አንዳንድ ሰዎች ወይም መበለጥን የሞት ያህል ይቆጥሩትና ያን የበለጣቸውን ግለሰብም ሆነ ድርጅት እሰይ በርታ በማለት ፋንታ አቃቂር በማውጣት ጥላቻን ለማሳደር ይራወጣሉ ይሄ ደግሞ የቆሙለትን ድረጅት ከነበረበት መውረድ ያሳያልና ቢታሰብበት ጥሩ ነው።እያንዳንዳችን ሃገራችንን እንጂ ኢትዮጵያዊነታችንን ወይም ሀይማኖታችንን ጥለን የወጣን አይመስለኝም ነበረ ነካስ እንዲህም ዓይነት ሰዎች አብረውን ተሰደዋል በእርግጥ አዜብ ጎላም ፈርተው የፈረጠጡ እንዳሉ ራሳቸው ነግረውናል እስኪ ለዛሬ እሱን ትተን እንደው ኧረ ይሄን የመጠላለፍ ፖለቲካ መቼ ነው የምንተወው በሰው ሐገር ተቀምጦ ምንም በሌለበት የሽግግር መንግስት እንመስርት ከማለት በላይ ምን ማሽቃበጥ አለ። መጠጊያ እና አማራጭ በሌለበት ወቅት ኤርትራን መጠጋት እንደ ሃጥያት የሚነገረው ለምንድን ነው ደግሞስ ከኤርትራ በላይ ማነው ለኛ የሚቀርበን ምን የሚሉት ቅናት ነው ምነው እንዲህ ቆረቆራችሁ ወደዳችሁም ጠላቹ የፈሪ መንግስት በባዕድ ሃገር ተቀምጦ መመመስረት ከማሰብ በላይ ድቀት የለም ። አርበኞች ግንቦት 7ም ሆነ ሌሎች በበረሃ ያሉ ወገኖች መሳሪያ ማንሳት በራስ መተማመንን እንጂ የወረቀት መንግሥት መመስረትን አይደለም የሚያሳዩት ለነገሩማ አወቅሽ አወቅሽ ሲሉዋት………………መኮኑ ይመስለኛል።
ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች
ጁን 8/ 2016