Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ልዩ ጥበብ ገንባ

$
0
0

ፍቅር ታሞ ከርሞ አልጋ ላይ እንደሰው
ብዙ ዘመን ሆነ ሞቶ ከቀበርነው
ይሄ ሆኖ እያለ ሞቱን እያወቅን
ለአያሌ ዓመታት ዘፋኞች በዘፈን
አሁንም እንዳለ ህይወት እስትንፋሱ
ጨርሶ እንዳልሞተ እንዳልወጣች ነፍሱ
አድርገው ሲዘፍኑ ሲያቀብሉን ውሸት
ነገሩን ዋጥ አድርገን አብረን ጨፈርንበት

ከሁሉ ‘ሚገርመው የሚደንቀው ነገር
አለ የሚባለው የአሁን ዘመን ፍቅር
ገንዘብን ውሃልክ አ’ርጎ ተመስርቶ
በዓይናችን እያየን መካካዱ ከፍቶ
ዘፋኙ ተነስቶ ሲለን ፍቅር ፍቅር
በሆታ በስክስታ የኛ አብሮ ማጫፈር

ከ «እማትበላ ወፍ»«እዘበናኝ» ድረስ
ሆዴ አንጀቴ እያለ ተሸክሞ እንደ ውርስ
ወጣቱም ያንኑ ሲያማስል ሲያቁላላ
ስለከረመበት ሳይቀይር በሌላ
ያወጣው ሙዚቃ ሳይሰማ ጣፍጦ
ዘፈኑ ይሞታል ዘፋኙ ተቀምጦ
ይህ ሁሉ ሲሰራ ይህ ሁሉ ሲፈጠር
እስከዛሬ ቆየን ምንም ሳንናገር
ስለዚህ ወደፊት ትዝብት እንዳናተርፍ
ሌላው ቢቀር እንኳን መልዕክት እናስተላልፍ

እንግዲህ ወጣቱ ድምጽህን ተጠቅመህ
ዘፈን ስታወጣ ሙዚቃ አቀናብረህ
የሌለች አይነት ሴት የሌለ አይነት ፍቅር
ለዘፈኑ ሲባል ሀሳብ ከምትፈጥር
የምድሪቷን ፀጋ የተፈጥሮን ውበት
የሰውን ባህሪ ክፋት ከደግነት
ስለ እናቶች ሙያ ስለአባቶች ገድል
ስለ ቀለበት ሰርግ ዓመታዊ በአል
ስለ ህጻናቶች ጨዋታ ፍንደቃ
ስለ ‘ምታጅብህ የማታ ጨረቃ
የጥሩ የመጥፎን የዘመን ትዝታ
የወዳጅ የዘመድ የናትን ውለታ
የህይወት ገጠመኝ አስደናቂ ውሎን
በጣፈጠ ዜማ ይቻልሃል መዝፈን
እነ «ተማር ልጄ» «ቀጠሮ ይከበር»
ምሳሌዎች ናቸው ላነሳሁት ነገር
ስለዚህ በወደድኩ የውሸት ወከባ
ተጨማሪ ሆነህ ተራ ከምትገባ
የራስህ የሆነ ልዩ ጥበብ ገንባ!

<!–

–>


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles