የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ወደ ካዛንችስ ጎራ ብሎ ያነጋገረው አይነስውሩ ሊስትሮ ብርሃኑ የአይን ብርሃኑን ያጣው በ1996 የ5ኛ ክፍል ተማሪ ሳለ ነበር፡፡ ልመናን የሚጸየፈው ብርሃኑ ግን የዓይን ብርሃኔን አጣሁ ብሎ ብዙዎች በተጓዙበት መንገድ ወደ ልመና አላመራም፤ ይልቁንም ከሚኖርበት ከጉራጌ ዞን ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በሊስትሮ ሙያ ተሰማራ እንጂ…
እነሆ ብርሃኑ በሊስትሮ ሙያ ሲሰራ 10 ዓመቱን ደፈነ…
በዚሁ የሊስትሮ ሙያው ሚስቱንና የ5 ዓመት ወንድ ልጁን የሚያስተዳድረው ብርሃኑ የቤት ኪራይ 1 000 ብር በሚከፍልበት ቤት ውስጥ ኑሮውን ተያይዞታል ይለናል የልዩ ወሬው ዘገባ፡፡
‘ሌሎች ሊስትሮዎች ካልሲን ቀለም እየቀቡ ሲያበላሹ እሱ ግን ዓይነ ስውርም ሆኖ እንዲህ አይነት ስህተት ሲሰራ አይተን አናውቅም’ ሲሉ የብርሃኑ ደምበኞች ይናገራሉ፡፡
ጠዋት 1፡30 ላይ ባለቤቱ እየመራችው ካዛንችስ የሊስትሮ ድንጋዩ ጋር አድርሳው ትመለስና 7፡00 ላይ ደግሞ ለምሳና ለእረፍት ወደ ቤት ይዛው ትሄዳለች፡፡ ከዚያም 9፡00 ላይ መልሳ ወደ ስራው ቦታ ታመጣውና 12፡00 ሰዓት ላይ ደግሞ መልሳ ወደ ቤታቸው ትወስደዋለች ይለናል ወንድሙ፡፡
ብርሃኑ ወደፊት ሱቅ የመክፈት ህልም እንዳለውም ለወንድሙ ኃይሉ አጫውቶታል፡፡