Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

በአንዳርጋቸው ጉዳይ የእንግሊዝ መንግስት ከፍተኛ ወቀሳ ተሰነዘረበት

$
0
0

Andy-Tsege-v3

(ሳተናው) የእንግሊዝ መንግስት  የ60 ዓመቱን እንግሊዛዊ አንዳርጋቸው ጽጌን በቁጥጥር ስር ለማዋላቸው ተጠያቂ እየተደረጉ የሚገኙትን የኢትዮጵያን የደህንነት ሰራተኞች የግብር ከፋዩቹን ገንዘብ በመጠቀም መርዳቱ እንዳሳዘናቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታውቀዋል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በኢትዮጵያ ወታደሮች የሚመሩ ማዕከሎችን በስልጠና መልክ ለመርዳት የእንግሊዝ መንግስት በሚልዩኖች  የሚቆጠር ፓውንድ ማውጣቱን በመጥቀስ ተቃውሟቸውን አቅርበዋል፡፡

ለኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ መስሪያ ቤት ባለፈው አመት ብቻ የተደረገው ድጋፍ በእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ኮመንዌልዝ ቢሮና በመከላከያ ሚንስትር አማካኝነት እንደተሰጠ  የጠቀሱት ድርጅቶቹ ቀውሶችን ለመፍታትና ለደህንነት ማጠናከሪያ ተብለው መሰጠታቸውንም ገልጸዋል፡፡

ከግማሽ ሚልዩን ፓውንድ በላይ በደህንነት ዙሪያ ለተወሰዱ የማስተርስ ዲግሪዎች ወጪ ተደርጓል ያሉት ድርጅቶቹ 546.500 ፓውንድ ደግሞ ለኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይል ማዕከል የስልጠና ድጋፍ የተሰጠ  መሆኑን ድርጅቶቹ ከኮመንዌልዝ ቢሮ አገኘነው ያሉትን መረጃ በመጥቀስ ገልጸዋል፡፡

የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት አምና  ድጋፍ ሲያደርግ የአገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ስለሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ መረጃ ስለማግኘቱ  ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም መረጃውን መስጠት የእንግሊዝንና የሌሎች አገራትን ግኑኝነት ያበላሻል በማለት መከላከሉን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የሚ ኃይለማርያም ለኢንዲፐንደንት ‹‹አንዳርጋቸው ከታሰረ ጀምሮ ቤተሰባችን በጭንቀት ውስጥ ነው ፣ እኛ የምንፈልገው ወደቤቱ እንዲመለስልን ብቻ ነው፡፡ከእስሩ ቀን ጀምሮም እስካሁን ድረስ ይህንን እያሰቡ መጨነቅ በጣም አስፈሪ ነው፡፡እንግሊዝ አንዳርጋቸውን የያዙትን የደህንነት አካላት ትረዳለች እኛ ግን ተስፋ የምናደርገው እንግሊዝ  አፈና የፈጸሙትን ከመደገፍ ይልቅ ያላትን የጠበቀ ግኑኝነት በመጠቀም አንዳርጋቸው እንዲለቀቅ ታደርጋለች ብለን ነው››ብለዋል፡፡

የሪፕራይቭ የሞት ቅጣት ለማስቀረት የሚታገል ቡድን መሪ የሆኑት ማያ ፎ በበኩላቸው ‹‹ድጋፉ የእንግሊዝ መንግስት ከኢትዮጵያ የደህንነት ኃይሎች ጋር ባላት ግኑኝነት ዙሪያ መሰረታዊ  ጥያቄ ማስነሳት የሚችል ነው››ብለዋል፡፡

ሬድረስ ለተባለው የሰብአዊ መብት ድጋፍ ቡድን የህግ አማካሪ የሆኑት ኬቪን ላው ‹‹አንዳርጋቸው ከእስር ተፈትተው ወደቤታቸው እንዲመለሱ ከመጠየቅ ይልቅ የእንግሊዝ መንግስት  ፍትህን በማፈን የሚታወቀውን የኢትዮጵያን የደህንነት አገልግሎት ብቃት ለማሳደግ ድጋፍ ማድረጉ አስገራሚ ነው››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles