(ሳተናው) ላለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄዎቻቸውንና ተቃውሟቸውን ሲያቀርቡ የቆዩት ኢትዮጵያዊያኑ ሙስሊሞች ዛሬ ከጁምዓ የጸሎት ስነ ስርዓት በኋላ አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘውና በተለምዶ ጀርመን መስጂድ በሚባለው የጸሎት ስፍራ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
በጀርመን መስጂድ ጎላ ያለ ተቃውሞ ሲደመጥም በታሪኩ የመጀመሪያው በመሆኑ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡መንግስት በብዛት የጸጥታ ሰራተኞቹን በመርካቶ፣ፒያሳና ፍልውሃ አካባቢ በሚገኙ መስጂዶች አሰማርቶ የነበረ ቢሆንም በተጠቀሱት ቦታዎች የጸሎትና የስግደት ስነስርዓቶች ያለምንም ተቃውሞ መጠናቀቃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጀርመን መስጂድ የተሰባሰቡ የሐይማኖቱ ተከታዩች ያዘጋጇቸውን መፈክሮች በማውለብለብና የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡በወቅቱ በምዕመናኑ የተያዙትና ከተስተጋቡት መፈክሮችም መካከልም
ትግላችን ይቃጥላል
ዲናችንን አናስንቅም
ድምፃችን ይሰማ
ፍትህን ቀበሯት
ሰላም ከነሳችሁን ተመሳሳይ ኑሮ እንድንኖር ታስገድዱናላችሁ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ዛሬም የኢትዮ ሙስሊሞች ፍትህን እንሻለን