የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንደዘገበው ትግራይን የኢንዱስትሩ ማእከል ለማድረግ ከሌሎች ክፍለ ሃገራት የፋብሪካ መሳሪያዎች እየተነቀሉ ወደ ትግራይ ተወስደዋል። በወንበዴና ዘራፊ እቃዎች ቢዘረፉ አያስደንቀም። ሆኖም አገርን እና ሕዝብን እጠብቃለሁ በሚል የሕወሃት ቡድን ግን መሳሪያዎች እየተዘረፉና እየተነቀሉ መወሰዳቸው ከፍተኛ መንግስታዊ ዉንብድና ብቻ ሳይሆን ትልቅ ዘረኝነት ነው።
የትግራይ ክፍለ ሃገር በደርግ ጊዜ በጦርነት ምክንያት ብዙ ጉዳት የደረሰባት እንደመሆኑ፣ ከጦርነቱ በኋላ ለተወሰኑ አመታት ከሌሎች ክፍለ ሃገራት በተለየ ሁኔታ ልዩ ትኩረት ማግኘቷ፣ የፈራረሱ ኢንፍስትራከቸሮ መገንባታቸው አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ተገቢ ነበር። ሆኖም ግን ሌሎች ክልሎች አፍርሶ፣ ከሌሎች ክፍለ ሃገራት የፋብሪካ መሳሪያዎች ነቅሎ ወደ ትግራይ መዉሰድ የትግራይን ህዝብ መጥቀም ሳይሆን የትግራይን ሕዝብ ሆን ብሎ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ጋር ማጋጨት ነው።
“ኢሳት የጎንደሩን ጀነሬተር በ1985 ዓም በህወሀት አማካኝነት ተወስዶ በትግራይ ሀውዜን መተከሉን የሚገልጽ ዘገባ ካቀረበ በኋላ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸሙን የሚያሳዩ መረጃዎች በውስጥ መስመር እየመጡ ነው። ወደፊት በስፋት ጉዳዩን ለመቃኘት እንሞክራለን። የጎንደሩ ጀነሬተር ሲወሰድ የሚያሳየውን ፎቶግራፍ ላደረስከኝ ወዳጄ ምስጋናዬ ከልብ ነው” ሲል ጋዜጠኛ መሳይ ከጎንደር ተነቅሎ ወደ ሃዉዜን የተወሰደዉን ጄኔሬተር አሳይቶናል።
The post ጎንደርን ገድሎ ትግራይን ማልማት ? አሰፋ ቤርሳሞ appeared first on ሳተናው .