የተከበሩ ለማለት ትንሽ ይከብደኛል ( የተዋረዱ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ) የኢትዮጵያን መንግስት ወክለው ሲከራከሩ የሚያሳይ ውይይት ተመለከትኩ። እንደተለመደው አዘንኩ ። የነ አክሊሉ ሃብተወልድ ሃገር በተራ ዱርዬዎች እና የዱርዬ ተወካይ ዱርዬ አምባሳደሮች እንደምትመራ ማየት እጅግ ይጎመዝዛል ። « እኔ ኦሮሞ ነኝ አሮሞ ምንም አልሆነም » ማለት « አልሞተም ፥ አልታሰረም ፥ አልተገደለም » ይላሉ ጋሽ ሙፍቲ። ይሁንሎ እንዳልሎ ፥ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች እንዴት እንዴት ሆነው እንደተገደሉ እና እየተገደሉ እንደሆነ ስለማውቅ በንግግሮ « ጥርሴን አፋጭቻለሁ!» ።እኔ የምፈራው ይህንን የርሶን ንግግር የሰሙ የኦሮሞ ልጆች ቤተሰቦ ላይ አደጋ እንዳያደርሱ ነው ።
ለማንኛውም እንዲህ ስትጣሉ ፥ ስታንሱ እና ስትፎርሹ ማየት ደስ ይላል ።
↧
ዲና ሙፍቲ ፥ የአምባሳደር ቲያተር ዘበኛ ወይስ አምባሳደር ( ሄኖክ የሺጥላ )
↧