የጨረታ ማስታወቂያ (ከ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ኢብኮ)
በመንግስት ኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ድርጅት በአዲሱ ስሙ ኢብኮ ያላገለገሉ እና ጥቅም ላይ ያልዋሉ የቦንብ፣ የፈንጂ፣ የሚሳኤል እንዲሁም የተለያዩ ልማትን የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ድርጅቱ በቅርብ ጊዜያት በአርባ ምንጭ ብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አሸባሪዎችን ከነ ትጥቃቸው ማረከ በሚለው ዜና ስር ያስቀመጠው የመሳሪያ ፎቶግራፍ የኢራቅ ታጣቂዎች ተያዙ በሚል በሁለት ሺህ አራት አመተ ምህረት አሜሪካን ሃገር የሚገኝ ድረ ገጽ ጥቅም ላይ ያዋለው ሲሆን በወልዲያ የውስጥ ለውስጥ ባቡር መስመር ግንባታ ዜና ላይ በልማት ህብረተሰቡን ለማማለል የተጠቀምነው ፎቶግራፍም ምንጩ በካሊፎርኒያ የሚገኝ ግንባታ ሆኖ ተገኝታል።
ድርጅታችንን ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነትን ለማግኘት ያላገለገሉ እና በየትኛውም ድረ ገጽ ላይ ተለጥፈው የማያውቁ የቦንብ፣ የፈንጂ፣ የሚሳኤል እና ታንክን ጨምሮ ማናቸውንም የመሳሪያ ፎቶግራፎች እንዲሁም የግድብ፣ የባቡር መንገድ ስራ እና የመሳሰሉትን ልማት የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች አሉን የምትሏቸውን ፎቶግራፎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኮሚኒኬሽን ጽፈት ቤት ድረስ ማምጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን!