Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመልካም አስተዳደር እና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግር (ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ)

$
0
0

31934866በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምሬት እና ሮሮ በረከተ…ዋ.ዋ.ዋ! በሰንበቴ ቶማ የሁለት ግራ እግር አመራር አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ ጉዞ!!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመልካም አስተዳደር እና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ከተንሰራፋባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል የመጀመሪያውን ሥፍራ ተቆጣጥሯል፡፡ በተቋሙ ሥራዎች የሚከናወኑት እና ውሳኔዎች የሚሰጡት ህግንና አሰራርን መሰረት በማድረግ ሳይሆን በግለሰቦችና በቡድኖች ፍላጎትና በጎ ፈቃድ በመሆኑ የሰራተኞች ቅሬታና አቤቱታ በርክቷል፡፡ በተለይ ሰንበቴ የሚባል ፕሬዚዳንት ከመጣ በኋላ የመንግስት ሥራ ህግንና አሰራርን ተከትሎ የመስራት አዝማሚያ በመጥፋቱ ጥቂት በጥላቻ የተሞሉ ገለሰቦች ይህን ክፍተት በመጠቀም በኪራይ ሰብሳቢነት ከመሰማራታቸውም በላይ ተቋሙ ውስጥ ኔትወርክ እና ጎጠኝነት እንዲስፋፋ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ሰንበቴ እና መሰሎቹ የሰራተኛውን ቅሬታና አቤቱታ ተቀብለው ብልሹ አሰራራቸውን ከማስተካከል ይልቅ ሰራተኛውን በማስፈራራት እና በማሸማቀቅ ተግባር መሰማራትን መርጠዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ተቋሙ አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ ጉዞ ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ የሰራተኛው የሥራ ሞራል እና ፍላጎት በመውደቁ ምክንያት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሥራ የሚለቀው ሰራተኛ ቁጥር ጨምሯል፡፡

በሰንበቴ በመሰለኝ እና በደሳለኝ አመራር ተቋሙ ከማይወጣበት አዘቅጥ ውስጥ ገብቷል፡፡ ሰውየው በራሱ የአመራር ክህሎት፣ እውቀትና ልምድ ማነስ የተከሰቱ ችግሮቸን ወደ ቀድሞ አመራር በማላከክ የራሱን ውድቀት ለመሸፋፈን እሞከረ ይገኛል፡፡ ከሱ ከማይሻሉ ተከታዮች ጋር በመሆን በተቋሙ ውስጥ የጥላቻና የጠባብ ብሄርተኝነት ዘር በመዝራት ላይ ይገኛል፡፡ በራስ የመተማመን አቅም የሌለው ከመሆኑም በላይ በየበታችነት ስሜት ውዝግብ ውስጥ መግባቱን በዙሪያው የሰበሰባቸው ግለሰቦች ጭምር ወደ አደባባይ ለማውጣት ተገደዋል፡፡

በሌላ በኩል በተቋሙ ውስጥ በርካታ አቅም ያላቸው ዶክተሮች ቢኖሩም ትኩረት ሰቶ አቅማቸውን ለተቋሙ ቀጣይ እድገት ከመጠቀም ይልቅ እንደራሱ ሁለት ግራ እግር የሆኑትንና አቅመቢሶቹን በመሰብሰብ ተቋሙ ላይ መቀመጥን መርጧል፡፡ የሰውየውን ሥራ የተመለከቱ ብዙዎች ህንድ ከመማር ከልምድ መማር ይሻላል ብለው ወደ ህንድ ለትምህርት ከመሄድ ተቆጥበዋል፡፡

ሰንበቴ ከሰራቸው ስህተቶች አንዱ የኪራይ ሰብሳቢነትን ማስፋፋቱ ሲሆን ሌላው በቀድሞ አመራር በአቅም ማነስ፣ በድሲፕሊን ችግር እና በኪራይ ሰብሳቢነት ከኃላፊነት የተነሱ ገለሰቦችን ወደ ኃላፊነት ማምጣቱ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት እየታገለ ቢሆንም ከፌደራል መንግስት ተቋማት ተጨማሪ ድጋፍና ከትትል ይሻል፡፡

በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ የሚያሳስበው ቀጣዩ ፕሬዚዳንት እንዴትና ኬት ይመደባል የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ይህን በተመለከተ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ እናሳስባለን፡፡ በተለይ ባለፈው ከጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በነበረው የውይይት መድረክ ላይ የተነሱ ጉዳዮች መዘንጋት የለባቸውም፡፡

 

ሰላም ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ!

በጋራ ትግል ብልሹ አሰራሮችንና ኪራይ ሰብሳቢነትን እናስወግዳለን!!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles