ስደተኞች የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ኮሚሽነር አንቶንዮ ጉተረስ ወደ ዳዳብ በሚባለው የኬንያ የስደተኞች መጠለያ በሚጎበኙበት ወቅት ኮሚሽነሩን ለማየት ተሰብስበው እ.አ.አ. 2015 /ፎቶ – አጃንስ ፍራንስ ፕረስ/
በርምጃው ቁጥራቸው ወደ አራት መቶ ሺህ የሚገመት ስደተኞች ይጎዳሉ ተብሏል። የኬንያ መንግስት ዓርብ ባወጣው መግለጫ ለብሄራዊ ጸጥታችን ስንል ስደተኞን ማስተናገዳችንን ማቆም ይኖርብናል ብለዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ — የኬንያ መንግስት በሀገሪቱ ያሉትን ሁለት ትላልቅ የስደተኛ ካምፖች፤ የዳዳብንና የካኩማን ካምፖች፤ ለመዝጋት ዕቅድ ያለው መሆኑ አስታወቀ። በርምጃው ቁጥራቸው ወደ አራት መቶ ሺህ የሚገመት ስደተኞች ይጎዳሉ ተብሏል።
የኬንያ መንግስት ዓርብ ባወጣው መግለጫ ለብሄራዊ ጸጥታችን ስንል ስደተኞን ማስተናገዳችንን ማቆም ይኖርብናል ብለዋል።
ባለ ሁለት ገጹ የኬንያ መንግስት መግለጫ መንግስት መጀመሪያ የስደተኛ ጉዳይ መምሪያውን እንደሚዘጋ እና ከዚያም ካምፖቹ ባጭር ጊዜ የሚዘጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል ከማለት ባለፈ በካምፖቹ ያሉትን ስደተኞች እናባርራለን አይልም።
ከዓለም እጅግ ግዙፉ መሆኑ የሚንገርለት በመዕከላዊ ኬንያ የሚገኘው የዳዳብ ካምፕ የሚበዙት ሶማሊያውያን የሆኑ ወደ ሶስት መቶ ሰላሳ ሺህ ስደተኞች አስጠልሏል። ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንም ይገኛሉ። ሰሜን ምስራቅ ኬንያ ያለው ካኩማ ደግሞ ሃምሳ አምስት ሺህ ስደተኞች ተጠልለዋል።
ኬንያ ባጠቃላዩ ስድስት መቶ ሺህ ስደተኞች እያስተናገደች ስትሆን ሶስት አራተኛው ከሶማሊያ ከቀሪዎቹ የሚበዙት ደግሞ ደቡብ ሱዳናውያን ናቸው።
ኬንያ ካሁን ቀደምም ካምፖቹን እዘጋለሁ ብላ ካስፈራራች በኋላ ዳር ሳታደርሰው መቆየትዋ ይታወሳል። ባለፈው ዓመት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የዳዳብ ካምፕ ተዘግቶ ሶማሊያውያኑ ስደተኞች በግድ ወደ ሃገራቸው መመለስ እጅግ ከባድ ሰብዓዊ ችግር እንደሚያስከትል አስጠንቅቋል።
ትናንት የኬንያ መንግስት ውሳኔው ስደተኞችን እንደሚጎዳ አምኖ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ችግሩን ለማቅለል ርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቡዋል። ካምፖቹን ለመዝጋት የወሰንነው እንደ አል-ሸባብ ካሉ ጽንፈኛ ቡድኖች የደህንነት አደጋ ስለተደቀነብንና ስደተኞችን ወደ ሃገራቸው የመመለሱ ሂደት ስለተጓተተ መሆኑን አመልክቷል።
The post የኬንያ መንግስት ትላልቅ የስደተኛ ካምፖች ዳዳብንና ካኩማን ለመዝጋት ዕቅድ ያለው መሆኑ አስታወቀ (ቪኦኤ) appeared first on ሳተናው .