የዋዜማ ራዲዮ አርጋው አሽኔ እንደዘገበው
የኢትዮዽያ መንግስት ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠት የሚያስችል ረቂቅ አዘጋጅቶ ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር መዘጋጀቱን አስታውቋል። ይህ የመንግስት ጥረት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ላይ ያነጣጠረ እንድሚሆን የከዚህ ቀደም የመንግስት ሙከራዎች ያመላክታሉ። መንግስት በተመሳሳይ ከሳዑዲ አረቢያና ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር ድርድር መጀመሩን ገልጿል። በእርግጥ ይህ የመንግስት እርምጃ ለተቃዋሚዎች ስጋት ነውን? ተቀባይነቱስ?