ዋሽንግተን ዲሲ — ሰኔ አምስትና ስድስት ቀን በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ላይ የተወሰደው ወታደራዊ እርምጃ ዩናይትድ ስቴትስን ክፉኛ እንዳሳሰባት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ (JOHN KIRBY) ማምሻውን በጹሑፍ ባወጡት አጭር መግለጫ አስታወቁ።
ኢትዮጵያና ኤርትራ በ1992 ዓ.ም የተኩስ ማቆም ስምምነት መፈራረማቸውን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ የላኩት መግለጫው አስታወሶ፤ ወታደራዊ እርምጃ ለሁለቱ ሀገሮች መፍትሔ ሊሆን እንደማይችል ይጠቅሳል። ስለዚህም “ኢትዮጵያና ኤርትራ ከወታደራዊ ርምጃ ታቅበው ጉዳዩን በፖለቲካዊ ውይይት መፍታት ይጠበቅባቸዋል” በማለት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለፖለቲካ ውይይት ጥሪ አቅርቧል።
በመግለጫው የመጨረሻ ክፍልም፤ “ሁለቱ ሀገሮች በአካባቢው መረጋጋትና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አብረው እንዲሠሩ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ያሳስባል” ይላል።
መግለጫውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
if(typeof(jQuery)==”function”){(function($){$.fn.fitVids=function(){}})(jQuery)};jwplayer(‘jwplayer-1’).setup({“file”:”http://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2016/06/85bb5e3e-f3a6-4c57-b46b-eb9b6d479b2d.mp3″});