በ2005 ዓ.ምቱ አገር አቀፍ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት በሰሜን ወሎ ዞን መስተዳድር፣ ሀብሩ ወረዳ፣ ልዩ ስፍራው ጊራና ተብሎ በሚጠራ የገጠር ከተማ ናትናኤል ሰይድ የሚባል በቅስቀሳ ላይ የነበረ የሰማያዊ ፓርቲ የአካባቢው ተፎካካሪ በአካባቢው ወሮበላ ካድሬዎች(Common chiefs) አነሳሽነት ክፉኛ ይደበደባል። በወቅቱ ጥቃቱ የተፈፀመበትን ፖለቲከኛ አቶ ናትናኤል ሰይድን ዋቢ አድርገው የጀርመኑ ዶቼዌሌና ቪኦኤ ዜናውን ይዘግቡታል፤ ይሁንና በዚህ አጋጣሚ ከመንግስት ወገን የተሰማ ክፉም ሆነ ደግ ነገር አልነበረም። በዚያው ሰሞን ይሄን መረጃ ያደረሰኝን አብሮ አደግ ጓደኛየን ጨምሮ በሰሜን ወሎ ዞን መስተዳድር ስር ከሚገኙ ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ (ጓደኛየ እራሱ ቁጥራቸውን በውል የማያስታውሳቸው) ካድሪዎች በዞኑ ዋና ከተማ ወልድያ አንድ አዳራሽ ውስጥ በአቶ ገዱ ሰብሳቢነት ይሰበሰባሉ።
ወቅቱ የምርጫ ሰሞን እንደመሆኑ አጀንዳውም ስለምርጫ ነበር፤ አቶ ገዱ ስለምርጫው ህግና ደንብ ብሎም Code of conduct አንዳንድ ነገሮችን ከተነተኑ ቡሃላ፣ የተቃዊሚ ፓርቲዎች ተወዳዳሪዎችም መብትና ግዴታ በዚያው በተነተኑበት የህግ ማእቀፍ አውድ ውስጥ እንደሆነ አስረግጠው ተናግረው፤ “በተለምዶ ተቀዋሚዎች የምንላቸው ወገኖች…የራሳችን እህት ወንድሞችና የሀሳብ ተፎካካሪዎቻችን እንጂ እንደምናስበውና እንደሚባለው ከየትም የመጡ ጠላቶቻችን አይደሉም!” ሲሉ ያለውልውል ይነግሯቸዋል።:
አቶ ገዱ ንግግራቸውን በመቀጠል… ከላይ የገለፅኩትን የሰማያዊ ፓርቲ ተወዳዳሪ ድብደባ ከህግም ሆነ ከሞራል አኳያ ምንም ተቀባይነት እንደሌለው አያይዘው በተናገሩበት ቅፅበት ከአብዝሃኛው ተሰብሳቢ ወጣት ሞቅ ባለ ጭብጨባ ድጋፍ ተሰጣቸው፤ ይሁንና ከጥቂት ያነሱ የህወሀት ሰርጎ ገቦችና የስርአቱ ሆድ አደሮች ንግግራቸውን ተቃውመው ማጉረምረም ሲጀምሩ፣ አቶ ገዱ ቆፍጠን/ቅጭም እንዳሉ፦ “ስነስርአት!” ብለው ፀጥ ካሰኟቸው ቡሃላ ንግግራቸውን በመቀጠል የአገሪቱ ህግና የምርጫ ስነስርአት ከሚፈቅደው አውድ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ወንጀል እንደሆነና በዚህም ወንጀል ውስጥ ተዘፍቆ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ያለምንም የፖለቲካ ከለላ በህግ አግባብ በቀጥታ እንደሚጠየቅ እንቅጩን ነግረዋቸው ስብሰባውን እንደቋጩ፣ አብሮ አደጌና ጓደኛየ በአንድ ወቅት አጫውቶኛል።
እንግዲህ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከህግና ሞራል አኳያም እንዲህ ናቸው!!!

Endegena Meyessaw Metta to የፕሮፌሠር አስራት ልጆች ተነሱ
·
The post ስለ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአብሮ አደጌና ከብአዴን/ኢህአዴጉ ካድሬ ጓደኛየ አንደበት የሰማሁትን ምስክርነት እንደሚከተለው አቀርባለሁ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.