Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ኢትዮ ቴሌኮም ቫይበርና ዋትሳፕን በክፍያ፣ ያልተቀረጡ ሞባይሎችንም ከአገልግሎት ውጪ አደርጋለሁ አለ

$
0
0

telecom

(ሳተናው) በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔትን በመጠቀም የስልክ አገልግሎት የሚሰጡትን እንደ ቫይበርና ዋትሳፕ ያሉ አገልግሎቶችን በክፍያ ለማድረግ በመወሰኑ አገልግሎቶቹን የሚቆጣጠር መሳሪያ መጠቀም መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አንዷለም አድማሴ ስም ባወጣው መግለጫ በቫይበርና ዋትሳፕ ምክንያት ድርጅቱ ማግኘት የሚገባውን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሉ አገልግሎቶቹን በክፍያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል፡፡

‹‹ምንም እንኳን አገልግሎቶቹን ለመጠቀም የኢንተርኔት ግኑኝነት ክፍያ መፈጸም የሚያስፈልግ ቢሆንም ኢትዮ ቴሌኮም በአገልግሎቶቹ ምክንያት የሚያጣው ገንዘብ ለኢንተርኔት ክፍያ ከሚፈጸመው ከፍ ያለ በመሆኑ አገልግሎቶቹን መቆጣጠር አስፈላጊ ሆኗል››ማለታቸውን ለንባብ በቅቷል፡፡ድርጅቱ በተጨማሪም ቀረጥ ያልተከፈለባቸውንና ሳይቀረጡ በውጪ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው የሚልኳቸውን የስልክ ቀፎዎች ክፍያ እንዲፈጸምባቸው ለማድረግ በአገሪቱ የሚገኙ ህጋዊ ቀፎዎችን የሚመዘግብ መሳሪያ መጠቀም እንደሚጀምርም አስታውቋል፡፡

ቴሌ ኮም እንደሚጠቀምበት የሚናገርለት መሳሪያ ቀረጥ ባልተከፈለባቸው የስልክ ቀፎዎች ውስጥ የሚገኙ ሲም ካርዶችን መቆለፍ(አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ)ብቻ ሳይሆን የስልኩ ቀፎ ቀረጥ እንዳልተከፈለበት ከታወቀ ወዲያውኑ ስልኩን የሚቆልፍ ስለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በስራ አስኪያጁ ስም የወጣው መግለጫም ሰሞኑን ብዛት ባላቸው አካባቢዎች የቫይበርና የዋትሳፕ  አገልግሎቶችን ማወክ መቻሉን የኢትዮ ቴሌኮምን ብቃት ያሳያል ብሏል፡፡ በመግለጫው ባይካተትም በአገሪቱ በዋናነትም በኦሮሚያ ዋትሳፕና ቫይበርን ጨምሮ ማህበራዊ ድረገጾችን መጠቀም አለመቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምንጭ ኢትዮ ቴሌኮም

 

The post ኢትዮ ቴሌኮም ቫይበርና ዋትሳፕን በክፍያ፣ ያልተቀረጡ ሞባይሎችንም ከአገልግሎት ውጪ አደርጋለሁ አለ appeared first on ሳተናው .


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles