Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ሁለት ኬንያዊያን በኢትዮጵያ ወታደሮች ታፍነው ተወሰዱ

$
0
0

በመርሳቢት ካውንቲ ሞያሌ ከተማ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁለት ኬንያዊያንን አፍነው መውሰዳቸው ተነገረ፡፡ የግዛቱ ኮሚሽነር ሞፋት ካንጊ 100 የሚደርሱ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሞያሌ ቦሪ መንደር ዘልቀው በመግባት ሁለቱን ሲቪል ኬንያዊያንን መውሰዳቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ኮሚሽነሩ የተወሰዱትን ኬንያዊያን ለማስመለስ እየሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ ሁለት መሳሪያዎችን የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰርቀው መውሰዳቸውን አስረድተዋል፡፡
‹‹ጥቃቱን ያደረሱበትን ምክንያት ለማወቅ እየጣርን ነው፡፡ሰዎቹ የኢትዮጵያ የደህንነት ኤጀንሲዎች አባላት ናቸው፡፡የጸጥታውን ጉዳይ በተመለከተም በአካባቢው የሚቆጣጠሩት እነርሱ ነበሩ፡፡ሁለት መሳሪያዎችን ሰርቀው ከመውሰዳቸውም በላይ ሁለት ኬንያዊያንን ወስደዋል፡፡ጉዳዩን በዲፕሎማቲክ መስመር እየተከታተልነው እንገኛለን›› ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ካንጊ ከጥቃቱ በኋላ በድንበሩ አካባቢ የጸጥታ ሰራተኞቻቸውን ማስፈራቸውንም ተናግረዋል፡፡‹‹ከኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳዩ የሚሰጠንን ማብራሪያ እየጠበቅን ቢሆንም የድንበሩን አካባቢ ደህንነት ለማስከበር ጥበቃችንን አጠናክረናል››ብለዋል፡፡
ባሳለፍነው ወር ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በድንበሩ አካባቢ የሚከሰተውን ግጭት ለማስቆምና አካባቢውን ወደ ልማት ያሸጋግራል የተባለለትን የ20 ቢልዩን ሺሊንግ የንግድ ስምምነት መፈራረማቸው አይዘነጋም፡፡
በህዳር ወር የኬንያ መከላከያና የፖሊስ ኃይል በድንበሩ አካባቢ እንዲሰፍር መደረጉ ይታወሳል፡፡በወቅቱ በመርሳቢት ሶሎሎ ግዛት የገቡት የኢትዮጵያ ወታደሮች ሶስት የኬንያ ፖሊሶችን መግደላቸው አይዘነጋም፡፡
የኢትዮጵያ ወታደሮች በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ የሚናገሩለት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተዋጊዎች ግድያዎቹንም ሆነ አፈናዎቹን እንደሚፈጽም ይናገራሉ፡፡

The post ሁለት ኬንያዊያን በኢትዮጵያ ወታደሮች ታፍነው ተወሰዱ appeared first on Medrek.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles