Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ቱጃሩ ጻድቃን በወያኔ ላይ በተደቀነው አደጋ እንቅልፍ አጥቷል!

$
0
0

(ከአቻምየለህ ታምሩ)

ቱጃሩ ጻድቃን ገብረ ተንሳይ

ቱጃሩ ጻድቃን ገብረ ተንሳይ ግማሽ ሕይወቱ ወደ ሞት ተለውጦ እውር ድንብሩን እየሄደ ያለው የትግራዩ የአፓርታድይ አገዛዝ የወያኔ ህልውና ጉዳይ እንቅልፍ የነሳው ይመስላል። ጻድቃን እንቅፍል የተነሳው የትግራይን የበላይነት የሚያረጋግጥ ኃይል ሳይፈጠር ወደሞት እያመራ ያለው ወያኔ በሕዝባዊ ትግል ተጠራርጎ እንዳይወገድበት ነው። እነ ጻድቃን ለስሙ አለን የሚሉትን ኃሳብ በኢትዮጵያ ስም፤ የኢትዮጵያን ስም እየጠሩ አደባባይ ያውጡት እንጂ ዋናው አላማቸው መቀጠል አለበት የሚሉት አይን ያወጣው የትግራይ የበላይነት ነው። ወያኔም ዛሬ፣ ዛሬ ሕገ መንግሥቱ፣ የአገሪቷ ጉዳይ፣ ወዘተረፈ የሚለን ስልሳ ሺህ ወጣቶች ገብሬበታለሁ የሚለውን የትግራይ የበላይነት ጉዳይ በተዘዋዋሪ ለመግለጽ ነው።

የሁለቱ ወያኔዎች የጻድቃንና የመለስ ዜናዊ ልዩነት የትግራይን የበላይነት እንዴት እናስቀጥለው የሚለው ጉዳይ ብቻ ነው። ጻድቃን ከሰሞኑ ከወያኔው ወናፍ ከዳንዔል ብርሀነ ወንድም ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ መለስ ዜናዊ ያዘጋጀውን የሕወሓት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመተቸት የመለስ ዜናዊ ፖሊሲ ለትግራይ የበላይነት ከሰጠው ጥቅም በላይ የትግራይን የበላይነት የሚያስጠብቅ አዲስ የፖሊሲ አቅጣጫ እንደሚያስፈልግ ተናግሯል። የጻድቃን ገብረ ተንሳይ ቃለምልልስ ከዚህ ላይ ያንብቡ ወይም ያድምጡ [ ኢትዮጲያን መልሶ የቀይ ባሕር ሀይል የሚያደርግ ፖሊሲ ያስፈልጋል ~ ጻድቃን ገብረትንሳኤ]

ቱጃሩ ጻድቃ የወደብ ጉዳይም ያሳሰበው ይመስላል። ለነገሩ ቢያሳስበውም የተገባ ነው። ባሁኑ ወቅት ለቱጃሩ ጻድቃንና በዙሪያው ላሉ የትግራይ ባለሀብቶች የወደብ ጉዳይ የአገር ጉዳይ ሳይሆን የግለሰብ ጉዳይ ነው። ዛሬ ላይ ትግራይ ውስጥ ያመረቱን የፋብሪካ ሸቀጥ ለአለም ገበያ አቅርበው ወደብ ካላቸው አገራት ጋር ተወዳድረው አትራፊ ለመሆን ወደብ ያስፈልጋቸዋል። ይህ ማለት ለድሀው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚያስፈልገው በላይ ወደብ ለጁራሮቹ ለነጻድቃን ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው። ጻድቃንና መሰል በወያኔ ዙሪያ የተኮለኮሉ የትግራይ ባለሀብቶች ከኢትዮጵያ በላይ ሀብታም የሆኑ ቡርዣዎች መሆናቸው አገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ሀቅ ነው። ስለሆነም እነዚህ ቱጃሮች የዛሬው ብቻ ሳይሆን የነገው ሐብታቸው የበለጠ እንዲስፋፋ፤ የውጭ ንግዱ በብዛት አትራፊ እንዲሆን፤ ወደ ውጭ ከሚልኩት ሸቀጥ በተጨማሪ ለግዙፍ ፋብሪካዎቻቸው የሚሆኑ ከባድ[bulky] ጥሬ እያዎችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ወደብ እጅግ አስፈላጊ ነው። ጻድቃን ስለቀይ ባህር አካባቢ እንቅሴቃሴና ስለወደብ ተጨንቆ ሲያወራ የነበረው እየገነቡት ያለው የትግራይ የኢኮኖሚ ኢምፓየር ወደፊት የሚያጋጥመው አደጋ እየታየው ነው።

ጻድቃን ከተግባራዊነቱ በስተቀር ምንም ያልቀረውን የታላቋ ትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ ተከትሎ አዲሷ አገር ለብልጽግናዋ የሚያስፈልገውን ወደብ ለማስገኘት ሲል ከወዲሁ እንደ ሁልጊዜ በኢትዮጵያ ስም በወደብ አሳቦ የአስር ሺዎችን ሕይወት በድጋሜ ሊማግድ ጫፍ የደረሰ ይመስላል። ደማችንን እየመጠጡ የአለም ዶላር ሚሊየነሮች መሆናቸው ሳያንስ በነፍሳችን ለተስፋይቱ ምድራቸው ወደብ ፍለጋ ደግመው ደጋግመው ሲቀልዱብን ዝም ብለን ማየት ያለብን አይመስለኝም።

ሻዕብያ በኤርትራ ወጣቶች ላይ እያደረሰ ካለው ችግር በላይ ፋሽስት ወያኔ በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ አረመኔያዊ ጭካኔ ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ይገኛል። ይህ ግን ለጻድቃን አይታየውም። ለጻድቃን የሚታየው ፋሽስት ወያኔ በየቅያቸውና በየቤታቸው እየሄደ የጨፈጭፋቸው የኢትዮጵያ እንቦቀቅላዎች ነፍስ ሳይሆን በኢሳያስ የአፈና አገዛዝ ምክንያት ከኤርትራ በየቀኑ ወደ ኢትዮጵያና ጎረቤት አገሮች የሚሰደዱ ኤርትራውያን ወጣቶች ጉዳይ ነው። ይህ ማለት ጻድቃን ከኢትዮጵያውያን በላይ ለኤርትራውያን ይጨነቃል ማለት ነው። ጻድቃን ከኢትዮጵያውያን በወያኔ መጨፍጨፍ በላይ የኤርትራውያን ስደት የሚያሳስበው አንድም ከኢትዮጵያውያን በላይ ኤርትራውያን ይቀርቡኛል ብሎ ስለሚያስብ ነው፤ሌላም ወያኔ ኢትዮጵያውያንንን የሚጨፈጭፈው እሱ የተዋጋለትን የትግራይ የበላይነት ለማስጠበቅ ስለሆነ ነው። ባጭሩ ጻድቃን ኢሳያስን እናስወግድ የሚለው የሰብዓዊነትና የፍትሕ ጉዳይ ሳይሆን የትግራይን የበላይነት በኢትዮጵያውያን መቃብር ላይ ያለምንም ስጋት ማስቀጠል የሚቻለው በዚያ መንገድ ብቻ ነው ብሎ ስለሚያስብ ነው። ጻድቃን «ኢሳያስን ማስወገድ አለብን» የሚለው በኢሳያስ አገዛዝ አማካኝነት በኤርትራውያን ወጣቶች ላይ እየደረሰ ያለው መከራ አሳስቦት ቢሆን ኖሮ መረብን ሳይሻገር ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ይታየው ነበር።

ስለዚህ ጻድቃንን ከመለስ ዜናዊ ወይንም ከወያኔ የተሻለ አድርጋችሁ የምታስቡ ብጹዓን አትሳሳቱ። የትግራይን የበላይነት ከወያኔ በተሻለ ለማስቀጠል ካልሆነ በስተቀር ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚቆረቆር የወያኔ ግርፍ የትግራይ ብሔርተኛ ከተከዘ ማዶ ሊፈጠር አይችልም። እነ አረጋዊ በርሀን ጨምሮ የወያኔን ርዕዮተ ዓለም በሚጋሩ የትግራይ ብሔርተኞች መካከል ያለው ጠብ የትግራይን የበላይነት ከወያኔ በተሻለ እኛ እናስቀጥለዋለን የሚል ብቻ ነው! ይህ በወያኔ ርዕዮተ ዓለም ዙሪያ የተኮለኮሉ የትግራይ ብሔርተኞች ሁሉ የፖለቲካ ሀ፣ ሁና የአፍ መፍቻ ቋንቋ ነው። አበቃ!

The post ቱጃሩ ጻድቃን በወያኔ ላይ በተደቀነው አደጋ እንቅልፍ አጥቷል! appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles