ የሚጠበቅ ስራ ነዉ:: የኢትዮጵያ አንድነት ሲባልም የአንድ ፓርቲ አጀንዳ እንዳልሆነም ማወቅ የምርጫ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነዉ::

እኔ እራሴ ያማምነዉ ብሎም ምናልባት ወደ ፖለቲካዉ ጠቅልዬ ከገባሁም የምደራጀዉ በአንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በሚያምን የፖለቲካ ጥላ ስር ነዉ::ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከእግዚአብሄር የተገኘ ሚስጥር መሆኑን አምናለሁና የሚሰማ ከተገኝ ለሁሉም ወገን የማስተላልፈዉ መልዕክትም ሁሉም ወገን ኢትዮጵያን በጥቅል በማዳን ላይ ልቡን እንዲያኖር ይሁን:: ኢትዮጵያ በምልዓት ካልዳነች አማራም ሆነ ማንኛዉም የኢትዮጵያ ህዝብ በአስተማማኝነት እና በቀጣይነት እንደማይፈወስ እሙን ነዉ::

ሆኖም የአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እየተከናወነበት እያለ እና ይሄን የዘር ማጥፋት ሂደት ለመቀልበስ የሚሰሩ ሀይላትን የሚቃወም:ጠልፎ ለመጣል የሚሰራ ወይም ከነዚህ ሀይላት ጋር ትንቅንቅ የሚገባ የአንድነት አካሄድ የሚያስከትለዉ መዘዝ ብዙ መሆኑን ሳላስረዳ ባልፍ አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የማዬት ምኞቴ ሀሰት ነዉ ማለት ነዉ::

በመሆኑም ሁሉንም ወገን የሚበጅ አካታች እና ልዩነቶችን በማቻቻል የሚሰራ ከድርጅትና ከፓርቲ ህሳቤ የዘለለ ሀገራዊ አጀንዳን ያነገበ መድረክ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል በሚሉ ሀይላት ሁሉ እንዲቀመር አሳስባለሁ:: አለዚያ አሁን ያለዉ የተቃዉሞ ጎራ አካሄድ እርስ በርሱም ተጠፋፍቶ ኢትዮጵያንም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሊያጠፋ የሚችል አካሄድ መሆኑን ሁሉም ወገን ግንዛቤ ሊይዝ ይገባዋል::

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርካት !

የአስራት አብርሃም “የህገ መንግስቱ ፈረሰኞች” ዕይታ እና የኢፌዴሪ ህገ መንግስት – በይርጋ አበበ

$
0
0

በይርጋ አበበ (ሰንደቅ ጋዜጣ፣ የካቲት 22/2009)

የደርግን መንግስት በትጥቅ ትግል ጥሎ ስልጣን ላይ የተቀመጠውና አሁንም ስልጣን ላይ ያለው መንግስት በ1987 ዓ.ም ዘውጌ ተኮር ከበሬታ የተቸረውን ህገ መንግስት አወጣ። ህገ መንግስቱ በመግቢያው ላይ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መርጠው በላኳቸው ተወካዮቻቸው አማካኝነት ኅዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ያጸደቁ መሆናቸውን  ሲል ይገልጸዋል። አሁንም ድረስ በስራ ላይ ያለውና ላለፉት 22 ዓመታትና ከዚያ በላይ ዕድሜ አስቆጥሮ አንድም ጊዜ ያልተሻሻለውን ህገ መንግስት ከረቂቅነቱ ጀምሮ እስከ ማጽደቅ ድረስ ያሉትን ሂደቶችና “የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች” ያደረጓቸውን ውይይቶችና ክርክሮች አቶ አስራት አብርሃም “የህገ መንግስቱ ፈረሰኞች” ሲሉ በመጽሀፍ መልክ ሰሞኑን ለንባብ አብቅተውታል።

የአቶ አስራት አብርሃምን መጽሀፍ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች ካጸደቁት የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጾች ጋር በማነጻጸር ከዚህ በታች በተቀመጠው መልኩ ለመዳሰስ ሞክረናል። መልካም ምንባብ።

 

የህገ መንግስት ታሪክ በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ረጅም የመንግስት ታሪክ ያላት አገር ብትሆንም ቃለ መንግስት (ህገ መንግስት) ሳይኖራት ቆይታ በ1923 ዓ.ም የመጀመሪያው ህገ መንግስት በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት መውጣቱን ብዙዎቻችን የምናውቀው ሀቅ ነው። አቶ አስራት አብርሃም ግን ከ1923 ዓ.ም በፊት በኢትዮጵያ መንግስታት የሚመሩበት ህገ መንግስት እንደነበረ ይገልጻሉ። ይህም ህገ መንግስት “ክብረ ነገስት” የሚለው መጽሀፍ መሆኑን በምሳሌ ሲያስቀመጡ “የህገ መንግስት ጽንሰ ሀሳብ በኢትዮጵያ ጥንታዊ መሰረት አለው። ከ1270 ዓ.ም ጀምሮ ዘመናዊ ህገ መንግስት እስከተረቀቀበት 1923 ዓ.ም ድረስ ክብረ ነገስት የሚባለው መጽሀፍ እንደ ህገ መንግስት ሆኖ አገልግሏል። ለዚህ ነው አጼ ዮሀንስ ‘ሀገሬና ህዝቤ ያለ እርሱ አይገዛልኝምና ክብረ ነገስት የተባለው መጽሀፍ በማን እጅ እንዳለ አፈላልገው ይላኩልኝ’ የሚል ደብዳቤ በ1872 ዓ.ም ለእንግሊዙ  ሎርድ ግራንቪስ የጻፉት” ሲሉ አገርና ህዝብ በህገ መንግስት ብቻ ይተዳደሩ እንደነበረ የአጼ ዮሐንስን ደብዳቤ በመጥቀስ ይገልጻሉ።

ህገ መንግስት ዓላማው ስለ መንግስታት የስልጣን ምንጭ መግለፅ እና የአስተዳደር ጉዳዮችን በተመለከተ አገርና ህዝብ የሚመሩበት የህግ ሰነድ ነው። ለምሳሌ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት የመንግስት ስልጣን ስለሚገኝበት መንገድ ሲገልጽ “በዚህ ህገ መንግስት ከተደነገገው ውጭ በማናቸውም አኳኋን የመንግስት ስልጣን መያዝ የተከለከለ ነው” ሲል በአንቀጽ ዘጠኝ ንዑስ አንቀጽ ሶስት ላይ ይገልጻል። የመንግስት ስልጣን ምንጩም በህዝብ ድምጽ ብቻ መሆኑን እንዲሁ በአንቀጽ 50/3 ይደነግጋል። ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ የመንግስት ስልጣን ለመያዝ መሞከር ወይ መፈንቅለ መንግስት ነው ወይም ደግሞ በዘመኑ አጠራር “ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል በመናድ የመንግስት ስልጣን መያዝ” ነው። ይህ ደግሞ ተቀባይነት እንደለሌለው ነው ህገ መንግስቱ የሚገልጸው።

ክብረ ነገስት የሚባለው መጽሀፍም የመንግስታት የስልጣን ምንጭ የትና እንዴት እንደሚገኝ ሲገልጽ “የስልጣን ምንጭ መለኮታዊ ኃይል ሲሆን ይህም በነብዩ ሳሙኤል አማካኝነት ለንጉስ ዳዊትና ለዘሮቹ የሰጠው ቅብዓ ንግስና ነው። የኢትዮጵያ ህጋዊ ገዥነትም የንጉስ ዳዊት ልጅ ከሆነው ከንጉስ ሰለሞንና ከንግስተ ሳባ ለሚወለደው ምኒልክ ቀዳማዊ ዘሮች እንደሚገባ ይደነግጋል። ከዚህ ውጭ ለሆኑ የነጋሲነት ክብር እንደማይገባ ሲገልጽም እስራኤላዊ ሳይሆኑ መንገስ ህግን መተላለፍ ነው በማለት ነው” ሲሉ አቶ አስራት ክብረ ነገስት የህገ መንግስት ሚና ሲጫወት መቆየቱን በማንሳት የኢትዮጵያን የህገ መንግስት ታሪክ ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ ከዘመን ዘመነ የተሸጋገሩት አጼዎችም በዚህ ህግ መሰረት ብቻ ወደ ስልጣን ማማ ላይ መውጣታቸውን ያስታወሱት አቶ አስራት “አጼ ቴዎድሮስ” ብቻ ራሳቸውን “የሰለሞን ዘር” ብለው ሳይመፃደቁ የነገሱ ብቸኛ መሪ መሆናቸውን ይገልጻሉ።

ለ700 ዓመታት ገደማ አገሪቱ እንደ ህገ መንግስት ስትተዳደርበት የቆየችው ክብረ ነገስት ከ1923 ዓ.ም በኋላ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት በወጣው የመጀመሪያው ዘመናዊ ህገ መንግስት ተተክቷል። ከዚያ ጊዜ በኋላም ሶስት ህገ መንግስቶች ስራ ላይ የዋሉ ሲሆን (በ1948፣ በ1978 እና በ1987 ዓ.ም የወጡት) አንድ ህገ መንግስት ደግሞ(በ1966 ዓ.ም) ተረግዞ ገና ሳይወለድ ተጨናግፏል።

የህገ መንግስቶቹ ቅቡልነት

የንጉስ ሰለሞን ዘር ነኝ ሳይሉ የነገሱትን አጼ ቴዎድሮስን ጨምሮ ሁሉም ጦራቸውን ሰብቀው አንደኛውን ባለጊዜ ገልብጠው በተራቸው ባለጊዜ በመሆን ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ የነበሩ አጼዎች “ክብረ ነገስትን ተቀብለው ነበር የሚነግሱት” ሲሉ አቶ አስራት ከዘመናዊያኑ ህገ መንግስቶች ይልቅ ክብረ ነገስት በህዝቡም ሆነ በአጼዎቹ ተቀባይነት እንደነበረው ገልጸዋል። “ከክብረ ነገሰት ቀጥለው የወጡት ሁሉም ህገ መንግስቶች ምንም አይነት ተቀባይነት ስላልነበራቸው ያወጧቸው መንግስታት ዕድሜ ሲያበቃ የእነርሱም ዕድሜ አብሮ ሲያበቃ ነው የሚታየው” በማለት ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ።

ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የህገ መንግስቶቹ ስሪት ህዝብን ለመጥቀም ሳይሆን የመንግስት ስልጣን የያዘውን አካል ስልጣን ለመጠበቅ የሚወጡ አሳሪ ህጎች በመሆናቸው እንደሆነ አቶ አስራት ሲገልጹ “ሁሉም በኢትዮጵያ የወጡ ዘመናዊ ህገ መንግስቶች ያላቸው ግብ ተመሳሳይ ነው። በእጅ የገባን ስልጣን ህጋዊና ዘላቂ ማድረግ ነው” ብለዋል።

የህገ መንግስቱ ፈረሰኞች ማንነት በአቶ አስራት አብርሃም ምልከታ

ቀደም ሲል በተጠቀሱት ሁለት ንዑሳን ርዕሶች የኢትዮጵያንና የህገ መንግስቶቿን ግንኙነት በአጭሩ ተመልክተናል። ከዚህ ቀጥሎ ባሉት ተከታታይ ክፍሎች ደግሞ ስለ ኢፌዴሪ ህገ መንግስት እና ስለ አስራት አብርሃም ምልከታ የሚመለከተውን ሀሳብ ይሆናል።

አቶ አስራት አብርሃም የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ጸድቆ በሰነድ መልክ ተዘጋጅቶ ቃለ መንግስት ሆኖ ለህዝብ ይፋ ከመደረጉ በፊት የነበረውን የማርቀቅና የማጽደቅ ሂደት አስቀምጠዋል። በመጽሃፋቸው “ቀዳሚ ገጽ” (መቅድም) ላይ መጽሃፋቸውን ያዘጋጁት ከ800 ገጾች በላይ ያለውን የህገ መንግስት ጉባኤ የተባለውን መዝገብ በማገላበጥ እንደሆነ ተገልጿል። “የህገ መንግስቱ ፈረሰኞች”ን ማንነት ሲገልጹም በ1986 ዓ.ም የተቋቋመውና 26 አባላት ያሉት የህገ መንግስት አርቃቂ ኮሚሽን አባላት ስራቸውን የሚያከናውኑት በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት ሳይሆን ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ በሚመራቸው ሀይል አማካኝነት እንደሆነ አቶ አስራት በመጽሀፋቸው አስፍረዋል። እነዚህን ሀይላትም የህገ መንግስቱ ፈረሰኞች ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

ጸሀፊው ሀሳባቸውን ሲያጠናክሩም “የኢፌዴሪ ህገ መንግስት የተረቀቀው በኢህአዴግ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደነበር የምንረዳው የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ምስክርነት ስንመለከት ነው። በአርቃቂ ኮሚሽኑ ውስጥ ኢህአዴግ የተወከለው በዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እና በአቶ ዳዊት ዮሐንስ ቢሆንም ማታ ማታ በአቶ መለስ ዜናዊ የሚመራ ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮቸ ስብሰባ ላይ ሁለቱ ተወካዮች በሚያመጡት ሪፖርት ላይ ተመስርቶ የዕለቱ ውሎ ይገመገማል። ጠንካራና ደካማ ጎኑ ተለይቶ በቀጣይ ውይይቶች ላይ በምን አቅጣጫ መሄድ እንዳለባቸው መመሪያ ይሰጣቸው ነበር” በማለት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሀፍ ላይ የገለጹትን ሀሳብ በማንሳት ህገ መንግስቱ ሲረቀቅ አቶ መለስ የሚመሩት ፈረሰኛ ቡድን እንደነበረ ገለጸዋል።

አቶ አስራት ከዶክተር ነጋሶ ምስክርነት በዘለለ በራሳቸው መላምት ተነስተው ህገ መንግስቱ ነጻ ሆኖ ያልተረቀቀ ሰነድ መሆኑን ሲገልጹም “የአርቃቂ ኮሚሽኑ የህግ ባለሙያ ሆነው የተሰየሙት ዶክተር ፋሲል ናሆም (የኢፌዴሪ ህገ መንግስትን ጨምሮን ጨምሮ በ1978 የወጣውን የኢህዴሪንና ስራ ላይ ሳይውል ተጨናግፎ የቀረውን የ1966 ህገ መንግስትን ጨምሮ ያረቀቁ ምሁር ናቸው) ህገ መንግስቱን ያዘጋጁት ከኢህአዴግ ቁልፍ ሰዎች ጋር እየተማከሩ ወይም የፓርቲውን የፖለቲካ ፕሮግራም እየተከተሉ መሆን እንደሚችል ለመገመት አይከብድም” ሲሉ ያስቀምጣሉ። ህገ መንግስቱም ስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት የፖለቲካ ፕሮግራሙን ህገ መንግስታዊ መልክ እንዲኖረው ለማድረግ ብዙ ርቀት ሂዷል ብሎ ደፍሮ መናገር የሚቻል ነው ሲሉ ሀሳባቸውን ያጠናክሩታል።

የኃይል አሰላለፍ በህገ መንግስቱ መጽደቅ ወቅት

ህገ መንግስት እንደሌሎች አዘቦታዊ ህጎች አይደለም። ሌሎች አዘቦታዊ ህጎች ህገ መንግስቱን ምርኩዝ አድርገው የሚነሱበት ሰነድ በመሆኑ ጠንካራ መሰረት ኖሮት ሊጸድቅ የሚገባ የህግ ሰነድ መሆን አለበት። ለዚህ ደግሞ ህዝብ ይወክሉኛል ያላቸውን ሰዎች መርጦ ወደ ጉባኤው በመላክ የህዝቡን ሀሳብ ወክለው በረቂቅ ሰነዱ ላይ ውይይት ይደረግበታል። ጠንካራ ውይይት ከተካሄደበት በኋላም የጉባኤው ሀሳብ ለህዝብ ቀርቦ ህዝቡ ይሁንታ ከሰጠው ህገ መንግስት ሆኖ ይጸድቅና የሁሉም የአገሪቱ ህዝብ የቃል ኪዳን ሰነድ ሆኖ ያገለግላል።

የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚጸድቅበት ወቅት 543 ተወካዮች የተሳተፉበት ቢሆንም “ከ86 በመቶ በላይ የሚሆኑት የኢህአዴግ እና አጋር ደርጅቶች አባላት” መሆናቸውን አቶ አስራት አብርሃም የህገ መንግስቱን ጉባኤ ጠቅሰው አስቀምጠዋል። በዚህም ምክንያት የሀይል አሰላለፉ ወደ አንድ አቅጣጫ ያዘነበለ እንደሆነ የሚገልጹት አቶ አስራት፤ እንደ ሻለቃ አድማሴ ዘገየ እና አቶ ዳንኤል በላይነህ በግል ከአዲስ አበባ ተወክለው ወደ ጉባኤው ከገቡት ሰዎች ውጭ ሌሎቹ ተመሳሳይ አቋም ብቻ ሲያራምዱ እንደነበረ የጉባኤው ቃለ ጉባኤ ያስረዳል ሲሉ አቶ አስራት ገልጸዋል።

ህገ መንግስቱ በሚጸድቅበት ወቅት በተነሱ መሰረታዊ ነጥቦች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን የሚጠቀሱት አቶ አስራት ሆኖም ሁሉም ነጥቦች በአሸናፊው ሀይል (በኢህአዴግ) የበላይነት የሚጠናቀቁ መሆናቸውን በመጽሀፋቸው ገልጸዋል። ለአብነት ያህልም በሰንደቅ ዓላማው ጉዳይ ላይ በተነሳው ነጥብ በሶስት ጎራ የተከፈለ እንደነበር አቶ አሰራት አብርሃም ገልጸዋል። አንደኛው ጎራ ቀደም ሲል የነበረው (አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለም ያለው) እንዳለ ይቀጥል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ጎራ ደግሞ የተወሰነ ማስተካከያ ይደረግበት የሚል (ምናልባት አሁን ያለው ሊሆን ይችላል) ሲሆን ሶስተኛው ጎራ ደግሞ ፈጽሞ ይቀየር የሚል እንደነበረ ነው ከአቶ አስራት መጽሀፍ ላይ የሰፈረው መረጃ የሚገልጸው።

ሻለቃ አድማሴ ዘገዬ እና አቶ ዳንኤል በላይነህ የተባሉ የአዲስ አበባ ተወካዮች “ባንዲራው የአባቶቻችን ተጋድሎ፣ የኢትዮጵያ ነጻነትና አንድነት የሚያሳይ የታሪክ ምልክት ነው። ከባንዲራው ላይ አንድ ነገር ቢጨመር ወይም ቢቀነስ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያዝንና ህገ መንግስቱንም እንደማይቀበል” አፅንኦት ሰጥተው መከራከራቸውን የገለጹት አቶ አስራት በሌላኛው ጎራ የነበረው የኢህአዴግ እና የአጋሮቹ አቋም ደግሞ “ባንዲራው ለህዝቦች ነጻነት የቆመ ሳይሆን ህዝቦች የታረዱበትና የተጨፈጨፉበት፣ የጭቆና፣ የወረራ፣ የግፍና የብዝበዛ ምልክት ሆኖ ለዘመናት ያገለገለ የገዥ መደቦች የጭቆና መሳሪያ ነው” የሚል እንደነበረ ገልጸዋል። በመጨረሻም የሰንደቅ ዓላማው ይዘትና ቅርጽ በህገ መንግስት አንቀጽ ሶስት በተቀመጠው መልኩ ተወስኖ ጸድቋል (አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለማት በእኩል መስመር ተቀምጠው መሀሉ ላይ ብሔራዊ አርማ ያለው። ዓርማው የብሔር በሔረሰቦች ህዝቦችና የሀይማኖቶች በእኩልነት በአንደነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንጸባርቅ ነው ይላል)

የሀገር ግዛት ወሰንን በተመለከተም የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ ሁለት “የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን የፌዴራሉን አባሎች ወሰን የሚያጠቃልል ሆኖ በዓለም አቀፍ ሰምምነቶች መሰረት የተወሰነው ነው” በማለት አስቀምጧል። ይህ አንቀጽ የህገ መንግሰቱ አካል ሆኖ ከመጽደቁ በፊት በተደረጉ ውይይቶች ከኢህአዴግ የተለየ ሀሳብ ሲያራምዱ እንደነበር በአቶ አስራት አብርሃም መጽሀፍ የተጠቀሱት ሻለቃ አድማሴ ዘገየ እና አቶ ዳንኤል በላይ ነህ ሲሆኑ እነሱም “የአንድ አገር ህገ መንግስት ሲቀረጽ አብይ ተግባር የአገሪቱን አንድነት ወሰኗንና የህዝቦቿን ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥ መሆን እንዳለበት፤ በተቃራኒው ይህ ህገ መንግስት ለዚህ እውቅና የማይሰጥ በመሆኑ እንደማይቀበሉት አመልክተው አባቶቻችንና አያቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አያሌ መስዋእትነት ከፍለው አንድነቷን ጠብቀው ያቆዩአትን አገር ይህ ህገ መንግስት ማስጠበቅ እንዳለበት አስገንዘዋል” ሲሉ አቶ አስራት በመጸሀፋቸው ገልጸዋል። በሌላ በኩል ያለው ሀሳብ ደግሞ ኢህአዴግንና አጋሮቹን ወክለው የሚከራከሩት ሰዎች አሰተያየት ነው።

ለምሳሌ አቶ አባይ ጸሀዬ “ባለፉት ስርዓቶች የነበረው የግዛት ወሰን አከላለልና አመለካከት አንድ ንጉስ ወይም ፊታውራሪ ከእነሰራዊቱ ተንቀሳቅሶ ሊደረስ የቻለበት መሬት ሁሉ እንደነበረ ገልጸው የአሁኑ የግዛት አወሳሰን ግን የአገርን አንድነት በጽኑ መሰረት ላይ የሚያቆም መበታተንን እና መከፋፈልን የሚያስቀር ሲሆን የዓለም አቀፍ ስምምነቶች መደንገጉም ከአጎራባች አገሮች ጋር ያለው ግንኙነትም በመልካም ግንኙነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ስለሚያደርገው በጦርነት ከመፈላለግ የሚያድን ነው” ሲሉ መከራከራቸውን የሚገልጹት አቶ አስራት፤ አቶ ግርማ አዱኛ የተባሉ ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ የአቶ አባይ ጸሀዬን ሀሳብ ደግፈው ሲናገሩ “ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የማታከብር አገር ስለነበረች ህዝቦቿ ከጎረቤት አገሮች ጋር የነበራቸው ግንኙነት የወንድማማች ሳይሆን በጥርጣሬ የመተያየት ነበረ። ከሶማሊያ ጋር በተካሄደው ጦርነት አያሌ ህዝቦች ያለቁትም በዚህ ምክንያት ነው። የኢትዮጵያ የግዛት ወሰንም ቀይ ባህርን የሚያካልል ነው የሚለው አባባልም አሮጌ ታሪክን ይዞ መንገታገት ነው” ሲሉ የኤርትራን መገንጠልም ሆነ የሶሜሊያ ጦርነት ምክንያቱ ኢትዮጵያ በተጠናወታት የድንበር መግፋት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን መናገራቸውን የአቶ አስራት አብርሃም መጽሀፍ ያስረዳል።

ከእነዚህ ነጥቦች በተጨማሪም የክልሎች አወቃቀርን፣ የፈዴራል መንግስት የስራ ቋንቋን፣ የመሬት ጉዳይና ስለመገንጠል የሚያተኩሩ የህገ መንግስቱ ክፍሎች ከመጽደቃቸው በፊት እንደተለመደው ሰፊ ክርክር የተደረጉ ቢሆንም በኢህአዴግ አሸናፊነት በመጠናቀቃቸው አሁን ያለውን መልክና ቅርጽ ይዘው ሊወጡ ችለዋል። ለምሳሌ አንቀጽ 39 ላይ የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠል የሚለው ክፍል ‘መገንጠል’ የሚለው ቃል እንዲገነጠል፣ የክልሎች አወቃቀር በማንነት ላይ ያተኮረ መሆኑ ቀርቶ በአስተዳደር አመቺነት እንዲሆን፣ መሬትም የመንግስት መሆኑ ቀርቶ የህዝብ እንዲሆንና ህዝብ እንደፈለገ እንዲሸጥና እንዲለውጥ መብቱ ሊሰጠው ይገባል የሚሉት የክርክር ሀሳቦች በእነ አቶ ዳንኤል በላይነህና ሻለቃ አድማሴ ዘገዬ በኩል የቀረቡ ነበሩ።

አዝናኝ እውነታዎች በአቶ አስራት አብርሃም መጽሃፍ

የአቶ አስራት አብርሃም መጽሀፍ ከላይ በተቀመጠው መልኩ ጠንከር ጠንከር ያሉ ቁምነገሮችን የያዘ ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን አዝናኝ ሀሳቦች አልታጡበትም። ለምሳሌ የመሬትን ጉዳይ አስመልከቶ ከትግራይ ክልል የተወከሉ ቄስ አለፈ ወልደእዝጊ የተባሉ የኢህአዴግ አባል “በአሁኑ ወቅት በህዝብ ትግል መሬት የሁሉም እንድትሆን በመደረጉ ከዚህ በኋላ መሸጥ መለወጥ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስን በ30 ብር እንደተሸጠው ያህል ይቆጠራል” ማለታቸው በቃለ ጉባኤው ሰፍሮ እንደሚገኝ አቶ አስራት ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የባንዲራን ጉዳይ በተመለከተ አሁን ያለው የኢፌዴሪ ሰንደቅ ዓላማ አርማ (መሀል ላይ ያለው ኮኮብ) በተመለከተ ራሳቸው አቶ አስራት “በዚህ ምልክት ዙሪያ ብዙ ውዥንብር እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል። አንዱ የትግሬ አምባሻ ነው ይላል። ነገር ግን ባንዲራው ላይ ያለው አርማ አምባሻ መጋገር የማትችል ሴት የጋገረችው ካልሆነ በቀር አምባሻ አይመስልም” ሲሉ በባንዲራው ምልክት ዙሪያ የሚሰጠውን አሉባለታ የገለጹበት መንገድ አዝናኝነት ይታይበታል።

“የሀገረ መንግስት ስያሜ” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር በጻፉት ላይ ደግሞ “የፂም መርዘም ሰውን ፈላስፋ አያደርገውም” የሚለውን የጣሊያኖች አባባል ተጠቅመዋል። ይህን አባባል የተጠቀሙት የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ አንድ “የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሚል ስም ይጠራል” የሚለውን ሀሳብ ለመተቸት የተጠቀሙበት ነው። በዚህ ርዕስ ስር ባሰፈሩት ጽሁፍ አብዛኞቹ አምባገነን መንግስታት ስያሜያቸውን “ዴሞክራሲያዊ እና ሪፐብሊክ” የሚል ተቀጥያ መጨመራቸው ፂምን አሳድጎ ፈላስፋ ለመባል ከሚደረግ ከንቱ ሙከራ ጋር አገናኝተውታል። ይህን ሀሳባቸውን ሲያጠናክሩም በአንድ ወቅት አስመራ ውስጥ ከአንድ ጣሊያናዊ ቤት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች አንዲት የትግሬ ኮረዳ ጣሊያናዊው ውሻውን “አሉላ” የሚል ስም ስለሰጠው ትበሳጭና አንድ ቀን ትገድለዋለች። ጣሊያኑ መጥቶ ውሻው ምን ሆኖ ሞተ ቢላት “ስሙ ከብዶት” ብላ እንደመለሰችለት ያስታወሱት አቶ አስራት የኢትዮጵያ መንግስትም አሉላ ሳይሆን አሉላ ነኝ ማለቱ (ዴሞክራሲን ሳይላበስ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሚል ስም መጠራቱ) ስሙ ከብዶት እንዳይሞት ስጋታቸውን የገለጹበት ክፍልም አዝናኝነት ይታይበታል።

 

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live


Latest Images