በኢትዮጵያ ወታደራዊ ደህንነት በኩል በከፍተኛ ሚስጥር እንዲያዝ በታቀደ ሁኔታ በሰሜኑ እዝ ዉስጥ ከተጠቃለሉት ክ/ጦሮች በተጨማሪ ከማእከላዊ እዝ ወታደሮችና ሜካናይዝድ ብረት ለበስ ሰራዊቶች እየተደራጁ ይገኛሉ።
በጎንደር በኩል በተለየ ሁኔታ ከሁመራ እስከ ኡማህ ጅር እንዲሁም በሰሜን 14.718326 አየር ካርታ ዳር ዳሩን በምያዝ ከአፋር ዞን 1 እስከ አፋር ዞን 2 ብሎም እስከ አድዋ ከድዋ እስከ አዲ አቡን ድረስ ሰራዊት ለማሰማራት ታቅዶ የሐይል እጥረት መከሰቱን መከላከያ ምንጮች ጠቁመዋል።
በኤርትራ በኩል ከፍተኝ ጥበቃ እየተደረገ በመሆኑ ምክንያት እንዲሁም ኤርትራ ባደረገችዉ መልሶ ጥቃት ምክንያት ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት የወያኔ ሰራዊት እንከን የገጠመው ከመሆኑ በተጨማሪ የሰራዊት ክዳት ከፍተኛ ችግር ማድረሱም ተረጋግጧል!
በሰሞን በተቀሰቀሰዉ ጦርነት ብቻ ከ140 በላይ ወታደሮች ከሰሜኑ እዝ በመኮብለል የተሰወሩ ሲሆን አንድ በጄኔራልነት ማእረግ ላይ የሚገኝ አመራር ብዛት ያላቸዉ ወታደሮችን ይዞ ወደ ኤርትራ ገብቷል።
ዜና በልዑል አለሜ