Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ራስህን ጠይቅ ( ሄኖክ የሺጥላ )

$
0
0

politicsፖለቲከኛ ማለት ከአብዛንኛው ህዝብ በተለየ የመዋሸት ስጦታ የተሰጠው ሰው ማለት ነው ። ፖለቲከኞች መጀመሪያ ታጋይ በመሆን ይጀምሩና ፥ የሚታገላቸውን በማፍራት ይጨርሳሉ!

ፖለቲከኞችን ሁሉ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ፥ ሁሉም የሚያወሩት ስለ አንድ ጭቁን ገበሬ ሲሆን ፥ በሚገርም ሁኔታ ሁሉም ገበሬውን አያውቁትም !

ፖለቲከኞች ሁሉም ስለተጨቆነ ህዝብ በተሰናሰነ መንገድ ማውራት ይችላሉ ። በዚህም ዲስኩራቸው ከጎናቸው እልፎችን ያሰልፋሉ ። በተከታይ ሲፋፉ ፥ መናጢ ሳሉ ያምኑበት የነበረውን ውይይት እና ሃሳብ ማንሸራሸር አንቅረው ይተፉታል ፥ የመናገር ነፃነት ይከበር ብለው ትግል የጀመሩት ፥ « እነዚህማ በመናገር ነፃነት ያምናሉ » ብለህ ስትናገራቸው ፥ ስትወቅሳቸው ወይም ስታርማቸው ፥ እንደ ጎረምሳ ድመት ያብጣሉ ።
በ ተቆርቋሪነት ስም የኮለኮሏቸውን የነሲብ ተከታዮች ፥ የገበሬውን ጭቆና ለማቅለል ከመጠቀም ይልቅ ፥ የሃሳብ ነፃነትን ለማድቀቅ ያሴሩበታል ።

ይህ ይህ ነው በማይባሉ አድር ባይ ጋዜጠኞች ፥ ውሸታም አክቲቪስቶች ፥ ሌባ ታጋዮች ፥ እና ከምንም በላይ ዱርዬ የሃገር መሪዎች ላይ የሚታይ ተመሳሳይ በሃሪ ነው ።
ሁሉም በአንድነት ስለ ፍትህ እና ነፃነት ያወራሉ ፥ ሁሉም ግን ከትዕቢት እና ተንኮለኝነት ነፃ አይደሉም ። ሁሉም !

ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅምን ከዘለቄታዊ ሃገራዊ ጥቅም አንፃር ለክተው እና መዝነው ሳይሆን የገቡበት ውስጥ የሚገቡት ፥ በነሲብ እና የሚፈልጉትን ነገር ለማስፈጠም ቀዳዳ በመፈልግ በመጠመድም ነው ። ይህ ደሞ ለውጥ ሳይሆንን ልውውጥ ነው የሚያመጣው ።
ለምሳሌ ህዝቡ ሰልችቶታል ። ውሸት ሰልችቶታል ፥ ድህነትም ሰልችቶታል ! ለምሳሌ እውነት መስማት እንፈልጋለን ። ትግል ውስጥ ነን የሚሉትም ሆኑ ትግሉን የሚደግፉት መሰረታዊ ምክነታቸው ምክንያታቸው ነፃነትን መሻት አለመሆኑ ነው ።

የጥገኝነት ወረቀት ለማግኘት ሲሉ የተቃዋሚ የትግል ጎራን የተቀላቀሉ ብዙዎች ነበሩ ፥ አሉም ። የጥገኝነት ወረቀታቸውን ሲያገኙ የትም የትም ሲታዩ አይስተዋሉም ። ከነሱ ወረቀት ባሻገር ያለው ገበሬ ህይወት የሚኖረው የነሱ ወረቀት እስኪሳካ ብቻ ነው ። መሪዎች ነን ባዮች ይህንን በደንብ ያውቃሉ ፥ በማወቃቸው የአመለካከት ለውጥ ብሎም መሰረታዊ የነፃነት ጥያቄ ምን መሆን እንዳለበት ፈር ከማስያዝ ፥ ከማስረዳት እና በዚያ ጎን ከማደራጀት ይልቅ ልቦናቸው እያወቀው ፥ የሚሰበስቡትን ሰብስበው ፥ አንድ ሁለት ጥቅስ ተናግረው ስብሰባውን ይበትናሉ ። ይህንን ድክመታቸውን ደፍሮ የሚናገረውን ፥ ቆምንለት የሚሉትን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ሃሳብ ገፍትረው ጥለው እውነቱን ከመሞገት ይልቅ በስድብ እና በ character assasination ይጠመዳሉ ።

እስቲ ለምን ይመስላችኋል ትናንት ሲቃወም የነበረው ዛሬ ኢትዮጵያ ስላፈራው ሃብቱ በመፍራት ዝምታን መርጦ ቁጭ ያለው ? ወያኔ ጠንካራ ስለሆነ ነው ? አይደለም!የተቃዋሚ መሪዎች ፥ ደጋፊዎቻቸው መሰረታዊ የፖለቲካ ንቃት ፥ መረዳት ብሎም እውነቱን በአግባቡ የማወቅ ስራን ስለማይሰሩ ነው ። ሰራን የሚሉት ከሰሩት አንፃር ይህ ነው የሚባል ስላልሆነም ነው ። በየቦታው የሚነሱን ህዝባዊ አመፆች « የኔ ነው » ብሎ ከማለት ውጪ የነሱ ስለመሆኑ አንዳችም ማሳያ በሌለበት ሁኔታ ፥ ለወረቀቱ ሲል ደጋፊ የሆናቸውን ጥቅማም ተከታይ እንዴት የሃገር መፍረስ እንዲገባው ልናደርግ እንችላለን ?

በግርግር የሚመጣ ለውጥ የለም ። ቢመጣም የግርግር ስርዓትን ነው ፈጥሮ የሚያልፈው ። ከጭብጨባው ጀርባ ያለውን እና ያልተሰራውን ትልቅ ስራ ለመስራት በመጀመሪያ ድክመቶቻችንን አምነን እንቀበል ። ሲነግሩን እንስማ ። ሲመክሩን ቢያንስ « ቢሆንስ » ብለን እንበል ። ስለ ነፃነት እየሰበክን ፥ ነፃ ስብዕናዎችን እይገደልን መኖር እንዴት ይቻለናል ። ለምን ይህን ያህል ለፍተን አልተሳካም የሚለውን መመለስ የምንችለው ህዝቡን ሳይሆን ራሳችንን በመመርመር ብቻ ነው ! ( በመጀምሪያ !)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles