ከ ኢፌዴሬ የተሰጠ መግለጫ፤
በቅርብ ጊዜ በገላን ኮንደሚኒየም ሳይት ሰማኒያ ስምንት የኮንደሚንየም ቤት ብሎኮች እምጥ ይግቡ እስምጥ ሳይታወቅ መጥፋታቸው ታውቋል።
ቤቶቹን የሙርሌ ጎሳ አባላት ከዘረፏቸው ከብቶች እና ይዘዋቸው ከተሰወሩት ህጻናት እና ሴቶች ጋር አብረው ወስደዋቸው ሊሆን ይችላል እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሰረት የሌለው ሲሆን፤ ጉዳዩ እንኳን የተያያዘ ቢሆን እና የሙርሌ ጎሳ አባላት እነዚህን ኮንደሚኒየም ቤቶች እየነዱ ወስደዋቸው ከሆነ፤ መከላከያ ሰራዊታችን ህዝባዊነት በተሞላበት፣ አርቆ አሳቢነት በታከለበት፣ ርህራሄን ከከላሽ ጋር ባነገበ እና በበሳል አመራር በመታገዝ በድርድር ኮንደሚኒየም ቤቶቹን አንድ በአንድ የሚመለሱበትን ሁኔታ እስኪያመቻች ድረስ ህብረተሰቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ እናሳስባለን።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የጠፉት ሰማኒያ ስምንት ብሎኮች በጠፉበት ጊዜ በውስጣቸው ሰዎች ነበሩ ወይስ ባዶ ቤቶች ናቸው የሚለውን ለማጣራት ኮሚቴ ተዋቅሮሞ እየሰራ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን!
ሃሃ…
(ኧረ ሳቅ አዋጡ እኔ ሳቅ አለቀኝ….
ጸሃዩ መንግስቴ እየኮረኮረኝ)