(ክፍል 2)
ሀ) መግቢያ
ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድነት ሃይሎችና በጎጠኞች መካከል የተካሄደው ፍልሚያ ፤ በጎጠኞች አሸናፊነት ከተደመደመ ወዲህ እራሱን የቻለ የፖለቲካ ውጥንቅጥ እስከትሎ እንደሚመጣ የተገመተ ቢሆንም ወደ ዘር ማጥፋትና ማጽዳት ያመራል ብሎ የተነበየ ከቶ አልነበረም። የጎጠኞች ያልተጠበቀ ድልና እሱንም ተከትሎ የመጣው ስካር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ደም አፍሷል፤ እያፈሰሰም ነው። ክረምትና በጋ ፣ ቁር ፣ ሃሩር ሳይለይ ሌት ተቀን ሳይባል፤ ምስራቅ ይሁን ሰሜን ሳይል ፣ ክብረ በአልና የሰርክ ቀናት ሳይለይ ፣ ከ1983 እስከ ያዝነው 2008 ዓ.ም የዐማሮች እጣ ፋንታቸው መፈናቀልና መገደል ሆኗል። እንደከብት የታረዱት ፣ እሳት የበላቸው ፣ በግፍ ያለቁት በሺዎችና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ዐማሮች ደም በኢትዮጵያ ምድር በአራቱም ማእዘናት በመጮህ ላይ ነው! —[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-