Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ከተሜ ጋር ለደቴን በዝዋይ እስር ቤት አሰላፍኩ – ታሪኩ ደሳለኝ

$
0
0

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንግስት የፈረደበት ፅኑ የ3 አመት የእስር ግዜ ሊጨርስ ዛሬ ሰኔ 15/09ዓ.ም 3 ወር ከ15 ቀን ብቻ ይቀረዋል። አኔም እንደለመድኩት ዛሬን ካስገቡኝ ብዬ ዝዋይ እስር ቤት ተገኝቻለሁ። ከገባው ተሜንም ጠይቄ ልደቴንም አክብሬ እመለሳለሁ ከላገባውም የስር ቤቱን ደጃፍ ላይ እንደቆምኩኝ ወንድሜን ባዓይነ ህሊናዬ አይቼ እመለሳለሁ ብይ ነው የተገኘሁት። አንዳንዴ እንደማየስገቡኝም እያወኩኝ ዝዋይ እስር ቤት ደጃፍ እገኛለሁ ዓይነ ህሊና ሲቀርብ የበለጠ የሚያሳይ እየመሰለኝና እየጓጓሁ። የሆነው ሆኖ ግን ዛሬ ገባቻለሁ። ባዓይነ ህሊና ሳይሆን በዓይነ ሥጋ ተሜን ለማግኝት አስገብተውኛል።

ተሜን ሲመጣ አየሁት ፈግግ አንዳለ ነው ከፊትም ከኋላም ወታደሮች አሉ ተነስቼ ጠበኩት መጣ እንደ መጣ እቅፎ ስላም እያለኝ “እሺ ባለ ልደት እንዴት ነህ” አለኝ መለስኩ አሁንም ስለናታታችን ጤንነት ጠየቀኝ መለስኩ የመጣሁትን ስንቅ አቀበልኩት። ጤንነቱን ጠየኩት ምንም ለውጥ የለውም አለኝ። አጅበው ካመጡት ወታደሮች በተጨማሪ 4 ወታደሮች ተጨምረው በ6 ወታደሮች ተከበን ነው የምናወራው።

ህክምና ስለመከልከሉ ስናወራ አንዱ በለ ማአረግ ወታደር “ይህን ማውራት አትችሉም” አለ ተሜም “የማወራውን አትመርጥልኝም” አለው ወታደሮቹ ተያዩ ተያየተው አንገታቸውን ነቀነቁ በዛቻ ይሁን ተሜ ያለውን በመቀበል አንገታቸውን መነቅነቃቸውን የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው። ተሜና እኔ የምናወራውን አውርተን ጨርሰን። ለመሰነባበት ተነሳን ተሜ እንደ ታላቅ ወንድምም እንደ አባትም እያየኝ “መልካም ልደት” አለኝ በቃ ምሴን አገኘው ደስታዬ ጣራ ነካ ይህ ፈልጌ ነው የመጣሁት የመጣሁበትንም አገኘሁ ትልቁን የልደት ቀን ማሳመሪያ ቃልም ሰማው ።

ተሜ ሲሄድ ከኃላው አየሁት በአረንጓዴ በቢጫ በቀይ የተሰራ የባንዲራ ቀበቶ አደርጓል ወታደሮቹ ከፊትና ከኃላ ቢሆኑም ባንዴራውንም ተሜንም መከለል አልቻሉም ይልቅስ በክብር ያጀቧቸው ይመስላሉ። ከእስር ቤቱ መውጣት ስጀምር ስሜ ሲጠራ ሰማሁ ዞርኩኝ ከ 6ቱ ወታደሮች አንዱ ወደኔ እየመጣ ነው። ቆሜ ጠበኩት። እንደደረሰ “ለደት እስር ቤት ውስጥ ማክበር አይቻልም” አለኝ ገና መናገር ስጀምር “ጨርስኩ” ብሉኝ ሄደ።ፈገግ አልኩኝ እንግዲህ የተነገረው ተናግረክ ና ለመስማት እንዳታስብ አንደተበለ ገባኝ። እስር ቤት ግቢ ውስጥ እንደቆምኩኝ ዙሪያውን ተመለከትኩ አሁንም ተሜ ወደ ሄደበት አቅጣጫ አየሁኝ አሳሪ ነን የሚሉ ባለጠብ-መንጃዎች በቦታው ላይ ቢተራመሱም አኔ ባለ ህሊናውን ለሀገሩ ሲል እስከ ቀራኒዮ ድረስ ነው መንገዴ ያለውን ተመስገንን ብቻ ጉልቷ አየሁት።

እንደቆምኩ የታወቀኝ እየሄድክ የሚል የጩኸት ድምፅ ነው። ደምፁን ወደ ሰማሁበት ዞርኩ ሌላ በለጠብ-መንጃ ወታደር አየሁ። “እኔማ እሄዳለሁ ያታሰሩትም ይፈታሉ እስር ቤቶችም ትምህርት ቤት ይሆናሉ ሀገራችንም ለሚያስብ ሰው እስር ቤት አይኖራትም ፍትህና ሰባዓዊነት ይነግሳሉ በህግ የበለይነት አንገዛለን ጠብ-መንጃዎቹም ዝቅ ይለሉ ኢትዮጲያዊነት በውዴታ ከፍ ይላል” ይህን ለራሴ እያልኩኝ ለደቴን ዝዋይ እስር ቤት አክብሬ ወጣሁ።

 

ታሪኩ ደሳለኝ


ሰኔ 15/09 ዓ.ም

The post ከተሜ ጋር ለደቴን በዝዋይ እስር ቤት አሰላፍኩ – ታሪኩ ደሳለኝ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles