Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

በዓዲ ሕርዲ የትግራይ ኮማንዶ ልዩ ሃይል ተሰማራ (አምዶም ገብረስላሴ)

$
0
0

13230196_1052417231516599_5846534147188290561_nየቓፍታ ሑመራ ህዝብ ከቀበሌ እስከ ፌደራል በህወሓት እጅ የቆየው ውክልናየ ኣንስቻለው እያለ ነው። በትግራይ ክልል ቓፍታ ሑአራ ወረዳ የዓዲ ሕርዲና ዓዲ ፀፀር በሩባሳ ኣከባቢ “ለወጣቶች የቤት ማታከያ ይሰጣልና በቦታው ተገኝታቹ ተረከቡ” የሚል የመንግስት ትእዛዝ ምክንያት በቦታው የተገኙ የሁለቱ ቀበሌዎች ወጣቶች ሳያስቡት በሩባሳ ኑዋሪዎች ጥቃት ስለተፈፀመባቸው የተነሳው ግጭት የዓዲ ሕርዲና ዓዲ ፀፀር ህዝብ “የመንግስት እጅ ኣለበት፣ ህዝቡ ለማጣላት ሆን ብሎ ሰርተዋል” በማለት ከፍተኛ ቁጣ ፈጥረዋል።

የሁለቱ ቀበሌዎች ህዝብ “ህወሓት በሁሉ መስክ ኣስተዳደራዊ ዘርፎች ለኛ የሚመጥን መንግስት ስላልሆነ ከዛሬ(እሁድ 15 ጉምበት) ከቀበሌ እስከ ፌደራል ይዞብን የነበረው ውክልናችን ኣንስተናል” ብለው ኣውጀዋል።

ይሄ ውሳኔ የተላለፈው ከ15 ሺ በላይ ህዝብ ለእሁድ 14 / 09 / 08 ዓ/ም ሰለማዊ ሰልፍ ለማካሄድ እንዲፈቀድላቸው ለወረዳው ኣስተዳደር የጠየቁ ሲሆኑ ወረዳው ጥያቄው ኣግዶታል።

13245280_1052417414849914_7899347818317534688_nየሰልፉ ክልከላ ተከትለው የሁለቱ ቀበሌዎች ኑዋሪዎች ራሳቸው ስብሰባ በማካሄድ ነባር የህወሓት ታማኝ ካድሬዎች በማባረር ከህዝቡ መሃከል የራሳቸው ህዝባዊ ኣስተዳዳሪዎች መርጠዋል።

የትግራይ መንግስት ኮማንዶ ልዩ ሃይል እሁድ ሌሊት ከመቐለ ወደ ስፍራው ልከዋል።

ኮማንዶ ልዩ ሃይሉ እሁድ 15/ 09 /08 ዓ/ምሌሊት ዓዲ ሕርዲ ቀበሌ ገብተዋል።

የዓዲ ሕርዲ ና ዓዲ ፀፀር ህዝቦች “የህወሓት ውክልናችን ኣንስተናል” ከእምባስነይቲ ቀጥለው ታሪካዊ ውሳኔ የወሰኑ ተጋሩ ኢትዮጵያውያን ሆነዋል።

ህወሓት ራስዋ ስልጣኔና ራሴ የወሰድኩት የህዝብ ውክልና ለህዝቤ መልሼ ኣስረክባለው ካላለች ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት በኣጭር ግዜ ሙሉ በሙሉ ሊነሳት እንደሚችል ክስተቱ ኣብሪ ምልክት ነው።

የትግራይ ህዝብ ህወሓት ኣትወክለኝም ማለቱ ቀጥሎበታል።

ፎቶው የእምባስነይቲ ነው።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles