Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የወርቅ ክምችት ያለበት ሻኪሶና ዳዋ ኦኮቴ ለሚድሮክና ለኤፈርት በመሰጠቱ ነዋሪው ተቃውሞ አሰማ

$
0
0

Alamudiበደቡብ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሚድሮክ ኩባንያ የወርቅ ማዕድን በሚያወጣበት ሻኪሶና እና በቅርቡ ወርቅ ይወጣበታል ተብሎ ለሚድሮክና ኤፈርት ኩባንያዎች በተሰጠው ዳዋ ኦኮቴ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ማሰማት ጀመሩ።
ብዙ የወርቅ ክምችት አለበት በተባለው አኮቴ ተጨማሪ መሬት ንብረትነቱ ለሼክ መሃመድ አል-አሙዲን ለሆነው ሜድሮክና የህወሃት ንብረት ለሆነው ኤፈርት መሰጠቱ ህዝባዊ ቁጣ ቀስቅሷል።
ሚድሮክ ኩባንያ በሻኪሶ ለገደምቢ ከ20 አመታት በላይ የወርቅ ማዕድን ቢያወጣም የአካባቢው ህብረተሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ አለመሆኑ ቁጭት እንደፈጠረበት ተመልክቷል።
ሚድሮክ በየአመቱ 4.5 ሜትሪክ ቶን ወይም 4500 ኪሎግራም ወርቅ ሲያወጣ ቢቆይም የነዋሪው የዕለት ተዕለት ህይወት ከእጅ ወደአፍ እንደሆነ መቀጠሉ ተገልጿል።
የለገደምቢ ወርቅ እየተሟጠጠ ሲሄድ ሚድሮክ እዚያው አካባቢ ወደሚገኘው ሰብሮ የወርቅ ክምችት ፊቱን በማዞር ማምረቱን ቀጥሏል። በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ወርቅ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ማዕድናት ይመረታሉ።
በመንግስት የተያዘው የማዕድን ልማት ድርጅት ከ160 ሚሊዮን ቶን በላይ ክምችት ያለው ታንታለም ማዕድን እያመረተ ወደ ቻይና ይልካል።
ከ4 ዓመት በፊት በ2004 ዓም ክምችቱ ከ550ሺ ኪሎግራም እንደሆነና 5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያወጣ የተነገረለት ወርቅ በዳዋ አኮቴ መገኘቱን ብሄራዊ የማዕድን ኮርፖሬሽን የተባለ ድርጅት ማስታወቁ የታወሳል።
ከትናንት ጀምሮ የተቀሰቀሰው አመጽ በዚሁ አካባቢ የወርቅ ማዕድን ለማውጣት በሚል ተጨማሪ መሬት ለሚድሮክና የህወሃት ለሆነው ኤፈርት በመሰጠቱ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ።
በሻኪሶ ህብረተሰብ የሚጠጣው ውሃ የሌለውና አንድ ጄሪካን ውሃ በ10 ብር እንደሚገዙ ይገልጻሉ። ሚድሮክ ለአካባቢው ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ፣ እና ሌሎች መሰረተ-ልማቶችን ለመስራት ቃል ቢገባም ህዝቡ መሬቱን ተነጥቆ ከመሬቱ ውስጥ የሚገኘው ወርቅ ከአካባቢው ተጭኖ ሲሄድ ከማየት ውጪ የተጠቀሙት ነገር እንደሌለ በምሬት ይናገራሉ።
በዳዋ አኮቴ በተነሳው ተቃውሞ ፌዴራል ፖሊስ የሃይል እርምጃ ወስዶ ህዝቡን መደብደቡንና በርካታ ሰዎችን እያሰረ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ቡሌ ሆራ ኬላ የጣሰ የጭነት መኪና ለመያዝ በሚል ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ሁለት ሰላማዊ ሰዎች በመገደላቸው ነዋሪው ተቃውሞውን እየገለጸ ነው።
ተቃውሞውን ለማስቆም የመንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ህዝባዊ ቁጣ ተባብሶ የኬላ መጠበቂያና የጉምሩክ ጽህፈት ቤት በእሳት ተቃጥሏል።
በትላንትናው ዕለት በፖሊስ የተገደሉ አለሙ ያቦ እና ንጉሴ ጉዴ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ህዝቡ ዛሬም እየተጠየቀ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

( ኢሳት )


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles