Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

ሁለት ፕሮፌሰሮች፡– ፍቅሬ ቶሎሳና ጌታቸው ኃይሌ

$
0
0

በአንድ ሰኮንድ ውስጥ ስንት ነገሮች ስንት ሁኔታዎች ይታያሉ?፣ ስንት ድርጊቶች፣ ስንት ሥራዎች ይፈጸማሉ? ስንት ሰዎች ይሞታሉ? ስንት ሰዎች ይወለዳሉ? … አንድ ሰኮንድ ባዘለው ጊዜ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች አሉ፤ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ የስድሳ ሰኮንዶችን ያህል ጥያቄዎች ይፈለፈላሉ፤ በአንድ ሰዓት ውስጥ 60*60= 3600 እነዚህ ደግሞ በ24 ሰዓት ሲባዙ 86 400 ይሆናሉ፤ የሚሆኑትንና የሚደረጉትን ነገሮች ሁሉ መዝግቦ፣ የሚነገሩትን ነገሮች ሁሉ አጣርቶ ይዞ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፍ አለ ወይ? የትናንትናውን ሃያ አራት ሰዓት በዝርዝር ማስታወስ የሚችል አለ ወይ? ጊዜውና መሣሪያው ያላችሁ የሳምንቱን፣ የወሩን፣ የዓመቱን ሰኮንዶችና ያቀፉትንና ያዘሉትን ጉዳዮች አጣርታችሁ ለማወቅና ‹‹ተረቱንና ታሪኩን›› ለመለየት ሞክሩ፡፡

እንደኔ የጂኦሎጂ ሀሁ የሚያውቅ ደግሞ ሌላም ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል፤ በጂኦሎጂ ታሪክ የሚቆጠረው በሚልዮን ዓመታት ነው፤ የዛሬ መቶ ሚልዮን ዓመት ምድር እንደዚህ ነበረች፤ ከዚያ በኋላ በዚህ፣ በዚህ ተለዋወጠች እያለ ይነግረናል፤ ተረት ነው የምንለው ወይስ ታሪክ? እንዲያውም አንድ እውነት ልንገራችሁ፤

አሜሪካ አኔ በተማርሁበት ዩኒቨርሲቲ አንድ በበረዶ ድንጋይ በዓለም የታወቀ ፕሮፌሰር ነበረን፤ አንድ ቀን ለመስክ ጥናት ወስዶን አንድ አነስ ያለ ሐይቅ ያለበትን ረባዳ መሬት ቁለቁል እያሳየን የድንጋይ በረዶው ከየት ተነሥቶ ወዴት ሲንሸራተት እንደነበረና ምን እንዳገደውና ሐይቁ እንዴት እንደተፈጠረ ነግሮን ሲጨርስ አጠገባችን ቆሞ ሲያዳምጥ የነበረ የአካባቢው ሰው ድምጹን ከፍ አድርጎ ‘ይህንን ሐይቅ የሠራነው እኛ ነንእኮ!’ አለ፤ የኛ ዓለም ያደነቀው ፕሮፌሰር ሁለቱንም እጆቹን ወደሰማይ ዘርግቶ፣ ‘ያውላችሁ የኔ ሀሳብ ብትንትኑ ወጣ!’ አለን! ታሪክን ተረት ማለት ተረት አያደርገውም፤ ተረትን ታሪክ ማለትም ታሪክ አያደርገውም፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ታሪክ ሊቃውንት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ከአረብያ ፈልሰው የመጡ ናቸው እያልን ፈረንጆች የነገሩንን እናስተምር ነበር፤ ሁለመናችን ከአረቦች የመጣ መሆኑን አስተምረናል፤ አሁን አንድ ሌላ ፈረንጅ መጣና ‘የለም፣ ሰዎች ከኢትዮጵያ ወደአረብያ ፈለሱ እንጂ ከአረብያ ወደኢትዮጵያ አልፈለሱም፤ ኢትዮጵያ ሰጪ እንጂ ተቀባይ አልነበረችም፤’ ይለናል፤ የቱ ነው ተረት? የቱ ነው ታሪክ? አንዱ የኢትዮጵያ ታሪክ ሊቅ በቅርቡ በጻፈው የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ታሪክ ውስጥ ‘አጼ ምኒልክ ወደደቡብ ሲስፋፉ’ ብሎ ይጀምራል፤ አጼ ሱስንዮስ ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት ደቡብ እንደነበረ፣ አንድ ንጉሠ ነገሥትም ዘይላ አካባቢ እንደሞተ፣ የደቡብ እቴጌዎች እንደነበሩ ይነገራል፤ ታዲያ ተረቱ የቱ ነው? ታሪኩ የቱ ነው? ፈረንጅን ተከትሎ ማነብነብ የዘመኑ ባህል ሆነ፤ ጎፈሬን እኛ ስንጠላው ፈረንጅ አገር ገባና ስሙን ለውጦ አፍሮ ተብሎ መጣልን!

የፍቅሬ ቶሎሳን መጽሐፍ ከጊዜው የስደተኞች ፖሊቲካ ጋር አያይዘው የፖሊቲካ አስታራቂነት ተልእኮ የሚሰጡት ሰዎች የመጽሐፉ መሠረት የገባቸው አይመስለኝም፤ እኔንም ካላመለጠኝ መጽሐፉ ሁለቱን የዓለም መሠረታዊ ባላ — ቦታንና ጊዜን — አቀራርቦና አዋኅዶ የያዘ በመሆኑ ከጊዜያዊነት ውጭ መስሎ ይታየኛል፤ መጽሐፉ ለብዙዎቻችን ከባድ የሆነውም በዚህ ምክንያት ይመስለኛል፡፡

ስንት የፈረንጅ ተረቶችን ሳንጨነቅ ታሪክ ብለን አስተምረናል? ስንት የራሳችንን ታሪክ ተረት ብለን ጥለናል? ፍቅሬ ቶሎሳ ያቀረበው አዲስ ነገር ነው፤ አበሻ ደግሞ አዲስ ነገርን አይወድም፤ የፍቅሬን መጽሐፍ እኔ መሀከሉ ደርሼ መቆሜን ነግሬዋለሁ፤ ሰኮንዶቹን፣ ደቂቃዎቹንና ሰዓቶቹን፣ ቀኖቹንና ወሮቹን፣ ዓመቶቹን መንጥሮ ያላየ ሰው እንዴት ብሎ በምን መለኪያ ተረቱንና ታሪኩን በእርግጠኛነት መለየት ይችላል? ለመሆኑ የፍቅሬ ቶሎሳን መጽሐፍ ተረት ነው ለማለት የምንችለው ርእሱን በየት በኩል አልፈን ነው? እኔ መጽሐፉን አንብቤ አልጨረስሁትም፤ በሕይወቴ ጀምሬ መጨረስ ያቃተኝ መጽሐፍ የፍቅሬ ቶሎሳ ሁለተኛው ነው፤ ሌላው ከጀመርሁት ሃምሳ ዓመት የሚሆነው መጽሐፍ የፈረንሳዩ ፈላስፋ የዣ ፖል ሳርትር አንድ መጽሐፍ ነው፤ ሁለቱንም መጽሐፎች አንብቤ ሀሳብ ለመስጠት አለመቻሌ የኔ ጉድለት እንጂ የደራሲዎቹ አይደለም፡፡

በበኩሌ እንደፍቅሬ ያሉ ከያለበት ቃርመው፣ የራሳቸውን አእምሮ አስረግዘውና በምጥ አስጨንቀው አዲስ ነገርን የሚያቀርቡልንን ያበርታችሁ እላለሁ! ግን እንድንደርስባችሁ አለምልሙን!

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
የካቲት/2009

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)


ዳንኤል ሺበሹ/አናኒያ ሶሪና ኤሊያስ ገብሩ ይናገራሉ (ስንታየሁ ቸኮል እንደዘገበው)

$
0
0

ፍጹም ድፍረት የሀገር ፍቅር የትግል ፍላጎት ተመልክቼ ተመለስኩ! የማይደክሙ የነጻነት እግሮች ወደ ቦሌ ክ/ከ/ ፖሊስ መምሪያ ዛሬም አቀናሁ። ምክንያቱ ደግሞ እንደተለመደው በሕግ አልበኝነት የእስር ቤት በር የተዘጋባቸው ጓደኞቼ ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ -ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጓድ ዳንኤል ሺበሺ ለመጠየቅ ነበር፡፡ ቦታው ላይ ከደረስኩ ከጥቂት መጠበቅ በኃላ ተገናኘን የሞቀ ፈገግታ በሰላምታ ተለዋውጠን ስናበቃ በወቅታዊ ጉዳይ ትንሽ ማውጋት ጀመርን። ምንም የማይደክሙ አንደበቶች ያወራሉ። በአንባገነኖች እስር ቤት ውስጥም ሆነው ዛሬም እጃቸውን ኣጣምረው ድጋፋቸውን በኣደባባይ ይገልጻሉ ፡፡ እነዚህ ልበ ሙሉዎች ስለውጫዊ ትግል መጠናከር ኣጥብቀው ይመክራሉ፡፡

“ሁለት ኣመት በእስር ላይ ቆየሁ። መልሰው አሰሩኝ ለነጻነት የምከፍለው ዋጋ ነው” ይላል ዳንኤል ሺበሺ

ጋዜጠኛ ኣናኒያ ሶሪ- ከሞላ ጎደል እንዲህ አለ….

“አስቸካይ ጊዜ ኣዋጅ ጥቂት የስርዓቱ ተጠቃሚዎች ከወጀቡ ለመጠበቅ ሲባል ሀገሪቱን በወታደር የጥርነፋ እዝ ለማስገባት የታለመ እንጂ የሀገሬ ሕዝብ ከማንም በላይ ሰላም ወዳድ ነው፡፡ -ሕግ አውጪ ኣካል 100% በሞላው ም/ቤት ከሀገር አኳያ ሳይሆን ከህወሓት ድርጅታዊ ጥቅም ኣንጻር እየተመዘነ ሕግ ያወጣል። መልሶ የፍርድ ቤት ስልጣን ወስዶ ሽብርተኛ በማለት ራሱ ይወስናል፡፡ ሰሞኑን የኣሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የሰባት አገር ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ያወጡት መመሪያ በፌዴራል ፍ/ቤት ውድቅ ተደረገ! በሌላ በኩል የኬንያ መንግስት የስደተኞች መጠለያ (ዳዳብ) ሊዘጋው ያሳለፈውን ውሳኔ የሀገሪቱ ፍርዱ ቤት ሰብዓዊነት የጎደለው ትህዛዝ አገደ፡፡ የሰው ልጅ በሚኖርበት ሀገር ማንም ከስርዓት በላይ እንደልቡ አይዘልም፡፡ በዚህ ሀገር አንድ ጀነራል ተነስቶ ሕግ ያወጣል።እኛም እንደምንታሰር እያወቅን የምንታገለው ለዚህ ነው፡፡ ”

ሌላው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ .. በእዚህ እስር ቤት ሆኜ የማስተላልፈው ቢኖር ” ይህ ትግል የአንድ አካባቢ ትግል አይደለም ” ይህ ትግል በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጀርባ የተደቀነ አደጋ ነው፡፡ ከሌሎችም ኣካባቢ የመጡ በርካታ ሰዎች እዚህ ታስረው ይገኛሉ። ሁለም የሚያስበው አንድ አይነት ቋንቋ ነው። ከዚህ ጨቋኝ ስርዓት መገላገል በእስር ያለው እንዲህ እያሰበ ሌላው በንትርክና አጉል ጭቅጭቅ ጊዜውን ሊያጠፋ አይገባም ወደፊት ማየት ብቻ ፡፡

የሪፖርተርን ርእስ አንቀጽ ወድጄዋለሁ #ግርማ_ካሳ

$
0
0

በተቃዋሚዎችና በአገዛዙ መካከል ይደረጋል በተባለው ድርድር ዙሪያ ሪፖርተር ጋዜጣ ግሩም ርእስ አንቀጽ አውጥቷል። ይሄን ርእስ አቀንጽ እኔ ልጽፈው የምችለው ሙሉ ለሙሉ የምጋራው ርእስ አንቀጽ ነው።

“ውይይትም ሆነ ድርድር ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኙት ሁለቱ ወገኖች ያለፉትን ቂምና ቁርሾዎች ወደ ጎን በማድረግና ለአገርና ለሕዝብ ምንም ጥቅም እንደሌላቸው ከልብ በማመን፣ አዲሱን ጉዞ በሠለጠነ መንገድ ላይ ቢጀምሩ ጥቅሙ ለአገር ነው፡፡ የፖለቲካ ምኅዳሩ ሰፍቶ ሁሉም የአገሪቱ ፓርቲዎች በእኩልነትና በነፃነት እንዲፎካከሩ ማድረግ የወቅቱ ዓቢይ ጥያቄ ነው፡፡ ከፖለቲካ ፍጆታነት የማይዘሉ አጓጉል ድርጊቶችን በማስወገድ የዜጎችን አንገት ሲያስደፋ የኖረውን አስከፊ የፖለቲካ ባህል መለወጥ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ድርድሩም ሆነ ውይይቱ በቀና መንፈስ እንዲጀመር ሲፈለግ በቅድመ ሁኔታዎች እያመካኙ ምክንያት መደርደር ሊቆም ይገባል፡፡ ድርድሩም ሆነ ውይይቱ ለሰጥቶ መቀበል መርህ ክፍት ከሆነ ቀዳሚው ጉዳይ የአገርና የሕዝብ ጥቅም ይሆናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ቁጠርኛ መሆን ግዴታ ነው፡፡”

ይላል ሪፖርተር በረስ አንቀጹ።

በሪፖርተር ላይ የሰፈሩትን ጠቃሚ ሐሳቦች ማንም አገሩን የሚወድ የቀና አስተሳሰብ ያለው ሰው በሙሉ የሚደግፈው ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ። ሆኖም ግን አንድ በትልቁ ሊሰመርበት የሚገባ ነገር አለ። እርሱም ይሄ በሪፖርተር እንዲኖር የተፈለገው መንፈስ እንዳይኖር እንቅፋት የሆነው ራሱ ገዢው ፓርቲ መሆኑ ነው።

አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ( በዉጭ ያሉትን አይመለከተም፤ እኔ ዉጭ ያሉት እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ አላያቸዉም፤ለምን እዳያስፖኢራ ሆኖ፣ ከህዝቡ ርቆ ፣ ድጋፍ ከመስጠት ዉጭ የሚደረግ ትግል ስለሌለ) በአገዛዙ ላይ ቁርሾ የላቸዉም። በሕወሃት የፖለቲካ ዉሳኔ የታገደው እነ አቶ ግርማ ሰይፉ አመራር የነበሩበት የአንድነት ፓርቲ በአገዛዙ ላይ ቁርሾ አልነበረውም። አብዛኛው አመራሩ አገዛዙ የዘረጋቸውን የልማት ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ ፍላጎት የነበራቸው፣ የአባይን ቦንድ የገዙና ገንዘብ ያዋጡ ናቸው። አቶ ግርማ ሰይፉ ከነ አባ ዱላ ጋር በመሆንም በአባይ ግደብ ዙሪያ ሁሉ ግብጽ ድረስ በመሄድ አጋርነትን ያሳዩ ናቸው። ሆኖም አገዛዙ ሞደሬት፣ ዘመናዊ የተባሉ ድርጅቶችን ሁሉ ነው በኃይል የጨፈለቀው። የሚገድለው፣የሚያስረው፣ ጽ/ቤት የሚያዘጋው፣ የተለያዩ ሕጎች እያወጣ የሚያሽብረው፣ ከሥራ የሚያባረርው፣ ከቤት የሚያፈናቅለው አገዛዙ ራሱ ነው። ሌላውን እንደጠላት እያየ ለማጥቃትና ለመንቀሳቀስ የሞከረው ራሱ አገዛዙ ነው። እንጂ አገር ቤት ያሉ በሰላም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ኢሕአዴግን እንደ ጠላት የቆጠሩበት ሁኔታ የለም።

ስለዚህ ሪፖርተር ያሰፈረው ሐሳብ ተግባራዊ እንዲሆን፣ የሰለጠነ ፖለቲካ፣ ሰላም በአገራችን እንዲሰፍን በዋናነት መለወጥ ያለበት አገዛዙ ራሱ ነው። አገዛዙ ተቃዋሚዎችን እንደ ጠላት ማየት ማቆም አለበት። በመድበለ ፓርቲ የሚያምን ከሆነ፣ የተጨበጡ ተግባራት መፈጸም አለበት። ለድርድር መተማመን እና መቀባበል ያስፈለጋል። ይህ መተማመን እንዲኖር፣ የታሰሩ የተቃዋሚ እስረኞችን በሙሉ መፈታት አለበት። አንዱዋለም አራጌን፣ ዮናታን ተስፋዬን፣ ተስፋዬ ታሪኩን፣ ዶር መራራ ጉዲናም፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ የመሳሰሉትን አስሮ ለድርድር መቅረቡ ሂደቱን ከወዲሁ እንዲበላሽ የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን መተማመንን የሚያመጣ አይደለም። ብዙዎች ካለፉት ታሪኮች በመነሳት “ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው። ወያኔ አይታመንም” የሚል ጠንካራ አቋም አላቸው። በአንድ በኩል ትክክል ናቸው። ሆኖም ግን የአሁኑ ሁኔታ ከዚህ በፊት ከነበረው በእጅጉ የተለየ በመሆኑ፣ እንዳልፈው የይስሙላ ብቻ ድራም ላያደርጉ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ። እንግዲህ አገዛዙ በርግጥ እንደከዚህ በፊቱ አስመሳይ አለመሆኑን በተጨባጭና በተግባራ ማሳየት አለበት።

እንደ አየለ ጫሚሶ ቡድን ያሉ ግብስብ ቡድኖችን እንተዋቸዉና ተቀባይነት ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች (በተለይም መኢአድ፣ ሰማያዊ፣ መድረክ እንዲሁም ኢዴፓ) የተጨበጠ ነገር በሂደት ካላዩ ፣ ምንም እንኳን አሁን ቅድመ ሁኔታ ባያስቀመጡም፣ ሂደቱን አቋርጠው መወጣታቸው የማይቀር ነው።

ደግሜ እላለሁ፣ ገዢው ፓርቲ ይሄንን እድል ማበላሸት የለበትም። ይሄ የሰላም ድርድር በሕዝብ ተአማኒነት እንዲኖረው የሚያደርግ ሥራ በቶሎ መስራት አለበት። ደግሜ እላለሁ ይሄ ስራ መጀመርም ያለበት የተቃዋሚ መሪዎችን ሁሉ በመፍታት ነው።

የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞችን ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም የሚያስከብር አዋጅ ጸደቀ

$
0
0

ከሁለት ዓመት በፊት በጭምጭምታ ደረጃ ወሬዉ ወደ አደባባይ የወጣዉ ባለሥልጣናት “ጡረታ” ሲወጡ የሚከበርላቸዉ ጥቅማጥቅም አሁን “ህጋዊ  ዕዉቅና” አግኝቷል።

ሐሙስ ዕለት በዋለዉ የኢህአዴግ “ፓርላማ” የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከኃለፊነታቸዉ ሲነሱ ጥቅማጥቅማቸዉን የሚያስከብር አዋጅ ተሸሽሎ እንዲጸድቅ ተደርጓል።

የተሻሻለዉ አዋጅ ከኃላፊነታቸዉ የሚነሱ የመንግስት ባለሥልጣናት እንደ የኃላፊነት ደረጃቸዉ የመቋቋሚያ አበል፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣መኖሪያ ቤት፣የቤት ሰራተኞች፣ የምግብ አብሳዮች፣ የቀንና የማታ ቤት ጠባቂዎች፣ የተሸከርካሪ አገልግሎት ከነአሽከርካሪዉና ጠባቂ (body guard) እንዲሟላላቸዉ አዋጁ ያብራራል።

ቀደም ሲል ለኢህአዴግ ነባር ታጋይ ባለሥልጣናት መኖሪያ ቤት በሚል ከመንግስት ካዝና ያለ ፓርላማዉ ይሁንታ (ምንም እንኳን ልዩነት ባይኖረዉም) በአዲስ አበባ ወረገኑ አካባቢ አርሶ አደሮችን በማፈናቀል “ጡረታ ለሚወጡ ስድስት ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በመቶ ሃምሳ አራት ሚሊዮን ብር (እያንዳንዳቸው ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ በድምሩ 154 ሚሊዮን ብር) መጦሪያ ቤቶች ተገንብተው እየተጠናቀቁ” መሆናቸውን ጉዳዩን በኃላፊነት የሚመራው ተክለጻዲቅ ተክለአረጋይ (አቡነአረጋይ) ታህሳስ 1፤2008ዓም/November 12, 2015 ለሸገር ሬድዮ መናገሩ በዕለቱ ተዘግቦ ነበር። ተክለጻዲቅ ሲቀጥልም “አገራችን እነዚህን ቤቶች ለባለስልጣኖች መገንባቷ ከአፍሪካ አንደኛ ያደርጋታል” ከማለቱ በተጨማሪ “የመዋኛ ገንዳ (ስዊሚንግ ፑል) ያላቸው እነዚህ ቅንጡ ቤቶች የሚገነባላቸው ባለስልጣኖች ተለይተው መታወቃቸውን” ማስረዳቱ የህወሃት/ኢህአዴግን ዓይነደረቅነት ያሳየ ተግባር ሆኖ ነበር።

ዜናውን አያይዞ “ከጠቅላላ ሕዝቧ ውስጥ ከ2 ፐርሰንት በታች ለሆኑ አዛውንት ዜጎቿ የጡረታና የማህበራዊ ዋስትና የሌላት አገር ብትሆንም በስልጣን ዘመናቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ለዘረፉ ሌባ ባለስልጣኖቿ ግን ቅንጡ መጦሪያ ቤት የምትገነባ አገር ሆናለች” በማለት በወቅቱ በተጨማሪ መዘገቡ የሚታወስ ነው

ሳራ አሊሲዮ ከ 1ወር ህጻን ልጇ ጋር በዋርዴር – Associated Press

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የዕለት ምግብ ደራሽ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር  ህወሃት/ኢህአዴግ ባመነዉ መረጃ መሰረት 6.2 ሚሊዮን ይሆናሉ። ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ዜጎች ቁጥር ደግሞ 24 ሚሊዮን ደርሷል። በከተሞች እጅግ ሥር የሰደደ ድህነት ይታያል። ከዚህም አልፎ በሀገሪቱ በተከሰተዉ ድርቅ በየዕለቱ የሚሞቱ የጋማና የቀንድ ከብቶች ቁጥር እያሻቀበ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ክፍል በችጋር እየተሰቃየ ባለበት ሁኔታ ለባለሥልጣናቱ እንዲህ ቅንጡ የሆነ ጥቅማ ጥቅም የታከለበት አዋጅ ማጽደቁ የጤና አለመሆኑ አስተያየት ተሰጥቶበታል። በአዋጁ ላይ “የተሻሻለዉ አዋጅ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ይረዳል” በሚል የሰፈረው ሃሳብ “ህወሃታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ይረዳል” ተብሎ ይነበብ ሲሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ተሳልቀዋል።

ለጎልጉል ሃሳባቸውን የሰጡ የህግ ባለሙያ እንዳሉት “ዓይን ቀቅለዉ የሚበሉት የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የጡረታ ጊዜያቸዉን በቅንጡ ህይወት ለማጀብ አዋጅ እስከማሻሻል ደርሰዋል። በሥልጣን ላይ እያሉ የሚዘርፉትን ገንዘብ የት እንደሚያደርሱት አደባባይ ላይ የተሰጣ እዉነት ቢሆንም አንድ ቀን ወደ ህዝብ እንደሚመለስ ተስፋ እንደርጋለን። እስከዚያዉ ኢትዮጵያና አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የሰቀቀን ህይወት እየኖሩ በሚገብሩት ግብርና በኢትዮጵያ ሥም በሚለመነዉ ገንዘብ ዘመን ያገነናቸዉን ጅቦች ሲቀልብ ይኖራል” ብለዋል!!

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ከሥልጣናቸው ከለቀቁ በኋላ ከጡረታ፣ ከመኖሪያ ቤትና ከመሳሰሉ መሠረታዊ ጥቅማጥቅሞች አኳያ እጅግ ብዙ ግፍ መቀበላቸው ይታወሳል።

አዋጁ ከተጻፈበትና በውስጡ ካካተተው መረጃ አንጻር ጥቅማጥቅሞቹ “ከጥልቅ ተሃድሶ” ጋር በተያያዘ በጡረታ እንዲገለሉ የሚደረጉ የህወሃት/ኢህአዴግ ሹሞችን አፍ ማስዘጊያ ሆኖ የቀረበ አንዱ “የጥልቅ ተሃድሶው” ውጤት ነው ተብሏል። “በመበስበስ መታደስ!

ፎቶው ከYona Bir ፌስቡክ የተወሰደ


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ ንብረታቸዉ ወድሟል የተባሉ የትግራይ ሰዎች ካሳ ሊከፈላቸዉ ነዉ

$
0
0

በ2008ዓ.ም. መገባደጃ ወራት ላይ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ የኮሚቴ አባላትን የህወሃት/ኢህአዴግ ኃይሎች በጎንደር ከተማ ለማፈን ያደረጉት ሙከራ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ቀስቅሶ የህይወትና የንብረት ዉድመት መድረሱ ይታወሳል። በወቅቱ “ንብረታቸው ወድሟል” የተባለላቸው የትግራይ ተወላጆች የካሣ ክፍ ሊፈጸምላቸው መሆኑ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ “የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ንብረት እየተለየ ጥቃት ደርሶበታል” በሚል በህወሃት/ኢህአዴግ (“የፌዴራል መንግሥት”) የበላይ አደራጅነት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ጎንደር ከተማ ለሚኖሩ ትግራዋያን ነጋዴዎች “የጠፋባቸዉንና የወደመባቸዉን ንብረት” ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ በማስመዝገብ የካሳ ክፍያና እንደ አስፈላጊነቱ የረዥም ጊዜ የብድር አገልግሎት ሊመቻችላቸዉ እንደሆነ የጎልጉል ታማኝ የመረጃ ምንጮች ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተወክለዉ የተላኩ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የንብረት ገማች ባለሙያዎች ጎንደር ከተማ ተገኝተዉ “ተአረፉና ወደሙ” የተባሉ የትግራዋያንን የንግድ ደርጅቶች ወርቅ ቤቶችን፣ ሱቆችን፣ ሆቴሎችንና መኖሪያ ቤቶችን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል። እንደ ጎልጉል የመረጃ ምንጮች  በጎንደር ከተማ በንግድ ሥራ የተሰማሩ ትግራዋያኖች ከፍተኛ ግነት ባለዉ መልኩ ያልጠፋቸዉን ንብረቶች (በስቶክ ያልተመዘገቡ) አስመዝግበዋል።በተለይም የሁመራ፣ የተክሌ፣ የመሀሪ ወርቅ ቤት ባለቤቶች በህዛባዊ ተቃዉሞ ጊዜ ወርቅ ቤቶቻቸዉ ተዘግተዉ የነበረ በመሆኑ በርና መስኮታቸዉ ላይ በድንጋይ ድብደባ ጉዳት ከመድረሱ ዉጪ ይህ ነዉ የሚባል ንብረት ባልተዘረፈበት ሁኔታ ከፍተኛ የንብረት ዉድመት መድረሱንና በሚሊዮኖች ብር የሚያወጣ ወርቅ መዘረፋቸዉን አስመዝግበዋል።

ቅዳሜ ገበያ በተቃጠለበት ጊዜ

በተመሳሳይ መልኩ የሁመራ ፔንሲዮን፣ ጣና ሆቴል፣ ሮማን ሆቴልና ቋራ ሆቴል ባለቤት የሆኑ ትግራዋያን ወደመብን የሚሉትን ንብረት በሚሊዮኖች ደረጃ አስመዝግበዋል። በአንጻሩ በጎንደር ከተማ የሚኖሩ አማሮች በህዝባዊ ተቃዉሞዉ ጊዜ የወደመባቸዉ ንብረት በከተማ አስተዳደሩ እንዲመዘገብላቸዉ በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም “ከክልል ትዕዛዝ አልተሰጠንም” የሚል ምላሽ ሲሰጣቸዉ ቆይቷል። በተለይም ከትግራይ ክልል በመጡ ሰርጎ ገቦች እንደተፈጸመ የሚጠረጠረዉ የከተማዋ ዋና የገበያ ማዕከል የሆነዉ “ቅዳሜ ገበያ” 446 የባህልና የዘመናዊ አልባሳት መሸጫ ሱቆች፣የጫማና ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችና መደብሮች “በድንገተኛ” የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ የወደመባቸዉ ነጋዴዎች ዛሬም ድረስ አስታዋሽ አጥተዉ ባሉበት ሠዓት ለትግራዋያን ተወላጆች ብቻ ለይቶ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸዉ የከተማዋን ተወላጆችና ተጎጅዎችን እንዳሳዘናቸዉ የጎልጉል የመረጃ ምንጮች ከወደ ጎንደር ያደረሱን መረጃ ያመለክታል።

“በርግጥ ኢትዮጵያ ዛሬም ያልተሟላች ሀገር ነች። ለአንዱ ማርና ወተት የምታዘንብ ለሌላዉ ደግሞ መዐትና መከራ የምታወርድ ጉራማይሌ ሀገር ሆናለች። ተስማማንበትም አልተስማማንበትም በአንድ ሀገር እየኖርን በዚህን ያህል መጠን መለያየታችን እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነዉ። በአደባባይ አይን ያወጣ የብሄር መድሎ መፈጸም ሀገሪቱን ፍጹም ወደ አልተፈለገ መስመር ይመራታል እንጅ መፍትሄ አይሆንም። ትግራዋያንም ቢሆን በዚህን ያህል መጠን እንደ ብሄር ሊባል በሚችል መልኩ የሀገር ሀብት ቅርምት ተሳታፊ መሆናቸዉ ለነገ ዉርስ ዕዳ እያስቀመጡ መሆኑን ሊያዉቁት ይገባል። የሀገራችን ሰዉ “ግርግር ለሌባ ይመቻል!” እንደሚል የጎንደሩን ህዛባዊ ቁጣ ያስታከኩ ትግራዋያን ባለሀብቶች ጎንደር ላይ ያልታሰበ የትርፍ ሲሳይ ዘንቦላቸዋል” በማለት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አስተያየት ሰጪ ለጎልጉል ተናግረዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ባንዶች፤ የዐማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆችና የመስዋት በግ የሆነው ገበሬ

$
0
0

(ሙሉቀን ተስፋው)

ባንዳነት (ከጠላት ጋር ማበር) የተጀመረው በቀይ ባሕር አካባቢ በሚኖሩ ትግሬዎች ቢሆንም በጊዜና በመጠን እየተለያየ በሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ነበረ፤ አለ፤ ወደፊትም ይኖራል። የማኅበረሰብ ተፈጥሮ ጥሬ ብስል ተጎራሰም ነው፤ ለሕዝብ የሚያስብ፣ ራሱን የሚወድ፣ ለገንዘብ የተገዛ፣ በጥቅም የማይደለል… ዓይነት ሰዎች በየትኛውም ሕዝብ ውስጥ አሉ።

ለምሳሌ የራስ አበበ አረጋይን እና ቤተሰቡን ታሪክ ማየት ይቻላል፤ ራስ አበበ አረጋይ ታላቅ ስመ ጥር አርበኛ ነበር፤ የሚያሳዝነው ግን አባቱ እልም ያለ ባንዳ ሆኖ ከልጁ ጋር በተለያየ ግንባር መሰለፉ ነው። የአንድ ቤተሰብ አባላት ውስጥ ባንዳና አርበኛ መፈጠራቸው ለዚያውም አባት ባንዳ ልጅ አርበኛ ሲሆኑ መመለክት እጅግ ይገርማል። ይህን ጉዳይ ያለ ነገር አላነሳሁትም።

የዐማራ የጎበዝ አለቆች ጋር ስንነጋገር ያደረሱኝ መረጃ እጅግ አስገርሞኛል። ለማስተማሪያነት ይሆናል ይፋ አድርገው ስላሉኝም ነው ይህን መጻፌ።

ምትኩ ገላው የተባለ ወጣት የዐማራ አርበኞችን ከወንድሙ ጋር ከተቀላቀለ ቆይቷል። በጥር 26 ቀን 2009 ዓ.ም. ‹‹ቤተሰብ ጋር ደርሼ መመለስ አለብኝ›› የሚል ሐሳብ ያነሳል፤ ፈቃድ ተከለከለ፤ አደጋ ይደርስብሃል ተባለ። ተማጽእኖው ቀላል አልነበረም። ይሁን ተባለና ሔደ።

የዐማራ ታጋዮች በነጋታው ጥር 27 ቀን በደባርቅ ወረዳ ቆላው አካባቢ ይሔዱ እንደነበር ያውቃል። ሆኖም ምትኩ ገላው ወንድሙን ጨምሮ ብዙ ጓደኞቹ የዐማራ ሕዝብን ስቃይ እንቅልፍ ነስቷቸው ከወያኔ ጋር መቆራረጣቸውን እያወቀ ‹‹ባንድነት›› ባሕሪው ይሆናል ብለው አላሳቡትም ነበር።

የጎበዝ አለቆች ሔዱ፤ አቶ ምትኩ በቀጣዩ ቀን 450 እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ የወያኔ ወታደሮችን ይዞ ከተፍ አለ፤ ፍጥነቱ ከብርሃንም ይልቃል። የዐማራ ታጋዮች ከነፍሳቸው ይልቅ በልጁ ባንዳነት ሐዘን እጅግ ተጎዱ። ግን አርበኝነት የዘራቸው ነው፤ ነፍጥ አተኳኮስ፤ ከበባን መስበር ብላቴ ወይም ጦላይ የጦር ትምህርት ቤት አልተማሩም፤ እድሜ ለአርማጭሆ ጫካዎች። ሙሉ በሙሉ መንገዶች ሁሉ ተዘግተዋል። በጀርባቸው ያለው ላጥ ያለ ገደል ብቻ ነው። ገደሉን ለመውረድ እንደ ሰሜን ጭላዳዎች ልምምድ ያስፈልጋል።

ጀግኖቹ ግን አንድም ሰው ሳይጎዳ ከበባውን ሰብረው ሔዱ። ባንዳው አፈረ፤ አረመኔዎቹ የወያኔ ወታደሮች አንድ በእርሻ ቦታ ላይ የነበረ ምንም ስለጉዳዩ ዕውቀት እንኳን የሌለውን ዐማራ ገበሬ በቀትር ተኩሰው ገደሉት። በሚያርሰው መሬት ትልም ላይ የምስኪኑ ገበሬ ደም ፈሰሰበት። ገበሬው የመስዋት በግ ሆነ።

ሌላም ጊዜ እንዲህ ያለ ባንዳ ገጥሟቸዋል። አቶ አሳየኸኝ ተቀባ ይባላል። በታኅሳስ 12 ቀን 2009 ዓ.ም ከድቶ ገብቶ የወንድሞቻችን ሕይወት አስቀጥፏል። አቶ አሳየኸኝና አቶ ምትኩ አሁን ከወያኔዎች ጋር ናቸው፤ በባንዳነት የተገኘ ሀብትና ክብር የጠዋት ጤዛ እንደሆነ ደካማው አእምሯቸው ገና አልተገለጸለትም።

የዐማራ ሕዝብ ትግልማ ያለምንም ጥርጥር በቆራጥ ጀግኖቻችን ያሸንፋል!!

ሰበር የመረጃ ግብአት – ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

ጅዳ ውስጥ አንድ የኢራቅ አውሮፕላን ከእሳት ቃጠሎ አደጋ ተረፈ !
=========================================
* በውስጡ የነበሩይ 356 ተሳፋሪዎችን ይዞ ነበር
* አንድም ጉዳት የደረሰበት ሰው የለም

የጸሎት ተጓዦችን የያዘውና ንብረትነቱ የኢራቅ የሆነ እውሮፕላን ጀዳ በሚገኘው የንጉስ አብድልአዚዝ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በማረፍ ላይ እንዳለ በጎማው ላይ ጭስ የቀላቀለ እሳት ተከስቶ በአየር ማረፊያው የእሳት አደጋ ብርጌድ ባደረጉት ፈጣን ርብርብ ቃጠሎው በቁጥጥር መዋሉ ታውቋል። ትናንት ማለዳ ከኢራቅ ተነስቶ ጅዳ ሲገባ በጎማው ላይ ጭስ መመልከቱን ምድር ላይ ለሚገኙ የአየር መንገዱ መቆጣጠሪያ ሰራተኞች ሪፖርት ባደረገው አብራሪ አማካኝነት አውሮፕላኑ አንዳረፈ እሳቱን ለማጥፋት የሳውዲ እሳት አደጋ ቡድን እሳቱን ሊቆጣጠረው መቻሉ ተጠቁሟል ። መሬት ላይ እንዳረፈ ዘመናዊ የእሳት መከላከያ መሳሪያ የታጠቀው የእሳት አደጋ ብርጌድ በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩትን 356 ተሳፋሪዎች አንድም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከአየር መንገዱ ሰራተኞች ጋር በመተባበር ወደ እንግዳ መቀበያ ማረፊያ መወሰዳቸው ታውቋል።

ወደ እስልምና ቅዱስ ቦታዎች መካና መዲና ለጸሎት የሚመጡና ጸሎታቸውን አደርሰው የሚመለሱ ምዕመናንን በማስተናገድ በኩል ጅዳ የሚገኘው የንጉስ አብደልአዚዝ አየር ማረፊያ ዋና መግቢያና መውጫ በር ሲሆን ከመላው አለም ወደ ሳውዲ የሚመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናንን በአመት በማስተናገድ የሚተካከለው የለም ።

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
የካቲት 5 ቀን 2009 ዓም

ዬኢትዮዽያ ቀን – ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ – ሥላሴ  13.02.2017 (ዙሪክ – ሲዊዘርላንድ)

„ፍርድና ልቅሶ በሚደረግበት ቀን፥ እግዚአብሄር በሚመጣበት ቀንና ቊርጥ ፍርድ በሚፈረድበት ቀን ፥የእግዚአብሄርን ህግ የዘነጉ ሰዎች በሚቆሙበት ቦታ ይቆማሉ።“
(መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፫ )

… ፊቱ ውሃ ሲሄድበት ዬከረመ ይመስላል። የዕንባው ወራጅ ቁልል ኮረብታን ገንብቷል። ብልዘቱ እንደ መልካም ነገር ከሩቅ ያሳጣል። ክርክም ባልተሠራለት የአንገቱ ወለል ላይ ውስጡን እያነቃና … እያደራጀ በሰቀ-ደረቱ ላይ ለሽ ያለው ዬእንባ ኖራ፥ ዬመከፋት ቀለም ቀቢነቱ በቡዙ ውስጡን በቅኔ ቅንነት ይተረጉማል። የወጣት ሰአሊ ነው። የብራናው ሰሌዳም ገፁ፥ ሜሮኑም የዐይኑ ጨው ነው። ከቃጠሎውም ዬተነሳ የቁስለቱ በስጋት የተገነዘ ፍዳ ደረቱ ላይ ዬእሳተ ጎመራ ቀለ ሰርቶ፥ ጎጆውን በእልህና ወኔ ቀልሷል። ውስጡ በመከራና በአሳር ፍሞ አክስሎታል። ቀረብ ብሎ ከውስጥነት ካላዩት ተክለ ቁመናውን ሆነ የገጹን ላሂ በውስጥ ቃጠሎው ምሬት የተነሳ እሱ መሆኑን መለየት ፈጽሞ አይቻልም።

ከእማ ዬተጠጋ ቀን ሁልጊዜም እንዳለቀሰ ነው። ዕጣው ከእርሷ ጋር እንደ ጠነዘለ። ያልፍልኛል ብላ ባለመችበት ሰዓት፣ ወቅትና ዘመን ሁሉ ለቅሶ – ይደገስላታል። ለምሾዋ ማጫ – ይመታባታል። እሷ ማዲያት – በማድያት መሆኗ ውስጧን ሲሟጥጠው ዋይታ ይለፍ ተሰጥቶት ይታወጅባታል። ቀን ዬቀናቱን ታጣፊ አልጋነት ልተወው ቢል እንኳን፥ እረፍት ሰጪ ከቶ ዬላትም። ውጋቷ እንዲያጥድፋት ይታከል፥ ይታከል፥ እያለ … ተጠቋቋሚው ሁሉ ያለባት የፋሽስት አሳር ላይበቃ፤ ሌላውም ፋታ አልቦሽ በተደራቢነት ይወግራታል – ይሰልቃታል፤ ያልፍልኛል ስትል ይቀማታል፥ አረመኔ ሲያሯሩጣት መጠጊያ ስትሻ ዋሻ ያለችውም ዘንበል ቀና እያለ – ያለዛታል። ሸማዋ እንኳን ተቀናቃኝን ደጅ እንዲጠና ዱብ … ዱብ እዬተባለለት ነው … ህም!

እምም! ደግሞ ዬሚገርመው እሷው ለቻለችው፥ እሷው ለተሸከመችው፤ እሷው ለተጫነችው „አታልቅሺ ይሏታል“ያልተያዘ ግልግል ያውቃል“  እንደሚባለው። ስለምን አታነባ? አርማ – ኮትኩታ – ዬአዘራችው ቡቃያ ዬተባይ ቀለብ ሲሆን፥ እኮ! ስለምን እንባዋን አትለቀው? ዬማግስት መጋኛ ሲገን፤ ግን እኮ! ስለምን እሪ አትል? እሸቷ ሲነቃቀል፥ እኮ! ስለምን አታምርር? እንዲህ ጨለማ ሲውጣት፤ እኮ! ስለምን – ዋይተኛ አትሁን? ህሊናዋ ዬፍም ረድፈኛ ሲሆን፥ እኮ! ስለምን ኡኡ አትል? ተስፋዋ ዬምድጃ፤ የረመጥ ቤተኛ ሲሆን ሲያንስ …. ነዲዱ ጎጆዋን አመድ ዱቂት ሲያደርገው፤ በጢስ ታፍና ስታምጥ፤ ልጇቿ በታቀደ ቃጠሎ እንደ በግ፥ እንደ ሰንጋ ሥጋ የእሳት መፈተኛ ሲሆኑ ጨርቋን ጥላ አለማበዷም እሷ ሆና ነው። የፈረደባት፤ ጠላቶቿን ጡት አጥብታ አሳድጋ በነጋ በጠባ ሲኮንኗት፤ ሲያጣጥሏት ልጠው ሲጠብሷት ይውላሉ  – ያድራሉ፤ ይሄው ያምሷታል፥ ይቆሏታል ይፈጯታል። እየጠሏት – ይግጧታል፤ እየናቋት – ቁርጥም አድርገው ይበሏታል፤ አናውቅሽም ተብላ ይሞሸሩባታል። የወላድ መካን ዬሆነች – ባተሌ ። እያገላበጡ ሀገር በቀል ፋሽስቶች – አነደዷት። ሲዘነጥሏት ለአፋቸው ሞግድ አልሠራለትም። የህዳር ዝናቦች። እያዬ እዬሰማ እግዜሩም ዝም አለ።

„ዬደላው“ አሉ። ሲመሽም ሲነገም ለባቴሌዋ ያው ነው፤ ዜሮ ሲደመር ዜሮ ያው ዜሮ። ከዜሮ ላይም ዜሮ ሲቀነስ ያው ዜሮ። ዜሮ ሲባዛ በዜሮም ያው አምሳያው ነው። አሽሙሩ መረረኝ ስትል መስቃው፥ መስቃው ወቃኝ ስትል ውርዴቱ፤ ውርዴቱ ተከመረብኝ ስትል ግልምጫና ልግጫው ፈረደባት በእፋኝት የድንጋይ ሽበት፤ እሷ በመኖሯ ፈጥራ „ምጥ ለእናቷ“ ሆኖ ፈጠርንሽ ይሏታል። ጠላቷን መክታ ለወግ ለማዕረግ ስላበቃች፤ ጠላትሽን ቅስሙን ሰብረሽ ማባረርሽ እንግዳ ወዳጅ አለመሆንሽን ተፈላስመንበታል ይሏታል፤ እንቁላል ተሽጦ በተሸመነው የሐረግ ዝርግ። መንኰራኲራቸው ባነዳነት፤ ትዕቢተኝነታቸው ልሳነ ፍግ ነውና።

… ያልፋል ስትል እንደ መጫኛ ዬሚያፋ፤ ይሆናል ስትል እንደ ህልም ብን … ትን … ትርትር ዬሚል፤ ደረስኩ ስትል እንደ ጉም ሽንት ዬኋልዮሽ – ዬሚያሰኘው፤ ስለቱ መረረኝ ስትል – ገጀሞው፤ ገጀሞውም ፋታ ነሳኝ ስትል – መዶሻው፤ መዶሻውን እህል ውሃውን ያሳጥርልኝ ብላ ስታጣውር እሳት ዬላሰ – ፋስ፤ ፋሱን ተገላገልኩ ስትል – ባሩድ፤ ባሩዱ አላተረፈኝም ብላ ልታመልጥ ጉሩቦ ከጉሩቦ ከፈርኦን ጋር ስትገጥም በመርዝ — ህም! እና እሷ ያላለቀሰች ማን ያልቅስ? እሷ ያላማጠች ማን ያምጥ? እሷ ማቅ ያለበሰች ማን ይልበስ? እሷ  ለፈጣሪዋ በእንባ ያላመለከተች ማን? እኮ ማን? ቀኗ እራሱ ስቅስቅ ብሎ አብሯት ከውስጧ መከፋት ጋር ይታደማል። በምህላ በበገና፤ በሱባኤ በክራር ይታደማል። ከስግድቱ ብዛት ጉልበቱ ሌላ ሸከር ያለ ተደራቢ ሞረድ ቆዳ አብቅሏል።

እሷማ ሁልጊዜም ዒላማ ናት! በቅላ እንዳትታይ ወፍበላ ዬሰፈረባት፤ ዬተስፋ ቀን ጠኔ ዬሚያጥመነምናት፤ ስለምጧ ቀን ተንበርክካ ዬምትማስን  – አሳረኛ። ሀገር በቀል ሪህ መቅኖዋን ምጥጥ አድርጎ ያለባት፥ በደረቁ ዬላጫት፤ በአለሎ – ዬሚደቁሳት፤ በመዳመጫ ያሻውን ያህል ዬሚድጣት ከቀኗ ጋር ያሻታል – በሽታሽቶ። ተወልጄ ነኝ ይላታል። ድንቄም¡ አሰር ውሃ፤

በ20 ዓመት ቀና ዬምትል ባተሌ ከኖረች ዬእሷማ ስፍር ቁጥር በሌለው መጋኛ – ትጣደፋለች። እንደ አንስት በባለደምነት ዬተፈረጀባት ሐገር እንደ ኢትዮዽያ እንደ ሌለ ሰማዕቱ ዬኢትዮዽያ ቀን እንባውን ተግ አድርጎ፤ ዘለግ ባለ ቃና ዬፍዳዋን መጫኛነት ይመሰክርላታል።

እሱ እቴ ዬዋዛ! ዬኢትዮዽያ ቀን ዕውነት እኮ ነው ትንፋሹ። አቅም ያላቸው ሴቶች እንደ ባለደም መታዬታቸው አልበቃ ብሉ ዬመከራ ሙከራ ቤት መሆናቸው ዕንባማው ዬኢትዮዽያ ቀን ከሁሉ በላይ – ያብሰለስለዋል። ሁሉ እያላቸው መተንፈሻቸው ታስሮ መረማመጃ መሆኑ ውስጡን – ይፈጀዋል።

እሱ ግን ዕንባማው የኢትዮጵያ ቀን እግዚአብሄር ዬተመሰገነ ይሁን እንጂ፤ ቅርባቸው ለመሆን – ቆርጧል። እነ አቤቶ አውሎውን ካላኩበት። ለነገሩ ዬእነሱ ነገር ምን ገና „አቡጊዳ ሳይደርሱ“  ይለቅማል በወጥመድ – አቤቶ ፈርኦናዊው ማኒፌስቶ፤ እቴ አምጡልኝማ ዬዛሬውን ዘመን ዬአርበኝነት ውሎ፤ ማነ ነው ዬሚሉት አያ? እ … መጣልኝ ሴት ብሎገሪስት፤ ሴት አክቲቢስት፥ አዎን እነሱንም ሳጥናኤል ልቅምቅም አድርጎ  – ከርቸሌ።

ህም፤ አንስት ያልተፈራ ማን ይፈራ? መቼስ አንስት ብቅ ስትል ዬሳጥናኤል ሰይፋ ጨንገር ተነስቶበት ልቡ ጥፍት እስኪል ድረስ ያስነካዋል። እንቱን -ን፤ ዛሩን ከሰጠሰጠ በኋላ፤ ያቺ በ20 ይሁን በ30 ዓመት ብቅ ዬምትል ዬምንቴ ትሁን ዬትዋቡ፤ ዬጣይቱ ትሁን ዬዘውዲቱ ብቻ ምንአለፋችሁ መረብ ዘርግቶ አደኑን ያጣድፈዋል። መቼስ ሴት ቀና ካለች ያክለፈልፈዋል – ስላችሁ። ይጐማጃል – ቅስሟን እንክትክት ለማደረግ። ስጋ ያዬ ጅብ ነው ዬሚሆነው። ጉምጅታም – አራዊት

ወይ ፍዳ! ተሰጦዬን በብራና ላወራርድ ዬሚል ዬብዕር ጠብታን ብራና ላይ መሰስ ሲያደርገው – ቀለም ፈራሹ ዬፈርኦን ሰይፌ ጨንገር ክላሽን ያህል ፈርቶ ከርሸሌ ቀኑ ይሆናል፤ እስቲ ባለችኝ እንኮን ከእንባሽ ጎን ልቁም፤ አጋርሽም ልሁን፤ ባይሆን ዛሬ ዬዓንችው ዓይን ፍሰት ተግ ይበልልሽ፤ ተረኛ እኔ ልሁን ብሎ ሲሰለፍ „መሀይም ብሎ ፖለቲከኛ¡ መሀይም ብሎ ዬሐገር ተቆርቋሪ¡ ተብሎ ቀን ያሰለፈችው ትንታግ ከማህበረ ዬነፃነት አርበኝነት በፎርፌ፤ እሺ! እነኛ ያልተማሩ ከተባሉ፤ በቀለም በሰል ካሉት ሲባል ደግሞ ዬዓላማ ማህበራቸውን ዬቀራኒዎ ቀን። ዬኢትዮዽያ ቀን ውጋቱ ብዙ ነው። ለዚህ ነው ዬእማምዬ ዝናቧ እራሱ ዕንባ ዬሆነው። መሬቷም ልማቱ በዕንባ መስኖ። ልማታዊ – ቅብጥርሶ – ምንትሶ – ገለመሌ – ወለሜሌ የሚሉት እኮ ወስፋት ታስሮ ለ“ቁምራ“ አንጀት ለማትደርሰው የቆረባ ማስታገሻ ቁራሽ እኮ ነው። ለእሷም ሰዓት እላፊ ታውጆባታል አሉ። ምን መሽቶ ሲቲነጋ ዓዋጅ ነው ሲረቅ ውሎ የሚታድረው። አንቀጡ ቢዘረጋጋ አምላካችሁ አለ ምድሪቱን ባለበሳት።

አዎና የምድር ስጋጃ አንቀጥ በሰለጠነው የጫካ ተመክሮ። የአንቀጥ ገመድ፤ የአንቀጥ መረብ፤ የአንቀጥ ትሬኮላታ ኧረ ምኑ ተጨውቶ፤ የእነ እንቶፎቶ ስልቻ የቃሬዛ ስንብቻ፤  የአንቀጥ ካቴና። ትንፋሻቸው መስንበቻዋ እኮ የነጋሪት ጋዜጣ – በጋሬጣ።

ስደት እያገላበጠ እንደ ዶሮቄት ዬሚቆላው ዬኢትዮዽያ ቀን ተዚህም ዬት ሲቀርላት፤ ሥደቱ ቋያ፤ ዬፈርዖን ጀሌ ቋያ፤ ነገ ስለአንቺ ቀን ቆርጠናል፤ ታጥቀናል ዬሚለውም ባለችው መብት ለሌላው በገደብ፤ በደንበር፤ በወገን፤ በአድሎ፤ በአጋ፤ በደረጃ፤ በከፍና ዝቅ ተሰቅዞ ስደቱ ላይበቃው በግራ ቀኝ በውከባ ወበቅ ሲገረፍ … ዬኢትዮዽያ ቀን ዓይኑን ብቻ ሳይሆን አብራክንም ያዝና በላይም በታችም በምጥ ዬታጀበ ዕንባውን በጣምራ ሲለቀው ላዬ ምናኔ በስንት ጣሙ ያሰኛል። ለዚህ እኮነው የቅኔው ግሥ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን የወንድ ልጅ ዕንባው ሆድነቱን የተቃኘው።

አልቃሻው ዬኢትዮዽያ ቀን መፍትሄ ዬሚባል መላዕክን ይመኛል፥ ይናፍቃል፥ ሽው ይለዋል፥ ይርበዋል ግን ይቻለው ይሆን? ህልም ፈቺ ከተገኘ? ውሸታም ያልሆነ ወይንም ያልሆነች። አደባባይን ውስጡ ያደረገ ወይንም ያደረገች ፥ ዬጓሮ ጉዞን ዬተጸዬፈ ወይንም የተጠዬፈች። ዕውን ተናፋቂው ዴሞክራሲ ጋር መምከር ዬቻለ ወይንም የቻለች።

ጨለማን ገፎ በጠኃይ የሚያንቆጠቁጥ፤ ብሩክ፤ ወይንም ደግሞ ወዘተረፈውን ካቴና እንኩትኩቱን ያወጣች ብርክት ምህረትን ከሸበላው ብሩህ ተስፋ ጋር ታኮመኩሙን ይሆን? … እስቲ ይርዳቸው አንድዬ እንደ – ዬመንገዳቸው ጠላታቸውን ሰብሮ የልብ – ለልብ የሚያደርስ ቀን ያምጣ። ከእቱ ከእናቱ የተጠጋውም ዓጤው ቀኖ ከዕንባው ጋር ፍቺ የሚመጣለት ንዑድ መላዕክ ይዘዝለት። አሜን!

መከራን የሚረታ፥ ፍቅራዊነትን የሚያንሰራፋ፥ በቀልን በምህረት አቅም ድል የሚያደርግ፥ የዕውነተኛ የተስፋ ቀን ፈጣሪ ይስጠን። አሜን!

ለአላዛሯ ኢትዮዽያ አዲስ ቀን ፈጣሪ አምላካችን መርቆ ይስጥልን። አሜን!

መሸቢያ ጊዜ፥ እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 


አርበኛ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ – ቀሪን ገረመው

$
0
0

ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ

ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ በስማቸው እና በፆታቸው ሴት ናቸው ። በቆራጥነታቸው እና በጀግንነታቸው ግን የወንድነት ስም የተሰጣቸው ዝነኛ አርበኛ ነበሩ ። በሴትነታቸውም ቢሆን በዘመናቸው ከነበሩት ወይዛዝርት የበለጡ እንጂ ያነሰ ውይዝርና አልነበራቸውም ። በአርበኝነት ደግሞ እንኳን ለሴቶች ለወንዶች አርአያ የሚሆኑ ሙያ በማሳየታቸው በታሪክ ዓምድ የሚልቋቸው ወንዶች ጥቂቶች ናቸው ። ከፈጸሟቸው የጀብዱ ሙያዎች አንደንዶቹን ብናስታውሳቸው ለትውልድ ደስታ እና ኩራትን ያጎናጽፋሉ ።

አንድ ቀን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የኢጣልያ ሲሰቀል አልቅሰሻል ተብለው ተከሰው ከፋሽስት ከፍተኛ የጦር ሹማምንት ፊት ቀርበው ተጠይቀው ነበር ። ጀግናዋ ወ/ሮ ግን በዚያን ግዜ የፍርሃትና የሴትነት መንፈስ ሳያሳዩ ያላንዳች መርበትበት ቁርጥ ያለ አነጋገር ምንም ክሳቸውንም አላስተባበሉም ፣ << አዎ አልቅሻለሁ ፤ የእናንተ አገር ሴቶች በሰው አገር ቀንተው የጣታቸውን ቀለበት እያወለቁ ኢትዮጵያን ለመውረር ለመጡት ሽፍቶች ሲያበረክቱ እኔ አገሬ በባዕድ ሕዝብ ሲወረው መንግሥት ጠፍቶ የአገሩ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ ሌላ ሲሰቀል ለሰንደቅ ዓላማዬ ማልቀስ ይነስብኝ ወይ ? >> ሲሉ መልሰዋል ። ከዚህም በቀር ለአርበኞች ስንቅ ታቀብያለሽ ፣ ቀይ መስቀልን ትረጃለሽ በሚል ተወንጅለው ለጥያቄ ቀርበው ነበር ። ወይዘሮዋ ግን አሁንም በክሱ ሕሊናቸው ሳይሸበር << ሰለ ነፃነት ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው የሌሊት ቁርና የቀን ሐሩር ከሚገርፋቸው የአገሬ አርበኞች ጎን ተሰልፌ ጠላቴን መውጋቴ ቀርቶ የረኃብና የጥም መድኃኒት እያዘጋጀሁ መላኩ ቁም ነገር ሆኖ ነው የተጠየቅሁበት ? እኔ ይህን ባለማድረጌ ለሀገርም ባልቆረቆር እንኳን እንኳን እነሱ እናንተም እንደምትታዘቡኝ ይሰማኛል ። >> ሲሉ ለቀረበባቸው ክስ እጅግ አስደናቂ የሆነ ያገር ፍቅር የተሞላበት መልስ ቆራጥነት በተቀላቀለበት አነጋገር መልስ ሰጡ ።

በጠላት አደባባይ ቆሞ ይህን የመሰለ ኃይለ ቃል በመናገር ጠላትን ካስደነቁ ጀግኖች ወ/ሮ ሸዋረገድ የመጀመርያዋ ናቸው ። ወ/ሮ ሸዋረገድ ይህን መልስ በሰጡበት ሰዓት አንድ የፋሽስት ባለስልጣን << አርበኞችን ከረዳሽ እንግዲያ እኛን አትወጅማ ፤ >> ሲል ኃይለኛ ጥያቄ ቢያቀርብላቸው ታላቋ አርበኛ ወ/ሮ ሸዋረገድ ያላንዳች ፍርሃት << አዎ አልወዳችሁም ፤ ማን ነው የአገሩን ደመኛ የሚወድ ? >> ሲሉ እንደገና ጥያቄውን በጥያቄ መልሰውለታል ።

ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ልጅ ባለመውዳድቸው እናዝናለን ፤ ግን ሰው ሰሙን ሊያስነሳውና ሊያስረሳው የሚችለው በመውለድና ባለመውለድ አይደለም ። የተወለደው የተባረከና ቁም ነገረኛ ካልሆነ ቢወለድም እንዳልተወለደ ነው የሚቆጠረው ። እንዲያውም አንድ አንድ ልጆች በጀግንነትም በቁም ነገረኛነትም ሙያቢስ እየሆኑ ዘር ከሚያሰድቡ ክርስቶስ ይሁዳን ሰው ባይወልድ ይሻለው ነበር ሲል እንደተናገረው እነሱም ያልሆነ ልጅ ወልደው አሳድገው ስማቸውን በከንቱ ከሚያስነሱት መካን ሆነው በቀሩ በተሻላቸው ነበር ። እንግዲያስ የሰው ስም ሕያው ሆኖ ሊኖር የሚችለው ከመውለድ ይልቅ በጥሩ ሥራው ነው ። ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድም የልጅ መካን ቢሆኑም የታሪክ እናት በመሆናቸው ስማቸው በጀግንነት ታሪክ ውስጥ ለሰለዓለሙ ሕያው ሆኖ ይኖራል ።

ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ለአባታቸው ሴት ልጅ ናቸው ። ግን ሴትነታቸው ወንድነት ሙያ ከመፈፀም ሊያግዳቸው ባለመቻሉ የአባታቸውን ሰም ለማስጠራት ወንዶች አልቀደሟቸውም ።

ቀሪን ገረመው
የአርበኞች ታሪክ የተወሰደ !

“ወደ ትጥቅ ትግሉ የገባሁት እንደ ኢትዮጵያዊነቴና ለመላው ኢትዮጵያዊ እንጂ እንደ ህውሃት የጠበበ የዘር ፓለቲካ አንግቤ አይደለም” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

$
0
0

ዘርይሁን ሹመቴ

ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር በቀጥታ በኔት ወርክ በ46 የአለማችን ከተሞች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ንግግር ማድረጋቸውና ለቀረበላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ መስጥታቸው ታወቀ።

ከሊቀመንበሩ በተጨማሪም በበርሃ ለነጻነት የሚታገሉ አርበኞችም የትግሉን መንፈስ ፣ ትግሉን ፍሬያማ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ቁርጠኝነትና ርብርቦሽ ከበረሃ በቪዲዮ የተቀረጸ መልክታቸውን ለተሰብሳቢዎች ማስተላለፋቸውንም መገንዘብ ተችሏል ።

ይህ በአይነቱ አዲስና ለየት ያለ ቁጥራቸው የበዛ በተለያዩ የአለም ክፍል የሚገኙ ከተሞችን በኔት ወርክ በቀጥታ በማገናኘት የተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በተሳካ መልኩ እንደተጠናቀቀ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

የንቅናቄው ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተለያዩ ከተሞች ይህንን ህዝባዊ ስብሰባ ከተካፈሉት ኢትዮጵያውያን የቀረበላቸውን ወቅታዊ ጥያቄዎች ረዘም ያለ ሰአት በመውሰድ  ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በስብሰባው የተካፈሉት ኢትዮጵያውያን ከዚህ በፊት እንደዚህ ያለ በቁጥር በዛ ያሉ ከተሞችን በተመሳሳይ ሰአት ያካተተ ስኬታማ ስብሰባ አድርገው እንደማያውቁ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ተሰምተዋል።

ወደ ትጥቅ ትግሉ የገባሁት እንደ ኢትዮጵያዊነቴና ለመላው ኢትዮጵያዊ እንጂ እንደ ህውሃት የጠበበ የዘር ፓለቲካ አንግቤ አይደለም በማለት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ታዳሚዎችን በአድናቆት የማረከ ንግግር ሲያደርጉ ተደምጠዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተጨማሪም አገር የምትገነባው በሆደ ሰፊነት እንጂ በጠባብና በትእቢት አካሄድ እንዳልሆነ በቀጥታ ለሚከታተሉዎቸው ታዳሚዎች አስረድተዋል።

እሳቸው የሚመሩት ድርጅት የዘር ኩታን መሰረት በማድረግ የተዋቀረ እንዳልሆነ የተናገሩት ፕሮፌሰሩ ድርጅቱን ለመቀላቀል ዋንኛውና ድርድር የሌለው መስፈርት የሆነው ኢትዮጵያዊ መሆንና ኢትዮጵያ የሁላችን እንደሆነች መስማማት እንደሆነም አረጋግጠዋል።

የድርጅቱ በተለያዩ የስራ ሃላፊነት የሚገኙ አመራሮችም ከታዳሚዎች ጋር በመሆን የሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ቀጥታ የጥያቄና መልስ ዝግጅት በተጋባዥነት እንደተከታተሉና ተጨማሪ ማብራሪያዎች እንደሰጡም ሪፓርቶች አመልክተዋል።

በተለያየ አገራትና ከተሞች የታደሙት ተሰብሳቢዎች የወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ የተጀመረውን የነጻነት አርበኞች ቁርጠኛና እልህ አስጨራሽ ትግል ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።

ሁሉም ከተሞች በእያንዳንዱ ከተማ እየተደረገ ያለውን የጨረታና የገቢ ማሰባሰቢያዎች በቀጥታ የኔት ወርክ ዘዴ በስክሪን እንዲከታተሉ የተደረገው ጥረት ስኬታማ እንደነበረም ተገልጻል ።

የገቢ ማሰባሰቢያ ጨረታው በአንድ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተገኙ ታዳሚዎች መካከል ከመሆን አልፎ በበተለያዩ የአለም ከተሞች በሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል በሚያስደንቅ የፉክክር መንፈስ በስኬት መደረጉ በርግጥም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅታዊ መዋቅሩ እጅግ ጠንካራ እንደሆነ ያሳየ ነበር።

የድርጅቱ በድስፕሊን መብሰል ፣ በትጋት ለአንድ አላማ በጸናት መቆምና ወጥ የሆነ ድርጅታዊ አሰራር ሂደት ይህንን ከዚህ በፊት ተተግብሮ የማይታወቀውን በተለያዩ የአለም አገራት ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በተመሳሳይ ሰአት ያሳተፈ ስኬታማ ህዝባዊ ስብሰባ እንዲደረግ እንዳስቻለው የዝግጅቱ ግብረ ሃይል ገልጸዋል።

የፊንፊኔ ደላላ – ሀብታም ጋቢ ተከናንቧል! ገንዘብ በአገሩ ጠፍቷል! (ዋዜማ ራዲዮ)

$
0
0

26ኛው ዙር ወጥቷል!    ሀብታም ጋቢ ተከናንቧል!   ገንዘብ በአገሩ ጠፍቷል!

ጤና ይስጥልኝ ጌታዬ!

ገረመው እባላለሁ፡፡ እሳት የላስኩ የፊንፊኔ ደላላ ነኝ፡፡  ምስጉን ‹‹ጉዳይ ገዳይ›› ስለመሆኔ እግዜርም ሰይጣንም ያውቃሉ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ መሆኔን ድሪባም ኩማም ያውቃሉ፡፡

ዉሎና አዳሬ ‹‹ብሔራዊ››፣ ጠባዬ የባሕታዊ፣ ‹‹ላየን ባር›› ቤቴ፣ ‹‹ቴሌ ባር›› ግዛቴ…፡፡

ጥሎብኝ አልረጋም፡፡ ካዛንቺስ ነው ሲሉኝ ሳሪስ፣ ቀበና ነው ሲሉኝ ባምቢስ…ሄሄሄ የዛሬ ደላላ ምን ቀልብ አለው ብለው ነው!!

እርስዎ ግን እንዴት ነዎት?

ቢዝነስ ጥሩ እንዳይደለ አይንገሩኝ ጌታዬ! አውቀዋለሁ፡፡ ሥራ ጠፋ አይበሉኝ፣ እረዳለሁ፡፡ እርስዎ ጋ ብቻ አይደለም! ሁሉም ጋ ነው፡፡ እውነት ለመናገር አስደንጋጭ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ነው ፊንፊኔን የገጠማት፡፡ ዜና ስለማይከታተሉ ነው እንጂ ይህ ነገር በተቀረው ዓለም አዲስ አይደለም፡፡ እንኳን ፊንፊኔን ግሪክም ይሄ ነገር ገጥሟት ያውቃል፡፡ እርስዎ ጋዜጣ ስለማያነቡ ይሆናል ያላወቁት፡፡ ይቅርታ ያርጉልኝና እርስዎ ገንዘብ እንጂ ዜና መቼ ይከታተሉና፤ ለዚያ ይሆናል ያልሰሙት፡፡

በብዙ አገር ኢኮኖሚ ላሽቆ ያውቃል፡፡ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በፊንፊኔም የኾነው ይኸው ነው፣ ሌላ አይደለም፡፡

ልንገርዎታ!

ለምሳሌ የካልዲሷ ወይዘሮ ፀደይ አስራት የአራት ኪሎ ቅርንጫፏን ዘግታለች፡፡ አብዛኛው ካልዲስ አፉን ከፍቶ ነው የሚዉለው፡፡ ሥራ የለማ! ሸዋ ዳቦዎች የኢሊያና ሆቴሉን ቢሎስ ኬክ ቤት ድርግም አርገው ዘግተዋል፡፡ ገበያ የለማ! አሁን ኬኩን ትተው ዳቦውን በጥሞና እየሸጡት ይገኛሉ፡፡ እውነቴን ነው!

ደሞ ልንገርዎ!

ይሄ ጌቱ ገለቴ ዱባይ ከኢሚሮች ጋ በዉስኪ ቢራጭ አይግረምዎ! የጌቱ ኮሜርሻል ተከራዮች በገበያ እጦት በአሁን ሰዓት በእንባ እየተራጩ ነው የሚገኙት፡፡ የመገናኛው ዘፍመሽ ላይ ዝር የሚል ወፍ ጠፍቷል፡፡ ደንበል እንዲሁ ጧት ይከፈታል፣ ማታ ይዘጋል፡፡ የመርካቶ ነጋዴዎች አይሱዙ ላይ እቃ የሚያስጭን ነጋዴ ቢጠፋባቸው ስልካቸው ላይ ጌም እያስጫኑ ነው፡፡ ሥራ የለማ! እያዛጉ እስክስታ ሆኗል እኮ ነገሩ፡፡

ከሁሉም ከሁሉም ባንኮች አንጀት ይበላሉ፡፡ ደንበኞቻቸው ጋር እየደወሉ ገንዘብ አስቀምጡ ይላሉ፡፡ በሌለ ገንዘብ፡፡ ጉም በኾነ ገንዘብ፡፡

ጌታዬ! ዛሬ እንኳን ያበደሩት ይቅርና ካርድ ያጎረሱት ኤቲኤም ማሽን ብር መስጠት አቁሞ የለም እንዴ!! በፊት በፊት No network ነበር የሚለው፡፡ አሁን አሁን No Money ማለት ጀምሯል፡፡

ፊንፊኔ እኮ ተቀዛቅዛ ተቀዛቅዛ የጎርደን በረዶ ኾናለች፡፡ ብር የገባበት አልታወቀም፡፡

የሚገርም ጊዜ ነው!! ሀብታሙ ከድሀው እኩል የሚያለቅስበት ጊዜ ላይ ደረሰናል፡፡

ለምሳሌ የኔ ደንበኞች በሙሉ ንብረት አላቸው፡፡ ብር ግን የላቸውም፡፡ ሁሉም ንብረታቸውን ወደ ብርእንድቀይርላቸው ይማጸኑኛል፡፡ ያልተረዱኝ ግን በአሁኑ ሰዓት በፊንፊኔ ሁሉም ገዢ ወደ ሻጭነት መቀየሩን ነው፡፡አሃ! ሰው ሁሉ ሻጭ ከሆነ ገዢው ማን ሊሆን ይችላል?

ለምሳሌ ባልደራስ ሦስት መኝታ ኮንዶሚንየም አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ከሸጥኩ ሦሰት ወር አልሞላኝም፡፡ አሁን በስምንት መቶ ሺ ጥንቡን ጥሏል፡፡ ለምሳሌ ሲኤምሲ አንድ ቅልብጭ ቪላ 6 ሚሊዮን ያወጣ ነበር፡፡ አሁን አምስት የሚቆጥር ጠፋ፡፡

አትላስ መደዳ አስፋልት የሚያዩ ባዶ ቦታዎች በሙሉ በ25 ሚሊዮን የቸበቸብኳቸው እኔ ገረመው ነኝ፡፡ ዛሬ በ20 ሚሊዮንም ዞር ብሎ የሚያያቸው ጠፍቷል፡፡ የአቶ የማነ ካፒታል ሆቴል ይሸጣል! የፊንፊኔ አብዛኛው ጅምር ፎቅ ይሸጣል፡፡ ማን ይግዛው!!

አያት ሪልስቴት ቤት ገዢ አጥቶ ልመና ገብቷል፡፡ እንዳውም በአሁኑ ሰዓት ያልተገነባ ሪልስቴት በነጻም ዉድ ነው እየተባለ ነው፡፡ የሚገርም ነገር እኮ ነው የኾነው!

በገጠር አምስት ሚሊዮን ወገን ድርቅ መታው ይባላል፡፡ የከተማውን ማን አየ!! ለሐብታም ረሐብ ማለት የሚላስ ዳቦ ማጣት እንዳይመስልዎ! የገበያ ድርቅ ከመታው ማንኛውም ሐብታም ይቆረፍዳል፤ ይቆራመዳል፣ ይጃጃል፣ ይፋጃል፡፡ 

በዚህ መሐል ነው እንግዲህ ኦቦ ድሪባ ኩባ ጨረታ ያወጡት፡፡ አልሰሙም ይሆናል ጌታዬ! 26ኛው ሊዝ የመሬት ጨረታ ወጥቷል እኮ! እና ምን ይጠበስ ነው ያሉኝ??

የደወልኩላቸው ደንበኞቼ ሁሉ እንዲያ ነው ያሉኝ፡፡ የሊዝ ጨረታ መዉጣቱን ስነግራቸው ጆሮዬ ላይ ስልክ የዘጉብኝ አሉ፡፡ አሃ ልክ ነዋ! አይፈረድባቸውም፡፡ አልተቀየምኳቸውም፡፡ በዚህ ሰዓት ገዢ መሆን የሚፈልግ ማን አለ!! እንኳን ቤት መሬቱ የባህር ትራንዚቱ ለገበያ ቀርቦ የለም እንዴ!!!!

ጌታዬ!!

በሳምንት ሦስት ጊዜ መታተም የጀመረው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ማክሰኞ ለታ 176 ኪስ ቦታዎች ለገበያ መቅረባቸውን በፊት ገጹ ያበስራል፡፡ ለኔ ግን መርዶ ነው፡፡ ለደንበኞቼም እንዲሁ፡፡ በዚህ ሰዓት ማን ነው ገንዘቡን በትኖ መሬት የሚቀራመት፡፡

እኔ ግን 26ኛ ዙር ጨረታ ወጣ ቢሉኝ ጥያቄ አለኝ እልኩኝ፡፡ ለኦቦ ድሪባ!! የ25ኛው ዙር መቼ ተሸጠና፣ ለ24ኛ ዙር ማን ከፈለና፡፡ አዳሜ ይሄን ገንዘብ በጨረታ ፎርም ሞጅራ ሞጅራ ክፈል ስትባል አይደለም እንዴ ፈሷን ጥላ የጠፋችው!! ፎርም ላይ ብዙ ዜሮ መጻፍ ቀላል ነው፡፡ ቼክ ላይ ነው ከባድ፡፡

እርስዎ ግን እንዴት ነዎት ጌታዬ!!

ትዝ ይልዎ እንደሁ ባለፈው ጊዜ በአሜሪካን ግቢ ጉድ ተሰምቶ ነበር፡፡ ጣሊያን ወርቅ ቀብሮ የተሰወረ እስኪመስለን ድረስ ለቁራሽ መሬት ሚሊዮን ሲከሰከስ ነበር፡፡ ያ ለካሬ 355ሺ 500 ብር ሰጥቶ አገር ጉድ ሲያሰኝ የነበረው ጋርደን ሪልስቴት አሁን የገባበት አልታወቀም፡፡ እውነቴን ነው!! ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው አራት መቶ ሺህ ብርም ቀልጧል፡፡ ቦታውም ለድጋሚ ጨረታ ቀርቧል፡፡

ጋርድን ሪልስቴት ብቻ መሰልዎ እንዴ እምጥ ይሁን ስምጥ የገባበት ያልታወቀ?? ኸረ ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ከርሱ ጎረቤት እንጅሎፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ለ964 ካሬ ቦታ ለአንዲት ካሬ 311ሺህ 500 ብር አቅርቦ አሸንፎም ነበር፡፡ ዉሰድ ሲባል ግን ጠፋ፡፡ ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው 3መቶ ሺህ ብር ቀልጧል፡፡ ቦታው ለድጋሚ ጨረታ ቀርቧል፡፡ 

እዛው ሰፈር አቶ ሙዘሚል መሐመድ አሕመድ ለ343 ካሬ ቁራሽ መሬት ያቀረቡት ዋጋ አነጋጋሪ ኾኖ ነበር፡፡ ቦታው አሜሪካ ግቢ የሚገኝ ቢኾንም አሜሪካን አገር የሚገኙት የአቶ ሙዘሚል ዘመዶች ሳይቀሩ ሰውየውን “አብደዋል ወይ!፣ እዚህ እኛ አገር እንኳ ለመሬት እንዲህ ውድ ብር አይቀርብም” ብለው ስለኮነኗቸው ያስያዙትን መቶ ሺ ብር ቀልጧል፡፡ ቦታውም ለድጋሚ ጨረታ ቀርቧል፡፡

ጌታዬ! ያ የእብደት ዘመን ያበቃ ይመስላል፡፡ አሁን ሌላ ታሪክ የምንሰማበት ወቅት ነው የሚኾነው፡፡

ከትናንት በስቲያ ከአስሩ ክፍለ ከተሞች ሰባቱ መሬት አቅርበዋል፣ በርከት ያለ መሬት ነው ታዲያ! በድምሩ 176 ቦታዎች ገበያ አልወጡም ብለው ነው?!

በንፋስ ስልክ ላፍቶ 18 ቦታዎች፣ በቦሌ ወረዳ 9 እና 10 አያትና ጎሩ እንዲሁም ቦሌ ለሚ አካባቢ የሚገኙ 94 ቦታዎች፣ በኮልፌ ወረዳ 7 እና ወረዳ 3  የሚገኙ 23 ቦታዎች፣ በየካ ወረዳ 1 እና ወረዳ 3 የሚገኙ ስፋታቸው 150 ካሬ የሆኑ  ዘጠኝ ቦታዎች፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድና ወረዳ 10 የሚገኙ 13 ቦታዎች፣ በቂርቆስ አፍሪካ ኅብረትን የሚጎራበቱና ስፋታቸው 1300 ካሬ የሚኾኑ ሁለት ቦታዎች፣ በልደታ ወረዳ 10 የሚገኙ ስፋታቸው አንድ ሺ ካሬ የሚሆኑ 2 ቦታዎች፣ በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 4 እና ወረዳ 9 ገላን ኮንዶሚንየም አካባቢ የሚገኙ 13 ቦታዎች ለገበያ ቀርበዋል፡፡

መሬት እንዲህ እንዳሁኑ በርከት ብሎ እንደ ቲማቲም ለገበያ ሲቀርብ ይረክሳል ብለን እንጠብቃለን፡፡ ቸር ወሬ ያሰማን!

ደጋግሜ እንደነገርክዎ እኔ ገረመው በፊንፊኔ መሬት ጥርሴን ነቅያለሁ፡፡ አሁን ግን ሥራ አጥቻለሁ፡፡ ሥራ ያጣ ቄስ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል፡፡ ሥራ ያጣ ደላላ ምን ያደርጋል?

ጌታዬ! በኔ በኩል ስንቅ መቋጠር ቢያቅተኝ ስንኝ እቋጥራለሁ፡፡ ለዚህ ክፉ ዘመን ብቀኝ ማን ምን ይለኛል!!

ንብረት ጥንቡል ጣለ፡፡

ሻጭም ጨርቁን ጣለ፡፡

ገንዘብ የት ነህ ቢሉት ጉም ኾኛለሁ አለ!

ገረመው ገረመው ለምን ትለኛለህ!

ገንዘብ ያልገረመው የት አይተህ ታውቃለህ፡፡

ደላላው ደላላው ለምን ትለኛለህ

ገንዘብ ያልደለለው ማን አይተህ ታውቃለህ!

ጌታዬ! እንደኔ የሚደለል ጠፍቶ የሰው ፊት ከማየት ይሰውርዎ!!!

ገረመው ግዛው ነኝ (ከላየን ባር)

ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ በፅኑ ህመም ሆስፒታል ናቸው

$
0
0

Home Home ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ በፅኑ ህመም ሆስፒታል ናቸው
ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ

ዋዜማ ራዲዮ- ከኢትዮጵያ አንጋፋ ምሁራን አንዱ የሆኑትና በተለያየ ሀላፊነት መንግስትን ያገለገሉት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ በፅኑ ታመው በሆስፒታል አልጋ ላይ እንደሚገኙ የዋዜማ ምንጮች ተናግረዋል።
ፕሮፌስር አንድርያስ ስሞኑን ያረፉት የወዳጃቸው የዶር ገብሩ መርሻ ሞት አልተነገራቸውም።
በተማሪ ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ የነበሩትና በብሄር መብት ጉዳይ ተሟጋችነታቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር አንድርያስ የአንድ ልጅ አባት ናቸው። ከሽግግር ዘመን ጀምሮ ለገዥው ፓርቲ ህገ መንግስት በማርቀቅና በማማከር ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት ፕሮፌሰር አንድርያስ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መምህርና ፕሬዝዳንትም ሆነው አገልግለዋል። በቅርብ አመታትም የሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አማካሪ ሆነው ሲሰሩ ነበር።
በፖለቲካ አቋማቸው ቀላል የማይባል ውግዘት የሚቀርብባቸው ፕሮፌሰር አንድርያስ ላመኑበት አላማ በመቆም ፅናታቸው ምስጋናም አላጡም። በምሁራዊ ብቃታቸውም አንቱታን አግኝተዋል። ፕሮፌሰር አንድርያስ ከዚህ ቀደም ከገጠማቸው ብርቱ ህመም ውጪ ሀገር ሄደው በመታከም ማገገማቸው ይታወሳል። አብዝተው ሲጋራ በማጨስ የሚታወቁት አንድርያስ ያለፉትን ወራት በተደጋጋሚ ሲታመሙ እንደነበርና ያሁኑ ግን ጠንከር ያለ መሆኑን የቅርብ ወዳጆቻቸው ይናገራሉ።

አስደንጋጭ ዜና፤….በደብረ ታቦር ከተማ በ6 ወር ውስጥ 112 ሰዎች ተገድለው ተገኝተዋል፤ – ሙሉቀን ተስፋው

$
0
0
ሙሉቀን ተስፋው

ሙሉቀን ተስፋው

በከተማ አስተደደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት ውስጥ ሾልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ማንነታቸው ያልታወቁ 112 ሰዎች በጥይትና በድብደባ ተገድለው ተገኝተዋል፡፡ ከዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ ደብረ ታቦር ምድብ እና የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት ካሉ ሠራተኞች ማረጋገጥ እንደተቻለው በርካታ ሰዎች በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ተገድለው ተገኝተዋል፡፡ መረጃውን የሰጡን የፖሊስ አባላት ‹‹ከዚህም ቀደም አፍልፎ አልፎ ሰዎች ሞተው የሚገኙ ቢሆንም ሕዝባዊ ተጋድሎው ከተጀመረበት ከነሐሴ ወር ወዲህ ግን የሚገደሉ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ በሆነ መልኩ ጨምሯል›› ብለዋል፡፡

አብዛኛዎቹ ሟቾች የተገደሉት በጥይት እንደሆነ የሚያመልከተው መረጃ አስከሬኖች ከሌላ ቦታ ተገድለው መንገድ ላይ ሊጣሉ እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡ የሟቾችን ማንነት ለመለየት የሚያስችል መታወቂያም ሆነ ማንኛውም ዓይነት መረጃ ስለማይኖር የሟቾችን ማንነት መለየት አልተቻለም ተብሏል፡፡ የተገደሉበትን ምክንያት ለማወቅ የሚደረግ የአሻራና የአስከሬን ምርመራም ተደርጎ እንደማያውቅ ነው የተነገረው፡፡

በአጅባር፣ ሐሙስ ገበያ፣ ሰኞ ገበያ፣ ታቦር፣ አይጋጥ፣ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ፣ አባ በላይ ውኃ የመሳሰሉ ሰፈሮች አስከሬን በሌሊት ተጥሎ ከሚገኝባቸው ሰፈሮች ዋነኛዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡ አስከሬኖቹ የማይታወቁ ከሆነ ከየት እንደመጡና በማን እንደተገደሉ ግምታቸውን ሲያስቀምጡ ‹‹ምናልባት ከጎጃም ወይም ከሰሜን ጎንደር ራቅ ካሉ አካባቢዎች ታስረው በደኅንነት ወይም በኮማንድ ፖስት ተገድለው ማንነታቸውን አጥፍተው ጥለዋቸው ሊሆን ይችላል›› ብለዋል፡፡

በመንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ባልሆኑ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ለማጣራት ምንም ሙከራ ያልተደረገ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ የሚነሳ አስከሬን እና የተበላሸ ሰውነት ሰላማቸውን እንደነሳቸው ጭምር የፖሊስ አባላቱ ገልጸዋል፡፡

6 ጠቃሚ ነጥቦች ከዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሃፍ: የጣናዉ ከምድረ አዉሮፓ – ምስጋና ለጸሃፊው !

$
0
0

በዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ የተጻፈዉ   “የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ”   መጽሃፍ  ሰውን ለሁለት ከፍሎ እያወያየ ና እያከራከረ ነው። ሂደቱም  ቀጣይነቱ የማይቀር

ነው።እኔም ባለፈው በፃፍኩት ጽሁፍ (ሃላፊንት የጎደለው ሞያዊ ያልሆነ ስራ በመረራስ አማን በላይ በዶ/ ፍቅሬ ቶሎሳ, http://www.zehabesha.com/amharic/archives/71138)፤ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሃፉን ለመጻፍ የተጠቀመበት ና በመረራስ አማን በላይ ተገኘ የተባለው ‘’ጥንታዊ’’ ብራና በእዉነት ካለ መመርመር አለበት ብየ  ከመሰረታዊ የጥናት ና ከምርምር ጽንሰ ሃሳብ በመነሳት ሃሳቤን ገልጫለሁ። ይህ ሃሳቤ  እንዳለ ሆኖ መጽሃፉን ሳነብ ይጠቅማሉ ያልኳቸዉን አቀርባለዉ። የጽሃፊዉ ሃሳብ ተቆርጦ እንዳይቀር ስል ሙሉ አንቀጾችን ከመጽሃፉ በቀጥታ እወስዳለዉ።

 

1-ኦሮሞኛን በላቲን ፊደላት ስለመጻፍ

 “…ለዘለቄታውም መታሰብ አለበት፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ ቁጥር በጣም በርካታ ስለሆነ ካናዳ ውስጥ እንግሊዝኛንና ፈረንሳይኛን የሥራ ቋንቋዎች አድርገው እንደሚሠሩባቸው በኢትዮጵያ ውስጥም ከአማርኛ ጎን ለጎን ኦሮምኛ ሁለተኛው የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋእንዲሆን ሊታሰብበት እና ጥቅምና ጉዳቱ በተጨባጭ እየተመዘነ፣ አዋጭነቱ በሳይንሳዊ መንገድ እየተጠና፤ አማርኛን እንደ ሁለተኛቋንቋቸው በተቀበሉ እንደ ደቡብ ክልል ባሉ ሕዝቦች ላይ ጭነት አለመሆኑም በደንብ አየተረጋገጠ በጥንቃቄ ሊመከርበት ይገባል፡፡ ይህ ጉዳይ ባንድ ቀን ጀንበር የሚፈጸም ሣይሆን አዲስ ቋንቋን ለመማር በቂ ጊዜ ስለሚያስፈልግ ዓመታት ሊወስድ ይችላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አሁን እጂግ አስፈላጊና አንገብጋቢ የሆነው የፊደሉ ጉዳይ ነው፡አሮሞ ያልሆኑ የቋንቋው ተናጋሪዎች በኦሮምኛ ለመጻፍ በላቲን ፊደል እንዲጠቀሙ ሊገደዱ ነው? ‘’ጊዜና ገንዘብ ከሚያባክነው ከላቲኑ ፊደል ይልቅ ቆጣቢ፣ ቀልጣፋና ምቹ በሆነውና በምናውቀው ባገራችን ፊደል እንጽፋለ’’ቢሉ  ምን ሊደረጉ ነውን ? በባእዳን ፊደል የሚጽፉ በቅኝ ገዢዎች ሲገዙ የነበሩና አማራጭ ያልነበራቸጡ ሕዝቦች ናቸው። እኛ በጀግኖች አባቶቻችን ደም እና አጥንት ነዓነታችን ተከብሮልን የኖርንና አኩሪ ቅርስ የሆነ የራሳችን ፊደል ያለን ሕዝቦች እንደነሱ ልንሆን አይገባምዘ ብለው ቢቃወሙ ምን ሊባሉ ነውን ¿ይህ መሠረታዊ ጥያቄ ባግባቡ መልስ ሊያገኝ እንጂ እንደ ዎዛ ሊታለፍ አይገባም፡፡……”

ይሄ  እጅግ ጠቃሚ መልእክት ነው።አማርኛ ከሌሎች ቋንቋወች የሚለየው በፊደላት ድምጽ ላይ መመስረቱ ነዉ።ይሄ ደግሞ በላቲን ፊደላት  ሲጻፉ  ብዙ ፊደላትን የሚፈልጉ ረጅም ቃላት በአጭሩ ለመጻፍ ያስችላል ።ኦሮሞኛም በላትን ፊደላት ሲጻፍ ደግሞ  ብዙ  የሚደጋገሙ ፊደላት ይበዛሉ። ይሄን ለይቶ ማወቅ ደግሞ ትልቅ ራስ ምታት፣ ሌላ ተጨማሪ የቤት ስራ ነው።በተለይ  ረጃጅም  የሳይንስ ና ቴክኖሎጅ ቃላትን እንጻፍ ከተባለ ደግሞ ሲጽፉ ዉሎ ማደር  የማይቀር ነው። በተዘዋዋሪ ባገራችን ፊደል መጠቀም የህትመት ወጭ ይቀንሳሉ።በእጅ ለመጻፍም ድካም ይቀንሳል።ጽሃፊዉ ይሄን በገጽ 104-109 ላይ በምሳሌ በደንብ  አስረድተዋል። ጽሃፊዉ በቃላት አላስቀመጡትም አንጅ  (ጽንሰ ሃሳቡን ገልጸዋል) ፤ የአማርኛ ፊደላትን ያወቀ ሁሉ የአማርኛ  ቃላትን ያልስተት  መጻፍ (ያለ spelling ስህተት) ና ማንበብ ይችላል ማለት ነው።ትልቅ ግልግል ነው።ስለዚህም ከቋንቋ አንጻር አማርኛ ማንበብ ና መጻፍ ለሚችሉ ኢትዮጵያዉያን ኦሮሞኛ በላቲን ከመማር ትግርኛ መማር አጅግ ይቀላል።ምክኒያቱም ያለምንም ጊዜ ማጥፋት ና ያለምንም ፈተና ቃላትን መጻፍ ና ማንበብ ይችላሉና።ቋንቋ እንደ ሸቀጥ ነዉ፣ገዥ ካልወደደዉ፣ከልተመቸዉ ግዛ ተብሎ አይገደድም።

2- ስለ ጡት መቁረጥ

“….የአዔ ምኒልክ ወታደሮች አብዛኞቹ ክርስትያኖች ነበሩ።ጡት መቁረጥ በሻሪያ የሚተዳደሩ የአረቦች ባህል እንጂ የኢትዮጵያውያን አይደለም፡፡ ስለዚህ ክርስትያኖች  የአዔ ምኒልክወታደሮች የገዛ የሀገራቸውን የተከበሩ ሴቶች ጡት ቆረጡ ማለት ፍጹም የፈጠራ ወሬ እና ለስሚው ግራ ነው። እኔ በአደረኩት ምርምር ይህን የሚያረጋግጥ አንድም ሰነድ አላገኘሁም፡፡ ርካሽ ጥላቻን ለመንዛት ይህን ለህዝብ ምንም ጥቅም የሌለውን ሃውልት የአቆሙት ፓለቲከኞች  ይልቅ ለሀዝባቸው የሚፈይዱ ፋብሪካዎች ቢያቆሙላቸው ከድህነት ይላቀቃሉ ይህን የጥላቻ ሃውልት ነቅለው ፋይዳ ያላቸው ፋብሪካዎች ለሀዝባቸው አንዲተክሉላቸው በዚህ አጋጣሚ አመክ ራቸዎለሁ፡፡ ሌላው ስለ አዔ ምኒሊክም የተነዛ ሃሰት 5 ሚልየን ኦሮሞዎችን ፊጁ የሚል ነው፡፡ ይሀም ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በዛ ጌዜ የነበረው ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግፋ 10 ማሊዎን የሚደርስ ነበር፡፡10 ማሊዎን ከተገደለ ምን ሰዉ ተረፈ? ደግሞስ ጀግናው የኦሮሞ ህዝብ ዝም ብሎ አንገቱን ለእርድ የሚጋብዝ ነበር እንዴ ቢያንስ በአልሞትፀባይ ተጋዳይነት አይዋጋም ነበር እንዴ?  የአሮም ህዝብ የማይበገር ጦረኛ እና ጀግና ስለነበር ተዋግቶ ለራሱ ይመክታል እንዲሁም ይገላል እንጂ በዝምታ እንደ በግ አይታረድም ነበር። ስለእዚህ የአፄ ምኒልክ ሰራዊት 5ሚሊዎን ኦሮሞዎች ፈጅተዎል የሚለው ወሬም ለርካሽ ፕሮፓጋንዳ የተተረተ ነው፡፡ ልክ እንደ የወላይታ ንጐሥሀ ጦና እና የከፋው ንጉስ ጋኪ ሼሮቾ ሰራዊቶች የሚኒልክን መስፋፋት በመቃወም የተቃወሙት ኦሮሞዎች ላይ ግድያ መፌፀሙ  እሙን ቢሆንም 5ሚሊዎኖች ተገደለ ማለት ወሰን የሌለው አጋኖ ነዉ፡፡…”

ጭንቅላት ያለዉ ስዉ መቸም ይሄን የዉሸት ዉንጀላ ይቀበላል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። 5 ሚልየን ሰው ለመግደል ፤  ሚኒልክ ስንት ሚሊየን ወታደር ነበረው? ምን አይነት ዘመናዊ መሳሪያ  ነበረው?። ጦርነቱስ ለስንት አስርት ወይም መቶ  አመታት በካሄድ ነዉ? ብሎ መጠየቅ ያስፈሊጋል።ሰው ደግሞ ከባህሉ ዉጭ ድርጊት አይፈጽምም።በጭንቅላቱ ዉስጥ የሌለን ነገር ከየት ያመጣዋ።። ለምሳሌ አይሁድ ሰውን በመስቀል ላይ የመስቀ ባህል ነበራቸዉ። እየሱስንም በዛው ባህላቸው ሰቅሉት። በኢትዮጵያ ባህን ጡት መቁረጥ በየትኛዉን ባህል የሌሌና የልተመዘገበ ነዉ።ታዲያ ሚኒልክ ከየት ያመጣዋል? ክርስቲያኑ ሚኒልክ  ቁጭ ብለው  አስበዉ ና አውርደዉ ይሄን ፈጠሩቱ ማለት እብደት ነው።

3- አማራ

“….በአዲሱ የኦሮምያ ፖለቲካ ካርታ መሰረት ጎጃምና ጎንደር ብቻ ናቸው ለአማራ የተወሰኑት፡፡ አማሮች በመላ አገሪቱ ስለሚኖሩ ሰፋ ያለ ምርጫ ተሰጣቸዉ  በነዚህ በሁለቱ አካባቢዎች ብቻ ራሳቸውን የሚገድቡ አይመስለኝም፡፡ መላዋ ኢትዮጵያ የኛ ናት ብለው ነው አማሮቸ የሚያስቡት፡፡ ምክንያቱም ባለፉት 3ዐዐዐ ዓመታት  ውስጥ በውትድርና ሙያቸው መንግሥታትን ሲጠብቁ አና የአገሪቱን ዳር ድንበርና የግዛት አንድነት ሲያስከብሩ ጠንካራ የኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ስሜት ገንብተዋል። ለኢትዮጵያ ሀገርነት መኖር ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን የፊዐሙት ታላቅ ጀብድ አንደ ተጠበቀ ሆኖ፥ ስለእውነት ብለን እውነት ብንናገር በኢትዮጵያ ነጻነት ሳይ አማሮች የመሪነት ሚና ባይጫወቱ ኖሮ ቅኝ ገዢዋ ጣልያን ኢትዮጵያን በቀላሉ ድል አድርጋ ለመያዝ በቻለች ነበር፡፡ የዚህም ምስክሩ ጣልያን ናት፡፡ የአማራን ወሳኝ ሚና በመረዳትዋ ጣልያን ከሁሉም በፊት አማራንና ተዋሕዶ ሃይማኖታቸውን ነበር ለማጥፋት የተነሳችዉ፡፡ አማሮች ከተበታተኑ ኢትዮጵያም እንደምትበታተን ጣልያኖች በሚገባ ያውቁ ነበር፡፡ ኢትዮጵያን አዳክመዉ ለመቆጣጠር የሚሹ ከባህር ማዶ የመጡም ሆኑ የውስጥ ኃይሎች ሁሉ ይህንኑ አድርገዋል። የአማራ ጠላት የበዛውም ለዚሁ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን የኦሮሞ አርበኞች እና ሌሎችም ነፃነት ወዳድ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ለመጠበቅ ያደረጉትን የጀግንነት ተጋድሎ ማሳነስ አይደለም፡፡…..”

ጠላቶቻችን እንኳን የጥንካሬ መሰረታችን ወይም ምሰሶ የትላይ አንዳለ አውቀው በተዘዋዋሪ እየነገሩን ነዉ፡፡ይሄን  በቁጥር የሚያረጋግጥ በፕ/ር መስፍን ወልደ ማሪያም “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” መጽሃፍ  ገጽ 129  ላይ ሰፍሮ ይገኛል።ፕ/ር መስፍን  መረጃዉን የወሰዱት ከጣሊያናዊዉ የታሪክ ጸሃፊ አልበርቶ  ሳባኪ (Ethiopia under Mussolini የሚለዉን መጽሃፍ   የጻፈ) ነው ።የጣሊያኖች የአርበኞች ቁጥር ስርጭት ግምት ከታች ባለው ሰንጠረዥ ሰፍሯል።  ከሰንጠረዡ አንደምናየዉ ከሆነ ጣሊያኖች በጎጃም ና በበጌምድር  ላይ  የጠበቁት የአርበኞች ቁጥር (95,500) ከቀሪው (23,850) በ4 እጥፍ ይበልጣል፡፡  ይሄ ያስመሰግናል እንጅ  እንዴት ያስወቅሳል? በጋራ የሰራዉን ቤት ምሰሶ አፍርሶ ቤት ይኖረኛል ብሎ የሚያስብ አላዋቂ ብቻ ነው።  ይደክማል ደግሞ አንጅ ምሰሶዉም አይፈርስም።ሩቅ ሳንሄድ ወያኔ 25 አመት ለፍቶ አልቻለም።ቢሆን ኖሮ  ድሮ ድሮ ይፈርስ ነበር።

4- ስለ ቋንቋ እና የባህል  ተዕኖን

“…የቋንቋ እና የባህል ተዕኖን በተመለከተ እውነቱን ለመናገር አማራው ኃይልን ወይም ሕግን ተጠቅሞ ቋንቋውን እና ባሕሉን አማራ ባልሆኑ ላይ ፈጽሞ በግድ አልጫነም፡፡ ቢፈልግ እንኳ እንዲህ ዓይነት  ተፅእኖ ለማሳደር የሚያስችል የመንግሥት ሥልጣንም እማራው ይዞ አያውቅም። ከሁሉም በላይ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ተፅዕኖ ማሳደር ተፈጥሮአዊ ባሕሪው አይደለም፡፡ ቋንቋውንና ባሕሉን ሌሎች የተጠቀሙበት በፈቃዳቸው ነው እንጂ በግድ አይደለም።…..”

እዚህ ላይ  አንድ ነግር ላንሳ። አንድ አንዶች ኢትዮጲያዊነት ሳንፈልግ ተጭኖብን ኖረናል ብለዉ ያላዝናሉ። አንግዲህ የኢትዮጲያዊነት በህላችን መገለጫ አንዱ ሁላችን የሚያግባባን አማርኛ ቋንቋ ነዉ። ክርስትና ና እስልምናም  መሰረታቸዉ ኢትዮጵያ ነዉ (ክርስትና አምነትን በሃገር ደረጃ የተቀበለች የመጀመሪያ ሃገር  ናት።ታላቁን ነብይ ሙሴ የተማረዉ ና ሚስቱን ያገኘዉ  ኢትዮጵያ ነዉ ። የነብዮ ሙሃመድ ተክታዮችን ተቀብላ እርዳታ በማረግ  እሰለምና እንደስፋፋ ያረገቸ  ሃገር ኢትዮጲያ ናት )።የሚገርመው አነዚህ ሰወች ኢትዮጲያዊነት ሳንፈልግ ተጭኖብን  ብለዉ የሚጽፉት፣ በራዲዮ ና ቴሌቪዥን ቀርበዉ የሚያማርሩት በዛው በአማርኛ ቋንቋ ነዉ። አብዛኖቹም የሚኖሩት በዉጭ ነዉ ፤  በእዉነት  ተጭኖባቸዉ ከሆነ አማርኛን አሁን አርግፍ አርገዉ ለምን አይጥሉትም ? ክርስትና ና እስልምናም ትተዉ ቡዲዝም፣ ሂንዱዝም ና ሌላዉን እምነት ለምን አይዙም?

ነገር ነገር ያነሳዋል ነዉ ና አንድ ነገር  ልጨምር። ነፍሱን ይማርና ታላቁ ደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር አንዲት የመጽሃፉ አንባቢ የሆነች ሴት ’’ያንተን መጽሃፎች ደግሜ ደጋግሜ ባነባቸዉም አልገባኝ አሉ።ምን ይሻለኛል?’’ ብላ ጠየቀችዉ።አሱም ሲመልስ ‘’ቆንጅት የማን ነሸ አራዳ፣ደግመሽ ደጋግመሽ መጽሃፎቸን የምታነቢያቸው ቢገባሽ፣ቢጥምሽ ነው።አንዲያ ባይሆን ኖሮ አንዴ አንበሽ ካልገባሽ ትጥያቸው ነበር’’ አላት። አሁንም ኢትዮጲያዊነት ሳንፈልግ ተጭኖብና ብለዉ፣ አማርኛ አስከ አሁን የሚጠቀሙት ተጭኖባቸዉ ሳይሆን ቢመቻቸዉ፣ ቢጥማቸዉ፣ቢጠቅማቸዉ ነዉ። መሰረታቸዉ ኢትዮጲያ የሆኑትን  ክርስትና ና እስልምናም የሚከትሉት ለገነት ያበቁናል ብለው ሰለሚያምኑ አንጅ በእዉነት ተጭኖባቸው አይደለም።

5-ስለ ስም መቀየር

“…በአዲስ አበባና በትልልቅ ከተሞች፣ በትምህርት ቤቶችና በሥራው ዐለም ተቀባይነት ለማግኘት ብለው ወላጆቻቸው ያወጡላቸውን ስሞች ወደበቆንጆ”  የአማርኛ ስሞች የለወጡ ሰዎች አሉ፡፡ አነዚሀ ደግሞ ኦሮሞዎችና የደቡብ ሀዝቦች ብቻ ሳይሆኑ ራሳቸው አማሮችም ጭምር ናቸው። እላይ በተባሉት ምክንቶች አማሮች ሳይቀሩ ስሞቻቸውን ይለውጡ እንደነበር ዐይነተኛ ምሳሌ የሚሆኑት አሁን በባህር ማዶ የሚኖሩመንኒ አቶ ለይኩን ቤተሰቦች ናቸው። ተሪካቸጡም ዕውነተኛ ነው፡፡ 1933ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን ከለቀቀች በኋላ የአርበኛው የአቶ ወልደጻድቅ ክብረት ቤተሰቦች ከመራቤቴ ወደ አዲስ አበባ አመሩ። ስሞቻቸውም <<ዳባሽ>> <<ባፈና>> እና <<ሺናባቸው>> ነበሩ፡፡ እነዚህን ስሞች የሰሙ የአዲስ አበባ ሰዎችም በጣም እየሳቁባቸው ስለቀለዱባቸው ስሞቻቸውን ለመለወጥ  ተገደዱ። ስለዚህም <<የውብዳር>> <<ኮከብ>> እና <<ወርቁ>> ተባሉ። የአቶ ለይኩን ሌላ ዘመድ በመንዝ ይኖሩ ነበር፡፡ ስማቸው <<ነቅንቄ ጎንጤ>> ነበር። ይህ ስም በአዲስ አበባ መሳቂያ ስለሆነ የራሳቸውንም፣ ይባስ ብለው የአባታቸውንም ስም ለወጡት በስዋሰው ክብረትዘ ሲሉ፡፡ የጎጃምና የጎንደር አማሮችም ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ እንዲሁ ስማቸውን ይለውጡ ነበር፡፡ የእኚሁ የአቶ ለይኩን የጎጃምና ጎንደር ቤተዘመዶችም በአዲስ አበባ ከተማ ስማቸውን ለመቀየር ጫና ደርሶባቸው ነበር፡፡ ለምሳሌ የጎጄሜዎቹ ወይዘሮ <<ሰውበኒት>> እና <<ውጭ አደሩ>> ስሞቻቸው በአዲስ አበባ አሳፍረዋቸው <<ሰውነት>> እና <<ባንቺሀ>> ተብለዋል። ይሀም የሚጠቁመን ለቦታና ለሥራ እንዲያመች አቅዶ ስሞችን መለወጥ በኦሮሞዎች ብቻ የተጀመረ አይደለም፡፡በአማሮችም እንጂ፡፡ ስለዚህ ኦሮሞዎች ይህን በእነሱ ላይ ብቻ የደረሰ ትልቅ በደል ማድረግ የለባቸውም፡፡ ነገሩን አስፍተው መመልከት እንጂ፡፡…”

ምን አልባት ጽሃፊዉ የጠቀሷቸዉን ሰወች ከጊዜዉ መርዘም አኳያ ላናቃቸዉን  እነችላለን፡፡ አንድ ሁላችን የምናቀዉ ሰዉ ላንሳ። ጎንደሬዉን ሙዚቀኛዉ ኤሊያስ ተባባል የመጀመሪያ ስሙ  <<ልዋጥህ ተባባል>> ነው። ከገጠር መጥቶ አዲስ አበባ ስኬት ካገኘ በሁዋላ የመጀመሪያ የሙዚቃ ካሴቱን ሲያወጣ ስሙ ቸግር ፈጥሮበት ነበር። የሙዚቃዉን  የሰራለት ሙዚቃ ቤትም የስሙ አሳስቦት ነበር።በመጨረሻ በስምምነት ስሙ ከ<ልዋጥህ>> ወደ <<ኤሊያስ>>ተለወጠ።ይሄን ራሱ ከታማኝ ጋር ባረገዉ ቃለ ምልልስ  ገልጿል። አሁን በወያኔ ጊዜ እንኳን  ወርቃማ  የሃገራችን ስሞች  በነ ኪኪ፣ሊሊ፣ቢቢ፣ሚኪ፣ሱዚ፣ጃኪ እየተቀየሩ ነው። ድሮ ሳዉቅ እነዚህ ስሞች የሚሰጡት ለዉሻ ና ለድመት ነበር።እንዴት አድገዉ የሰው ስም ለመሆን እንደቻሉ ይገርማል። ምን ይሄ ብቻ :: የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከጎበዝ ተማሪ ጋር ለመቀመጥ ስንቱ ነዉ ሰሙን የቀየረ? ስንቱ ነዉ የለለ ፊደል ከስሙ ፊት የጨመረ? ይሄ በመሆኑም ወያኔ አይወቀስም።ምርጫዉና ሃላፊነቱ የግለሰቡ ነዉ።

ነግሩን አጥበን አይተነው ነዉ እንጅ  በኛ ሃገር ብቻ ያለ አይደለም።ለምሳሌ  በእንግሊዝ ሃገር <<Fox>>፣<<Stone>> ና <<Drinkwater>>  የሚባሉ ታዋቂ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያ  መጥተዉ መኖር ቢጀምሩ  ስሞቻቸዉ ምን አይነት ግርምትን እደሚፈጥር ግልጽ ነዉ። ለየት ያለ ነገር በአንደ ማህበረሰብ ሲመጣ ግርምት ቢፈጥር  ምኑም አይደንቅም።ባጭሩ ገለሰቡ የተሰማዉን ሰሜት መስረት አርጎ ስም ቀየረ እንጅ አዋጀ ወይም ግዴት አልነበረበትም።

6- ዘረኛ ትንኮሳ ላረገባቸው ግለሰብ  የመለሱት

“….የዘር ጥላቻ የሚያሰራጭ፣ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ፣ ከሰው ተራ የወረደ፣ ያልስለጠነ፣ ኋላቀር ክፉ አውሬ ነው፡፡ እሱን መልሶ መስደብ ዓየር የመሳብ ያህል ቀላል ነበር፡፡ ሆኖም እንደዚያ ማድረግ እንደሱ ዝቅ ማለት በመሆኑ ትቼዋለሁ። ከሱ ጋር መመላለስ ክብር እንዲሰማው ማድረግ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ስለዚህ በዚች ዓለም ላይ ያልተፈጠረ ያህል ንቄ ተዉኩት፡፡ እሱ ግን እንድናደድና የሱን ዘር በሙሉ በግምት እንድጠላ ተንኩሶኝ ነበር፡፡ ደግሞ ምከንያታዊነት ነው ለኔ፡፡ በሱ የተነሳ ከኢትዮጵያ ሰንደቅዐላማ፣ ከባሕሏም ጋር ምንም ጉዳይ የለኝም ብዬ ኢትዮጵያዊነቴን አልክድም፡፡ በፍጹም ይህን አላደርገውም፡፡ ….“

ብዙወቻችን ዘረኞን ንቀን ብንተዉ መልካም ነዉ። ዉሃ ሲወስድ አየሳሳቀ ነው ነገሩ። ሳናስበው ወደ አንሱ ጭዋት እንዳንገባ። የወያኔ ጥንካሬዉ ወታደሩ፣ደህንነቱ፣የዘረፈዉ ሃብቱ  ሳይሆን ተከፋፍለን አልደማመጥ ያልን ወገኖች ነን። ሊቁ ‘’The world is a dangerous place to live; not because of the people who are evil, but because of the people who don’t do anything about it.’’ ይላል ሃገራችንም እየጠፋች ያለችው  በዘር ተከፋፍልን ምንም ማረግ ባለመቻላችን ነዉ።

 

ምስጋና  ለጸሃፊው !

የጣናዉ    ከምድረ አዉሮፓ

yetanawlij2000@gmail.com

 

 

 

የህብር ሬዲዮ  የካቲት 5 ቀን 2009 ፕሮግራም

$
0
0

…ወያኔ የዘር ማጥፋት ወንጀል በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ነው ። የገበሬውን ቤት እያቃጠለ ህብረተሰቡን ለማዳከም እየሰራ ቢሆንም የከፋኝ እንቅስቃሴ ሰሞኑን በበለሳ ከነበረው ጠንካራ ውጊያ በላይ እየሰፋ ነው…በአሁኑ ወቅት እነሱ ታላቂቱን ትግራይ ለመመስረት ለሱዳን በአደራ ጭምር እየሰጡ ያለውን ድንበር ላይ ሕዝቡ ትኩረት አልሰጠም።ይሄ ትኩረት ማግኘት አለበት ። ከሱዳን የተረፈውን መሬት በባለሃብት ስም የሕወሓት ካድሬዎች እየተቀራመቱት ነው።ይሄ ሲሆን መከላከያ ሰራዊቱ ድንበር አቅራቢያ ቆሞ እያየ ነው። በተቃራኒው ግን እኛ ትኩረት የሰጠናቸው የሚያለያዩ ጉዳዮች ላይ ነው ።ይህ ሁኔታ ግን…> አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ በአሁኑ ወቅት በአገር ቤት በሰሜን ጎንደር ያለውን ህዝባዊ ተጋድሎ በተመለከተ ከህብር ተጠይቆው ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ( ቀሪውን   ያድምጡት)

…ማህበራዊ ሚዲያውን እርስ በእርስ ለመማማር ብንጠቀምበት ለለውጡ አጋዥ አድርገን መጠቀም መልካም ነው። በዛሬው የአርበኞች ግንቦት ሰባት የዲሲ ሜትሮ አካባቢ ስብሰባ የተሳካ ነበር። ኢትዮጵያውያን ለወሬ ትኩረት እንደማይሰጡ አሳይተዋል። በሕዝቡ ኮርቻለሁ ፕ/ር ብርሃኑም ማህበራዊ ሚዲያውን ለለውጥ እንድንጠቀምበት መክረዋል።ስብሰባው የተሳካ ነበር …> አክቲቪስት መኮንን ጌታቸው ከዲሲ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሀይል በሜሪላንድ የተካሄደውን አርበኞች ግንቦት ሰባት የጠራውን ስብሰባ በተመለከተ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

የዘንድሮ የታክስን በተመለከተ ውይይት ከአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ አቶ ተካ ከለለ ጋር የተደረገ ቆይታ (ልዩ ቃለ ምልልስ)

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተስቦች እና ደጋፊዎች የአንዳርጋቸው የልደት በዓልን በተቃውሞ ጥሪ አከበሩ

“የአንዳርጋቸው መታሰር አንድን ሰው ወደ አንበሳ ጎሬ የመወርወር ያህል ይሰማኛል…የዛሬ ዓመት የአንዳርጋቸው የልደት በዓልን ከአንዳርጋቸው ጋር በጋራ እንደምናክብር ተስፋ አለኝ” የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወ/ሮ የምስራች ለዜና ሰዎች ከተናገሩት የተቆነጠረ(ልዩ የልደት በዓል እና የቅስቀሳ ዘመቻ ጥንቅር)

በደህነት ስጋት በአየር ማረፊያ በተደረገ ምርጫ ወደ ስልጣን የዋጡት አዲሱ የሶማሊያ ፕ/ት መሀመድ አብዱላሂ/ፎርማጆ አገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ተስፋዎች እና የተደቀኑባቸው ችግሮች ሲፈተሹ(ልዩ እና ወቅታዊ ምልከታዎች )

ከፕ/ አለማየሁ /ማርያም ጋር ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ ስለሰጡት ውሳኔ የሕጋዊነት ጥያቄ እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ያደረግነው ውይይት ቀታይ ክፍል

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

ሕወሃት በቅማንት ስም የእርስ በእርስ ግጭት በማስነሳት የታላቁዋን ትግራይ ሕልም ከማሳካት እንደማይመለስ የብሄሩን ተወላጆች ሰብስቦ አስፈራራ

ፕ/ር ብርሃኑ የነጻነት እየተባለ የሚጠቀሰው የትግል እንቅስቃሴ የድርጅታቸው ትግል መሆኑን ገለጹ፣ ለወሬ ቦታ የለም ብለዋል

በኦሮሚያ ውስጥ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ  ሲጠናቀቅ ለአዲስ ተቃውሞ እንደሚወጡ ተናገሩ

ኢህአዲግ፣ተቃዋሚዎች እና አክቲቭስቶች ዘላቂ እርቀ ስላም የሚያመጡ እይመስለኝምጦማሪ ዘለአለም ክብረት ለእንግሊዙ ጋርዲያንጋዜጣ ከስጠው አስተያየት የተወስደ

የሶማሊላንድ መንግስት ዛሬ የበርበራ ወድብን ለአረብ ኤሜሬት ወታደራዊ ሰፈርነት መፍቀዱ ከኢህአዲግ አገዛዝ በኩል ተቃውሞ ገጠመው

በአገር ቤት በይስሙላ ድርድር የሚሳተፉ ተለጣፊ ተቃዋሚዎች አገዛዙ ከሕዝብ ጥቃት እንዲጠብቃቸው ጠየቁ ሌሎችም

ትውልደ ኢትዩጵያዊው እውቅ ድምጻዊ አቤል በለገሰው በካናዳ ዩኒቨርስቲ የግዕዝ ቋንቋ ማስተማር ተጀመረ

ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በጠራራ ጸሐይ ዝርፊያ አድርገዋል የተባሉ ሁለት ኢትዪጵያዊያን ወጣቶች ከፓሊስ እጅወደቁ፣በኢትዬጵያ አየርመንገድ አማካኝነት አደገኛ እጽ በሆድ እቃው የሽሽገ ናይጄርያዊ ህንድ ውስጥ እጹን እንዲተፋ ተደረገ

ለዓመታት ደም የትቃቡት የኢትዬኬኒያ አርብቶ አደሮች ስለዘላቂ ሰላም ምክክር አደረጉ፣አብረውም ገበታ በጋራ ተቋደሱ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይምበቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነውበእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።


ትንሽ ማብራሪያ ስለ እረኝነት – የጣናዉ ከምድረ አዉሮፓ

$
0
0

ሰሞኑን “እረኛ” በምትል ቃል የተነሳ ጫጫታ በዝቶ ነበር።ጫጫታ ያልኩት ነገሩ ምንም ጭብጥ የሌለዉ አፍ መክፈት ስለሆነ ነው።መነሻዉም አላዋቂነት፣በራስ ያለመተማመን፣ጥራዝ ነጠቅንት ነዉ።አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል ነዉ። ባዶነታቸዉን በአደባባይ  በራሳቸዉ ፍቃድ አሳይተውናል ።ለዚህ ሊመሰገኑ ይገባል። በዛላይ ለ3 ስአት ያን የመሰለ ቁም ነገር ሲወራ አንድ ቃል ብቻ መያዝ በጣም ያሳዝናል።ፕ/ር ሀይሌ ላሬቦ በድጋሚ “እረኛ” የምትለዉን ቃል ትርጉም ከተለያየ አቅጣጫ አስረድተዋል። እኔም በዚህ ጽሁፍ ከሊቁ ፕ/ር ሀይሌ የበለጠ ለማብራራት ሳይሆን ፤ እንደው ቀለለ ባለ አቀራረብ ቢገባቸዉ  ከሚል ነዉ።

እኔ ያደግኩበት ሰፈር ዮናስ የሚባል የ5 አመት ህጻን ነበር።ዮናስ ከእድሜ ጏደኞቹ የተለየ ልጅ ነበር።ጥሎበት አልቃሻ ልጅ ነበር።ስምህ ማን ነዉ ቢሉት ማልቀስ የሚቃጣዉ አይነት ልጅ ነበር።ጏደኞቹ ሲመቱት፣ሲሰድቡት እያለቀሰ ወደ አባቱ ነበር የሚሄደዉ። አባቱ ድግሞ በዚህ በጣም ይናደዳል። ወንድ ልጅ ነህ ፤  ሲመቱህ ተማታ፣ ሲሰድቡህ ተሳደብ ሁሌ እያለቀስክ አትምጣ ይለዋል። ዮናስ ግን ታጥቦ ጭቃ።አገሌ መታኝ፣አገሌ ሰደበኝ እያለ ሁሌም ወደ አባቱ። አንድ ቀን ቤት ቁጭ እያለቀሰ መጣ።አባቱም ተናዶ ደሞ ዛሬ ማን መታህ? አለዉ። እሱም ሰድበዉኝ ነው አለ እንባዉን እየጠረገ። አባቱም ምን ብለው ሰደቡህ? አለዉ። ዮናስም “የሃብታም ልጅ” ብለው አለ።ሁላችን  የልጅ ነገር ብለን ሳቅን። እንግዲህ ስድብ እናርገዉ ከተባለ ሁሉም ቃል ስድብ ይሆናል። አንተ ሃኪም፣አንተ መሃንዲስ፣አንተ አስተማሪ …ወዘተ።ዮናስ አሁን የ 20 ልጅ ነዉ ። ይሄን ገጠመኝ ልጅ ስለነብር አያስታዉስም። ግን ካደገ በሁዋላ አባቱ እያስታወሰ የልጅነት ጸባዩን ይነግረዋል። አሁን አሜሪካ እየሰራ ይማራል። ኑሮ ሲከብደዉ የሃብታም ልጅ እየተባልኩ አባቴ ጋር ብኖር ይሻለኛል እያለ ይቀልዳል። “እረኛ” የምትል ቃል ያንጫጫቸዉ ሁሉ ከ5 አመቱ ዮናስ በአስተሳሰብ ምንም አይለዩም።ሳይብሱም አይቀሩም እንዳያያዛቸዉ።

ለመሆኑ “እረኛ” ምን ማለት ነው?ስድብስ ነው ወይ?አሮሞወችስ እረኛ ከልነበሩ ምን ነበሩ?

1- የመዝገበ ቃላት ትርጉም

“እረኛ” ማለት ከብትን አሠምርቶ ወደ ክፉ ቦታ እንዳይሔድ የሚጠብቅ ማለት ነዉ።በእንግሊዝኛዉም ተመሳሳይ ነው።ምንም ማብራራት አይጠይቅም ።ስራ ሁሉ ደግሞ ክቡር ነዉ።አለምን አለም ያረጋት ሁሉም ስዉ በተለላይ ሞያ መሰማራቱ ነው። ዛሬ አለም የሚጠጣዉን ቡና ያበረከተዉ  ካልዲ የሚባል የፍየል እረኛ አይደለምን?

2-“እረኛ” በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ

በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ እረኛ” የሚል ቃል ቢያንስ 6 ቦታ ተጠቅሶ ይገኛል። እነሱም:

– ትንቢተ ኢሳይያስ 40:11

መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።

-ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:23

በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው፤ ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል።

ትንቢተ ሕዝቅኤል 37:24

ባሪያዬም ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል፤ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል

1 የጴጥሮስ መልእክት 5:4

የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።

የዮሐንስ 10:11

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል

ወደ ዕብራውያን 13:20

በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥

ከላይ እዳየነው “እረኛ” የምትል ቃል ለጥሩ ነገር እንጂ መጽሃፉም በስድብ አይጠቀምበትም። ትርጉሙም መጋቢ፣ ጠባቂ፣ ተንከባካቢ ማለት ነው።

3-አሮሞወችስ እረኛ ከልነበሩ ምን ነበሩ?

አሮሞወቹ እረኛ ነበሩ ማለት አኮ: ወተቱን ይጠጡ ፣እርጎዉን፣ስጋዉን፣አይቡን አንደ ልብ ይበሉ ነበር ማለት ነዉ።ይሄ ምኑ ክፉ ነው?ነዉሩ ምን ላይ ነው? አሁንስ ቢሆን አኦሮሞወች ላም አላቸዉ አይደል አንዴ?አለም በሙሉ ከብት ያረባ የል አንዴ? የት ሃገር ነው ከብት ማርባት ስድብ ና ዉርደት የሆነዉ? አሮሞወችስ ለከብት ሲያረቡ ላሞቸ ከአውሬ የሚጠብቅላቸዉ ማን ነበር? መላእክት ከሰማይ ወርደው ወይስ አሮሞወች እረኛ ከቻይና ና ህንድ እያስመጡ ወይስ በሮቦት በመታገዝ? ላሞች ለምለም ሳር ና ጥላ ስር የሚሰማሩት በርቀት መቆጣጠሪያ ወይስ በእረኛ? ከቤት ለሳር ግጦሽ የወጣ ከብት ቤቱ የሚመለሰዉ በጂፒኤስ መታገዝ ነበር ወይስ በእረኛ?

 

ቸር አንሰንብት።

የጣናዉ    ከምድረ አዉሮፓ

yetanawlij2000@gmail.com

 

 

 

የወገራ ገበሬዎች የወያኔን ጦር ሰብረው በሰላም ወጥተዋል

$
0
0

ከሙሉቀን ተስፋው

በሰሜን ጎንደር በወገራ ወረዳ የእንቃሽ ገበሬዎችን ለማፈን በሌሊት የተንቀሳቀሰው የወያኔ ሙሉ መካናይዝድ ጦር ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 12.00 ጀምሮ ከበባ አድርጎ ነበር፡፡ ከቦታው መረጃውን የሰጡን የአካባቢው ገበሬዎች እንደሚሉት ጠዋት ከመኝታቸው ከመነሳታቸው በፊት ነበር የወያኔ ጦር ከገበሬዎቹ ላይ ጦርነት የከፈተው፡፡

ገበሬዎቹ በጎበዝ አለቆቻቸው አማካይነት እስከ እኩለ ቀን ድረስ ሲዋጉ ከዋሉ በኋላ የወያኔ ጦርን ከበባ ሰብረው ለመውጣት ችለዋል፡፡ አሁን ላይ በጫካ ተበትነው እንዳሉ የሚናገሩት የጎበዝ አለቆች ‹‹በሰላም ወጥተን መግባትም ሆነ ሰላማዊ ሕይወታችን መቀጠል አልቻልንም፤ አሁንም በጫካ ተበትነን ነው ያለነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ባገኘነው መረጃ መሰረት እስካሁን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም የወያኔ ጦር ኃይሉን አጠናክሮ በአካባቢው እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡ ‹‹ማዶ ለማዶ እየተያየን አለን›› ሲሉ ከቦታው ያገኘናቸው አባት ተናግረዋል፡፡

ወያኔ በእንጅባራ የሚገኙ 70 የሚደርሱ ወጣቶችና 6 በእድሜ የገፉ አዛውንቶችን በእንጅባራ_ማረሚያ ቤት አስሮ እያሰቃያውቸ ነው

$
0
0

ከእነዚህም ምንም አይነት ክስ ሰይመሰርትባቸው አማራ በመሆናቸው ብቻ ግፍና መከራ እያዩ ናቸው።
አብዛናዎቹ የታሰሩት በአማራ ተጋድሎ የተጀረመረበት ወቅትና ከዚያ በኋላም የቤተሰብ አስተዳዳሪና ረዳት የሌላቸው መሆናቸው ታውቋል።
እነዚህን እና ሌሎች ያለምንም ወንጀል አማራ በመሆናቸው ታፍነው የሚኙኘት በአስቸኳይ የማይለቀቁ ከሆነ ማንኝፕውንም እርምጃ በማንኛውም ሰዓት ለመውሰድ እንገደዳለን ብለዋል የአካቢበው ነዋሪዎች።
#አያሌው_መንበር

 

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ግንኙነቷን ለማጠናከር የማግባባት (Lobyying) ስራ ከሚሰራ ኩባንያ ጋር የ1.8 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመች

$
0
0
ግርማ ብሩ

ግርማ ብሩ

ኢሳት (የካቲት 6 ፥ 2009)የኢትዮጵያ መንግስት በተያዘው የፈረንጆች አመት ከአሜሪካ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የማግባባት (ሎቢንግ) ስራ ከሚያካሄድ አንድ ድርጅት ጋር የ1.8 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት መፈራረሙ ታወቀ።

በዚሁ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ግርማ ብሩ መንግስትን በመወከል SRG-LLC ከተሰኘ ኩባንያ ጋር የፈረሙት ሰነድ የውጭ ወኪሎችን ጉዳይ የሚዘግበው ፎሪን ኤጀንትስ ሬጂስትሬሽን በድረ-ገጹ ላይ ባፈረው መረጃ አመልክቷል።

በዚሁ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ ከአሜሪካው ኩባንያ በየወሩ 150ሺ ዶላር ክፍያን በመክፈል ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት እንደሚደረግ ለመረዳት ተችሏል።

ከኩባንያው ጋር የተፈረመው ይኸው ስምምነት የአሜሪካ የምክር ቤት አባላትን በማግባባት በፖሊስ እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ኢትዮጵያ የምታነሳቸው አጀንዳዎች ትኩረት እንደሚያገኙ ኩባንያው በተያዘው አመት ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያካሄድ ታውቋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ካሉ ሃገራት መካከል ለተመሳሳይ ስራዎች ከፍተኛ ገንዘብን በመመደብ ከግብፅና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ተወዳዳሪ መሆኗን አፍሪካ ኢንተሊጀንስ የተሰኘ የደህንነት ተቋም ባለፈው አመት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ-ኦባማ አስተዳደር የኢትዮጵያ መንግስት ለሎቢንግ ስራዎች ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ ሲንቀሳቀስ እንደነበር የተለያዩ አካላት ይገልጻሉ። በአሜሪካ በቅርቡ የተደረገውን የመንግስት ለውጥ ተከትሎም ኢትዮጵያ SRG-LLC ከተሰኘው ኩባንያ ጋር ለአንድ አመት የሚዘልቅ ስምምነት ደርሳለች።

በአሜሪካ ህግ መሰረት ማንኛውም የአሜሪካ ኩባንያ ከውጭ መንግስት ጋር የሚያደርጉትን ስምምነት ለህዝቡ ይፋ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ሲሆን የዚሁኑ ስምምነት ምክንያት በማድረግ ኩባንያው የደረሰውን ስምምነት ለመዝጋቢው ተቋም አስረክቧል።

በፈረጆቹ ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ በኢትዮጵያ መንግስትና በሎቢንግ ኩባንያው መካከል የተፈረመው ስምምነት ኢትዮጵያ በየሶስት ወሩ ክፍያን እንዲፈጸም የሚያዝ ሲሆን፣ ገንዘቡም በዌልስ ፋርጎ ባንክ በኩል ገቢ እንዲያደርግ በሰነዱ ተመልክቷል።

የማግባባት ስራውን ለማከናወን ስምምነት የደረሰው ኩባንያ በበኩሉ ኢትዮጵያን በመወከል የመገኛኛ ብዙሃንን ጨምሮ የፖሊሲና የተለያዩ የቢዝነስ ጉዳዮች በአሜሪካ በኩል ትኩረት እንዲያገኙ የማግባባት ስራን እንደሚያከናውን በዶክመንቱ አስፍሯል።

ይኸው በሚስተር ግሬግ ሎሙማን የተፈረመው ስምምነት የተለያዩ ተጨማሪ ወጪዎች በሚኖሩ ጊዜ ደንበኛ ወይም የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሸፍን ገልጿል።

በአሜሪካ ህግ ይፋ እንደሚያደርጉ ከሚጠየቁ መረጃዎች ውጭ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረጉ ልውውጦችም ሚስጢራዊ ሆነው እንደሚቆዩ በሰነዱ ተመልክቷል።

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የምክር ቤት አባላት በሎቢንግ (በማግባባት) ስራ እንዳይሰማሩ አዲስ ህግ ተግባራዊ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ 11ሺ 143 የተመዘገቡ የሎቢስት አካላት የሚገኙ ሲሆን፣ እነዚሁ ግለሰቦች የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትና መንግስታትን በመወከል ከአሜሪካ መንግስት ጋር ያላቸው ጥቅም እንዲጠበቅ የማግባባት ስራዎችን እንደሚያከናውኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከልማት ባንክ ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ዝርፊያ የምርመራ ሂደት ቀጥሎአል

$
0
0

የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ መላኩ ፋንታ ከእስር ቤት ተጠርተው ተጠይቀዋል፤ የባንኩ ከፍተኛ ባለስልጣናት የነበሩ መጥሪያ ደርሷቸዋል፤ የህወሃት መካላከያ አባላት ሰነድ አጥፍተዋል፤ ከአገር የወጡም አሉ።

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን የሰሩትና የሙስና ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ ፋንታ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ መሬት ዝርፊያ ጋር በተያያዘ መረጃ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። አቶ መላኩ ለጥያቄ የተፈለጉት በሃላፊነት ላይ በነበሩባቸው አመታት ከህውሃት የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለው ግለሰቦች “ ባላስቀመጡት ገንዘብ ልክ የብድር አገልግሎት ወስደው ለግል ጥቅማቸው አውለዋል” ተብለው በተጠረጠሩት በጋምቤላ ክልል ከተፈጠረው የመሬት ዝርፊ ጋር በተያያዘ የክስ ዝግጅት እየተደረገባቸው ባሉ ባለሃብቶች ዙሪያ ባንኩ የተከተለውን አሳራር እና ቦርዱ ያሳለፈው ውሳኔ የሚያሳየው ሰነድ በመጥፋቱ ነው።

የውስጥ ምንጮቻችን እንደገለጹት በቤንሻንጉል ክልል “ሰባቱ ስታሮች” ተብለው የሚታወቁት እና ከፍተኛ የእርሻ ኢንቨስተሮች ከልማት ባንክ በወሰዱት እና ላለፉት ስምንት አመታት መሬት ተረክበው ጦም አሳድረዋል በተባሉት አቶ ሳለ እግዚአብሄር በርሄ፣ አቶ ኃይሉ ነጋ፣ ሻለቃ አዕምሮ ገ/ክርስቶስ፣ ሻለቃ ኪዱ ጣዕም፣ ኮማንደር ሙሉ ሁሉፍ፣ ኮማንደር ትርሃስ ገ/ዮሐንስ እና ጄኔራል ዮሐንስ አለም ሰገድ ከባንኩ ምንም አይነት ካፒታል ሳይቀበሉ በሽዎች የሚቆጠር ሄክታር መሬት በቢንሻንጉል ክልል የእርሻ ልማት ኢንቨስትመንት እንደሚሰሩ የፈቃድ ማስረጃ ከክልሉ በመቀበል 113 ሚልየን ብር ወስደው፣ በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ቦታ ሽያጭ እና የሪል እስቴት ንግድ ተሰማርተው ላለፉት ስምንት አመታት የወሰዱትን መሬት ጦም በማሳደር ለፈፀሙት ወንጀል በሌሉበት ክስ ለመመሰረት እንቅስቃሴ ተጀምሯል። መርማሪ ፖሊስ ግለሰቦቹን ከሚኖሩበት ዱባይ በኢንተርፖል ድጋፍ ለመያዝ የአቶ መላኩ ድጋፍ ያስፈልገኛል በማለት አቶ መላኩን ለማነጋገር ተገዷል።

አቶ መላኩ ምንም አይነት ማስረጃም ሆነ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

አቶ መላኩ “ ፍርድቤት ለሚያጣራው ጉዳይ ለፍርድ በሚቀርቡ አካላት እንጅ ከሀገር በወጡ እና በማይቀርቡ አካላት ዙሪያ ምንም ለመናገር ፈቃደኛ አይደለሁም” በማለታቸው መርማሪዎች የሚፈልጉትን ሳያገኙ ወደ እስር ቦታቸው ተመልሰዋል፡፡
በወቅቱ የቦርድ አመራር ለነበሩት አቶ አቢ ገ/መስቀል ፣ አቶ ያዕቆብ ያላ ፣ አቶ ሙሐመድ አህመድ፣ አቶ ተካ ይብራህ ፣ አቶ ነጋ ፀጋዬና አቶ አማረ ተክለማርያምም መጥሪያ እንደቀረበላቸው ታውቋል።

አገባብ ያለው የቴክኒክ ምርምራ ሳያደርጉ መንግስትን ለኪሳራ ዳርገዋል የተባሉትን በወቅቱ የአመራር አባላት የነበሩትን አንድ የባንኩ ኘሬዝዳንትና ሶስት ምክትል ኘሬዝዳንቶች እና የባንኩ ሥራ አስፈፃሚ የሥራ አመራር አባላትን ማለትም አቶ ኢሳያስ ባህረ፣ የባንኩ ፕሬዝዳነት ፣ ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ም/ ፕሬዝዳንት እና የብድር አገልግሎት፣ አቶ ገነነ ሩጋ፣ ም/ ፕሬዝዳንት እና የኮርፖሬት አገልግሎት፣ እንዲሁም አቶ ግርማ ወርቄ ም/ ፕሬዝዳንት ና የድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ኃላፊዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል መረጃ በመሰብሰብ ላይ መሆኑም ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በልማት ባንክ ይተዳደሩ በነበሩ ፕሮጀክቶች ውስጥ፣ 349 ሚሊዮን 600 ሺ ብር ምዝበራ መፈጸሙን የደህንነት መስሪያ ቤት መረጃ ማቅረቡን ተከትሎ፣ የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የማጣራት ስራ እንዲጀመር ለፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ትእዛዝ ሰጥቷል። ጉዳዩ ከሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጋር እንደተያያዘና ከፍተኛ ፖለቲካዊ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ምንጮች ተናግረዋል።

 

ለጠ/ሚኒስትር ቢሮ የቀረበው መረጃ “ በመንግስታት፤ በተቋማትና ወኪል ድርጅቶች ስም “ፈንዶችን” እንዲያስተዳድር በተሰጠው ስልጣን መሰረት፣ ልማት ባንክ ብሔራዊና ዓለምአቀፋዊ የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ አገር በቀል ድርጅቶች፣ የውጪ አገር መንግስታትም ሆኑ አበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት አንድም በተናጠል አልያም በጋራ ሆነው ለልማት የሚመድቧቸውን ፈንዶች ለማስተዳደርና ለታለሙት የልማት ፕሮግራሞች ወይም ፕሮጀክቶች በማዋል ዋነኛ የፋይናንስ መተላለፊያ የልማት ተቋም በመሆን እስከ 2002 ዓ.ም ባስተዳደራባቸው ዘጠኝ ዋነኛ የገንዘብ ምንጮች ላይ፣ 349 ሚልዮን 600 ሺ ብር ምዝበራ ተፈፅሟል” የሚል ነው። የፀረ ሙስና ኮሚሽን በቀረበው መረጃ ላይ ተመስርቶ የማጣራት ስራ ጀምሯል።

 

“ምዝበራ ተፈጽሞባቸዋል ተብለው የተለዩት በልማት ባንክ የሚተዳደሩ የመንግስታት፤ የተቋማትና ወኪል ድርጅቶች ፈንዶች” የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የሰጡባቸው ሲሆኑ እነዚህም፣ የቀድሞ ወታደሮችንና የጦር ጉዳተኞችን መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ፈንድ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ማገገሚያና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ፈንድ፣ የሐይቅ ዓሣዎች ልማት ፕሮግራም ፈንድ፣ የፓን አፍሪካ ምላሽ ሰጪ የተባይ መቆጣጠሪያ ፕሮጀክት ፈንድ፣ የኢትዮ ኢጣሊያ የአርሲና ባሌ የብድር ፕሮግራም ፈንድ፣ ፋርም አፍሪካ ፈንድ፣ የስዊስ ስታቤክስ ፈንድ ፣ ከፊንላንድ መንግስት ለሰላሌ አርሶአደር የወተት ከብት ልማት ፓይለት ፕሮጀክት በብድር የተሰጠ ፈንድ እንዲሁም በገጠር የመብራት ኃይል ማስፋፊያ ፈንድ ናቸው።

አብዛኞቹ ምዝበራዎች የተፈጸሙት በነባር የህወሃት ታጋዮችና ወታደራዊ መሪዎች እንዲሁም በስልጣን ላይ ባሉ ታዋቂ ባለስልጣኖች ድጋፍ በመሆኑ፣ ምርመራው ውስብስብ ሊሆን እንደሚችልና ፖለቲካዊ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል ምንጮች ተናግረዋል። በተለያዩ የመካለከያ የስልጣን ደረጃዎች ላይ የሚገኙ ከስልጣን የወረዱና ያሉ ባለስልጣናትን ለመክሰስ የሚደረገው ዘመቻ በቀጥታ በመከላከያ አዛዦች ላይ የተቃጣ ጥቃት ተደርጎ ሊታይና ያልታሰበ ነገር ሊፈጥር እንደሚችል ምንጮች ግምታቸውን ያሰፍራሉ።
የኢትዩጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ምዝበራ ከተፈጸመባቸው ተቋማት መካከል አንዱ ነው። ባንኩ 107ኛ ዓመቱን ዘንድሮ አክብሯል፡፡ የመጀመሪያውና በኢትዮጵያ የልማት ባንክ ታሪክ ፈር ቀዳጅ የሆነው የእርሻና የንግድ ማስፋፊያ የኢትዮጵያ ማኀበር ዳግማዊ አፄምኒልክ በፈቀዱትና ግንቦት 23 ቀን 19ዐ1 ዓ.ም ባስነገሩት አዋጅ መሠረት የዛሬ 107 ዓመት የተቋቋመ ነው፡፡

በአክስዮን መልክ የተቋቋመው ይኸው ማኀበር አቋሙ የታመነና ጠንካራ ይሆን ዘንድ በሚል ዳግማዊ አፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ መሥራች ማኀበርተኛ ሆነው እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ከንጉሱና ንግስቲቱ በተጨማሪ ራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው፣ ራስ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ፣ በጅሮንድ ሙሉጌታ ይገዙና ነጋድራስ ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደሚካኤልም ማህበርተኞች ነበሩ፡፡
ልማት ባንኩ በማሻሻያ ደንብ ቁጥር 116/1997 ዓ.ም እንደገና ሲቋቋም የተፈቀደ ካፒታሉ ወደ ብር 3 ቢሊዮን አድጓል፡፡ ልማት ባንኩ ሙሉ በሙሉ የመንግሥት ድርጅት ሲሆን የበላይ ተቆጣጣሪውም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን እንዲሆን ከተደረገ በሁዋላ በአሁኑ ወቅት የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ በበላይነት ይቆጣጠረዋል ። በወቅቱ አቶ አሰፋ አብርሃ እና ኢንጂነር ግዛው ተ/ማርያም ባንኩን በበላይነት መርተውታል፡፡ በቅርቡ ደግሞ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ባህረ ከሃላፊነት ከተነሱ በሁዋላ በአገዛዙ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ዘንድ ውዝግብ ተነስቷል።

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live