የታንዛኒያ ባለስልጣናት ” ችግራችን እርቃን ገላ በማየት ፣የሴትን ጭን እና የወንድን ደልዳላ ደረት በመመልከት አይፈታም” በማለት በአምስት ሙዚቀኞች ላይ ዕገዳ ጥለዋል፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እርቃን ቀረሽ የወሲብ መጥሪያ የሚመስሉ ክሊፖች እረፍት የነሷት ታንዛኒያ የዜጎች አለባበስም ሊሻሻል ይገባዋል ብላለች፡፡የሴት ልጅ እርቃን ገላም የወሲብ ሸቀጥ የማስታወቂያ ሰሌዳ መሆን የለበትም፣እንዳይሆንም ብልግናን በሚሰብኩ ክሊፖች ላይ ቅጣቱ ዘላቂ ይሆናል ፡፡
የታንዛኒያን ቅጣት ተከትሎ ኬኒያ፣ሩዋንዳ እና ቡሩንዲም ቅጥ አጥተው የወሲብ ማስታወቂያ በሚመስሉ የሙዚቃ ክሊቦች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው፡፡ምስራቅ አፍሪካውያን የሰሀራን በረሀ አረንጓዴ ለማልበስ እየጣርን እንዴት ሴቶቻችን ከሰሀ በረሀ በላይ እርቃን ሁነው በወሲብ ሀሩር ወጣቱን በወጣት ያቃጥላሉ?? እንደ ጥንብ አንሳ በየሙዚቃ ክሊፑ በየትራሱ በሚንከባለሉ እርቃን ዳሌ ና ትክሻ በመመልከት ጊዜውን የሚያጠፋ ወጣት መኖር የለበትም ተብሏል፡፡አሁን ላይ ወሲብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማህበራዊ ቀውስ እያሰከተለ ይገኛል፡፡
ለዚህ ደግሞ ቀስቃሽ የጥበብ ስራዎች ተጠያቂዎች ናቸው፡፡፡ለዚህም በምስራቅ አፍሪካ ጠንከር ያለ እርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡ ታንዛኒያ ባለፉት ወራት ብቻ 500 ሴተኛ አዳሪዎችን እና 300 ወንድ ደንበኞቻቸውን በእስራት መቅጣቷ ይታወሳል ፡፡በታንዛኒያ ህግ ሴተኛ አዳሪነት ከባድ ወንጀል ነው፡፡ፕረዜዳንት ማጉፉሊም ከባለስልጣን እሰከ ባለሙያ ያሉ ዜጎች ትኩረታቸው ስራ ላይ ብቻ እንዲሆን ባህልን፣ስነ ልቦናን፣ምጣኔ ሀብትን የሚጎዱ ድርጊቶችን እያስወገዱ ነው፡፡