“…መቴክ 77 ቢልዮን ብር ከ 10 ሱኳር ፋብሪካዎች መዘበረ…” የሚለው ዜና ሲሰማ ሁለት ጭሆቶች ከ ኢህኣዴግ ፤ ኣንድ ትልቅ ጭሆት ደግሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ ተሰሙ።
ሁለቱ የኢህኣዴግ ጭሆቶች፦ ከብኣዴን የሚነሳው “የመቴክ ሃላፊ ጀነራሎች ከህወሓት ናቸውና ህወሓት ተጠያቂ ነው”፣ የሚልና ኢህኣዴግ እንደ ድርጅት ነው መወቀስ ያለበት፣ ሁላችን ነው የዘረፍነው ፣ብቻየ ኣይደለም መጠየቅ ያለብኝ” የሚል የህወሓቶች ለቅሶ እየሰማን ነው።
“ብኣዴን ስልጣኔ ሊቀማኝ ፈልጎ ነው ዘረፋው ለብቻየ የሚያሸክመኝ” ይላል ህወሓት።
እኔን ጨምሮ ሌላው ኢትዮጵያዊ ደግሞ የተዘረፈው 77 ቢልዮን ብር የሃገር ሃብት ነው። ዘራፊው ከኢህኣዴግ፣ ብኣዴን፣ ህወሓት ይሁን ሌብነት ነውና ዘራፊዎቹ ወደ ህግ ይቅረቡ የሚል ነው።
የስኳር ኮርፔሬሽን የድሮ ሃላፊ ኣቶ ኣባይ ፀሓየና የወቅቱ ሃላፊም በህግ ፊት ቀርበው ሊጠየቁ ይገባል።
ከዚህ ባለፈ “ጀነራሎችና ኣባይ ፀሓየ ተጋሩ ስለሆኑ መጠየቅ የለባቸውም” የምትሉ የህወሓት ኣባላትና ፍቅራቹ ሳትጨርሱ መቃወም የጀመራቹ ተጋሩ፤ “በምዝበራው ግንባር ቀደም መሪዎቹ ህወሓት ስለ ሆኑ እነሱ ብቻ ይጠየቁ” ለምትሉ ብኣዴኖች ሰሚ የላቹም።
ሌባ ጀነራል ይሁን ባለ ስልጣንና ተራ ሰራተኛም ካለ በህግ ፊት ቀርቦ መጠየቅ ኣለበት።
እቺ ጠጋጠጋ … እንደሚባለው ህዝባችን የኢህኣዴግ ዘራፊዎች ሲነቃባቸው ከብሄር እያጣበቁ ማለቃቀስ ድሮ ተነቃባት።
የትግራይ ህዝብም ቢሆን በጭንቅ ግዜ በስሙ መነገድ ነቅቶባታል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።