ከሶስት አመት በፊት ነው። የሚከተለዉን ጽፌ ነበር። “ግልጽ ደብዳቤ ለግንቦት ሰባት አመራሮችና አባላት” በሚል፣ አክብሮት በተሞላበት፣ መረጃዎችን በአግባብና በብዛት በማቅረብ፣ ምክር ቤት ለግሰን ነበር።
“ኤርትራና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ እንደምታውቁት ኢሳያስ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ የተገለለ ነዉ። ከቀይ ባህር አሳዎች ጋር በስተቀረ፣ ከኤርትራ አጎራባቾች ሁሉጋር ጦርነት ገጥሟል። የኤርትራዉያን ደም ቢፈስ ምንም የማይመስለው፣ የሕዝቡን ደም በመጠጣት የሚረካ የተረገመ ሰው ነዉ። በዚህም ምክንያት የተባበሩትመንግስታት የፀጥታዉ ምክር ቤት፣ በኤርትራ ላይ በርካታ ዉሳኔዎችን አላስልፏል። ከዉሳኔዎቹ መካከል ፣ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ወደ ኤርትራ እንዳይገባ፣ኤርትራ የጎሮቤት አገሮች ላይ የምታደርሰውን «ሽብር» እንድታቆም፣ ከጎሮቤት አገሮች ጋር ያላትን ችግር በሰላም እንድትፈታ፣ በግዛቷ ያሉ ሽምቅ ተዋጊዎችንመደገፍ እንድታቆም የሚጠይቁ ዉሳኔዎች ይገኙበታል። እንግዲህ ይሄ የሚያሳየው ከሻእቢያ ተወዳጅቶ የሚደረግ እንቅስቃሴ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋርየሚያጋጭ መሆኑን ነዉ። በተዘዋዋሪ መንገድ የጸጥታው ምክር ቤት ዉሳኔን እየጣሳችሁ ነዉ። የአለም አቀፍ ማህብረሰብን ከበሬታ እያጣችሁ ነዉ። አንድ ምሳሌልጥቀስ። በቅርቡ ከግንቦት ሰባት አመራር አባላት ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው የተከበሩ አና ጎሜዝ አዲስ አበባ መሄዳቸዉን እና በዚያም ከነአባ ዱላ ጋርመነጋገራቸው በሰፊው ተዘግቧል። የአና ጎሜዝ ወደ አዲስ አበባ መሄድ፣ የተለያዩ ትርጓሜ ሊሰጠው ይችላል። ነገር ግን፣ ቢያንስ ቢያንስ የግንቦት ሰባት ድርጅታችሁንየዲፕሎማሲ ሽንፈትና ኪሳራ በግልጽ ያሳየ ነዉ። ግድ የለም ከሻእቢያ ጥገኝነት ዉጡ”
http://ethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/ginbot_versus_shabia.pdf
ግንቦት ሰባቶች ግን ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም። ጭራሹኑ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባዬ፣ በሻእቢያ የሚፈጸመውን ግፍና ጭካኔ በማጋለጡ፣ ግንቦት ሰባቶች፣ እነዚህ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ በመቃወምና ሻእቢያን በመደገፍ ፔቲሽኖችን የማስፈራም ዘመቻ አካል ሆነውም ነበር።
“Eritrea is the most stable, peaceful and secure country that has managed to keep the harmony and peaceful co-existence of its society that is multilingual and multi-ethnic with varied religions…. we, call on all members and supporters of the Patriotic Ginbot 7 worldwide and all other patriotic Ethiopians who understand the implication of the sinister agenda against Eritrea ( ኤርትራዉያን ላይ እየደረሰ ያለውን ዘግናኝና ኢሰብአዊ ጭፍጨፋን የማጋለጡን ሂደት) to sign the online petition launched by Eritrean communities worldwide (ሻእቢያ ማለታቸው ነው)” በማለት ነው እንድንፈርም ሲቀሰቅሱ የነበሩት።
በነገራችን ላይ ፈርሙ እያሉ ሲቅሰቅሱ የነበሩት ፔትሽን ላይ ለምሳሌ እንዲህ የሚል አለ “The SR and COIE reports ignored central dimensions, such as Ethiopia’s 16-year long occupation of sovereign Eritrean territories” ። የትኛው መሬትን ማለታቸው ነው ? ባደመን ? እንደዚያ ከሆነ ግንቦት ሰባት ባድመ ለኤርትራ እንዲሰጥ ይፈልጋል ማለት ነው ? አያችሁ። ግንቦት ሰባት በአገር ጉዳይ አልደራደርም ይላል እንጂ ብዙ ነገሮች ተደራድሮ የጨረሰ ነው የሚመስለው። ባድሜን እና ሌሎች ለኤርትራ ለመስጠት፣ ኢትዮጵያ ባህር አልባ ሆነ እንድትቀር …የመሳሰሉትን።
ሁኔታው በዚህ እንዳለ ዛሬ ደግሞ ጭራሹኑ ለይቶለታል። የግንቦት ሰባት የ ”ክብር ፕሬዘዳንት” አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በይፋ ከነ ሚሎሶቬች እና ቻርልስ ቴለር ምድብ ተቀምጠዋል።
የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በይፋ ኢሳያስ አፈወርቂን በአለም አቀፍ ሄግ ፍርድ ቤት ከሷል። “Crimes against humanity” የተባለውን ወንጀል በመፈጸም በሚል። 45000 ኤርትራውያን ኮሚሽኑ የኤርትራ መንግስት ላይ ቅጣት እንዲጀመር ፊርማ በማሰባሰብ መጠየቃቸውን Mr. Mike Smith የተባሉትየኮሚሽኑ አባል ተናግረዋል። (ግንቦት ሰባቶች ሲያስፈርሙት የነበረው ጸረ-ህዝብ እና ጸረ-ሰብአዊነት ፔቲሽን፣ ስንት ሰው እንደፈረመ አይታወቅም። ምናልባት ከካድሬዎች በስተቀር ማንም የሚፈርም ስለማይኖር ነው መሰለኝ ሆን ብለው ቁጥሩ እንዳይታይ አድርገዉታል)
አሁንም የግንቦት ሰባት ንቅናቄ humility አሳይቶ፣ ከግትር አቋሙ ተላቆ ፣ የሰብዓዊ መብት በሁሉም ቦታ፣ በማንም ሲፈጸም የሚቃወምና የሚታገል መርህ ይዞ፣ ከሻእቢያ ጥገኝነት ወጥቶ፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ደርጅቶች ጋር በመተባበርና በመቀናጀት፣ ውጤት በሚያመጣ መልኩ፣ በስሜትና በፉከራ በማጭበርበርና በንዴት ላይ ያልተመሰረተ ፣ በእውቀት ላይ የሆነ ፣ የተባበረ የኢትዮጵያዉያኖች ትግል የሚጀመርበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንዲሰራ እጠይቃለሁ። ኢትዮጵያዉያን ለመብታቸውና ለነጻነታቸው ለሚያደርጉት ትግል፣ በአለምአቀፍ ፍርድ ቤት በ Crimes against humanity የተከሰሱ ጨካኞች ድጋፋ አያስፈልጋቸውም። የሻእቢያ ኮቴ መከተል አለብን ማለት የኢትዮጵያን ህዝብ መሳደብ ነው። በመሆኑን እነርሱም አብረው ከሻእቢያ ጋር ገደል ሳይገቡ ወደ ትክክለኛ መስመር ይመለሱ ባይ ነኝ።
በነገራችን ላይ ይሄን ለምን ጻፍችሁ የምትሉ ካላችሁ ያለውን ሪያሊቲ እንድትመለከቱ፣ ከስሜት ወጣ ብላችሁ እንታገናዝቡ እንመክራቹሃለን። እኛ ከጅምሩ ስንጽፍ፣ ስናስጠነቅቅ ፣ ስንመክር ነበር። ግንቦት ሰባቶች “ወያኔ” እያሉ መሳደብ እንጅ እስቲ የሚሉትን እንመዝን ብለው ጠይቀው አያውቅም። ትችት የምናቀርበውን እንደ ጠላት ነው የሚያዩን። አሁን ግን እዉነት አፍጦ መጣባቸው። ኢሳያስ አፈወርቂ አንድ ነገር ከሆነ በሚል ተደናግጠው ለሻእቢያ ድጋፍ ፔቲሽን ፈርሙ እስከማለት ደረሱ። አይ ጉድ ……ለጊዜው እዚህ ላይ አበቃለሁ።