(ምንሊክ ሳልሳዊ)
ወያኔ ኢሕአዴግ ስልጣን የተቆጣጠረበት እና የስጋና የመንፈስ መንታ ወንድሙን ገድሎ እሱ የተነሳበትን 25 አመት በማክበር ላይ ይገኛል::ሕወሓት መራሹ ኢሕአዴግ አፄ ሃይለስላሴ በገነቡት ስታዲየም ውስጥ ምንም የመሰብሰቢያ አዳራሽ/ስታዲየም ሳይገነባ ስለ ልማት ሲያወራ ውሏል::ኢሕአዴግ ራሱን የሚያወዳድረው ከራሱ እቅድ እና ከሕዝብ ፍላጎት ጋር ሳይሆን ከሞቱ እና ከተቀበሩ ጨቋኝ ገዢዎች ጋር መሆኑን የሚያመለክተው ነገር ቢኖር ራሱ ወያኔ ጨቋኝ አምባገነን መሆኑን ብቻ ነው::
ለግንቦት ሃያ አከባበር 20 ቢሊዮን ብር መድቦ ድንኳን በየመንገድ ዳር ተክሎ የሚጮሕወ ወያኔ በቢሊዮን ዶላር እርዳታ የሚፈልጉ በድርቅ እና በረሃብ የተጎዱ በስማቸው ገንዘብ ለምኖ የሚሰበስብባቸው ዜጎችን ለማስታወስ ፍላጎት የለውም::
ግንቦት 20 አምባገነኑና ጨቋኙ የደርግ ስርዓት የተገረሰሰበት ብቻ ሳይሆን ስር የሰደደ የድህነትና የድንቁርና ምዕራፍ በዲሞክራሲ ሽፋት ተከፍቶ ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ሕዝብን ሲፈጅ የኖረበት የእኩይ ቀን መጀመሪያ ነው:: በከፍተኛ ወጪ የአንድ ቀን ፌሽታ ከማድረግ ይልቅ ለዘለቄታው የተጎዱ ኢትዮጵያውያን መታደግ እየተቻለ ከነካድሬዎቹ ተሰብስቦ ጮማ እየቆረጠ ውስኪ የሚራጨው የሕወሓት አገዛዝ ቀንከቀን የሚወቅሳቸውን የንጉሱን እና የደርግን ተግባር በመድገም ብቻ ሳይሆን በአደባባይ በውሸት ሸፋፍኖ ለማለፍ ሲጣጣር እየተጋለጣ ይገኛል::በሙስና ተወዳዳሪ ያልተገኘላቸው ባለስልጣናቱን በመታቀ ከሃገር ውስጥ የሚገኘውን ሃብትና ንብረት እንዲሁም ከውጪው አለም የሚገኘውን እርዳታ እና ብድር ቅርጥፍ አድርገው በመብላት ሃገሪጥውን በልማት እያራመድን ነው በማለት ታይቶ የማይታወቅ ድህነት በደብል ዲጂት አሳድገዋል:: ኢትዮጵያ ዜጎች ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የማያደርጉባትና ቢያደርጉም በጠራራ ፀሃይ የሚገደሉት ነበረች ነች እየሆነችም ነው::
ስንቱን እንስተን ስንቱን እንደምንጥል አናውቅም::በሃገር ቤት ባሉት የግል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ በላያቸው ላይ ነጋዴ ሆኖ የተነሳው አገዛዝ የኤሌክትሪክ ሃይል በማቋረጥ ብቻ 40 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ በ6 ወር ውስጥ አድርሶ በ9 ወር ከኤሌክትሪክ ኤክስፖርት የተገኘውን 35 ሚሊዮን ዶላር “ኪራይ ሰብሳቢነት ለአደጋ አጋልጦናል::” የሚለው ኢሕኣዴግ በሙስና ተቀራምቶታል::ይህ እድገት ብለው የሚያወሩት በሌላ መንገድ ደሞ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ብለው ኢኮኖሚው ስጋት ላይ መሆኑን የሚነግሩን ችጋራም ባለስልጣኖች ሃገሪቷን እየገደሏት ነው::ሃገሪቷን በተለያየ መንገድ እያጠፏት የሚገኙት ወያኔዎች ለክብረ ባዓላቸው ያወጡት ከፍተኛ ገንዘብ በርካታ ዜጎችን ከረሃብ ሃገሪቷንም ከልመና ታሪኳ ይገላግላት ነበር::ቢሆንም ይህን ለማድረግ ባለመቻላቸው ስለ ልማት በባዶው ሲደሰኩሩ እየሰማን ነው::ይህንን ድንፋታም እና ሃሰተኛ መንግስት ለመጣል እርስ በእርስ ከመነቋቆር ወጥተን ለሕብረት ቆመን ተግባራዊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል: