Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ኣባት እና ልጅ (ናትናኤል አስመላሽ)

$
0
0

አቶ ሃይለስላሴ ኣሰፋ የሕድሮም ሃይለስላሴ ኣሰፋ ኣባት ናቸው፣ አቶ ሃይለስላሴ ኣሰፋ የህውሓት ታጋይ ነበሩ፣ኣቶ ሃይለስላሴ ኣሰፋ አምባገነኑን ደርግ ለመጣል በተደረገው ትግል ውስጥ በጀግንነት መስዋእትነት የከፈሉ ታጋይ ናቸው። ሕድሮም ሃይለስላሴ ደግሞ ኣሁን የዓረና መድረክ ኣባል ነው። አሁን ሕድሮም ሃይለስላሴም ከዓረና መድረክ ጎን በመሰለፍ በትግራይ ህዝብ ብሎም በኢትዮጲያ ህዝብ ለሚደርስ ጭቆና በቁርጠኝነት እና በጀግንነት እንደ ኣባቱ አቶ ሃይለስላሴ ኣሰፋ መስዋእት እየከፈለ ይገኛል።

13330963_10206313366897329_7877690526768475462_nኣባት አቶ ሃይለስላሴ ኣሰፋ የከፈለው መስዋእትነት እንካንስ ለትግራይን ህዝብ እና ለኢትዮጲያ ህዝብ ቀርቶ ለልጅም ነጻ ማውጣት አልቻለም። ለዚህም ነው ልጅ ሕድሮም ሃይለስላሴ እንዳባቱ ጀግና ሆኖ የትግራይን ህዝብ እና የኢትዮጲያ ህዝብ ከአምባገነኑን ህውሓት ነጻ ለማውጣት እየታገለ ብሎም መስዋእትነት እየከፈለ የሚገኘው። በህውሓት ትግል እስካሁን ድረስ ነጻ የወጣ ህዝብ የለም፣ነጻ የወጡ ኣምባገነኖች ግን ኣሉ፣ እነሱም ኣሁን ስልጣን ላይ ያሉ የህውሓት መሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ብቻ ናቸው። በህውሓት ትግል ጊዜ መስዋእትነት የከፈሉ ኣባቶች ልጆቻው ገና ነጻ ኣልወጡም።

13335545_10206313367737350_8236554433657507742_n (1)ሕድሮም የዓረና መድረክ አባል በመሆኑ ብቻ ብዙ ብዙ ችግሮች ደርሰውበታል፣ እንግዲህ በህውሓት ብዙ ግፍ ደረሰበት እያልነው ያለነው ልጅ ኣባቱ የህውሓት ታጋይ የነበረ ልጅ ነው። በትግራይ ውስጥ ብዙ የሰማእታት ልጆች ከትግሉ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆኑ የትግሉም ሰለባ ሆነዋል። ሕድሮም የዓረና መድረክ አባል በመሆኑ ብቻ ሲያርሰው የነበረ መሬት ዉሃ እንዳያገኝ ተደርገዋል። ሕድሮም እና ቤተሰቦቹ በማሳቸው ሲያልፍ የነበረ የመስኖ ውሃ አቅጣቻው በማስቀየር የዘራውን በሙሉ በውሃ እጥረት ምክንያት እንዲወድም ተደርገዋል። ለግጦሽ የሚሆን ስለሌለም በጎቹ እና ከብቶቹ ለሞት ተዳርገዋል፣ በገንዘብ ለመተመኑ የሚያስቸግር ኪሳራ ደርሶበታል።

ሕድሮም ይህ ብቻ ሳይሆን ባለፈው ምርጫ ዓረና መድረክን ወክሎ በመወዳደሩ ብቻ በህውሓት ደህንነቶች ድብደባ ደርሶበታል፣ በድንጋይ ጭንቅላቱ ተመቶ ራሱን እስኪሲት ድረስ መሬት ላይ ወድቀዋል ደሙ እንደ ጎርፍ ፈሰዋል። ከዚህም ኣልፎ ጥይት ተተኩሶበት ከሞት ተርፈዋል።ሕድሮም እንደ ማንኛው ዜጋ ስራ ተወዳድሮ መቀጠር አልቻለም፣እ ንደማይችልም ህውሓቶች አረጋግጠዋል። ከዚህም ኣልፎ እንደ ማንኛው ዜጋ የቀበሌ መታወቅያ መብቱ ተነግፎ በቅርቡ በስንት ውጣ ውረድ ኣግኝተዋል። ይህ በልጅ የሚደርስ በደል አባት ቢሰማ ምን ይላል? እንግዲህ ህውሓቶች ስልጣን (አራት ኪሎ) ላይ ያደርስዋቸውን ሰማእታት ረስተው ብቻ ሳይሆኑ የሰማእታትን ልጆችም እያሰሩ፣እየገደሉ እና እየደበደቡ ይገኛሉ። ባጭሩ ትግሉ በጥቂቶች ተጠልፎ ከደርግ ኣምባገነንነት ወደ ህውሓት ኣምባገነንነት ተቀይረዋል።አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ ማለት ይህ ነው።

ትግራይ ውስጥ ብዙ የሰማእታት ቤተሰቦች ኣሉ። ከነዚህ ውስጥ ከትግሉ ተጠቃሚዎች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፣ እነሱም አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን እና ቤተሰቦቻቸውን ብቻ ናቸው!!! ፎቶው ላይ የምትመለከትዋቸው የሕድሮም ሃይለስላሴ ኣባት የህውሓት ታጋይ ነበር አቶ ሃይለስላሴ ኣሰፋ ናቸው። ሌላው ምስል የህድሮም ሃይለስላሴ ነው። ይህ ምስል የምታዩት ሕድሮም ሃይለስላሴ ባለፈው ምርጫ በድህንነቶች በድንጋይ ተመቶ ደሙ ሲፈስ ነው። የትግራይ ወጣት ሆይ፣ ወላጆችህ የከፈሉት መስዋእትነት በጥቅቶች ተጠልፈዋል እና አባቶችህ አምባገነኑ ደርግ እንደታገሉት እና እንደጣሉት አንተም አምባገነኑ ህውሓትን ለመጣል እና ለመታገል ጊዜው አሁን ነው። ኣባቶችህ ልጆቻቸውን ከአምባገነኑ ደርግ ነጻ ለማውጣት እንደታገሉት ኣንተም ልጆችህን ከአምባገነኑ ህውሓት ነጻ ለማውጣት ታገል።ህውሓት ለታጋይ ቤተሰቦች ያልሆነው ለትግራይ ህዝብ ኣይሆንም እንደወላጆችህ ጸረ ኣምባገነኖች ታገል!!!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles