* ልማታዊ ካድሬዎች የሚገፉት ዲፕሎማሲ ትርፉ
የጀርመን ራዲዮ ወይም የዶቸ ቬሌ የትናንት እሁድ ” ኢትዮጵያ 26 ዓመታት በኢህአዴግ አመራር ” የሚለውን ውይይትት አደመጥኩት ። እጅግ በጣም በሳል ፖለቲከኞች ያደረጉትን ውይይት እያዳመጥኩ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ስደት የማውቀው የኢትዮጵያን ስደተኛ በውል የማውቀው የ 20ዓመት ጉዞ ከፊቴ ድቅን አለ ። ውይይቱን እያደመጥኩ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠውን ድጉስ በሁነኛ አሳታሚና ተከታታይ ሰው እጦት ተዘጋጅቶ ግን ያልታተመውን መጽሐፊን በትዝብት እየተመለ ከትኩ እንደ ስደተኛ የሆነብንን በቁዘማና ትካዜ መካከል አሰንኩት ። ሀገር አድጋ ተመንድጋ ወጣቱ ሀገር ገንቢ ሀገሩን ጠልቶ ስደተኛ የሆነበትን ምክንያት ከተወያዮቹ ብሰማም አሳማኙን ምክንያት ከተገፊ ስደተኞች በበርሃው ላይ ሰምቸዋለሁና አልደነቀኝም
ፍትህ ርትዕ በጎደለባት ፣ የሀብት ክፍፍል እኩል በማይደረግባት ፣ አንዱ ባቋራጭ ሲከብር ለፍቶ አዳሪው ለማደግ አሳር ፍዳውን የሚበላባት ሀገረ ኢትዮጵያ ያደገች ግን ሀሀር ግንቢ ወጣት ዜጎቿን ከስደት ያልታደገች ድሃ ሀገር መሆኗ ደረቁ እውነት ነው ! በውይይቱ በፖለቲለኞች የሰማሁት እውነት ፣ ባልታተመው መድብሌም ከአረቡ ሀገር ስደተኛ ባለታሪክ ወገኖቸ የማውቀው ሌላ ያፈጠጠ ያገጠጠ እውነት ነው
የሚያም እውነት
ብቻ ግሩም ድንቅ ውይይቱን ሰምቸ ጨርሰኩትና ወደ ራሴ ተመለስኩ ፣ ወደ ሳውዲው ስደት የሁለት አስርት አመታት ትዝታዬ ተጓዝኩ …
የጀርመን ራዲዮን ውይይት ከዚህ በታች አያይዥዋለሁ ፣ አድምጡት ! እኔም በሳውዲ ስደት ዙሪያ እዚህ ያደረሰንን መንገድ ዳሰሳ ወግ ጀመርኩት እንጅ አልጨረስኩትም ። ወጋችን ፈታ ፈታ አድርገን እናወራለን … በሳውዲው ስደት ዙሪያ የምታውቁትን ዛሬ ሀሳባችሁን ስጡበት ፣ እኔም ከእናነተ ጥቆማና አስተታየት ለጥቆ በቀጣይ የምዳስሰው ወግ ይሆናል !
ልጠይቅዎ !
========
* የምህረት አዋጁ ሊገባደድ ነው ፣ ምን ተሰርቷል ምንስ ተሳክቷል?
* የኮንትራት ስምምነቱ ተፈርሟል ዝርዝር መረጃ ለምን አልወጣም ?
* በስምምነቱን ወደ ተግባር ለመግናት እውን 6 ወር ይፈጃል ?
* የተባለው ዝግጅትስ ተደርጓል ?
* ካለፈው የከሸፈ ዲፕሎማሲና መብት ጥበቃ ምን እንማራለን ?
* ከስደተኛውና ከመንግስት ምን ይጠበቃል ?
* ስደቱ እንዴት ነበር ? እንዴትስ ኖርነው ?
* ኩሩው ዜጋ ” ውጣ” ተብሎ ለምን አልወጣም ?
* ሀገር እያለው ወደ ሀገሩን መመለስ ለምንስ እልፈለገም ?
* አስዎጭቹንስ ለምን ሳይፈራ ለምን ” ና ” ባይ መንግስትና ሀገሩን ፈራ ?
* ያልተሳካው የመብት ጥበቃና ያልተሳካው ዲፕሎማሲ እስከ ምን ?
…ብዬ እጠይቃለሁ መልስ ያላችሁ ወዲህ በሉ ፣ እንወያይበት !
ቸር ይግጠመን !
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 5 ቀን 2009 ዓም
The post የማለዳ ወግ…የኢህአዴግ አገዛዝ ጉዞና የሳውዲው ስደት ! – ነቢዩ ሲራክ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.