Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የኢራቅ ፓርላማ በተቃዋሚዎች ተወረረ (ሳተናው)

$
0
0

parlament

(ሳተናው) በሺህዎች የሚቆጠሩ የሻዒት ሙስሊሞች በባግዳድ የሚገኘውን የኢራቅ ፓርላማ በመውረር የአዲሶቹን  ካቢኔዎች ዕጩነት ፓርላማው ለማጽደቅ የወሰደበትን ረዥም ጊዜ ተቃውመዋል፡፡

የሻዒቶች መምህር የሆኑት ሞቃታዳ ሳዲር ደጋፊዎች የፓርላማውን አጥር በመጣስ ወደ ውስጥ በመዝለቅ የአዳዲስ ሚንስትሮቹን ሹመት ለማጽደቅ ያንገራገሩ የፓርላማ አባላትን ተቃውመዋል፡፡ፓርላማው በሰልፈኞቹ ቁጥጥር ስር መውደቁን ተከትሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን ፓርላማው አቅራቢያ የሚገኘውን የአሜሪካ ኢምባሲ ፖሊሶች በመክበብም በሰልፈኞቹ ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ተዘግቧል፡፡

ሰልፈኞቹ ፓርላማውን በወረሩበት ሰዓትም ስብሰባ ለይ የነበሩ የፓርላማ አባላት በሌላ መውጫ በመጠቀም መሸሻቸው ተሰምቷል፡፡ተቃውሞ አቅራቢዎቹ ከፓርላማው በመውጣት ግሪን ዞን ተብሎ የሚታወቀውን ቦታ መቆጣጠራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

መምህሩ ሳዲር የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይዴር አል አባዲ ከአንድ ወገን ብቻ ተመርጠው የተሾሙትን ሚንስትሮች ሁሉን በሚያስማማ መልኩ ለመቀየር የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ሲጠይቁ ቆይተዋል ነገር ግን በፓርላማው ተሰሚነት ያላቸው ኃይሎች የሚንስትሮቹን መለወጥ በመቃወም ሲያጓትቱ ቆይተዋል፡፡

የኢራቁ ፕሬዘዳንት ፉዓድ ማሱም ተቃዋሚዎቹ ፓርላማውን እንዲለቁና የፓርላማ አባላቱ የሚንስትሮቹን ለውጥ እንዲያጸድቁ መጠየቃቸውንም ቢቢሲ አትቷል፡፡

ምንጭ ቢቢሲ

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles