Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ደቡብ ሱዳን ‹‹በጋምቤላው ግጭት እጄ የለበትም ካላመናችሁኝ ኢትዮጵያን ጠይቁ››አለች

$
0
0

Gbandi_1_0_2_0

(ሳተናው)ጊዜያዊው የደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ከ200 ሰዎች በላይ በተገደሉበት የጋምቤላ ክልል ግጭት መንግስታቸው እጁ እንደሌለበት መግለጻቸው ተሰምቷል፡፡

ባንዲ ለሪፖርተሮች ስለሁኔታው በሰጡት አስተያየት በጥቃቱ የደቡብ ሱዳን መንግስት እጅ እንደሌለበት ኢትዮጵያ ማስታወቋን አስታውሰዋል፡፡በጥቃቱ ከአንድ መቶ የሚልቁ ህጻናትና 2000 እንስሳት ከኢትዮጵያ መወሰዳቸውን መረጃዎች ይገልጻሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ አባላት ጥቃቱን ማድረሳቸውን ቢገልጽም የሙርሌ ጎሳ የትኛው ታጣቂ ቡድን ለጥቃቱ ተጠያቂ እንደሚሆን አልጠቀሰም፡፡

ባንዲ በማብራሪያቸው ‹‹ይህ ጥቃት በደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ ቡድኖች ተፈጽሟል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት በይፋ የደቡብ ሱዳን መንግስት በጥቃቱ እጁ የለበትም በማለት በማስታወቁም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡የጥቃቱ አድራሾች ወንበዴዎች ናቸው፡፡እንደ መንግስት ደግሞ እንዚህን መዋጋት የእኛ ኃላፊነት ነው››ብለዋል፡፡

ባለስልጣኑ ታፍነው የተወሰዱትን ህጻናት ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት አስመልክተውም ‹‹ልጆቹንና ሌላው ቀርቶ እንስሳቱን ለማስመለስ ጠንክረን በመስራት ላይ እንገኛለኝ ይህንን ማድረግም የእኛ ኃላፊነት ነው››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር በመደወል ሐዘናቸውን መግለጻቸውን የሚጠቅሱት ባንዲ የጦር ኃይላቸው ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ባንዲ ለጋምቤላው ጥቃት ተጠያቂ የሚሆነው የትኛው የደቡብ ሱዳን ቡድን እንደሆነ ባይጠቅሱም በደፈናው በቀጣይ የሚመሰረተው ጊዜያዊ መንግስት የታጠቁ ቡድኖችን መሳሪያቸውን ማስፈታት እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡

ከጥቃቱ በፊት የጥቃቱ ፈጻሚዎች ሰዎቻችንን ሲያስፈራሩ ቆይተዋል ማለታቸውንም ጋዜጦች አስነብበዋል፡፡

ምንጭ አሶሼትድ ፕሬስ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles