Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

“ሥር ነቀል ለውጦች ብዙ ዋጋ አስከፍለውናል … ሀገር በድርድር ነው የሚገነባው”

$
0
0

ከውይይቱ ምን ይጠበቃል?

በሀገሪቱ የተፈጠሩ ተቃውሞና ግጭቶችን ተከትሎ አንጋፋዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ጋር የድርድርና ውይይት መድረክ እንዲዘጋጅላቸው በተደጋጋሚ መወትወታቸው አይዘነጋም፡፡

የመጀመሪያው የድርድርና የውይይት መድረክም ባለፈው ሳምንት በፓርላማ ተካሂዷል። አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውይይቶቹና ድርድሮቹ ለመገናኛ ብዙኃን ፍጆታ የሚውሉና የይስሙላ እንዳይሆኑ ስጋት ቢኖራቸውም አብዛኞቹ በመድረኩ መዘጋጀት ደስተኞች ናቸው። ውይይቱ በታቀደው መሰረት በተከታታይ የሚቀጥል ከሆነ፣ እያንዳንዱ ፓርቲ የውይይት አጀንዳዎቹን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

ለመሆኑ ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ/መንግስት ጋር መወያየት ያለባቸው በምን ጉዳዮች ላይ ነው? ሂደቱስ? ከውይይቱ ምን ይጠበቃል? ከተወያዮቹስ?

የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፣ በዚህ ዙሪያ የጦማሪያንን ሃሳብና አስተያየት እንደሚከተለው አጠናቅሯል፡፡

“የተቃዋሚዎችን የመደራደር አቅም እጠራጠራለሁ” አጥናፈ ብርሃኔ (ጦማሪ)

የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና ትንሽ መላወሻ ቦታ የሚያመጣ ከሆነ፣ ድርድሩን እንደ መልካም ውጤት አድርጌ ነው የምወስደው፡፡ አሁን የሚደራደሩት ፓርቲዎች ይሄን ለማድረግ ከቻሉ ትልቅ ነገር ነው፡፡

ኢህአዴግስ እውነት የሚያምንበትን ነው እያደረገ ያለው? በሚለው ላይ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ከዚህ ቀደም የተደረጉ ድርድሮች አሉ፡፡ የምርጫ ስነ ምግባርን በተመለከተ ድርድር ተደርጓል፡፡ ግን ምን ውጤት አመጣ? ያ ድርድር ለማን ነው የጠቀመው? ከዚያ ድርድር በኋላ በምርጫ ምን ውጤት መጣ? ይሄ መመርመር አለበት፡፡ ይህ የምርጫ ስነ ምግባር ድርድር ላልተደራደሩ ፓርቲዎች ማነቆ ሆኖ ነበር። ብዙ ተጎድተውበታል። ችግሮችን ሲፈጥርባቸው ነበር፡፡ አሁን ላይም ተቃዋሚዎቹ የመደራደር አቅማቸውን እጠራጠራለሁ፡፡ ከዚያ ውጪ ገዥው ፓርቲ እስካሁን ምንም አይነት መለሳለስ እያሳየ አለመሆኑ ሌላው ተግዳሮት ነው።

የአድርባይነት ስሜት የህዝብን አመኔታ የሸረሸረ በመሆኑ የገዥው ፓርቲ መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ነው የምሰጋው፡፡ አቅም ኖሯቸው መደራደር ቢችሉ እንዲደራደሩባቸው ከሚያስፈልጉ ጉዳዮች ዋናው፡- ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ ጉዳይ፣ የፖለቲካ መጫወቻ ሜዳው መጥበብ፣ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ዶ/ር መረራን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ የመድረክ አመራሮች ካሉ፣ እነሱ መፈታት በሚችሉበት ጉዳይ ላይ መደራደር አለባቸው፡፡ በግሌ ውጤት ያመጣል ብዬ ባልጠብቅም ውጤቱን ከሂደቱ መጠበቅ አለብን፡፡

“ሀገር በድርድር ነው የሚገነባው” አቤል ዋበላ (ጦማሪ)

እንደ ሀገር ባለፉት ሁለት ስርአቶች የተፈፀሙ ስር ነቀል ለውጦች ብዙ ዋጋ አስከፍለውናል፡፡ ስር ነቀል ሲሆን ብዙ ነገር ወደ ኋላ ይመለሳል፡፡ አሁንም ቢሆን ስር ነቀል ለውጥ የሚታለም ከሆነ፣ ለህዝቡ የተሻለ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም፡፡ ያለውን ስርአት ለማስተካከል ንግግሩ መጀመሩ በራሱ ጥሩ ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡

ድርድር ሲባል የሚታወቀው በተመጣጣኝ ኃይሎች መካከል የሚደረግ ነገር ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ እውነታ፣ ተቃዋሚው በመንግስት በደረሰበት ተደጋጋሚ ጫና በጣም ተዳክሞ ነው የሚገኘው፡፡ ድርድሩ የምር ችግር ፈቺ እንዲሆን ከተፈለገ፣ በተቃዋሚው ወገን ያለውን የኃይል መሳሳት የሚቀንስ መሆን አለበት፡፡ ተቃዋሚው እንደፈለገ ህዝቡን በዙሪያው እንዲያሰባስብ ክፍት መሆን አለበት፡፡ መሪዎቻቸው የታሰሩባቸው ፓርቲዎች አሉ፡፡ እነዚህ መሪዎቻቸው እንዲለቀቁላቸው ያስፈልጋል፡፡ ይህ ከሆነ ተቃዋሚዎችም በህዝብ ዘንድ ያላቸው አመኔታ ስለሚጨምር ድርድሩ አቅምና ውጤት እንዲሁም ተአማኒነት ይኖረዋል፡፡ ድርድራቸውን በሚዲያዎች አጠቃቀም፣ በፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ላይ ቢያደርጉ የበለጠ ውጤት ማምጣት ይቻላል፡፡

ኢህአዴግ ለፖለቲካ ትርፍ ሲል ብዙ ጥፋቶች ሰርቷል፡፡ አሁን ግን ስልጣንን የማዳን ሳይሆን ሀገርን የማዳን ስራ ነው መስራት ያለበት፡፡ ይህ ድርድር የዚህ አይነት ውጤት ይዞ መምጣት አለበት፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም እንደ ፊጋ በሬ ኢህአዴግን ሳያስደነግጡት፣ በአግባቡ በኃላፊነት ስሜት ሊደራደሩ ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ ኢህአዴግም ይሄን እድል ማባከን የለበትም፡፡ ሀገር በድርድር ነው የሚገነባው፡፡

“ድርድሩ በቅንነትና በቁርጠኝነት መካሄድ አለበት” በላይ ማናዬ (ጦማሪና ጋዜጠኛ)

ድርድሩ ከልብ የሚካሄድ ከሆነ መልካም ነው። በተለያየ አጋጣሚ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ሆኑ ሌሎች በሃገራቸው ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ ሰዎች ሲጠይቁት የነበረው የነበረው ይሄንኑ የድርድና የውይይት መንገድ ነው፡፡ የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከልብ መነጋገር፣ መደራደር በየትኛውም ሁኔታ የሚደገፍ ነው፡፡ እኔ በግልም በተደጋጋሚ በፅሁፎቼ ስጠይቅ የነበረው መነጋገር ወሳኝ እንደሆነ ነበር። ይሄ ድርድርና ውይይት ግን ቅንነት በተሞላበት መንገድ፣ በደንብ ችግሮችን እያነሱ በጥንቃቄ መካሄድ አለበት። እንዲሁ ለይስሙላ የአንድ ሰሞን ጫጫታ ብቻ ሆኖ እንዳያልፍ በአንክሮ መከታተል ያስፈልጋል፡፡

በዚህ ድርድር ላይ በተቃዋሚዎች ቢነሳ ብዬ የማስበው፣ በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ለእስር ተዳርገውብናል ያሏቸው ሰዎች እንዲለቀቁ፣ የፓርቲ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች ታስረዋል፤ እነዚህ ተፈተው የድርድሩ አካል መሆን አለባቸው። በትክክል የድርድሩ አካል መሆን ያለባቸው የታሠሩ የፖለቲካ አመራሮች አሉ፤ እነሱ እንዲሳተፉ መጠየቅ አለባቸው፡፡

ሌላው ከህገ መንግስቱ ተፃራሪ ናቸው እየተባሉ በህግ ባለሙያዎች አስተያየት ይሰጥባቸው የነበሩ ህጎች ላይ ጠለቅ ያለ ድርድር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አንዳንዶቹ በህግ ባለሙያዎች ተጠንተው ቢሰረዙ ምኞቴ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ጋር በሚደረገው ድርድር ተቃዋሚዎች የህዝቡን ሃሳብና ስሜት በማንፀባረቅ ከልባቸው ሊሰሩ ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ መንግስት ቁርጠኝነቱን እስከ መጨረሻው የሚቀጥል ከሆነ ጥሩ ነው፡፡ ግን በተደጋጋሚ ካየነው ልምድ ስንነሳ፣ ቁርጠኝነቱ እስከ ምን ድረስ ነው በሚለው ላይ ጥርጣሬ ያድርብኛል። ግን ካለመነጋገር መነጋገሩ የተሻለ በመሆኑ ጠንክሮ መደራደሩ የተቃዋሚዎች ሚና ነው ብዬ አምናለሁ። በሌላ በኩል በድርድሩ የተገለሉ የፖለቲካ ሃይሎች እንዳይኖሩ ቢደረግና ሁሉንም አካታች ቢሆን መልካም ውጤት ያመጣል፡፡

የህዝቡ ድምፅ በሙሉ እንዲሠማ ከተፈለገ፣ አሁን ካሉት ፓርቲዎች በተጨማሪ ሌሎች ያገባናል የሚሉም መካተት አለባቸው፡፡ በዚህ መንገድ የሚካሄድ ከሆነ፣ ድርድሩና ውይይቱ ውጤት ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ አለኝ፡፡

“በድርድሩ ሁሉም እኩል መሆን አለባቸው” ናትናኤል ፈለቀ (ጦማሪ)

በአንድ አካል መልካም ፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ፣ ሌሎች ደግሞ ተለማማጭ ሆነው የሚካሄድ ድርድር ትክክለኛ ውጤት አያስገኝም። ድርድር ከተባለ ሁሉም በእኩልነት መጥተው፣ ለሁሉም ምቹ የሆነ ውጤት እንዲኖረው ነው የሚፈለገው፡፡ ነገር ግን አንዱ የፈለገውን ማድረግ የሚችል፤ ሌሎቹ ደግሞ አሉ ለመባል ያህል የሚገቡበት ድርድር የአንደኛውን ወገን ብቻ ፍላጎት ይዞ እንደሚጠናቀቅ መተንበይ ቀላል ነው። እኔ ለምሳሌ “ከዚህ ድርድር መልካም ውጤት ትጠብቃለህ ወይ?” ብባል፣ እንድጠብቅ የሚያደርገኝ ነገር ስላላየሁ አልጠብቅም፡፡ ከዚህ በፊትም እንዲህ ያለው ነገር በተለያዩ ስሞችና ቅርፆች ተሞክሯል፤ ግን ምንም የተለየ ነገር አላመጣም፡፡ ይሄም ያመጣል ብዬ አልጠብቅም፡፡

በድርድሩ ለምሳሌ “ህገ መንግስቱ ይከበር” የሚባል ከሆነ ምንም አዲስ ነገር የለውም፡፡ ዋናው ተግባር ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተደራድረው ቢለያዩ፣ አንደኛው ወገን ስልጣን ሁሉ በእጁ ያለ በመሆኑ ስምምነቱን እንደፈለገ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ግን ድርድሩ የታሠሩ ፖለቲከኞች ይፈቱ፣ ሚዲያው ነፃ ይሁን፣ የፖለቲካ ስልጣን እንጋራ . . . ከሆነ ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ፓርቲዎቹ የምርጫ ስርአቱ ላይ ብቻ ተደራድረው ሊወጡም ይችላሉ፡፡ ይሄ ደግሞ ያን ያህል ውጤት የለውም፡፡ በየትኛውም ሥርዓት ውስጥ በሃቀኝነትና በቁርጠኝነት ከተሰራ ለውጥ ይመጣል፡፡ ስለዚህ መንግስት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊያደርግባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ አጠንክረው ቢደራደሩ ነው መልካም የሚሆነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በፖለቲካ መሳተፍ አስፈሪ በሆነበት ሰዓት የተፈጠሩ ፓርቲዎች በመሆናቸው፣ይብዛም ይነስም በዚህ ድፍረት ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችን ልናበረታታ ይገባል፡፡ ሌላ ወካይ እስከሌለ ድረስ ህዝቡን ወክለው መደራደር ይችላሉ የሚል እምነትም አለኝ፡፡


የትግራይ ወፍ ገልብጣ ነፋች – አብርሃም በየነ

$
0
0

ታሪክ እንደ ፀሃፊው ነው። ትርክትም ዕውነቱና ውሸቱ እንደ ዶናልድ ትራምፕ አገላለጽ አማራጭ ሀቅ (alternate fact)የለውም። ነጭና ጥቁር ነው። አንድም ዕውነት አለያም ውሸት። አማራጭ ዕውነት ብሎ ነገር የለም። ታሪክና ትርክት ግን ለዘመናት የውሸትና የዕውነት ገጽታ ተላብሰው ሲጓዙ መኖራቸው አይካድም። ሩቅ ሳንሄድ “የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው” የሚለውን የወያኔን ክህደት ይጠቅሷል። “ኢትዮጵያ ጀግና ኖሯት አያውቅም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ ሆኖም አያውቅ……….” የመሳሰሉት የስብሃት ነጋ የተስፋ መቁረጥ ምልክቶችን ልብ ይሏል።    

የዛሬው አነሳሴ  እንኳ የስብሃት ነጋን ውሸት ለመዘርዘር ሳይሆን የመምህር ገብረኪዳን ደስታን የእንጨት ሽበት አበቃቀል ለመዳሰስ ነበር። የወያኔ ሽማግሌ የለውም። ከብዙዎቹ ራስ ላይ የምታዩት ነጭ ፀጉር የዕንጨት ሽበት ነው። የአረጋዊነት ምልክት አይደለም። ስለዚህ  የወያኔ ሽማግሌ፤ የጦጣ መንኩሴ፣ የጅብ ደፋር ፈልገን እናገኛለን ብላችሁ አትድከሙ። አልፈጠረላቸውም። እንደ ወያኔ ውሸታም፣ እንደ ጦጣ አጭበርባሪ እንደ ጅብ ፈሪ ፈልጋችሁ ካገኛችሁ እኔ ከዐረብ ዳኛ ፊት ቆሜ ቅጣቴን እከፍላለሁ።

  በባህላችን የሽምግልና ዕድሜ መቆንጠጫው ዕውነት ነው። ሁለት ፀጉር አብቅየ….. ይላሉ አባቶቻችን። ከዕውነት ውጭ ምንም ቃል የሌላቸው መሆናቸውን ሲያረጋግጡ። የወያኔ መሪዎች ግን ለዚህ ፀጋ አልታደሉም። ውሸታቸው ገደብ ዕድሜአቸው አደብ ገዝቶ አያውቁም። በቅርቡ መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ የተባሉ “የታሪክ ምሁር” ስለ ጎንደርና ስለ ትግራይ የግዛት ክልል ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል። ስለ ወልቃይት።

 በዚሁ ነጥብ ዙሪያ ቀደም ሲል ዶ/ር ገላውዲዎስ አራያና ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ቃለ ምልልስ አድርገዋል። የፊተኛው በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የኋለኛው ደግሞ በኢሳት ቴሌቪዥን። የሁለቱ ቃል ግን አንድ አልነበረም። ገላውዲዎስ “ወልቃይት በአጼ ዮሓንስ ዘመን የትግራይ ነበር” ብሎ ሲዋሽ፤ ልዑልነታቸው ግን “በኔም በአባቴም በአያቴም ዘመን ወልቃይት የጎንደር እንጂ የትግራይ ሆኖ አያውቅም” ሲሉ የህሊናቸውን ዕውነት ተናግረዋል። መምህር ገብረኪዳን ደስታ ግን እንደ ዶ/ር ገላውዲዎስ ህሊናቸውን ክደውታል። የሆነው ሁሉ ሆኖ ግን የወልቃይት ጎንደሬነት ወይም ትግሬነት በታሪክ ማስረጃ በፍርድ ቤት እሰጥ አገባ የሚወሰን ክርክር አይደለም። አሁን እንደ ተወሰነው ወደፊትም የሚወሰነው በጉልበት ነው። የጎንደሮችና የትግሬዎች የወደፊት የጅግነነት  መክሊት ወልቃይት ስለሚሆን አሁን ታሪክን ዋቤ ጠርቶ መከራከሩ አጉል ግንጭ ማልፋት ይሆናል። ወሳኙ ጠመንጃ ነውና ታሪክ አጣቅሶ መመለሱ ፋይዳ የለውም።  

“የታሪክ ምሁር” የተባሉት መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ ቀደም ሲል ቅኔ ማህሌትና ዜማ የተማሩት በጎንደርና በጎንደር አካባቢ በሚገኙ ት/ቤቶች እንደ ነበር ገልጸዋል። ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ዘመናዊ ትምህርታቸውንም የተማሩት በዚያው በጎንደር እንደ ነበር ገልፀዋል። ለጎንደርም ህዝብ  ክብርና ፍቅር እንዳላቸው አልሸሸጉም። የትግራይ ህዝብና የጎንደር ህዝብ ከቋንቋ በመለስ ልዩነት የላቸውም ሲሉም የህዝቡን የቆየ ትስስር ገልፀዋል። ዳሩ ይህን ሃቅ በመሰከሩበት አንደበታቸው ግን መልሰው ነጭ ውሸታቸውን ሲነሰንሱበት ተስተውሏል። “የትግራይ ህዝብ ለጎንደር ህዝብ ባለውለታ ነው። አጼ ዮሐንስ መተማ ላይ 100 ሺህ ትግሬ ወታደር ሰውተው ጎንደርን ከድርቡሽ ወረራ ታድገውታል። ወያኔም ጎንደርን ከሻለቃ መላኩ አገዛዝ ነጻ አውጥቶታል” ብለዋል።

ሀቁ ግን አጼ ዮሓንስ ለጎንደር ባለውለታ ሳይሆኑ ደመኛ ናቸው። ምራጭ ካሳ (አጼ ዮሐንስ) ለእንግሊዞች ጌታ አድሮ የናፒየርን ጦር ከምጽዋ እስከ መቅደላ እየመራ ያመጣ በሀገር ክህደት ወንጀል በታሪክ የሚጠየቅ ከሃዲ መስፍን ነበር። ለአጼ ቴወድሮስ ሞትም ተጠያቂ እርሱ ነው። ምራጭ ካሳ መቅደላ የነበረውን የአገሪቱን ነዋየ ቅድሳትና ቅርሳቅርስ በናፒየር ጦር ያስመዘበረ የእንግሊዞች ቅጠረኛ መስፍን ነበር። በኋላም በንግሥና ዘመኑ የወሎን እስላሞች ወይ ተከስተኑ(ክርስትና ተነሱ) ወይ አገሬን ለቃችሁ ውጡ በማለት እስላሞችን በግድ አከስትኗል። በዚህ ምክኒያት ኃይማኖታቸውን መለወጥ ያልፈለጉ በርካታ የወሎ እስላሞች  ወደ ሱዳን ለመሰደድ ተገደዋል። እነዚህም ስደተኛ የወሎ እስላሞች ቤተ መንግሥቱን ደብረ ታቦር አድርጎ የነበረውን አጼ ዮሓንስን ድል ነስተው ወደ አገራቸው ለመመለስ ከድርቡሾች ጋር ተባብረው ወደ ጎንደር ዘምተዋል። ጎንደርም በዘመቻዎቹ ሶስት ጊዜ በሳት ጋይታለች።  

ለቃጠሎው ተጠያቂ የሚሆኑት አጼ ዮሐንስ እንጂ ወሎየዎቹ ወይም ድርቡሾቹ አይደሉም። ሊሆኑም አይችሉም። ለወሎ እስላሞች መከፋትና መሰደድ ተጠያቂው ዮሐንስ ነበርና። ዮሐንስም 100ሺህ የትግሬ ጦር ሰውቶ ድርቡሾቹን ድል አደረገ የሚሉን “የታሪክ ምሁር” መምህር ገበረ ኪዳን የሞተው ወታደር ትግሬ ብቻ መሆኑን የታሪክ ማስረጃ አጣቅሰው  ግልጽ አላደረጉልንም። የሆነው ሁሉ ሆኖ ግን ንጉሡ ደብረታቦር ከከተሙ በኋላ ወታደራቸው ትግሬ ብቻ አልነበረም። ከተሰዋው ወሎየ፣ጎንደሬና ጎጃሜ ጋር አብሮ የሞተው ትግሬ ወታደርም የጌታውን ድል ላለማስነጠቅ ህይዎት ገበረ እንጂ ለጎንደር ህዝብ ብሎ አልነበረም። ህይዎቱን የገበረውም ጠላት አገርህን ወሯታልና ዝመት ስለተባለ ነበር የዘመተው። ለጎንደር ህዝብ የሚደማ ልብ ኖሮት አይደለም። ለዚህም ማረጋገጫው የንጉሡ አንገት መቀላትና መሞት እንደ ተሰማ ትግሬው ወደ አገሩ ለመመልስ ጊዜ አልፈጀበትም። ከንጉሡ ሞት በኋላ ቆይቶ የመከላከል ወጊያ ሲያደርግ የቆየው ትግሬ ያልነበረው ወታደር ነበር። ስለዚህ 100 ሺህ ትግሬ መተማ ላይ ለጎንደር ተሰዋ የሚለው የመምህር ገበረ ኪዳን “ታሪክ” ውኃ አይቋጥርም። አድዋ ላይ የተሰዋው ኦረሞ፣ወላይታ፣ጉራጌና አማራ ለትግራይ ህዝብ ብሎ እንዳልተሰዋው መተማ ላይ የወደቀውም ትግሬ ለጎንደር ብሎ አልነበረም። እናም በዚህ እረገድ የትግራይ ህዝብ ለጎንደር ህዝብ ውለታ አልዋለለትም። ንጉሡም እንደ ዛሬዎቹ የልጅ ልጆቻቸው ለጎንደሮች ባለውለታ ሳይሆኑ ደመኛው ናቸው። ካንድም ሁለት ጊዜ የበደሉት።

“በቅርቡ ጎንደር የተፈፀመው ነገር አሳዝኖኛል” ብለዋል “የታሪክ ተመራማሪው” መምህር። ለዚህም “አስዛኝ” ድርጊት የክልሉ መስተዳደር የትግራይን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት አስምረውበት አልፈዋል። የትግራይ ወፍ ገልብጣ የነፋችውም እዚህ ላይ ነው። “መበደል መበደል ወታደር በድሏል ግን ባላገር ይካስ” እንደ ተባለው ፍርድ መሰለኝ። የወልቃይትን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አፍኖ ወደ ትግራይ ለመውሰድ የአማራውን ክልል መስተዳደር በትምክህት ንቆ ጎንደር ውስጥ የአፈና እርምጃ የወሰደው ትግሬ ነው ወይስ ክብሩ የተደፈረው አማራ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት? ማነው ይቅርታ ጠያቂ ማንስ ነው ይቅርታ ተጥያቂ? የመምህር ገብረ ኪዳን ሽበት የእንጨት ሽበት ሲሆን የሚታየውም እዚህ ላይ ነው።

መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ ከፍ ሲል የተፈጸመውን በደል ገልብጠው “ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ነው” ሲሉም ድርጊቱን ተመጻድቀውበታል። ማነው ማንን ያጎረሰ? ማነው የማንን እጅ የነከሰ? ማነውስ ለማን ውለታ የዋለ? ጎንደር ነው ለትግሬ ወይስ ትግሬ ነው ለጎንደር ባለውለታ?

ባለፉት በርካታ ዘመናት ራሳቸውም ያልካዱት እርሳቸውንና ወላጆቻቸውን ጨምሮ ወደ ጎንደር እየመጣ ቀን አውጥቶ የሚመለሰው የትግሬ ቁጥር ይኸ ነው አይባልም። ጎንደር ለትግራይ ህዝብ የቀን መውጫ ሆና መኖሯ አይካድም። እኔ እስከ ማውቀው ድረስ የትግራይ ህዝብ በያመቱ ከህዳር እስከ ግንቦት ወር መጀመሪያ ወደ ጎንደር እየተሰደደ በመኸር ወቅት ሴቱ ቀርም ሲለቅም ወይም በችፍርግ የተለቀቀ አውድማ ሲጠርግ፤ ወንዱ ደግሞ አዝመራ አጭዶ እህል ወቅቶ በቀን ሠራተኝነት ሸቅሎ ያጠራቀመውን ወረት ወደ ትግራይ ይዞ ሲመለስ ነው።

     ከተማ የገባው ባለ እጅና ነጋዴም ወይ “ልዋጭ ልዋጭ” በማለት አለያም ሰባራ ገንቦ በመለሰን ቀን አውጥቶ ወደ ትግራይ ይመለሳል እንጂ ጎንደሬ ወደ ትግራይ ተሰዶ ቀን ያወጣበት ዘመን ኖሮ አያውቅም። ትግሬ እንጂ ወደ ጎንደርና ጎጃም ሄዶ ተምሮ የሚመለስ አማራ አልነበረም። ስለሆነም አእምሮውን በዕውቀት አጎልምሶ፤ ርሃቡን በዕህል ውኃ አስታግሶ፤ እርቃኑን ልብስ አልብሶ ትግሬን ሰው አድርጎ ያኖረው የጎንደር ህዝብ ነበር። በትግሬ እጁ የተነከሰውም የጎንደር ህዝብ ነው። እናም ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ማለት ያለበት ጎንደሬ እንጂ ትግሬ ሊሆን አይችልም። ለጫንቃው ጨርቅ ለእግሩ መጫሚያ ሳይኖረው ወደ ጎንደር ተሰዶ የጠነጠነ ሃብታም የሆነው ትግሬ ነው የበላበትን ውጭት ሰባሪ የሆነው። ወደ ሁመራና ወልቃይት በቀን ሠራተኛነት የሄደው ትግሬ ለማዳ ሆኖ ቀርቶ ነው ዛሬ አፉን ሞልቶ ወልቃይት የትግሬ ነው የሚለን።

  መምህር ገበረ ኪዳን ደስታ ከናዚና ከሞሶሎኒ ጋር አመሳስለው ኢህአፓን “የትግራይ ህዝብ ጠላት” ሲሉ ከሰውታል። ዐይን ራሱን አያይም ሆኖ እንጂ የትግራይ ህዝብ ጠላት ማንም ሳይሆን ትግሬ ነው። ለመምህሩ ግን አይታያቸውም። በጥቅም ታውረዋልና። እርሳቸውን ያሳሰባቸው የትግራይ ህዝብ ችግር አይደለም። የራሳቸውና የቤተሰባቸው ድሎት መደፍረስ ነው። ለዚህም ነው “ነቅናቂ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል” ሲሉ የተደመጡት። ጥሯቸውን ያደፈረሰውም ኢህአፓ እንደ ሆነ አማርረው ተናግረዋል። ግን በትግራይ ህዝብ ማሳበቡ አስገምቷቸዋል። እንዳው ለነገሩ ግን መምህሩ ከደረታቸው ጋር የተጣበቀው ሳንባቸው አቀበት አያስወጣቸው እንደሁ ባላውቅም ወደ አዲ ዩሮፕ ወይም ወደ አጋሜ አውራጃ ወደ አንዱ ወረዳ ጎራ ቢሉ የትግራይ ህዝብ  ለኢህአፓ ኢህአፓም ለትግራይ ህዝብ  ያለውን ፍቅር በተገነዘቡ ነበር። ስለ ሞሶሎኒና ስለ ናዚ ያላቸው ግንዛቤ ግን “የታሪክ ተመራማሪነታቸውን” እርቃኑን ያቆመው መሰለኝ። ያን አገላለጻቸውን ኢህአፓ ያስተማረው የበለሳ ወይም የጠለምት ገበሬ ቢሰማ “መምህሩ” ሁለተኛ ከሰው ፊት እንኳን የታሪክ ተመራማሪ ነኝ ሊሉ ፊደል የቆጠርኩ ሰው ነኝ ለማለት አይደፍሩም።

መምህር ገበረ ኪዳን ደስታ ወያኔንም እንደ አጼ ዮሐንስ ለጎንደር ህዝብ ባለውለታ ነው ብለውታል። መላኩን የመሰለ ገዳይ ያስወገደለት የወያኔ ሠራዊት ነው ብለዋል። ሀቁ ግን ለጎንደር ህዝብ ወያኔ ሌላው መላኩ ነው። እንዳውም ወያኔ ከመላኩ የከፋ ነው።  መላኩ የገደለው ሰውን ነበር። ወያኔ ግን ሰውም አገርም ገዳይ ነው። መላኩ አንድን ዘር ነጥሎ አልገደለም። የገደለው ትግሬውንም አማራውንም ኦረሞውንም ጉራጌውንም….. በጅምላ ነበር። ወያኔ ግን አማራ እንጂ ትግሬ አይገድልም። ዛሬ በጎንደር ገዳዩ ትግሬ ነው። ወያኔ ጎንደርን የነገ ብድር ከፋይ አድርጓታል። ያውም ከነ አራጣው።             ጥር 2009

 አብርሃም በየነ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተወሰኑ የአፍሪካ ሐገራት ማግኘት የነበረበትን 220 ሚሊየን ዶላር ማግኘት እንዳልቻለ ተሰማ… – (ንጋቱ ሙሉ)

$
0
0

አየር መንገዱ ከናይጄሪያና ግብፅ እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪካ ሐገሮች ነው 220 ሚሊየን ዶላሩን ማግኘት ያልቻለው ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያና ግብፅ እንዲሁም ሌሎች የአፍሪካ ሐገራት አገልግሎት የሰጠበትን ክፍያ ማግኘት ቢኖርበትም ሐገራቱ በነዳጅ ዘይት ዋጋ ማሽቆልቆል የተነሳ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላጋጠማቸው የአገልግሎቱን ክፍያ በዶላር መቀበል እንዳልቻለ ነው የተወራው፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ጉዳዩ ፈተና ሆኖብናል ሲሉ ነግረውኛል ብሎ መረጃው ፅፏል፡፡

ዩናይትድ ኤይርላይንስ እና ኤምሬትስ የመሳሰሉት አየር መንገዶች ናይጄሪያ የገጠማትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት አድርገው ወደዚያች ሐገር አንበርም ባሉበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ ናይጄሪያን በክፉ ጊዜዋ ከጎኗ አልርቅም፣ በረራዬም አይቋረጥም ማለቱ ይታወሳል፡፡

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለወሬው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡

 

ሱማሌ ና ደቡብ ሱዳን ከወያኔ ቁጥጥር ስር እየወጡ ነው ! ኬንያስ ትከተል ይሆን ? – ዘነበ ዘ ቂርቆስ

$
0
0

በተለይ ባለፉት 8 አመታት የወያኔ መንግሥት በኦባማ መንግሥት በሚደረግለት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እርዳታና የፖለቲካ እገዛ ከሰሜን እስከ መካከለኛው ደቡብ አፍሪካ ግዛት ድረስ የነበረው ትልቅ ተደማጭነት አሽቆልቁሏል ። በተለይ በዚህ መሰሪ ስራው የገንዘብ ምንጩ እንዳይደርቅበት ሲል የምስራቅ አፍሪካን ሰላም ማደፍረስ ዋናው ተግባሩ ሆኖ ቆይቷል ። በሰሞኑ ግን ያ የምናየው ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ አቅጣጫውን ቀይሯል ። የደቡብ ሱዳን ለብዙ አመታት የወያኔ ግዛት ሆና መቆየቷ ይታወቃል በተለይ ደግሞ የወያኔ ባለስልጣናት በደቡብ ሱዳን ውስጥ ከቀላል እስከ ከባድ ኢንዱስትሪ ውስጥ በመሰማራት የደቡብ ሱዳኖችን ሃብት አሟጠው ዘርፈዋል በዚህም ብቻ ሳያበቃ በአገሪቱ ላይ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግና በመሃል ደግሞ አስታራቂ በመምሰል አገሪቷን እንዳትረጋጋ አድርገው ቆይተዋል ሆኖም ግን ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ባላት ችግር ምክንያት እጇን በደቡብ ሱዳን ውስጥ እንድታስገባ እረድቷታል ለዚህም ደግሞ ለግብፅ ትልቁ የጀርባ አጥንት የሆነላት የትራምፕ አስተዳደር ፊቱን ወደ ግብፅ የመመለሱ ጉዳይ ነው ታዲያ ሁለቱ መንግሥታት ማለትም ግብፅና ደቡብ ሱዳን ባለባቸው የወያኔ ጥላቻ ምክንያት አዲስ ፍቅር ላይ ገብተዋል ። ባለፈው በተጠናቀቀው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ስብሰባ ላይ የወያኔው ስርዓት ትኩረቱና አጀንዳው ሆኖ የሰነበተው የአንድነት ድርጅቱ ስብሰባ ሳይሆን ግብፅንና ደቡብ ሱዳንን ለማስተናገድ ሽር ብትን ሲል የነበረው የሁለቱን መንግሥታት መለማመጥ ነበር የያዘው ።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ሰሞኑን ደግሞ በተካሄደው የሶማሌ ምርጫ ወያኔ አጥብቆ የለፋለት አሻንጉሊቱ የሶማሌ ፕሬዚዳንት ተሸንፎ በቦታው አዲስ የሱማሌ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ አብዱላሂ ሙሃመድ ፋራጂሆ ተሹሟል አዲሱ የሶማሌው ፕሬዚዳንትም በአገሪቱ ላይየወያኔን ጣልቃ ገብነት እንደማይፈልግ በምርጫው ቅስቀሳ ላይ አስታውቆም ነበር ። ታዲያ የወያኔው ስርዓት በዚህና በአለው የዶላር ችግር ምክንያት እንዲሁም የአሜሪካ የወቅቱ የፖለቲካ ስትራቴጂ መለወጥ ምክንያት በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ የነበረው የወያኔ ስርዓት የበላይነት ሁኔታ እየወደቀ ይገኛል ይህም ለምስራቅ አፍሪካ የሰላምና መረጋጋት ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚያደርግ ይታመናል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም በዚሁ አመት የሚካሄድ ሲሆን ምናልባትም የኬንያው ተቀናቃኝ ፓርቲም ካሸነፈ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወያኔ ስርዓት በአካባቢው ያለው የበላይነት ያከትማል ማለት ነው ። ወያኔ እንደሚታወቀው አሁን ያለውን የኬንያ መንግሥትን የሚደግፍ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የኬንያ ተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮች የወያኔን በኬንያ ፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እየከሰሱት ይገኛል ።

ምንአልባት ይህ ሁኔታ የአካባቢውን የፖለቲካ ሁኔታ ይቀይረው ይሆን ? ሁሉንም በሂደት የምናየው ይሆናል

ቸር እንሰንብት

የምድር ዕንቧይ – ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 10.02.2017 (ዙሪክ – ሲዊዘርላንድ።)

… እግዚአብሄርን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ፤ ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል፥ ለአጥንትህም ጠገን።
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፯ እስከ ፰)

ይድረስ ለብአዴን ላዕላይ መዋቅር   – ባህር ዳር።

እንዴት ባጃችሁ አይባል ነገር። በዐትን በፋሽስት አስጠምዳችሁ – እያሳረሳችሁ። ነገን በቤንዚን -እያቃጠላችሁ። የየ- ዘመኑ ዕንባ ላይበቃ ይሄው በመትረዬስ – ታሳጭዱታላችሁ። ሰላሙን አስቀምታችሁ ከአስገዳያችሁ ጋር ጽዋ – ታነሳላችሁመራሮች። ዛሬም እንደ ትናንቱ ባድማውን በደም አላባ ሲታጠን፤ እነ አቤቶ አባሪ ተባባሪ ሆናችሁ ሁለመናውን – አስቀማችሁት። በቀብራችሁ ላይ ድንኳን ጥላችሁ ፅዋ ማንሳታችሁ የወያኔ ሃርነት ትግራይን ህልም የአለማወቃችሁ ዕብንነት፤ ለዝክረ ታሪካችሁ የአመድነት መሰናዶ ማሟላታችሁ፤ – የበለጠውን ውስጣችሁን ገልጦ አሳየኝ። ስለዚህም የዕንባየን ድምጽ፤ የውስጤን ፍም ገላጭ ቃል ባጣ ቀንጫጭቤ – ልኬላችሁአለሁ። ከ25 ዓመት እንቅልፋችሁ ካባነናችሁ …

„ጊዜው ለትግራይ አስተማማኝ አይደለም ሲል ብአዴን አስታወቀ“  ምኑን ይሆን የምታሳውቁት? አንጋጦ ማዘዝ እንደሌለ ታውቁታላችሁ፥ ለነገሩ የሞት ደመመን መሸከሙም ሊያደነዝዝ ይችል ይሆናል።  http://www.satenaw.com/amharic/archives/30220 … የሆነ ሆኖ እስኪ እናያለን??? ቀበቶው ከቦታው ከኖረ? ካልተመደመደ?  – ካልተሽመደመደ?

ይሄው ስጦታየ። ለቃላቱ መፍቻ አልፃፍኩም፤ ስለምንተዋወቅ። ጫካ ወረድ ብላችሁ የምድር እንቧይን አምጥታችሁ በየቢሯችሁ ብታስቀጡት ግብዣዬ ነው። መካልም የንባብ ጊዜ። ከአምሳያ ስንኛት ጋር ገጥ – ለገጥ … ግብግቡን አስነኩት።

የምድር ዕንቧይ።

ህ!

ሱሪው ካለ፥ ጥሎህ ካልሸ – በክንድህ ከኖ?

ከታጠከው ከሰመ?

ካልተሸረሸ ወይም ካልተበረበ ወይንም ካልተጎረጎ?

እስኪ እንዬው ካልከሳሰረ፤

ፈራ ተቀልብሶ ካፈረ!

ተቀንጥሶ ካልፈረ።

————- የአባ ታጠቅ የዛ ጀግና፥

————- የእስመ-ለዓለም ገናና!

አሊ አትለው ዛሬ አሳይቶኃል ———-፥

——————————- ወንድነቱን ሲያመሰክር፤

——————————- ሚስጢራቱን ሲያሳጥር፥

——————————- ወኔው እንዴያ ሲር … ሲን

——————————- አሳይቶኃል ልበሙሉ ያ … የአደራ አር፥

——————————- የልብ አድርስ ለዳር ደንበር።

አንተማ፥ እየታየህ በቀብር ———፥

————————- ተሸክመህ፥ የአሞሌ ብድር፤ የክህት ቀንበር፥

————————- የጎርምዴ፥ የነር … ምንር፤

————————– መፈክሩ ላይሆን ለዘር፥

————————— መቦኑ ላያድን ከሥር፤

————————— አራዊቱ ሲዘፍንብህ፥ ውሎ ሲያድር፥

————————— የል እንጨት ግግር፤

————————— የአልቦነት ግርግር።

ነገረ አንተ የጅል ክምር —–፥

————————- እንጀራ እናት ለእትብትህ፥

————————- የእንጀራ አባት ለወገንህ፥

————————- የውስጥ ማዲያት የኮሶ ትል፤

————————- የመጋኛ የተባይ ድልድል፥

————————- የምድር ዕንቧይ ዝክንትልትል።

መኖር ካልከው ————-፧

————— አጎንብሰህ መገመድ

————— ተገርድፈህ ማጎብደድ

—————- ከአንገት በላይ መጎመድ

—————- ተሸርክተህ ማቅራራት

—————- ተቀፍድደህ መተንፈስ

—————- ተቆራርጠህ መለሰን

—————- አዳር ካልከው ይሁንል¡

—————- ቀብርህ ሆኖል መሰንበት

ያየንህ —–

——- እርሳው አንተ ግምል ዘው፥

——- ለደም መሬት አጋፋሪው … ዝባዝኬው፤

——- መቼ ሆንለት … ለአንተነትህ???

——- የክህት በት ነው ህብረትህ።

አያ ሆይ¡ የደደቢት ግር —–

———————— ይነዳኃል … አሳምሮ፥

———————— የትዕቢቱ …  ማሰሮ፤

———————— የጥጋቡ … ከበሮ፥

———————— የፈንድሻ … ጉሮሮ።

አትሸንግለኝ! የችካል ግልል፥ የምስማር ሮ ———

—————————- አትንገረኝ ስለ ዕንባዬ፥

—————————- ቃጠሎ ነህ ለአንቫዬ።

—————————- ቃር ሆኗኝ የአንተው ነገር፥

—————————- ስለከንቱ ልዩ ገር።

ግርዝዝ ———–

——– ስርዝ ድልዝ

——– ግን– ጉምዝዝ፥

——— ቅልብ – ድንብዝ፥ … ቡዝዝ፤

——— ገለማኝ! … የአትራኖስህ ንዝንዝ፥

——— ጥ-ዝ-ጥ-ዝ … ጥንብዝዝዝዝዝ።

ልበሱ፥ የነባለቀኖ አሸርጋጅ —-

————————- ለክስመትህ ለአንተ … ለሹመኛው¡

————————- ለቅርፊቱ … ለነቀርሳው፤

————————- መኖርህን እሱን እርሳው!

————————- የል … ግርሻው።

አንተው —

—— ታሪክህን … አሳመህ፥

—— ለትውፊት ወጋት ሆነህ፥

—— ለደጉ ህዝብ ማጭድ ሆነህ፤

—— በሌነት የተፋህ፦

—— አለት ነህ!

ዬብል ግብር ——–

————- ጀንበር ልትሽ … አሽቆልቁላ፥

————- ምር ሆነ ያ…  ባድማ፦ በአለ ባላ፦

————- በብል በተከዘነ ገ

ተጠዬቅ! በለው እስኪ ህሊናህን —–፧

—————————— ውርዴ ለአንተ ለህሊና

—————————— ስላቅ ሲሆንልህ ስንቅ

—————————— „በቃኝ“ ማለት በቀናቀን

—————————— „እንቢኝ“ ማለት ሰቀቀን

—————————— ሆኖ አረፈው የአንተው ዝናህ¡

ሥለሥያሜህ ——፤

———– ስለውርዴት ቅንዝረኛው ሰብዕናህ …፥

———– ስለሰው ልጅ ሞገስ የህ፤

———– በመሆንህ ውስጥ የፋህ!

———– ጎልቶ ወጣ ከብትነትህ!

አትነግድ በነኝ ——

————– ሞት ጥርኙ ቢቃላህ ወይ ቢከላህ?

————– ይሻል ይሆን እንደ ሩሕህ ርቃንህ?

————– የባንዳ ልጅ ሽምጥ ሲጋልብህ፦

————– ተጠኽም ትዘግናለህ … ትድኃለህ፤

————– ትብያ ተብለህ ትዘፍናለህ።

አረንቋነት ስለአሰኘህ ይሄውልህ —-

——————————– ለገዳይህ ወበራ ነህ፦

——————————– ለመጥፊያህም ሠራዊት ነህ፦

——————————– ለሴራውም አርበኛ ነህ፦

——————————– ወልደግራ ግርንቢጥ ነህ፤

——————————– የመርዝ ብልያጥ ገመና ነህ።

ስንብቱ ———-

—— ስንብቱ የዛ ከንቱ፤

—— አደራ እንደበላ ሆኗል አሟሟቱ፤

—— ደመር ሆኖል ግምቱ፤

—— ያለወረ ካባቱ፤

—— ሹልከቱ … የውልፊቱ።

 

„ … ቀኑ መሽቷልና የማታውም ጥላ ረዝሟልና ወዮልን። (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ከ፬ እስከ ፭)

 

„አማራነት ይከበር!“

አማራነት ሰባዕዊነት ነው!

መሸቢያ ጊዜ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

ነገረ ቴዲ አፍሮ

$
0
0

ቴዲ አፍሮ

ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ ሲባረሩ የልጅነት ጓደኞቻችንን አቅፈን እቃቸውን አብረን አሻሽጠን አልቅሰናል:: ያኔ ላቅመ ፖለቲካ ላልደርሰነው ለብዙወቻችን “ኤርትራ ትገንጠል” ብለው ድምጽ ከሰጡ ወላጆቻቸው ይልቅ ሜካፕ ያልደረሰበት የነነቢያት ውበት ፤ የነርሻን የልጅነት ቁንጅና ፤ የነስምኦን አብዶ ፤ የነመዋእል ተንኮል ፤ የነሚካኤል ጅልነት ዘላለም ከልባችን የማይወጣ የልጅነት ትዝታችን ነው:: ኋላ ላይ ለሻእቢያ ብር ታዋጣ እንደነበር የተወራው ለተተንሳይ እንኳን አሮን ልጇ የፍጥር ጀግናችን ነበር:: በባዶ እግሯ ስትሮጥ ጀርባዋ ላይ የሚጨፍረውን ጸጉሯን እያዩ ከነቢያት ጋር ሌባና ፖሊስ መጫወትን የመሰለ ደስታስ የት ነበረ??!! “መሬቱን እንጂ ሰውን አትወዱትም” ሲሉን ፤ የኖርነው ሃቅ ፤ የነ አወት የነ ልዋም ፊት አይናችን ስር እየቆመ በከሳሾቻችን ላይ ይስቃል:: ይህንን ሁሉ የልጅነታችንን አንድ ጉማጅ ከቴዲ አፍሮ በላይ የዘከረልን ማን አለ?! ቴዲ አፍሮ “ፊዮሪና”  እያለ ሲጣራ ‘ግራ የገባው ሰው ዘፈን ፣ የድሮዋን ኢትዮጵያ ናፋቂ’ ይሉታል:: እሱ ግን የብዙወቻችንን እውነት

“እስኪያበቃው አይኔን ላይንሽ የሱ ስራ

ጓል አስመራ ጓል አስመራ”  

እያለ መጫወቱ ከድንበር ባሻገር ስላለው ሰውኛ ወግ ማውራቱ ባይሆን ኖሮ አስቀድሞ ዳህላክን ባነሳበት ዜማ “ዝሆኖች ተጣልተው ሰበሩት ድንበሩን” ይል ነበርን?  እኛ የከሳሾቹን ሸር ሳይሆን የቴዲ አፍሮን ፍቅር እናውቃለን::

ከምድላየ!!! 

ቴዲ አፍሮ ግዙፍ ነው! ቴዲ አፍሮ ብዙ ነው! ቴዲ አፍሮ አባቶቻችን የሰጡን፣ ዘመዶቻችን የሞቱላት ፣ ባወረሰችን መከራ ሁሉ የማንጠየፋት የኢትዮጵያችን ድምጽ ነው::ኢትዮጵያ ውስጥ የአርቲስትነት ከፍታው አላሙዲን ቤት መንከባለል እና ዳንጎቴ ደረጃ ላይ ማሽቃበጥ በሆነበት በዚህ ዘመን የካሳሁን ገርማሞ ልጅ  በኩራት እና በታላቅነት የህሊናው ሰው ሆኖ ይኖራል:: ጫታቸውን እንኳን በሼኩ ምጽዋት የሚቅሙ እነ ነዋይ ደበበ ባሉበት አገር ቴዲ አፍሮ ‘ካንትሪ ክለብ እርጥባንህን አልቀበልም :: እኔ መኖሪያ ቤቴን ሰርቼ እንጂ ተመጽውቼ አልወስድም’  በማለት የከተማውን ምርጥ ማንሽን ቅንጡ ቤት እጅ መንሻ ወደጎን የሚገፋ ኩሩ አበሻ ነው:: ዛሬ ዛሬ  “ኩሩ አበሻነት” እንደ ቅርስ በየአዛውንቱ ባዮግራፊ ውስጥ እንጂ መሬት ላይ በማይገኝበት በዚህ ዘመን የካሳሁን ገርማሞ ልጅ ከገንዘብ ከፍ ብሎ ፣ ለገዥው ስልጣን ከማሽቋለጥም ራሱን ሰውሮ ለህሊናው ታምኖ ይኖራል:: አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር እንዲል !!

ተቦርነ የሚባል ባህላዊ በያጅ ቴዲአፍሮ ላይ በአደባባይ የዘመተ የመጀመሪያው ሰው ነው:: የተቦርነ ባህላዊ ትችት ያንድ ሰሞን መንጫጪያ ከመሆን አልዘለለም:: ወዲያው ግን የቴዲ አፍሮ ስራዎች ትችት አዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ጉብ አለ:: አሁን ትችቱ ከመደዴ ነቆራ ወደ ‘ኢንተሌክቿል’ ሂስ አደገ:: ስራዎቹም ‘ቴክኒካሊ’ ተብጠለጠሉ:: ትችቶቱቹ ከአዳማጭ ‘ኦፒንየን’ነት የዘለሉ እንዲሆኑ ሰርጸ ፍሬስብሃትም የበኩሉን እንዳዋጣ እንገምታለን:: ያኔ ይህ መሆኑ ችግር አልነበረውም:: ቴዲ እንደ ማንኛውም የጥበብ ሰው ከትችት አያመልጥም:: ዛሬ ላይ ግን ኬኔዲ መንገሻ ከታፈነ ሰርኑ ስር በሚለቃት ዘፈን ሲቀውጥ የኖረ አገር እና ሚካኤል በላይነህ የሚባል እጅግ መደበኛ የሆነ ድምጻዊን አግንኖ ማሳየት የሚፈልግ ልሂቅ ቴዲ አፍሮን በድምጹ እና በድምጹ ብቻ መበየን እና ማሳነስ ሲፈልግ ታዝበን እንስቃለን:: ስቀንም እንናገራለን:: ያን ሰሞን ሰርጸ አንዱ ጋዜጣ ላይ “ቴዲ በተለያየ ሬንጅ መዝፈን የሚችልና በርካታ የድምፅ ቴክኒኮች አፈራርቆ መጠቀም የሚችል አይደለም” ማለቱን እየጠሩ ዛሬም ጽሁፋቸውን ለማድመቅ  የሚሞክሩ ወዳጆቻችን ስለምን እዚህ አሳብ ላይ ተሰፉ የሚለው ነገር ግርም ይለናል:: የሙዚቃችን ከዋክብት ጥላሁን ገሰሰ እና ሙሉቀን መለሰ የ6ኛ እና የ4ኛ ክፍል ተማሪዎች በነበሩበት አገር ቴዲ አፍሮ ““ትምህርት ቤት የመግባት ድፍረቱ ሊኖረው ይገባል፤ ታሪክ ፍልስፍናና ቋንቋ ኮርሶችን ቢወስድ አቅሙን ይበልጥ ማጎልበት ይችላል ብዬ አስባለሁ” የሚለውን የሰርጸ ፍሬስብሃት የሰከረ ትችት ዛሬም አለአውዱ ስቦ ማምጣት እጅግ አስቂኝ ተግባር ነው [ላውረን ሂል እየተንከባለለች የምትስቅ ይመስለኛል] :: መሃሙድ የትኛው ኮሌጅ ተመርቋል? አለማየሁ እሸቴ የትኛው ካምፓስ ነበረ? አሊ ቢራ ካገር ከመውጣቱ በፊት እና ተወዳጅ የሆነባቸውን ዘፈኖች በዘፈነበት ዘመን ስንተኛ ክፍል ነበረ? ብዙ መጠየቅ ይቻላል:: ቴዲ እጅግ ዝነኛ እና ገዢ ከሆኑ ጥቂት ዘፋኞቻችን አንዱ በመሆኑ አይን ማረፊያ መሆኑ አይገርምም ነገር ግን ቴዲ ላይ በኢንተሌክቿል ስም የሚቀርቡበት ክሶች እሱ ላይ ብቻ ያተኮሩ እና ፌይር ያልሆኑ ናቸው ብሎ መደምደም ይቻላል:: 

ቴዲን የሚጠሉት ለምን ይጠሉታል?? የትግሬ ብሄርተኞች ቴዲ ላይ በጥላቻ ከዘመቱት የመጀመሪያዎቹ ናቸው:: ልክ በማሲሞ ዱቲ ሱፍ ቂቅ ብለው አዲስአበባ እንደገቡ ነገር ቁምጣችን ለምን ተጠራ በሚል እንዲሁም “ያስተሰርያል” የምርጫ 97 አስማት ሰልፍ ዋና ግብአት መሆኑን ተከትሎ ጠምደው ይዘውታል:: የሚገርመው ነገር ቴዲን በግለሰብ ደረጃ ያጠቁት ሰዎች ሆነው ሳለ ፤ ቴዲ ግን መሪያቸው ቢሞት ለቅሶ ለመድረስ ልቡን ያልከበደው ፣ የሚያወራውን የሚኖር ከፍ ያለ የሞራል ማማ ላይ የተሰቀለ ልኡል መሆኑን ማሳየቱ ነው:: እንደ ኃይሌ ገብረስላሴ እንባና ንፍጥ ሳይቀላቅል ፣ እንደ ትግስት ወይሶ የማስመሰል ዳንኪራ ሳይደነክር ፣ እንደ አትርሱኝ ባይ አርቲስቶች ተሰብስቦ ጭራውን ሳይቆላ እንደ ተራ ግለሰብ ከባለቤቱ ጋር ለቅሷቸውን የደረሰውን ሰው “ትግሬ ይንቃል” እያሉ ጠማሞች ስለ ቴዲ ጠማማ ጠማማውን ያወራሉ:: የጃዋር ሰልፈኞች ደግሞ  በሌላው ወገን የተሰለፉ ቴዲን የሚያጥላሉ አስቂኝ ፍጥረቶች ናቸው:: እነዚህ ስለሁላችን የሚዘፍነውን ቴዲን ነቅለው ዘረኝነትን የሚሰብከውን ሃጫሉን መትከል የሚፈልጉ ናቸው:: ድልድይ ሰሪ ነን በሚል ይህንን የጃዋር ሰልፈኛ የተደገፈ ሌላ ቡድን ደግሞ አለ ቴዲን በመጥላት የተጠመደ:: ለጥላቻው ምሁራዊ ምርኩዝ ሲፈልግ  የሰርጸን ትችት ይስባል:: ዞር ብሎ ደግሞ የመጨረሻውን አቨሬጅ ዘፋኝ ሚካኤል በላይነህን ሲያወድስ ታየዋለህ :: ‘ቴዲ የኦርቶዶክስ ዘፋኝ ነው’ ይልሃል ሃሳዊው ድልድይ ሰሪ::  “ሼ መንደፈርን” ስትጠራበት አፉ ዲዳ ይሆናል:: አያርፍም:: ‘ቴዲ የአማራ ዘፋኝ ነው ይልሃል’ መንገድ ቀይሮ ሲመጣብህ:: “ጥቁር ሰው” የተዋቀረበትን ችክችካ እና ሸጎዬ ስትጠቁመው ደግሞ ተመልሶ ያንኑ የጅል እንጉርጉሮውን “ቴዲ ድምጹ አያምርም” ያንጎራጉርልሃል:: ድልድይ ሰሪ ነኝ ብሎ እራሱን ለሾመው እንዲህ ያለ መንቻካ ሰው በረከት በላይነህ በቀደም የገጠማትን ስንኝ ወርውረህለት ታልፋለህ:: 

“ባ’ሻጋሪ ገጹ መራራቅ የሚስል

መአት ግድግዳ አለ ድልድይ የሚመስል” 

ቴዲን የምንወደውስ ስለምን እንወደዋለን ? በተማሪ ብራችን “እንደ ቢራቢሮ” ብለን ስላበድን? ከንፈሯን በሳምን ማግስት “አሁን አየ አይኔ” ብለን ስለጨፈርን? ወይስ ከነኢክራም ጋር “እኔም ልማል ባላህ አንቺም በቁልቢ” ስለተባባልን? ይህ ሁሉ ሊሆን ይችላል:: ግን ቴዲ አፍሮ ከዚህ ሁሉ ይልቃል:: ነውረኛ ምሁራን ለጎሳ ፖለቲካ በኢንቴግሪቲ ስም ሲያሸረግዱ በከረሙበት አገር ፣ የመንፈስ ደሃ የሆኑ አርቲስቶቻችን ንዋይ ፈለጋ በየባለጸጋው ደጃፍ በተኮለኮሉበት አገር ፣ ስለ አንድነታችን የሚዘምር ፣ ስለፍቅር የሚሰብክ ፣ የሚናገረውን የሚኖር ፣ የገዥዎቻችን እርግጫ የሚነቁር የካሳሁን ገርማሞ ልጅ ቴዲ አፍሮ ብቻውን አዲሳባ ላይ ተቸንክሮ ጠበቃችን በመሆኑ ባንወደው ነው የሚገርመው:: ቴዲ የቆመለት መንፈስ እንዲሰበር የሚፈልጉ ሁሉ ቴዲን ያጠቁታል:: ቴዲ የቆመለት መንፈስ እንዲያብብ የሚፈልጉ አንዳንዶች በተጓዳኝ ቴዲን ሲጠሉት ደግሞ ያስገርሙናል::  እኛ ግን ሃቁን አንስተውም!!! “ጃ ያስተሰርያል” ብቻውን ዛሬም አዲስአበባን ያስረግዳል:: ማንም ምሁር ፣ ማንም ፖለቲከኛ ፣ ማንም ተናጋሪ ነኝ ባይ የማይቀሰቅሰውን የፍቅር እና የአንድነት ማእበል ቴዲ አፍሮ ብቻውን ያናውጠዋል:: “የጠላሽ ይጠላ” ያለው ጥልዬ ፣ “ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ” ያለው ጥልሽ ዊልቸሩ ላይ ቁጭ ብሎ “አይኔን ባይኔ አይቼዋለሁ ፣ ብሞትም አይቆጨኝ” ብሎ ስለአልጋ ወራሹ ስለቴዲ አፍሮ ሲናገር ፣ ስለቴዲ ድምጽ እያወራ አልነበረም  https://goo.gl/zZEs7s  :: እሱ በጉብዝናው ወራት ስለዘፈነላት ኢትዮጵያ እና ቴዲን ስላሸከመው የአገር ፍቅር እያወራ እንጂ:: በሚገባ! ቴዲ በሞራልም ፣ በህልሙም ፣ በመንገዱም ከፍ ያለ የጥላሁን ገሰሰ ልጅ ነው:: ስለዚህ እንወደዋለን:: ስትዘምቱበት ዝም አንልም:: አላግባብ ስትጎነትሉም እንዳላየ አንሆንም:: የሚበዛው በቴዲ ሚዛን ሲመዘን የቀለለ ገለባ ነው:: ቴዲ የመጠበቂያው ማማ ላይ የቆመ ድምጽህ ነው::

ልትደግፈው ግድ ይልሃል::

Source – ethioforum.or

ከአሜሪካ ለኢንቨስትመንት የመጡት ከፍተኛ ግፍ ተፈፀመባቼው!

$
0
0

( ለጥንቅሩ የጎህ ጋዜጠኛ ዞብል ነኝ)
ከጎንደር
ከጎንደር ከተማ ታፍሰው ባለፈው ወራት ብርሸለቆ ታሰረው ከነበሩት መካከል የተወሰኑ የተፈቱ እንዳለ ሆኖ ፣ በርካታ ቁጥር ያላቼው ግን እሰከ ዛሬ ድረስ ያልተፈቱ እንዳሉ ይታወቃል።
አንድ አሳዛኝ ዜና ከወደ ብር ሼለቆ አገኜሁ መላው አለም ይሰማው ዘንድ እንዲህ ዘገብኩት ፣ ከኢትዮጵያ ተሰደው 25 ዓመት በአሜሪካ የኖሩ እና ያጠራቀሙትን ገንዘብ በመያዝ በሀገሬ ኢንበስት አድርጌ እራሴንም ወገኔንም እጠቅማለሁ ብለው በማሰብ በ ጠገዴ ወረዳ በእርሻ ስራ ተሰማርተው የሚገኙት በለሃብት የጠገዴ ተወላጅእና በእድሜ የገፉ ማለትም የ60 ዓመቱ አዛውንት አሁን በወያኔ ማጎሪያ በብርሼለቆ ከሌሎችም የከፋ ከባድ ስቃይ እየደረስባቸው እንዳለና ማንም ጠያቂ እንዳይጎበኛቸው መደረጉን የውስጥ መረጃዎች አጋልጠዋል። ጎንደሬነት ወንጄል በሆነበት በዚህ ዘመን ጎንደር በህዋህት ታፍኖ እየተቀጠቀጠ ይገኛል።

በተያያዘ ዜና በሰሜን ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብራጅራ የኮርሁመር የግራ ውሃ የአብደራፊ የዘመነ መሪቅ የመጎሴ ቀበሌ ኑዋሪዎች መኖራቸውን እየለቀቁ መሆኑ ታውቋል ።
መኖራቸውን ለቀው እንዲሄዱ ምክንያት የሆናቸው በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም ባለመኖሩ ሲሆን የተለመደው የንግድ እንቅስቃሴም ዜሮ ላይ መድረሱን ከአካባቢው የተገኘው መረጃ አመልክተዋል

ምጧ የተራዘመባት- ኢትዮጵያ! – ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

$
0
0

ኤልያስ ገብሩ

ሀገረ ኢትዮጵያ፡- ከአገዛዝ፣ አገዛዝ ስትሻገር በጭቆና በትር ተቀጥቅጣ ስትማቅቅ በርካታ ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡ የህዝቦቿ መከራም ቅርፁን እየቀያየረ ሲያሻውም እየተመላለሰ ትናንትን አቋርጦ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ለጭቆና በትሩ ተግባር ወለድ መፍትሔዎች ካልተበጀላቸው መከራው ነገም ይቀጥላል አገዛዙ አለና!

ሀገር በጉልበት ሲገዛ ወረቀት ላይ በደማቁ አምሮ የተጻፈ ሕግ በመርህ መተግበር ሲሳነው ህዝብና ገዢ ኃይል የአይጥና የድመት ኑሮን ለመኖር ሲገደዱ የነቃ የተማረ በሚባለው የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ የሀገርን ሳይሆን የግል ጥቅምን ማስቀደም እንደ አዋቂነት ሲቆጠር ሲተገበር ለቁስ መንሰፍሰፍና “ለእኔ ብቻ!” የሚል የስግብግበነት መንፈስ አይን አውጥቶ በገሃድ ሲታይ የጤናማ ይሉኝታ ባህል ተሸርሽሮ ገደል ሲገባ ሀገር በቀል ባህላዊ እሴቶችን ይዞ መኖር ኃላ ቀርነት ሲያስብለን ፖለቲካ በሀሳብ ሙግት ሳይሆን በጥላቻ በጠልፎ መጣል በጉልበትና በፍረጃ ሲሰራ የእራስን ዜጋ ንቆ ፈረንጅን ማምለክ ዘመናዊነት ሲመስል እውነትን መጋፋጥ ሞኝነት በውሸት /በሀሰት/ ውስጥ መኖርና ማምለጥ እንደ ብልጠት ሲወሰድ አድርባይነት ሆድ አደርነትና ጥቅመኝነት የህብረተሱ ዋነኛ መገለጫ መሆናቸው ሲያመዝን ጉቦ ሌብነትና ዘመናዊ ሙስና እንደክብር መግለጫ ሲቆጠሩ

“እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” ከሚል የመነጨ ጥልቅ የሥልጣን ጥም ሰፊውን ህዝብ ሲያሰቃይ ባለሥልጣናት በየረገጡበት የውጭ ሀገራት ክብርን ሳይሆን ውርደትን ሲከናነቡ ገዢ ኃይል ሀገርን ወደፊት ማራመድ ሲሳነው ሀገር የቁልቆለት መንገድ ላይ መሆኗን በጥቂቱ ያመላክታል ብዬ አምናለሁ፡፡

ቀደምት ስልጡን ሀገር መሆኗ በታሪክ ተደጋግሞ የሚወሳላት ኢትዮጵያለ በህወሃት/ኢህአዴግ የጉልበት የሥልጣን ዘመንም በርካታና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮችን ፀንሳለች መከራዎችንም አርግዛለች ዛሬም በእነኚህ ችግሮችና መከራዎች እየዳከረች ነው፡፡

የህወሃት አገዛዝ፣ ከደርግ ውድቀት ማግስት በኃላ “ሰላምና መረጋጋት”፣ “ተሃድሶ” የሚሉ ሃሳቦችን ሲያቀነቅን ነበር፡፡ በተራዛሚ ሂደትም “ህዳሴ፣ ትራንስፎርሜሽን“ ሲል ከርሞ አሁን ደግሞ፡- “በጥልቀት መታደስ!” የሚል ወቅታዊ ነጠላ ዜማ በመልቀቅ የሀሰት ነጋሪት ጉሰማውን ተያይዞታል፡፡

ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ በሥልጣን ማማ ላይ ያሳለፈው ይህ አምባገነናዊ አገዛዝ፣ ብዙ ያወራላቸውና በፕሮፖጋንዳ ማሽኖችም ብዙ ያስነገረላቸው ተንኮል – ወለድ ዕቅዶቹ በሙሉ በክሽፈት አዙሪት ውስጥ የሚናውዙ ናቸው፡፡

ይህንን ለመረዳት ነገሮችን በአንክሮ መከታተልና ማጤን ወሳኝነቱ አሻሚ አይሆንም እንደማሳያም ከላይ የጠቀስኳቸው ቃላቶች መካከል ሦስቱን በምሳሌነት ላስቀምጥ፡-ህወሃት ኢህአዴግ የጉልበት ሥልጣንን “ሀ” ብሎ ሲጀምር በህዝቡ ዘንድ እንዲሰርፅለት የታተረው ቃል “ሰላምና መረጋጋት” የሚል ነበር፡፡

ለአንዲት ሀገር ህልውና፣ ለህዝቦቿ በአንድነት መኖር ሰላምና መረጋጋት ወሳኝ ኹነቶች ናቸው፡፡ በወቅቱም የሚፈለገው እውነተኛ ሠላም መኖርና መረጋጋት መስፈን/አለመሸፈት ሀቅን የመመርመር ህሊና ላላቸው ባለአዕምሮ ዜጎች ልተወውና ወደ ዛሬው እውነታ እንለፍ፡፡

ከ2008ዓ.ም የመጀመሪያ ወራት ጀምሮ “በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ልዩ ዞኖች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሥር ይካተቱ” የሚለውን የህወሃት/ኢህአዴግ እኩይ እቅድን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የተጀመረውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ጠንካራና ተግባር ተኮር በመሆኑ የተነሳ አገዛዙን አንገዳግዶት ከባድ ስጋት ላይ ጥሎት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው አንዱም የታሪካችን አካል ነው፡፡

ከተጠቀሰው አመት አጋማሽ በኃላም በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን ተከትሎ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞና ትግል የአገዛዙን ህልውና በብርቱ መፈተኑም ይታወቃል፡፡

በያዝነው ዓመት መስከረም ወር በደብረዘይት/ቢሾፍቱ ከተማ በየዓመቱ የሚከበረው የእሬቻ በዓል ላይ የደረሰው እጅግ አሳዛኝና ዘግናኝ የሞት አደጋ አይረሳም፤ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ወንድምና እህቶቻችንን አጥተናል!

ይህ ዘግናኝ ኹኔታ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ዳግም ህዝባዊ ቁጣን ቀስቅሶ በርካታ ፋብሪካዎች ተሽከርካሪዎች ንብረቶች…… በእሳት ቃጠሎ መውደም ጀመሩ፡፡ ተቃውሞ አድራጊዎችና የአገዛዙ የፀጥታ ኃይሎች ፊት ለፊት ሲላተሙ የበርካቶች ህይወት አለፏል፡፡ ወዲያውም የሀገሪቱ ሰላምና ደኅንነት ከባድ አደጋ ላይ መውደቁን ገዢው ኃይል አመነና ይህ አሁንም ድረስ ያለንበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለስድስት ወራት ታወጀ፡፡

ከእዚህ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው ህወሃት/ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ አልፎ አልፎ አንጻራዊና ወቅታዊ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቷ ከመፍጠር ባለፈ እውነተኛና ዘላቂነት ያለው ሰላምና ደኅንነትን እውን ማድረግ አለመቻሉን ነው፡፡

ከ25 ዓመታት በኃላም ሰላምና መረጋጋት በሀገሪቷ እና በዜጎቿ ዘንድ ሊረጋገጥ አልቻለም፡፡ ለእዚህ ደግሞ ዋናው ተጠያቂ “ሀገሪቷን እያስተዳደርኩ ነው” የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ የሀገርና የህዝብን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ አለመቻሉ የታላቅ ክሽፈቱ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

በሌላ ረገድ ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ማግስት ጀምሮ ባሉ ጥቂት ዓመታት “ተሃድሶ” የሚለው ቃል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በአሁኑ EBC በስፋት ይቀነቀን ነበር፡፡ የተሃድሶን ቃል ስንገልጠው “መታደስ” የሚል ፍቺን ይሰጠናል፡፡ መታደስ አንደ አዲስ መለወጥ ነው፡፡ በጎ ህሊና ያለው ሰው ተሃድሶን ይሻል፡፡

በመልካም መታደስ ለሰው ልጅ እፈላጊ ነውና ህወሃት/ኢህአዴግ፡- ሰፊው ህዝብና ሀገራችን በመታደስ ጎዳና ላይ ቢገኙ እጅግ ደስታና ሀሴት ነበር፡፡ ሆኖም፡- በ25ዓመታት ውስጥ “ተሃድሶን ውሃ በላት” በአገዛዙ በተግባር እውን ሊሆን አልቻለምና ዛሬም “በጥልቀት” የሚል ተቀጽላ ቃል ተጨምሮባት በድጋሚ አፍአዊ ተግባር ላይ ውላለች፡፡ ‹‹ጥልቅ ተሃድሶ››ን በቃላት ማነብነብና በተግባር በጥልቀት ለየቅል ናቸው፡፡

ጥልቅ የሥልጣን ጥም ያለው ኃይል፣ በጥልቅ ሙስና የበሰበሰ አገዛዝ በጥልቅ ጥላቻ የገዛ ወንድምና እህቶቹን የሚያሰቃይ የሚያስር የሚያሳድድ፣ የሚገድል……. ቡድን በጥልቅ የገዛ ጥላውን ጭምር የሚፈራ ግለሰብ፣ ከቶ እንዴት በጥልቀትሊታደስ ይቻለዋልን???

ህወሃት/ኢህአዴግን ለ25 ዓመታት በአንክሮ ለተከታተለው በጥልቀት ሊታደስ ቀርቶ በጥቂቱም ወደ መልካምነት ሊቀየር አለመቻሉን መረዳት ይቻላል፡፡ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን አፈራርሶ የግል ሚዲያን አንቆ ገድሎ ነፃና ገለልተኛ የሲቪክ ማኅበራትን አክስሞ ዜጎችን በፍርሃት እስር ቤት ውስጥ ከርችሞ ጠባብነትና ትምክተኝነትን አስፋፍቶ ዘረኝነትን አንግሶ ጥቅመኝነትን ፈልፍሎ………. ወዘተ “በጥልቀት መታደስ” ማለት ቧልት ይሆናል፡፡ “ከድጡ ወደ ማጡ” ነውና ነገሩ፤ መታደስ አለመቻል ሌላኛው የአገዛዙ መገለጫ ነው፡፡

በ2002ዓ.ም የተደረገውን “ሀገር አቀፍ ምርጫ”ን ተከትሎ 99.6% “ድል” ወደ አገዛዙ ሄደ፡፡ ከምርጫው በኃላም በስፋትና በ“ጥልቀት” የምትቀነቀነው ቃል “ትራንስፎርሜሽን” ሆነች፡፡ የአምስት ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በሚል እጅግ የተለጠጠውና በአማላይ ቃላቶች የተንቦረቀቀው የዕቅዱን ዝርዝር መለስ ብሎ ማየት ይቻላል፡፡

ዕቅዱና አፈፃፀሙ በአልተገናኝቶ መስመር ሲነጉዱም አይተናል፡፡ እቅዱ 2ኛ ዙር ቢኖረውም ፍሬያማ አልነበረም፡፡ እቅዱ 3ኛ፣4ኛ ዙር ቢኖረው እንኳን ህወሃት/ኢህአዴግና ትራንስፎርሜሽን በተግባር የሚታዩ የሚነካ የሚዳሰስ የሚቆነጠር ህልውና አይኖራቸውም፡፡

ለምን? እውነተኛ ትራንስፎርሜሽን ከቅንነት፣ ከህዝባዊነት፣ ከአርቆ አላሚነት ከድፍረት፣ ከእውቀት ከትጋት ከቁርጠኝነት…….ወዘተ የሚወለድ ሲኾን በአንጻሩ ጠባብነት ትምክህተኝነት ወገንተኘነት ሙሰኝነት ሴሰኝነት የሥልጣን ጥመኝነትና ክፋት ባለበት ቦታ እውን አይሆንም፡፡

ሀገርን “ከአንድ ዝቅ ካለ ደረጃ ወደ ላቀው ሌላኛው ከፍታ አሸጋግራለሁ!” የሚል ኃይል በተቃራኒው የአዘቅት መንገድ ላይ አይገኝም ነበር፡፡ ግን ይህ በሀገራችን ሆነ! በመሆኑም አገዛዙ በብዙ ረገድ ሀገርን ወደ ከፍታ ሳይሆን ወደ አዘቅት ውስጥ ከቶታል፣ እየከተተም ይገኛል፡፡

…….“በ25 ዓመታት ውስጥ መታደስ አልቻልኩምና አሁን ገና በጥልቀት መታደስ አለብኝ!” የሚል ቡድን እንዴት የአንድን ሀገር የትራንስፎርሜሽን እቅድ እውን ሊያደርግስ ይቻለዋል?! ይህም ያልዘሩትን ዘር አዝመራ እንደማጨድ ይቆጠራልና ሌላኛውን የአገዛዙ ክሽፈት ነው፡፡

ከላይ በመግቢያዬ እንገለፅኩት ኢትዮጵያ በዘመነ ህወሃት/ኢህአዴግ በርካታና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮችን ፀንሳለች መከራዎችንም አርግዛለች እነኚህ ችግሮችና መከራዎች፡- ምጧ እንዲረዝም ስቃይዋም እንዲበረታ አደርገዋታል፡፡ ከምጧ እና ከስቃይዋም በሌላም መንገድ ለመገላገል በተፈጥሯዊ መንገድ አምጣ እውነተኛ ሰላምን ነፃነትን ዴሞክራሲን ፍትህን፣ እኩልነትን፣……… መውለድ ይጠበቅባታል፡፡

አልያም የምጥ ማፍጠኛ መርፌ መውጋት ከቀላል እስከ ከፍተኛ የሚደርስ ቀዶ ጥገና ማድረግ የግዷ ሊሆን ነው፡፡ እኒዚህም ካልተሳኩ አሳዛኙን እውነታ መቀበል የዜጎቿ እጣ ፈንታ ይሆናል፡፡ ውስብስብና አስቸጋሪ ነገሮች ካልተፈጠሩ በቀር አንዲት እርጉዝ ሴት በተፈጥሯዊ መንገድ አምጣ ብትወልድ ጥሩ መሆኑን የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ሁሉ ሀገራችንም እውነተኛ ሰላምን ነፃነትን ዴሞክራሲን ፍትህን እኩልነትን፣…… በተፈጥሯዊ መንገድ አምጣ ብትወልድ ለዜጎቿም እፎይታ ነው፡፡

ይህ እውን እንዲሆን ግን ዴሞክራሲያዊ ለውጥን የሚሹ ዜጎች (በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ) ከመቼውም ጊዜ በላይ ስለሀገራቸው ቀጣይ ፖለቲካዊ እጣ ፈንታ በአንክሮና በስክነት ማሰብ ማሰላሰል ይጠብቅባቸዋል፡፡ የሀሳብ ልዩነት የትም ቦታ አይጠፋምና ልዩነትን ችሎ አንድነት ላይ ግን ይበልጥ ጠንክሮ መቆም የውዴታ ግዴታቸው መሆኑን አሻሚ አይሆንም፡፡

የልዩነት መንገዶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ለዓመታት መሰራቱ ወደታች ሲያወርዱን እንጂ ወደ ከፍታ ሲያወጡን በተግባር አልታየምና እያቃረንም ውስጣችንን እየተፈታተነንም ቢሆን የልዩነት ድንበርን በድፍረት ተሻግረን ለተሻለ የሀገር ስሪትና ምስረታ አንድ እንሁን!

ለዴሞክራሲያዊ የለውጥ እንቅስቃሴ እንተባበር!


የብአዴን ፅሕፈትቤት ለኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ፃፈው የተባለው ሪፖርት

$
0
0

የብአዴን ፅሕፈትቤት ለኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ፃፈው የተባለው ሪፖርት እነሆ (ብአዴን ኢህአዴግ መሆኑ አንርሳ። ኢህአዴግም የህወሓት የእጅ ስራ ነው። በህወሐታዊ ድርጅት ኢህአዴግ ውስጥ ምን እየተደረገ እንደሆነ ለማወቅ ሪፖርቱን እናንብብ። ህወሐት የሚያመጣው ጣጣ! ሳንበላ በሉ! ደግሞኮ በህወሐት-ኢህአዴግ በራሱ መፃፉ ነው የሚገርመው)
————

የብአዴን ጽ/ቤት ለኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት የመምህራን መድረክ ማጠቃለያ ሪፖርት ከላከው የተቀነጨበ – Reference Number: ቁጥር ብአዴን /ማዕ.ኮ/2131ሪ ቀን 23/05/2009 ዓ.ም.
ምሁራኑ ስለ ህወኃት እና ትግራይ የሚከተለውን ዘመን ተሻጋሪ እውነታ አስቀምጠዋል፡፡
1. ፍትሀዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል የለም፡፡ ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ ነው፡፡
2. ጥሬ ሀብት ከአማራ እየተመረተ ፋብሪካው የሚገነባው ትግራይ ነው፡፡
3. ትግራይ እስካሁን ሲወስድ የነበረው ኢንዱስትሪዎች፣ በጀት ና ትልልቅ የስልጣን ቦታዎች ነበረ አሁን አሁን ግን ቅርሶችን ልክ እንደ ላልይበላ፣ ዳሸን ተራራን የትግሬ ነው በማለት ታዋቂነታቸውን በመጨመር ለልማት አጋዥ አቅም እየጨመሩ ነው፡፡
4. ትግራይ መሬት የማስፋፋት ስራ እየሰሩ ነው፡፡
5. አሁን በተደረገው የመምህራን ስብሰባ ትግራይ አበል ሲከፈል እኛ ጋር አይከፈልም ይህም ትግራይ የበላይነትና ጥንካሬን የሚገልጽ ነው፡፡
6. የወልዲያ የሀራ ገበያ መቀሌ የሚገነባው የባቡር መስመር አማራን ለመጥቀም ሳይሆን ለትግራይ ታስቦ የሚሰራ ነው ለእኛ ያለው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የለውም፡፡ እዳውም አማራ ላይ እዳይፈተሸ እና ከምሀል ሀገር እና ከወደብ በቀጥታ ትግራይ እንዲገባ በማስብ ከከተማ በርቀት የአማራን ክልል ገጠር ወረዳዎች እየነካ ነው የሚያልፈው፡፡
7. የሰሜን ወሎዋ ‹‹ዋጃ›› ወደ ትግራይ የተከለለው በህዝቡ ፈቃድ ሳይሆን በግዳጅ ነው፡፡
8. የውጭ ጎብኝዎች ሲመጡ ቅድሚያ የማስተዋወቅና እንዲሄዱ የሚደረጉት ወደ ትግራይ ነው፡፡
9. ላስታ አቡነ የወሴፍ ላይ እየተሰራ ያለው የህዋ ምርምር መቀሌ ዩኒቨርስቲ እንዲመራው መደረጉ በሂደት ወደ ትግራይ ለማካለል የሚደረግ ሴራ ነው፡፡
10. ወልቃይት ጥንት ጀምሮ የአማራ የጎንደር መሬት ነው መመለስ አለበት፡፡ ከዋጃ እስከ ኮረም ያለው ወደ ትግራይ መከለል አልነበረበትም አሁንም መመለስ አለበት፡፡
11. የአሸንደዬ በአል በአማራም በትግራይ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በዩኒስኮ የተመዘገው ግን የትግራይ ነው፡፡
12. አጼ ዬሀንስ ሙስሊሙን ሲገድልና ሲያጠምቅ ለነበረው የተቀመጠ ነገር የለም ነገር ግን ሚኒሊክ ጡት ሳይቆርጥ እንደቆረጠ ተደርጎ አኖሌ ሀውልት መታሰቢያ ተሰራ፡፡
13. ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህወሀት አመራር ታዛዥ ነው፡፡
14. አንቀጽ 39 መሰረዝ አለበት ትግራይም ግዛቱን ለማስፋፋት የሚሯሯጠው በሂደት ለመገንጠል ነው፡፡
15. የፌደራሊዝም ስርዓት ለኢትዮጵያ አይበጃትም፤ በፌደራል ሽፋን የአንድ ብሄር የበላይነት እየተገነባ ነው፡፡
16. ኢትዮጵያ ውስጥ የዜግነት ደረጃ አለ፤ ቀዳሚው ትግሬ ነው፡፡
17. የብአዴን አመራር ለአማራ ህዝብ እድገት እየሰራ አይደለም፡፡ ያሉት ልማቶች ከትግራይ ክልል ጋር ሲነጻጸር በፋብሪካም ሆነ በሌሎች ልማቶች በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡
18. ብአዴን የሚመራው በህወሀት ነው እራሱን ችሎ አይመራም፡፡
19. በከፍተኛ ደረጃ የአማራ አመራር የለም፡፡ ያሉትም አመራር በአማራ ሽፋን የሌሎች ብሄር ዘር ያላቸው ናቸው፡፡ ለአብነት አዲሱ ሀረር፣ በረከት ኤርትራዊ፣ ካሳ ተ/ብርሀን ኮረም ፣ ህላዊ የወሴፍ ደቡብ ናቸው እነዚህ በአማራ ስም ያሉ ናቸው፡፡ እንዴት ለአማራ ሊቆረቆሩ ይችላሉ፡፡
20. የአማራ ህዝብ በሌሎች ብሄሮች ጥላቻ እንዲፈጠርበት ሆን ተብሎ እየተሰራበት ነው፡፡ ለአብነት የአኖሌ ሀውልት፣ ትምክህተኛ እያሉ መፈረጅ
21. ትምክህትና ጠባብ አመለካከቶች መሰጠት ያለበት ለትግራይ ነው፡፡
22. በ10ኛ ክፍል የስነ ዜጋና ስነ ምግባር መጽሃፍ በትግራይ እና በአማራ ክልል መካከል ያለው የድንበር ስህተትም ሆነ በ6ኛ ክፍል የእንግሊዘኛ መጽሀፍ ራስ ዳሸን በትግራይ ክልል እንዳለ ተደርጎ የተቀመጠው ሳይታሰብ ሳይሆን ሆን ተብሎ የተፈጠረ ሴራ ነው፡፡ ምክኒያቱም ትምህርት ሚኒስተር ችግሩን ካወቀበት ቀን ጀምሮ እንኳን ለረዥም ጊዜ ሳይታረም የታለፈ መሆኑ፤ ሌላው ይቅርታውም የህዝብ ጭጭት ግፊት እንጂ ከልብ የመነጨ አይደለም በህግ መጠየቅ ይገባል፡፡
23. አዲስ ከተሾሙት ሙሁር መሳዩች ጀርባ የትግራይ በላስልጣናት እጆች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ለአብነት ከዶር ነገሬ ሌንጮ ጀርባ ዛዲግ አብርሃ የሚባል የሚዲያ ጠላት አለ፡፡ እና እንዴት ሁኖ ነው ፕሬሱ ነፃ የሚሆነው፡፡
24. በአገራችን የአንድ ብሄር የበላይነት አለ፡፡ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እና የአስተዳደር ሁኔታ የለም፡፡
25. የአማራና በትግራይ መካከል ያለውን የድንበር ችግር ፌደራል መፍታት ነበረበት ለክልሎች መግፋቱ ስህተት ነው፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ከሚስታቸው ጋር እያወሩ ነው

$
0
0
  • ምነው ተከዝሽ?
  • ብዙ ነገር ያሳስበኛል፡፡
  • ምን ያሳስብሻል?
  • የወደፊት ሕይወታችን፡፡
  • የወደፊት ሕይወታችን ምን ሆነ?
  • መቼ ይገባሃል አንተ?
  • ማለት?
  • ቤት እንኳን መቼ አለን?
  • ይኼኛው ቤትስ?
  • አይ አንተ?
  • ምነው?
  • ቤቱ እኮ የመንግሥት ነው፡፡
  • ቢሆንስ እየኖርንበት አይደለ እንዴ?
  • ዕድሜ ልክህን ሥልጣን ላይ የምትቆይ ይመስልሃል?
  • የሰማሽው ነገር አለ እንዴ?
  • ምን?
  • ከሥልጣን ልነሳ ነው እንዴ?
  • ኧረ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን፡፡
  • ታዲያ ምንድን ነው የምታወሪው?
  • ስለወደፊቱ ዕጣ ፈንታ ከአሁኑ ማሰብ አለብህ፡፡
  • እና ምን ይደረግ እያልሽ ነው?
  • ከአንድ ሰው ጋር ሳወራ ነበር፡፡
  • እሺ፡፡
  • እነዚህ የ40/60 ቤቶች በጣም አሪፍ ናቸው አሉ፡፡
  • እሱማ እኔም ሰምቻለሁ፡፡
  • ታዲያ እነሱ ቤቶች እንዴት ናቸው?
  • ምን እያልሽ ነው?
  • የምለውማ ገብቶሃል፡፡
  • ሴትዮ ጤነኛ ነሽ ግን?
  • በሚገባ እንጂ፡፡
  • እነሱ እኮ የሕዝብ ናቸው፡፡
  • አይ አንተ?
  • ስሚ ሕዝብ ቆጥቦ እኮ ነው የተሠሩት፡፡
  • ቢሆንም እኔ ወሬ ሰምቻለሁ፡፡
  • የምን ወሬ?
  • የተዘጋጁት ለማን እንደሆነ፡፡
  • ለማን ነው?
  • ለባለሥልጣናት!

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ ወዳጃቸው ሚኒስትር ጋ ደወሉ]

  • ሄሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት ነህ ወዳጄ?
  • ሰላም ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ቢዚ እንደሆንክ አውቃለሁ፣ አንድ ነገር ልጠይቅህ ነበር፡፡
  • ምን ክቡር ሚኒስትር?
  • እነዚህ 40/60 ቤቶች እንዴት ናቸው?
  • ያው በጥሩ ሁኔታ እየተሠሩ ነው፡፡
  • እሱማ አውቃለሁ ግን…
  • ግን ምን ክቡር ሚኒስትር?
  • ቤቶቹን እንዴት ማግኘት ይቻላል?
  • ተመዝግበዋል እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • ኧረ በፍጹም፡፡
  • እና ቤቶቹን ወደዷቸው?
  • በጣም ነው የወደድኳቸው፡፡
  • ዋናው እንኳን እርስዎ ወደዷቸው፡፡
  • ማግኘት እችላለሁ እንዴ?
  • እንዴታ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የተሠሩት ለሕዝቡ መስሎኝ?
  • የተሠሩትማ…
  • እ…
  • ለእኛው ነው!

[የክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ዘመድ ደወለላቸው]

  • ሄሎ ጋሼ፡፡
  • እሺ እንዴት ነህ?
  • ኧረ ችግር ውስጥ ነኝ ጋሼ፡፡
  • የምን ችግር ደግሞ?
  • ትንሽ ከመንግሥት ጋር እየተጋጨሁ ነው፡፡
  • ተቃዋሚ ሆንኩ እንዳትለኝ?
  • እንደሱ አይደለም ጋሼ፡፡
  • ታዲያ ምን ተፈጠረ?
  • በታክስ ጉዳይ ነው፡፡
  • ታክስ አትከፍልም እንዴ?
  • ኧረ እኔ እከፍላለሁ፡፡
  • በታክስ እኔ ቀልድ እንደማላውቅ ታውቃለህ?
  • አውቃለሁ ጋሼ፡፡
  • ታዲያ ምንድን ነው?
  • አንድ ከገጠር ያመጣሁት ዘመዳችን ነበር፡፡
  • እሺ ምን ሆነ?
  • ለእሱ የከፈትኩለት ሱቅ ነበር፡፡
  • እሺ፡፡
  • እኔ ሳላውቅ ለካ ለዓመታት ታክስ ከፍሎ አያውቅም፡፡
  • ታዲያ አንተ ምን አገባህ?
  • ሱቁ በእኔ ስም ነው ያለው፡፡
  • ወይ ጣጣ፡፡
  • አሁን ዓቃቤ ሕግ ነገሩን እያከረረው ነው፡፡
  • እና ምን አድርግ ነው የምትለኝ?
  • አንተ ሚኒስትር አይደለህ እንዴ ጋሼ?
  • ታዲያ ብሆንስ?
  • ክሱን አስቋርጠው፡፡
  • እስቲ ለማንኛውም የዳኛውን ስምና ቁጥር ቴክስት አድርግልኝ፡፡
  • እሺ ጋሼ፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ ዳኛው ጋ ደወሉ]

  • ሄሎ፡፡
  • እንዴት ነህ ክቡር ዳኛ?
  • ማን ልበል?
  • ክቡር ሚኒስትር ነኝ፡፡
  • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • ሰላም ነኝ፡፡
  • ምን ልርዳዎት?
  • አንድ ዘመዴ አንተ ጋ ኬዝ ነበረው፡፡
  • የምን ኬዝ?
  • ትናንትና በታክስ ጉዳይ ፍርድ ቤት የነበረው ኬዝ፡፡
  • እ… አወቅኩት ሰውዬውን፡፡
  • ስለእሱ ጉዳይ ለማውራት ነበር፡፡
  • ያውሩኛ ምን ችግር አለው?
  • በስልክ ጥሩ ስላልሆነ በአካል ተገናኝተን ብናወራስ?
  • ክቡር ሚኒስትር ሥራ ስለሚበዛብኝ ከቻሉ የሚፈልጉትን በስልክ ይንገሩኝ፡፡
  • ሰውዬው ጥፋተኛ አይደለም፡፡
  • እሱማ በፍርድ ቤት የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡
  • አይገባህም እንዴ አንተ?
  • ስልኩን ልዘጋው ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • በጣም ተናንቀናል ማለት ነው፡፡
  • ምን አሉኝ?
  • የምነግርህን አትሰማም እንዴ?
  • ክቡር ሚኒስትር ፍርድ ቤቱ በትዕዛዝ አይደለም የሚሠራው፡፡
  • እና በምንድን ነው የሚሠራው?
  • እንዴት እንደሚሠራ ለማወቅ ሕገ መንግሥቱን ቢያነቡት ጥሩ ነው፡፡
  • እና ትዕዛዙን አትቀበልም?
  • ለመሆኑ ሰሞኑን ሚዲያ ተከታትለዋል?
  • በምን ጉዳይ ላይ?
  • አሜሪካ ስለተፈጸመው ጉዳይ፡፡
  • ምን ተፈጸመ?
  • ፕሬዚዳንቱ አንድ ትዕዛዝ አውጥተው ነበር፡፡
  • እሺ፡፡
  • ከዛ በኋላ ግን የፕሬዚዳንቱን ትዕዛዝ ፍርድ ቤት ሻረው፡፡
  • ምን እያልከኝ ነው?
  • ልልዎት የፈለኩትማ ፍርድ ቤትን ማንም አያዘውም ነው፡፡
  • ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ አሉ፡፡
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • አሜሪካ ሌላ…
  • እ…
  • ኢትዮጵያ ሌላ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • ስማ ይኼ ትራምፕ የሚባለውን ሰውዬ እየተከታተልከው ነው?
  • በሚገባ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ያወጣውን መመርያ ሰምተሃል አይደል?
  • ትራቭል ባኑን ነው?
  • ታዲያስ?
  • እሱ እኮ እኛን አይመለከትም፡፡
  • እንዴት አይመለከትም?
  • ለሰባት አገሮች ነው እኮ የወጣው፡፡
  • እኔ እሱን አይደለም የምልህ፡፡
  • ታዲያ ምን እያሉኝ ነው?
  • እዛ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ጠራርጎ ሊልካቸው ነው፡፡
  • ማለት?
  • በቃ ይኼ ዶክመንት የሌለው ሁሉ መጠረዙ አይቀርም፡፡
  • ኧረ እንደዛ የሚባል ነገር የለም፡፡
  • ሰውዬው ሕገወጥ ስደተኛን አባርራለሁ ብሏል፡፡
  • ቢሆንም due process የሚባል ነገር አለ፡፡
  • ምንድን ነው እሱ?
  • አሜሪካ ምድር የረገጠ ሰው ዝም ብሎ አይባረርም፡፡
  • እንዴት አይባረርም?
  • ኬዙ በፍርድ ቤት ተይዞ እስከ አሥር ዓመት ሊቆይ ይችላል፡፡
  • ሰውዬው ለምን እንደተመረጠ ታውቃለህ?
  • ለምንድን ነው?
  • የማስፈጸም ብቃቱ ፈጣን በመሆኑ ነው፡፡
  • ምን እያሉ ነው ታዲያ?
  • አዲስ ስትራቴጂ ነው የሚጠቀመው፡፡
  • ምን ዓይነት ስትራቴጂ?
  • Fast due process የሚሉት፡፡
  • ስለ due process አላውቅም ብለውኝ አልነበር እንዴ?
  • የምትለውን ልስማ ብዬ ነው እንጂ በደንብ ነው ጠንቅቄ የማውቀው፡፡
  • እኔ ግን አሁን ስለሚሉት ነገር ሰምቼም አላውቅም፡፡
  • አታነብማ ችግሩ እሱ ነው፡፡
  • ብለው ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ለማንኛውም አሁን መዘጋጀት አለብን፡፡
  • ለምኑ ነው የምንዘጋጀው?
  • አሁን የመንግሥትን ልማት ሲያንቋሽሹ የነበሩ ጠላቶቻችን መምጫቸው ቀርቧል፡፡
  • እ…
  • በቃ በየጊዜው ባለሥልጣናትን ሲያዋርዱ የነበሩ ጉዳቸው ነው፡፡
  • አልገባኝም ክቡር ሚኒስትር?
  • ስማ ያ ሰውዬ ጠርዞ ሲልካቸው እዚህ በሚገባ እንቀበላቸዋለን፡፡
  • ሰሞኑን ግን መንግሥት መግለጫ አውጥቷል፡፡
  • ምን የሚል?
  • እዛ ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግሥትን የሚቃወሙት ለግሪን ካርድ ስለሆነ ወደ አገራቸው ተመልሰው በልማት ላይ መሳተፍ ይችላሉ ብሏል፡፡
  • እሱማ የሚሰማሩት ልማት ላይ ነው፡፡
  • ታዲያ እርስዎ ምን እያሉ ነው?
  • ጥያቄው የሚያለሙት ምንድን ነው የሚለው ነው?
  • ምንድን ነው የሚያለሙት ታዲያ?
  • ቂሊንጦን!

ፕሮፌሰር ሐይሌ ላሬቦ አስቀየሙን (ሰመረ አለሙ)

$
0
0

(ሰመረ አለሙ) semere.alemu@yahoo.com

ፕሮፌሰር ሐይሌ ላሬቦ

ፕሮፌሰር ሐይሌ ላሬቦ

ባለፈዉ የተከበረዉ የኢትዮጵያ ልጅና የአንድነት ሀይል ፕሮፌሰር ሐይሌ ላሬቦ ባልተለመደ መልኩ በኢሳት መስኮት ቀርቦ ኢትዮጵያዊነትን አስመልክቶ በምሁር እይታዉና በሀገር ወዳድ ምልከታዉ ለሁሉም በማያዳላ መልኩ ታሪክንና ኢትዮጵያዊነትን እንዳለ በመልክ በመልኩ አስረድቶን ለማመሰገን ቃላት ስንመርጥ በተከታዩ ቀን ከሌላዉ የኢሳት ማእከል ሌላዉ ጋዜጠኛ  ኢትዮጵያዉያንን ይቅርታ እንጠይቀለን ሐይሌ ላሬቦ ኢትዮጵያዉያንን አስቀይሞብናል የሚል ዜና ሰማን።

የዚህ ነገር ዉዥንብር እስኪጣራ ግራ ተጋብተን እያለ ሐይሌ ላሬቦ እንደገና በግሉ ማብራሪያ ሰጠበት እኛም የነገሩን ጭብጥና አቡዋራዉን ያስጤሰዉን ነገር  አገኘነዉ። ተከፉ የተባሉ ወንድሞቻችን ያስቀየማቸዉ የኦሮሞ ህዝብ እረኛ ነበር የሚለዉ አጠራርና ባጠቃላይ ለነገዱ የተሰጠዉ መጠሪያ መሆኑ ተገለጸልን።

መጀመሪያ በፈረንጆቹ ቀጥሎ የትላንት ጠቅላይ ግዛታችን ኤርትራና የህወአት አስተዳደር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት በርትተዉ በመሰራታቸዉ እኛም በማንቀላፋታችን  ዛሬ እነዚህ ወገኖች ላይ ሀሳቡ ፍሬ አፍርቶ ልባቸዉ ባገራቸዉና በወገናቸዉ እንዲሁም በታሪካቸዉ ላይ እንዲሸፍቱ ሁኗል። በእርግጥ ሐይሌ ላሬቦ እነዚህን ወገኖች የተናገረዉ አስቆጥታቸዉም አይመስልም ምክንያቱም ባለፈዉ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ከዚህ በባሰ መልኩ ነገር አሳመርኩ ብሎ አጥግቦ ሰድቧቸዋል ካማኝ የነገረኝ የሚባል ብሂል አለ። ሐይሌ ላሬቦ በዚያ መግለጫዉ ጋዜጠኛዉ ለጠየቀዉ መልስ የኢትዮጵያን  አመሰራረትና በየጊዜዉ የሚነሳዉን ተረት ተረት አጥርቶ ማለፍ ስላለበት ከሙያዉ አንጻር በማያሻማ መልኩ በዚህ ነገር እንዳንመላለስ ማህተም አትሞበት አልፏል በዚህም ሊመሰገን ይገባዋል ካንድ ምሁር የሚጠበቀዉም ይኸዉ ነዉ። በዚያ ቃለ ምልልስ ሐይሌ ላሬቦ ባብዛኛዉ የኦሮሞን ህዝብ ታላቅነትና በኢትዮጵያ ግንባታ ያደረገዉን አስተዋጽኦ ነበር የዘከረዉ ነገር ግን የሐይሌ ላሬቦ ከሳሾች ወደሁዋላ ተጉዘዉ ታሪክ አጣቅሰዉ ማህደር አስደግፈዉ የተናገሩበት አንድም የአለም መድረክ አላየንም ይልቁንስ የአንድነት ሐይሎች ከነሱ ልቀዉ የኦሮሞን ህዝብ የሚያኮራ ደጎስ ያለ ድርሳናት አስነብበዉናል።

ማንም ሆነ ማንም ፈረንጆች ከነገሩዋቸዉ  አስተሳሰብ ዉጭ ከተሄደ በኦሮሞ ጠላትነት ይፈረጃል ቀጥሎ ዘመናዊ ገዳ ይካሄድበታል እንዲህ አይነት አሸባሪ ድርጊቶች በፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፤በፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሐይሌ፤በዶክተር ታየ ወ/ሰማአት፤በአቶ አሰፋ ጫቦ፤ በኢንጂነር ሐይሉ ሻዉል፤በቴዲ አፍሮ፤በአቶ ግርማ ካሳ፤ደምስ በለጠ፤ በሔኖክ የሺጥላና በሌሎችም በተለያየ መልኩ  ተካሂዷል። በበኩሌ ሐይሌ ላሬቦ መሀመድ ግራኝን አስመልክቶ የተናገረዉ አልተመቸኝም ስፍር ቁጥር የሌለዉን ቤተ ክርስቲያናት ያቃጠለ ዜጋ የፈጀ  በሀይሌ ላሬቦ ምልከታ ሌላ ቦታ ይዟል እኔን ያልተመቸኝን በመናገሩ  ከኑሮዉ እንዲሰናከል ክብሩም እንዲነካ አልፈቅድም እኔም በተለያዩ ጉዳዮች የራሴ ምልከታ ስላለኝ የሱንም አከብራለሁ ከእኔ ምልከታ አንጻር ግን ትክክል ያለመሆኑን አስረዳለሁ በዚህ ሁኔታ የሚዳኙን ሌሎች ይሆናሉ ማለት ነዉ እነሱም የራሳቸዉ የመመሪያ ስልት ይኖራቸዋል እዉነትን የሚያጣሩበት።

በወቅቱ በህብረተሰብ እድገት ዛሬም ቢሆን የኦሮሞ ነገድ ከከብት ጋር ቁርኝት ያለዉ ነዉ ከብቶችም የሀብት ምልክት ናቸዉ ዛሬም ድረስ። ከብቶች ሲዋለዱ ሰፊ ቦታ ያስፈልጋቸዋል ያንን ለማስከበር የኦሮሞ ነገድ አካባቢዉን እያሰፋ ሄደ ይህ ሂደት ደግሞ ወታደራዊ እንቅሰቃሴዎችን ይጨምራል በስምምነት ቦታህን ልቀቅ ስለማይባል ይህን ተከትሎም ሰፌ እልቂት ይሆናል ። እንግዲህ በከብት እርባታ(ፓስቶራሊዝም) የተሰማራ ህብረተሰብ እረኛ ነበር ማለቱ ስህተቱ ምንደነዉ እስከዛሬስ ይህን የሚተካ ምን ቃላት አሉን? ወይስ በወቅቱ የኦሮሞ ነገድ በከብት እርባታ ሳይሆን በሀይ ቴክ (high tech) ላይ የተሰማራ ነበር እንበል? ትልቅ የሚያደርገዉን ነገር የኦሮሞ እንባ ጠባቂ ነን የሚሉት ያሳንሱታል። ታላላቅ ጀግኖቻቸዉን ከኢትዮጵያ ጋር በማቆራኘት ስማቸዉን  ጥላሸት ይቀባሉ።

ነብሱን ይማረዉና ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ኦሮሞ ነዉ በኦሮሞነቱም የሚኮራ ነዉ ምንም እንኳን አዲሶቹ ኦሮሞ ነን ባዮች ወይም ደግሞ የታብሎይዱ ተስፋዬ ገ/አብ ገዳ ቢጠሉትም። በጥልቅ እዉቀቱ ወደር የማይገኝለት ሎሬት ጸጋዬ በአንድ ጽሁፉ ጋላ የሚለዉን መጠሪያ “የጸሀይ ብርሀን ፋና” ነዉ ብሎት ያለፈዉ። እንግዲህ ሎሬት ጸጋዬ ከተስፋዬ ገ/አብ ገዳ፤ከሁለቱ ሌንጮዎች፤ከህዝቅኤል ጋቢሳ፤ከጸጋዬ አራርሳ ያነሰ ኦሮሞ አልመሰለኝም። በእርግጥ ከሎሬት ጸጋዬ በላይ ፈረንጂ የነገረንን እናምናለን ብለዉ ከተቀበሉ ምርጫቸዉ የነሱ ነዉ በዚህ ቅዋሜ በበኩሌ የለኝም ታሪክን ወደሗላ ሂዳችሁ አታመሳክሩ ማለት ግን እዉቀት ላይ የተፈጸመ ወንጀል በመሆኑ አቅሙ ያለዉ ምሁር ሊቋቋመዉ ይገባል።  አለሙን የሞላዉ የኦሮሞ ምሁር እያለ የኦሮሞን ታሪክ የሚጽፉት አስመሮም ለገሰና ተስፋዬ ገ/አብ ናቸዉ በእርግጥ እነዚህ ግለሰቦችና ሻቢያ ለኦሮሞ ስስ ልብ ነሯቸዉ ነዉ ወይስ ደካማ አእምሮ ፈልገን ዘራችንን እንዝራ ብለዉ በማሰባቸዉ ነዉ? መልሱን ለጊዜ እተወዋለሁ።

ቀደም ባለዉ ጊዜ ከላይ በጠቀስኳቸዉ ወገኖች ላይ አድማና ስም ማጥፋት ተካሂዷል በእርግጥ አብዛኛዉ የሳይበር ጥቃት ቢሆንም በሐይሌ ላሬቦና በቴዲ አፍሮ ላይ ግን መተዳደሪያ ላይ ያነጣጠረ ክፉ ዘመቻ ነበር። በወቅቱ የአንድነት ሐይሉ በቂ ምላሺ ባለመስጠቱ በክፉ ስራቸዉ ተበረታተዉ ዛሬ ሐይሌ ላሬቦ ላይ በድጋሚ ተመሳሳይ ዘመቻ ከፍተዉበታል። ሐይሌ ላሬቦ ሌሎችም ከላይ የጠቀስኳቸዉ ግለሰቦች በወቅቱ እንዲህ ያለ ዘመቻ የተዘመተባቸዉ በግል ጉዳያቸዉ ሳይሆን ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ለማድረግ ጥረት በማድረጋቸዉና የዜግነት ግዴታቸዉን በመወጣታቸዉ ነዉ።የሚያሳዝነዉ በወቅቱ የአንድነት ሐይሉ የተወረዉን ድንጋይ መልሶ ባለመወርወሩ እነዚህ ወገኖች ዱላዉን ብቻቸዉን ተቀብለዉታል። እንደዉም አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት የጸረ ኢትዮጵያ ሐይሎች መጠቀሚያ ሁነዉ የገዛ ወገናቸዉን አስደብደበዋል ለዚህም ኢሳት በዋናነት ይጠቀሳል G7 የተባለዉም ድርጅት እንዲሁ ከበሬታና አንድነቱን ከነዚህ ገንጣዮች ጋር አስተካክሏል። ሌሎቹ በዚህ ነገር አቅዋም እንዲወስዱ ቢጠየቁም ግርግሩን ለድር ገጻቸዉ አድማቂነት በመፈለግ የዜግነት ግዴታቸዉን ሳይወጡ ቀርተዉ አገር ለማበጣበጥ አንድነትን ለማላላት የግል አስተዋጽኦ አድረገዋል።  ሌላዉን ወደ ጎን ትተን የኢትዮ ሚዲያዉ አብረሀ በላይ የሻቢያዉን ተስፋዬ ገ/አብ ጽሁፍ አላስተናግድም ብሎ እስከ አሁን ባቋሙ ጸንቷል በዚህ ነገር ብቻ ልናመስግን እንወዳለን።

በመስታወት ዉስጥ ያለ ሰዉ ድንጋይን ለመወርወር የመጀመሪያዉ አይሆንም።ጁዋር መሀመድ በሀጂ ነጂብ አማካይነት የዝግ ስብሰባ ተደርጎ ፕላኑን ሲናገር ክርስቲያን ያልሆነዉን ሁሉ በሜንጫ መቅላት ነዉ ብሎ ለተከታዩ ሲናገር ተከታዩ በታላቅ ጭብጨባ ሃሳቡን ሲያጸድቅ ሐጂ ናጅብ እንዳነተ አይነቱን ያብዛልን ያሉት ቪዲዮ በእጃችን ይገኛል ይህን ተከትሎም ክርስቲያኑ እና አብያት ክርስቲያናት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ደርሷል ንብረት ወድሟል ዜጋ ተገድሏል። (https://www.youtube.com/watch?v=RMLLmAMWdG8)   ጁዋር መሀመድ ብልግናዉን ከጨመረበት ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ንቆ አረባዊነትን ከመረጠ፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከችሎታዉ በላይ ከተለጠጠ፤ ምድር ላይ ካለዉ እዉነታ ይልቅ ጭብጨባና ተረትን ከመረጠ፤ የአንድነት ሐይሎችን ሆነ ብሎ መተናኮሎን ካላቆመ  የአንድነት ሐይሎች በየጊዜዉ ያደረገዉን የድንፋታ ንግግር እና የሜንጫዉን ጨምረን ይህን እንቅስቃሴ ወደሚጠሉ ተቋሞች እንደምንሄድ ሊያዉቀዉ ይገባልhttps://www.youtube.com/watch?v=1uICobhc3DM።  ተስፋዬ ገ/አብ ገዳም ከዚህ የተለየ እድል አይኖረዉም አኖሌን አስከትሎ ለደረሰዉ እልቂት ። ሌሎች ሐይሌ ላሬቦ ላይ ያነጣጠሩት የኦለፍ አመራርና አቀንቃኞች የነበሩ በአርባ ጉጉ፤ በበደኖ፤ በሀረር እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ዘርን በማጥፋት በቀጥታ የተሳተፉ በመሆናቸዉ የነሱም መረጃ በእጃችን ስለሚገኝ እነሱም በህግ ፊት ስራቸዉ ወደ ሗላ ተኪዶ ይመዘናል።

 

ባለፈዉ አቶ አሰፋ ጫቦ በህይወት እያለሁ ታሪክ እንዲህ መላ ቅጡን ሲያጣ አላይም በማለት ሰዉ የተቀጠፈበት፤ ወገን ባሪያ ተብሎ የተፈነገለት በኦሮሞዉ አባጅፋር በመሆኑ በዛ ለተፈነገሉት ወገኖቻችን ላይ ጂሬን የተባለ ቦታ ከአኖሌ የገዘፈ ሐዉልት ይሰራልን በማለት በተረት በጥላቻ ሳይሆን ታሪክን አስጨብጦ ማህደር አያይዞ አቅርቦልናል። ተዲያ አሰፋ ጫቦ እንደ ሌሎቹ ሲተፋበት ስለማይቀበል ከገፋም ለህግ ስለሚያደርሰዉ ሀሳቡ በጉምጉምታ እና በፓል አልሞ ተኳሾች ሙከራ ተደርጎ ነገሩ በአቶ አሰፋ ጫቦ ቁጥጥር ስር ዉሏል። ሰዉየዉ ክፉ ነዉ ተደብቀዉ ሊያጠቁት ቢየስቡም ሊደርስበት ይችላል መጠንቀቅ ጥሩ ነዉ።

ቀደም ባለዉ ጊዜ በላክሁት መልእክት የኢሳት ዋና አላማ በድፍረት ሊፈተሺ ይገባል። የኢትዮጵያ ባንዲራ ተሸፍኖ የኦለፍን ባንዲራ ያቀረበልን፤ ለኢሳይያስ አፈወርቅና ለመንግስቱ አፈቀላጤ የሆነ የሚዲያ ተቋም ዛሬ ሐይሌ ላሬቦ ታሪክን ታሪክ በማድረጉ ይቅርታ እንዲጠየቅ ያስገደደዉ ሐይል ማን እንደሆነ የኢሳት ተከታታዮች ሊያጣሩ ይገባል እላለሁ። እዚህ ላይ አያቆምም ጁዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ብሎ በአለም አቀፍ የሚዲያ ተቋም የመሰከረዉን ሰቱዲዮ ድረስ ጋብዞ ለዳግማዊ ስድብ ማመቻቸት አላማዉ ምንድነዉ? ከጁዋር ባላነሰ የቀድሞ ኦለፍ አባላት እና የኦሮሞ አክትቪስቶችስ ነን የሚሉት አላማቸዉና አካሄዳቸዉ እየታወቀ የኢሳት እሽሩሩ ከምን የመጣ ነዉ?  የራሳቸዉ የሆነ ከበቂ በላይ ሚዲያ ይዘዋል ለመግባቢያነትንም ቁቤን መርጠዋል ስለዚህ እነዚህን ሰዎች ጋብዞ የአንድነት ሐይሉ እንዲላላ፤ እንዲሳከር፤እንዲወናበድ ማድረግ ጠቀሜታዉ ለማን ነዉ?

ባጠቃላይ ኢሳት በኢትዮጵያዉያን መዋጮ የሚንቀሳቀስ ድርጂት ይመስለኛል በእርግጥ ስርጭቱና ሽፋን የሚሰጣቸዉ ፕሮግራሞች  እንደ ተዋጣዉ ገንዘብ ከሆነ ሻቢያና የአረብ አገሮች ይደግፉታል የሚባል ጭምጭምታ ስላለ ኢሳት የህዝብ ወይም public organization በመሆኑ አመታዊ ሒሳቡን በድረ ገጹ በግልጽ ለሚፈልገዉ ለእይታ ማብቃት ግዴታዉ ይመስለኛል የሀገሩም ህግ ያዛል። ይህም ማለት ገንዘቡ ከየት እንደመጣና ለምን ለምን አገልግሎት እንደሚዉል በዝርዝር እንዲቀርብ ሕጉ ያስገድዳል ። ይህ የሚዲያ ተቋም ጁዋር መሀመድ፤ ዳዉድ ኢብሳ፤ በያን አሶባን  በአክብሮት ጋብዞ ክፍሌ የሻዉን፤ ሐይሌ ላሬቦን፤ አሰፋ ነጋሺን ማበሻቀጡ የጤንነት ስላልሆነ እኛም አማራጫችንን እናጠንክራለን ጂብ ካለፈ ዉሻ ጮኸ እንዳይሆንብን።

ለማጠቃለያ ኢትዮጵያዉያን በአንድ ሳምባ እንደሚተነፍስ ሁሉ እንደ መንጋ አንነዳም የማስተዋል የረቀቀ አእምሮ አለን እንዲህ አይነቱን ምልልስ የምናደርገዉ ነገርን ለማጥራት እና አንድነታችንን ለማጠናከር አንጂ ወያኔ እንደሚያስበዉ ለመበላላት አይደለም ጽሁፉ ያነጣጠረዉ ኦሮሞን ወክለናል ለሚሉ ዉክልና ለሌላቸዉ በአላማ ከወያኔ ላልተለዩ ለአንድነት ጠላቶች መሆኑ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ።እዚህ ላይ የኦሮሞ ህዝብ በታሪክ የተከበረ ቦታዉን ይይዛል ኢት ጵያዊነትንም ያጠነክራል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 

 

 

 

 

በአማራ ህዝብ ህልውና ላይ የተቃጣውን የወያኔ ትግሬ ፋሽስቶች ተንኮል

$
0
0

ጫንያለው በዛበህ

በአማራ ህዝብ ህልውና ላይ የተቃጣውን የወያኔ ትግሬ ፋሽስቶች ተንኮል መቀልበስ የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ግዴታ ነው!
ጎንደር ላይ ጭንብል አጥልቀው ህዝብ እያመሱ ያሉ ወያኔ ትግሬዎች ተለይተው ታውቀዋል!
=====================================
አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅቱ ተጠናቋል።በጭልጋ ወረዳ የፋሽስት ህወሃትን አማራን ህዝብ ከፍሎ እርስ በእርሱ በማባላት አንድነቱን በማዳከም የትግሬን የበላይነት በዘላቂነት ለማስቀጠል በገንዘብ ተገዝተው የጭንብል ትግሬ ቡድኑን ተንኮል ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሱ ያሉ ጥቂት ቅጥረኞች ተለይተው የታወቁ ሲሆ እርምጃ ለመውሰድ ጥብቅ ክትትል እየተደረገባቸው ነው። ፋሽስት ህወሃት አማራ ህዝብ ጉያ ተመሳስለው የሚኖሩ ትግሬዎችን በቅማንት ጭንብል አደራጅቶ ቅጥረኞችን በገንዘብ በመግዛት የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራን ህዝብ ጥያቄ ለመቀልበስና የአማራን ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ለማዳከም ስትራቴጂ ቀይሶ በሰፊው ሲንቀሳቀስ መክረሙ ይታወሳል።

የዶክተር በያን አሶባ ጆኒያ ሙሉ ውሸትና ዘረኛ የፈጠራ ታሪክ

$
0
0

(አቻምየለህ ታምሩ)

ቀደም ሲል የኦነግና አሁን ደግሞ የኦዴግ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር በያን አሶባ በቅርቡ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የአማርኛው ክፍል ቀርበው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ «አከራካሪ ጉዳዮች ዙሪያ» ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌና ከዶክተር ብርሀኑ መንግስቱ ጋር በጋዜጠኛ ትዝታ በላቸው አጋፋሪነት ተከራክረው ነበር።

ዶክተር በያን አሶባ ለኦነግና ሌሎች ተገንጣይ የዘር ድርጅቶች ትግል መነሾ የሆናቸውን «የብሄረሰብ ጭቆና» ያሉትን ዋና ማሳያ ሲገልጹ «የአጼ ምኒልክ ወረራ ሁለት ህዝቦችን ነው ኢትዮጵያ ውስጥ የፈጠረው፤ ለዚህ መረጃ የመጀመሪያው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ህገ መንግስት ሲሰራ፤ ኢትዮጵያዊ ማነው? ለሚለው ጥያቄ የመጀመሪያው አንቀጽ ነው መልስ የሰጠው። ያ ህገ መንግስት. . . ምንድን ነው የሚለው ኢትዮጵያ ከሁለት ህዝቦች ነው የምትመሰረተው፤ በእንግሊዝኛ ቋንቋ Natives ከሚባሉትና subjects የሚባሉት በጋራ ነው የኢትዮጵያን ህዝብ የሚመሰርቱት ይላል» ይላሉ።

ዶክተር በያን አሶባ ቀጠል አድርገው «በአንድ አገር ውስጥ Native የሚለውን National ወይንም ዜጋ እንበለው፤ subjects የምንላቸው ደግሞ ዜጋ ያልሆኑ ወይንም ከዜጋ ያነሰ መብት ያላቸው እንደማለት ነው።» ይላሉ። ከዚያም ከጓዶቻቸው ጋር ሆነው ኦነግን መስርተው ለመገንጠል እንዲታገሉ ያደረጋቸውን መነሾ ሲያስረዱ «ይሄ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ህዝቦች ከመንግስት ጋር ያላቸው ግንኙነት [ህገ መንግስቱ ዜጋ የሆነና ዜጋ ያልሆነ ይላል ያሉትን ማለታቸው ነው]፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸው status [ደረጃ] ነው የሚያታግለን» ሲሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ህዝቦች ስለመጨቆናቸው ማስረጃው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ አንድ መሆኑንና የሚያታግላቸውም ይህ ዜጋ «የሆኑና ዜጋ ያልሆኑ» በሚል በህገ መንግስቱ የዘፈረው ጉዳይ እንደሆነ የፈጠራ ታሪክ ደርተው እንደ ታሪካዊ ሰነድ ይጠቅሳሉ።

ዶክተር በያን አሶባ የህግ «ምሁር» እንደሆኑ በቃለ መጠይቁ መግቢያ ላይ ተጠቅሷል። ሆኖም ግን በኛ አገር የግራ ፖለቲከኞች ዘንድ «ምሁርነት» ማለት ለፖለቲካ መጠቀሚያ የሚንጠለጠል ማዕረግ እንጂ ማገናዘብን፣ ማመሳከርንና ማጣራትን፤ ደግሞ ደጋግሞ መፈተሽን አይጨምርም። በአገራችን የግራ ፖለቲከኞች ዘንድ ምሁርነት የእንጀራ መበያ ካባና የህዝብ ማታለያ ጭንብል እንጂ የእውነት ማጣሪያ ልቀት [የexcellence ደረጃ] አይደለም። ያገራችን የግራ ፖለቲከኛ ምሁራን እግራቸውን አስንተው ሲዋሹ፤ የፈጠራ ታሪክ እያመረቱና መጽሀፍ ሲደርቱ ለፖለቲካ እስከ ጠቀማቸው ድረስ የህሊናም ሆነ የሞያዊ ስነ ምንግባር ልጓም የላቸውም።

ዶክተር በያን አሶባና የትግል ጓዶቻቸው ኦነጋውያን ላለፉት አርባ ሁለት አመታት ኦነግን እየመሩ ሲታገሉና ሲያታግሉ፤ የውሸት ሮፓጋንዳ ሲሰሩ የኖሩት «የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝቦች ዜናጋ ዜጋ ያልሆኑ በሚል ስለሚከፍል፤ ኦሮሞ በህገ መንግስቱ የዜግነት status ስላልተሰጠው፤ የራሳቸውን አገር መስርተን ኦሮሞ የዜግነት status እንዲኖረው እናድርግ» በሚል ነው። ሰው እየተማረ ሲሄድ በአስተሳሰብና በስብዕው ላይ የአመዛዛኝነትና የኃላፊነት ስሜት ነው አብሮ እያደገ ይሄዳል። በግራ ፖለቲካ ኩሸት የተፈጠሩት የአገራችን የዘር ፖለቲከኞች ግን እየተማሩ ሲሄዱ የሚያገኙትን የዶክተርነትና ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የአመዛዛኝነታቸው መለኪያ ሳይሆን የፈጠራ ታሪካቸው ለማስረጽ የሚጠለቅ ክታብ አድርገው ያንሱበታል።

እስቲ ዶሴው ይውጣና እውነቱ ዶክተር በያን አሶባ ካሉት አኳያ ይታይ። በ1923 ዓ.ም. የጸደቀው የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት አንቀጽ አንድ እንደሚከተለው ይነበባል. . .

«የኢትዮጵያ መሬት፡ ከወሰን እስከ ወሰን በሙሉ የንጉሰ ነገስት መንግስት ነው። በንጉሰ ነገስት ግዛር ውስጥ በዜግነት የሚኖር የኢትዮጵያ ተወላጅ ሁሉ ባንድነት የኢትዮጵያ ህዝብ ነው።»

ዶክተር በያን አሶባ በ1923 ዓ.ም. የጸደቀው የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ «ዜጋ የሆኑና ዜጋ ያልሆኑ» ወይንም «Native እና Subject» ይላል ያሉት የሳቸውና የኦነግ ፍጹም ፈጠራ እንጂ በህገ መንስግቱ የመጀመሪያው አንቀጽ ላይ እንደዚያ የሚል አገላለጽ የለም።

እኔ የሚገርመኝ የተማሩ ተብለው ዶክተርና ፕሮፌሰር እየተባሉ የሚጠሩ ፖለቲከኞች ሲናገሩና ሲጽፉ፤ እንደ ወረደ የሚቀበል እንጂ እያንዳንዷን ነገር በአንክሮ የሚከታተል፤ የሚመለከትንና የሚናገሩትንም ሆነ የሚጽፉትን ነገር የሚፈትሽ፤ መረጃና ማስረጃ አገላብጦ እውነቱን የሚያወጣና የሚሞግታቸው ሰው የሚኖር አይመስላቸውም።

እነዚህ የውሽት ታሪክ እየፈጠሩ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ የሚሰሩ የዘር ፖለቲከኞች እስከ ዛሬ ድረስ እግራቸውን እያነሱ ለተከታዮቻቸው ሲዋሿቸውና ሲያታልሏቸው ሲኖሩ ከተከታዮቻቸው መካከል አንድም ሰው ተነስቶ እንደሚንቋቸውና እንዴት እንደደብ እንደሚዩዋቸው ተገንዝቦ ሲያጋልጣቸው አለማየቴ ሁል ጊዜ ይደንቀኛል።

ዶክተር በያን አሶባ እንደነገሩን ከትግል አጋሮቻቸው ጋር ሆነው ኦነግን መስርተው እንዲታገሉ ያስገደዳቸው በ1923 ዓ.ም. በአማርኛ ተጽፎ የጸደቀው የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት የመጀመሪያው አንቀጽ ላይ የኢትዮጵያን ህዝብ «ዜጋ የሆነና ዜጋ ያልሆነ» ተብሎ «መለያየቱ» ነበር ካሉንና ከዚህ ሁኔታ ለመውጣት መፍትሔው የኦሮሞን ነጻ አገር መስርተው በአዲሱ አገር ውስጥ ኦሮሞን ዜጋ ለማድረግ መታገል ነው» ብለው ህዝቡን ካደረጁና ካታገሉ፤ « የትግላችን መንስዔ ነው» በማለት በ1923 ዓ.ም. የጸደቀው «የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ «ዜጋ የሆኑና ዜጋ ያልሆኑ» ወይንም «Native እና Subject» ይከፍላል ያሉት ያልተጻፈ፣ ያልነበረና ደረቅ የፈጠራ ክስ ከሆነ ኦነግ የኦሮሞን መንግስት ለመመስረት የታገለው ራሱ በፈጠረው የውሸት ትርክት ላይ ተመስርቶ ነው ማለት ነው። የዶክተር በያን ንግግር በማስረጃ ሲፈተሽ የምንደርስበት ድምዳሜ ቢኖር ይህ ብቻ ነው።

ከታች ከታተመው በ1923 ዓ.ም. የጸደቀው የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት ማየት እንደሚቻለው አንቀጽ አንድ ዶክተር በያን አሶባ እንደሚሉት የኢትዮጵያ ህዝብ «ዜጋ የሆኑና ዜጋ ያልሆኑ» ወይንም «Native እና Subject» ተብሎ አልተከፈለም።

የሌላ ታሪክ ፈጥሮ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ «ዜጋ የሆኑና ዜጋ ያልሆኑ» ወይንም «Native እና Subject» ይላል በማለት በፈጠራ ክስ አንድ ህዝብ ማታለልና መዋሸት የሚያሳየው ነገር ቢኖር ኦነጋውያን ለሚዋሹት ህዝብ ያላቸውን ንቀት ብቻ ነው። አንድ ህዝብን የሚያከብር ድርጅት ህዝብን አይዋሽም! ኦነግ ግን ያልተጻፈ የህገ መንግስት አንቀጽ እንደተጻፈ በማስመሰል በልብ ወለድ ፈጠራ ««የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝቦች ዜናጋ ዜጋ ያልሆኑ በሚል የኢትዮጵያን ህዝብ ይከፍለዋል» ሲል ትውልዶችን አታሏል፤ አገርም አፍርሷል።
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ዶክተር በያን አሶባ እንደሚሉት ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ሁሉ የአንድ ቤተሰብ እኩል ዜጋ ከማድረጉ ባሻገር ኦነግ ባወጣው የመሬት ላራሹ አዋጅ የመሬት ባለቤትነት መብቱ ተነጥቆ የደርግና የወያኔ ጭሰኛ ከመሆኑ በፊት የኢትዮጵያን ገበሬ የግል የመሬት ባለቤትነት ያረጋገጠና በኢትዮጵያ ታሪክ ከተጻፉት ህገ መንግስቶቹ ሁሉ በተራማጅነቱ ታይቶ የማይታወቅ ህገ መንግስት ነበር።

እነ ዶክተር በያን አሶባ ግን ሁለት ጸጉር አብቅለው፤ በዲግሪ ላይ ዲግሪ ደርበው፤ የሰሩትን ደባና ያጠፉትን ጥፋት ለመሸፈን ሲሉ ብቻ ንግግራቸውንና ጽሁፋቸውን የሚመረምር ሰው ያለ ስለማይመስላቸው ከ42 ዓመታት በፊት አጀንዳ ያላቸው ላላዋቂዎች የፈጠሩትንና በሐሰት የመሰረቱትን የፈጠራ ክስ አሁንም እያመነዠኩ ሲዋሹት የኖሩትን ትውልድ እንደ ጴጥሮስ ደግመው ደጋግመው ዛሬም ይክዱታል፣ ያታልሉታል፣ ይንቁታል፤ ክብር እንደሌላቸው በአደባባይ ያሳዩታል።

ዶክተር በያን አሶባና ድርጅታቸው ኦነግ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ «ዜጋ የሆኑና ዜጋ ያልሆኑ» ወይንም «Native እና Subject» ሲል ይከፍላል በማለት የፈጠሩትን የኃጢያት ክስ አንባቢ ያገናዝብ ዘንድ በእጄ ያለውን በ1923 ዓ.ም. የጸደቀው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ኦሪጅናል የአማርኛ ቅጂ የመጀመሪያ አንቀጽ «ኢትዮጵያዊ ማነው?» ለሚለው ጥያቄ የህገ መንግስቱን መልስ ወረድ ብዬ ባተምሁት የህገ መንግቱ የመጀመሪያ ገጽ ላይ በቀይ መስመር አስምሬበታለሁ። ይህንን የተሰመረበት የመጀመሪያ አንቀጽ ነው እንግዲህ ዶክተር በያን አሶባ « የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ህገ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ «ዜጋ የሆኑና ዜጋ ያልሆኑ» ወይንም «Native እና Subject» ይላል፤ የታገልነውም በዚህ ምክንያት ነው» ሲሉ የታገሉት በውሸት ታሪክ እንደሆነ በአደባባይ ራሳቸውን የሚያጋልጡት።

ገራሚው ነገርኮ የያ ትውልድ የግራ ፖለቲከኞች ዛሬም ድረስ ባልፉት 42 ዓመታት የፈጠሯቸውን የሀጢያት ታሪኮች መመርመር አለመጀመራቸው ነው። ምናልባት እንዲህ ዶሴው ሲገለጥ ዶክተርነታቸው ከብዷቸው የፈጠሩት የውሸት ታሪክ ፍጹም ልብ ወለድ እንደሆነ ተገንዝበው ለስህተታቸው ትውልዱን ይቅርታ በመጠየቅ ረገድ ዶክተር በያን አሶባ የመጀመሪያው ይሆኑ ይሆን?ሲሆን ለመስማትና ለማየት ያብቃን!

ዶክተር በያን አሶባ በንግግራቸው የተናገሯቸውን ሌሎች የኦነግ የፈጠራ ትርክቶች ወደፊት በማስረጃ ታግዘን በምናቀርባቸው ጽሁፎች እንመለሰባቸዋለን።

ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የዳያስፖራው የባንክና የኢንሹራንስ አክሲዮኖች ለሽያጭ እየቀረቡ ነው

$
0
0

በባንኮችና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች ይዘው የቆዩ ከ700 በላይ የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባለድርሻዎች መገኘታቸው፣ ለብሔራዊ ባንክ ሪፖርት ቀረበ፡፡ የእነዚህ ባለአክሲዮኖችን ድርሻ ለኢትዮጵያውያን በሽያጭ ለማስተላለፍ ባንኮች ጨረታ ማውጣት ጀምረዋል፡፡

ከፋይናንስ ተቋማት አክሲዮን መግዛት ለውጭ ዜጎች የተከለከለ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች የውጭ ዜግነት ይዘው ባለአክሲዮን የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህንን ለማጣራት በተሰጠ የጊዜ ገደብ እስካሁን ከ700 በላይ የውጭ ዜግነት የያዙ ባለአክሲዮኖች መገኘታቸውን የሚያረጋግጥ ሪፖርት፣ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ከሁሉም የፋይናንስ ተቋማት ተሰብስቦ ለብሔራዊ ባንክ ሪፖርት የቀረበባቸው እነዚህ ባለአክሲዮኖች፣ በቅርቡ በወጣ መመርያ መሠረት ያላቸውን የአክሲዮን ድርሻና አክሲዮናቸው ያስገኘላቸውን ትርፍ ይዘው እንዲወጡ ዕድል ተሰጥቷቸዋል፡፡ የፋይናንስ ተቋማቱ ድርሻቸውን በመስጠት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሠርተፊኬቶቻቸውን እየተቀበሉዋቸው ነው፡፡

በአገሪቱ ሕግ መሠረት የውጭ ዜጋ ሆኖ በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የአክሲዮን ድርሻ መያዝ በወንጀል የሚያስጠይቅ እንደሆነ ቢታወቅም፣ በጉዳዩ ላይ ከተመከረ በኋላ የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድርሻቸውን ይዘው እንዲወጡ መወሰኑ መገለጹ አይዘነጋም፡፡ በዚህም መሠረት በግንባር ለቀረቡ ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻቸው በኩል አክሲዮናቸውንና የትርፍ ድርሻው ይዘውት የቆዩትን ደግሞ፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ለማስተላለፍ የፋይናንስ ተቋማቱ ግልጽ ጨረታ እያወጡ ነው፡፡

የባንክና የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ የውጭ ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖችን ድርሻ ለጨረታ እያቀረቡ ያሉትም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር FIS/01/2016 ባስተላለፈው መመርያ መሠረት ነው፡፡

በባንኮችና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች የውጭ ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስም የተመዘገቡ አክሲዮኖችና የአክሲዮን ሠርቲፊኬቶች ለኩባንያዎቹ ተመልሰው፣ አክሲዮኖቹን በገዙበት ዋጋ ለባለድርሻዎቹ እንዲከፈል ተወስኗል፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ እስካሁን የውጭ ዜግነት ያላቸው ተብለው የተለዩት 710 ናቸው፡፡ የባለአክሲዮኖች ድርሻም ከ0.8 እስከ 1.0 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይገመታል፡፡

በባለቤትነት ይዘዋቸው የነበሩ ባንኮችና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ክፍያ የፈጸሙባቸውን አክሲዮኖች በግልጽ ጨረታ እንዲሸጡ የሚገደዱ በመሆናቸው፣ የአክሲዮኖቹን ሽያጭ ለመፈጸም ባንኮች የጨረታ ማስታወቂያዎቹን ማውጣት ግድ ብሏቸዋል፡፡ ጨረታው ከዚህ ቀደም ለባለአክሲዮኖች ቅድሚያ ይሰጥ የሚለውን ወደ ጎን በማለት፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው በሙሉ የሚሳተፉበት ነው፡፡ አንዳንድ ባንኮች የአክሲዮን ሽያጫቸውን ከባለአክሲዮኖች ውጪ ለመሸጥ የሚያስችላቸው የመተዳደሪያ ደንብ ባይኖራቸውም፣ የውጭ ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተያዙ አክሲዮኖችን ለመሸጥ የውስጥ መተዳደሪያ ደንባቸውን እስከመቀየር ሊያደርሳቸው እንደሚችል የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ለጨረታ የሚቀርቡት አክሲዮኖች የሚያስገኙት ትርፍ በቀጥታ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡ ዋናው የአክሲዮን ዋጋ ደግሞ ባንኮች ለተሰናባቾቹ ባለአክሲዮኖች ቀድመው ክፍያ የፈጸሙ በመሆናቸው ለባንኮቹ ተመላሽ ይደረጋል፡፡ እስካሁን ቀርበው ያልወሰዱም ካሉ በመጡ ጊዜ የአክሲዮን ድርሻቸውን መውሰድ እንደሚችሉም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 34 የግል ባንኮችና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በድምሩ ከ140 ሺሕ በላይ አክሲዮኖቻቸው የውጭ ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተይዘው ነበር፡፡ ኩባንያዎቹ በአሁኑ ወቅት ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ በመሆናቸው፣ እስካሁን ሪፖርት በተደረገው መሠረት የውጭ ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ድርሻ ከ350 እስከ 400 ሚሊዮን ብር ዋጋ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዜና- ሪፖርተር

‹‹ከዚህ በፊት የታዩ ጉድለቶች በአሥረኛው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዳይደገሙ ይደረጋል››

$
0
0

አቶ ማቴዎስ አስፋው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን ኮሚሽነር

የ130 ዓመታት ዕድሜ ባለፀጋ የሆነችው አዲስ አበባ፣ አሥረኛውን ማስተር ፕላን በይፋ ተግባራዊ ለማድረግ የመጨረሻ ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ትገኛለች፡፡ ይህ ማስተር ፕላን በ2006 ዓ.ም. የመጠቀሚያ ጊዜው ያበቃውን ዘጠነኛውን ማስተር ፕላን የሚተካ ሲሆን፣ በውስጡ እጅግ አጓጊ ዕቅዶችን ይዞ ቀርቧል፡፡ ማስተር ፕላኑ በተለይ የመካከለኛውን የከተማው ክፍል ዞን አንድ ብሎ በመሰየም ረዣዥምና ከፍተኛ ጥግግት ያላቸው አገልግሎት መስጫ ግንባታዎች የትራንስፖርት አውታር መነሻ፣ የአረንጓዴ ልማት እምብርትና ለእግረኞች እንቅስቃሴም ሁነኛ ሥፍራ ሆኖ ተዘጋጅቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህንን አማላይ ዕቅድ በትክልል ተግባራዊ ለማድረግ አራት ተጨማሪ ተቋማት እንዲቋቋሙ ምክንያት ከመሆኑ ባሻገር፣ ፕላኑ በቅጡ ተግባራዊ እንዲደረግ ግዙፍ የመዋቅር ለውጥ ፕሮግራሞችን አስከትሎ ቀርቧል፡፡ በተለይ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ በከተማው ታሪክ ትልልቅ ለውጦች እንዲመጡ ምክንያት የሆነውን ዘጠነኛው ማስተር ፕላን፣ እንዲሁም በዘጠነኛው ማስተር ፕላን የታዩ ክፍተቶችን ሞልቶ የራሱን ወርቃማ መለያዎች ይዞ የተዘጋጀው አሥረኛው ማስተር ፕላን በማዘጋጀት በኩል ዋነኛ ተዋናይ የሆኑትን አቶ ማቴዎስ አስፋውን ውድነህ ዘነበ አነጋግሯቸዋል፡፡ አቶ ማቴዎስ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ለተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- አዲስ አበባ ከተቆረቆረች 130 ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡ በተለይ ከጣሊያን ወረራ በፊት ፍል ውኃ፣ አራት ኪሎና አራዳ ጊዮርጊስ፣ ከድል በኋላም የተወሰኑ ዘመናዊ አካባቢዎችን ማልማት ተችሏል፡፡ ከተማው በዚያን ጊዜ ከአሥርና ከሃያ ኪሎ ሜትር የበለጠ ስፋት አልነበረውም፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ከተማው ያለውን መሬት በሙሉ ተጠቅሟል ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ሁኔታ ፕላንን የተከተለ ነው ማለት ይቻላል? ምክንያቱም ከተማዋ ከተቆረቆረች ጊዜ ጀምሮ ዘጠኝ ማስተር ፕላን ብታስተናግድም ማስተር ፕላን የጎበኛቸው የማይመስሉ ግንባታዎች በስፋት ስላሉ ነው ይህንን የምጠይቅዎ?

አቶ ማቴዎስ፡- አዎን! ዕድገቱ ያመጣው ነው፡፡ ግን ግንባታው የተካሄደው በፕላን ብቻም አይደለም ልንል እንችላለን፡፡ ከፕላን ውጭ የተሠሩ ሥራዎችም ስላሉ ማለት ነው፡፡ የከተማይቱን የጎንዮሽ መስፋፋት እንዳየኸው ከአራዳ ተነስቶ በሁሉም አቅጣጫ በተለይ በምሥራቅ፣ በምዕራብና በደቡብ አቅጣጫዎች ተስፋፍቷል፡፡ በሰሜን እንኳ በብዙ ነገሮች  የተገታ ስለሆነ ያን ያህል አልሄደም፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት የተደረገው መስፋፋት ወደ ምሥራቅና ወደ ደቡብ ነው፡፡ እንዳልከው ከመሀል ተነስቶ በተለያየ አቅጣጫ እያደገ የመጣው በፕላኖቹ መሠረት ነው፡፡ ነገር ግን አዲስ አበባ አሁን ያለችበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክልል የምንለው የተደረሰበት በደርግ ዘመን በ1967 ዓ.ም. ተጀምሮ፣ በ1976 ዓ.ም. የተጠናቀቀው የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን ወቅት ነው፡፡ ከተማው የደረሰበት የጎንዮሽ መስፋፋት ማለት ነው፡፡ የዛሬ 32 ዓመት ይህ ማስተር ፕላን ለአዲስ አበባ መቶኛ ዓመት ቀርቦ  ተግባራዊ ሆኖ ነበር፡፡ ነገር ግን ኢሕአዴግ አዲስ አበባ ከተማ እስከገባ ድረስ ይህ ማስተር ፕላን ሲሠራበት ቆይቷል፡፡ ከሞላ ጎደል ሳይፀድቅ ቆይቶ ኢሕአዴግ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ማስተር ፕላኑን እንዳለ ወስዶ አፅድቆ ሲገለገል ቆይቷል፡፡

ሪፖርተር፡- እርስዎ በዘጠነኛውና በአሥረኛው ማስተር ፕላኖች ዝግጅት ላይ ዋነኛ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ከዚያ በፊት የነበሩት ስምንት ማስተር ፕላኖችን የመገምገም ዕድሉ ይኖሮዎታልና እንዴት ነበር አተገባበራቸው? በአብዛኛው ተግባራዊ ሆነዋል ማለት ይቻላል? በከተማው ላይ ያሳደሩት ተፅዕኖስ ምን ይመስላል?

አቶ ማቴዎስ፡- ስምንቱ ማስተር ፕላኖች የተወሰነ ተፅዕኖ ነበራቸው፡፡ በተለይ ዋና ዋና የመሠረተ ልማት አውታሮችን ከማሟላት አኳያና የከተማዋን የዕድገት አቅጣጫ ከመወሰን አኳያ ተፅዕኖ ነበራቸው፡፡ የመጀመርያው ማስተር ፕላን የምንለው በወረቀት ያልሰፈረው የእቴጌ ጣይቱ የአሰፋፈር ዕቅድ ጀምሮ፣ በየጊዜው የተዘጋጁት ማስተር ፕላኖች የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል፡፡ አንዳንዶቹ ማስተር ፕላኖች ለምሳሌ የቸርችል ጎዳናን ብንመለከት ማስተር ፕላኑን ተከትሎ የተሠራ ነው፡፡ ከተማይቱን እስከ አቃቂ ቃሊቲ የመውሰድ ዕቅድ ፕሮፌሰር ፓሎኒ ያዘጋጁት የማስተር ፕላን አካል ነው፡፡ የከተማይቱን ዕድገትና ዋና ዋና ማስተር ፕላኖች ከመወሰን አኳያ ተፅዕኖ ነበራቸው፡፡ ግን ወደ ዝርዝሩ ከሄድን የመኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚሠሩትን የቤት ዓይነቶች፣ የሥራ ቦታ አካባቢ የሚሠሩ ሕንፃዎችን፣ የሥራ ቦታዎችና የመኖሪያ አካባቢዎች፣ እንዲሁም የመዝናኛ አካባቢዎች የሚገኙባቸው የትራንስፖርት አውታሮችና እንዲሁም በከተማው ሊኖሩ የሚገባቸውን አገልግሎቶች በተዋረድ የማስቀመጥ ሒደት ላይ፣ በማስተር ፕላኑ የተቀመጡትን የመሬት አጠቃቀሞች በአግባቡ ከመተግበር አኳያ በርካታ ከማስተር ፕላኑ ያፈነገጡ ሥራዎች ነበሩበት፡፡ ይህ የሆነበትን በርካታ ምክንያቶች ማየት እንችላለን፡፡ ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ አንደኛ ፕላኖቹ የተዘጋጁት በአመዛኙ ከተማውን በማያውቁ ሰዎች ነው፡፡ ወይም ባለሙያዎች ለተወሰነ ጊዜ ከተማውን ዓይቶ ማስተር ፕላኑን አዘጋጅተው ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ማስተር ፕላኖች ደግሞ በፍፁም አገሪቱንም ከተማይቱንም አይተው በማያውቁ ለምሳሌ በጣሊያን ወረራ ጊዜ አንደኛው ማስተር ፕላን ሮም ከተማ ውስጥ ነው የተዘጋጀው፡፡ ከተማይቱን በማያውቅ ሰው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትልቁ ጉድለት የሚነሳው ከዚህ ነው፡፡ ማስተር ፕላኖቹ የተዘጋጁት የከተማውን ባህሪ፣ የሕዝቡን ሥነ ልቦና፣ ባህልና ታሪክ በማያውቁ ሰዎችና የከተማውንና የሕዝብን ፍላጎት በአግባቡ በማይረዱ ሰዎች ነበር፡፡ የማስተር ፕላን ዝግጅቱ በተመለደው የአውሮፓ ከተሞች ዕድገት ላይ ልምድ የነበራቸው ባለሙያዎች የሚያዘጋጁት ስለነበር ያንን አምጥቶ እዚህ ላይ የመጫን ሐሳብ ነበር፡፡

ሁለተኛው ለአንድ ከተማ ማስተር ፕላን ተዘጋጀ ማለት፣ ማስተር ፕላኑ ራሱ ወደ ተግባር የሚገባ አይደለም፡፡ ተግባር አካል ይፈልጋል፡፡ የአንድ ከተማ ማስተር ፕላን ማለት የአንድ ከተማ ሕገ መንግሥት ማለት ነው፡፡ በማስተር ፕላኑ ላይ የተቀመጠውን ራዕይ፣ በማስተር ፕላኑ ላይ የተቀመጡ ግቦችንና ዝርዝር ተግባራቸውን ለመተግበር የሚያስችሉ ተቋማት ያስፈልጋሉ፡፡  በሌላ በኩል ተግባሪ ተቋማት ብቻ ሳይሆን፣  ተቋማት ማስተር ፕላኑን ተከትለው መሥራት አለመሥራታቸውን የሚከታተልና የሚቆጣጠር የፕላኑ ባለቤት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህም አልፎ ማስተር ፕላኑ የፈለገውን ወርቃማ ሐሳብ ቢኖረውም፣ ለነዋሪውም ለአገሪቱም የሚጠቅም የተዋበ ሐሳብ ቢኖውም፣ የሚተገበረው በሕዝብ ላይ ነው፡፡ ከሞላ ጎደል ማስተር ፕላኑን ጠንቅቆ የሚያውቅ የከተማ ነዋሪ ያስፈልጋል፡፡ እንግዲህ እነኝህን ነገሮች ስናይ በተለይ እስከ ሰባተኛው ማስተር ፕላን ድረስ ስናይ ሕዝብ  ያውቀዋል? የሚቆጣጠር አካልስ አለ ወይ? ተግባሪ ተቋማት ያውቁታል ወይ? ተግባሪ ተቋማትን የሚከታተልና የሚቆጣጠር አካል አለ ወይ? ስንል እነዚህ ሁሉ የሉም፡፡ የነበሩን ማስተር ፕላኖች በወረቀት ላይ የተቀመጡ ነበሩ፡፡ ያንን ፕላን ተከትሎ የተጻፉ ማብራሪያ ጽሑፎች ነበሩ፡፡ ስለዚህ ያንን ማስተር ፕላን በአግባቡ ለመተግበር ተቋማት ባልነበሩበትና ስለማስተር ፕላኑ የሚያውቁ ባለሙያዎች ባልነበሩበት፣ ባለሙያዎች ስንል አገር በቀል ባለሙያችዎች ማለታችን ነው፡፡ በሕዝብም ዘንድ ስለማስተር ፕላን ምንም ግንዛቤ ባልነበረበት ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡

በተለይ በአመዛኙ በከተማው ውስጥ የሚካሄዱትን የልማት እንቅስቃሴዎች ፈር ከማስያዝ አኳያ በንጉሡ ዘመን የመሬት ባላባቶች ነበሩ ትልቅ ሚና የነበራቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የየራሳቸው ሚና ነበራቸው፡፡ ምናልባት የተወሰነም ቢሆን ስለከተማ ፕላን ምንነት፣ የከተማ ፕላን እንዴት ይሠራል? የሚለው ነገር የመጣው በስምንተኛው ኢትዮ-ጣሊያን ማስተር ፕላን ጊዜ ነው፡፡ ይህ ስምንተኛው ማስተር ፕላን በፌዴራል የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ሥር በተቋቋመ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አብዛኛዎቹ ባለሙያዎች የጣሊያን፣ የተለያዩ የአውሮፓና የኛም ባለሙያዎች በተወሰነ ደረጃ ገብተውበት ማስተር ፕላኑ ተዘጋጅቷል፡፡ ያኔ ነው በተወሰነ ደረጃ ባለሙያዎቻችን ስለማስተር ፕላን ዝግጅት ሐሳብና ዕውቀት ለማግኘት የቻሉት፡፡ ስለዚህ ስምንተኛው ማስተር ፕላን ለብዙ ነገሮች ፋና ወጊ ነበር፡፡ ምንም እንኳ የጣሊያን ባለሙያዎች የነበሩበት ቢሆንም፣ የእኛም ባለሙያዎች ተሳታፊ ነበሩ፡፡ የፕላን ዝግጀቱ ላይ ከጣሊያን አንድ ሥራ አስኪያጅ፣ ከኢትዮጵያ አንድ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ነበር ፕላኑን የመሩት፡፡ በእኛ ወገን ፕሮፌሰር ተከስተ ነበሩ፡፡ ፕሮፌሰር ተከስተ ዕውቅ ባለሙያ ነበሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ለከተማችንና ለአገሪቱ በቀጣይ ማስተር ፕላን ሊያዘጋጁ የሚችሉ ባለሙያዎች እንዲሰባሰቡ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱና ፕሮፌሰር ተከስተ የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነበር፡፡ ከዚያ በተገኘ ልምድ ነው በአገር አቀፍ ደረጃ የከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት ተብሎ የተቋቋመው፡፡ ለአገራችን ይህ የመጀመርያ ተቋም ነው፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዓላማ ይህን የማስተር ፕላን ዝግጅት በተከታታይ የውጭ ባለሙያዎች እየመጡ የሚያዘጋጁት መሆን የለበትም፡፡ አገራዊ ባለሙያዎች በኢንስቲትዩቱ ሠልጥነው የአዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን፣ የክልሎችንም ማስተር ፕላን እንዲያዘጋጁ ጥረት ሲደረግ ነበር፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ነው ወደ ዘጠነኛው ማስተር ፕላን የተገባው፡፡

ሪፖርተር፡- ሰባቱ ወይም ስምንቱ ማስተር ፕላኖች በውጭ ባለሙያዎች የተዘጋጁ ናቸው፡፡ እነዚህ ማስተር ፕላኖች የተዘጋጁት ከተማውን በሚያውቁ ሰዎች አልነበረምና አተገባበሩም መልካም አይደለም፡፡ በዘጠነኛውና አሁን በይፋ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠቀበውን አሥረኛው ማስተር ፕላን በትክክል ተግባራዊ ለማድረግ፣ ከተማውን በሚገባ የሚያውቁ  ባለሙያዎችና አመራሮች ያስፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በተለይ በአመራር ቦታ ላይ የሚገኙ ከተማውን በቅጡ ይረዳሉ ብለው እንደማያምኑ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የእርስዎ መሥሪያ ቤት ከተማው፣ ከተማውን በሚያውቁ ሰዎች እንዲመራ ለመንግሥት ያቀረበው ሐሳብ ይኖር ይሆን? የአዲስ አበባ ቻርተርም አዲስ አበባ በአዲስ አበባውያን ትመራለች ይላል፡፡

አቶ ማቴዎስ፡- የከተማ ፕላንና የከተማ ሥራ አመራር ተነጣጥለው የሚታዩ አይደሉም፡፡ እንዲሁም የከተማ ፕላን ስንል፣ የከተማ ፕላን ምንነት ሲገለጽ፣ ማስተር ፕላንን በሚገባ ተግባራዊ ለማድረግ የከተማ ሥራ አመራር አንደኛው መሣሪያ ነው የምንለው፡፡ ከተማን መምራት የሚያስፈልጉ በርካታ ሌሎች መሣርያዎች አሉ፡፡ ነገር ግን አንደኛው ማስተር ፕላን ነው፡፡ ስለዚህ ተነጣጥለው የሚታዩ አይደሉም፡፡ ከተማ እመራለሁ ስትል እጅህ ላይ ማስተር ፕላን አለ ማለት ነው፡፡ ማስተር ፕላን ሳይጨበጥ ከተማ እመራለሁ ማለት ባትሪ ሳይኖር የጨለማ ጉዞ እንደ መጓዝ ነው፡፡ ማስተር ፕላኑን ጨበጥን ማለት ማስተር ፕላኑ ላይ የተቀመጡ ጉዳዮችን፣ ማስተር ፕላኑ ከምን ተነስቶ እንደተጠና የተቀመጡ ግቦችን፣ ማስተር ፕላንና የከተማ ሥራ አመራርን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ግቦቹ የማይመጥኑ፣ ከከተማው ታሪክ፣ ሥነ ልቦና ከተማው በአገሪቱ ዕድገት ላይ የሚጫወተው ሚና፣ ከእነዚህ ሁሉ ተነስቶ ማኅበራዊ ጥናቶች፣ የኢኮኖሚ ጥናቶች፣ የአካባቢ ጥበቃ ጥናቶች፣ የሥነ ሕዝብ ጥናቶችን ጨምሮ በርካታ የተወሳሰቡ ጥናቶች ይካሄዳሉ፡፡ እነኚህ ሁሉ ታክለው ነው ማስተር ፕላኑ ራዕይና ግቡ የሚቀመጥለት፡፡ ስለዚህ ከተማ ማስተዳደር ማለት ትልቁ ጉዳይ፣ ይህ ሁሉ ሐሳብ ያለበትን ማስተር ፕላን ተረድቶ በዚህ መሠረት ከተማውን መምራት ነው፡፡ ስለዚህ አንተም እንደጠቀስከው በተለያዩ መድረኮች ላይ እንደምንለው አመራሩ ማስተር ፕላኑን በአግባቡን መረዳት አለበት፡፡ እንደ ትልቅ የከተማ መሣርያ አድርጎ ማየት አለበት፡፡ ስለዚህ የአመራሩን ብቃት የምናየው ከማስተር ፕላኑ ጋር አያይዘን ነው ማለት ነው፡፡ ከተማውንም በአግባቡ መረዳት አለበት ስንል ይህን ማለታችን ነው፡፡ ማስተር ፕላኑ የሚዘጋጀው በመጀመርያ ከተማውን በአግባቡ ከመረዳት ነው፡፡ በአመዛኙ ደግሞ መነሻ የሚያደርገው ለአብነት አሥረኛው ማስተር ፕላን ዘጠነኛውን ማስተር ፕላን ይዞ ይነሳል፡፡ በዘጠነኛው ማስተር ፕላን የስምንተኛው ማስተር ፕላን ተፅዕኖ አለ እንደማለት ነው፡፡ አሥረኛው የዘጠነኛውን ማስተር ፕላን ጉድለትና ሐሳቦች አገናዝቧል፡፡ ምርምርና ትንተና አድርጎ ይነሳል ስንል በፊት የነበሩ ሐሳቦች ተካተውበታል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከመሠረቱ ከተማይቱ እንዴት ነበረች? እንዴት መጣች? ከማስተር ፕላኑ አንፃር ደግሞ በቀጣይ መያዝ የሚገባቸው ምንድናቸው? በቀጣይነት ከተማይቱ የራሷን መለያ እየገነባች ነው ወይ? እነዚህ ነገሮች ሁሉ መታወቅ አለባቸው፡፡ ስለዚህ ነው አመራሩ ከተማይቱንና ማስተር ፕላኑን በወጉ መረዳት ይኖርበታል የምንለው፡፡

ሪፖርተር፡- በ1996 ዓ.ም. ተግባራዊ መደረግ ጀምሮ በ2006 ዓ.ም. የመጠቀሚያ ጊዜው ያበቃው ዘጠነኛው ማስተር ፕላን በኤግዚቢሽን ማዕከልና በተለያዩ ቦታዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ነበር፡፡ በዚህ ማስተር ፕላን የተካተቱት ዕቅዶች የከተማውን ነዋሪዎች ያማለሉ ነበሩ፡፡ ለአብነት 16 አዳዲስ ፓርኮችና በርካታ የገበያ ማዕከላት ግንባታ ታቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህና ሌሎችም ዕቅዶች ሳይተገበሩ ቀርተዋል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ለምሳሌ ጀሞ አካባቢ የኢንዱስትሪ ዞን ተብሎ ታቅዶ፣ በኋላ የቤቶች ልማት ተካሂዶበታል፡፡ ከእነዚህ ቁም ነገሮች አንፃር ዘጠነኛው ማስተር ፕላን በትክክል ተተግብሯል ማለት ይቻላል? ከዚህ በተጨማሪም ማስተር ፕላኑ ወደ ተግባር በመጣበት ወቅት ትልቅ የመዋቅር ለውጥ ተደርጎ አብዛኞቹ የከተማው አስተዳደር ሠራተኞች ከደረጃቸው ዝቅና ከፍ ተደርገዋል፡፡ አሥረኛው ይህን ዓይነት ክስተት ያስተናግዳል ወይ? ማስተር ፕላን ሲመጣ የመዋቅር ለውጥ ለምን ያስከትላል?

አቶ ማቴዎስ፡- እንዳልከው ዘጠነኛው ማስተር ፕላን ይዞ የተነሳቸውና ያስቀመጣቸው ጉልህ ጉልህ ሐሳቦች ምን ያህሉ ተተግብረዋል? ስንል አንተ የጠቀስከው በኤግዚቢሽን ማዕከል ለ15 ቀናት ሕዝባዊ ኤግዚቢሽን አድርገን ነበር፡፡ በማዘጋጃ ቤትም እንዲሁ ከአዳራሽ ውጪ ድንኳን ተክለን ከ150 በላይ ዓውደ ጥናቶች አካሂደናል፡፡ ያኔ ባካሄድናቸው ሒደቶች ማስተር ፕላኑ ላይ አመጣን ከምንለው ለውጥ አንዱ እሱ ነው፡፡ ማስተር ፕላኑ የሕዝብ ነውና ምንም እንኳ ባለሙያው በማስተር ፕላን ዝግጅት ትልቅ ድርሻ አለው ብንልም፣ አመራሩም ትልቅ ሚና አለው ብንልም፣ ሕዝብ በተለይ ደግሞ ነዋሪው የማስተር ፕላኑ ባለቤት ነው፡፡ በወቅቱ ማስተር ፕላኑ በወረቀት ብቻ ሳይሆን በሞዴል ደረጃም ተዘጋጅቶ የነበረ በመሆኑ ሕዝቡ ማስተር ፕላኑ ምን ይመስላል? የሚለውን ጭምር የተረዳበት ነበር፡፡ የመጀመርያው ለሕዝብ የቀረበ ማስተር ፕላን ልንለው እንችላለን፡፡ ታዲያ ወደ ተግባር ስንሄድ ምን ሆነ ሲባል ሁለቱንም ወገን እናያለን፡፡ ተተግብሯል ወይ? አዎ! አልተተገበረም ወይ? አዎ! ይህን ለይተን ማየት ያስፈልገናል፡፡ ይህን ለይተን ስናይ፣ ማስተር ፕላኑ በራዕይ ያስቀመጣቸው በርካታ ሐሳቦች ወደ ተግባር ተተግብረዋል፡፡ ለአብነት የመንገድና የመንገድ ትራንስፖርትን በተመለከተ ባለፉት 15 ዓመታት በከተማው የተከናወኑት በርካታ የመንገድ አውታር ግንባታዎች ማስተር ፕላኑን ተከትለው የመጡ ናቸው፡፡ መቶ በመቶ የሚባል ግን የለም፡፡ ከሞላ ጎደል ማስተር ፕላኑን የተከተሉ ናቸው፡፡ ከተማው ውስጥ ተካሄዱ የተባሉ የልማት እንቅስቃሴዎች አብዛኛዎቹ ማስተር ፕላኑ ባስቀመጣቸው ዕቅዶች፣ ዘጠነኛው ማስተር ፕላንን ተከትሎ የመጣው የአዲስ አበባ ከተማ የመዋቅር ለውጥና እርሱን ተከትሎ የመጡ የልማት እንቅስቃሴዎች ነበሩ፡፡ ስለዚህ ማስተር ፕላኑ ከነጉድለቱ በፊት ከነበሩት ስምንት ማስተር ፕላኖች እጅግ በገዘፈ ገጽታው ተተግብሯል፡፡ ምናልባት ማስተር ፕላኑ ካስቀመጣቸው ቁም ነገሮች ውስጥ 50 በመቶ ወይም 40 በመቶ  ሊሆን ይችላል የተተገበረው፡፡ በአብዛኛው አልተተገበረ ይሆናል፡፡

ነገር ግን ከነበረን የከተማ ሥራ አመራር፣ እንዲሁም ማስተር ፕላንን ከመተግበር አኳያ ዘጠነኛው ማስተር ፕላን በአገራችን ታሪክ፣ ማስተር ፕላን ተተግብሯል ብለን ልንናገር በምንችልበት ደረጃ አጽንኦት ሰጥተን ተተግብሯል ብለን ልንናገር እንችላለን፡፡ በተጨማሪም የአዲስ አበባ አስተዳደር መዋቅራዊ ለውጥ ሊያደርግ ይገባል፣ የከተማው ቻርተር ሊሻሻል ይገባል የሚሉት ሐሳቦች፣ የአመራርና አጠቃላይ መዋቅራዊ ለውጥ ሊደረግ ይገባል የሚሉት ሐሳቦች ከማስተር ፕላኑ የመነጩ ናቸው፡፡ ከዚያ በኋላ የፌዴራል መንግሥትም ሐሳቡን ወስዶና በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መሪነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደገና የማደራጀትና የመለወጥ ሥራ ተካሄደ፡፡ እሱን ግብ አድርጎ ማስተር ፕላኑ በነበረው የቀድሞ የከተማው አመራርና አወቃቀር ይኼን ማስተር ፕላን መተግበር የሚያስችል ሁኔታ የለም፡፡ ስለዚህ ይህን ማስተር ፕላን ለመተግበርና ከተማውን መለወጥ ካስፈለገ አመራሩንና መዋቅሩን መለወጥ አለበት የሚል እሳቤ ስለነበር፣ ቅድም እንደጠቀስከው ለውጡ ተደርጓል፡፡ ሌላው ትልቁ ለውጥ ማስተር ፕላኑ ተተግብሯል የምንለው፣ ከዘጠነኛው ማስተር ፕላን በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ማዕከላዊ መዘጋጃ ቤት ብቻ ነበር የሚተዳደረው፡፡ ሁሉም አገልግሎቶች አራዳ ጊዮርጊስ ባለው መዘጋጃ ቤት ብቻ የሚሰጡ ነበሩ፡፡ የመሬት ጉዳይ፣ የግንባታ ፈቃድና የልደት ሰርተፍኬት ሁሉም ጉዳዮች የሚፈጸሙት እዚያው ነው፡፡ ዘጠነኛው ማስተር ፕላን ይህን ለውጦታል፡፡ ከተማው እያደገ ነው፡፡ የሕዝብ ቁጥሩ እያደገ ነው፡፡ (በወቅቱ ሁለት ሚሊዮን) የሕዝብ ፍላጎት እየጨመረ ነው፡፡

ስለዚህ በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ስለማይቻል ያልተማከለ የአስተዳደር ሥርዓት በሚለው የመንግሥት ፖሊሲ በመመራት፣ አዲስ አበባ በአሥር ክፍላተ ከተሞች እንደትከፋፈል ተደርጓል፡፡ አሥሩ ክፍላተ ከተሞች ማለት አሥር ማዘጋጃ ቤቶች ማለት ነው፡፡ በክፍለ ከተማ የሚሰጡ አገልግሎቶች እንዲወርዱ፣ ከዚያም አልፎ 305 ቀበሌዎችን በማሰባሰብና ወደ ወረዳ በማሳደግ በ116 ወረዳዎች ተቋቁመዋል፡፡ ወረዳዎቹ አቅም ኖሯቸው የተለመደው ዓይነት አስተዳደር ብቻ ሳይሆን የአገልግሎት ማዕከላት እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ይኼንን እንግዲህ ባለፉት 15 ዓመታት የተካሄዱትን የልማት እንቅስቃሴዎችን ስንመለከት ይህን አደረጃጀት ሳናመጣ ሊካሄዱ የሚችሉ አልነበሩም፡፡ ታንቀው የሚቀሩ ነበሩ፡፡ ሌሎችንም ጉዳዮች ስንመለከት፣ ለአብነት የመኖሪያ ቤቶችን ስንመለከት ከዘጠነኛው ማስተር ፕላን በፊት የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እንዲሟላ የሚታሰበው ለሁሉም አንድ ግቢ፣ ቦታ ሸንሽኖ የመስጠት ሐሳብ ነበር፡፡ ኮንዶሚኒየም ቤት የተፀነሰው የዚያን ጊዜ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ዘጠነኛው ማስተር ፕላን መተግበር ሲጀምር ከተማው ቢያንስ 30 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ የነበረው ግንባታ ተስፋፍቶ ያለውን መሬት በሙሉ (54 ሺሕ ሔክታር) ተጠቅሟል፡፡ ምናልባት የቤቶቹ ልማት የታሰበው በመሀል ከተማ ቢሆንም፣ ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ ጋር ተያይዞ በተነሳው አለመረጋጋት የተሰየመው የባላደራው አስተዳደር ነዋሪዎችን አንስቶ ግንባታ ለማካሄድ አቅም ስላልነበረው፣ በአርሶ አደሮች የተያዘውን የከተማው ዳርቻ ቦታዎች ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡ ባላደራው አስተዳደር ከመሀል ከተማ ነዋሪዎች ይልቅ አርሶ አደሮችን ማንሳት ቀሎት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ከተማው ያለውን የመሬት ሀብት ተጠቅሞ ጨርሷል፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ጎን መስፋት አይቻልም፡፡ ግን ደግሞ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች በአግባቡ አልተካሱም፡፡ ይህ የዘጠነኛው ማስተር ፕላን ውጤት አይደለም? የተጣበበ ከተማስ እየተፈጠረ አይደለም? ሌሎች አነስተኛ ከተሞችን መፍጠር አስፈላጊ አልነበረም?

አቶ ማቴዎስ፡- እንዳልከው ከዘጠነኛው ማስተር ፕላን በኋላ ኢንቨስትመንቱ በሰፊው  ተቀላቀለ፡፡ በብዛት ልማቱ ላይ የማተኮርና በአተገባበሩ ላይ የተፈጠሩ መዛነፎች በርካታ ናቸው፡፡ ነገር ግን በመርህ ደረጃ ስናስቀምጥ ልማት ሕዝብ ተኮር ነው፡፡ ልማት የሕዝብ ነው፡፡ የአገሪቱ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች በሙሉ የሚሉት ይህንኑ ነው፡፡ ልማት የሚካሄደው የነዋሪውን ሕዝብ የኑሮ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ነው፡፡ ይኼን ብለን ወደ አፈጻጸም ስንሄድ የሚንጠባጠቡ ችግሮች ይከሰታሉ፡፡ እነኝህ ከምን ይመጣሉ? መነሻቸው ከማስተር ፕላኑ ነው? ወይስ ማስተር ፕላኑን ከሚመራው አካል ነው? የሚሉት ጉዳዮችን ስናስቀመጥ ጉዳዮቹ ብዙ ናቸው፡፡ አንደኛ ፕላኑ ያስቀመጣቸውን ሐሳቦች በትክልል ካለመረዳት የሚመጣ ነው፡፡ ሁለተኛ የአፈጻጸም ተቋማዊ ብቃት አነስተኛ ነው፡፡ በአፈጻጸም በኩል ያለው የሰው ኃይላችን እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ የተቋሞቻችንን በየጊዜው መቀያየር፣ ተቋማት ዛሬ ተተክለው ዛሬ የሚያድጉ አይደሉም፡፡ ተቋማት እንደ ሰው ልጅ ዕድገት ነው የሚያድጉት፡፡ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል፡፡ አንድ ተቋም አልሠራ ሲል እሱን አፍርሶ ሌላ ማቋቋም አለ፡፡ እንዲህ ዓይነት አሠራሮች ላይ ስናተኩር ነበር፡፡ እነዚህ ችግሮች ለምንድነው የሚመጡት? በአጠቃላይ በከተማ ልማት ዕድገት ላይ በአገር ደረጃ ስንመለከት በአመራሩም በባለሙያም ያለን ልምድ አነስተኛ ነው፡፡ ይህ ነው ጉድለቱ፡፡ በከተማ ልማት ላይ ያለን ጉድለት ከፍተኛ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ገጠሬዎች ነን፡፡ በአመዛኙ እሱ ነው የሚገልጸን፡፡ ሁላችንም ገጠሬዎች ነን ብንል እኛን ይገልጸናል፡፡ ስለዚህ ወደ ከተሜነት በምናደርገው ሽግግር ባለሙያውንም፣ ነዋሪውንም፣ አመራሩንም በአብዛኛው የሥነ ልቦና ዝግጅታችን የሚገልጸው ገጠሬነትን ነው፡፡ አሁን ነው በቅርብ የከተሜ ነዋሪ 20 በመቶ፣ የገጠር ነዋሪ ደግሞ 80 በመቶ ማለት የጀመርነው፡፡

ስለዚህ በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ውስጥ ነው ዘጠነኛው ማስተር ፕላን የተተገበረው፡፡ ከማኅበረሰብ፣ ከባለሙያው፣ ከአስተዳደሩና ከገነባቸው ተቋማት ሁሉ ስናይ ችግር አለ፡፡ ተቋሞቻችን ሁሉ ገና እንጭጮች ናቸው፡፡ ከተሞቻችንም አዳዲስ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ የ130 ዓመት ወጣት ናት፡፡ ስለዚህ ይኼንን ስንመለከት አዲስ አበባ የምትማርባቸው ሌሎች ከተሞች የሉም፡፡ ለመማር ስንፈልግ አውሮፓ፣ አሜሪካ ወይ የሩቅ ምሥራቅ ከተሞችን ነው የምንመለከተው፡፡ ወደ ተግባር ሲመጣ የአገር ውስጥ ባለሙያ የለም፡፡ አመራሩ በከተማ አመራር ልምድ ያለው አይደለም፡፡ ቅድም የጠቃቀስኳቸው ጉድለቶች ከዚህ አንፃር ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ ፕላን ሲተገበር ፕላኑን ለመፈጸም ምን ምን ያስከፍላል? ይኼን ለመፈጸም በምናደርገው እንቅስቃሴ ምን ላይ እንደርሳለን? የሚለው መታወቅ አለበት፡፡ ስለዚህ ያገኘነው ግብ ላይ ለመድረስ ይህን ሁሉ ዋጋ መክፈል ነበረብን ወይ? ስንል ከአቅማችን የመጣ እንጂ ፈልገን ያገኘነው ዋጋ አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህን በሒደት ማስተካከል አለብን፡፡ ከቦታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች አያያዝ ላይ ይኼ ከቀረፅናቸው ዝርዝር ስትራቴጂና ፕላኑን ለማስፈጸም ካዘጋጀናቸው ዝርዝር ፕላኖች፣ ፕላኑን ለማስፈጸም ካቋቋምናቸው ተቋማት ብቃት፣ አመራሮችና ባለሙያዎች ብቃት ላይ ነው የሚወድቀው፡፡ አጠቃላይ የማስተር ፕላኑ ግብና መርህ ላይ ችግር ወይም ግጭት አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ከስትራቴጂው አኳያ ትኩረት የሚያደርገው ሕዝብ ላይ ነው፡፡ በማስተር ፕላኑ ምክንያት የሚነካ የከተማው ነዋሪ ቢኖር እንኳ ወደ ተሻለ ኑሮ ይሄዳል፡፡ በእርግጥ የማይነካ የከተማው ነዋሪ የለም፡፡ ሁሉም ይነካል፡፡ በሚነካበት ወቅት ግን የሚመጣው ልማት ተጠቃሚ ያደርገዋል የሚለውን ነው የሚያስቀምጠው፡፡ እዚያ ውስጥ ግን ውጣ ውረዶች ይኖራሉ፡፡ ምክንያቱም የከተማ ልማት ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ነገር ግን ከተሞች ኮምፓክት (ከፍተኛ ጥግግት) በሆነ ቦታ ላይ ማደግ ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ከትራንስፖርትና  የበለጠ እሴት ከመፍጠር አኳያ ከተሞችን በከፍተኛ ጥግግት ማሳደግ አስፈላጊ ነው፡፡ አሁን ባለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ አንፃርም ቢሆን ከፍተኛ ጥግግት (ኮምፓክት ሲቲ) ፕላን አስፈላጊ ነው፡፡ ቦታም ቢኖር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አዲስ አበባን አሁን ባላት የቆዳ ስፋት ላይ መልሶ መጠቀም መቻል አስፈላጊ ነው፡፡ በእርግጥ የመሀል ከተማውን መልሶ ማልማት ብቃት ላይ አልነበርንም፡፡ አሁን ግን አቅም ተፈጥሯል፡፡ ተቋማትም እየፈጠሩ ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ጎን ሰፊ ቦታ ቢኖር እንኳ ወደዚያ መሄድ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ይህን በማድረጋችን ነው አረንጓዴ ቦታዎችን ያጣነው፡፡ ባለፉት 15 ዓታት የመሬት አጠቃቀማችን የተዛነፈው ለመኖሪያ የተባለውን ለኢንዱስትሪ፣ ለአረንጓዴ የተባለውን ለመኖሪያ የመጠቀም ችግሮች በዘጠነኛው ማስተር ፕላን ላይ ተፈጥረዋል፡፡ የማስተር ፕላኑ በጎ ውጤቶች እንዳሉ ሆኖ በርካታ ጉድለቶችም ተከስተው ነበር፡፡ ከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ በምናደርግበት ጊዜ ማድረግ የነበረብንን ጥንቃቄ ባለማድረጋችን ከፍተኛ ጉድለቶች ተፈጽመዋል፡፡ ከዚህ በፊት የታዩ ጉድለቶች በአሥረኛው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዳይደገሙ ይደረጋል፡፡

ሪፖርተር፡- አሥረኛው ማስተር ፕላን በሚታሰብበት ወቅት ሌሎችም አጎራባች ከተሞች አብረው እንዲያድጉ ታስቦ ነበር፡፡ ነገር ግን ውጥኑ ረዥም ርቀት ከሄደ በኋላ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በተነሳው ተቃውሞ እንዲቆም ተደርጓል፡፡ ውጥኑ መልካም ቢሆንም ሳይሆን ቀርቷል የሚሉ አሉ፡፡ እዚህ ላይ ሕዝቡ ምን ዓይነት መንገድ መያዝ ይኖርበታል ይላሉ?

አቶ ማቴዎስ፡- በአገር አቀፍ ደረጃ የምናቅደውም ሆነ በአዲስ አበባ ደረጃ የምናቅዳቸው  የተዛመዱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንግዲህ እንዳልከው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ማስተር ፕላኖች ሲያዘጋጁ፣ የአንዱ ከተማ ከሌላው ከተማ ጋር እንዳይጣረስ ለማድረግ ነው፡፡ ያንን ፕላን አስማምቶ የመሄድ ጉዳይ ነው፡፡ ይኼ እንግዲህ ትክክለኛውን መልክዕት ለሕዝቡ በአግባቡና በወቅቱ ባለመውረዱ፣ መንግሥትም እንዳስቀመጠው በኦሮሚያ ከተሞች ሲሠራ የነበረው እንዲቆም ተደረገ፡፡ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ለብቻው እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡

ሪፖርተር፡- አሥረኛው ማስተር ፕላን በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ማስተር ፕላን እንደ ዘጠነኛው ማስተር ፕላን ከፍተኛ መዋቅራዊ ለውጥ ይዞ መጥቷል፡፡ ማስተር ፕላን ሲመጣ ግዙፍ የመዋቅር ለውጥ አስከትሎ መምጣቱ የግድ ነው?

አቶ ማቴዎስ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመዋቅር ጥናት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አቋቁሟል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ መዋቅራዊ ለውጥ ማካሄድ የሚያስችል ጥናት እየሠራ ነው፡፡ ለውይይቱም እያቀረበ ይገኛል፡፡ ከዚህ የሚጠበቀው እስካሁን ድረስ በከተማችን በተለይ በማስተር ፕላኑ አፈጻጸም ላይ ከ1997 ዓ.ም. በኋላ ከመምጣቱ በፊት፣ የነበረው አደረጃጀት ማስተር ፕላኑን ለመተግበር ተአምር ሊሠራ የሚችል መዋቅር ነበር (በዶ/ር አርከበ ዕቁባይ የሚመሩት ካቢኔ)፡፡ ከ1977 ዓ.ም. በኋላ መፋለሶች በመከሰታቸው አዲስ አበባ ላይ መንገራገጭ ተፈጥሯል፡፡ ስለዚህ እነዚያን ክፍተቶችና ጉድለቶች፣ በፕላን ዝግጅትና በአፈጻጸሙ ላይ የታዩት የአደረጃጀትና የአሠራር ሥርዓቶች ምንድናቸው? የሚለውን ጉዳይ የመረዳትና ክፍተቶቹን መሙላት ያስፈልጋል፡፡ በአዲስ መልክ እየተደራጀ ያለውና የከተማው ምክር ቤት ያፀደቀው ፕላን ኮሚሽን እንደ ዓላማ በአደረጃጀትና በመዋቅር የነበረበትን ክፍተት ይሞላል፡፡ በዘጠነኛው ማስተር ፕላን ተግባሪ ተቋማት፣ ማስተር ፕላኑን በሚተገብሩበት ወቅት በትክክል ስለመተግበራቸው የሚከታተልና የሚቆጣጠር ተቋም አልነበረም፡፡ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ፕላን ኮሚሽን ተቋቁሟል፡፡

ሁለተኛው በፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የተጠኑት ከፕላን ኮሚሽን ሌላ ሦስት ተቋማት እንዲቋቋሙ ይደረጋል፡፡ አንደኛው የማዕከላትና የኮሪደሮች ልማት ኮርፖሬሽን ነው፡፡ ሁለተኛው የልማት ቅንጅትና የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ነው፡፡ ሦስተኛው የተፋሰስና አረንጓዴ ቦታዎች ኤጀንሲ ነው፡፡ በድምሩ እነዚህ አራት ተቋማት ከዘጠነኛው ማስተር ፕላን በተማርነው መሠረት አሥረኛውን ማስተር ፕላን በትክክል ዕውን ለማድረግ ቁልፍ ሚና አላቸው ተብለው የተለዩ ናቸው፡፡ ፕላኑ ባለቤት እንዲኖረው ፕላኑን የሚጠብቅና የሚቆጣጠር ተቋም ተፈጥሯል፡፡ ይህን አሳክተናል፡፡ ሌላው የማዕከላትና የኮሪደሮች ልማት ነው፡፡ ዘጠነኛውን ማስተር ፕላን በምንገመግምበት ወቅት ያየነው አንዱ ትልቁ ጉድለት ማዕከላትና ኮሪደሮች፣ በተለይም ማዕከላት አካባቢ በተመቀጠው ፕላን መሠረት ማስተር ፕላኑን ተከትለው እየተፈጸሙ አይደለም፡፡ ማዕከላት ስንል እንግዲህ የከተማው ዋና እምብርት በመሆናቸው በልዩ ሁኔታ ተጠንቶ መተግበር ያለበት ነው፡፡ እንደ ሌላው የከተማው አካባቢ የሚለማ አይደለም፡፡ በየደረጃው ወደ ክፍለ ከተማም ስንሄድ የክፍለ ከተማ ማዕከላትም የወረዳ ማዕከላትም በልዩ ሁኔታ ነው መልማት ያለባቸው፡፡ በዘፈቀደና በተበጣጠሰ ሁኔታ መልማት የለባቸውም፡፡ ማዕከላት የምንለው የከተማው ሕይወት የሚንቀሳቀስባቸው ዋና ቦታዎች ናቸው፡፡ የአገልግሎት ቦታዎች፣ የአስተዳደር ቦታዎች፣ የመዝናኛ ማዕከላት ናቸው፡፡ እነዚህ ቦታዎች በልዩ ሁኔታ መልማት አለባቸው፡፡ ግን በዘጠነኛው ማስተር ፕላን አልተፈጸመም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቦታዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ መንግሥታዊ የሆነ ተቋም ማቋቋም አስፈልጓል፡፡ የማዕከላትና የኮሪደሮች ልማት ኮርፖሬሽን እንዲቋቋም ሐሳብ አቅርበን ለማፀደቅ በሒደት ላይ እንገኛለን፡፡ ሌላው ከተማችን ውስጥ ደግመን የምናነሳው ከታችኛው ተራ ዜጋ አንስቶ ከፍተኛ አመራር ድረስ ደጋግመን የምናነሳው የመሠረተ ልማትና የልማት ቅንጅት አለመኖር ነው፡፡ በዘጠነኛው ማስተር ፕላን በዶ/ር አርከበ ዕቁባይ የሚመራው የከተማው ካቢኔ በተቋቋመበት ወቅት ይህን ችግር ለመፍታት ጥረት ተደርጎ ነበር፡፡ የመሠረተ ልማትና ግንባታ ሥራዎች ባለሥልጣን ተቋቁሞ ነበር፡፡ ባለሥልጣኑ ልማቶቹን እያቀናጀ ይመራ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የ1997 ዓ.ም. ውጥንቅጥ ከመጣ በኋላ ያ ተቋም መልኩን ቀይሮ ይህን አገልግሎት ሳይሰጥ ቀረ፡፡ ስለዚህ ትልልቅ ልማቶችን የተቋሞቹን ዕቅድ አንግበው እንዲሠሩ የሚያደርግ፣ የከተማውን የግንባታ ሒደት የሚቆጣጠርና ፈቃድ የሚሰጥ የመጠቀሚያ ፈቃድ የሚሰጥ የልማት ቅንጅት የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዲቋቋም እየተደረገ ነው፡፡

ሌላው ከተማው ውስጥ ሁሉም ነዋሪ እሮሮ የሚያሰማበት የአረንጓዴ ቦታዎች ጉዳይ ነው፡፡ አረንጓዴ ቦታዎችን ቅርጥፍ አድርገን በልተን በሐሩር እየነደድን ነው፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት ከተማ ውስጥ በተደረገ ልማት ያጠፋናቸው አረንጓዴ ቦታዎች አሁን ዋጋ እያስከፈሉን ነው ያሉት፡፡ በ30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የአዲስ አበባ አማካይ የሙቀት መጠን በአንድ ዲግሪ ሴልሺየስ ጨምሯል፡፡ ስለዚህ ይኼ በዚሁ ከቀጠለ ከተማችን ወደ በረሃማነት እየተለወጠ ይሄዳል፡፡ እዚህ ላይ ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል በማለት የተፋሰስና የአረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ እንዲቋቋም እያደረግን ነው፡፡ እንግዲህ እነዚህ አዳዲስና የመዋቅር ጥናት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ በርካታ ተቋማት ማስተር ፕላኑን በትክልል ማስፈጸም እንዲችሉ፣ እርስ በርሳቸው መገናኘት ባለባቸው ደረጃ በተለይ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትና የመንግሥት ሥራዎች በሚባሉት መካከል የመቀላቀልና የመዘበራረቅ ሁኔታ ስለሚታይ ለይቶ ያስቀምጣል፡፡ የልማት እንቅስቃሴ ያላቸውን ወደ ማዘጋጃ ቤት ሥር በመካለል በባለሙያ እንዲመሩ የማድረግ፣ የፖለቲካ አመራሩ ደግሞ ይበልጥ ስትራቴጂክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር የሚያደርጉ ሥራዎችን እየሠራ ነው ያለው፡፡ ይህ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል፡፡

 

ዜና- ሪፖርተር


ቫላንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን) ከባሕል ማንነታችን ጋር ምን ያህል ይቃረናል? – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

አበባን በስጦታ ማበርከት ከእኛ የተወሰደ ባሕል መሆኑን ያውቃሉ?


ቫላንታይንስ ዴይ (ፍቅረኞች ቀን) ምዕራባውያኑ ንግድን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅና የባሕል ወረራ ለመፈጸም እኛላይ ከጫኗቸው በዓላት አንዱ ነው፡፡ ይህ በዓል በእኛ ዘንድ አሁን ያገኘውን ያህል ተቀባይነት እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያ የብዙኃን መገናኛዎች በተለይም የኤፍ ኤም ሬዲዮዎች (ድ. ክ. ነጋሪተ ወጎች) ከፍተኛውን ተጽዕኖ አሳድረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የብሔራዊው የብዙኃን መገናኛውና ሌሎች የአጭር ሞገድ ነጋሪተ ወግ (ሾርት ዌቭ ራዲዮ) ጣቢያዎችም እንደዚያው ቁምነገሬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ የብዙኃን መገናኛዎች በተለይም የኤሌክትሮኒክሱ (የነርኃላዊው) በመልካም ጎንም ይሁን በመጥፎ ጎን ለሚመጣ ውጤት ታላቅ ጉልበት አላቸው፡፡ ከዚህ አንጻር ባጠቃላይ ለደረሰብን የባሕል ወረራና ጥቃት በዚህ የብዙኃን መገናኛ ከበጣም ጥቂቶቹ በስተቀር “የመዝናኛ ዝግጅት” በሚል ሥያሜ የአየር ሰዓት ወስደው የሚሠሩ እንደዜጋ የሀገርንና የሕዝብን እሴት ሀብት የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለባቸውና እንዴትም እንደሚጠበቅ ምንም የማያውቁ ወይም መጠበቅ የማይፈልጉ፣ ከመናኛ የግል ጥቅማቸው ባለፈ ይሄንን ከባድ ኃላፊነት ለመረዳት የአቅም ውስንነት የገደባቸው አዘጋጆች ይሄንን ዕድል ለነሱ ከሰጧቸው አካላት ቀጥሎ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ግለሰቦች ጀርባም ደግሞ ጨርሶ ኃላፊነት የማይሰማቸው የተለያዩ ስግብግብ የንግድ ወይም የአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች አሉ፡፡

ቫላንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን) ከባሕላችን አንጻር እንዴት ይታያል?

ቫላንታይንስ ዴይ ይጠቅማል? አይጠቅምም? ወደ ሚለው ከመሔዴ በፊት ይሔንን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ ባሕላችን፤ በነገራችን ላይ “ባሕላችን” ብየ ስል ንጥሩን (ኦሪጂናሉን) ማለቴ እንጅ ለምሳሌ አሁን አዲስ አበቤ ነን የምንለው እየኖርነው ያለውን በዘመናዊነት ሽፋን በባዕዳን ባሕል የተበከለውን ወጥነት ያጣውን ባሕል ማለቴ አይደለም፡፡ ከዚህ አንጻር ስናየው ሲጀመር ባሕላችን ፍቅረኝነትን ማለትም ከጋብቻ ውጪ ወይም በፊት የሚደረግን ወሲብን የሚጨምር ፆታዊ ወዳጅነትን የሚያውቅና የሚፈቅድ አይደለም፡፡ በእኛ ባሕል የፍቅር ሕይዎትና ወሲብ የሚኮመኮመው በትዳር ውስጥ ነው፡፡ በእርግጥ ባሕላችን እጮኝነትን ያውቃል፡፡ ይሁን እንጂ የእጮኝነት ወቅት እሷ የሱ እሱ የእሷ መሆናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ “የፍቅር ሕይዎት!” ሊባል በሚችል ደረጃ ፍቅር የሚኮመኮምበት አይደለም፡፡ በመታቀብ ውስጥ ሆነው አንድ የሚሆኑበትን ቀን የሚጠብቁበት ወቅት እንጂ፡፡

ይህ ቁጥብነት የተሞላበት ክቡር ባሕላችን ምን ያህል ክብርን፣ አካላዊና ሥነ-ልቡናዊ ንጽሕናን የጠበቀ እንደሆነ ከጋብቻ በፊት በሚደረጉ ፆታዊ ግንኙነቶች ከሚፈጠሩ ሕይዎትን እስከወዲያኛው ከሚያበላሹ ውስብስብና አደገኛ ችግሮች የጸዳ እንደሆነ መረዳት የሚሳነው ሰው ይኖራል ብየ መገመት እቸገራለሁ፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ ከባሕላችን ጋር ተቃርኖና ተጻርሮ ያለውን ግላዊና ማኅበራዊ ሕይዎታችንን አደጋ ላይ የሚጥልን ምዕራባዊ ባሕል ለማዋሐድ መሞከር ምን ያህል የተሳሳተ ብቻ አይደለም ኃላፊነትና ማስተዋል የጎደለው እንደሆነ ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ይህንን የምዕራባዊያን ድርጊት ወይም ባሕል መዋሱ ትክክል ይሆን የነበረው ከላይ የገለጽኩት ባሕላችን የተገለጸውን ዓይነት መሆኑ ከሞራል (ከቅስም)፣ ከሥነ-ምግባር፣ ከላቀ ሰብእና እነፃ፣ ከሃይማኖታዊ አስተምህሮዎች ወዘተ. አንጻር ችግር ያለበትና ነውረኛ ቢሆን ነበር፡፡ እንደምናየው ግን ያለው እውነታ የሚያሳየው ይህንን አይደለም፡፡ ከጋብቻ ውጪ ፆታዊ መወዳጀትን (ፆታዊ መወዳጀት የምለው ፍቅር ላለማለት ነው ፍቅር ማለት የትም ከማንም ጋር የሚፈጸም ወሲብ ማለት አይደለምና) መቀበላችን የሰውን ክቡርነት፣ የሕይዎትን ዋጋ ውድነትና ልዕልና ተቀብሎ ከተቀረጸው የጸዳና ኃላፊነት የተሞላበት ወይም የሚሰማው ባሕላችንን መተዋችን፣ የዚህን ተቃራኒ ውጤት ወደሚያመጣ መሔዳችን መውረዳችንን፣ መዝቀጣችንን፣ በማንነት ቀውስ ውስጥ መሆናችንን እንጂ ከፍ ማለታችንን፣ መላቃችንን የሚያሳይ አይደለም፡፡
በመሆኑም ያለንን የነበረንን ባሕል ልንንቅ፣ ልንለቅና ልንለውጥ የምንችልበት አንድም አመክንዮ የለም ማለት ነው፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ ይሄንን የባዕድ ባሕል ወደ ባሕላችን ስንቀላቅል እጅግ መሳሳትና መውረድ መሆኑ እርግጥ ነው ማለት ነው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን በአመክንዮ ያልደገፍነው ወይም ልንደግፈው ያቃተንን አስተሳሰብ ሥራ ላይ ስናውል ችግር ማጋጠሙ ዋጋ ማስከፈሉ የማይቀር ይሆናል፡፡ ምናልባት ይህ የጸዳው ባሕላችን የኑሮ ዘይቤ ጊዜ ያለፈበትና በዚህ ዘመን የሚኖረው ወይም የሚተገብረው የሌለ ተደርጎ ይታሰብ ይሆናል የሚል ሥጋት አለኝ፡፡ ነገር ግን ፍጹም የተሳሰተና ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ እንደሆነ አበክሬ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያ ሕዝብ 85% በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖርና ይህ የእኛ ባሕል ነው ብየ የገለጽኩትን የኑሮ ዘይቤ የሚኖር የሚከተል ነው፡፡ በባሕል መበረዝ እየተበከለ ያለው ሕዝብ በተቀረው 15% ከተማ ነዋሪ ያለው ሕዝብ ነው፡፡ ያም ቢሆን ሁሉም የከተማ ነዋሪ ለባሕል መበረዝ እጁን የሰጠ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ በመሆኑም አሳቢ ከተገኘ ስለዚህ ባሕላዊ እሴታችን መጠበቅ መከበር ማንሰራራት ለማውራት መምሸት አይደለም ገናም አልረፈደም፡፡ አይበለውና ሁላችንም ከዚህ ባሕላችን ውጭ ብንሆንም እንኳ ይህ ባሕላችን ቅርሳችን ማንነታችን ነውና ባንኖረውም ጠብቀን ልናቆየው፣ ለትውልድም ልናወርሰው እንጅ በይፋ በመጤ ባሕል እኛው እራሳችን ጨፍልቀን ልናጠፋው አይገባም፡፡

አንድ ጊዜ ምን ገጠመኝ መሰላቹህ ከፌስ ቡክ (ከመጽሐፈ-ገጽ) ጓደኞቸ አንዱ አንድ ፎቶ (ምስለ አካል) ለጥፎ ዐየሁ፡፡ በምስለ አካሉ ላይ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ የባሕል ልብስ የለበሱ ወንድና ሴት ሆነው ወንድየው ከሴቷ ፊት ተንበርክኮ የጋብቻ ቀለበቱን እያሳያት እሷ በድንገቱ በመገረም አፏን በእጇ ጭና ያሳያል፡፡ በዚህ ምስለ አካል በርካታ የመጽሐፈ ገጽ ተጠቃሚዎች ደስ በመሰኘት ምስለ አካሉን ተጋርተው በየራሳቸው መጽሐፈ ገጽ ለጥፈውት ነበር፡፡ እኔ ግን ነገሩ አልተመቸኝም ነበርና ከስሩ ይሄንን አስተያየት አሰፈርኩ፡፡

ወንድሜና እኅቴ በቅድሚያ ለዚህ ስላበቃቹህ እንኳን ደስ አላቹህ! ስቀጥል የተሰማኝን እንድገልጽ ከፈቀዳቹህልኝ እኔ በዚህ ምስለ አካል ላይ አልተደሰትኩም፡፡ ምናልባት የባሕል ልብስ ባታደርጉና ቦታውም ሌላ ቦታ ቢሆን ትንሽም ቢሆን መከፋቴን በቀነሰልኝ ነበር፡፡ ነገር ግን የባሕል ልብሳችንን ግጥም አድርጋቹህ እንዲህ አምሮባቹህ በዚህ በተቀደሰውና የኢትዮጵያዊነትን ልዕልና በሚመሰክረው ቦታ ላይ ከምዕራቡ ዓለም የተወሰደን ድርጊት መፈጸማቹህ ምን ያህል እንዳመመኝ ለመግለጽ እቸገራለሁ፡፡ እንደምታውቁት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶችን ሁሉ በመቅረጽ በመጠበቅና በመንከባከብ ትታወቃለች፡፡ ይሄንን ተግባር ስትፈጽምም ሌላ ፈጻሚ አካል ኖሮ ሳይሆን እኛው ልጆቿ እናት አባቶቻችንን ፊት አውራሪ አድርገን ነበር ይሄንን ከባድ ኃላፊነት ስንወጣ የኖርነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ ታዲያ እንዳለፉት ትውልዶች ሁሉ ማንነቱን ይጠብቅ ዘንድ ይልቁንም አሁን ካለብን በሉላዊነት (Globalization) ከተሸፈነ ጫናና የባሕል ወረራ አንጻር ካለፉትም ትውልዶች በተሻለ ብቃትና ጥንካሬ ማንነቱን ለመጠበቅ ከባድ የታሪክ ኃላፊነት ከተጣለበት ከዚህ ትውልድ አካል የሆናችሁት ከባሕላችን ውጭና ባዕድ የሆነን ድርጊት የኢትዮጵያዊነትን ልዕልናና ድል በሚመሰክረው ሥፍራ ላይ ስታደርጉት ሳይ በጦርነት ድል ተደርገን በግዛታችን ላይ የጠላት ሰንደቅ ቢውለበለብ ሊሰማቹህ የሚችለውን ዓይነት የሚተናነቅ ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡

በእኛ ባሕል እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት ፈጽሞ ቦታ የለውም፡፡ ሲጀመርም አንተ እሷን እሷም አንተን ስትቀራረቡ በምን ዓይነት አቀራረብ ለምን ዓይነት ጉዳይ እንደሆነ ማለትም ለትዳር መሆኑን ተማምናቹህ አስቀድሞ የጨረሳቹህት ወይም የቅርርባቹህ መጨረሻ ይሄ እንደሚሆን የሚጠበቅ የሚታሰብ በመሆኑ ይህ ድርጊትህ ከባሕላችን አንጻር በጣም የራቀና የተሳሳተ ነው፡፡

ወደ ምዕራቡ ዓለም ዜጎች ስትሔድ ግን አንድ ወንድና ሴት በፍቅር መጎዳኘት ሲያስቡ ሦስት አማራጮች ክፍት በሆኑበት ሁኔታ ነው፡፡ ምን ማለቴ መሰለህ ትዳር የሚለው ነገር ከፊት ለፊት ያለ አማራጭ ሳይሆን መጨረሻ ደረጃ ላይ ወይም በርቀት ያለ አማራጭ ነው፡፡ በየደረጃው አንደኛውን አማራጭ እየኖሩ ግንኙነታችን ተመችቶናል! ተጣጥመናል! ወደሚቀጥለው ደረጃ ይደግ እያሉ ነው መጨረሻ ላይ ትዳር ላይ የሚደርሱት፡፡ ትዳር ብለው የሚሉትም የእኛ ባሕል ለትዳር እንደሚሰጠው ትርጉምና ክብር ክብደት ዓይነት እንዳይመስልህ፡፡ በተመሠረተ በቀናት ልዩነት ሁሉ ሊፈርስ ይችላል፡፡ ትዳራቸው ጣጣውና ችግሩ ብዙ ነው ይሄን ለመዘርዘር ጊዜ የለኝም፡፡ ዋነኛው ችግሩ የሚመነጨው ግን አስቀድሞ በነበረው ግንኙነት ወቅት ፍቅራቸውን አጣጥመው ጨርሰው “ፍቅራቸው” አርጅቶ ስለሚገቡበት ትዳር ውስጥ አዲስ ነገር በማጣት በቀላሉና ወዲያው የመሰለቻቸት ችግር ከማጋጠሙ የተነሣ ነው ብየ አምናለሁ፡፡

ከእነዚህ ሦስት የፆታዊ ግኑኝነት አማራጮች የመጀመሪያው አማራጭ በመሀከላቸው ጥል ተፈጥሮ እስኪራራቁ ጊዜ ድረስ ወሲብን ጨምሮ “በፍቅር ውስጥ ልንፈጽማቸው ይገባናል!” የሚሏቸውን ነገሮች ሁሉ ላልተወሰነ ጊዜ እየፈጸሙ የሚኖሩበት አማራጭ ነው፡፡ ግንኙነቱ የፍቅር ጓደኝነት (love friend ship) ይባላል፡፡ በዚህ ሕይዎታቸው ደስተኞች ከሆኑ ልክ አሁን አንተ እንዳደረከው ወንድየው ተዘጋጅቶበት ይቆይና በድንገት የጋብቻ ቀለበቱን በማውጣት ግርምት ወይም ድንቀት (surprise) በመፍጠር ጥያቄውን ተንበርክኮ ያቀርባል፡፡ ሴቲቱ ያሳለፉት ሕይዎት ለሷም ከተመቻት ፈቃደኛነቷን በመግለጽ በእሽታ ትቀበለውና ለጋብቻ ይበቃሉ ማለት ነው፡፡ ከሁለቱ አማራጮች በኋላ ደግሞ አንድ ሌላ አማራጭ አላቸው እድሜአቸው የወጣትነትን ዘመን ሲሻገር ወይም ደግሞ ፍቺ የፈጸሙ የሚኖሩት ኑሮ ነው፡፡ እሱም ልክ ትዳር እንደመሠረቱ ጥንዶች ሁሉ ወንዱና ሴቷ ትዳር ሳይመሠርቱ እንደ ደባል ሆነው በአንድ ቤት የሚኖሩበት አማራጭ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሕይዎት ሲኖሩ ግንኙነቱን የወሲብ አጋርነት(sexual partner ship) ይሉታል ወንዱ ሴቷን አጋሬ ሲላት ሴቷም ወንዱን እንደዚያው በማለት ትጠራዋለች፡፡ ሲበቃቸውም የሚቀደድ ሰማኒያ ሳይኖር በቅተሽኛል! በቅተኸኛል! ተባብለው ወይም ሳይባባሉ እንደወጡ የሚቀሩበት የሚለያዩበት የግንኙነት ዓይነት ነው፡፡

ወንድሜ ታዲያ ከእነዚህ ደረጃዎች ጀርባ ከሃይማኖትና ከባሕል አንጻር የሚወገዙ ስንት አስተሳሰቦች አሉ መሰለህ! እንዱንና ዋነኛውን ብነግርህ “መጣጣምን ለማወቅ!” ሲባል እንደሆነ ያወራሉ፡፡ በዚህ ሒደት ውስጥ “በወሲብ የምትጥመኝን ወይም የሚጥመኝን አላገኘሁም!” በሚል ለቁጥር የሚያታክቱ ሰዎችን ለማወቅ ወደሚገደዱበት ሕይዎት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህ ድርጊት ደግሞ ለበሽታ፣ ለሥነልቡናዊና ተያያዥ ችግሮች እንደሚዳርጋቸው፣ ከሰውነት ወደ እንስሳነት እንደሚያወርዳቸው መታዘብ የምትችል ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ነው እነሱ ዘንድ ትዳር መቀለጃና ተገቢው ክብደትና ክብር የሌለው ሊሆን የቻለው፡፡
እንግዲህ ይህ አንተ ባለማወቅ ያደረከው ነገር ከጀርባው ይሄንን ሁሉ ጉዳቸውን የያዘ ስለሆነ ነው ያልተመቸኝ፡፡ ከጀርባው እንዲህ ያለ ርካሽና ነውረኛ፤ ከእኛ ባሕል፣ ወግና ሃይማኖት ጋር የሚቃረን፣ የሚወገዝ፣ የማይበረታታ የሕይዎት ጉድ ያለበት በመሆኑ ይህ ያደረከው ነገር ትክክል አይደለም፡፡ ምናልባት ግን ይህ ያደረከው ነገር ምንም እንኳ የምዕራባዊያኑ እንጂ የእኛ ባይሆንም ቅሉ በገለጽኩት ዓይነት የምዕራባዊያን ፆታዊ ግንኙነት ሕይዎት ሳታልፉ ማለትም ከጋብቻ በፊት በግብር ሳትተዋወቁ (ወሲብ ሳትፈጽሙ) ቆይታቹህ “በእግዚአብሔር ቤት እንዲህ ዓይነቱን ቃል ወይም የተቀደሰ ጥያቄ ባቀርብ ተገቢ ነው!” ብለህ አስበህ ጥያቄውን አቅርበህ ከሆነ ይቅርታህ ይድረሰኝ፡፡ ነገር ግን እሱም ቢሆን አሁንም በባሕላችን በሃይማኖታችንም ቀለበት የሚታሠረው በካህን ቡራኬ በመሆኑ ይህ የገለጽክበት መንገድ ትክክል አይደለም ማለት ነው፡፡ እናም ወንድሜ ግድ የለህም ይህ ምስለ አካል(ፎቶ) በተለይ ደግሞ በእግዚአብሔር ቤት የባሕል ልብሳችንን በለበሳቹህ ምእመናን መፈጸሙ ምን ያህል ለምዕራቡ ዓለም የባሕል ወረራ መንበርከካችንን፣ መሸነፋችንን፣ መማረካችንን፣ እጅ መስጠታችንን ነውና የሚያሳየው እባክህን አንሣውና ጥያቄህን በባሕላችን መሠረት ሽማግሌ በመላክ አቅርብ? ብየ አስተያየቴን አሠፈርኩ፡፡ እሱም እግዚአብሔር ይስጠውና ጥፋት መሆኑን ተረዳ መሰለኝ ያንን ምስለ አካል ወዲውኑ አነሣው፡፡

እንግዲህ ቫላንታይንስ ዴይ ተብሎ እየተከበረ ያለው የምዕራባዊያኑ በዓል በእንዲህ ዓይነት “የፍቅር” ገጽታና ቅኝት ስለሆነና እዚህም እየተከለ ያለው ተመሳሳዩን ገጽታና ቅኝት በመሆኑ ሃይማኖታዊ አስተምህሮን መሠረቱ ካደረገው ባሕላችን ጋር ፍጹም የማይስማማና የማይጠቅምም ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለነገሩ በምዕራቡም ዓለም ቢሆን ይህ በዓል ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት ያለው በዓል አይደለም፡፡ የዚህ በዓል ታሪካዊ ዳራ የካቶሊኮች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ፕሮቴስታንቶች አይቀበሉትም፡፡ እነዚህ ሁለቱ እምነቶች “በሃይማኖት” ልዩነት ምክንያት በተለያየ ጊዜ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አውሮፓ ጦርነት ወይም ግጭት እስከማድረግ የደረሱ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ አንደኛው ለሌላኛው እሴት አክብሮት የለውም፡፡ በመሆኑም ፕሮቴስታንት የሆኑ ሀገራት ቦታ የሚሰጡትና የሚያስቡት በዓል አይደለም፡፡ ጨርሶም የማያውቁት አሉ፡፡

የአበባ ስጦታና ባሕላችን ያላቸው ግንኙነትና ቁርኝት?

ከቫላንታይንስ ዴይ ጋራ ተያይዘው ከሚከወኑ ኩነቶች ውስጥ የስጦታ ልውውጥ በተለይም የአበባ ስጦታ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች እኛ ኢትዮጵያዊያን የአበባ ስጦታ የማበርከት ባሕል እንደሌለን አድርገው ያስባሉ፡፡ እውነታው ግን ከዚህ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ እንዲያውም ሲመስለኝ ሲመስለኝ ፈረንጆቹ አበባን የማበርከት ባሕል የወሰዱት ከእኛ ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ በባሕላችን ምድረ አውሮፓ ከነመፈጠሩ እንኳ በማይታወቅበት ዘመን ለተለያዩ ጉዳዮች አበባን የማበርከት ልማድ ወይም ባሕል ስንፈጽም እንደኖርን ታሪካችን ያስረዳናልና፡፡ በቤተክርስቲያናችን ማለትም በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አበባ እጅግ የከበረ ስጦታ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያዊ ባሕል ወይም እሴት ነው ተብሎ የሚታወቀውን ባሕልና እሴት በመቅረጽ በኩል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሚና ጎልቶ ይታያል፡፡ ያሉንን ኢትዮጵያዊ መገለጫ ያላቸውን ባሕላዊ በዓላትና ኩነቶችን መለስ ብለን ብናጤን ሃይማኖታዊ አሻራ የሌለበት አንድም እንኳን አታገኙም፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አበባ ለየት ያለ ሥፍራና አግልግሎት አለው፡፡ ለአብነት ያህል ሦስቱን እጠቅሳለሁ፡-

ቤተክርስቲያን ካሏት አጽዋማት ውስጥ ዋነኛ በሆነው በዐቢይ ፆም መጨረሻ በሕማማት ሳምንት የጌታችን፣ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በሚታሰብበት ቀን በመስቀሉ ስር ላይ ጽጌረጋ አበባ በመነስነስ ለክርስቶስ እንዲበረከት “ግብረ ሕማማት” የሚባለው መጽሐፍ በሚያዘው መሠረት በየዓመቱ የስቅለት ቀን ይህ ይፈጸማል፡፡
ሁለተኛው “ጽጌ” ፆምን የተመለከተው ነው፡፡ ጽጌ ፆም የጌታንና የተወዳጅ እናቱን ወደ ግብጽ መሰደድ ለማሰብ የሚፆም ፆም ነው፡፡ የዚህች ፆም ሥያሜ “ጽጌ” የሚለው ቃል ሲተረጎም አበባ ማለት ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ቅዱሳን አባቶቻችን በመጻሕፍቶቻቸው እመቤታችንን በአበባ ስለመሰሏት አንዱ ምክንያት ሲሆን ልላኛው ምክንያት ደግሞ ወቅቱ የአበባ ወቅት ስለሆነ በወቅቱ ሲጠራ ነው፡፡
ሦስተኛው ደግሞ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አንድ ዓመታዊ በዓል አለ መስከረም 10 ይውላል፡፡ ሥያሜው “ተቀጸል ጽጌ” (አበባን ተቀዳጅ) ይባላል፡፡ ቤተክርስቲያን ንጉሡን “እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰህ!” የምትልበት በዓል ነው፡፡ የጸሎቱና የቅዳሴው ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ካህናት በደመቀ የዝማሜ፣ የማስረገጥ፣ የወረብ፣ የሽብሻቦ፣ መዝሙር ታጅቦ ንጉሡንና ንግሥቲቷን እንኳን አደረሳቹህ በማለት አበባ የሚያበረክቱበት በዓል ነበር፡፡
በተጨማሪም ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆኑ ባሕላዊ ከሆኑትም በዓላቶቻችን ሁለቱን ስጠቅስ አንደኛው ድርጊቱ ከንግሥተ ሳባ ና ከእንቁጣጣሽ ታሪክ ጋራ ተያይዞ ይጠቀስ እንጂ ከዚያ አስቀድሞም ይፈጸም እንደነበረ ይገመታል፡፡ እሱም ልጃገረዶች የአበባየሁሽን ጭፈራ እየጨፈሩ የአበባ ስጦታን ለወላጅ ለጎረቤት ለዘመድ አዝማድ በማበርከት የ”እንኳን አደረሳቹህ!” መልእክትን የሚያቀርቡበት በዓል ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ የመስቀል በዓል ነው፡፡ የመስቀል በዓል ሲከበር ደመራው የእኛ ብቻ በሆነውና ሌላ ቦታ ጨርሶ በማይበቅለው ሁሌም አዲስ ዓመትን በሚያበስረን አደይ አበባችን አጊጦ የሚደመረው በዓል ነው፡፡ እናም እነኝህ እነኝህ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት የአበባና የሐበሻ ቁርኝት ቀደምቱና ጥንታዊው ታሪካችን ከሚጀምርበት አንሥቶ የነበረ በመሆኑ ከማንኛውም ሀገር የላቀና ለሌሎቹ አርአያ እንደሆነ በቀላሉ መገመት ይቻላል፡፡ የዚህ ዘመን ሰው ግን እንዲህ ዓይነት ታሪኮቻችንን ስለማያውቅ ወይም ልብ ስለማይለው የአበባ ስጦታ ወይም አበባን ማበርከት የእኛ ባሕል ያልሆነ ከባዕድ የመጣ ይመስለዋል፡፡ እውነቱ ግን ከላይ እንደተገለጸው ነው፡፡ እናም አበባ ስታበረክቱ የእኛን የራሳችንን ባሕል እየፈጸማቹህ እንደሆነ በማሰብ እንጅ ከፈረንጅ በተውሶ የመጣን ባሕል እየፈጸማቹህ እንደሆነ ተደርጎ እንዳይታሰብ መጠንቀቅ ያሻል፡፡

ይህ “ቫላንታይንስ ዴይ” ባዕዳዊ በዓል ከማኅበራዊ ሕይዎት አንጻር እንዴት ይታያል?

ይህንን በዓል ከማኅበራዊ ሕይዎትም አንጻር ስናየውም የምንጎዳበት ወይም የምናጎልበት እንጂ የምናተርፍበት ሆኖ አናገኘውም፡፡ ብዙዎቻችን እንደታዘብነው ሁሉ በዚህ በዓል ቀን ወላጅና ልጅ ግጭት ውስጥ የሚገቡበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ችግሩ ጎልቶ የሚታየው ለአቅመ ሔዋን ባልደረሱ ሴቶች እኅቶቻችን ላይ ነው፡፡ በዚህ የዕድሜ ደረጃ ያሉ ልጆችን በዓሉ በዚያ ሳቢና አባባይ ድምቀት በነጋዴዎችና በየ ሬዲዮው (ነጋሪተወጉ) አዳማቂነት ሲከበር ሲያዩ በሚፈጥርባቸው መነሣሣትና ጉጉት ያለ ወንድ ጓደኛ መሆናቸው ባዶነትና ወደ ኋላ መቅረት ወይም ያለመሠልጠን ሆኖ እየታያቸው ያለ ዕድሜያቸው የወንድ ጓደኛ እንዲይዙ ከባድ ጫና እያሳደረባቸውና ችግር ላይ እየጣላቸው ይገኛል፡፡ ጓደኛ ከያዙም በኋላ በሌሎች ጊዜያትም ሆነ በበዓሉ ቀንም በዓሉን ለማክበር በሚል ከወንድ ጓደኞቻቸው ጋር በሚሔዱባቸው ቦታዎች ላልጠበቁትና ላልፈለጉት በሕይዎታቸው ቋሚ ጉዳትና ችግር መዳረጋቸው የተለመደ ዜና ሆኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኤድስን ጨምሮ በሚከሰቱ የተወሳሰቡ ተያያዥ ችግሮች ቅድመ ጋብቻ ምንም ዓይነት ግንኙነት አለመጀመር መፍትሔ መሆኑ በታመነበት ዘመን ይሄንን መግባባት አፍርሶ እንደገና ወደ ኋላ የሚመልስን አፍራሽ ተግባር መከወን እውነት ያለመብሰል ብቻ ሳይሆን የለየለት ጠላትነትም ነው፡፡

በመጨረሻም ይሄንን ጣጣ ላመጡብን፣ ምን እየሠሩ እንደሆነ በውል ለይተው ለማያውቁት “የመዝናኛ ዝግጅት” አዘጋጆችና ስግብግብ ነጋዴዎች ማስገንዘብ የምሻው ጉዳይ አለ፡፡ አንድን ነገር ከሌላ አምጥታቹህ ከመዘርገፋቹህ በፊት እባካቹህ እንደዜጋ ከተለያየ አቅጣጫ ለመመርመር ሞክሩ፡፡ ይህን በማድረጋቹህ የምትጠቀሙት ነገር ቢኖርም እንኳ በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚፈጥረው ችግር የእናንተም መሆኑ አይቀርምና አስፍታቹህ ለማሰብ ሞክሩ፡፡
በአሁኑ ሰዓት ይሄንን ዕድል የሰጧቹህን አካላት ከመለመን ከማሳሰብ ከማስገንዘብ ይልቅ እናንተን መለመኑ ማሳሰቡ ሳይሻል አይቀርም፡፡ አነሱ እዛ ላይ ቁጭ ብለው ምን እየሠሩ እንደሚውሉ አልገባ ብሎኝ በጣም ተቸግሬያለሁ፡፡ እናም ወደናንተው ልመለስና እንዲሁ ስታስቡት የቸገረን ነገር ይሄና ሌላም የምትቀባጥሩት ፍሬ ፈርስኪ መሰል ድርጊቶች ናቸው ወይ? ከዚህ ይልቅ ምናለ በቸገረንና ሊኖረን በሚገባው ነገር ላይ ብታተኩሩ፣ ብትተጉ፣ ብትረባረቡ? እንዲህ እንደቀላል የሚወራ ወሬ ስታጡ የአየር ሠዓት ለመሙላት ብቻ ቀበጣጥራቹህት የምትወጡት ነገር ለእናንተ ቀላል መስሎ ቢታያቹህም ሀገርን ማፈራረስ ትውልድን መግደል የሚያስችል አቅም እንዳለውና እያፈራረሰንና እደገደለንም እንደሆነ ታይቷቹህ አያውቅም? እንደዜጋና እንደሚያስብ ሰው ይሄንን ላትረዱ የምትችሉበት ምንም ዓይነት ምክንያት ይኖር አይመስለኝም፡፡ ከስሜታዊነት ይልቅ ዕውቀትን ከግል ጥቅም ይልቅ ሀገርንና ሕዝብን የማስቀደም የሐሳብ መሠረት ላለው ሰው ይህ ፈጽሞ የሚቸግር ጉዳይ አይሆንም፡፡

ልጆች በተለይም ሴቶች በትምህርት ላይ እያሉ ወደ እንደዚህ ዓይነት ግንኙነት እንዲገቡ የማይመከረው ያለወቅቱ ወሲብ በመጀመራቸው ምክንያት ከወሲብ ጋራ ተያይዘው ተግተልትለው ከሚመጡት ዓይነተ ብዙ ሕይዎትን ከሚያመሰቃቅሉ ከሚያሰነካክሉ ከባባድ ችግሮች ባሻገር ትኩረታቸው ሙሉ በሙሉ ስለሚሰርቅ አቅጣጫቸውን ስለሚያስተው ነው፡፡ ትምህርት በራሱ የሙሉ ጊዜ ሥራ ነው፡፡ ሙሉ ጊዜን ለትምህርት አትኩሮት ሰጥተውትም ከስኬት ለመድረስ ስንት ፈተናዎች አሉት በዚህ ላይ ያለጊዜው ያለ ቦታው ፍቅር ውስጥ ከተገባ ለትምህርት ሊሰጡት የሚገባው ትኩረት ከመሰረቁ ጋር በተያያዘ ምን ያህል የብቃት መውረድ መንሸራተት መጎዳት ሊያጋጥም እንደሚችል በሁሉም ሰው ግንዛቤ ውስጥ ያለጉዳይ ነው፡፡ ፍቅር ቀናተኛ ነው ሙሉ ትኩረት ስጡኝ ባይ ነው፡፡ እንቅልፍና ምግብ እስከመከልከል ከዚያም አልፎ እስከማሳበድም ይደርሳል፡፡ ታዲያ እንዲህ ዓይነት ነገር ውስጥ ተገብቶ ትምህርን ያህል ከባድ ሥራና ኃላፊነት ወይም ጥናት እንደምን በብቃት መወጣት ይቻላል? ይሄም በመሆኑ ነው በተለይ ሴቶቻችን በየከፍተኛው የትምህርት ተቋማቱ የገቡትን ያህል ሳይሆን ለመጥቀስ በሚያሳፍር እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ለመመረቅ የሚበቁት፡፡ ከዚህ ችግር አምልጦ በትምህር መስክ ለስኬት ለመብቃት ያለው ብቸኛ አማራጭ “ይደረስበታል የራሱ ጊዜ አለው!” በሚል የበሰለና አርቆ ማሰብ የታከለበት ውሳኔ ፍቅርን ከትምህርት ወይም ከምረቃ በኋላ መቅጠሩ ብቻ ነው፡፡ እንደምናየውም ትምህርታቸውን በብቃት ተወጥተው በግሩም ነጥብ የሚመረቁት እራሳቸውን ከእንደዚህ ዓይነት ጉዳይ የቆጠቡት ናቸው፡፡

ወጣቱ ከዚህ የበሰለ ውሳኔ ደረጃ ላይ እየደረሰ በላቀ ብቃት ህልሙን እንዲያሳካ ለማስቻል የሁሉም ርብርቦሽ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይም የብዙኃን መገናኛው እጅግ ከባድ ኃላፊነት አለበት፡፡ እዚያ ላይ የተቀመጡ የየዝግጅቱ አዘጋጆች ባለሞያዎች ለመልካም ሰብእና ምሳሌና አርአያነት ያላቸው ሊሆኑ የግድ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ደረጃ የሚታዩ ካልሆኑም ሁለተኛው አማራጭ ካሳለፉት ከየግል የሕይዎት ተሞክሮዎቻቸውና ከውድቀት ጥንካሬዎቻቸው ወጣቱ እንዲማር የማድረግ ከባድ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ነገር ግን “እኛን የበላ ጅብ እነሱንም ይብላ!” በሚል የደነቆረና እጅግ ኃላፊነት የጎደለው የምቀኝነት ፈሊጥ ምኑንም የማያውቀውን ታዳጊ ወጣት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዲነጉድና እንዲጠፋ ማድረግ ቃል ሊገልጸው የማይችለው ድንቁርናና ከጠላትነት የከፋ ጠላትነት ነው፡፡

ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ የተገለጹት ቁም ነገሮች ለማይዋጡለትና መናኛ የግል ጥቅሙ የሚበልጥበት የጥፋት ዓላማ ላለው የመከነ ዜጋ ግን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ልብ ይስጥልን! ልብ የማይገዙና ሰይጣን ያገበራቸው ከሆኑ ግን ሳያጠፉን በፊት ይቅደምልን! ጉልበታቸውን ቀጤማ ያድርግልን! ከማለት ውጪ ምን ማለት ይቻላል ወገን?
ይህ ጽሑፍ ከዚህ ቀደም ለንባብ የበቃ ነው፡፡ ልብ ሊባሉ ሲገባ አሁንም ልብ ያልተባሉ ነጥቦችን በመያዙ ነው አሁንም ሊቀርብ የቻለው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

በድርድር የሚሳተፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በ3 ቡድን ተከፍለዋል

$
0
0

መርጋ ደጀኔ

“ድርድሩ በማን መሪነት እንደሚካሄድ ረቡዕ ይወሰናል”
– የተቃዋሚ ተደራዳሪዎች፣ ደህንነታቸው በመንግሥት እንዲጠበቅ ጠይቀዋል
– ኢህአዴግ – “ለድርድር እና ለክርክር ተዘጋጅቻለሁ”

  በድርድር ጉዳይ ላይ ከኢህአዴግ ጋር ለመነጋገር ለረቡዕ የካቲት 8 የተቀጣጠሩት ከደርዘን በላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሶስት ጎራ ተሰባስበውና ተከፋፍለው ከኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ወስነዋል፡፡

ድርድሩ በማን መሪነትና ታዛቢነት እንደሚካሄድ ገና አልተወሰነም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግረው ውሳኔ ለማስተላለፍም ነው ለረቡዕ የተቀጣጠሩት፡፡ ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች የድርድር መነሻ ሀሳቦችን በጋራ እና በተናጠል ለፓርላማ ጽ/ቤት እንዳስገቡ ገልፀዋል፡፡

የእነ ኢዴፓ ቡድን …
ኢዴፓ፣ ሠማያዊ፣ መኢአድ፣ ኢራፓ፣ መኢዴፓ እና ኢብአፓ፣ በጋራ ለመደራደር መሰባሰባቸውን ገልፀው ከኢህአዴግ ጋር የሚደረገው ድርድር እንዴት መካሄድ እንዳለበት የራሳችንን ሀሳብ አቅርበናል ብለዋል፡፡ የፈጠሩት ቡድን ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ በአደራዳሪነትና በታዛቢነት እነማን እንደሚሳተፉ በመዘርዘር የጋራ አቋም መያዛቸውን ስድስቱ ፓርቲዎች ጠቅሰው ሚዲያዎች ድርድሩን እንዴት እንደሚዘግቡትም አስታውቀዋል፡፡

6ቱ ፓርቲዎች የህዝብ ጥያቄዎች በሙሉ እስኪመለሱ እንደሚደራደሩና አስፈላጊ ከሆነ ህገ መንግስቱን የማሻሻል ድርድር ከገዥው ፓርቲ ጋር ለማድረግ እንደተዘጋጁ ጠቁመዋል፡፡

በድርድሩ ወቅት የህዝብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ፓርቲዎቹ ገልፀው ድርድር የሚያካሂዱት የፓርቲ ጉዳይ ለማስፈፀም ሳይሆን ህዝቡ በተቃውሞ ሲያነሳቸው የነበሩትን ጉዳዮች በማንገብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ ተቀስቅሶ የነበረው ተቃውሞና አመፅ፣ “በስርአቱ አምባገነንነት ሳቢያ የተፈጠረ ነው” የሚል አቋም መያዛቸውንም ፓርቲዎቹ ገልጸዋል። ተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ሲያቀርቧቸው የነበሩ የማሻሻያና የማስተካከያ ሃሳቦች በመንግስት በኩል ተቀባይነት ተነፍጓቸው ቆይቷል ይህም ሃገሪቱን ዋጋ አስከፍሏታል ብለዋል – ፓርቲዎቹ፡፡

የተጀመረው ድርድር በገዥው ፓርቲ በኩል በቅንነትና ቁርጠኝነት የሚከናወን ከሆነ ውጤት ያመጣል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ፓርቲዎቹ ጠቅሰዋል የድርድሩ ውጤት አንዱን ከስልጣን አውርዶ ሌላውን ወደ ስልጣን ማምጣት አይደለም የኛ ፍላጎት መንግስት በምርጫ የሚቀየርበትን ዘላቂና ቋሚ ስርአት እውን ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ገና ድርድሩ ሳይጀምር ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን በጠቆምም፣ በድርድሩ ላይ የሚሳተፉ አመራሮቻችን ከስጋት ነፃ እንደሆኑ የደህንነት ዋስትና ያስፈልጋቸዋል ይህም በመንግስት እንዲጠበቅላቸውም ጠይቀዋል ፓርቲዎች፡፡
ድርድሩ ከወዲሁ የህዝብ ተአማኒነት እንዲያተርፍ መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት ይጠበቅበታል ሲሉም ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል፡፡

የእነ አንድነት ቡድን
በአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር በአቶ ትዕግስቱ አወሉ አስተባባሪነት የሚንቀሳቀሱ ሌሎች 6 ፓርቲዎች በበኩላቸው የጋራ ቡድን በመፍጠር ለድርድር እንደተዘጋጁ ከትናንት በስቲያ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ የህዝብ ጥያቄዎች በሙሉ ምላሽ እንዲያገኙና ህዝባዊ ስርአት እንዲመጣ እንደራደራለን በማለት ፓርቲዎቹ ገልፀው ገዥው ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ የህዝብ ጥቅምን አስቀድመው እንዲደራደሩ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

ቡድኑን የመሰረቱት ፓርቲዎች፣ ቅንጅት፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ አንድነት፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ህብረት፣ የኢትዮጵያ ሠላማዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ ናቸው፡፡ መድረክን ጨምሮ ሌሎች ፓርቲዎች ደግሞ በተናጥል ለድርድር ለመቅረብ ወስነዋል፡፡

በሌላ በኩል የምርጫ ስነምግባር ደንብ ፈርመው የጋራ ም/ቤት አባል የነበሩ ፓርቲዎች “በምክር ቤቱ የነበረንን ቆይታ ስንገመግመው ምንም ውጤት አላስገኘልንም” ብለዋል፡፡
‹‹ምክር ቤቱ የተቋቋመበትን አላማና ግብ አላሳካም›› ያሉት የአንድነት ሊቀመንበር አቶ ትዕግስቱ በምክር ቤቱ የነበሩ ተቃዋሚዎች የአቅም ውስንነት ነበራቸው ብለዋል፡፡
የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው፣ የምክር ቤቱ ቆይታችን ውጤት አልባ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የራሱን የመደራደሪያ ሀሳቦችን እንዳዘጋጀ የገለፀው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሁሉም ፓርቲዎች ባቀረቧቸው የመነሻ ሃሳቦች ላይ ለመወያየት የካቲት 8 ቀን በፓርላማው አዳራሽ እንገናኝ በማለት ቀጥሯቸዋል፡፡
የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ድርጅታቸው የውይይት ሀሳቦችን ፕሮፖዛል ለፓርላማ ማስገባቱን የገለፁ ሲሆን ድርድር በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በግልፅ ለመደራደር ክርክር በሚያስፈልጋቸው የፖሊሲ ጉዳዮች ላይም ለመከራከር ወስነናል ብለዋል፡፡

ረቡዕ በሚደረገው ውይይት፣ “ድርድሩን ማን ይምራው? በምን መልኩ ይካሄድ?” በሚለው ጥያቄ ላይ ፓርቲዎቹ በውይይት ይወስናሉ ብለው እንደሚጠብቁ አቶ ሽፈራው ጠቁመዋል፡፡ በድርድሩ ስምምነት ላይ የሚደረስባቸው የህግ ለውጦችና ማሻሻያዎች፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋሉ ብለዋል፤ – አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፡፡

ፍጹም ድፍረት የሀገር ፍቅር የትግል ፍላጎት ተመልክቼ ተመለስኩ! (ስንታየሁ ቸኮል)

$
0
0

ሁለት ኣመት በእስር ላይ ቆየሁ መልሰው አሰሩኝ ለነጻነት የምከፍለው ዋጋ ነው (ዳንኤል ሽበሽ)

ፍጹም ድፍረት የሀገር ፍቅር የትግል ፍላጎት ተመልክቼ ተመለስኩ! የማይደክሙ የነጻነት እግሮች ወደ ቦሌ ክ/ከ/ ፖሊስ መምሪያ ዛሬም አቀናሁ ምክንያቱ ደግሞ እንደተለመደው በሕግ አልበኝነት የእስር ቤት በር የተዘጋባቸው ጓደኞቼ ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ -ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጓድ ዳንኤል ሺበሺ ለመጠየቅ ነበር፡፡ ቦታው ላይ ከደረስኩ ከጥቂት መጠበቅ በኃላ ተገናኘን የሞቀ ፈገግታ በሰላምታ ተለዋውጠን ስናበቃ በወቅታዊ ጉዳይ ትንሽ ማውጋት ጀመርን ምንም የማይደክሙ አንደበቶች ያወራሉ በአንባገነኖች እስር ቤት ውስጥም ሆነው ዛሬም እጃቸውን ኣጣምረው ድጋፋቸውን በኣደባባይ ይገልጻሉ ፡፡

እነዚህ ልበ ሙሉዎች ስለውጫዊ ትግል መጠናከር ኣጥብቀው ይመክራሉ፡፡ ጋዜጠኛ ኣናኒያ ሶሪ- ከሞላ ጎደል እንዲህ አለ….አስቸካይ ጊዜ ኣዋጅ ጥቂት የስርዓቱ ተጠቃሚዎች ከወጀቡ ለመጠበቅ ሲባል ሀገሪቱን በወታደር የጥርነፋ እዝ ለማስገባት የታለመ እንጂ የሀገሬ ሕዝብ ከማንም በላይ ሰላም ወዳድ ነው፡፡ -ሕግ አውጪ ኣካል 100% በሞላው ም/ቤት ከሀገር አኳያ ሳይሆን ከህወሓት ድርጅታዊ ጥቅም ኣንጻር እየተመዘነ ሕግ ያወጣል መልሶ የፍርድ ቤት ስልጣን ወስዶ ሽብርተኛ በማለት ራሱ ይወስናል፡፡ ሰሞኑን የኣሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የሰባት አገር ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ያወጡት መመሪያ በፌዴራል ፍ/ቤት ውድቅ ተደረገ! በሌላ በኩል የኬንያ መንግስት የስደተኞች መጠለያ (ዳዳብ) ሊዘጋው ያሳለፈውን ውሳኔ የሀገሪቱ ፍርዱ ቤት ሰብዓዊነት የጎደለው ትህዛዝ አገደ፡፡

የሰው ልጅ በሚኖርበት ሀገር ማንም ከስርዓት በላይ እንደልቡ አይዘልም፡፡ በዚህ ሀገር አንድ ጀነራል ተነስቶ ሕግ ያወጣል; እኛም እንደምንታሰር እያወቅን የምንታገለው ለዚህ ነው፡፡ ሌላው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ .. በእዚህ እስር ቤት ሆኜ የማስተላልፈው ቢኖር ” ይህ ትግል የአንድ አካባቢ ትግል አይደለም ” ይህ ትግል በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጀርባ የተደቀነ አደጋ ነው፡፡ ከሌሎችም ኣካባቢ የመጡ በርካታ ሰዎች እዚህ ታስረው ይገኛሉ ሁለም የሚያስበው አንድ አይነት ቋንቋ ነው ከዚህ ጨቋኝ ስርዓት መገላገል በእስር ያለው እንዲህ እያሰበ ሌላው በንትርክና አጉል ጭቅጭቅ ጊዜውን ሊያጠፋ አይገባም ወደፊት ማየት ብቻ ፡፡

 

እንኳን ደስ ያላሽ ባህርዳር! – ልያ ፋንታ

$
0
0

የባህርዳር የጣና ሞገዶቹ ጎንደር ላይ የሚያደርጉት ውድድር በአሼናፊነት እንዲጠናቀቅ የፋሲል አጼዎቹ ጭንቀት ላይ ነበሩ። የባህርዳር ከነማ ቡድን በሁለተኛው እናት መሬቱ በጎንደር ከተማ ውድድሩን ሲያደርግ መላው የአጼዎቹ ደጋፊ ከእርሱ ጄርባ ቆመ ያውስ ተፎካካሪው የአዲስ አበባ ፖሊስ አይደል። እናቶች ሁሉ ሰለ ባህርዳር ከነማ አሼናፊ መሆን ስለት ለቤተክርስቲያን መሳላቼውን ስስማ እኒህ ጎንደር እና ጎጃም ፍቅራቼው እንዴት ይገርማል አልኩ።

ትናንት እግሮች ሁሉ ወደ እስታዲዮሙ አመሩ ስታዲየሙ በተመልካች ተጨናነቀ፣ የባህርዳር ከነማ ተጨዋቾች በደጋፊዎቻቼው ደማቅ ጭብጨባ በሜዳ እንደተወርዋሪ ኮከብ እንዳሻቼው ሲፈነድቁ ዋሉ ። በመጨረሻም ባህርዳሮች 1 አዲስ አበባ ፖሊስ ዜሮ በሆነ ውጤት አሼናፊዎችም ሆኑ ።
እንኳን ደስ ያለሽ ባህርዳር ፣

ድል ለጣና ሞገድ የባህርዳር ከነማ ቡድን፣

ባህርዳሮች በሁለተኛ ሀገራቼው ጎንደር ስታዲዮም ውድድር ለማድረግ ጎንደር ከትመዋል። በባህርዳር እንዳያደርጉ የተጣለባቸውን እገዳ ከምንም አልቆጠሩትም ጎንደርም ጎጃምም የእነሱ ከተሞች ናቼው የበላይዎቹ ግቡ ተንፈላሰሱ በአጼዎቹ ቤተመንግስት።
መላው የጎንደር ከተማ ህዝብ ከባህርዳር የጣና ሞገድ ጄርባ እንደሚቆም አልጠራጠርም።
መልካም እድል ለባህርዳ ከነማ የስፖርት ቡድን ተመኜሁ፣

እኒህ መንትያዎች ጎጃም እና ጎንደር
ዘራፍ፣ ሲሉ አሰቀኑት የተኛውን መንደር

 

ሁለት ፕሮፌሰሮች፡– ፍቅሬ ቶሎሳና ጌታቸው ኃይሌ – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

የካቲት/2009

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

በአንድ ሰኮንድ ውስጥ ስንት ነገሮች ስንት ሁኔታዎች ይታያሉ?፣ ስንት ድርጊቶች፣ ስንት ሥራዎች ይፈጸማሉ? ስንት ሰዎች ይሞታሉ? ስንት ሰዎች ይወለዳሉ? … አንድ ሰኮንድ ባዘለው ጊዜ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች አሉ፤ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ የስድሳ ሰኮንዶችን ያህል ጥያቄዎች ይፈለፈላሉ፤ በአንድ ሰዓት ውስጥ 60*60= 3600 እነዚህ ደግሞ በ24 ሰዓት ሲባዙ 86 400 ይሆናሉ፤ የሚሆኑትንና የሚደረጉትን ነገሮች ሁሉ መዝግቦ፣ የሚነገሩትን ነገሮች ሁሉ አጣርቶ ይዞ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፍ አለ ወይ? የትናንትናውን ሃያ አራት ሰዓት በዘርዝር ማስታወስ የሚችል አለ ወይ? ጊዜውና መሣሪያው ያላችሁ የሳምንቱን፣ የወሩን፣ የዓመቱን ሰኮንዶችና ያቀፉትንና ያዘሉትን ጉዳዮች አጣርታችሁ ለማወቅና ‹‹ተረቱንና ታሪኩን›› ለመለየት ሞክሩ፡

እንደኔ የጂኦሎጂ ሀሁ የሚያውቅ ደግሞ ሌላም ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል፤ በጂኦሎጂ ታሪክ የሚቆጠረው በሚልዮን ዓመታት ነው፤ የዛሬ መቶ ሚልዮን ዓመት ምድር እንደዚህ ነበረች፤ ከዚያ በኋላ በዚህ፣ በዚህ ተለዋወጠች እያለ ይነግረናል፤ ተረት ነው የምንለው ወይስ ታሪክ? እንዲያውም አንድ እውነት ልንገራችሁ፤ አሜሪካ አኔ በተማርሁበት ዩኒቨርሲቲ አንድ በበረዶ ድንጋይ በዓለም የታወቀ ፕሮፌሰር ነበረን፤ አንድ ቀን ለመስክ ጥናት ወስዶን አንድ አነስ ያለ ሐይቅ ያለበትን ረባዳ መሬት ቁለቁል እያሳየን የድንጋይ በረዶው ከየት ተነሥቶ ወዴት ሲንሸራተት እንደነበረና ምን እንዳገደውና ሐይቁ እንዴት እንደተፈጠረ ነግሮን ሲጨርስ አጠገባችን ቆሞ ሲያዳምጥ የነበረ የአካባቢው ሰው ድምጹን ከፍ አድርጎ ‹ይህንን ሐይቅ የሠራነው እኛ ነንእኮ!› አለ፤ የኛ ዓለም ያደነቀው ፕሮፌሰር ሁለቱንም እጆቹን ወደሰማይ ዘርግቶ፣ ያውላችሁ የኔ ሀሳብ ብትንትኑ ወጣ!‹ አለን! ታሪክን ተረት ማለት ተረት አያደርገውም፤ ተረትን ታሪክ ማለትም ታሪክ አያደርገውም፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ታሪክ ሊቃውንት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ከአረብያ ፈልሰው የመጡ ናቸው እያልን ፈረንጆች የነገሩንን እናስተምር ነበር፤ ሁለመናችን ከአረቦች የመጣ መሆኑን አስተምረናል፤ አሁን አንድ ሌላ ፈረንጅ መጣና ‹የለም፣ ሰዎች ከኢትዮጵያ ወደአረብያ ፈለሱ እንጂ ከአረብያ ወደኢትዮጵያ አልፈለሱም፤ ኢትዮጵያ ሰጪ እንጂ ተቀባይ አልነበረችም፤› ይለናል፤ የቱ ነው ተረት? የቱ ነው ታሪክ? አንዱ የኢትዮጵያ ታሪክ ሊቅ በቅርቡ በጻፈው የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ታሪክ ውስጥ ‹አጼ ምኒልክ ወደደቡብ ሲስፋፉ› ብሎ ይጀምራል፤ አጼ ሱስንዮስ ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት ደቡብ እንደነበረ፣ አንድ ንጉሠ ነገሥትም ዘይላ አካባቢ እንደሞተ፣ የደቡብ እቴጌዎች እንደነበሩ ይነገራል፤ ታዲያ ተረቱ የቱ ነው? ታሪኩ የቱ ነው? ፈረንጅን ተከትሎ ማነብነብ የዘመኑ ባህል ሆነ፤ ጎፈሬን እኛ ስንጠላው ፈረንጅ አገር ገባና ስሙን ለውጦ አፍሮ ተብሎ መጣልን!
የፍቅሬ ቶሎሳን መጽሐፍ ከጊዜው የስደተኞች ፖሊቲካ ጋር አያይዘው የፖሊቲካ አስታራቂነት ተልእኮ የሚሰጡት ሰዎች የመ ጽሐፉ መሠረት የገባቸው አይመስለኝም፤ እኔንም ካላመለጠኝ መጽሐፉ ሁለቱን የዓለም መሠረታዊ ባላ — ቦታንና ጊዜን — አቀራርቦና አዋኅዶ የያዘ በመሆኑ ከጊዜያዊነት ውጭ መስሎ ይታየኛል፤ መጽሐፉ ለብዙዎቻችን ከባድ የሆነውም በዚህ ምክንያት ይመስለኛል፡፡

ስንት የፈረንጅ ተረቶችን ሳንጨነቅ ታሪክ ብለን አስተምረናል? ስንት የራሳችንን ታሪክ ተረት ብለን ጥለናል? ፍቅሬ ቶሎሳ ያቀረበው አዲስ ነገር ነው፤ አበሻ ደግሞ አዲስ ነገርን አይወድም፤ የፍቅሬን መጽሐፍ እኔ መሀከሉ ደርሼ መቆሜን ነግሬዋለሁ፤ ሰኮንዶቹን፣ ደቂቃዎቹንና ሰዓቶቹን፣ ቀኖቹንና ወሮቹን፣ ዓመቶቹን መንጥሮ ያላየ ሰው እንዴት ብሎ በምን መለኪያ ተረቱንና ታሪኩን በእርግጠኛነት መለየት ይችላል? ለመሆኑ የፍቅሬ ቶሎሳን መጽሐፍ ተረት ነው ለማለት የምንችለው ርእሱን በየት በኩል አልፈን ነው? እኔ መጽሐፉን አንብቤ አልጨረስሁትም፤ በሕይወቴ ጀምሬ መጨረስ ያቃተኝ መጽሐፍ የፍቅሬ ቶሎሳ ሁለተኛው ነው፤ ሌላው ከጀመርሁት ሃምሳ ዓመት የሚሆነው መጽሐፍ የፈረንሳዩ ፈላስፋ የዣ ፖል ሳርትር አንድ መጽሐፍ ነው፤ ሁለቱንም መጽሐፎች አንብቤ ሀሳብ ለመስጠት አለመቻሌ የኔ ጉድለት እንጂ የደራሲዎቹ አይደለም፡፡
በበኩሌ እንደፍቅሬ ያሉ ከያለበት ቃርመው፣ የራሳቸውን አእምሮ አስረግዘውና በምጥ አስጨንቀው አዲስ ነገርን የሚያቀርቡልንን ያበርታችሁ እላለሁ! ግን እንድንደርስባችሁ አለምልሙን!

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live