1) የሐገራችን የጎሣ ፌደራሊዝም ከሌላው ዐለም የፌደራል ስርዐት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ።
የሐገራችን የፌደራል ስርዐት ጎሣን መሰረት አድርጎ የተነሳ በመሆኑ ከሌላው ዐለም የፌደራል ስርዐት ይለያል ። በኛ ሐገር የጎሣ ስርዐት መሠረት አንድ ሰው ከተሰጠው የጎሣ ክልሉ ውጭ የቱን ያክል ብቃቱ ሰማይ ጠቀስ ቢሆንም የመወዳደር መብት የለውም ። ምክኒያቱም መስፈርቱ ችሎታ ሳይሆን “ዘር” ነው ። ይህ ደግሞ ከዲሞክራሲ ፅንሰ ሐሳብ ጋር በፍፁም ተቃርኖ ላይ ይገኛል ። ምክኒያቱም ዴሞክራሲ ስንል አንድ ግለሰብ የጎሣ ፣ የቋንቋ ፣ የቆዳ ቀለም ፣ የሐይሞኖት ወ.ዘ.ተረፈ መገለጫዎቹ መስፈርት ሳይሆኑ በብቃቱ ለተወዳዳሪነት የሚቀርብበትና በአብላጫ ድምፅ የሚመረጥበት የአስተዳደር ስርዐት ነው ።
(ኦባማ ሐገሩ ኬኒያ በነበረው ቆይታ በጎሣ ፖለቲካ የቆመ ሐገር ፈራሽ መሆኑን ሲናገር ኢትዮጵያ በማግስቱ የትግሬን ሐገራችንን ባንቱስታናይዝድ የማድረግ ደንብ ዲሞክራሲ በማለት አሞካሽቷል) ።
2) በጎሣ ፌደራሊዝም ዜግነት የሚባል ነገር አይታሰብም ።
በሐገራችንችን የክልል ሕገ መንግስት የተባለውን የትግሬ ደብተር ስናይ እያንዳንዱ ክልል ባለቤትነቱ ለዚያ ክልል ነባር (indigenous) ተብለው ለሚታሰቡት ብቻ ነው ። አንድ ሰው ሙሉ ኢትዮጵያዊ ለመባል ደግሞ የሙሉዋ ኢትዮጵያ ባለቤት መሆን አለበት ። የጎሣ ፌደራሊዝም እንኳን ዲሞክራሲን ሊያጎናፅፈን አንድን ሰው ዜግነቱን የሚቀማ የአፓርታይድ ስርዐት ነው ። ሕገ መንግስቱ ሙሉ ዜግነትን ለማንም አይሰጥም (ትግሬም ሕግ ጥሶ በጉልበቱ እንጅ ሙሉ ዜጋ አይደለም) ።
3) የጎሣ ስርዐት የጎሣ ባላባቶች ሕዝቡን ለፈለጉት ጥቅም የሚዘውሩበት ዕድል ይሰጣል ።
በጎሣ ስርዐት ውስጥ ሁሉም ነገር ከጎሣ ማንነት ጋር ስለሚያያዝ ማንኛውም አምባ ገነን ጎሣውን እንደመጠጊያ በማድረግ አነሳሁት ያልከውን ያሳጣሀል ። ለምሳሌ በቅንጅት ጊዜ እነ ቡልቻ ቅንጅት ጠንከር ሲል የአማራ ስርዐት ነው በማለት አፍራሽ ነገር ሰብከዋል ። ቅንጅትን እኮ በተወሰኑ ከተማዎች እንጅ ሐረርጌም ሆነ ባሌ አያውቋትም ።
4) በጎሣ ስርዐት ውስጥ የመገንጠል ሐሳብ እንጅ አብሮ የመኖር ባህል አያድግም ።
የትግሬ ጋርዮሻዊ የጎሣ ስርዐት ሕብረተሰቡን የሚቀርፀው በጎሣ ማንነቱ ነው ፤ የጋራ መገለጫዎች ዋጋቸውን ያጣሉ ። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማን በትግሬ ፤ በኦሮሞና በሶማሌ ብሔርተኞች እጅ ማየት ወደፊትም የሚናፍቀን ነው ። የጋራ መግባቢያችን አማርኛ ላይ የተዘመተውንም ተመልከት ።
5) የጎሣ ስርዐት በአከላለል ላይ የአናሳዎችን መብት ይጋፋል ።
ብዙ ጎሣዎች ባሉበት ሐገር የአንድ ጎሣ ተወላጆች ብቻ የሚኖሩበት አካባቢ አይገኝም ። በዚህም ምክኒያት ከለልኩት ያልከው ክልል ውስጥ ሌላ የክልል ጥያቄ ይነሳል ። ችግሩ በዚህ አያበቃም ክልል የመሆን ጥያቄ የሚያነሱም ተነስተዋል ። ለምሳሌ ኦሮምይያ በሚሏት ክልል ውስጥ ያሉ ነባር ጎሣዎች ምንም እንኳን የራሳቸው የተለየ ማንነት ቢኖራቸውም ማንነታቸው ኦሮምይያ ተብሎ ተጨፍልቋል ። ይንን ችግር ለመፍታት ትግሬዎች ዞን የሚባል ለዐማሮች ብቻ የማይፈቀድ ስርዐት ፈጥረዋል ። ችግሩ በዚህ አያበቃም ልዩ ወረዳ የሚሉት አሁንም ዐማሮችን የማይመለከት አከላለል አለ ። በደቡብም ተመሳሳይ ችግር ያለ ሲሆን የራሳችን ክልል ወይንም ዞን ይኑረን የሚለው ጥያቄ በብዙዎች ተነስቷል ። ሲዳማ ክልል መሆን የሚገባውና ጥያቄ ያለው ሕብረተሰብ ነው ። ጉራጌም ይህን ጥያቄ ያነሳዋል ።
ይቀጥላል ፦
-ይህን ችግር ችግሩን በመተንተን ብቻ አይፈታም(ስርዐቱ አይወገድም) ።
-ባሁኑ ስዐት ይህን ስርዐት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይቀበለዋል ።
-ዐማራ ይህን ስርዐት ለማስወገድም ይሁን ለመቀበል መደራጀት ግድ ብሎት ተደራጅቷል ። ወ.ዘ.ተ. ይቀጥላል
The post ስለ ወያኔ የጎሣ ፌደራሊዝም መታወቅ ያለባቸው 5 ነጥቦች – ወንደሰን በየነ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.